Wednesday, July 14, 2021

ይድረስ ደብዳቤዬ ለባሕርዳር ከተማ ባለሥልጣኖች እና ፖሊስ ኮሚሽነር ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/14/2021 ወንድሜን ስላሰራችሁት ጉዳይ

 

ይድረስ ደብዳቤዬ ለባሕርዳር ከተማ ባለሥልጣኖች እና ፖሊስ ኮሚሽነር

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

7/14/2021

ወንድሜን ስላሰራችሁት ጉዳይ

ታናሽ ወንድሜ ባሕርዳር ከተማ ውስጥ በሰላምና በፍርሓት ከሚኖርበት መኖርያ ቤቱ ትናንት ማታ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት አፍናችሁ ሁለተኛ ፓሊስ ጣቢያ አስራችሁታል። ከማንኛችሁ በላይ ወንድሜን አውቀዋለሁ። ትግሬ በመሆኑ ብቻ አስራችሁ እያሰቃያችሁት ነው።

 ቤተሰቦቼ ደውለው እንደነገሩኝ ወደ ሌላ ማጎርያ ሥፍራ እንዳይወስዱት ሰግተናል እና የምውቃቸው ባለሥልጣኖች ካሉ አነጋግርልን ስላሉኝ፡ እኔ እናንተን የማወቅበት መንገድ የለኝም። እናንተን የማውቀው እኔ ወያኔን ስታገ እናንተ ግን ወያኔን ስታገለግሉ እና አማራን ስታሰቃዩ በሞኖራችሁ ተቃዋሚያችሁ መሆኔን ነው የማውቀው።

ወንድሜን ስላፈናችሁት፤ በንዴት ወደ ወያኔ ካምፕ እንደማልገባ ግን ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። ከወራት በፊት ትግራይ ውስጥ በተደረገው ጦርነት የታላቅ እህቴን ልጅ በአይሮፕላን ተደብድሞ ሲሞት “አቋሜን ለውጨ” ብንዴት ሌሎቹ እንዳደረጉት ወደ ወያኔ ካምፕ አልተቀላቀልኩም።  ስለዚህም ምንም የሌለበትን ወንድሜን አሁኑኑ ፍቱት!!!

የማውቃቸው ሰዎች በመደወል ባለሥልጣናቱን እንድያነጋግሩልኝ በመጠየቅ ላይ ነኝ። ተከታዮቼም ትብብራችሁ እጠይቃለሁ።

የአማራ ክልል ባለሥልጣናት እና የደህንንት ሰራተኞች ን ትግሬዎች ወደ ወያኔ ካምፕ እንዲገቡ የምታደርጉት ግፊት አሁኑኑ አቁሙት!! የዘር አፈናው ለናንተም ለኛም አይጠቅምም። የጎስታፖ ሥራችሁን አቁሙ!! የጠላትን ጎራ እንዲጠናከር አታድርጉ!! ባለሥልጣኖችን የምታውቁ ሰዎች ካላችሁ እርደታችሁን እንጠይቃለን። ጌታቸው ረዳ በታገለላት አገር ቤተሰቦቼን ማሰር አንጀቴን ተፈታትኖታል። ግን በናንተ ዘረኝነት እኔ ወደ ወያኔ ካምፕ አልሄድም። መልእክቴ እንዲዳረስ እባካችሁን “ሼር” በማድረግ ተባበሩን።

ድል ለኢትዮጵያ

ጌታቸው ረዳ (የኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ ዋና አዘጋጅ። Ethiopian Semay  


Tuesday, July 13, 2021

የተደማሪ አምበጣዎች መሪ አብይ አሕመድ ከሠልጣን ይውረድ! ለሰላማዊ አመጽ የጥሪ ድምፅ!! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/13/2021

 

የተደማሪ አምበጣዎች መሪ አብይ አሕመድ ከሠልጣን ይውረድ!

ለሰላማዊ አመጽ የጥሪ ድምፅ!!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

7/13/2021



መግቢያ፡

በነዚህ ሁለት ነጥቦቸ ልጀምር።

ያልታጠቀ ሚሊዮን ሕዝብ ለጠላት እንዲጋለጥ አብይ አሕመድ ተዋጊ ሰራዊት ወደ ሗላ እንዲያፈገፍግ አድርጓል። ስለዚህም ትሪዝን (ክሕደት) ተፈጽሟል።

የአማራ ክልል ሥራ አስፈጻሚ ተብየው “የኦሮሙማዎቹ ባርያ” ከሰጠው ወቅታዊ መግለጫ ውስጥ አንድም የረባ ነጥብ አላስቀመጠም። ሠራዊቱ ለምን ከኮረም እና አላማጣ እንዲያፈገፍግ እንደተነገረው ለጌቶቹ የጠየቀበት ነጥብ አላስቀመጠም። ለምን? ባለመጠየቁ የሴራው ተባባሪ ነው።

8 ወር ሙሉ ጦርነት ሲካሄድ አብይ አሕመድ የትግራይ ገበሬ እርሻው እንዲያርስ በሚል ያ ሁሉ ጀግና ተዋጊ እና አዋጊ ኮለኔሎችን አስማርኮ እና አስገድሎ ሰራዊታችን ከትግራይ እንዲወጣ አደረገ። የተዋጉ አዋጊ መኮንኖች “አብይ እንደከዳቸው አድምጠናል” ። አብይ በሰራው ሴራ ከመቀሌ ሲወጣ ተቃዋሚ ወያኔዎች ታፍነው እንዲጠፉ ተደረገ።፡አሁን ደግሞ የአማራን ማሕበረስብ ለተጨማሪ ጥቃት እንዲጋለጥ ከኮረም፤ ከአላማጣ ጦሩ እንዲወጣ አዝዞ የአካባቢው ኗሪ በትግራይ ታሊባኖች “ጥርስ” እንዲታኘኽ ተደረገ፤ የቀረውም ሸሸ። ኢትዮጵያዊ ፓርላማ ቢኖር ኖሮ አብይ በስቅላት ይፈርደው ነበር።

ተቃዋሚ ተብየው ማፈሪያም፤ ምርጫ የሚባል ቀልድ አትግቡ ስንል አብይን አስመርቀው ለዘላለም አስገዙን። አብን የሚባል “ሚዲዮክር” ድርጅት ሕዝብን ለአመጽ ማስነሳት አልቻለም። ድሮም አሁንም!! አማራ የነ ደመቀ መኮንን 30 አመት መጫወቻ ሆነ። አሁን መደረግ ያለበት “አማራ ማሕበረሰብ ሞት የማይቀርለት ዕጣ ከሆነ” እራሱን ከሞት ለማዳን የነ ደመቀ መኮንን መንግሥት አልገዛም ብሎ አመጽ ማንሳት ቀዳሚና አንገብጋቢው አጀንዳ መሆን አለበት። ምክራችንን ስሙ! ኢሕዴን እስካለ ድረስ የአብይ ኦሮሙማዎቹ እና የትግራይ ታሊባኖች አማራውን ከማጥፋት አይቦዝኑም።

ሞት ተበይኖብሃል ስለዚህ ለሰላማዊ አመጽ አሁኑኑ ተነስ!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ


Monday, July 12, 2021

የትግራይ ታሊባኖች ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay 7/12/2021

የትግራይ ታሊባኖች

ጌታቸው ረዳ

ኢትዮ ሰማይ

Ethiopian Semay

7/12/2021

አፍጋኒስታን እና ትግራይ ሁለቱም ተመሳሳይነት አላቸው። አፍጋኒስታን በሃይማኖት አክራሪዎች ሰበብ ትግራይም በአክራሪ የነገድ ፖለቲካ አራማጆች ምክንያት ሁለቱ በጨካኝ ገጸ ባሕሪያቸው የታወቁ ሆነው በታሪክ ተዘግበዋል።

የአፍጋን ታሊባኖች በተቃዋሚ አፍጋኖች ላይ እንደፈጸሙት ሁሉ፤ በወያነ ትግራይ የተመራው የነገድ ፖለቲካም በተመሳሳይ መልኩ “ታዋቂ ገዳዮችን” በማፍራት እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ስቃዮች ፣ ጭፍጨፋዎች በጠቅላላ በእግዚኣብሔር ፍጡር ላይ ለማመን በሚያስቸግር የወንጀል ድርጊት በንፁሃን ኢትዮጵያዊያን አማራዎች እና ተቃዋሚ ትግሬዎች ላይ ፈጽመዋል፡፡

ትግራይ ውስጥ በ1967 ዓ.ም ደደቢት በተባለው የትግራይ ቆላማ በረሃ የተመሰረተው ተ.ሓ.ህ.ት. በሗላ ህ.ወ.ሓ.ት. የተባለ “በወርቃማ ዘር” ራሱን በማሞካሸት የተመሰረተ አክራሪ ድረጅት ከአፍጋን ታለባኖች የሚለይበት ባህሪ በጭካኔ አንድ ሲሆኑ ልዩነታቸው ታሊባኖች khimar ብለው የሚጠሩት የሻሽ ጨርቅ “ጭንቅላታቸው ላይ” ሲጠመጥሙት የትግራይ ወያኔዎች ደግሞ “ኩሹኽ” የሚባለው ስስ ጨርቅ በአንገታቸው ዙርያ በመጠምጠም ይለያሉ።

በነጮች አለም ውስጥ በነሱ ስነ ምግባር ያልተከተለ የነጭ ዘር “ዋይት ትራሽ” (የነጭ ጉድፍ) ብለው እንደሚጠሩዋቸው ሁሉ ታሊባኖችም “የጎደፈ እስላም” ብለው በሚሰይምዋቸው ተቃዋሚዎቻቸው ላይ “Hashshashin (ሓሻሺን) ብለው የሚጠርዋቸውን ነብሰገዳዮች በማሰማራት ግድያ ሲፈጽሙ የትግራይ ታሊባኖች ድግሞ “ሸዋውያን ተጋሩ” ብለው በሚሰይሙን የትግራይ ተወላጆች ላይ “ክርቢት” ወይንም “ፈዳይ” የሚባሉ ነብሰገዳዮች በማሰማራት “ንፁህ ትግራዋይ” ያልሆነውን የትግራይ ተወላጅ ለመማረክና ለመያዝ አስቸገሪ የሆነባቸውን ተቃዋሚያቸውን በመግደል፤ በህይወት የማረኩትንም አካላቱን በሰላ ቢላዋ ቆራርጠው ለጅብ ይጥሉታል።

በታሊባን ድርጅት ውስጥ በ 1990 ዎቹ ውስጥ “ሙላሕ ዳዱላህ” እና “ፒር አግሓን” የተባሉ የታሊባን ገራፊዎች እና የነብሰገዳይ እዝ አባሎች እጅግ ጨካኞች እንደሆኑ ሁሉ የወያኔ ገራፊዎች እና ነብሰገዳዮች ሰውን በእሳት እየለበለቡ ሲመረምሩ እና ሰውን ከአንገቱ በታች አመድ አልብሰው ‘አንገቱ ብቻ’ ከመሬት በላይ እንዲቀር ተደርጎ ሲጨነቅ ማየት ‘እርካታ የሚሰጣቸው’ የወያኔ በርካታ ገራፊዎች በሰለባዎቻቸው አንደበት በሚከተለው አገላለጽ ይገልጽዋቸዋል፡

 “ከላይ የሰው ቆዳ የለበሱ ከውስጥ አደገኛ የአራዊት ነብሳት የሚነድዋቸው አሰፈሪ ፍጡራን ናቸው” ብለው ይገለጽዋቸዋል።

የዘመናቱን ጭካኔና ወንጀላቸውን ብንተው ባለፉት ጥቂት ወራቶች ብቻ ብንመለከት ወያኔዎች የታሊባንን ጭካኔ የሚያስንቅ ወንጀል ፈጽመዋል። ሴቶችን ከመድፈር ጀምሮ ግድያ እና መንግሥታዊ ንብረትን በመዝረፍ፤ ከፍ ብሎም የአገራችንን የመከላከያ ተዋጊ ሰራዊት በተኙበት ከብበው 75% የሰው ሃይል እና ንብረት እንዳልነበረ አድርገዋል (ለዚህም ይመስላል የኤርትራ ድጋፍ ያስፈለገው) ። ከዚህ ባሻገር አማራ ላይ በማይካድራ እና በመሳሰሉት አካባቢዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል።

የባለፈው ወር የፈጸሙት አሰቃቂ ወንጀል ዜናው ሰምታችሁት ይሆናል። ትውልድ መንደሩ ከመቀሌ ትንሽ ወጣ ብላ ከምትገኘው “ዓዲ ጉዶም” ከምትባል ትንሽ መንደር የተወለደው  እምብዛ የተባለ በበይነ መረብ እውቀት የተመረቀ መሃንዲስ እና የሙዚቃ ባለሞያ፤ ትግራይ ውስጥ በነበረው ጦርነት ማሕበረሰቡን ለማረጋጋት ሲል በፈቃዱ በኢንቨስትመንት (ማእቶት/ልማት) የበኩሉን ለማገልገል ሲል ከሚኖርበት አዲስ አበባ ልጆቹና ባለቤቱን ጥሎ ወደ ትግራይ በመሄድ ጥቂት ወራት ከሰራ በሗላ፤ የትግራይ ሙዚቀኞች እና ባለሞያዎች ታሊባኖችን ተከትለው ወደ ትግራይ በረሃ ሲገርፉ ምስኪኑ “እንጂኔር እምብዛ” ግን አላማቸው ስላልወደደው፤ መንግሥት (?) ባሰማራለት የግል ሹፌሩ በተጠመደለት ሴራ ምክንያት ሹፌሩ ከወያኔዎች የህቡእ ግምባር አባላቾቻቸው በመመሳጠር ኢንጂነር እምብዛ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ወደ መቀሌ አየር ማረፊያ ጣቢያ በመኪና ሲወስደው የወያኔ ነብሰገዳዮች ተጠልፎ ሰውነቱ በቢላዋ ተወጋግቶ እጆቹ እና አንገቱን ቆራርጠው ለጀብ ጥለውት መሄዳቸውን ዜናውን ከየኔታ ዩቱብ እና የመሳሰሉ የዜና ማሰራጫዎች ተነግሯል።

ሰለሞን የተባለው የኢንጀኔር አምብዛ የቅርብ ጓደኛ ሰሞኑን ‘የኔታ ዩቱብ’ ላይ ከወጣት ጋዜጠኛ መቅደስ ጋር ባደረገው ቆይታ ተጨማሪ መረጃ ሰጥቷል። ከጅብ የተረፈው የተቆራረጠው የእምብዛ ሰውነት ተለቅሞ “ገብርኤል ቤተክርስትያን” ተቀብሮ ነበር። ሆኖም የትግራይ ታሊባኖች አካሉን መቆራረጣቸው ሳያረካቸው ሲቀር የተቀበረው የእምብዛ ቁርጥራጭ “አካላቱ” ከመቃብሩ ቆፍረው እንደገና ለጅብ እንዲሰጥ በማድረጋቸውን የዓድዋው ተወላጅ የሆነው ጓደኛው ወጣት ሰለሞን ፤ በጓደኛው ሬሳ የተፈጸመው የወያኔዎች ወንጀል ‘ቁጭትና ሓዘን’ በተሞላበት ለኢትዮጵያ ሕዝብ በመግለጽ የወያኔ ትግራይ ጭካኔ ምንነት አጋልጧል።

ወያኔዎች ሌላም የጭካኔ ተግባር መፈጸማቸው ወጣት ሰለሞን ነግሮናል። ተምቤን ውስጥ ከመከላከያ አባል ጋር የፍቅር ግንኙነት የነበራት “ሴት አዳሪ” ከባዕድ ወታደር ጋር ግብረስጋ ፈጽመሻል በሚል አንድ እጇን ቆርጠዋታል።

በዛው ሰሞን አቶ ምዑዝ የተባሉ የአጋሜ አውራጃ ተወላጅ የሆኑ የኢድዩ አዋጊ ሆነው ወያኔን ለ17 አመት የተፋለሙ የትግራይ ተወላጅ ሰሞኑ በሌላ የዜና ማእከል ቀርበው ወያኔዎች የፈጸሙባቸው የጭካኔ ተግባር እንዲሁ ገልጸዋል። በእሳቸው ላይ የተፈጸመው የወያኔዎቸ ግፍ “ሆስፒታል ተኝተው እያሉ “ዓይናቸው ላይ በተጠና ሴራ” ዓይነ ብርሃናቸው የሚያጠፋ መርዝ በመውጋት እንዲታወሩ አድርገዋቸዋል። አቶ ምዑዝ በቃለ መጠይቁ ጥቁር መነጽር አድርገው ቃለመጠይቁ ሲናገሩ እጅግ ያሳዝናሉ።

በዚህ ሳያበቃ፤ ወያኔዎች “የገዛ ልጆቻቸውን” በወያኔ ፖለቲካ ካጠመቁዋቸው በሗላ፤ ልጆቹ በወላጅ አባታቸው ላይ በማሴር በወያኔ አፋኝ ነብሰ ገዳይ ቡድኖች ተይዘው እንዲገደሉ ወይንም እንዲታፈኑ ከፍተኛ ክሕደትና ሴራ በልጆቻቸው እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።ወያኔዎች ልጆች ከወላጆቻቸው፤ ቤተሰብ ከቤተሰብ ተራርቀው እንዲገዳደሉ እና እንዲራራቁ በማድረግ የተካነበት ሴረኛ ቡድ ነው።

እዚህ ላይ ይህን ሳደምጥ ሂትለር ለጀርመን ወላጆች የተናገረውን “ልጆቻችሁ የናንተ ቢሆኑም አሁን የኔ ሆነዋል” ሲል ያነበብኩትን አስታወሰኝ።

ብዙዎቻችሁ የትግራይ ማሕበረስብ የወያኔ ጀሌ ነው ስንል በተለይ ብዙዎቻችሁ አማራዎች ስትቃወሙኝ አንዳንዶቻችሁም ስትሰድቡኝ እንደነበር ለታሪክ ያከማችሀዋቸው ሰነዶች ይመሰክራሉ። አሁን የትግራይ ሕዝብ በየትኛው ጎራ እንዳለ ጉልህ ስዕል እንደሰጣችሁ እርግጠኛ ነኝ።

በሚከተለው ጥያቄ ጽሑፌን ላጠቃልል፡

ለዚህ ጥያቄ ወጣት ሰለሞን በጋዜጠኛ መቅደስ ተጠይቆ ነበር፡

እንዲህ የሚል ጥያቄ፤

የትግራይ ሕዝብ ወያኔ በገዛ ፈቃዱ ወይም ደግሞ ለወያኔ ጥሩ አመለካከት አለው ብለህ ታምናለህ?

ሰለሞን፦

ሰው እየተገደለ ምን አገባኝ ብሎ አይቶ እንዳላየ የሚሄድ “ወያኔ በሚወስዳቸወ የጭካኔ እርምጃዎች  የተነሳ ምክንያት፤ የተሸማቀቀ ማሕበረሰብ ተከስቷል።

1) ወያኔ “ካሁን በፊት ታይቶ የማይታወቅ “ዘ-ሞስት ፈሪ ጀኔረሽን” ትውልድ ፈጥሯል”

2) ወያኔ “በታሪካችን አይተነው  የማናውቅ “ዘ-ሞስት ውሸታም” ጀኔረሽን/ትውልድ/ ፈጥሯል”

3)  ወያኔ “ዘ- ሞሰት ጨካኝ ጀኔረሽን እንዲፈጠር አድርጓል”                      

ሲል እውነታውን አስቀምጦታል።

እዚህ ላይ እኔም የማክልበት “ካሁን በፊት በትግራይ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ “የፋሺሰቶች ፖለቲካ” ተከታይ የሆነ “ወደ ሗሊት” ተመልካች ትውልድ ተፈጥሯል።

 በትምክሕት ጉራ የተወጠረ ፤ “በወርቃማ ዘርነት” የሚያምን ኢትዮጵያን እንደ ባዕድ አገር የሚያይ ፤ ጸረ አማራ ትውልድ ተፈጠራል።

ስናጠቃልል ፤ የትግራይ ታሊባኖች ከአፍጋን ታሊባኖች የሚለያቸው ታሊባኖቹ የእስልምና ሃይማኖት አክራሪዎች ሲሆኑ ፤ የወያኔ ትግራይ ታሊባኖች ደግሞ “ከወርቅ የዘር ሐረግ” የተወለድኩ ነኝ የሚል ፤ ማንኛውም የሚቃወመው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ከምድረገጽ በሃይል የሚያጠፋ አሸባሪ የሆነ አክራሪ የነገድ ድርጅት ነው።

እኛ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች ድርሻችን ስንወጣ እናንተም ማሕደሮቻችንን “ሼር” በማድረግ ግዴታችሁን እንድትወጡ እየደጋገምን በመወትወት ላይ ነን።

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

Wednesday, July 7, 2021

“የገባን ላልገባችሁ የማስረዳት ግዴታ አለብን” - የሀገራችንን ከፍታ ጠቋሚ ዋና ዋና ምልክቶች አምባቸው ዓለሙ (ከወልዲያ) 7/7/2021

 

“የገባን ላልገባችሁ የማስረዳት ግዴታ አለብን” - የሀገራችንን ከፍታ ጠቋሚ ዋና ዋና ምልክቶች

አምባቸው ዓለሙ (ከወልዲያ)

7/7/2021

1.     በአዲስ አበባ መስተዳድር ጥናት መሠረት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ምግብ ማግኘት የማይችሉ ዜጎች በአዲስ አበባ ከተማ አሉ፡፡ በሌሎች ከተሞችም ጭምር፡፡

2.    በዚህችው መናገሻ ከተማችን ውስጥ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ በረንዳና ጎዳና ተዳዳሪዎች፣ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዕብዶችና የትም አዳሪ ሰካራሞች፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤት አልባዎች፣ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ሴተኛና ወንደኛ አዳሪዎች፣ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ሌቦችና አጭበርባሪዎች፣ ሹዋሹዋዎችና መታቾች … እየተርመሰመሱ ይገኛሉ፡፡ ይመዝገብልን፡፡

3.    አንድ ሰው በየትኛውም ዲግሪ ተቀጥሮ በሚያገኘው የወር ደመወዝ ብቻ እየተዳደረ ቀዳሚውን ከተከታዩ ወር መግጠም የማይችልባት ብቸኛዋ ሀገር ናት - ኢትዮጵያ፡፡ በስርቆትና በሙስና ወይም በዘመድ አዝማድ ድጎማ ካልተደገፈ በስተቀር በተለይ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ በሚከፈለው ደመወዝ ወሩን ይቅርና ሣምንቱንም መኖር አይችልም፡፡ የጂቡቲና የሃርጌሳዋ ሶማሊያ ሠራተኞች የኢትዮጵያን የዱሮ ንዑስ ከበርቴ የአሁኑን ነጫጭባ ድሃ ሠራተኛ ሊደጉሙት ይችላሉ፡፡ አብዛኛው ዜጋ በሁለት ሽህ ብር ደመወዝ የ50 ሽህ ብር ኑሮ እንዲኖር ይገደዳል፡፡ ለቤት ኪራይ ብቻ እንኳን በማይበቃ ደመወዝ እንዴት ኑር ይባላል? ይህ የወያኔና የልጁ የዶክተር አቢይ አንጻባራቂ ክፍለ ዘመናዊ ድል በጉልኅ ቀለም ይመዝገብልን፡፡

4.   ከቀበሌ እስከ ከፍተኛ፣ ከከፍተኛ እስከሚኒስቴር መሥሪያ ቤት፣ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤት እስከባንኮችና አየር መንገድ፣ ከዚያም እስከ መከላከያ፣ ፖሊስና ደኅንነት ከያለበት እየተጠራራ ሥልጣኑንና የጥቅም ቦታዎችን የሚይዘው አክራሪ ኦሮሞና የነሱ ተላላኪ ብቻ ነው፡፡ ቀደም ሲል የቀን ጅቡ የትግሬ መንግሥት እንደዚሁ ከዐድዋና ከሽሬ እየተጠራራ የሀገሪቱን የጥቅምና የሥልጣን ቦታ መቆጣጠሩ የሚታወቅ ነው፡፡ አሁንም ቅኝቱ ስላልተለወጠ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ይህም ድል በወርቅ ቀለም ይመዝገብልን፡፡ አንዱ የከፍታችን ጠቋሚ ነውና፡፡

5.    በእንስት የዛር መንፈስ የሚነዳው ወጣቱ የአውሊያ ፈረስ በውሸታምቱ በዓለም አንደኛ ከመሆን አልፎ ወደፊትም ሆነ ወደኋላ በውሸታምት እርሱን ሊስተካከል የሚችል አንድም የዓለም ዜጋ ሊኖር አለመቻሉ ከከፍታችን ድሎች አንዱ ነው፡፡ ሲዋሽ ደግሞ ሀፍረት የሚባል ነገር ቅንጣት አይሰማውም፡፡ ከመቀሌ ለጥሞና ወጣን ሲል ጦሩን አካፑልኮ ቤይ ለሽርሽር ወስዶ ለማዝናናት አስመሰለው፡፡ አንዳቸው ለገበሬው ስንል፣ ሌላኛቸው ለዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ጫና ስንል፣ አንዳቸው አንድ ነገር ሌላኛቸው ሌላ ነገር እየዘባረቁ ውሸታቸው ለከት ያጣ መሆኑን ለዓለም ገለጹ፡፡ ካለበት የተጋባበት ነው፤ መምህራቸውና ፈጣሪያቸው ወያኔም ቆርጦ በመቀጠል የሚስተካከለው አልነበረም - የአሁኑን አያድርገውና፤ አሁንማ አቢይ አስከንድቷቸዋል፡፡

6.   መቶ ሽህ ብር የሚፈጅ አነስተኛ ፕሮጀክት በአምስትና አሥር ሚሊዮን ብር ይሠራና የአንበሣ ድርሻው የፕሮጀክቱ ገንዘብ ለባለሥልጣናት ይከፋፈላል፡፡ የተሠራው ሥራ እንደነገሩ ከመሆኑ የተነሣ ገና ከመመረቁ ወይም በተመረቀ ማግሥት ድራሹ ይጠፋል፡፡ እንዲያውም በአካል የሌለና ፍጹም የማይታይ ፕሮጀክት እንደተሠራ ተቆጥሮ ገንዘቡ እንደሚመዘበር ይሰማል፡፡ የትም ቢሮ ሄደህ ካለገንዘብ ጉዳይ ማስፈጸም ህልምና ቅዠት ነው፡፡ ገንዘብ እየተመለከ ነው፡፡ የግል ህክምናው ሌብነትና የለዬለት ዝርፊያ ነው - ለአልጋ የሚያስፍሉት ከሸራተን ዕጥፍ ነው፡፡ የትም ሂድ ገንዘብ ካልዘራህ ምንም ነገር አይሳካልህም፡፡ ቢሮክራሲው ሁሉ የሚከፈትልህ በብዙ ብር ነው፡፡ ዘረኝቱና ሙስናው ተባብረው ሊያጠፉን የቀራቸው አንድ ሐሙስ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በሙስናና ንቅዘት በዓለም አንደኛ መሆናችን የከፍታችን ስኬት አንዱ ማሳያ ነውና ይመዝገብልን፡፡

7.    ትምህርት፡፡ ትምህርቱ “ወደቀ”” የሚለው ቃል አይገልጸውም፡፡ የአብዛኛው ዜጋ ጥረት ወረቀት ለመያዝ እንጂ ዕውቀት ለመገብየት አይደለም፡፡ ውድድሩና ሩጫው ሁሉ ያበላል በሚባል አንድ ወይም ከአንድ በላይ የትምህርት መስክ እቤት ተቀምጦ በግዢና በለብ ለብ ልክ እንደመንጃ ፍቃድ ዲግሪን  ማግበስበስ የተለመደ ሆኗል፡፡ ዶክተር ሆኖ ስሙን በየትኛውም ቋንቋ አስተካክሎ የማይጽፍ የተማረ ደንቆሮ የሚገኝባት ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ናትና ይህም በከፍታችን ጠቋሚነት ይመዝገብልን፡፡ ለዚህም ነው እኮ “the ruling party” ወይም “the incumbent government” ለማለት “the buying government” የሚል ዶክተር የዩኒቨርስቲ መምህር፣ “unequivocally” ለማለት “equivocally” እና “by implication” ለማለት “by implies” የሚሉ ጠ/ሚኒስትሮች ልናይ የተገደድነው፡፡ ያልዘራነውን ከየት እናገኛለን ዱሮውንስ? ጉዳችን ፈልቶ! ብቻ ይህም ይመዝገብልንና ለታሪክ ይቆይልን፡፡ ማን ያውቃል - ነገ ሌላ ቀን ሊሆን ይችላል፡፡

8.   ትምህርቱ እስካጥንታችን ዘልቆ ብዙ ዐዋቂና አስተዋይ እንድንሆን ከማድረጉ የተነሣ እነዶክተር አቢይና ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ያዘጋጇቸው ኦነግ ሸኔዎች የነፍሰ ጡርን ሆድ በመዘርገፍ የሚያወጡትን የአማራ ሕጻን በሟች እናት ፊት መብላት የደረሱት፣ አማራን በተገኘበት ለማረድ የማይመለሱት፣ የአማራን ሀብትና ንብረት እየወረሱ የሚወስዱት ወይም የሚያቃጥሉት ሁሉ ለደረስንበት የከፍታ ማማ ጠቋሚ ነውና ይመዝብልን፡፡ ሰው ወደዐውሬነት መለወጡ ከፍታ ነዋ፡፡

9.   በየትም ሀገር የሌለ በኛ ሀገር ብቻ የሚገኝ የዘር ፖለቲካ አንዱን ጎሣ የበላይ አንዱን የበታች እያደረገ የበታቹን ለግድያ የበላዩን ለሥልጣንና ለጥቅም የሚያበቃ በመሆኑ ከፍታችን ከዓለም ወደር አይገኝለትም፡፡ በጎሣና በሃይማኖት የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመሠረት የሚፈቅድ ህገ መንግሥት ያለን ብቸኛዎቹ የኅዋ ውስጥ ፍጡራን በመሆናችን አጋንንተ ዓለም ጥልሚያኮስ ምሥጋና ይድረሰውና ይህም ይመዝገብልን፡፡

10.  ክልሎች ሁሉ ሌላ የልማትና የዕድገት ሥራቸውን እርግፍ አድርገው ትተው ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ በማሰልጠንና ከጎረቤቶቻቸው ጋር ወደማያባራ ጦርነት ውስጥ መግባታቸው ርሀብንና በሽታን፣ ኋላ ቀርነትንና ዕርዝታን በቅጽበት የሚያጠፋ ታላቅ ትልም በመሆኑ በዚህም የከፍታችን ታላቅነት ሊታወቅልን ይገባልና ይመዝገብልን፡፡ አፋር ልዩ ኃይል፤ ትግራይ ልዩ ኃይል፤ ኦሮሞ ልዩ ኃይል፣ አማራ ልዩ ኃይል፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ልዩ ኃይል፤ ሶማሌ ልዩ ኃይል፣ ሲዳማ ልዩ ኃይል፣ ደቡብ ልዩ ኃይል፤ ቅምብቢት ሚሊሻ፣ ዶሮ ግብርና ጎብዬ ሚሊሻ፣ ቱሉቦሎ ሚሊሻ፣ ደምቢዶሎ ሚሊሻ ….. ደስ ሲል! ከዚህ በላይ ከፍታ የት ይገኛል ታዳ?

11.    አሁን ዕድሜ ለጫጩ የዚህና የዚያ ወገን አእምሮዎች ‹ትግራይ›ና ኢትዮጵያ የሚባሉ ሀገራት ተፈጥረዋል፡፡ ዕድሜ ለኢሱ፡፡ የኢሱ ጦር በአቢይ ይሁንታ ትግራይን የዶግ ዐመድ አደረገ፡፡ ትግራይ ከሞላ ጎደል ጠፋች፡፡ አሁን ግን በእልህና በፖለቲካ ሤራ ምክንያት አንሰራራች፤ እውነትም እልህ ጩቤ ያስውጣል፡፡ ቢሆንም ግን የትም አትደርስም፤ ቋቷ ሞልቷልና፡፡ ጊዜያዊ ጉዳት ማስከተሏ ግና ገና ከጧቱ እየታዬ ነው፡፡ አማራ ካላወቀበት ለተወሰነ ጊዜ ይጎዳል፡፡ የአቢይ አካሄድም ለዚያ ይመስላል፡፡ ዝግጅት ያልተደረገበት ሽሽት መንስኤው ለአማራ እሾህ አሜከላ ለመፍጠር መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ አማራው ራሱን ይጠብቅ፡፡ ተስፋ የቆረጠ ዐውሬ የንጋት ጅብ እንደማለት ነው፡፡ ለማንኛውም ይህም የከፍታችን ምልክት ነውና ይመዝገብ፡፡

12.   ኦሮሚያ በትራክተር ልትታስና በስንዴ ልትጥለቀለቅ፣ አማራና ትግራይ በቦምብ ሊታረሱና በሰው ደም አላባ ሊጥለቀለቁ ዐውድማው ተሰናድቶ አልቋል፡፡ ጅሎች ይገዳደላሉ፤ ብልጦች ዳር ቆመው በማን አባት ገደል ገባ ሞኞችን ያጨራርሳሉ፡፡ ይህ ደግሞ አቻ የማይገኝለት የቅርብ ጊዜ የከፍታችን ምልክት ነው፡፡ ብዙ ማለት በተቻለ፡፡ ግን የሚሆንን ነገር ከመሆን ማስቀረት ላይቻል የሆድን ሁሉ ዘርግፎ መናገሩ ከንቱ ድካም ነው፡፡ አዳኛችን ግን አንድዬ ብቻ መሆኑን እንረዳ፡፡

Saturday, July 3, 2021

ኢትዮጵያ ሠራዊት ወይንስ የአብይ ወታደር? ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) 7/3/2021

 

ኢትዮጵያ ሠራዊት ወይንስ የአብይ ወታደር?

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

7/3/2021

ባለፈው ክፍል 1 ጽሑፌ “አመድ ልሳ እንደተነሳችው እንደ “ፎኒክስዋ ወፍችሁ ‘ዳግም ልደታችሁ” ለማየት በማዕቀብ ፈተና እንዲፈትናችሁ የኢትዮጵያን ሕዝብ እጠይቃለሁ!” የሚል እንደተነጋገርን በክፍል ሁለት እንደሚቀጥል ነበር ያቆምነው። ክፍል 2 በሰፊው በሚቀጥሉት ቀናቶች እንመለከተዋለን ላሁኑ ግን ኢትዮጵያ ሠራዊት ወይንስ የአብይ ወታደር የሚለው እንመለከታለን።

 ለሁላችሁም ግልጽ እንዲሆንላችሁ ‘በወያኔ ቀያሺነት የተመራው የትግራዋይነት የነገድ ፖለቲካና መረን የለቀቀ የነገድ ፍቅር” ጠንካራ ኢትዮጵያዊያን ተብለው ሲሞገሱ የነበሩ እንደ እነ ቴድሮስ ጸጋየ ሳይቀር እጅግ በሚገርም ሁኔታ የኢትዮጵያን ጦር “የአብይ አሕመድ ጦር” እያለ ሲጠራ ወያኔ ጦር የሚያይበት ትንታኔ ግን “የትግራይ መከላከያ ጦር” በሚል ስም “የትግራይ ሕዝብ ጦር” ሲል ያሞካሻቸዋል። በኔ በኩል ወያኔዎች የሚመሩት ጦር የትግራይ ሕዝብ ከሆነም ችግር የለኝም። ምክንያቱም ወያኔ ማለት የትግራይ ሕዝብ ነው። እኔ እና ርዕዮት ሚዲያ ልዩነታችን የኢትዮጵያን ጦር የሚጠራው “የአብይ ወታደር” በሚል በንቀት ሲሆን እኔ ግን ኢትዮጵያ ወታደር ነው እላለሁ። ያውም ቴድሮስ “ወራሪ” ነው የሚለው።

ወራሪ ጦር ማለት “ኮሎናይዘር” ቅኝ ገዢ ማለት ነው። እኔ ልክ እንደ ቴድሮስ ጸጋየ አብይን እቃወማለሁ። ግን አብይ የትግራይን ሕዝብ ሂዱና አጥፉት፤ ዝረፉት ሴቶችን ድፈሩ ብሎ እንደ ናዚ ወታደር ትዕዛዝ አስተላልፎ ሴቶችን አስደፍሯል፤ ለዚህ ደግሞ ትግራይን ስለሚጠላ የሚለው እውነታ ቢኖሮውም። ይበልጥኑ አብይ ከትግሬ ይልቅ አማራን ይጠላል ብትሉኝ እቀበላለሁ። ማስረጃወም ብዙ ብዙ ቢሆንም ፡ “ነፍጠኛ” እያለ እንደ አለቆቹ ወያኔዎች የሚገልጽበት ‘አውድዮ’ አለ። አማራ ጦር እንዳያደራጅ የሰራው ብዙ ነገር አለ። የወሎ ንግግሩን አንዱ ማስረጃ ያዙልኝ። ከዚያም አሳምነውን እንዴት እንዳጠፋው ሌላው የአማራው ጥላቻው ነው። ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል።

አብይ “ዓጋሜ፤ ወይንም “ቅማላም ትግሬ” ሲል ሰምቼው አላውቅም። እንደ ዕድል/ አጋጣሚ/ ለወደፊቱ አብይ ነገ ትግሬ ሴት ቢያገባ “አማቻችን” ብለው እንደ ጎንደሬዎቹ ይመርጡታል።

 ወደ ሗላ ልውሰዳችሁ።መለስ ለኤርትራ የነበረው ፍቅር አብይ ለትግራይ ተመሳሳይ ፍቅር አለው። በጦርነት ግን በጥቃት ምክያት መለስ ከሻዕቢያ ጋር አብይ ከወያኔ ጋር ተጋጭተዋል። አብይ ከመጀመሪያውኑ የወያኔ መሪዎችን ፋታ ሳትሰጥ ይዘህ ለፍርድ አቅርብ ፤ሗላ ሰበብ ያመጣሉ ስንለው ለእነ ስዩም መስፍንን የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትርነትህን ልስጥህ እያለ ሲተሻሽ  “ፍቅሩ ስላልጨረሰ “አክሱም እና መቀሌ” ድረስ እየሄደ ሲሽኮረመምና ሲያሽቀብጥ ፤ሰራዊታችን ለጥቃት አጋልጦ ሰጣቸው።” እውነታው ይህ ነው።

ቴድሮስ ጸጋዬ “ይህንን ምስኪን ሰራዊት “እምሽክ ብሎ ደቅቆ ተዋርዶ እስኪበቃው “መቀጥቀጡ” እጅግ ደስ ብሎኛል! ረክቻለሁ! እፎይታ ነው! ይላል ማይክሮፎኑ እስኪንቀጠቀጥ። የቴድሮስ ጸጋየ ንግግር ካመጥኩ በሗላ፤ ኒው ዮርክ ታይምስ በቪዲዮ የዘገበው ዘገባ ማየት አንጀት ያቃጥላል። ኒው ዮርክ ታይምስ የተባለ የዜና ማሰራጫ በሺዎች የሚቆጠሩ የተማረኩ ወታደሮች ወያኔ መቀሌ ከተማ ፒያሳ ላይ ሻዕቢያ በ1983 አስመራ ከተማ እንዳደረገው በኩታራ ታጣቂ ወያኔዎች ግራና ቀኝ ታጅበው ሕዝቡና ህጻናት ሳይቀሩ እየተገረሙ “እያንጨበጨኑ እያሾፉባቸው” ማየት አንጀት ያቃጥላል። አማራ ወታደሮች እያለ ሻዕቢያ በ1983 ዓ.ም አስመራ ኮምቢሽታቶ ሲያዞራቸው የነበው ወታደሮቻችን ዛሬ በድጋሚ ትግራኤኢ መቀሌ ውስጥ በሚገርም ጣሊያናዊ ትዕይንት በትግሬዎች ተደገመ። (ያው የተረከሉት ሃውልታቸው ሳንረሳ መለቴ ነው)

ይህ ብቻ አይደለም አሳዛኙ ትርኢት።  ቁስለኞች በወታደሮቹ ወሳንሳ /ቃሬዛ/ ተሸክመዋቸው በፕያሳ እንዲዞሩ መደረጉ ጣሊያን ያላደረገው በትግሬዎች መደረጉ የሚገርም ነው። ሙርከኛ ምን አለበት ቤት ወይንም ት/ቤት/ክሊኒክ/ካልተቻለ ጥላ ስር፤ ህንጻ እንዲያርፉ እና ስቃያቸው እንዲችሉ ቢደረግ ምናለበት? ቁስለኛን በቃሬዛ ሕዝብ እንዲያያቸው እና ህጻናት ፒያሳ ላይ እንዲሳለቁባቸው ማድረግ? ለምን? ያውም “ቁስለኛ” ስቃይ ውስጥ ያለን ሰው በቃሬዛ ለትዕይነት? ጣሊያን በየት መጣ ያሰኛል? የሙርከኛ አያያዝ የሚመጻደቅበት ወያኔ ስቃይ ላይ ያለው ቁስለኛ ምን እየሆነ እንዳለ እያየ ይሆን?

 የወያኔ ሰራዊት ትግራይን ተቆጣጥሮ፤ ዘረፋ፤ የሴቶች አመጽ፤ ግድያ… ሳይታይ ፤ ትግራይን በእፎይታ ተኝታለች ወደ እሚል ቅዠት እያንጸባረቀ ያለው ቴዲ በስቃይ የሚያቃስቱ ወታደሮቭ በቃሬዛ መቀሌ ፒያሳ ሲያዞርዋቸው ቢያይ ኖሮ ምን ይል ነበር ይሆን? በጥይት የተመታ ደም እያፈሰሰ ስቃይ ላይ ያለን ሙርከኛ? በስመ አብ!!

የወያኔ ጭካኔ ለከት የለውም። ወያኔ የሰሜን ዕዝ ጦር ወታደሮች ከነ ህጻናት ልጆቻቸው ማርኮ በየበረሃው ሲያንከራትታቸው ነበር ፎቶውንም ስዕለ ድምጹንም ከመነሻው ማስረጃ ለጥፌዋለሁ። ይህን ተመልከቱ ንባቡን ስትጨርሱ።

የመኖር ተስፋን የቀጠለው ህፃን - በሰሜን እዝ

https://youtu.be/vUU8yIyPePo

ትንሽ እየተበሳጨሁ ስለሆነ ቻሉኝ። ወደ ርዕሱ ልመልሳችሁ። ቴድሮስ ይህንን ልጅ ብያይ ምን ይሰማው ይሆን?

አሁን ከዚህ ሁሉ አሳዛኝ ሁኔታ ቴድሮስ እሰየው አረፍን! ብሎ እያለ ያለው፤ ወያኔ ወደ መቀሌ ሲገባ እነዚያ እየታፈኑ ያሉት የአሲምበባ እና አውራጃ ከተሞችና ገጠሮች፤ የግጀት እስላሞች፤  ንብረታቸው የተዘረፈ፤እየተቃጠለ፤ በወያኔ አፋኝ ቡድን እየተገደሉ ያሉ ሰለማዊ ሰዎች፤ ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ታፍነው ያሉ ተማሪዎች፤ ግን ለቴድሮስ የተሰማው እፎይታው ይህ ይመስለኛል። በሚገርም አባባሉ ዛሬ የሰማሁት “ትግራይ ውስጥ እጅግ ሰላማዊ ኑሮ እንዳለ ተነግሮኛል ይላል።

 በሌሎች ጽሑፎቼ እንደገለጽኩት የራሴ የታላቅዋ እህታችን ልጅ “ተምቤን “ወርቅ ኣመባ ውስጥ” በአይሮፕላን/ድሮን መገደሉን ገልጫለሁ። ሌሎቹ ዘመዶቼም በጣም ቆላ በሚባል አስቸጋሪ የጦርነት ቦታዎች ስለሚኖሩ ይሙቱ ይኑሩ አላውቅም። ስለዚህ “የሰላማዊ ትግሬዎች በደል አይሰማህም የሚሉኝ እና እነሱ ብቸኛ ትግሬዎች ሆነው የሚዘላብዱት ርቀት ዛሬም እየገረመኝ ነው።

  አንዳንዳንድ ስድ የወያኔ ባለጌዎች እማ ከነሱ በፊት የተወለድኩባት እትብቴን የተቀበረባት፤ያደግኩባት የወላጆቼ አፈር እና መሬት ገጠርና መንደር እየሄዱ ከራያ ገስግሰው እነ ጌታቸው ረዳ የሚሸሸጉበት አውራጃ እና መንደር የማን መንደር መሆኑን ሳያውቁ “ወያኔን ስለተቃወምኩኝ “አንተ አማራ” ነህ “ትግሬ አይደለህም” እያሉ የነገድ ምስክር ወረቀት ሰጪዎች ሆነው ሳያቸው እስቃለሁ። ስልክ ቢኖረኝ ገጠር ያሉ ዘመዶቼን ደውዬ፤ ወያኔዎች ሸሽተው መጠለያ ሲጠይቅዋችሁና ቁራሽ እንጀራ ሲለምንዋችሁ’ “እናንተ ማን ትባላለችሁ?” ብላችሁ ጠይቁልኝ እላቸው ነበር። የወያኔ ጀሌዎች ድፍረት ይገርመኛል!

ግፍ ተፈጸመ የሚባለው እስኪ ይጣራ። በፕሮፖጋንዳ መንጫጫት ጋብ አድርገን ሰከን እንበል፤፡ ግን ደረሰ የተባለው ግፍ “ለምን?” እንዴት?” ማን?” የሚለው ለወደፊቱ መጣራት ያለበት ነገር ነው። የተገደሉ የትግራይ ንጹሃን ሰዎች የተደፈሩ ሴቶች በሰራዊቱ ከተፈጸመ ወይንም በዱሩየዎች ወይንም በወያኔ ተዋጊዎች “የፈጸሙት ሰዎች” በሕግ መጠየቅ አለባቸው። በዚህ ምንም ልዩነት የለንም። 

ከዚህ ውጭ እንግዲህ ይህ ቀጥቅጦ አዋርዶ አስወጣው እያለ ደስታውን እየገለጸ ያለው ቴድሮስ ጸጋዬ ደስታውን የሚገልጽላቸው የሽምቅ ተዋጊ መሪዎች ግን እነማን ናቸው? ለምንስ የነሱ ሓጢያት ሊገልጸው አልቻለም? የሚል ነው እኔ የምጠይቀው። እስካሁን ድረስ ለ7 ወር ያህል ፕሮግራሙ የወያኔን ወንጀል ገሸሽ እያለ የአብይ ጦር የሚለውን ወታደር ጉንጩ እስኪደክም ድረስ በየቀኑ የሚቀጠቅጠው ወታደሩን  ብቻ ነው። ስድቡ በኩንታል ነው። ለምን?

አሁን በዳቦ ስም እየተጠሩ እየተሞካሹ ያሉት መሪዎቹ ቴድሮስም ሆነ እኛ የምናውቃቸው “የሰሜን ታሊባኖቹ” በወንጀል የተጨማለቁ ፤ የወያኔ መሪዎች ናቸው ወይስ ሌሎች ፍጡራን? አደለም እንዴ? የነሱ ወንጀል እንዴት እንዳልፈጸሙ እንዴት በዝምታ ይታለፋል? የአገር መከላከያ የሚያክል ሚሳይሎች ሁሉ ሲነጥቁና እንቅልፍ ተኝተው “በግሪደርና በጭነት መኪና” በላያቸው ላይ የተካሄደባቸው የአገሪቷ ምስኪን ወታደሮች ማን ነው የፈጸመባቸው? የትግራይ መከላከያ ጦር ተብሎ በማሞካሸት የተጠራው “የወያኔ ጦር” ነው ወይስ የማናውቀው ጦር አለ?

 የ 6 አመት ህጻን ልጅ የያዘ ወታደር አስገድደው ከነ ልጁ ወደ በረሃ ማርከው ሲያሰቃዩት አላየንም? ማን ነው ይህንን ጭካኔ የፈጸመው? ወያኔ ወይስ ““ሰራዊት ምልክኻል ትግራይ”? ለመሆኑ ይህ ስም በማን ዕዝ የሚታዘዝ ጦር ነው? ንገረን እሰኪ? በወያኔ ነው። አደለም እንዴ?

ይህ ጦር ለትገራይ ምን ግፍ እንደ ሰራ እንዴት ተዘነጋ? አምበጣ ሲከላከል እና ከደሞዙ ቀንጭቦ ትምህርትና ሕክምና ሲገነባላቸው፤ እርሻ ሲኮተኩትን የትግራይ ገበሬን ሲያግዝ “የአብይ ወታደር” ተብሎ ሲጠራ ነበር ወይስ “የኢትዮጵያ ጦር”? የነ አስመላሽ ዘሞ (አባዲ ዘሞ) እግር ሲያጥብ’ ውሃ ሲያጣቸው አላየንም? እንዴት ነው ነገሩ። ደጉን በደግነቱ ወንጀለኛንም ለይተን በወንጀሉ እንናገር እንጂ? በሓሽሽ ጭስ ሱስ ጦዞ “ከንፈሩ” የደረቀ ውሃ የጠማው የወያኔ ታጣቂ ወጣት “ተዋጊ” ውሃ ሲያጠጡት አላየንም?  አብይ ለጦር መሪነት ብቁ እንዳልሆነ እናውቃለን፤ ጦሩ ግን ለምን የግለ ሰብ ጦር ተብሎ ይጠራል?

ዛሬ ግን  የቴድሮስ ጸጋዬ “ሠራዊት ምክልኻል ትግራይ” ቁስለኛ እና ሬሳ ሲያዞሩ ጣሊያን የማረኩ ይመስል፡ ወታደሮችን ለትርዒት መቀሌ ከተማ ላይ አንደከብት እየነዱ ሲኩራሩ እያሳዩ ጥላቻን ሲያጎለብቱ አይተናል ።  ጊዜ እንጂ ሰው አሸናፊ እንዳልሆነ ዛሬም አልተማሩም (ፋሺሰት በአሸናፊነትና ተሸናፊነት ስለሚያምንወ መማር አያወቅም)። አሁን በቃ! የት እንደምትሄዱ አይተናል። እኔ ከ45 በፊት አካሄዳችሁ አውቃዋለሁ፤ ሌሎቹ ኣላወቁዋችሁም። ለዚህ ነው እየተጃጃሉ እስከዚህ ድረስ የፈረሱት!

ለመሆኑ አብይ ወታደር የምትላቸው ‘ነገ አብይ ከሥልጣን ሲሰናበት’ ወደቤቱ ይዟቸው ይሄዳል ወይስ የቴድሮስ ጸጋየ “ታሊባን መሳዮቹ የወያነ ታጁሮች የሚገዙት ሊሆን ነው? እየተስተዋለ እንጂ!! ትግሬ የሚኖሮው ለማንም አይደለም ለኢትዮጵያ ሲልም አይደለም” ለራሱ ሲል ነው። ይሻለኛል ካለ ይሂድ፤ ግን ልክ እንደ ኤርትራኖቹ ትግራይ ለግላችን ኢትዮጵያ የግላችን የሚለው የ27 ኢትዮጵያን ጡት እየጠቡ እየመጠጡ ሊፈቀድ አይቻልም።በቃ! በጣም፤በጣም በዛ!! ወያኔ ኢትዮጵያዊ ሆኖም ፤ ኖሮም ፤አድርጎትም፤ አያውቅም። ስለዚህ ማስፈራራታችሁ ይቁም! ማንም ለማንም ጥቅም ሲል አይደለም አብሮነት የመረጠው፤ ለራሱ ሲል ነው!

አንተ ቴድሮስ ጸጋየ የተናገርከው አነጋገር የሰማሁህ ግን የሚገርም ነው። “ትግራይ ብትገነጠል፤ መስጊዱ ክርሰትናው፤ ሃይማኖቱ ሁሉ አብሮ ወደ ትግራይ እንደሚሄድ እና አገራችን ያለ ትግሬ ሃይማኖት አልባ እና ታሪክ አልባና ፤ቅርስ አልባ” ሆና እንደምትቀር የምትደሰኩረው “ትዕቢት” ማዕቀብ ያስፈልገዋል። ትግሬ እንደማንኛውም አስተዋጽኦ አድርጓል፡ አክሱም የትግሬ ብቻ ነው ያለህ ማን ነው? በየትኛው ታሪክ? ትግሬ ሲጠቃ ሌሎቹ ስለ ትግሬ ደማቸው ሰጥተው ሞተዋል። እንዴት ነው ይህ ትዕቢት!? ይብቃኝ መሰለኝ፤ እጅግ ተቆጣሁ!

ሼር አድርጉት~!!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ