Tuesday, August 4, 2020

ከጥቂት ወራቶች በኋላ የሚከተለው አዲስ መጽሐፍ አሳትማለሁ፤ የጣሊያን ቅኝ ገዢነት በኢትዮጵያ በ1928 የትግራይ ቅኝ ገዢነትች በኢትዮጵያ ከ1983-2010 የኦሮሞ ቅኝ ገዢነት በኢትዮጵያ ከ2010 እስከ----


ከጥቂት ወራቶች በላ የሚከተለው አዲስ መጽሐፍ አሳትማለሁ፤

የጣሊያን ቅኝ ገዢነት በኢትዮጵያ በ1928
የትግራይ ቅኝ ገዢነትች በኢትዮጵያ ከ1983-2010
የኦሮሞ ቅኝ ገዢነት በኢትዮጵያ ከ2010 እስከ----

ቅጽ 1
Monday, August 04, 2020
የሚል ሦስቱንም ባንድነት ያጠቃለለ መጽሐፍ እያዘጋጀሁ ነኝ፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሦስቱም የተመሩበት የቅኝ ገዢነት አስተዳዳር መንትያነት ይተነተናል።

ትግሬዎችን በሚመለከት በሁለተኘው ረድፍ የተመለከተው ወደ 5 መጽሐፍት ስለጻፍኩ ብዙ አልሄድበትም። ትኩረቴ በሦስተኛ ረድፍ የተመለከተው በአብይ አሕመድ ዓሊ እየተመራ ያለው ፋሺስታዊ  ቅኝ ገዢነት በስፋት በማስረጃ  ይዘረዘራል። በዚህ ሰው መሪነት እና በመለስ ዜናዊ መሪነት በኢትዮጵያ ላይ የተሰነዘሩ እጅግ ዘግናኝ ጥቃቶች በአንዳንዱ እርምጃዎች ከጣሊያኖች ገዢነት የባሱ ጥቃቶች በሕዝባችን እና በሉዓላዊ ግዛታችን ላይ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። በዚህ ትንታኔ የውስጥ የቅኝ ገዢነትና የውጭ ወራሪ ገዢ ሃይል ያሉትን ተመሳሳይነት ይቀርባሉ።

ትናንተና አዲስ አባባ ከተማ የግድቡ ሁኔታ አስመልከቶ ሰላማዊ ሰልፍ ሲከናወን ኢትዮጵያን ከትግሬ ቅኝ ገዢነት ተረክቦ የቅኝ ገዢነት ባሕሪ እያስቀጠለ ያለው የሁለት ዓለም ሰላይ ሆኖ በድብቅ ብዙ አገራዊ ጉዳት ሲፈጽም የነበረ የኦሮሙማው የፋሺስቶች አስተዳዳር መሪ በአብይ አሕመድ ዓሊ (አውነተኛ ስሙ “አብዮት ካሳዬ በላይነህ” ) ትእዛዝ እና ዋስትና የተቀበሉ የኦሮሙሞ ርዕዮት ተከታይ ወታደሮች በሚያሳዝን ሁኔታ” በ1888 ዓ.ም በምኒሊክ መሪነት “ዓድዋ” እምባ ሰሎዳ ተራራ ላይ ጣልያኖችን አሸንፋ የተውለበለበቺው የወላጆቻችን ሰንደቅዓለማ በየከመኪኖቻቸው ላይ ለጥፈው ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ የነበሩትን አዲስ አበቤዎች ‘ሰንደቃላማቸውን እየተገነጠለ ጭቃ ላይ እንዲጎተት’ ያዘዘው እራሱ አብይ አሕመድ መሆኑን ስትመለከቱት ድርጊቱ የቅኝ ገዢዎች ዓይነተኛ ተግባር መሆኑን ይህ የተደጋገመ ጥቃት ለብዙ ጊዜ የተፈጸመ ድርጊታዊ እርምጃ አብይ አሕመድ በኢትዮጵያና በአማራ ላይ ያሳደረው ጥላቻ ከጣሊያኖችና ከወያኔዎች ያልተለየ ሥር የሰደደ መሆኑን ማሳያ ነው።

ቅኝ ገዢነት ከየት ይመነጫል ለምትሉ ጠያቂዎች ብትኖሩ  ምንጩ “ትምክሕተኛ አክራሪ ብሔረተኛነት በሚያመነጨው “ርዕዮተ እንቅስቃሴ” ይመነጫል። ለዚህ ነው ጣሊያኖችም ትግሬዎችም ኦሮሞዎችም በዚህ ርዕዮት በመቃኘት የሕዝብ ህይወት ምስቅልቅሉን በዋውጣት በታሪክ ተመዝግበው የምናያቸው።

ዓይናቸውና ሕሊናቸው የደደበባቸው ደደብ ተከታዮቹ ባይቀበሉትም፤ ወጣም ወረደ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ‘አብይ አሕመድ ልክ እንደ መለስ ዜናዊ” በታላቁ ፍትሕ ሰጪ በኢትዮጵያ አምላክ ውሳኔ ባጭሩ ይቀጫል። ኢትዮጵያ ከቅኝ ገዢዎች ነፃ ትሆናለች።
አመሰግናለሁ።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ ዋና አዘጋጅ)  


No comments: