መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተነገረ የወያኔ ትልቁ ንድፍ
“ነፋስ ላይ በአእዋፍ የተሠራች ዩቶፒያ ከተማ”
ጌታቻው ረዳ
(Ethiopian Semay)
4/19/2022
ደጋግሜ ሳስጠነቅቅ የነበረው “ዳቦ ስጡኝ አገር ላፍርስ” የትግራይ ወንጀለኛ ፖለቲከኞች ስልት ለማቆም የሚቀይስ አዲስ ኢትዮጵያዊ መሪ ካልተገኘ አብይ አህመድ የድሮ አለቆቹን ዳቦ እያጎረሰ ኢትዮጵያ እንድትፈርስ እንደሚያደርግ ብዙ ጊዜ ገልጫለሁ።
እየገፋ የመጣው የትግሬዎች ፋሺስታዊ ባህሪ ሮማዊያን ጃካርታን እንዳጠፍዋት አይነት ወይንም አቴናዊያኖች( Athenians) መሊያኖች (Melians) እንዳደረግዋቸው ዓይነት “የአካባቢ ጎብለልነት” እየተሰማቸው መጥቷል።
ከላይ በፎቶ የሚታዩት የወያኔ ምልምል ህጻናት ስትመለከቱ በጦርነት አውድ ልምድ ያላቸው ሰዎች ከጻፍዋቸው መጽሐፍት ውስጥ ካነበብኩት “Where Soldiers Fear to Tread” በሚል የሶማሌ ህጻናት ተዋጊዎች አስመልክቶ ሲናገሩ “አዋቂ ተኩሶ ሲገድል እና ሲዋጋህ የመሞት ልምድ ስሜት ይሰማሃል፡ ይላሉ፤ አስፈሪው ነገር ግን ‘ጣቱን ጥይት በተጫነው መተኮሻ ላይ አሳርፎ ወዳንተ የሚገሰግስ ህጻን ተዋጊ ጋር ፊት ለፊት ከመጋፈጥ የሚያስፈራ የከፋ ነገር ምንም የለም”። ይላሉ።
አቴናዊው የግሪክ ድራማ ባለሙያ ታላቁ አሪስቶፋነስ ትኩረትን ወደ አቴናውያን በማዞር በጥጋብ ተወጥራ የነበረቺው አቴና ተሰላችታ በማየቱ “በአእዋፍ ውስጥ” የሚል የሽሙጥ ቀልደኛ ጨዋታ (የመድረክ ትወና) በማዘጋጀት፣ በጦርነት ለደከሙ የአቴንስ ታዳሚዎች በ416 ዓ.ዓ (የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈፀመበት ዓመት ማለት ነው)። አርስቶፋነስ “አቴንስ ያሳየቺው የማይጨበጥ የጎብለሎች ሕልም” ለመግለጽ “ነፋስ ላይ በአእዋፍ የተሠራች ዩቶፒያ ከተማ” በማለት ነፋስ ላይ ተንጠልጥሎ የሚሰራ ከተማ ምን ሊመስል እንደሚችል አድማጮቹን በዓይነ ሕሊናቸው እንዲመለከቱ የጻፈው ተውኔት ሰሞኑን “ጀነሳይድ” የሚል መጽሐፍ ሳነብ ትዝ ያለኝ “ምስረታ ሃገረ ትግራይ” “በነፋስ ላይ በአእዋፍ የተሠራች ዩቶፒያ/፤የማይዳሰስ/ ከተማ ” ብሎ አሪስተፋነሰ የቀለደበት አገራዊ ምስረታ ተመሳሰለብኝና የጌታቸው ረዳ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ስብሰባው ከትግርኛ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ።
የወያኔ ትግሬዎች የዜና ማሰራጫዎችም ሆኑ በመሪዎቻቸው የሚካሄዱ ስብሰባዎችና ዘፈኖቻቸው ፋሺስታዊ ጉራዎች ስለሚበዙባቸው፤ ቀልብ ስለማይስቡ ኣብዛኛዎቹ አላዳምጣቸውም። በዚህ ላይ አንድ ወዳጄ “ለመመራመር እየመረረህም ቢሆን የግድ ማድመጥ አንዳለብህ እያለ ይመክረኛል”።
ሰሞኑን ግን የ “ዓ. ሽ. ኣ” ዎች የትግርኛ ንግግር ዘይቤ በደምብ ተምሮ እንደርታዎቹን እያስቀና በመናገር ላይ ያለው የራያው ጌታቸው ረዳ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ “አሻንጉሊት ምሁራኖች” ባደረጉለት የስብሰባ ጥሪ ተገኝቶ ያደረገው ረዢም የጥያቄና መልስ ውይይት የወያኔ ትልቁ ንድፍ “ከኢትዮጵያ መገንጠልና አገር ማቅናት” እንደሆነ በግልጽ ነግሯቸዋል። እነሱም ፍላጎታቸው ያ እንደሆነ ገልጸውለታል።
የጌታቸው ረዳ የንግግር ዘይቤ አንዱን ቅጠል ሳትጨርስ ወደ ሌላው ቅጠል እየዘለለች እንደምታመነዥክ ቀዥቃዣ ፍየል አይነት ስለሆነ ምኑ ከምኑ ለቅመህ እንደምታያይዘው የሚያስቸግር ዝርክርክ ተናጋሪ ነው። አንግሊዝኛ ቃላትን መጠቀም በየአረፍተ ነገሩ ያሰለቻል። ሆኖም የውጭ አገር ታዋቂ ሰዎች ንግግር እየጠቀሰም ሆነ ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ያጋጠሙት ገጠሞቹን እያስዋበ በማኖህለልም ሆነ አንዳንድ አስቂኞችን ጣልቃ እያስገባ ደናቁርቱን “በማስሳቅ” እያስጨበጨበ የሚሞክረው ችሎታው ግን የተሻለው የንግግሩ ክፍል አንዱ ነው።
ከደናቁርቱ አንዱ የሚከተለው
ይጠይቀዋል፤
እንዲህ ሲል፤-
“ እኛ አገር ለመመስረት ስንሞክር አሜሪካኖች አንዴ የመደገፍ አዝማሚያ ያሳዩና ተሎ ደግሞ ጥርጣሬ ውስጥ ይገባሉ፡ ይህ ሊሆን የቻለው ወያኔ በምትከተለው “የሪቮሊሺናሪ ዲሞክራሲ” መርሃ ግብር ይመስልሃል?” ይላል።
የሚከተለው ይመልስለታል፤-
“አሜሪካኖች ስለ ሪቮሊሺናሪ
ዲሞክራሲ ተከተልክ አልተከተልክ “ጉዳያቸው አይደለም!” እነሱ የሚያሳስባቸው “ቴሌኮሚኒኬሺን፤ ባንክ፤ የተፈጥሮ ሃብት ….ማግበስበስ
የሚችሉበት በር ከከፈትክላቸው ይቀበሉሃል፤ የሚያሳስባቸው ይህ ነው እንጂ ስለ ምትከተለው ፖለቲካ “ሁ ኬርስ!!” የዓለም አገሮች
“ሪቮሊሺናሪ ዲሞክራሲ” አያውቁትም ፤ ጉዳያቸውም አይደለም። “አየር መንገድ፤ ቴሌ፤ ትሸጡልናላችሁ ወይ? ብለው ነው የሚጠይቁን
፤ እሱም ቢሆን አገር ሆነን በሗላ የሚሆን ነገር ነው። በማለት አሜሪካኖች የሚፈልጉት ከሰጠናቸው የኛ አገርነት ይቀበሉታል። የሚል
ፍንጭ ከሰነዘረ በሗላ፤
በመቀጠል-
እኛ ማርክሲሰቶች ስለሆንን አሜሪካኖች አይደግፉንም የሚሉ የመንደር ወሬዎች አሉ። ይህ ቅዠጥ ነው። ብዙ ወዳጆች አሉን ስለምንከተለው ፖለቲካ ጉዳይ አይሰጣቸውም። ብዙ ወዳጆች አሉን፤ ብዙ ነገሮች ውስጥ ለውስጥ ለማምጣት እየሞከርን ነው። እነሱ ይህንን የሚያደርጉልን “መለስን ስለሚወዱ እኔን ሰለሚወዱ ወይንም ትግራይን ስለሚወዱ እንዳይመስላችሁ” ፤ የትግራይ አገርነት ፍላጎት በመደገፍ የነሱን ፍላጎት ይጠቅመናል ከሚሉት ጋር በማገናዘብ ሊደግፉን ይንቀሳቀሳሉ። ለምሳሌ ተከብበናል ስንል በድንገት … (?) ብሎ (ድሮን ?) ለማለት “አግኝተናል” ለማለት ይመስላል
“ሶርያ አግኝታለች” “የመኖች አግኝተዋል” በማለት በደፈና ስለ የውጭ ዕርዳታ ምን እንደተሰጣቸው ፍንጭ ሳይሰጥ ስለ የመኖች ሲያወራ “ድሮን” እንደተሰጣቸው የሚመስል ነር “ፍንጭ” ንግግር ሲናገር ይደመጣል።
ትግራይ እንደ አገር ዓለም እንዲያውቋት የሚገደዱበት ስራ መስራት አለብን። ያንን ማድረግ ከቻልን “ኢን ኤቭሪ እስቴፕ ኦፍ ዘ ወይ” (በያንዳንዱ ዘርፍ)ተፈላጊዎች እንሆናለን ማለት ነው። መጀመሪያ “ብሔረ ሃገረ ትግራይ” ለመመስረት አስፈላጊ “ኢንስትቱሽን” መስራት አለብን። “ሠራዊታችን” የዚህ አካባቢ “ጎብለል” እንዲሆን ካደረግነው ራሳቸው ይፈልጉናል። Red Sea/ የቀይ ባሕር/ ሃያሎች መሆናችን አሁን እያመኑ ነው። የዚህ አካባቢ “እስታብሊቲ” (የሰላም ምሰሶዎች) መሆናችን ማየት ጀምረዋል። ሌላ ቀርቶ “አብይ አሕመድ” ሠራዊታችን የትም ቦታ ገፍቶ መግባት እንደሚችልና የሚያቆመው ሃይል እንደሌለ ያውቃል።
በማለት ይህ ካብራራ በሗላ፦ ስለዘረፋ ያነሳል። እንደሚታወቀው አማራ “ክልል” ውስጥ ወያኔ ገብቶ የሕዝብ ንብረት ሲዘርፍ እንደነበር የታወቀ ቢሆንም፡ ጌታቸው ረዳ ዝርፍያው ተዋጊዎቹ ሳይሆኑ ከተዋጊዎች አብረው የመጡ የትግራይ ሰላማዊ ሰዎች (ሲቪሊያን) ቴሌቪዥን ሳይቀር እየዘረፉ ተሸክመው መዝረፋቸው አምኗል። ይህንን በማያያዝ እንዲህ ያለ የዘረፋ ስነ ምግባር ከትግራይ አገር ምስረታ ጋር የማይጣጣም “ስነ ምግባር” እንደሆነ እና ተዋጊዎቹ ያደረጉት እንዳልሆነ ሽምጥጥ አድርጎ ለሲቪልያን የትግራይ ሰዎች “ሌብነቱን” ያሳቅፋቸዋል።
“አዲስ አባባ እንኳን አልገባን” በማለት “ብንገባ ኖሮ” ይላል “ይህ ሁሉ መስዋእት ተከፍሎ እነዚህ ዘራፊዎች ከተማውን በመዝረፍ ድላችን ያበላሹት ነበር” በማለት ይገልጻል።
አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ ይላል ጌታቸው ረዳ ሰለ የወያኔ ታጋዮች ኢትዮጵያ በሚመለከት እንዲህ ይላል፤-
“ወዲ አሸብር የሚባል የተዋጊዎች መሪ አለ። 100 ተዋጊዎች እየመራ ሲያዋጋ ነበር፡ ወዲ አሽብር እስኪ ኢትዮጵያ የምትሉ ወይንም ትግራይ የምትሉ ሌላም አስተያየት ካላችሁ ተወያዩ ይላቸዋል። ከነዚህ ውስጥ 5ቱ ከኢትዮጵያ ጋር 15ቱ በፌደረሽን ይላሉ 80 ዎቹ ግን “ሃገር ትግራይ” ምስረታ ሲሉ ወሰኑ። ይህ የተለያየ ድምጽ ይኑር እንጂ እንደ አንድ መሪ ስለ ትግራይ ህልውና አንድ አድርጎ መምራት እንደሚቻል ማሳያ ነው።” ይላል።
አንድ ነገር ልንገራችሁ “የናይጄሪያው ባባ ሳንጆ” መቀሌ መጥቶ እያለ ፡”ደብረብርሃን አካባቢ” መድረሳችን ሲያውቅ “ስለ አየር መንገድ ምን ታስባላችሁ?” ሲለን ነገሩ እንደገባን እርሱም እንደገባው ተግባባን። ነገሩ አልቋል ማለት ነው።” ይህ ለናንተ እንደ “ለኮንሳምፕሺን” (ለፍጆታ) እንዲሆናችሁ በማለት ነው እየነገረኳችሁ ያለሁት። በማለት በንቅዝና የታወቀው የናይጀሪያው “ባባ ሳንጆ” አየር መንገድ ለመቀራመት መጓጓቱን አስታራቂ መስሎ በመግባት የጠቀሰለትን በፍንጭ ወርወር አድርጎ ተስበሳቢዎችን አስረዳቸው። አብይ የመረጠው ባባ ሳንጆ አጀንዳው ነግሮናል ማለት ነው።
ቀጠል ያደርግና አገር ለመመስረት ማድረግ ያለብን መጀመሪያ “ትግራይ አገር ነች ብለን” ማሳመን ነው። ከ’ሶማሊ ላንድም’ ሆነ ከማንም አፍሪካ አገር በጣም በተሻለ አገር የሚያስብል ግብአቶች አሉዋት። ነገር ግን እዛ ለመድረስ ቅደም ተከተሎቹን ማስቀመጥ አለብን።
የመጀመሪያው የሰብኣዊ ዕርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባ መረባረብ ነው። የደረሰብንን ጥቃት ከእንግሊዝ፤ከፈረንሳይ ወዘተ.. ዲፕሎማሲ ግንኙነት በማድረግ እነዚህን ማሳማን አለብን። ‘የሰብአዊ መብት ረገጣዎች’ እና ‘የምግብ እቃባ’ ትልቅ “ርዕስ” ሆኖ እየተነጋገሩበት ነው። ይህንን ማጥበቅ አለብን።
ከዚያም ከእስፐይን፤ ፈረንሳይ ጣሊያን.. ክብደት ያለው ውይይት (ኢንጌጅሜንት) እያደረግን ነው። ከትርኮች ጋርም በተለይ ንግግር ጀምረናል። ድሮን እየሰጣችሁ “የመንገዳችን ጉዞ እንቅፋት ሆናችሗልና እባካችሁ ታቀቡ ብለን ንግግር ጀምረናል። ተስፋ ሰጪነት ያለው ይመስላል፤ እውነት ይሁን አይሁን የሚታይ ነው።
…ተከበናል፤ ሕዝባችን በችግር ውስጥ ነው፤ እያልን እያሳመንናቸው ስለሆነ “ዓለም በቀላሉ የሚገዛቸው አጀንዳዎች ሆነዋል”።
ውጭ አገር ያሉ የትግራይ ተወላጆች የሚደነቅ ስራ በመስራት “የስልክ መገናኛ ባልነበረን ወቅት” ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ፤ዓለም ቀልቧ ወደ ትግራይ እንድታደርግ አድርገዋል። ትግራይ “በዓለም ማፕ/ካርታ/” እንድትታይ አድርገዋል።
ሁለተኛው መደረግ ያለበት ነገር- “ስለ ጀነሳይድ (ዘርን ማጥፋት)” በሚመለከት ነው። ትልቅ ወንጀል ስለሆነ “ቱርኮች በአርመኖች ዘር የማጥፋት ወንጀል ስለሚወቀሱ እኛ ቱርኮችን ያንን ስናስታውሳቸው እነሱ የሚወቀሱበት ስለሆነ ቱርኮቹን ያሳስባቸዋል። እያሰቡበት ነው። በቱርኮች ኤምባሲዎች ሰለማዊ ሰልፍ ሲደረግባቸው ፤ ”ይሰጋሉ”፤ አልወደዱትም እና “እባካችሁ በኤምባሲዎቻችን የምታደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ እባካችሁ ተውት” እያሉ ይጠይቁናል። ቱርኮቹ ከአዲስ አባባም ወጥተዋል።
ሌላው ደግሞ ‘’ጠላት መቀነስና ወዳጅ ማብዛት አለብን’። ፑቲን ጋር የሚያጣላን ነገር የለም። ገንዘብ ይዘን መሳሪያ ሽጥልን ብንለው ዛሬ ይሰጠናል። ገንዘብ አስካገኘ ድረስ ጉዳዩ አይደለም። ለምሳሌ አብይ ገንዘብ ስላለቀበት ሩሲያኖችን ወደ 90 የሚሆኑ ታንኮች በብድር እንዲሰጡት ሲጠይቃቸው “ባዶ ኪስህ” ስለሆንክ ‘ዞር በል’ አንሰጥህም ብለውታል። እያለ ተሰብሳቢውን አስቋቸዋል።
ወዳጅ እያበዛን በመሄዳችን ቱርኮችን ማሰሪያዎቻችሁን አቁሙ ስንላቸው “ካሁን በፊት የሰጠነው “በዋለበት ውለዋል” ካሁን ወዲያ ግን አብይ ‘ቅጥረኛ ከሃዲ’ መሆኑን ስለምናወቅ አንሰጠውም ብለውናል። እነውነታቸው ነው ወይስ አይደሉም; አናውቅም።”
አገራዊ ምስረታ በሚመለከት፡ እንዲህ ይላል፦
ትግራይ የቀራት አማራጭ ፡አገር መመስረት ነው። ያሉ አማራጮች እኔ እራሴ ሳስባቸው ሁለት ነገሮች አሉ “ፌደረሽን እና ኮን ፌደረሽን”። እነዚህ ኢትዮጵያ ጋር ሊያስኖሩን አይችሉም፤፡ ፌደረሽን የሚባለው የለም (ያለቀ ነገር ነው)። ኮንፌደረሽን ደግሞ ፡ጠላት ከምንላት ኢትዮጵያ ጋር ኮንፌደረሽን መመስረት አይቻልም። ምክንየታዩም ኮንፌደረሽን ስትመሰርት የጋርደዮሽ አንድነት መስርተህ “የጋራ ጠላት” ሲኖርህ የምታነጣጥረው ጥምረት ነው። የኛ ጣለት ኢትዮጵያ ስለሆነች “ጠላታችን” ከምንላት አገር ኢትዮጵያ “የጋርዮች ኮንፌደረሽን” መመስረት የማይቻል ነው።”
ማድረግ ያለብን “ሌት ኣስ አስዩም” ትግራይ አገር መሆን አለባት ብለን ለዚህ ስኬት ለማሳካት በጋራ እንነሳ። አገር ለመሆን የነጠረ አቋም ይዘን ካልተጓዝን የተቀረው “ቅራቁንቦ ፖለቲካ ነው”። ‘ሶማሊ ላንድ’ ደጋግሜ ሄጃለሁ። በአውሮፓ ‘እስታንዳርድ’ (መለኪያ) በጣም ዲሞክራቲክ ነው። የክላን (የጎሳ) ፖለቲካ አጥፍተውታል። ትግራይ ይህ ሁሉ የደም መስዋዕት ከፍላ እንደ ሶማሊ ላንድ “ዲፋክቶ እስቴት” (እንጥልጥል አገር) ለመሆን ከሆነ ስህተት ነው።
በየአገሩ እና አምባሲዎች በመሄድ ትግራይ ከሶማሊ ላንድ የተለየችና የተሻለች አገር እንደምትሆን የአፍሪካ ቀንድን በማረጋጋት ከፍተኛ እና ዋነኛው ሚና መጫወት የምትችል አገር መሆንዋን ማሳመን አለብን። ዓለምን ማሳመን አለብን። ‘ህ .ወ. ሓ .ት’ ይህንን በመምራት ሚና መጫወት ካልቻለች የራስዋ ጉዳይ፤ ግን ይህ ግብ ግን ትመራዋለች ብለን እናምናለን። አሁን የወያኔ ጉዳይ አይደለም የትግራይ ሕዝብ ጉዳይ ነው።የዚህ ሕዝብ “አስፒረሽን” ፍላጎት በድርጅት የሚገታ አይደለም። ዋናው የትግራይ ታላቅነት በመፈክር ሳይሆን በልጆችዋ ታላቅነት ነው መመስረት ያለበት። እውነት ሳይንስ በመፍጠር ላይ የተመሰረተ ታላቅነት ማለት ነው።
ካለ በሗላ “ህወሓት” ስለ አገራዊ ምስረታ “ኮምፐሮማይዝ” (አሳልፎ የሚሞዳሞድ) ከሆነ ሁላችሁ መቃወምና ይህንን መሞዳሞዱን እንዲያቀም ማድረግ አለባችሁ”; በማለት ወያኔ ስለ ትግራይ አገር ምስረታ መሃል ላይ የቆመ በማስመሰል የቅጥፈት ፖለቲካ ሲሰራ ይደመጣል። አገር ምስረታ እየሄዱበት ያለው ዋነኛ መንገድ በ27 አመት ውስጥ እና በቅርቡም የተሳተፉበት“ብዙ የዘር ማጥፋት እና ብዙ ወንጀሎች” በኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ በመፈጸማቸው “መሸሸጊያ” ይፈልጋሉ። መሸሸጊያቸው ድግሞ አሁን እየሄዱበት ያለው ርቀት ነው።
አሁን ጥያቄው ግልጽ ነው። አብይ አሕመድ የመሰለ ቅጥረኛ ባይኖረን ኖሮ እና አገራዊ መሪ ቢኖረን ኖሮ “አሁን ዳቦ ላኩልኝ ባንክ እና ስልክ ክፈቱልኝ” እያለ በሌላ በኩል አገር እገነጥላለሁ “ኢትዮጵያ ጠላቴ ናት አፈርሳታለሁ” የሚል የትግሬዎች ግልጽ አዋጅ ሲነገረን “አንዱን ምረጥ” የሚል መሪ አንሰማ ነበርን።
አሁን ግን ዳቦ ስጠኝ እና፤ በኢትዮጵያ ገንዘብ፤ በኢትዮጵያ ቴሌፎን እና አየር መንገድ እየተጠቀምኩ “አገርህን አፍርሼ ሚሰትህንን ልጅህን ዘርፌ፤ ቴ/ቪዥን እና ንብረትህን ተሸክሜ “ለአገረ ትግራይ ምስረታ እገሰግሳለሁ” የሚል የወንጀለኞች ሰብስብ “የትግራይ ሕዝብ ከነዚህ ጋር መደመር ወይስ እነሱን ማባረር” የሚል ጥያቄ ይቅረብለትና ምርጫው ካሳወቀ እልባት ይኖረዋል። ካልሆነ ግን ፋሺሰት ጉራ ትኩሳት የሚያበርድ መሪ መፈለግ የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው።
የዚህ ሁሉ ጠንቅ አብይ አሕመድ
ነው። ችግሩን ለማስወገድ ከወደ አማራ ያለው ፋኖ እራሱን በማደራጀት
አዲስ ንቅናቄ በመፍጠር የአካባቢውን ተባባሪ መሪዎችን በማስወገድ የሽምቅ ውግያ በመክፈት ስፋት እንዲኖሮው በማድረግ “ከወያኔና
ነብሰ በላው ኦነግ እኩል ወይንም በላቀ ጉልበት ተገዳዳሪ ሃይል” በመሆን “አብይ አሕመድ ከሥልጣን እንዲወርድ በማስጨነቅ፤ ወታደሮችን
በማሳመን ይዘው “በፍርድ ሂደት እንዲረሸኑት” ካልረተደረገ “ትግሬዎች
ከሚልከሰከሱበት ከውጭ ጠላቶች ተሻርከው አገር/የተዋለደን ሕዝብ/
ብጥብጥ አስገብተው የማፍረስ ፍላጎታቸው ሊቆም ከቶ አይችልም። በዚህ ኢትዮጵያዊ ብሂል ልሰናበታችሁ “ሊገድልህ የመጣን ጠላት ቢለምኑት
አይመለስም”።
ጽሑፉ የታሪክ ሰነድ ስለሆነ
አስተላልፉት!
ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ)
No comments:
Post a Comment