Sunday, May 29, 2022

ኢትዮጵያ ብላ ብላ በዚህ ሰውዬ እጅ ትውደቅ? ፈጣሪን ምን ብንበድለው ይሆን? ብሥራት ደረሰ 5/29/2022 Ethiopian Semay

 

ኢትዮጵያ ብላ ብላ በዚህ ሰውዬ እጅ ትውደቅ? ፈጣሪን ምን ብንበድለው ይሆን?

ብሥራት ደረሰ

5/29/2022

Ethiopian Semay

Ethiopian Semay

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ዐይኔን ጨፍኜ ዝም ብዬ በዐይነ ኅሊናየ ስመለከት ብዙ ነገሮች እውነት እውነት አይመስሉኝም፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ነገር ትያትር ይመስለኛል፡፡ እውነት የሚመስሉኝ ሁለት ነገሮች መምሸት መንጋቱና የሰዎች በእርጅናም ይሁን በህመም ወይንም በአደጋና በሰዎች እጅ መሞት ናቸው፡፡ ጊዜው ሰዓቱን ጠብቆ ይነጉዳል - እየመሸ እየነጋ፡፡ ሰውም ከቅርብ ዘመድ ጀምሮ እስከሩቅ ትውውቅ ይታመማል፤ ይሞታል፡፡ እነዚህ ጥንት የነበሩና አሁንም ያሉ ተፈጥሯዊ ክስተቶች ናቸው፡፡ በተረፈ ኢትዮጵያ አለች የምልበት አንድም ነገር የለም፡፡ በኔ ዕድሜ እንዲህ ያለ ዝብርቅርቅ ያለ ሁኔታ ይገጥመኛል ብዬ አስቤው አላውቅም፡፡ ዕድሜ ዘልዛላው ግን ብዙ ያሣያል፡፡

በልጅነቴ የማውቃት ኢትዮጵያ አሁን ድራሹዋ ጠፍቷል፡፡ ሰው ተንቀሳቃሽ ሮቦት ከሆነ ሰነበተ፡፡ አብዛኛው ሰው አእምሮው ተቃውሶ ብቻውን እያወራ ይሄዳል፡፡ አብዛኛው ዜጋ ከመሠረታዊ የሰው ልጆች አስፈላጊ ነገሮች ተፋትቶ በቀን አንዴም መቅመስ አቅቶትና አንዴ ትከሻው ላይ ባጣበቃት አሮጌ ጃኬት ወይ ሹራብ ቢጤ ተጨብጦ በየበረንዳውና በየታዛው ተቀምጦ መዋል ማደሩን ተያይዞታል - ሌላ ምርጫ በማጣት፡፡ የመንግሥት ሥራ ለስም እንጂ በተግባር የለም፡፡ ጉቦና ሙስናው እግር አውጥቶ እየሄደ ነው፡፡ የኦሮሙማ ሰዎች በኬኛ ፖለቲካቸው ሁሉንም ካልዋጥን ካልሰለቀጥን ብለው ከአዲስ አበባ ጎንደር በተዘረጋ ማፊያዊ ሥርዓት በተለይ አማራን መቆሚያ መቀመጫ አሳጥተውታል፡፡ ከዚህም የተነሳ የአንድ ዓመት ሕጻን ሳይቀር በማገት ከጣሊያኑ ማፊያም፣ ከአልቃኢዳም፣ ከአይሲስም፣ ከአልሻባብም፣ ከቦኮሃራምም፣ ከማዕከላዊ አፍሪቃ የቀድሞ አማፅያን ቡድን ከቱዋሬግም የበለጠ የእገታ ሪከርድ አስመዝግበዋል፡፡ እኛም በሣቅ ጦሽ እያልን በ“እያነቡ እስክስክስታ” ልናልቅ ነው፡፡ እንደጥርስ ሞኝ የለም መቼም - አንገት በጎራዴና በሠይፍ ተቆርጦ እየበረረ እኮ ጥርስ ይስቃል - ልክ እንደኛ፡፡

ኢትዮጵያ መረገሟን በትክክል የተረዳሁት የሁሉም የሥነ ልቦና ህመሞች መጋዘን የሆነው አቢይ አህመድ እንዲገዛት እግዚአብሔር ፈቃደኛ ሆኖ መገኘቱን ስገነዘብ ነው፡፡ ለነገሩ ሲያንሰን ነው! እኛም አብዝተነው ነበር፡፡ የክፋታችን ብዛትና ዓይነት፣ የኃጢኣታችን ነዶና ክምር እኮ ወደር የለውም፡፡

አቢይ አህመድ ምን ዓይነት ኢትዮጵያና በምን በምን ችግሮች እየተጠበሰና እየተወገረ ያለ ሕዝብ “እንደሚመራ” እንኳንስ እኛ የመከራው ገፈት ቀማሾች መላው ዓለም ያውቀዋል፡፡ ይህ ሰው ነው እንግዲህ፣ ራሱ በባዶ እግሩ እየሄደ መንግሥት አለኝ ብሎ ለመንግሥት በከፈለው ግብርና ቀረጥ ቫጋቦንዱ አቢይ አህመድ የ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ቤተ መንግሥት እያሠራ የሚገኘው፡፡ አንድ ሎሚ በአምስትና አሥር ብር ቸርችራ በምታገኛት ትንሽዬ ሣንቲም ነፍሷን አውላ ከምታሳድር የጉሊት ሴት በተሰበሰበ ገንዘብ 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የፈጀ የማዘጋጃ ቤት ሕንጻ የታደሰው በአቢይ ዘመንና በርሱ በቅንጡው ሰውዬ ቡራኬ ነው - የመጀመሪያ ግንባታው 3 ሚሊዮን ያልፈጀ ሕንጻ ዕድሳቱ ብቻ ምን ያህል እንደፈጀ (ከነሙስናው ነው ታዲያ) ልብ በሉ - በነዚህ ሰዎች እጅ ነው የወደቀችው ሀገራችን፤ በዚህ ብቻም በተውን በስንት ጣሙ፡፡ ሕዝበ አዳም ይልሰውና ይቀምሰው አጥቶ በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ሕዝብ በረንዳ እያደረ ለመናፈሻ ሥፍራ ማስፋፊያ በሚል ብዙ ሽህ ካሬ ሜትሮችን ከዜጎች የሚቀማው፣ ጂቡቲን የሚያህል የመሬት ስፋት እንደአሜሪካንና ፈረንሣይን የመሰሉ ኤምባሲዎች አለገደብ ተቆጣጥረው ባሉባት ሀገርና ከተማ ዜጎች 50 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ተነፍገው ከተማዋን መናፈሻ በመናፈሻ እያደረገ የሚገኘው ድሃ ጠሉ አቢይ ነው፡፡

ሀገር በጦርነትና በዜጎች መፈናቀል፣ በኦሮሙማዊ የዘረኝነት ክርፋትና ጥምባት እየታመሰች አስመሳዩ አቢይ ግን ጉዳ ጉዱን ለመሸፈን የሕንጻ ቀለም ቀይሩ በማለት ለከተማ ውበት የሚጨነቅ መሆኑን ይደሰኩራል፡፡ ይህ ባሕርይው ዲሊውዥን የሚለውን የሥነ ልቦና ደዌ ያስታውሰናል፡፡ ይህ በሽታ ነባራዊ እውነትን ከሚያጥበረብር የህልም ዓለም መለየት ካለመቻል የሚመነጭ የአእምሮ ልክፍት ነው፡፡ መጥፎነቱ ይህ ዓይነቱ ሥነ ልቦናዊ ደዌ መድሓኒት የለውም፡፡ ለነገሩ የሥነ ልቦና በሽታዎች በአብዛኛው መድሓኒት የላቸውም፡፡ የአቢይ ህመሞች ደግሞ ከብዛታቸውም የተነሣ ለመፈወስ የሚሞከሩ አይደሉም፡፡

አቢይ አህመድ ከርሱ በስተቀር የተማረ የተመራመረ ሰው ያለ አይመስለውም፡፡ እርሱ ብቻ ሁሉን አዋቂ፣ እርሱ ብቻ ዶክተር፣ እርሱ ብቻ መሃንዲስ፣ እርሱ ብቻ ፓይለት፣ እርሱ ብቻ ሾፌር፣ እርሱ ብቻ የህክምና ጠቢብ፣ እርሱ ብቻ አትክልት አጠጪ፣ እርሱ ብቻ ትራፊክ ፖሊስ፣ እርሱ ብቻ ጥሩ ባል፣ እርሱ ብቻ ቅን፣ እርሱ ብቻ ጥሩ አባት፣ ምን አለፋህ …. ከእርሱ ውጪ ማንም ቢሆን የሰውነትን የውኃ ልክ ያላሟላ መስሎ ይታየዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ ሌላ ሰው፣ ከነጭርሱ ሰው አይመስለውም፤ እናም ይንቀዋል፤ ይሰድበዋል፤ ያንጓጥጠዋል፤ በሌሎችም ያስቅበታል፡፡ የዚህን ሰው ባሕርይ ለመረዳት የዲክቴተርን ፊልም ዋና ገጸ ባሕርይ አድሚራል ጄኔራል አላዲንን ማየት በቂ ነው፡፡ እንዲህ ያለ ጠባይ አንድን ሰው የሚጠናወተው ሰውዬው ለራሱ ካለው የተጋነነ ግምት በመነሳት ነው፡፡ ያ ዓይነቱ ጠባይ በሥነ ልቦናው መስክ ናርሲሲዝም ይባላል፡፡ የዚህ ሳይኮፓቲክ ደዌ በሌላ አገላለጽ ሜጋሎማንያ ሊባልም ይችላል፡፡ ራስን ከሁሉም አስበልጦ የማየት በሽታ በሥነ ልቦናው ዘርፍ እንዲህ ነው የሚጠራው - ሰውዬው ደግሞ ሜጋሎማንያክ፡፡

አቢይ ካልሳቁለትና ካላንቆለጳጰሱት የጠሉት ይመስለዋል፡፡ በርሱ ተወዳጅ ለመሆን በግድ ማሞካሸትና “ካላንተ ይቺ ሀገር ዋጋ የላትም” እያሉ ዘወትር ማሟሟቅ በጤና ለመኖር ወሳኝ ነው፡፡ እንደዚያ ካልሆነ ነገር የሚጎነጉኑበት ይመስለውና ወጥመድ መዘርጋት ይጀምራል፡፡ ሳያጠፋ ደግሞ አይለቅም፡፡ እየሣቀና እያሳሳቀ ገደል ይከታል፡፡ ለዚህ ማስጃው ከባህር ዳር እስከ ሸገር የሠራው የግድያ ጀብድ ምስክር ነው፡፡ ይህ ጠባዩ የፓራኖያ ተጠቂ መሆኑን ያሳያል - ሰውዬው ደግሞ ፓራኖይድ ይባላል፡፡ ምን አለፋህ - አቢይ ያልተጠቃበት የሥነ ልቦና ደዌ የለም ቢባል ምንም አልተጋነነም፡፡

አቢይ ከርሱ በምንም መንገድ የሚበልጥን ሰው አይወድም፡፡ ይህ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው ሊባል ቢችልም በርሱ ግን ይከፋል፡፡ ምክንያቱም በሥራ ስኬትም ይሁን በስምና በዝና እርሱን የሚገዳደር ከሆነ አንድም ያጠፋዋል ወይንም በሹመት አሳብቦ ከፖለቲካው መድረክ ያርቀዋል፡፡ በነአምባቸውና በነአሣምነው ሁኔታ ካየነው ደግሞ ተቃዋሚውንና ተቺውን ከነጭርሱ ሊያስገድልም ይችላል፡፡ አቢይ የሚፈራው ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ኃይል ስለሌለ ማንም ላይ ምንም ነገር ከማድረግ አይመለስም - ሚስቱ ላይም ጭምር - አሁንም ድረስ በሚስትነት ካለች ማለቴ ነው፡፡ ሲሾ ደግሞ በጥቅሻ የሚታዘዙለትን ደናቁርትና ገና ሮጠው ያልጠገቡ ጮርቃ ሕጻናትን ነው፡፡ በነዚህ ሴቶች በሚበዙባቸው ዘረኛ ኩታራዎች እየተዳደረች ኢትዮጵያ የት እንደምትደርስ ለማየት የሚጓጓው ዜጋ ብዙ ነው፡፡   

አቢይ በ26 ወሮች የዶክትሬት ትምህርቱን እንደጨረሰ አንብቤያለሁ፡፡ እንኳን የሱን ዓይት ጥራዝ ነጠቅ ሰው ለጎበዝም ቢሆን ይህ የትምህርት ደረጃ ከአራትና አምስት ዓመታት በታች አይታሰብም፡፡ ስለዚህ የዚህ ሰው ሕይወት በዕንቆቅልሽ ስለመሞላቱ ከዚህ በላይ ማስረጃ የለም፡፡ ይገርማል፡፡

አቢይ ሲዋሽ ለነገየ አይልም፡፡ ገና ሥልጣን እንደጨበጠ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ “ሀገራችን ነዳጅ ልታወጣ ሂደቱን ጨርሳለች፡፡ በቅርቡ ምርት ይጀምራል” አለና ወስፋታችንን አንጫጫ፤ በተስፋ ዳቦም ሆዳችንን ቀበተተ፡፡ ግን የውኃ ሽታ ሆኖ ቀረ - ውሾን ያነሳ ውሾ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ “ኦሮሞ ከሚገባው በላይ የተለዬ ጥቅም አግኝቶ ከሆነ በ24 ሰዓታት ውስጥ ሥልጣኔን እለቃለሁ፡፡” አለና አስጨበጨበን፡፡ እውነቱ ግን ከአየር መንገድ እስከ ጎጃም መንገድ አክራሪ ኦሮሞ ሁሉን ተቆጣጥሮት ሀገሪቱ በኬኛ ፖለቲካ ስትታመስ ማየት ሆነ፡፡ ሌላው ቀርቶ አዲስ አበባ ላይ የወያኔ/ኦህዲድ/ኦነግ የይስሙላው ህገ መንግሥት ተጥሶ የኦሮሚያ መዝሙር በግዳጅ ሲዘመርና ባንዲራውም ሲሰቀል እያየን ነው - የሌሎቹ ክልሎች መዝሙርና ባንዲራም እንዲዘመርና እንዲሰቀል ብንጠይቅም የአንበሣው ተረት ነው ምላሹ - “ ‹አንበሣ ምን ይበላል?› ቢሉ ‹ተበድሮ› ‹ምን ይከፍላል?› ቢሉ ‹ማን ጠይቆ?›” ዓይነት አካሄድ ነው እየተስተዋለ ያለው ለማለት ነው፡፡ ለአንዱ ብቻ ማዳላት ነውርም ኢ-ህገ መንግሥታዊም ድፍረትም ዕብሪትም ነው፡፡ ይህ ወልጋዳና ሸፋፋ አሠራር ደግሞ “ቢያዝ ኤንድ ፕሬጀዲስ” የሚባሉትን የአቢይን ሥነ ልቦናዊ ህመሞች በግልጽ የሚጠቁም ነው፡፡

በዚህ መልክ ከሄድኩ መቼም አልጭርስም፡፡ ስለዚህ ዋና ዋና ነገሮችን ልጠቁምና ልሰናበት፡፡

አማራ ዒላማ ውስጥ ከገባ ቆዬ፡፡ አሁን የፍጻሜው ጨዋታ ላይ ይገኛል፡፡ የተሸፈነ ነገር ዝንታለሙን እንደተሸፈነ አይቀርምና የአቢይ ዓላማ ግልጽ ከወጣና የላኪዎቹን አጀንዳ እያስፈጸመ እንደሆነ አማራውም ሌላውም ተረድቷል፡፡  ጊዜው የመኸር ወቅት ነው፡፡ ጃልመሮና ጃል አቢይ በአማራው ላይ ቆርጠው ተነስተዋል፤ ደግሞም በአራዶች ቋንቋ ለመግለጽ ያህል በቀላሉ አይፋቱትም፤  ምክንያቱም ከዐውሬው ጋራ በነፍሳቸውና በደማቸው ተፈራርመዋል፤ ይህን እኔ አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ አማራን ለማጥፋት ሲባል በሤራ ፖለቲካ ተዘፍቀው በከንቱ ሲባዝኑ የከረሙ ሁሉ ክንዳቸውን አስተባብረው መጪዋ ክረምት ሳታልፍ ይህንን ነገድና በእርሱ ትወከላለች የምትባለዋን ኢትዮጵያ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ተማምለዋል፤ ቤተ መንግሥቱና ታንኩና ባንኩ ብቻ ሳይሆኑ የእያንዳንዳችንን ሕይወት በመያዣነት ስለያዙ ለነሱ ይህ ተልእኮ ቀላል መስሎ ቢታያቸው አይገርምም፤ ለዚህም ነው አሁን እንደሚስተዋለው ጻፍክና ተናገርክ በሚል የመጀመሪያውና ቀላሉ የዴሞክራሲ ግብኣት የተነሣ ሁሉንም አማራ ዘብጥያ ለማውረድ የቆረጡ የሚመስሉት፡፡ በዚህ ጎራ ውስጥ ግብጽ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ሕወሓትና አብዛኛው  በወያኔ ፕሮፓጋንዳ የተጠለፈ የትግራይ ሕዝብ፣ ኦነግ/ኦህዲድ፣ በገንዘብና በሆድ የተገዛው ብአዴን … ይገኙበታል፡፡ አማራ ደግሞ ጥቂት ወገኖችና ፈጣሪው ከጎኑ ተሰልፈው መጪውን ክረምት ይጋፈጣሉ፡፡ አሸናፊው ግን ከአማራው ወገን የተሰለፈው ኃይል ነው፤ በጣም ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም ሌሎች ጠንቀቅ ማለት አለባችሁ ማለት ነው፡፡ ይህን የምለው ለራሳችሁ ነው - ለአማራው አይደለም፡፡ አማራውማ ሁሉንም ለምዶታል፡፡ ከዚህ በላይ አልናገርም፡፡ ግን ግን ስትጣሉ ለዕርቅ በሚያመች መልኩ እንዲሆን ከአሁኑ ብዙም ሳይዘገይ አስቡበት፡፡ አሁን የምትቃዡበት ፋኖ … ለነገሩ ምን አገባኝ በዚህ፡፡

ይሄ ሰዎችን በተለይ አማሮችን የማፈን ነገር ኦነጎች ደግማችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት፡፡ ወደፊት ሕዝብ አንድ ሆኖ ይነሳል፡፡ ያኔ የለያዩትንና ሀገሩን የበታተኑበትን ወገኖች እያሳደደ ከነዘር ማንዘራቸው ቆረጣጥሞ ይበላቸዋል፡፡ መቅኖ ያሳጡትን ለገንዘብ ያደሩ ባንዳዎችን እገቡበት ገብቶ ያንቃቸዋል፡፡ ስለሆነም ብትችሉ ሰዎችን አታፍኑ፡፡ ለአንድ ዕብድ ሥነ ልቦናዊ እርካታ ስትሉ ታሪካችሁን አትበርዙ፤ አትከልሱ፡፡ ተገድዳችሁ የምታፍኑ ካላችሁ እንኳን የምትይዟቸውን ሰዎች በአግባቡ እንደሰው ያዟቸው፡፡ አታሰቃዩዋቸው፡፡ ወያኔ ሰውን ስታሰቃይ ከርማ አሁን ምን እንደደረሰባት አስታውሱ፡፡ የዘሩትን ማጨድ አለና እባካችሁን ሰውን ስታግቱ ጥቃቄ አድርጉ፡፡ የነገ ሰው መሆን ከፈለጋችሁ ደግሞ ከዚህ አፋኝ ሥርዓት በቶሎ ተላቀቁ፡፡ በርሀብ መሞትም ካለባችሁ ሙቱ - ሰውን በማሰቃየት ከሚገኝ ሲዖላዊ የሰይጣን ገንዘብ ይልቅ በድህነትና በርሀብ መሞት የተሻለ ዘላለማዊ ዋጋ አለውና ወገኖቼ በወራት ውስጥ ዕልባት በሚያገኝ ችግር ለመክበር አትቋምጡ፡፡ እኔ ተናግሬያለሁ፤ መስማት የናንተ ድርሻ ነው፡፡

በኑሮ ውድነት ህዝብን እያሰቃያችሁ ያላችሁ ማሰብ ጀምሩ፡፡ ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ የኅሊና ጠባሳ አታስቀምጡ፡፡ ዛሬ ትናንትን እንዳልሆነ ሁሉ ነገም ዛሬን አይሆንምና ከእንስሳነት ወጥታችሁ ሰው ሰው ለመሽተት ሞክሩ፡፡ አንተ ውስኪ ስትደፋና ጮማና ብርንዶ ስትቆርጥ አጠገብህ ያለ ድሃ በአሥር ሽህ የወር ደሞዝ መኖር አቅቶት በረንዳ ላይ እያደረ መሆኑን ተረዳ - ከርሱ የባሰውንማ ቤቱ ማለቴ በረንዳዎች ይቁጠሩት፡፡ በቃኝ  ባክህን …..

Tuesday, May 24, 2022

ኤርትራ የሞተችበት ቀን አክብራለች! 5/24/22 ጌታቸው ረዳ

 

ኤርትራ የሞተችበት ቀን አክብራለች!

5/24/22

ጌታቸው ረዳ

 “Wherever there is an ignorant mass, you will see a flag of an ignorant leader fluctuating with glory!”

(Mehmet Murat ildan)

 ምድሪ ባሕረ/ባሕረ ነጋሽ/ ተብላ ስትጠራ የነበረቺው የጣሊያን ስርትዋ የዛሬዋ “ኤርትራ” ነፃ በመውጣትዋ ሳይሆን “ሞታ ተገንዛ የሞተችበት” ቀን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዘጎችዋ ጥለዋት በመፈርጠጥ “የሸሹዋት”፤ሞታ የተገነዘቺበትን 30ኛዋ የሙት በዓልዋን አክብራለች።እንኳን ሰው የኤርትራ ውሾች ሳይቀሩ ተሰድደው በመጠለያ ጣቢያ ሲመዘገቡ በዜና ተመዝግቦ አድምጠናል።

ነፃነት ማለት ላሰቃየቻቸው ኤርትራ “የነፃነት ጣእም” ለኤርትራ ምን ማለት እንደሆነ ባይገባቸውም፤  ስደት ፤ባርነትና ሞት  “እንደ ነፃነት” የሚያጣጥሙ ሕዝቦች በዓለም ውስጥ ኤርትራኖች በቻ ሆነው ስንመለከት እጅግ አስገራሚ ነው።

የሳሕል ተራራ “ጋንግሰተሮች” የሚንደላቀቁባት ምድር ኤርትራ በሚያሳዝን ሁኔታ  “በዕልልታ የተቀበላቸውን ሕዝብ” ባርያቸው አድርገው የተቃዋሚ ኤርትራን ሬሳ ወደ አገር እንዳይገባ በማገድ፤ ሲያሻቸው፤ መግረፍ፤ ሲፈልጉ ዶክተሮችን “በኤይድ ቫይረስ” ወግቶ መበከልን ኤርትራኖች ራሳቸው የሚዘገቡዋቸው ዜናዎችን ስንመለከት፤ እውነትም የነፃነት ትርጉም “ኤርትራኖች ዘንድ ስትደርስ ትርጉም የላትም”።

በሕዝቡ ላይ “የመናገር ነፃንትን መንፈግ ፤የስደት፤የሞትና የፍርሃት” ቀንበር የጫኑበትን “የሳህል ጋንግስተሮች” የነፃነት ቀን ብለው “ኤርትራኖች” የገዢዎቻቸውን “የነጻነት ቀን” የነፃነታችን ቀን ነው ብለው እየጨፈሩ መመልከት እውነትም “ባሮች ጌቶቻቸው ሲታመሙ የሚታመሙ፤ ሲጨፍሩ አብረው የሚጨፍሩ፤ ሲስቁ አብረው የሚስቁ” አዳዲስ ባሮች በምድር ይከሰታሉ ተብሎ በትንቢት የተነገረው በኤርትራኖች ላይ አየነው።

 የሚያሰዛነው ግን ዳግም ላንመለስሽ ብለው “ድንጋይ” ወርውረውባት “የሰደቡዋትን” ፤ “ያወገዝዋትን” ኢትዮጵያ “እግርዋ ላይ ወድቀው ተሳልመው፤ጥገኝነት ስጪን” ብለው ገብተው እንደገና አንመለስብሽም ባልዋት ምድር አዲስ አባባ ውስጥ “አህያ” እያሉ ኤርትራ ውስጥ ከጨፈጨፍዋቸው የአማራዎች የጉራጌዎች፤የኦሮሞዎች፤ የጋምቤላዎች የጋሞዎች ፤የሶማሊ…አገር መዲና አዲስ አባባ ላይ ሲጨፍሩ ማየት ለኛ ኢትዮጵያዊያን “ሞትና ውርደት” እንደሆነ ተሰምቶኛል።

 ዳሩ ግን እነሱ ምን ያድርጉ? አብይና ወያኔ እስካሉ ድረስ “በአህዮች አገር” እንዲጨፍሩ ተፈቅዶላቸዋልና ነፃ በሚሊዋት ነፃ ኤርትራቸው ውስጥ ያልተፈቀደላቸው ነፃነት አዲስ አበባ ውስጥ አገኙዋት! “በሞኞች መንደር ቀምበር ይቆረጣል” ይባል የለ!

“Wherever there is an ignorant mass, you will see a flag of an ignorant leader fluctuating with glory!” “መሃይም ሕዝብ ባለበት ቦታ ሁሉ የመሃይም መሪ ባንዲራ በክብር ሲውለበለብ ይታያል!”

( መህመት ሙራት ኢልዳን)

እውነት ነው። መሃይም ሕዝብ ባለበት አዲስ አበባ ውስጥ ፤ያውም የባሕር በራችን የዘጋንን የመሃይም መሪ ባንዲራ በክብር ሲውለበለብ ከማየት የሚያም ነገር የለም !”

ኤርትራ የሞተችበት ቀን አክብራለች! እንኳን የሞታችሁበት፤ ለስደት የዳረገቻችሁ ነፃነታችሁ ቀን አደረሳችሁ! ለእኛ ግን የተዋረድንበት፤ እናንተም ተሰድዳችሁ የምትጨፍሩባት ኢትዮጵያ በማግኘታችሁ “ከመሞት መሰንበት” ይሉታል ነፃነት ማለት ይህ ነው። ኢትዮጵያ ሆይ “የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” የተባለው ለካ ለእንደዚህ አይነትም ነው።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

  

Sunday, May 22, 2022

አስቸኳይ ደብዳቤ ፣ ይድረስ ለአቢይ አህመድ ከደብሩ ነጋሽ (ሃኪም) ሕትመት -Ethiopian Semay- 5/19/2022

 

አስቸኳይ ደብዳቤ ይድረስ ለአቢይ አህመድ

ከደብሩ ነጋሽ (ሃኪም)

ሕትመት -Ethiopian Semay-

5/19/2022

ለዛሬ “ከትውስታ ማህደር” ውስጥ መርጬ  ኦትዮ ሰማይ  ላይ ታትሞ የነበረ ሰነድ በማቅረብ በአብይ አሕመድ አገዛዝ ሥር የተፈጹ አሰቃቂ ወንጀሎችን ባጭር ደብዳቤ የተጠቃለለ የሚያስረዳ ሰነድ ከሕሎናችን እንዳይጠፋ የሚያሳስበን ሰነድ እነሆ ያንብቡ!!

የኦሮሞው ሹማምንቶችህ ህጋዊ ቤቶች የማፍረስ ዘመቻ፣ በኢትዮጵያውያን ላይ የጦርነት አዋጅ ነው።

ለዘመናት ሲያሰቃይ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ወራሪ ወያኔን በአመጽ አፍረክርኮ፣ አንተንና መሰሎችህን ስልጣን ሲያስጨብጥ፣ ፈንጥዟል። ክስተቱ የመለኮት ስራም ነው ያሉ የዋሆች ነበሩ። በተለይ አንተንና ለማ መገርሳን፣ ሲያወድሱ የነበሩት ጥቂት አልነበሩም። ባደባባይ ትናገሩ የነበረው፣ ህዝብ ሊሰማ የሚፈልገውን ነበር። የብዙ ህዝብ ደም በግፍ ካፈሰስው ኦነግ፣ የምትለዩ ስለመሰለው ነበር።    በህዝብ አመጽ ልስልጣን በቅተህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊሰማ የሚፈልገውን በመናገርህና፣ በርካታ በግፍ የታሰሩን በማስፍትታትህ፣ ህዝብ ተደሰተ።  እመነት የጣለብህ፣ በከንቱ እንደሆነ ያለፉት ሁለት ሶስት ወራት ክስተቶች ያመለክታሉ። ለነገሩ የግንዛቤ እጥረት ካልሆነ የስራዐት እንጂ የሹማምንት መቀያየር እርባና እንደሌለው በተረዳ ነበር።

ስልጣን ከያዝክ ጀምሮ ያንተም ሆነ የባለሟል ኦርሞዎች ማንነት ይፋ ሆኗል።  የሰሞኑ የመግስትህ ድርጊት ግን በእትዮፕያውያን ላይ ጦርነት እንዳወጅክ ግልጽ ነው። ‘’ጅብ እስኪነክስ ያነከስ’ ‘እንዲሉ፣ ያንተና የለማ፣ ቃላት ፍሬከርስኪነት ታውቋል። ድርጊታችሁ፣ ከጅብ ትክክለኛ ባህርይ ያመሳስላችኋል። ላብነት ከዚህ የሚከተሉትን እንዘርዘር።

    ‘አደባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ

ታልንት በወለጋ አያሌ ባንኮች ኦነግ በተሰኘው የኦሮሞ ቡድን  ሲዘረፉ ንጹሃን ሲፈጁ፣ አዛዣቸውም መንግስት እያንደላቀቀ ሆቴል እያኖረው፤ እርሱም ሆነ ከምንዝሮቹ አንድ ሰው ተይዞ ለፍርድ አልቀረበም በርካታ ሚሊየን የህዝብ ገንዘብ ተዘርፎ ሳንቲም አልተመለሰም።  አንድ ሚሊየን ህዝብ ሃረርጌ ሲባረር፣ ወደተወለደበት ከመመለስ ይልቅ፣ የኦሮሞን ቁጥር በአዲስ አበባ ለማግዘፍ በሚመስል መልክ፣ አዲስ አበበ እየሰፈረ ነው።  እንግዲያው ገጠርና ቆላማ በሆነው ሃረር፣ በእርሻና ከብት ርቢ ይተደደር የነበረውን ህዝብ፣ ከኖረበት መልሶ፣ በሙያው እንዲተዳደር ያለመደረጉ፣ ለእኩይ አላማ መሆኑ ግልጽ ነው። የስራ እድል በሌለበት ነባር ነዋሪዎች በመብራት፣ የውሃ ችግር ሲሰቃዩ፣ የአማራና የሌሎች ዜጎችችን ቤቶች፣ ለገዳዲና ለገላፍቶ በግፍ እያፈረሱ፣ ከሃረር ኦሮሞዎችን ማስፈር አንተም ሆንክ፣ ቡድንህ ከመጠየቅ አይድንም።

ከወራት በፊት፣ በትግራይ ድንበር ላይ የነበረ ሰራዊት ወደ ማህል አገር በመንቀሳቀስ ላይ ባለበት ግዜ ደጋግሞ ታግቷል። ለቀናት መንገዱን በዙጉበት ዜጎች አንዲት ጥይት አልተተኮሰም። ይህም ተገቢ ነበር። ግን ይህ በሆነ በሳምንት ግዜ ጎንደር አካባቢ ይሀው   ኢትዮጵያ ሰራዊት 29 ሰላማዊ ሰልፍ የወጡን አማሮችን በግፍ በጥይት ደብድቦ 9 ውድያው ገድሏል። የወያኔን የመንገድ ስራ ድርጅት ተሽከርካሪዎች በፍርድ ቤት ማዘዣ ለመፈተሽ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በነበሩ አማሮች የጥይት ናዳ ያወረደባቸው የወያኔን ግል ድርጅት ያጀበ ሰራዊት ነው። በትግራይ ውስጥ ጠጠር ሳይወረወር፣ በአማራው ላይ ጥይት ያዘነበው ሰራዊት የጦር አበጋዝ፣ ለዎያኔ ያደረ ምርኮግኛው ኦሮሞ መሆኑን ልብ ይሏል።

የድንበርን ውዝግብ ይፈታ ዘንድ በሚል ምርህ፣ በተቋቋመው ቡድን በሃይል የወልቅይትና ራያን ወደ ትግራይ የከለለውን የወያኔ የቀድሞ መሪ ሳይቀር አካተሃል። ወሎን፣ ሸዋን ቆራርጦ ኦሮምያ ለተባለው ግዛት ለደለደለውና  ለበርካታ ሚሊዎን  አማራ እልቂትም ሆነ፣ ባገርቷ ለደረሰው መከራ ከሚጠየቁት መሃል አንዱን፣ ነጋሶ ጊዳዳን  ጭምር ሰይመሃል። ለድንበር ዳኝነት ያሰባስብካቸውን አላማውን የሚዋጅ ስብዕና የሌላቸውን ጭምር ናቸው። ግማሹ ከኦሮሞ ነገድ ነው።የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥአደል?   እሪ በይ አይ እትዮጵያ ያሰኛል።

በመጨረሻ፣ የባለቤትነት ህጋዊ ሰነድ ያላቸውን ሰዎች ቤቶች፣ ከማፍረስ የባሰ የጦርነት አዋጅ የለም።  በለገዳዲና ለገጣፎ መሬቱን የቸበቸቡ የኦሮሞ ሹማምንትና አፍራሽ ግብረሃይል፣ እንደወራሪ፣ ቤቶቹን ሲያፈርሱ፣ ኡኡ ይሉ የነበሩን ባለቤቶች  ‘መጤበማለት እየተሳደቡም፣ነበር። እንኝህ ለህግም ሆነ፣ ለስረአት ባይተዋር የሆኑ፣ የኦሮሞ ሹማምንት፣መጤየሚሉት ያን የፈረደበትን አማራ ብቻ አደለም። ከድፍን ኢትዮጵያ የመጡ ወገኖቻችን ሁሉ ነበር። ይህ የፈሪዎችና የአይምሮቢስ ኦነግ ልሂቃን ድርጊት የጨዋና የደጉ ኦሮሞ ህዝብ ሊያውግዘው ይገባል። ይህ ግፍ ከቀጠለ፣ የኦሮሞን መንግስት ወረራ  የማይቋቋም የለም።

የኢትዮጵያውያን ለአንድ ትውልድ፣ የግፍ ግፍ የፈጸሙባቸውን የወራሪ ወያኔዎች ቡድን ሲንገዳገድ ተገንዝቦ ህዝቡ ስራዐቱ የተገረሰሰ መሰሎት ነበር። ከጅምሩ፣ ረዥም እድሜውን በወያኔ ሞግዚትነት ላደገ ዜጋ፣ ለኢትዮጵያዊነት ባዕድ ሊሆን ይችላል። የኢትዮጵያን ጥንታዊነት፣ ተረትና የቅርብ ግዜ ፈጠራም እንደሆነች ሲሰማ ለኖረ በወያኔው ግብረ፟_አበር በኦነግ ትርክት ምንሊክ 5 ሚሊየን ኦሮሞን ፈጅቷልየሴቶች ጡት ቆርጧል እየተባሉ በደረቅ የሃሰት ታሪክ ላደጉ ኦሮሞ ሹምምንት፣  ይህ የተፈጸመው ግፍ ከመጤፍ አይቆጠር ይሆናል። የአቢይና ለማ ማንነት ከዚህ አይዘልም።  ‘’ከወርቁ’’ የትግሬ ነገድ የተፈጠረውን አለቃህን ይመስል፣ መቀሌ ሄደህ፣ እንደበቀቀን፣ያንን ስትደግም፣ አልተቸገርክም። ባንጻሩ አሜሪካ በሄድክበት ወቅት፣ አለም ያወቀውን ጸሃይ የሞቀውን ፣በአማራ ላይ የተፈጸመ የዘር ፍጅት፣ በአደባባይ የካድክ ጎበዝ ነህ።

በአኖሌው የጥፋት ሃውልት ግንባታ፣ ግዙፍ ተሳትፎ እንደነበረህ አይካድም።

በሃሰት ትርክት በተመሰረተ ወንጀል፣ ያልታጠቀ፣ያልጠረጠርንራ እልቆ መሳፍርት የሌለውን አማራ እልቂት ያስከተለን ሃውልት፣ ከመቅጽበት መናድ ሲገባህ፣  አስካሁን ተገትሯል።  ስልጣን እንደያዝክ ኦሮምያ በሚባለው የደባ ክልል የሚኖረውን 15 ሚሊዎን ህዝብ ሰቆቃ ፣ቀጥለህበታል በአማርኛ እንዳይማር፣ እንዳያስተምር በመንግስት ተቋማትም እንዳይገለገል የሚያደርገውን ፣የግፍ እግድ እንኳን አላነሳህም። እነኝህን ከማንሳት ይልቅ፣ ኦሮሞ ያልሆኑን ኢትዮጵያውያን ህጋዊ ቤቶች ማስፈረስ፣ አጣዳፊ ልምን እንደሆነብህ ትጠየቅበታለህ!!

አንድ በሰሞኑ ለገጣፎ ቤቷ የፈረሰባት እናት፣ ያንተን ከኤርትራን ጋር እርቅ መሻት ስትደሰት እትዮጵያውያንን በግፍ በመንቀልህ የደም እምባ እያለቀሰች ነበር ለውጭ ስደተኛ የሚሳሳ መንግስትህ፣ በእትዮጵያውያን ላይ ይህን ግፍ በማስፈጸምህ ይቅር የምትባልበት አደለም።

ይህ ኦሮምያ በሚሉት መስተዳደር የተጧጧፈው የሌሎችን ዜጎች በህግ የተሰሩና ለአመታት ይገበርባቸው የነበሩን መኖርያ በቶችን በነዋሪዎቹ ላይ የማፍረስ ዘመቻ ያንተንም ሆነ የምትወክለውን ህዝብ ስነልቦና ምንነት ጠንቅቆ ያሳያል። ኢላማ የተደረጉት የከተማዋ አብዛኛ ነዋሪ የሆነው በህግ ከለላ የሚፈጀውና የሚፈናቀለው አማራ ብቻ ሳይሆን፣ ከተለያዩ ቦታዎችህ የመጡ ነባር ኢትዮጵያውያን ናቸው።

                                                   ‘ትኩስ እረሳ፣የደረቀን አስነሳ

ይባስ ብለህ አማራንም ሆነ ለሎችህ ኢትዮጵያውያንን  ቤቶች አፍርሶ በሺዎች የሚቆጠሩን ወገኖቻችንን ለቀን ሃሩር፣ ለሌሊት ቁር መዳረግህ፣ መልዕክቱ ግልጽ ነው። ልክ በፋሽስት ጣልያን ግዜ ተሞክሮ እንደከሸፈው ሁሉ፣ የሸዋ ኦሮሞ፣ በወገኑ አማራውም ሆነ ለሌሎች፣ አጋር ወንድምነቱን በመግለጽ፣ ልዕልናውን እንደገና አስመክሯል።

የአቢይ መንግስት  ግንትኩስ እሬሳ፣የደረቀውን አስነሳአስኝቶናል።  የኦሮሞው መንግስት ድርጊት፣ የትላንቱን የከፋውን አባጆቢርና፣ መሰሎቻቸው፣ በወለጋ በኢሉባቦር፣ በሃረር ፣በጣልያን ሃይ ባይነት፣ የተፈጁትን፣ ያልታጠቁ አማሮች ሰቆቃ ያስታውሳል። ዛሬ መሳቂያ ባደረገውአዲስ አበባን የኦሮሞ ናት የሚለው ቅዠት፣ የሚናውዘው የኦሮሞው መንግስት፣ አቅም ቢኖረው፣ ከፋሽስቱ ወያኔና  ከጣልያን ያልተለየ ግፍ ባማራውና በሌሎች ወገኖች ከመፈጸም የምይመለስ መሆኑን ነው።   በህዝብ አመጽ ልስልጣን በቅተህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊሰማ የሚፈልገውን በመናገርህና፣ በርካታ በግፍ የታሰሩን በማስፍትታትህ፣ ህዝብ ተደሰተ።  ህዝቡ እመነት የጣለብህ፣ በከንቱ እንደሆነ ያለፉት ሁለት ሶስት ወራት ክስተቶች ያመለክታሉ። ለነገሩ የግንዛቤ እጥረት ካልሆነ የስራዐት እንጂ የሹማምንት መቀያየር እርባና እንደሌለው በተረዳ ነበር። ዘመቻህ ያንተም ሆነ የባለሟል ኦርሞዎች ማንነት ይፋ አድርጓል።

የአዲስ አበባን በረራነት አትስተውም። በትንሹ 1500 ዘመናት በፊት የአማራ፣ የጉራጌና ጋፋቶችና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ከተማ መሆኗን አታውቅም አይባልም ነባርቹ ኢትዮጵያን እንክዋን የኛ ብቻ ከተማ ናትብለው አልቀለሉም።

ማንኛውም ነገር ገደብ አለው። ያንተን አመራር ጨምሮ። ዛሬ አንተ የምትመራው በሚመስለው የወያኔ መንግስት የሚፈጸመው ግፍ አንድ እና  ሁለት የለውም። ያለአንዳች ሃፍረት፣ ይሉኝታ፣ ፈሪሃ እግዚብሄር፣  ህዝብን ለርስበርስ ለጦርነት የሚገፋፋ ድርጊት መፈጸሙን መገንዘብ የሚሳንህ አይመስልም። ምናልባትም የትም አይደርሱበሚል የትዕቢት ከሆነ ተሳስትሃል።

ስለዚህ አንድ ነገር ልብ አድርግ።  ለግብር ይውጣ የሚደረግ  ማንኛውም  ነገር ዘለቄታ አይኖረውም   ዛሬ የሚፍጸመው ግፍ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀሬ ነው። እዳው ከባድና ከነአራጣው  መከፈል ስለሚኖርበት አበው  ‘አደባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱእንዲሉ። ከመቅጽበት ይህንን የህዝብ ሰቆቃ ካላቆምክ፣ የተፈጥሮ ህግ ነውና፣ የተገፋው ይነሳል። አታቆመውም።

በመጨረሻ፣ የግራኝን ወደር የለሽ ገድል በመጥቀስ ልሰናበት ጥሎበት አማራውን እጅግ ይፈራው ነበር። ስለሆነም   ሃይማኖት ሳይለይ፣ እስላምና ክርስቲያኑን አማራ እኩል ነበር ይፈጀው የነበረው። ብዙ ከተዋጋቸው አማራ መሃል ከአስሩ ነዋሪ፣ አንድ ብቻ የተረፈበት ግዜ ነበር። ዛሬ ወያኔና ኦነግ በአማራው ህዝብ ላይ ተመሳሳይ የጥፋት ዘመቻ የተያያዙ ይመስላል። በሁለቱ ጣምራ ጦር የተፈጀው ህዝብ፣ ሂትለር ከፈጃቸው አይሁዶች ቁጥር ይበልጣል። ግፍ ዘለቄታ አይኖረውምና   ይቅናሃ!!

Posted - Ethiopian Semay