Wednesday, February 3, 2021

ከራሴ ጥቅሶች አንዱን ላስተዋውቃችሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) (Ethiopian Semay) 2/3/2001

 

ከራሴ ጥቅሶች አንዱን ላስተዋውቃችሁ

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)

(Ethiopian Semay)

2/3/2001

ይህ ጥቅስ የጻፍኩት ውጭ አገር በሚኖሩ ሕብረ ብሔራዊ ነን የሚሉ የፖለቲካ ተቃዋሚ አባሎች እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ በተነሱ ልዩ ልዩ የጎሳ ፖለቲካ አራማጅ የፋሺዝም ተከታዮች ሲደርስብኝ የነበረው ዘለፋ አስገርሞኝ አንድ ሌሊት ሳስበው፤ሳስበው ሕሊናየ ላይ የተደቀነ የራሴ ሙግት ነው።

ይህ ጥቅስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀምኩበት ግንቦት 7 የተባለ አደገኛ ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅት እና ዛሬ አብይ አሕመድ እየተመራበት ያለው መርሃ ግብር ያዘጋጀው (አንዳርጋቸው ጽጌ በነገረን መሰረት) ያኔ አንዳርጋቸው ኤርትራ ውስጥ እያለ ‘‘የቀራንዮው እየሱስን’ ስም የተቸረው የአንዳርጋቸው ጽጌ ገበና ማሕደር፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ታጋዮች ጉዳይ!’’ ክፍል -2- በሚል በጻፍኩት ርዕስ የጠቀስኩት የራሴ ጥቅስ ነበር።

እንዲህም ብየ ነበር

<< በአንድ ጠረጴዛዬ ላይ ቁጭ ብየ ሳስብ አማካሪዬ እና ተሟጋቼ የሆነው ሕሊናዬ አንዲህ አለኝ፦

“እኔ እና አንተ የምናርስበት የእርሻ ቦታ ታሪክ ይባላል።በእርሻው ላይ ጊንጦች፤ እባቦች እና አመኬላዎች ይጋሩናል። ምርታችን “ፍትሕ ነው” ። ፍትሕን አንዘራለን፤አንኮተኩታለን፤እናሳድጋለን። አጭደን ከምረን ፈጭተን የምንመገበውም ምግብ ከፍትሕ ሌላ ምግብ አናውቅም ። የሰዎች ልጆች ሁሉ የላቀ ምርት ነውና ፤እየተነደፍንም ሆነ ከሥር እየተወጋን ፍትሕን ከመከላከል የማንቦዝን በታሪክ እርሻ የምንገኝ የፍትሕ ሰብል አምራች ገበሬዎች ነን አለኝ” (ጥቅስ ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)

በወቅቱ ይህ የኔን ጥቅስ የጠቀስኩበት ምከንያት በርዕሱ ክፍል 2 በጻፍኩት የግንቦት 7 (ስለ አንዳርጋቸው) ጉዳይ ስጸፍ እንዲህ በማለት ሰፊውን ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፤

 “ይህ ሐተታ፤ ፍትሕን እየረገጡ፤ስለ ፍትሕ መጮሕ ልማድ ለሆነባቸው አንዳንድ የዲያስፖራ ጸሐፊዎች፤የሕግ ምሁራን፤ ተቃዋሚዎች እና ሚዲያዎቻቸው የዳሰሰ ሐተታ ነው። ባለፈው ሰሞን የሕዝባዊ ሃይል/ግንቦት 7 አባል የነበረው አንተነህ ጌትነት ጋዜጤኞችን "ጠያቂዎች ብቻ መሆናችሁን አታስቡ ተጠያቂዎችም እንደሆናችሁ አትዘንጉ።" በማለት ለአንዳረጋቸው ጽጌ በመወገን ፤ኤርትራ ውስጥ በሕዝባዊ ሃይል ታጋዮች ላይ አንዳርጋቸው ጽጌ የፈጸመባቸው “ሰብአዊ ጥሰት” ለተቃዋሚ ሚዲያዎች እንዲዘግቡት ቢያሳውቁም፤ የአንዳርጋቸውን ገበና ላለማጋለጥ በወገንተኛነት ለግንቦት 7 ወግነው እሮሮአቸውን “አፍነው” ፤ ወገንተኞች በመሆን የተቃዋሚ ሚዲያዎች እና ጸሐፊዎቻቸው ላይ አባሪ ተባባሪነታቸውን በቅሬታ የገለጸበት በእኔ ብሎግ ላይ ከተለጠፈው ካለፈው የተወሰደ ሚዲያዎችን የወጠረ ሓተታ ነበር። ዘሬም ሌላው የአንዳርጋቸው ጽጌ ሰለባ የሆነው ወጣት ሽታው ሽፈራውን እና ኤርትራ ውስጥ ለ10 አመት መሽገው ወያኔነን ለመጣል ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት ግንቦት 7 ስር የተሰለፉ ወገኖቻችን ስለ የሻዕብያ መሰሪ ገበና በአካል የሚያወቁ ሰዎች የሰጡንን መረጃ በጥልቀት አንቃኛለን። በማለት ዝርዝር የጻፍኩበት ጥቅሴ ነበር።

ሰፊውን ላላነበባችሁት ካላችሁ የቀራንዮው እየሱስን ስም የተቸረው የአንዳርጋቸው ጽጌ ገበና ማሕደር፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ታጋዮች ጉዳይ!’’ ክፍል -2- ጌታቸው ረዳ  (Ethiopian Semay) ብላችሁ ብትጽፉ ጉደኛ የግንቦት 7 ወንጀሎችን ወደ ሗላ ተመልሳቸሁ ብትመለከቱት ሳደርገው የነበረውን ሙግት በከፊል ተዘርዝሮ ታገኙታላችሁ። ለዛውም ብዙ ዘለፋወችን አሳልፌአለሁ። ይኸኼው ዛሬ እነ ብርሃኑ ነጋ እና ጀሌ ጋዜጠኞቹ ዛሬ የያኔው የድርጅታቸው ባህሪ  በድጋሚ ፋሺሰታዊው ኦሮሙማው አብይ አሕመድን በመደገፍ እንደገና የፖለቲካ ሽርሙጥና ሲፈጽሙ እያያችሁት ነው። ስለሆነም የኔም ዛሬም ሕሊናየን ያማከረኝ ምክር አውነተኛነቱን ለሁለተኛ ጊዜ አረጋገጥኩ

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


No comments: