Saturday, February 27, 2021

ተቃወሚዎቹ ቻሜሎኖች ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay 2/27/2021

 

ተቃወሚዎቹ ቻሜሎኖች

ጌታቸው ረዳ

 (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

2/27/2021


ቻሜሎን የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል በአማርኛ  "እስስት" ተብሎ የነበብ። የኛ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ምንግሥት በተለዋዋጠ ቁጥር እንደ “ቻሜሎኖቹ” ቀለማቸው እየለዋወጡ አገሪቱ መሰረታዊ ለውጥ እንዳታገኝ እንቅፋት ሆነዋል።

በቅርቡ እየታየ ያለው የተቃዋሚዎች ወደ ምርጫ ተመዝግቦ መግባት ካበሳጩኝ ቀዳሚው ነገር ነው። ሥልጣን ላይ ያለው “የኦሮሙማው ፋሺሰታዊ የነገድ ፖለቲካ አቀንቃኙ መሪ አብይ አሕመድ” ባዘጋጀላቸው ምርጫ ተብየው ዘልለው ለመግባት እያነፈነፉ ያሉት ተቃዋሚዎች ምን ለመለወጥ ነው? የሚል ጥያቄ ማንሳት መሰረታዊ ነው።

መንግሥት/ሥርዓት/ሕገ መንግሥት ለመለወጥ ወይስ የፋሺቶቹን ዕድሜ ለማስረዘም? እነዚህ ከሆነ እርማቸውን ማውጣት አለባቸው። ካለፈው ምንም አልተማሩም። ወያነ በምርጫ እንዳልተለወጠ ሁሉ የወያኔው ዲቃላ “የኦሆዴድ መንግሥት” በሽግግር መንግሥትና በአመጽ ካልሆነ በምርጫ ሊለወጥ እንደማይችል እንዴት ማወቅ ተሳናቸው? ለውጥና ሕገ መንግሥት የሚመጣው በምርጫ ሳይሆን፤ ወያኔን በሕዝብ አመጽ አስጨንቆ ሥልጣኑን እንዳስለቀቀው ሁሉ ሥልጣን ላይ የሚገኙት የዛሬዎቹ “የወንጀለኞችና የሙስና ንጉሦች ስብስብ” የሆነው “ኦሆዴድን/ብልጽግናን” በምርጫ አይለቅም። የሚለቀው ተቃዋሚዎቹ ሕዝብን ለሰለማዊ አመጽ በማስነሳት ለሽግግር መንግሥት በር እንዲከፍት ካልተገደደ “አሻጋሪያችሁ እኔ እና እኔ ብቻ ነኝ” የሚላቸው አብይና አብይ ባዋቀራቸው “የምርጫ ጋሪዎች” ተቀምጦ ወደ ለውጥ መጓዝ ፈረንጆቹ “ጃክ ኣስ” (jack ass) ወይንም moronic የሚሉት የሞኝ ሞኝ የመሆን ዕብደት ነው። አህን ፈረንጁ እንደሚለው “ቱ ሌት” ጊዜው አልፏል።

ተቃዋሚዎቹን ለምን በቻሜሎን መሰልኳቸው? ቻሜሌኖች ቀለማቸውን በማሳመርና ላለመታወቅ አከባቢውን ለመመስል እንደሁኔታው ቀለማቸውን በመለዋወጥ የታወቁ ብቸኛ እንስሳት ናቸው ፡፡ ተቃዋሚዎቹ በሥርዓቱ ሲሰቃዩ የግዳጅ አያያዝ ነውና ልክ ቻሜሎኖችም በግድ ሲያዙ ለጆሮ የሚሰቀጥጥ የጩኸት እና መንከስ አጸፋ ያሳየሉ፡፡ ሆኖም የቻሜሎኖቹ መንከስ የሚያሠቃይ ቢሆንም ለሰዎች መርዛማ ወይም ጎጂ እንዳልሆነ ሁሉ ተቃዋሚዎችም ልክ እንደ ቸሜሎኖቹ የሚያሰሙት የጩኸት ድምጽ ሥርዓቱን ለአደጋ አጋልጦ ከሥሩ ገርስሶ የሚጥል አጸፋ አይሰነዝሩም ፡፡ ብዙዎቹ ቻምሌኖች የተለያዩ ባህሪ እንዳላቸው ሊቃውንት ይናገራሉ - አንዳንዶቹ ሲስተናገዱ በደስታ ይቀበላሉ ፣ ሌሎቹ ግን እንዳይነኩ ይመርጣሉ ፡፡ እንዳይነኩ ሲመርጡ ግን ብዙዎቹ የሚለቁት መርዝ ገዳይ እንዳልሆነ ሁሉ ቢያንገራግሩም “ዝግምተኞች” ስለሆኑ በቀላሉ ይያዛሉ። ተቃዋሚዎቹም በገዢው መንጋ በተለያየ ጥቅም ተስተናግደው ሲያዙ (ልክ የኪነቱ ሰው “አቶ ደበበ እሸቱ” እንዳለው “ቤተመንግሥት እንደገባና እንድጎበኝ ያደረገኝ እኮ የኔው መሪ አብይ አሕመድ ነው” እንዳለው ሁሉ በቀላሉ የሚያዙ ተቃዋሚዎችም እንዲሁ አሉ።

ተቃዋሚዎቹ ለከፈሉት መስዋእት ምስጋና የሚገባቸው ቢሆንም የሕዝቡን እሮሮና ፍላጎት ግቡ ድረስ እናደርሰዋለን ካሉ አሁን እየገቡበት ባለው መንገድ ግቡ ሊደርስ አይችልም። መጀመሪያ እየታገሉት ያለውን ሥርዓትና መሪ ማወቅ በተገባቸው ነበር፡ ሆኖም አላወቁትም። አገራችን በከፋ መልኩ የዘር ጭፍጫፋ “ጀነሳይድ” እየተካሄደ ባለበት አገር እና ለዚህ ወንጀል ተባባሪ የሆነው መሪውና ሥርዓቱን ለመጣል ሕዝባዊ አመጽ ወይንም ሰላማዊ አመጽ ለመጥራት አመቺ መንገድና በቂ ምክንያት ተከፍቶ እያለ ለ3 አመት ያህል ያንን ክፍተት ሊጠቀሙበት ፍላጎት አላሳዩም።

የሃይማኖት ተቋማት እየተቃጠሉ፤ ጥንታዊ ቅርሶች እየፈረሱ፤ በተለይ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ አማኞች የአንገታቸው ማተብና መለያቸው የሆነውን ሰንደቃላማቸው እየተነጠቁ ለማመን በሚያስቸግር የመብት ግፍተራ እየተፈጸመባቸውም ቢሆን ምንም ሳይሉ “ሃይላችን ፈጣሪ ነው” የሚለው “ራስን መከላከል ወንጀል ነው ብሎ ፈጣሪያቸው የነገራቸው ይመስል” ራስን የማታለያ መንገድ መርጠው “የቅኝ ግዛት አይነት” “ዘግናኝ ግፉን” አሜን ብለው መቀበላቸው አላንስ ብሎ ተቃዋሚውም እራሱ “ዓድዋ” ላይ ወራሪዎችን ያሸነፈቺው አርማችንን ይዘው ሲገኙ “እየተነጠቁ፤ ሲታሰሩና ሲደበደቡ” አመጽ ያስነሳሉ ተብሎ ሲጠበቅ ከነጭራሹ “ወደ ምርጫ” መግባት ብቸኛው አማራጭ ነው ብለው ሥልጣኑን የያዘ “የወንጀለኞችና የሙሰኞች ስብስብ” ዕድሜን ለማራዝም የሚያስከትለው ሰበብ “ኢትዮጵያ” የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንደምትበታተን ይታየኛል። የቻሜሎኑ ተቃዋሚ ውሳኔ ጊዜው ቢዘገይም ተሎ ከነቃ ‘አሁን ከገባበት ጨዋታ ተሎ ወጥቶ’ “ሰላማዊ አመጽ” ካላስነሳ እየቀፈፈኝ እና እየዳዳሁም ቢሆን  “ኢትዮጵያ መዳኛ የላትም” ወደ ማለት እየዳዳኝ ነው።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) (Ethio Semay)

Monday, February 22, 2021

እነሆ ዛሬ የ ህ.ወ.ሓ.ት ፋሺዝም ያስከተለው የሲኦል ህይወት ተጀምሯል!!! ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) 2/22/2021

 

እነሆ ዛሬ የ ህ.ወ.ሓ.ት ፋሺዝም ያስከተለው የሲኦል ህይወት ተጀምሯል!!!

ጌታቸው ረዳ

(Ethio Semay) 2/22/2021




አሁን ወደ ርዕሳችን ልግባ።ወደ ዋናው ርዕሰ ከመግባቴ በፊት መጀመሪያ የሐዘን መግለጫየን ላስቀምጥ። ሰሞኑን በወያኔ ፋሺሰት ነብሰገዳዮች ህይወቱን ባጭር ለተቀጨው የፈንቅል እንቅስቃሴ መሪ ለነበረው መምህር “የማነ ንጉሰ” ነብስ ይማር በማለት የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ ሐዘኑን ይገልጻል። ወያኔ ሲፈጠር “ፈሪ” ስለሆነ ባስተሳሰብ የሞገተውን በጥይት በመቅጨት የለመደበት ባህሪው ስለሆነ ብዙ ሺዎቹን የትግራ ተወላጆችና ኢትዮጵያዊያን ተቀናቃኞቹን ቀጭቷል። መስዋዕቱ የማነ ሲሰጣቸው በነበረው አንዳንድ ሃሳቦች ባይጥሙኝም፤ በመራራው ረዢም የትግል ጉዞ ካፈራናቸው የትግራይ ወጣቶች አንዱ የሆነ ይህ የትግራይ ወጣት ኮቴአችንን በመከተል “ወያኔ” በፍርሃት እንዲርበደበድ ያደረገው ጉልህ ሚና የማይረሳ የትግራይ ወጣት ታጋይ ስለነበር አድናቆቴን ልቸሮው አፈልጋለሁ። ነብስ ይማር! አምላክ ለቤተሰቡ መጽናናትን ይስጥ! ትግሉ ይቀጥላል!

 

እንደምታውቁት ልክ እንደ ኦሮሞ ማሕበረሰብ 95% በሚያስብል ግምት ኦነግን እንደተከተለ ሁሉ በተመሳሳይነት ቁጥር ትግሬዎችም  እንዲሁ በ1928 ዓ.ም ጣሊያኖች ለኢትዮጵያዊያን ትተውልን የሄዱት የቀየሱትን የፋሺዝም ርዕዮት “የአንጎል አጠባ” ተጠቂዎች ናቸው። የትግራይን ሕዝብ ከኢትጵያዊነት ስነ ልቦና ለማላቀቅ ረዢም ጊዜ ተወስዶ በርካታ የአእምሮ ማጠቢያ ቴክኒኮችን (ዘፈኖችን፤ተውኔቶችን፤መጽሐፍቶችን፤ንግግሮችን….ወዘተ) ተካሂደዋል።

በሚገርመኝ ሁኔታ የፋሺሰት ተቃዋሚ ነን የሚሉ ሳይቀር ደደቢት በረሃ ውስጥ ወያኔ የመሰረተው የየካቲቱ 11/1967 ዓ.ም የኢትዮጵያን የባሕር ወደቦችን ለጠላት ለመስጠት እና ፋሺዝም ለማንገስ የተመሰረተው የትግል ቀንና ወር መከበር አለበት ፤ ለዚያ መስዋዕት የሆኑትን እና ለነመለስ ዜናዊ ጭምር የቆመው የመቀሌው ሃውልትም በክብር መያዝ አለበት እያሉ “የወያኔ ፖለቲካ ተቃዋሚ ነን” እያሉ ነገር ግን የወያኔን “አርቲፋክት” (ቅርስ/አሻራ) የሚያከብሩ የፋሺዝም አሽቃባጮች ሳያፍሩ ዛሬም ችግሩ እንዲያብብ ድጋፍ እየሰጡ ነው።

በዚያ ወር እና አመተምህረት የትግራይ ብሔረተኞች የቀየሱትን ጸረ ኢትዮጵያ የሆነው “የትግሬዎች የፋሺዝም ፖለቲካ” ትግራይ በረሃ ውስጥ ለዚህ ርዕዮት “መወለድና ማደግ” ለሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ስቃይ መነሾ የሆኑት ህይወታቸውን የሰው የወያኔ ታጋዮች ከተሰውትም መሃል የሰው ልጅ በእሳትና በፈላ ውሃ እየለበለቡ ሲመረምሩ የነበሩ ሰው መሳይ አራዊቶችም እንደ ቅዱሳን መላዕክት እንዲታዩ በክብር እንዲነሱ እያደረጉ ነው። በዚህ አሳዛኝ ታሪክ በላንበት ወቅት “የትግራይ ፋሺዝም” በሰፊው ሕዝብ ሕሊና ተቀባይነት እንዲኖሮው የሙታን ድርሳኖችን፤ ግጥሞችን እና ማስታወሻዎችን በየትምህርት ቤቶች እና በዓላት በማሰራጨት ሰፊ የሕሊና አጠባ በመደረጉ ወያኔ እና የትግራይ ሕዝብ ባስተሳሰብ አንድ ናቸው ስል የነበረውን በምክንያት እንደነበር ለበርካታ አመታት ጽሁፎቼን የተከታተላችሁ አንባቢዎቼ የምታውቁት ታሪክ ነው።

 

እነሆ ዛሬ ምንም በማያውቁ የትግራይ ህጻናት እና ሌላ ቀርቶ አስነዋሪ በሚባል ስነምግባር በውሾችና በፈረሶች “ወገብ” ላይ “ሽጉጥ” እያስታጠቁ በኬሚካል የተቀመመ ቀለም የወያኔ ባንዴራ በእንሰሰታቹ ቆዳ ላይ በመቀባት በወታደራዊ የሙዚቃ ማርሽ እያጀቡ ፋሺስታዊ አይበገሬነታቸውን (Invincibility) በሕዝቡ ጭንቅላት እንዲቀረጽ በማድረግ የትግራይ ማሕበረሰብ በማይወጣው ስቃይ ውስጥ እንዲገባ አድርገውታል።

 

ቀደም ብየ በበርካታ ጽሁፎቼ እንደገለጽኩት ኤርትራኖች በተከተሉት የተሳሳተ የትግላቸው በመጨረሻ ያገኙት ትርፍ ቢኖር “የረገሙዋትን ኢትዮጵያን ተመልሳ እንድታኖራቸው በስደት መልክ መለመንን፤ ውርደትን ፤ ስቃይን ፤ አካለ ስንኩልነት...” ነው። ለዚህ ሁሉ ውርደት ኢሳያስ አፈወርቂ ነው ቢሉም መጀመሪያ ተጠያቂዎቹ ማንም ሳይሆን ኤርትራኖች በራሳቸው ያመጡት ስቃይ ተጠያቂዎቹ እራሳቸው እንደሆኑት ሁሉ” በትግራይ ሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ስቃይም ተጠያቂው ወያኔና እንዲሁም 99% የትግራይ ምሁራኖች እና እራሱ የትግራይ ሕዝብ እንዲሁም የወያኔ ዲቃላው “አብይ አሕመድ” እንደሆኑ ከሦስት ሳምንት በፊት በጻፍኩት ላይ መመልከት ይቻላል።

 

ኤርትራኖች ከ29 አመት በፊት ዘምባባ እና ከበሮ ይዘው እየዘለሉ ሲጨፍሩ የነበረውን የስካርና የትዕቢት መንፈስ ዛሬ እንዴት እንደበረደላቸውና ለስቃይ እንዴት እንደታደረጉ የታዘብነውን ያህል ትግሬዎችም የፋሺዝምን ምስረታ ያበሰረው የካቲት 11 በመጣ ቁጥር፤ ሕሊና ቢስ የኪነት ሰዎችን እየሰበሰቡ ሕዝቡን እያማለሉ ሲያስጨፍሩት “ትግራይ አሁን ላለቺው የሲኦል ህይወት” እንደሚዳርጓት ስንናገር ነበር። እንዴት እንደሆነ እንመልከት።

 

 ኤርትራኖች “በስካራቸው ዘመን” ጆሮአቸው መስማት እንዳቃታቸው ሁሉ ፤ እኔ እንደ ትግሬነቴ አሁን ያለው እየመጣ የነበረው አደጋ ስለታየኝ እየተጓዛችሁበት ያለውን አደገኛ ጉዞ ተሎ ካልገታችሁት በትግራይ ሕዝብ (በራሴ ዘመዶችም ጭምር) ላይ መራራ ህይወትን ያስከትላል ብየ ሳስጠነቅቅ ማንም ሰሚ አልነበረም። በሚገርም ሁኔታ አሁን ወያኔዎች “ተከበብን” እያሉ ያሉትን ሁኔታ በ4 መዓዝን ተከብብው መውጫ በር እንደሚያጡ በቃለ መጠይቄ ገልጬ ነበር። ወቅቱም “ሕገምንግሥታችን ከተነካ በየመንደራችን እንከፋፈላለን ወይንም ወደ ሌላ ሁለተኛ የጦርንት አዙሪት እንገባለን” ሲል “ስብሓት ነጋ” በተናገረበት ወቅት” (በ1997 ምርጫ ይመስለኛል ፤ አመተምህረቱን በትክክል ባላስተውሰውም) አበበ ሃይሉ በሚያዘጋጀው ሳንሆዘ ዩኒቨርሲቲ ራዲዮ ጣቢያ ላይ ስብሓት ነጋ በሰነዘረው የግንጠላ አማራጭ እንዳብራራ ቃለመጠይቅ አድርጎልኝ አሁን እየታየ ያለው “በተለያዩ የጠላት ድምበሮች ተከብበናል” እያሉት ያለውን ኡኡታ እንደሚከሰት ተንበየ ነበር። እነሆ ዛሬ የ ህ.ወ.ሓ.ት ፋሺዝም ያስከተለው የሲኦል ህይወት ተጀምሯል።

 

በተደጋጋሚ እንደምታውቁት የትግራይ ምሁራን ራሳቸውን ለፋሺዝም አምልኮ ሸጠዋል። የወያኔ መሪዎች የትግራይ ምሁራንን በመያዝ ሕዝቡን በማሕበራት አደራጅቶ የሕዝቡን ሥነ-ልቦና ለራሱ በሚመች በመበዝበዝ በቁጥጥራቸው ሥር አድረገውታል። በቁጥጥር ስር ለማድረግ ዘገምተኛና ረቂቅ የትግራዋይነት “ኔትወርክ” በመዘርጋት ያከናወኑት ስልት የአእምሮ አጠባ የተከናወነበት የትግራይ ሕዝብ በፋሺዝም ትምህርት እንደታጠበ እንኳን ሕዝቡ እራሱ የተሸረበለት ሴራ አይገነዘበውም። ሌላ ቀርቶ በጣም ብሩህ ፣ በጣም ራሳቸውን የሚገነዘቡ ሰዎች የሚባሉት እንኳን በዚህ መሰሪ ወጥመድ ተይዘው ሊወድቁ ችለዋል፡፡ የወያኔ ፋሺቶች ያከናወኑት ተመሳሳይነቱ “ለብ/ሞቅ ባለው/ ድሰት የተጣደቺዋን የእንቁራሪቷ ታሪክ የተሰማት ደስታ እና መጨረሻ ውሃው ቀስ እያለ እየፈላ እንዴት ጠብሶ እንዳቃጠላት ሁሉ፤ የትግራይ ሕዝብም በጭፈራ ጦዞ የትዕቢት ሐረጎችን ያዘሉ ዘፈኖችን እያመነዠከ ቀስ እያለ በቀበኞቹ ተንኮል እራሱን ለማቃጠል በቅቷል።

 

እኔ እንደምረዳው ለመፍትሄ አስቸጋሪ የሚያደርገው ነገር፡ ዛሬም እንደዚያ ችግር ውስጥ ገብቶ ፤ ለዕርዳታ የመጣለትን እህል “አዳኞቼ” የሚላቸውን ወያኔዎች መንገድ ላይ ጠብቀው እህልና መድሃኒት የጫኑ መኪኖችን ሲያጋዩዋቸው እያየ ተቃውሞ ያለማሰማቱ የሚያስገነዝበን ነገር ቢኖር የትግራይ ሕዝብ የአንጎል አጣባው የተኮናወነው በወያኔ መሪዎች ምስል ስለተገነባ ወያኔን አስወግዶ በራሱ አስተሳሰብ መቆም እንደማይችል ስላሳመኑት በአሳዛኝ ሁኔታ ግማሽ ጎኑ ጭለማ ውስጥ እየገባ ነው። ከወያኔ አስተሳሰብ ተላቅቆ በእራሱ ምስል እንደገና ለመቆም የታጠበበትን ዘመን ያህል እንደገና ያን ያህል ብዙ አመታትን ይጠይቃል። እንደገባኝ ከሆነ “ሕዝቡ እራሱን ትንሽ አድርጎ ‘ወያኔን’ ትልቅ አድርጎ እንዲያምን ተደርጓል።

 

ዛሬ በየሚዲያው የምናደምጣቸው የወያኔ ጀሌዎች የበለጠ ሰብዓዊነት የጎደለው ነገሮችን ሲያደርጉና እየዋሹ መሆናቸውን እያወቁም ቢሆን ለነገ የሚባል ጭንቅላት አልተፈጠረባቸውም፡፡ በሚገርም ሁኔታ የወያኔ አጃቢዎች ያልነበሩ አዳዲስ ጀሌዎች እየተከናወነ ባለው ጦርነት የወያኔ መሪዎች በሚያሳፍርና በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተማረኩ አይተው ምክንያቱ በማናውቀው ሁኔታ “የቡድኑ አካል” ሆነው የወያኔ ቱልቱላ አዳማቂዎች ሆነው የተቀላቀሉ ብዙ ሰዎችን ታዝበናል።

 

ወያኔ በደረሰበት ሽንፈት ምክንያት የወያኔ ሚዲያዎች “አልሞትንም” ለማለት ፋሺዝም ማራኪ ለማድረግ የሚያሰራጩዋቸውን ምስሎችን ተመልከቱ። መሳጭና የብሔረተኞችን ልብ የሚያማልሉ ሙዚቃዎችን በማስደመጥ የተከታዮቻውን የልብ ምት ለማረጋጋት ሌት ተቀን እየጣሩ ነው። የዚህ ቀቢሰ ተስፋ ዓላማ “ዓይነ ስውር ታዛዥነትን” ቀጣይነቱ እንዲኖሮው መግፋት ነው። ሆኖም የወያኔ ትግራይ ፋሺዝም ‘የትግራይ ሕዝብ ዛሬም የሙጥኝ ካለ’ ወደ ማይወጣው የገሃነብ ህይወት በራሱ ፈቃድ እየገባ መሆኑን ግንዛቤ እንዲይዝና ውጭ አገር በምቾት እየኖሩ ያሉት “የወያኔ ትግራይ” ጀሌዎች አሁን እየነደደ ከሚታየው ከሚንቀለቀለው እሳት የራቁ ስለሆኑ ጦርነት ለነሱ “እንደ ኳስ ጨዋታ” አድርገው ጦርነቱ እያበረታቱት ስለሆነ፤ እራሳቸው ወደ ጦርነቱ መክተት ያልፈቀዱ ከነዚህ “የሃሰት ቡድኖች” ራሳችሁን እንድታርቁ ምክሬን እለግሳለሁ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

Saturday, February 13, 2021

የመቀሌ ሕዝብ የመገንጠል አባዜ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 2/13/2021

 

በኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ ስለ የመቀሌ ሕዝብ የመገንጠል አባዜ ከተቸሁባቸው ከቆዩ ማሕደሮች አንዱ ‘ሕዝብ በፋሺስቶች ፖለቲካ የስሜት ህዋሳቶቹን ሲያሰክር’ ‘በራሱ ላይ የሚያስከትለው ሰበብ ጎጂነቱን ትናንትን ከዛሬ ጋር ለማነጻጸሪያ እንዲመቻችሁ እነሆ ላስነብባችሁ!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

2/13/2021



ርእሱም እነሆ ከታች እንደሚከተለው ዘግቤው ነበር!

“የትግራይ ሕዝብ መቀሌ በተካሄደው ሕዝባዊ ስብሰባ የኢትየጵያን መበተንን እንደ ሁለተኛ አማራጭይደገምበማለት የደብረጽዮንን ንግግር አጽድቆለታል”

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ተከታታዮቼ እንደምን አላችሁ። ሰሞኑን በጣም በርካታ አንባቢዎች አይቻለሁ። ትችቶቼ ለበርካታ አመታት በጥርስ አልባዎቹ ተቃዋሚ ድረገጾች ቢታገድም፤ አንባቢዎቼ እየተበራከቱ መምጣታቸው የሚያሳየኝ ምልክት ቢኖርትችቶች በዚህ ዘመን ማፈን እንደማይቻል ማሳያ ምልክት ነው ሰሞኑን ለአብይ አሕመድ ያስተላለፍኩት በእንግሊዝኛ የጻፍኩት መልዕክት ከመቸውም ጊዜ እጅግ አስገራሚ የሆነ ያልጠበቅኩት የአንባቢ ብዛት ብድረገጼ ጎብኝተውታል። ወደ አብይ ስብሰባ ከኼደው ተሰብሳቢ እርግፍ ብሎ 15 እጅ ዕጥፍ ወደ ድረገጼ የመጣ በሚመስል መልኩ ነው የተነበበው። ለዚህም አመሰግናለሁ። ፌስ ቡክ የሚባል ስለሌለኝ፤ በድረገጼ ላይ የአንባቢ ብዛት አንዴ ያድጋል አንዴ ያንሳል- ሆኖም እዛው መድረሳችን አይቀሬ ነው። አመሰግናለሁ። ዋናው አላማ ትምህርት መለዋወጥ ነው።

 

   ትናንት 7/27/2018 (ፈረንጅ አቆጣጠር) በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተጀመረውን የሰላም ጥረት በመደገፍ የመቐለና አካባቢው ነዋሪዎች ህዝባዊ ሰልፍ አደረጉየሚል ዜና በተዘረጋው የዩ ቱብ ዜና ማሰራጫ በኩል ትዕይንቱን በቪዲዮ አይቸው ከመቸውም ጊዜ በላይ ትግሬዎች በወያኔ ፋሺስታዊ ርዕዮት የጣሉትን ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ ስሜት በረዢም ሂደት ቀስ በቀስ ወደ ትግራዋይነት አጥር የመሽጉበት የህሊና ማፈግፍግ ዛሬ ግልጽ ወደ ሆነው መፈክራቸውመበታተንወደ እሚለው የተቀመጠላቸው የአንቀጽ 39 የመበተን ሁለተኛው ምርጫቸው በይፋ በዕልልታ ያሰመሩበት ስብሰባ መሆኑን የታዘብኩበት አስገራሚ ትዕይንት ነበር።በዛው ላይ አስገራሚ የሚያደርገው ይህ ሰልፍ ደግሞ የአሁኑ /ሚኒስትር ኣብይ ኣሕመድ ፎቶግራፍን ይዘው ሳይሆን የተሰለፉት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረገው የወያኔው /ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፎቶግራፍ ይዘው ነበር የተሰለፉት። ይህ ተደራርቦ የሚያሳየን ክስተት እና ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ አንባቢ ሊፈርደው ይችላል።ባጭሩ ለለውጡ ያላቸው ስሜት በተጻራሪ እንደሆነ የሚያመላክት መልዕክት ነው።

 

ብዙ ጊዜ በመጽሐፍቶቼም በቃለ መጠይቆቼም ለበርካታ አመታት እንደነገርኳችሁ። እኔ ትግሬ ስለሆንኩኝ ትግራይ ውስጥ የበቀለው የፋሽስት ችግኝ እንዲነቀል ብዙ ታግያለሁ።እንደ እኔ የመሰሉ በርካታ የታሪክ አዋቂ ሽማግሌ እና ወጣቶች በወያኔዎች ጥይት ተበልተዋል። ግማሹም ጠፍተዋል፤ ተሰድደዋል፤ንብረታቸው፤ከብቶቻቸው ያለ ምንም ፍትሓዊ የሕግ ተቀውዋም ተዘርፏል (በሃሳብ ልዩነታቸው ብቻ!!) ወያኔዎች በከርክር ማሸነፍ ሲያቅታቸው መጨረሻ እኔም ሆንኩኝ ገብረመድህን አርአያን አማራዎች ናቸው፡ ወደ እሚለውፍሬ ከረስቺገብተው ሲምቦጫረቁ ይኼው 27 አመት ሞልቷቸው መጨረሻ ተከታዮቹ የተከተሉት ርዕዮትአሁን ወደ አሉበት የጭንቅ የመከራ የመገለል፤ የመባረር፤የመዋረድ ዕድል እንደደረሳቸውእያየን ነው።

 

17 አመት የተካሄደው ጸረ አማራ የተከተሉት የፋሺዝም መስመር በደርግ የሚታዘዘው ሠራዊት በውስጥ አስተዳደር ጉድለት በደረሰበት የሞራል መላሸቅ ሆን ብሎ መዋጋቱን በማቆምመሳርያውን እየጣለፋሺስዝም በኢትዮጵያ ለማስፈንሲታገሉ ለነበሩት የትግራይ ታጋዮች እጁን በመስጠት፤ የትግራይ ሕዝብ የላከልን የፋሺዝም መሪመለስ ዜናዊወደ ሥልጣን አስገብቶ ጣሊያኖች ያሰመሩቱትን የፋሺስቶች አስተዳዳር በማስቀጠልወደብ ዘግቶ  ኢትዮጵያ በቋንቋ እና በነገድ” “ባልካናይዝድበሆነ የአፓርታይድ ክልሎች አዋቅሮ ሕዝቡ ለበርካታ አመታት እርስ በርሱ ሲጠላላ፤ የጥላቻ ሃውልት ሲተክል፤ 44 ሰንደቃላማ አስሰፍቶ አገራዊ ማንነቱን ክዶ በብሔሩ እየተመዘገበ ማስታወቂያ እንዲይዝ ተደርጎ መጀመሪያ እኔ ሰው ነኝየሚለውን ከማስቀደምመጀመሪያ እኔ ትግሬነቴ/ኦሮሞነቴ/ሶማሌነቴ ነው ቀዳሚው እንጂ ሰው በመሆኔ ሰብኣዊነቴን ወይንም አገራዊነቴን አላስቀድምምእንዲል አስተምረውት በያዘው የነገድ መታወቂያው እየተለየ እንዲገደልና እንዲባረር ለግጭት ዳርገውት ይኼው ዛሬ የትግራይ ሕዝብ የተከተለውና ሲመካበት የነበረውየፋሺስት ርዕዮትሲያዘግም የነበረው ተቃውሞበድንገትፈንድቶ አሁን የትግራይ ሕዝብመበታተንን” (አንቀጽ 39ኙን ሳንረሳ) እንደ ሁለተኛ አማራጭ ወደ መደገፍ ገብቷል። / አብይ ምንም ቢከፋንም  ማስተካከል እና ምንም ቢመጣ ምርጫችን መደመር ነው ሲለን ወያኔዎች እነ ደብረጽዮን እና የትግራይ ሕዝብ ደግሞ እኩል ካልሆንን እንበታተን፤ እያሉ መበታተንን በዕልልታ እና በጭብጨባ ሲያሽሞነሙኑት እያደመጥን ነው፡

 

መቀሌ ከተማ ወደ ተከናወነው አስገራሚ ሕዝባዊ ትዕይንት ልምራችሁ።  

 

 

ከላይ በመግቢያው የጠቀስኩት ይህ ስብሰባ የተካሄደበት ዋነኛ ምክንያት ስለ መሃንዲስ ስመኝህ በቀለ እና ስለ ኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት የተመለከተ ቢመስልም- በዋናነት የተንጸባረቀበት መልእክት ግን ብትግራይ ሕዝብ የተደገፈውና የተወደደው ፋሺስቱ የወያነ ሓርነት ትግራይ ድርጅት (በእስረኞቹ ላይ የወንድ ዘር ብልትን የሚያኮላሽ፤ በሴቶች ማህጸን ቃርያ እና ምጥሚጣ የሚጨምር፤ ጥፍርን የሚነቅል ገራፊ (የትግራይ የጎስታፖ ቡድን) አደራጅቶ በኢትዮጵያ ምድር ፋሺዝምን ለማስፈን) በትግራይ ሕዝብ ልጆች የተከፈለው መስዋእትነት ለማሳሰብ የተንጸባረቀበት ስብሰባ ነው። ለዚህም ከአጥናፍ አጥናፍ እንደ ተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይዞት የተሰለፈውን ልሙጡን ሰንደቃላማ ሳይሆን የትግራይ (የመቀሌ) ሕዝብ ይዞት የተሰለፈው ሰንደቃላማ የህወሓት ድርጅት ባንዴራ እና ብሔራዊ ብሎ የሰየመው ባለ አምቧሻው የሰይጣንናውያን ተከታዮች አምልኮ የሚያመልኩትን  ባለ ኮኮብ ምልክት ያለው ሰንደቃላማ ነበር።

 

በዚያ ሳይበቃ -በመክፈቻው በዓል ላይ የተለቀቀው ዘፈንኣንታ ወያናይ ትግራዋይ

                   ትርጉም

             ( የትግሬ ወያኔው

              አንተ እምቢተኛው

             ( ሃሞተ ኮስታራው!)

በማለት በጣም የተጋነነ ነገዳዊ ፋሽስታዊ የማበረታቻ ፕሮፓጋንዳ የተሞላ የማነሳሻ ዘፈን በመዝፈን

                  እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትነህ

                  ወርቅነትክን ዓለም ሙሉ አስመሰከረህ

                  ብሔር ብሔረሰብ ሕዝቦችን አንድ አድርግህ…..…”

 

የሚል ዘፈን በሰልፉ ሜዳ ላይ በመልቀቅ በትግሉ ዘመን የተሰውባቸው የታጋዮች ፎቶግራፎች በወላጅ ዘመዶቻቸው በኩል ተይዞ እስክስታ እየወረዱ የወያኔ ትግል እንዳይረሳ የትግራይ ሕዝብ እንደፎኒክስዋ ወፍዳግም ልደታቸውእንዲቀጥል ለማድረግ የተዘጋጀ ሕዝባዊ የሕሊና አጠባ እንዲሆን የተዘጋጀ ስብሰባ እንጂ የኢትዮ-ኤርትራ ሰላማዊ ግንኙነት ወይንም ስለ ሟቹ መሃንዲስ ስመኝህ በቀለ ሞት ለማጽናናት ያለመ ሕዝባዊ ትዕይንት አይመስልም።

 

በነገራችን ላይ ብዙ ሰዎች ትግሬዎች በኢንጂኔር ስመኝህ በቀለ ሞት በማዘኑ የተሰማው ሓዘን የትግራይ ሕዝብ ያሳየው የሓዘን ማሳያ ነው ሲሉ የጸፉ ወገኖች  አንቤአለሁ። እኔ በዚያ አላየውም። እውን ትግሬዎች ስለ እንጂኔሩ ሕልፈት አዝነው ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሆኖም መርሳት የሌለብንየአባይ ግድብ ፕሮጀክት” (ሕዳሴ ግድብ) የሚባለው በትግሬዎች በመለስ ዜናዊ የተመራ እና በትግሬዎች የታቀደ (አባይን የደፈረየሚለውን ልብ በሉ) ግድብ በትግሬዎች ትግል የተመዘገበ ነው ብለው ስለሚያምኑ፡ ከግድቡ ጋር የሚያያዝ ማንኛውም ጉዳይ የትግሬዎችን ፕሮጀክት የሚነካ አድረገው ስለሚያዩት፡ በዛው ንክኪ የተያያዘ ነገር ሁሉ ትግሬዎችን የሚነካ መስሎ እንደወሰዱት አልጠራጠርም። ሌሎቹ በሌላ ይወስዱታል እኔ ግን እለያለሁ።

 

ትግሬዎች እውነት አንድ የታወቀ  ገናና ሙሁር ሲቀጭ ሓዘን ቢሰማቸው ኖሮ ብዙ ምሁራን በወያኔ (ጎስታፖዎች) የተቀጠፉ በርካታ የታወቁ ምሁራን አጥተናል። ስለ እነሱ ሲቆዝሙ ሲያወግዙ፤ሲያዝኑ በታሪክ አልተመዘገበም።  መቶዎች ምሁራን መቁጠር እችል ነበር ግን ለመቆጠብ ያህል አንድ ምሳሌ ልስጥ፦ የፕሮፌሰር አስራት (ልዩ እና ብቸኛ የልብ ቀዶ ጥገና ሃኪም ሲሞቱ ሓዘናቸውን መግለጽ ነበረባቸው።አይደለም እንዴ?  የምሁር ሰው ባጭር እና ያለ አግባብ መቀጨት የሃዘን መገለጫው ሚዛን ከሆነ ትግሬዎች ሓዘናቸው ለፕሮፌሰሰሩ ሓዘናቸውን ማስመዝገብ ነበረባቸው። ዛሬ ትግሬዎች የይፋ ሓዘናቸው ለመሓንዲሱ የቸሩበት ምክንያት በቅጡ ካላወቃችሁ ከዚያ ወዲያ ግልጽ ልሆን አልችልም።አስራት ወልደየስእና አኒጂኔሩሁሉም ለአገራቸው በየሙያቸው ልዩ ምሁራን ነበሩ። ሆኖም ላንዱ ሲያዝኑ ላንዱ የተለየ ስሜት መታየቱ ከፖለቲካ ወገንተኛነት ሊያልፍ አይችልም። ሚዛናዊ አይደለም። ባጭሩ የሰልፉ ጥሪኢትዮ ኤርትራእናየመሃንዲስ ስመኝህ በቀለ ሞትአስታክኮ የተላለፈው መልእክትሓሞተ ኮስታራው አንተ ነህ ወያናይ ትግራዋይመፈክር፤ግጥም፤ዘፈን ከተባለው የስብሰባ ጥሪ ጋር ምን ተያያዥ አንዳለው አልገባኝም።

 

ወያኔዎች የትግራይን ሕዝብ ስለ ኤርትራ ሰላም መፍጠር ሲሰብክ የመቀሌ ሕዝብ ደብረጽዮንን የትግራይ ሕዝብ ከወንድሞቹ/እህቶቹ የሆኑት የባሕር ነጋሽ ልጆች ጥቁር ደም ያቃባን ወያኔ ነውና ከስልጣን ውረድ የተቀረው ራሳችን እናበጀዋለንለማለት ለምን እንደማይደፍሩ ይገርመኛል።ጎሰኝነት የዓን ሚዛንን ይጋርዳል። 

 

ከዚህ ቀጥሎ ያለው እዚህ ላይ ላሰምርበት የማልፈልገው ነገር ብዙ ሰው ሊገባው የማይችል የኛው ድብቅ የሆነ ሌሎቹ የማይገባችሁመልእክት የምናስተላልፍበት ባሕርይ አለን ይህም አስገራሚ የሆነ ከሕዝቡ የተደመጠ ልሳን ነው ልነግራችሁ የምፈልገው። በስታድየሙ የተሰበሰበው ሕዝብ ሊያስተናግድ የተመደበው የመድረኩ አስተዋዋቂ የወያኔውን ሊቀመንበር ደብረጽዮን /ሚካኤል ወደ መድረኩ መጥቶ ንግግር እንዲያደርግ ሲጋብዘው ከሕዝቡ የተሰማ አንድ መፈክር ተስመቷል። ልብ ብላችሁ ተከታተሉኝ።

 

ደብረጽዮን ወደ መናገሪየ ፖድየሙ (ሰገነቱ) እንዲመጣ ሲጋበዝ፤ በከፍተኛ ጭብጨባ እና በከፍተኛ ጩኸት እና ዕልልታ የታጀበ ድምፅኣይዞኻ ናይና አይዞኹም ናይና” (የኛዎቹ ኣይዟችሁ!------ የኛው ሰው አይዞህ!!”) በማለት አስገራሚ የሆነወገንተኛነትንየሚያንጸባርቅእኛ እና እነሱ/አንተ እና እነሱበሚለው መፈክር ነው የተቀበለው።

 

 ሕዝቡ 27 አመት ይዞት የተራመደውን መፈክር ባሁኑ ጊዜ ዛሬም ያንኑ ማስተጋባቱ የሚነግረን ምልክትየትግራይ ሕዝብ አሁንም ተንጠልጥሎ በከፍተኛ ጩኸት ተደግፎ የቆመበት የሕሊና አጥር የት ቆሞ እንዳለ አመለካች ማስረጃ ነው። ይህኣይዞኻ ናይና አይዞኹም ናይና” (የኛዎቹ ኣይዟችሁ! -የኛዎቹ ኣይዟችሁ! -የኛው ሰው አይዞህ!!”  -- የኛው ሰው አይዞህ!!”) የሚለው መቀሌ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ እንደ ባህል ተወስዶ በኳስ ጨዋታም ይሁን በፖለቲካ ወይንም በቡድን ድብድብ ሲስተጋባ የቆየ አስቀያሚ ወገንተኛነትን ልዩነትን እና ጥላቻን የሚያጠናክር መጥፎ ባሕሪ ነበር (በዘፍንም ሲዘፈንበት የቆየ ነው)  

 

ዛሬ ይህ ጥላቻ፤ ልዩነትንና ወገንተኛነትን የሚሰብክ የቡድን ማበረታቻ መፈክር በተለይ ወያኔዎች 27 አመት የተጨማለቁበት ፋሺስታዊ ሥልጣናቸው ዛሬ ሲንገዳገድ በይበልጥ እየጎላ መጥቶ አሁን ሕዝባዊ ባሕሪ ወደ መሆን መምጣቱ አስፈሪ የግጭት ጥሪ ምልክት መሆኑን ላሰምርበት እፈልጋለሁ። ይህ በጩኸት የተደገፈ መፈክራዊ መልዕክት ሰላማዊ ጥሪ ከተጠራው ስብሰባ ጋር ምን አንዳገናኘው ባይገባኝም። አሁን ካለው አዲስ ለውጥ ጋር የተያያዘ ተቃውሞ እንደሆነ ለሚመረምር የስነልቦና ተመራማሪ ትርጉሙ የሕዝቡ ስነ ሉቦና የሚንጸባረቅ ለየት ያለ ነገር እንዳለ ሊገልጽለት የሚችል ክስተት ነው።  አሁንምወያኔ የኛ ነው” “አይዝዋችሁ ወያኔዎችአትደናገጡ ከጎናችሁ ቆመናል ነው ዋናው መልዕክቱ።

 

የደብረጽዮን ዋና ዋና ነጥቦች ወደ 17 ነጥቦች ስጨምቃቸው ከነሱ መካከል የሚገርሙ ንግግሮቹን ልጥቀስ፡

 

 

1-እንደሚታወቀው ትግራይ ሕዝብ ሥልጣኔ በአገራችን የላቀ ቦታ አለው።

 

2-ሕዝባችን (የትግራይ ሕዝብ) ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ መከላከያ ሆኖ ጠላት ወደ መሃል አገር አንዳይመርሽ ምሽግ ሆኖ መስዋእት መክፈሉ የማይካድ ሃቅ ነው።ይላል።

 

(እዚህ ላይ ማስመር የምፈልገው- ትግራይ ብቻ አይደለም -ሌሎች ድምበሮች፤ እና የሌሎች የባሕር አገሮች ወደቦች ያሉባቸው የጠላት መሸጋገሪያዎች አሉ። ሁሉም በየወቅቱ ዘብ ቆሟል።  ሓረር አለ ጋምቤላ አለ፤ ጎንደር አለ፤ ጎጃም አለ….-ሁሉም በየድምበሩ ጠላት እንዳይገባ መክቷል፡ ለምን የትግሬው ድምበር ልዩ እንደሚሆን አልገባኝም።)

 

  3-ግስጋሴአችን ያልጣማቸው የውስጥ እና የውጭ ሃይሎች ምክንያት ሕገመንግሥታችን እና ስርዓታችንን ለማፍረስ፤ በተለይ ደግሞ ጸረ የትግራይ ሕዝብ እየዘረጉት ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ የተጀመረው ልማት እንዳይቀጥል ለማሰናከል ነው።ይላል።

        

(እዚህ ላይ ሁሌም ይገርመኛል። ጸረ ትግራይ ሕዝብ ፕሮፓጋንዳ በሚያናፍሱ ክፍሎች ላይ በቃለመጠይቆቼም ሆነ በጽሑፌም ሆነ በመጽሐፍቶቼ የሚባሉት ክፍሎች ተቃውሜ ተጋፍጬአቸዋለሁ። ሁላችሁም የምታውቁት ነው። ሆኖም የወያኔ መሪዎች በአማራ እና በኦርቶዶክስ፤ እንዲሁም ዋልድባ ገዳም ሲኖሩ በነበሩ አማራ ሴት መነኮሳት ሰይጣናዊ በሆነ ስነ ምግባር ታይቶ-ተሰምቶ የማይታወቅ የጾታ ጥቃት  በገዳሙ አስተዳዳሪ በሆኑት ትግሬዎች እውቅና ሲደፈሩ፤ ትግሬዎች አንዲትም የውግዘት ቃል ሳያሰሙ ከርመው፤ ዛሬ ትግሬዎች ሲባረሩ አማራዎች 27 አመት ሲጠቁ መለስ ዜናዊ የሚሰብካቸውን እያዳመጡ እና እየደገፉአፋቸውን ሲዘጉ ኖሮውዛሬ ትግሬዎች ሲደበደቡ (የኔ የገዛ ወንድም ጭምር ተደብድቧል) እና ሲባረሩ ዓለም ቀውጥ ሲያደርጉት ማየት በፍትሕ እና በሞራል ዓይን ሕጋዊ ቢሆንም በምን የሞራል መመዘኛ ነው ትግሬዎች አሁን ደርሰውሌላውንለመውቀስ ለማውገዝ የሚጥሩት? ደብረጽዮን የት ነበርክ? ደብረጽዮን የት ነበርክ? አስራት ውልደየስ አማራ ስለሆኑ ብቻ አንተ የውሸት ማሕተም እና ፌርማቸው ያልሆነ ፌርማ አገጣጥመህ ለሞት እና እስራት ስትዳርግ ያኔ ያንተ ሕሊና የት ነበር? ዛሬ አንተ የፍትሕ፤ የልማት፤ የሰላም፤ የወንድማማችነት፤ አብሮነት፤ እና የእኩልነት ሰባኪ ሆነህ በጎሳ ፖለቲካ በአክራሪ ብሐርተኝነት የጦዘ ሕዝብ ስታስጨበጭብ እና ይደገም ይደገም ስታስሰኛቸው ፈጣሪን አትፈራም? ለመሆኑ የወያኔ መሪዎች በፈጣሪ ያምናሉ? ቤትኛው ማሕደራቸው ፈጣሪን ሲፈሩ አይተን!  

 

4- በማንኛውም ከማንም ብሔር ይምጣ ሰርቶ በሰላም እንዳይኖር

እየደረሰበት ያለው ችግር እያየን ነው። በተለይ ደግሞ በትግሬዎች ላይ ያነጣጠረ ስርዓት ለማፍረስ እና ለመበተን (ለማፍረስ) የታቀደ ሴራ ነው። ይላል ደብረጽዮን።

 

(እጅግ ይገርማል። ሰላምን 27 አመት ሲያውክ፤ (የትግራይን ሕዝብ ጭምር ሲታወክ መኖሩ የታወቀ ነው) ፕሮፌሰር አስራትን ሲያሸብር የነበረ ሰው ስለ ሰላም ሲሰብክ የመቀሌ ሕዝብ ይደገም ይደገም እያሉ ሲጮህለት ማየት ሕዝቡ ምን ያህል ደንዝዟል? ነኝ የምለው?)

 

 

5- ይህ ትዕግስተኛ ልባም እና ኩሩው የትግራይ ሕዝብ ትናንት በትግል ያሸነፋቸው ተሸናፊዎች እና ተስፈኞች የሆኑ የትምክህት ሃይሎች (እዚህ ላይ ንግግሩን አቋርጠው በጩኸት እና በጭብጨባ ድጋፍ ለደብረጽዮን ሲያስተጋቡ ይሰማል። በጩኸቱ ድጋፍ ምክንያት ሰሜታቸው እስኪበርድ ድረስ ለሰከነዶች ያህል ንግገሩን ቆም አድርጎ ሲጠብቃቸው፤ ሕዝቡይደገም!!”  ይደገም!!”  በማለት አዲስ አበቤዎች ለዶ/ አብይ የተለገሰለትን ኮፒ በመቅዳትይደገምብለው ስለጮሁ (የትምክህት ሃይላት እና ተሸናፊዎች..) የሚለው ንግገሩን ደግሞላቸዋል) በውሸት የትግራይን ሕዝብ ገናና ስሙን በማጥቆርላይ እና ታችእያሉ ይገኛሉእያለ አስጨብጭቦአቸዋል።

 

(ትግሬዎች ለምን ሌላ ቦታ የተደረገ እንደሚቀዱ አልገባኝም። ይደግም ሲባል እነሱም ያንን ቀድተው አብይን በደብረጽዮን ለመጫረት ይመስለኛል በደብረጽዮን ላይ ይደገም እያሉ ዕልል አሉ። ጎንደሬዎች የኤርትራን ኳስ ተጫዋጮች እንዲገጥሙ ሲጠይቁ እነሱም ተከትለው ያንኑ መሳይ ጥያቄ ለኤርትራ ስፖርት ሃላፊዎች ጥያቄ አቀረቡ። ምን እሚሉት ባህሪ እንደሆነ አልገባኝም?)

 

6- በተለይ በቅርቡ በሕዝባችን ደም የተገኘ ሕገመንግስታችን ለማፍረስ በመጣር፤ የአገራችን ክብር እና ሉኣላዊነት ጥያቄ ውስጥ የገባበት እና በዓለም ፊት በበጎ ሲታይ የነበረው የአገራችን ክብር የሚያበላሽ ሁኔታ ተፈጥሯል። በዚህ ምክንያት ሕገመንግሥታችንነ ለማፍረስ በሚጥሩ ላይ በማንነታቸው የደረሰባቸው ወገኖቻችን የተሰማንን ሃዘን እየገለጽን የተበላሸው ሰላማችንን ከተጎዱ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ሆነን በመደራጀት እንድንመክታቸው ሲያስፈልግ፤ የተጎዳችሁ ብሄረሰቦች.. ከጎናችሁ ቆመን የምንመክታቸው መሆናችንን ልንግልጽላችሁ እንወዳለን።  በየአካባቢው ሰለማችንን የሚዘርጉ ስርዓት እንዲያስይዛቸውጥሪአናቀርባለን። ይላል።

 

(ሚዲያዎቻቸው ሳይደብቁ እንደሚነግሩን ግምባር የሚፈጥሩት ደግሞ አጋር ከሚሉዋቸው ከቤን ሻንጉል እና ከእነ ሶማሌዎች ጋር እንደ እነ አብዲ ኢሌ የመሳሰሉትን ጋር ነው ግምባር ሊቆሙ የሚችሉት። ይህንን ለማረጋጋጥትግራይ ኦን ላይንየተባለውየአጋዝያን ግንጣላ አጀንዳ አኮብካቢ ድረገጽየሚተላለፉ መልዕክቶችን መመለክቱ ማስረጃ ነው)

 

 

  7- የትግራይ ሕዝብ የላቀ መስዋእትነት የከፈለ እንጂ የላቀ ጥቅም አልጠየቀም።ይላል። (“ይደገም!! በማለት ይህንን ንግግሩ አስደግመውታል)

 

(የላቀ ጥቅም ካነሳን ብዙ  ሊያወያየን ነው። እዚህ አልዘረዝረውም : ካሁን በፊት ገልጨዋለሁ።እስኪ የላቀ ጥቅም ካልፈለገ (ካልጠየቀ) አማራ ነን የሚሉ የወልቃይት፤ጠገዴን፤ጠለምትን፤ሰቲት ከወሎ ራያ ቆቦ ወልድያ አላማጣ ….ጥንታዊ ኗሪዎችን እያሳደደ : እየገደለ እያሰረ መሬታቸውን ነጥቆ ለትግሬዎች ሲያከፋፍል ሑሞራን ለትግራይ ሲሰጥ፤ ትላልቅ እርሻ ቦታዎች ለትግሬዎች ሲዘዋወር (ቆየት ብሎም ቤንሻንጉል- (የራስ ዳሸን ተራራ የካርታው ታሪክንም አትርሱ) ከዚህ ወዲያ የላቀ ጥቅም የት ይኖራል? ) የትግራይ ሕዝብ የጎንደር እና ወሎ መሬቶች ትግሬዎች ይስፈሩበት እዛው ያሉት አማራዎችም አማርኛ እንዳትናገሩ በትግርኛ ተማሩ ጻፉ እየተባሉ ግፍ ሲፈጸምባቸው ከዚያ ወዲያ የላቀ ተጠቃሚ መሆን ምን ሊኖር ይችላል?)

 

እዚህ ላይ ደብረጽዮን አንድ ትልቅ ነጥብ ንግግር ተናገሯል። እንዲህ ይላል፦

 

8- ያለን ዕድል ወይንም ተከባብረን መኖር ነው ወይንም መበታተን ነው።ብሏል ደብረጽዮን። አንድ መሪ ችግር ካለ ችግሩ እስኪወገድ ትግላችን ይቀጥላል (ለፍትሕ እንታገላለን) ብሎ ሕዝብን ያስተምራል ያጽናናል ጽናት ይሰጣል እንጂእንዲህ ካልሆነ” “በመታተንነው፡ ብሎ ሕዝብን ማስተማር፤ ለአገር መበታተን በር መክፈትና ተስፋ ቆራጭ ማህበረሰብን ማፍራት መልዕክቱ ምንድ ነው? ለምንስ እንዲህ ይታሰባል?

 

እነኚህ ሰዎች ሃገራዊ ስሜት ያልታጠቁ አካባቢያዊ አጀንዳ እንዳላቸው ግልጽ ማሳያ ነው። አስገራሚ ያደረገው ደግሞ የትግራይ ሕዝብ በዚህ የመበታታን ምርጫ እንደ ሌለው አማራጭ የተስማማ መሆኑን የሚያሳየን ሕዝቡ በጩኸት እና ለረዢም ጊዜ በሆሆታ፤ በዕልልታይደገም፤ ይደገምሲል ድጋፉን አስተጋብቷል። ትግሬዎች አሁንም እዛው አጥር ውስጥ አሉ ብለን እኔ እና ጥቂት ጓዶቼ ለማስገንዘብ የምንለፋው ይህ በቂ ማመላከቻ ማስረጃ ነው። በመበተን፤በመበታተንየሚሉ ቃላቶች ወያኔ ከመጣ ወዲህ የተለመደ ቃል ሆኖ አሁን እየቀጠለ ነው። በኢትዮጵያ መሪዎችም ሆነ በሌሎች  አገር መሪዎች ችግር ሲፈጠር መበተንን አይሰብኩም እንደ ምርጫም አያስተናግዱም። በዚህ ረገድ ወያኔ እና የትግራይ ሕዝብ ልዩ ነው።

 

 

ትግሬዎች ባሕርን ለማስዘጋት ኤርትራ ድረስ ሄደው ኢትዮጵያውያንን በጥይት በሞርታር በመትረየስ ረሽነዋል። ኢትዮጵያን ለመበተን ኤርትራ እንድትገነጠል ቀዳሚ ጠበቃዎች ሆነው እስከ የተባባሩት መንግሥታት ድርስ ሄደው ፈቃድ ሰጡ። ዛሬም የመበታተኑ ምርጫ በይደገም በጭብጨባ እና እልልታ ሲደገፍ መስማት የምንጠብቅ እና ስንለው የነበረ ቢሆንም በይፋ እንዲህ ይደሰቱበታል ብለን ግን አልጠበቅናቸውም ነበር። የራሱን ባንዴራ ሰርቶ አንቀጽ 39 በሕገ መንግሥት እንዲሰፍር የታገለ እና ያስተዋወቀ ሕዝብ ከዚህ ሌላ ምን ይጠበቅበታል ይባላል?

 

9- ሕዝባችን በትግሉ ወቅት ከባድ እና አስቸጋሪ የተጠላለፉ አስቸጋሪ ጋሬጣዎች እያሸነፈ ከድል ወደ ድል እየተሸጋገረ ድልን ያስመዘገበ የድል ባለቤት ነው። ብሎ ደብረጽዮን ሲነፋቸው (ሕዝቡ አሁንም በስሜት በዕልልታ ሰክሮ ሲጮህ ሲቦርቅ ይደመጣል)

 

  10- ታጋዮቻችን ወደ ኤርትራ በረሃየኤርትራ ሕዝብ ነፃነት በመቀበል ከኤርትራ   ሕዝብ ጎን ቆሟል። ወደ ኤርትራ በመሄድም ከኤርትራ ታጋዮች ጋር ሆነው መስዋዕት ከፍለው ባንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል፤ ሲል ደብረጽዮን  (አሁንም ሕዝቡ ይደገም በማለት እንዲደገም አድርጓል) ከዚያ በሗላም ኤርትራ ስደተኞችን ተቀብሎ ከፍተኛ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል። ሲላቸው ደብረጽዮን፤  ኢትዮጵያን ወግተው ለኤርትራ ያዳሉበትን ባንዳዊ ታሪካቸው እንደ ኩራት ቆጥረውትይደገምሲሉ ማድመጥ ይዘገንናል።

 

11-  የትግራይ ሕዝብ ዳግም ታሪክ ወደ እሚሰራበት ምዕራፍ ደርሰናል። ይላል።

 (ደብረጽዮን ዳግም ምዕራፍ የሚለውመበታተንወይንስየጦርነትምዕራፍ?

 

12- በጊዜአዊ ችግር ሳትደናቀፍ ወደ ፊት መርሽ!” ሲልም= ሕዝቡ ሰክሮ በዕልልታ ተቀብሎታል።

 

13- ዛሬም እንደጥንቱ አንድ ሆነን የማንሻገረውአስቸጋሪ ወንዝአይኖርም።

በማለት ድሮ የዘፈኑት የሜዳ መዝሙራቸው እና ዛሬም ብሔራዊ መዝሙር ያደረጉትን ይህንንየማንወጣው ታራራ እና የማንሻገረው ወንዝ የለምየሚለውን መዝሙራቸው ሲደግምላቸውበሆታ ስካር ጭብጨባውን አቅልጠውለታል። አሁንም ትግሬዎች የወያኔ ቀኝ እጆች እና የሚሉትን ሚያንጨበጭቡ ናቸው ስንል ከዚህ ማስረጃ በመነሳት ነው። የተገፋ ሕዝብ ገፊዎቹን በዕልልታ ካከበረ ከዚህ ወዲያ ክርክሩ የኔ ሳይሆን የናንተው ይሆናል። እኔ ጨርሻለሁ።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) getachre@aol.com