የወያነ ፍቅር ሰግጦ የያዘው የአማዞንን ገበያ ያጨናነቀው የአኖሌው ደራሲ ክህሎት የተላበሰው ያየሰው ሽመልስ
ክፍል 1
ትችት
በጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
4/11/2024
እንደ አምሳዮቹ ተቀጪዎች እግዚሃር በሎጋ ዕድሜው በቅጣት የቀጠፈው “የአባ ገዳ ኦሮሞነት ዜጋ” የተቀበለው ኤርትራዊው ተስፋየ ገብረአብ ‘የኦንግና ሻዐቢያ ሁነኛ ስላይ ሆኖ’ ሁለት ስሞች ነበሩት፡፡ አባ ገዳ የተባለ ‘ኢንስትቱሽን’ የሰጠው የኦርሞነት ዜጋ ሥሙ ”ገዳ” (Gaddaa) እና ሕጋዊ ሥሙ ተስፋየ ገብረአብ የአጻጻፍ ችሎታው ማራኪ ነበር፡፡ዛሬ በአጻጻፍ ችሎታው ገዳ/ተስፋየን የተካው ኢትዮጵያዊው የአማዞን ገበያን ያጨናነቀው <<የሴራ ዕርካብ የደም መንበር>> ደራሲ <<የጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ>> መጽሐፍ አንብቤ አልጨረስኩትም ፤ ገና በጣም ከጀምሩ የእንቅፋት ክምሮች አላስክይድ ሲሉኝ አቆመኩና ትንሽ ለማለት መረጥኩ፡፡ በቀሩኝ ¾ኛው የመጽሓፉ ገጾች ምን እንደታቅፉልኝ ባላውቅም ገና ከጅምሩ እንቅፋቶች ከበዙ ምን የተለየ ንባብ እንደማነብ ሳስበው መንታ መንገድ ላይ ቆሚያልሁ፡፡
ደራሲው የማስታወስ ችሎታውና የጽሑፍ ቅንብር በጣም ውብ ፤ በፍሰቱ የሚተርካቸው ርዕሶች ፖለቲካው እንዳይሰልቸን በሚመስጥ
አተራረክ ከፖለቲካ ውጭ የሆኑ ማሕበራዊ ገጠሞቹን እየፈተፈተ ሲያጎርስ ከመጽሓፉ እንዳትላቀቅ ያደረገው የቅንብር ፍሰት በ33 አመት
ከተከሰቱ ከታወቁ ውብ ብዕርተኞች ምናልባት ከፍታውን ይይዛል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ባጨሩ ገዳ ገብረአብን ተክቶታል፡፡
ጋዝጠኛና ደራሲ ያየሰው ‘የፋሺስቶች ኩሊው አብይ አሕመድን’ ሲተች ሰምተናቸው በማናውቃቸው ወንጀሎችና ብምናውቃቸው ሰይጣናዊ
ሴራዎቹ በሚያጋልጥበት ብዕሩ ውስጥ የወያኔዎች ፍቅር ሰግጦ እያዳለጠ ሲጥለው ታዝባአልሁ፡
ለማ መገርሳ የተባለው ኦነግ “ኢትዮጵያ ሱስ ነች” በሎ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያውያን ያንን ድምፅ ከሰሙ ደርግ ከለቀቀበት
ወዲህ በኽር ስለሆነባቸው በትግሬዎቹ መንግሥት ‘የታፈነው ደወል’ ድንገት ሲስተጋባ ገንፍሎ የወጣው አገር ውስጥ ሆኖ አገር የመናፈቅ ስሜቱን ያስተጋባውን ሕዝብ “ቀኝ አክራሪ
የአማራ ፖለቲከኞች <<ኢትዮጵያ ሱስይ አለልን>> ብለው እልል አሉ>> እያለ ሰማዩንም ምድሩንም የሚሸፍን ኢትዮጵያዊ እልልታና “አንጀት የባሰበት” የባባ
ስሜት በማንኴሰስ ደራሲና ጋዜኛ ያየሰው ሸምልስ “ቀኝ አክራሪ የአማራ ፖለቲከኞች ዕልልታ” በሎታል፡፡
ሥልጣን ለትግሬዎች የተሰጠ ተፈጠሮአዊ ዙፍን አድርጎ የሚያምነው የያየሰው ውዳጅ የሆነው ውድብ <<ህዝባዊ ሓርነት ትግራይ>>
<<ሥልጣናችን ከተቀማን ወደየ መንደራችን እንበታተናለን>> በሎ በገሃድ ያሰጠነቀቀን ወያኔ ፤ ሥልጣን ደንገት ክእጁ ሰትሾልክበት
‘ተፈጥሮአዊ ምሽጉ ወደ ሆነቺው ‘መቀሌ/ትግራይ/ ተጠራርቶ ተሰባሰቦ “ማርና ወተት፤ዲሞክራሲና አክሱማዊነት የተላበሰች
<<አመድ ልሳ የምትነሳዋ ፎኒክሲትዋ
ሃገረ ትግራይ>> ለመመስረት ሲያውጅ፤ በሌላ በኩል መቀመጫው አዲስ አበባ ያደረገው
ሥልጣን ቀሚው ‘አዲሱ የፋሺስት ሥርዓት አዳሽ
አብይ አሕመድ’ ደግሞ ሥልጣኔን ካልተቀበላችሁ ወዮላችሁ በማለት ሁለቱ የፋሺስት መንጋዎች “ወዮልሀ
እስኪ ልይህ” ተባብለው በገቡበት ጦርነት ውሰጥ ደራሲው በሚያሳዝን እና በሚያበሳጭ ሙግት የወያኔ ፕሮፓጋንዲስት ሆኖ “ወያኔዎች ጡት ነካሾች የተባሉበትን ‘ነካሾች‘
እንዳልሆኑ” በሚያሳብቅበት አገላለጽ ይነበብበታል፡፡
ክዚህ አልፎ የኢትዮጵያ ውታድሮች በታንክና በሲኖትራክ እየተጨፈለቁ የናዚዎች ባሕሪ በተላበሰ የአገዳደል ጭካኔ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ወደ ወያኔ ከድተው በገቡ የድሮ የመከላከያ የትግራይ ተወላጅ መኮንኖችና ወታደሮች ነጂነት
ሲጨፈለቁም ሆነ፤ ከነ ሕይውታቸው ወደ ገደል ተገፍትረው ይተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ወታድሮች
ላይ እንዳልተፈጸመና << ለፕሮፓጋነዳ ፈጆታ የዋል የተፈበረከ>> አድርጎ ይከራክራል፡፡
ጣሊያኖች ሲያደምጡት የሌሊት ቀዥት (ናይት መየር) ሆኖባቸው የሚያባንናቸውን ፤ እነ ወያኔዎቹ እነ ገብረኪዳን ደስታ ያስተማሩትን
“ቀረርተኛዋና ሸላሊትዋ ፎካሪትዋ ኢትዮጵያ’’ አልወዳትም የሚለው “የወያኔዎች ኮድ” እየተጠቀመ፤ ውብ በዕሩን ሲያቆሽሸ ፤ ፎካሪትዋና አቀራሪትዋ
ኢትዮጵያ ያሰትላልፍቺለትን ክብረት (እሴቶች) ግን ሲያደንቅ፤ “ኢትዮጵያ ስትፈጠር የፉከራ፤የቀረርቶና የሽለላ ጠቀሜታዎችና መልዕከቶችን የያዘው ሰሌዳ በዳሰተሩ ብዕር ሲደመስስና ሲያነኴሰስ ይነበባል”፡፡
“ትግሬዎች ፖለቲካሊ “ሆሞጀኒየስ” (አንድ
ወጥ) ተደርገው መሳላቸውን ተገቢ ፍረጃ እንዳልሆነ የብዙ ገራገር ተከራካሪዎችም ሆነ የያየሰው ሸመልስም ይሁን አብይ አሕመድ ‘ትግሬዎች አስተሳሰብ አንድ ወጥ አይደሉም” ) ኢዲዩን፤አረጋዊን፤ባይቶናን፤ሳልሳይ ወያነን
ተመልከቱ’’ እያሉ ያንድ ሳንቲም አንድ ገጽታ መሆናቸውን በመካድ ከወያኔ አስተሳሰብ የተለዩ እንደሆኑ ሁሌም በሚያስቀኝ ፌዝ መሳይ
ከርከራቸውን ሳደመጥ እገረማለሁ፡፡ ደራሲውም የ’ነዚህን ቡደን ተጋሪ ነው፡፡ የትግራይ ሆመጀኒየስነት (አንድ ወጥነት) እምነት አብይ አሕመድም ሆነ ያየሰው ሽመልስ አንድ ናቸው (አብይ መስመሩ በየወቀቱ
እንደሁኔታው ቢለዋወጥም)፡፡
በመጨረሻ ደራሲው በክፍል 2 ትችቼ የምገልጸውን የክሕደት ክሕደት እንዲህ ይላል፡_
<< በሰፊው “’ (ወታደሩ) ሲኖትራክ ተነዳበት ወዘተ፣ የሚል ፕሮፓጋንዳ ያመጣው የሕዝብ
ልብ ለመግዛት በሚል ነበር፡፡ ደግሞም ተሳክቷል፡፡ የህ ሁሉ እንዳልተፍጸመ የትግራይ አመራሮች ብቻ ሳይሆኑ
ዐብይም፤ብርሃኑ ጁላም ሆነ አዳምነህ መንግሥቴ (የሰሜን ዕዝ ሲማረክ ምክትል አዛዠ የነበረው ያውቃል፡፡>>
በማለት የወያኔ ፍቅሩን ለመግለጽ በታንክ በሲኖትራክ የተደፈጠጡትም ሆነ ከ’ነነብሳቸው ወደ ገደል የተገፈተሩት ውታደሮች ነብስ ሲሳለቅ ታነቡለታላችሁ፡፡
በዚያም አልተገታ ትግራይ ውስጥ በጦርነቱ ወቅት ወታደሮቹ በአማራነታቸው ወይንም በየብሔራቸው እየተለዩ አልተገደሉም ወይንም ጥቃት አልደረሰባቸውም እያለ ተጠቂዎቹ አዛኝ እንደሌላቸው ሆዳቸው ባርባር እንዲላቸው በቁስላቸው ላይ ጨው ነስነሰበት፡፡ያንን በዝርዝር መጠቃታቸውን በማስረጃ ከመሳስሉ ጉዳዮች በክፍል 2 አቀርባልሁ፡፡
የወያኔ ፍቅር አልለቅ ላለው የአማዞን መጻሕፍት ገበያ ያጨናነቀው ለያየሰው ሽመልስ የኔን ጠቅላላ የትችት ንቅሳቶች የማደርገው “ሩቡታል” ስሞኑን ጠብቁኝ፡፡
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment