Sunday, February 12, 2023

“ወልቃይት ጸገዴ” እንጂ “ወልቃይት ጠገዴ” አይደለም” ትላለች ስለ ትግራይ ሴቶች መደፈር ብቻ የሚያማት “አልትራ ናሺናሊሰት” ጎሰኛዋ መአዛ ግደ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 2/12/23

 


“ወልቃይት ጸገዴ” እንጂ “ወልቃይት ጠገዴ” አይደለም” ትላለች ስለ ትግራይ ሴቶች መደፈር  ብቻ የሚያማት “አልትራ ናሺናሊሰት” ጎሰኛዋ መአዛ ግደ

 

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

2/12/23

ትናንት በድንገት የፌስቡክ ቪዲዮዎችን ስመለከት “ኢትዮጵያ፦ የሰላም መንገዶች - ክፍል 2” የሚል  ርዕስ በ ቪ.ኦ.ኤው ጋዜጠኛ “አሉላ ከበደ” አዘጋጂነት የተዘጋጀ በፕሪቶሪያ ተደረገ የተባለው ስለ ስምምነቱ ጉዳይ የሚነጋገሩ ብዙ ሰዎችን ያካተተ የቪዲዮ ውይይት ስመለክት ነበር።

ከተወያዮቹ መካካል የኢትዮጵያንና የአማራ ህልውናና ስም በማጠልሸት ዕድሜው ሙሉ የሐሰት ትርክት በመንዛት የታወቀው የኦነጉ ካድሬ “ረዳት ፕሮፌሰር “ኢታና ሃብቴ” እና ‘የዓፋርና የአማራ ሴቶች መደፍርና መጠቃት እንዲሁም በአማራ ማሕበረሰብ ላይ በትግሬ ተዋጊዎችና መሪዎች ትዕዛዝ እንዲሁም የትግራይ ማሕበረሰብ የተሳተፈበት አንዳንድ የዘር ማጥፋት ሱታፌ የተፈጸመው “ጀነሳይድ” ሳያሳምማት “የትግራይ ሴቶች መጠቃትና ፤ስለ ትግራይ ሕዝብ ግፍ ብቻ በመጮህ የምትታወቀው  የትግራይ አገርነት አቀንቃኝዋ “አለም አቀፍ ግንኙነት እና የትግራይ ሴቶች መብት ተሟጋች ነች” የሚባልላት የትግራይ ዲያስፖራ አልትራ ናሺናሊሰትዋ “መአዛ ግደይ” የተካፈሉበት መድረክ ተሰምጬ ተመለከትኩ።

አወያዩ አሉላ ከበደ ተናጋሪዎቹን ሃሳብ ሳያስጨርስ ካንዱ ወዳንዱ የተቆራረጠ ሃሳብ ሲያንሸራሽር አይቼው ድሮውኑ ቪ ኦ ኤ የተባለ ጣቢያ መመለክት ከተውኩት በግምት ወደ 15 አመት ከሆነኝ አንዱ ምክንያት ይህ ነው። አንግዶች ይጠሩና ሃሳብ ሳያስጨርሱ የሰዎቹን ጭብጥ ሳይጨርሱ ከዚያ ወደዚያ እየዘለሉ ፕሮግራሙ ያልቃል።

ታዲያ ወጣትዋ መአዛ ግደይ ያወቅኳት በዚህ ጦርነት ወቅት ነው። አማራ አገር ያደገች ትመስላለች “አማርኛዋ ከኔ በተሻለ ጥርት ያለ አማርኛና ልሳን ትናገራለች”። ታዳጊ ወጣት ስለሆነች ወያኔ ያጋታትን ፋሺስታዊ የብሔረተኛ ፖለቲካ ተጠምቃ “በትግራይ፤ትግራዋይነት” ጭፍን ስካር ከተጓዙት ግምባር ቀደም ሆና ስለተገኘች ሴረኞቹ የውጭ አገር ሚዲያዎች እርስዋን በመጋበዝ ስለ የትግራይ ፖለቲካ ሊሰሙት የሚፈልጉትን እንድትደሰኩርላቸው ይጋብዟታል።

በዚህ ወይይት ውስጥ አንድ እንግዳ ስለ ወልቃይት ጉዳይ አንስቶ “ወልቃይት ጠገዴ” የሚል ቃል ሲናገር ስትሰማ “በነገራችን ላይ “ወልቃይት ጸገዴ” እንጂ “ወልቃይት ጠገዴ” አይደለም” ሰትል ተናጋሪውን ለማሸማቀቅና ለማረም ሰትሞክር ሰምቻት’ እውነትም ይሄ ጎሰኛነት እጅግ ደፋር ነው አልኩ። ይህ ድፍረት ብዙ ትግሬዎች በውይይታቸው እንደ እውነት አድርገው ወስደው ሲናጋገሩበት ሰምቻለሁ። ግን ስሜት እንጂ እውነት አይደለም።

የወልቃይት አማራዎች “ጠገዴ” እንጂ “ጸገዴ” አይሉም። ምክንያቱም እቴጌ “ጣይቱን” ጻይቱ እንደማይሉት ሁሉ ጠገዴም “ጸገዴ” ብለው አይጠሩትም። ኤርትራ ያደጉ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራኖችን “ተስፋጺን” ብለው ሲጠርዋቸው አዲስ አባባ ያደጉ ኤርትራኖችን ደግሞ “አሚቼ”
 የልዋቸዋል። ለምን ተስፋጺን እንደሚልዋቸው ሲናገሩ “ትግርኛ ተናጋሪዎቹ በየንግግራቸው “ጸ/ጸ/ፀ/ፀ” የሚል ቃል ስለሚያበዙ “ተስፋጺን” ይሏቸዋል። አሁን ደግሞ መአዛ ግደይ ወያኔዎች ሲናገሩ ሰምታ “ጸገዴ” እንጂ “ጠገዴ” አይባልም ሰትል 
 አማርኛ  ትግርኛ ለማድረግ ከጅሏታል።

ይህንን ስታዘብ የራስዋን ትግርኛ ተናጋሪዎችን የቃላት ልዩነት እንዳለንም አታውቅም ማለት ነው።

ለምሳሌ “አሁን” የሚለው ቃል የሽሬ አውራጃ ትግርኛ ተናጋሪዎች እንደ ኤርትራኖቹ “ሕጂ” ሲሉ “እኛ አክሱሞች ደግሞ “ሕዚ” እንላለን ሌሎቹም የእንደርታ፤ ራያ፤ ተምቤን፤ ክልተ አውላዕሎ እና ዓጋመ ደግሞ “ኸዚ” )ኸ የሚለው ቃል በላንቃቸው ፍቀው ያደምጡታል”” በነዚህ ሁሉ የሚታየው ልዩነት የመጀመሪያው ፊደል ሲሆን የመጨረሻው ፊደል “ዚ” በሁሉም ቦታዎች አለ (ልክ እንደ ጠጌደ/ጸገዴ። ስለዚህ ይህች ምስኪንዋ መአዛ ወያኔዎች ሲሉት ሰምታ  የወልቃይት አማራዎችን ልሳንና የቃል የቦታ አጠቃቀም የግድ እንደ ትግሬዎቹ “ጸ” ለምን አትሉም ብላ በድፍረት ለማረም መሞከርዋ የሚገርም ትዕቢት ነው።

ሌላው ምሳሌ ልስጣችሁ፡

አማራዎች ስለ “ሐ”  ቃላት ሲጠቀሙ ልክ ግዕዝ “ሐ” እንደሚለው አማራዎቹም አንደ ግዕዙ “ሐ” ይጽፋሉም ያደምጡታልም። ትግሬዎች ግን ይህ ቃል ሲያደምጡትም ሆነ ሲጽፉ የተለየ ነው። ሐ ለመጻፍ “ሓ” ይጽፋሉ “ሐ” እንደ “ኸ” ያደምጡታል። ትግሬዎች “ኸ” ሲጠቀሙ አማራዎች የሚያደምጡት ላላ ብሎ የሚደመጠው እንደ “ይሄ/ይኸ/ አይነት ሲሆን እኛ ትግሬዎች ደግሞ “ኸ” የምንጠቀመው በላንቃ ጎሮሮ ፍቀን የምናወጣው አስቀድሜ ከላይ የጠቀስኩት ኸዚ (አሁን) እንደሚለው እንጠቀማለን። አማራ ኸ አላልቶ ሲያደምጠው ትግርኛ በጉሮሮ ፍቆ የተለየ ትርጉም ይሰጠዋል።

“ዓ” አማራዎች አላልተው ሲጠቀሙ (ልክ እንደ “አ” ትግሬዎች ግን ዓ የሚለው ፊደል በጉሮሮ ፍቀን እናወጣዋለን። ትግርኛ “ዓ” (ዓይኒ) ዓይን ሲሉት በጉሮሮ ፍቀን ነው የምናወጣው አማርኛ (አይን /ዓይን) አ በማላላት ያደምጡታል። አማራ እና ግዕዝ “አክሱም” አክሱም ሲሉት ትግሬዎች ግን “ኣኽሱም” አንለዋለን ሁለት የፊደል አጠቃቀም ልዩነት ትግሬዎች አጣምመውታል ማለት ነው። ስለዚህ አንዱ አማራ ተነስቶ መአዛ “ኣኽሱም”  ስትል  የሰማት “አክሱም” እንጂ “ኣኽሱም” አይደለም ቢልሽ ምን ይሰማሻል? መልስ አለሽ ለዚህ?

ስለዚህ መአዚትዬ እቴጌ ጣይቱን “ፃይቱ” እንጂ “ጣይቱ” አይደለም ልትያቸው ይሆን? ትግሬዎች ፀሓይ ሲሉ አማራ በተለይ ገበሬዎቹ “ጣሃይ/ጠሃይ” ይላሉ።  አማራዎቹን እንዳንቺው በ ፀ/ጸ/ እንዲያደምጡ ባታርሚያቸው እና የኔ ልሳን እንጂ የናንተ ልሳን ልክ አይደለም ከሚለው የወያኔነት ድፍረት ታቀቢ።

ኢትዮጵያ፦ የሰላም መንገዶች - ክፍል 2

https://youtu.be/7XJrK6_wMcQ


ጌታቸው ረዳ

No comments: