Saturday, July 25, 2020

በኢሳያስ አፈወርቂ ትዕዛዝ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ተወካይ በሆነው በአብይ አሕመድ ዓሊ ተባባሪነት ኢትዮጵያዊ ትንታጉን ልደቱ አያሌውን አስሮ እያሰቃየው ነው! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) Saturday, July 25, 2020



በኢሳያስ አፈወርቂ  ትዕዛዝ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ተወካይ በሆነው በአብይ አሕመድ ዓሊ ተባባሪነት ኢትዮጵያዊ ትንታጉን ልደቱ አያሌውን አስሮ እያሰቃየው ነው!
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
Saturday, July 25, 2020



እንዴት አብይ አሕመድ ኢሳያስ ሥር የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ተወካይ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ግራ ሊገባችሁ ለምትችሉ አንዳንድ አንባቢዎች ይህንን የአብይ አሕመድ የራሱን ቃል ልጥቀስላችሁ፡
“ ኤርትራን በሚመለከት በተለያየ መድረክ ስናገር ከሰማችሁ ዛሬ “ኦፊሻሊ” ክቡር ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ሥራ  እንድሰራ ሥልጣን ስለሰጡኝ በየሄድኩበት ቦታ አቶ ኡሰማንን ወክየ የሥራ መዛባት እንዳይመስላችሁ!”   (አብይ አሕመድ)  ከኢሳያስ ፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲናገር በደምጽ ከቀዳሁት ማሕደር።


ይህንን ከተናገረ በሗላ ኢሳያስ በበኩሉ ስለ አብይ ውክልና እንዲህ ሲል አረጋግጦለታል፤
“በተደጋጋገሚ፤ በተደጋጋሚ ብያለሁ፤ ሊደረግ የሚገባው የሆነ ነገር ሲኖር ውክልና ሰጥነሃል። ወኪላችን አንተ ነህ” (ኢሳያስ አፈወርቂ)  ለተሸላሚው ለኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአብይ አሕመድ ያደረገው ንግግር በደምጽ ከቀዳሁት ማሕደር”


ከላይ አንዳደመጣችሁት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያደረግ የሚፈለገውን ነገር ሲኖር በወኪሉ በአብይ አሕመድ በኩል ይፈጸማል ማለት ነው። በውክልናው መሰረት አንጀቴን እጅግ ያዘነለትን ወንድሜን ልደቱ አያሌውን ሊገድለው ባለመቻሉ በትዕዛዙ መሰረት እስርቤት ከትቶታል። ይህ ማፈሪያና ወራዳ ግለሰብ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ አገር እጁ ውስጥ ገብታ ኢትዮጵያን በክብር ከመምራት ይልቅ ኢትዮጵያውያንን በመጨፍጨፍ እጁን በደም የጨቀየን ግለሰብ ወኪል ነኝ ብሎ መሳቂያ አድርጎናል። ይህ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ አገር የመሪነት ባሕሪ የለውም ስንል የነበረውም ለዚህ ነው።  ስለዚህ ኢትዮጵያን እየመራት ያለው ኢሳያስ ሆኖ በውክልና- አብይ አሕመድ እየተመራች ነው  የምንለው ለዚህ ነው።  የትግርኛ ተናጋሪዎች አንድ አስገራሚ ነገር ስንታዘብ የምንለው ነገር አለን  ‘ን ኣዳም ገረሞ” (ለአዳም/ ለዓለም ሕዝብ ያስገረመ)። ልደቱ አያሌው ለምን እንዳሰረው አሁን ግልጽ እንደሚሆንላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።


ይህ ታላቅዋን ኢትዮጵያ በድንገት እጁ ውስጥ የገባች አገር አንዲህ እያዋረዳት ያለውን ድሮ ከነ ተስፋየ ገብረአብ ሆኖ ለኦነግና ለኢሳያስ ምስጢር እያሳለፈ ሲሰልል የነበረውን ወንጀል   በመቀጠል የኢሳያስ የስለላ ውክልናውን በግሃድ አስታውቋል።በዚህ ውክልናው ለኢትዮጵያ መቅሰፍት ሆኗታል። በሁለት አመት የሥልጣን ጊዜው “የሲኦል በሮችን” ከፍቶ “የሲኦል ጭራቆችን” አስገብቶ አገሪቷን ለዋይታ ለጭፍጨፋ እና ለስቃይ ዳርጓታል። ጦርነት ሲነሳም ሆነ በተለያዩ መንገዶች “የሕዝብ ዕልቂት” ሲፈጸም ሥልጣንን ለሚጎመዡ እንደ አብይ አህመድ የመሳሰሉ “ሥግብግብ” ፍጡራን የሥልጣን ማጠናከሪያ እና የዝና መድመቂያቸው ያደርጉታል። ይህንን ተንተርሶ የሚቃወማቸው ተቃዋሚን በማሰር በመግደል ይጠቀሙበታል። አብይ አሕመድ ልደቱን ለመግደል የነበረው ሴራም ሆነ ለማሰር የሄደበት ርቀትም ይህንኑን አጋጣሚ በመጠቀም ነው።


ሰው ይሳሳትል፤ ከስሕተቱ ይታረማል። በዚህ መልክ ልደቱ ላይ የነበረኝ አንዳንድ ትችቶች ከብዙ አመታት ጀምሮ ስተቸው የነበረ እና ስቃወመው የነበሩ አቋሞቹን ይቅርታ ጠይቆ በአዲስ መንፈስ ተነስቶ በሚገርም ሁኔታ ባለው ተፈጥሮአዊ ብልህነት የአብይ አሕመድን  ሥርዓት በመቃወም ኮለኔሉ “የለበሰው የአፓርታይድ  ካባ” በመግፈፍ እርቃኑን ስላስቀረው “የተቃውሞ ድምፅ ሲሰማ መንፈሱ ተሎ የሚረበሸው”  የእነ ተስፋየ ገብረአብ የስለላ መረብ አባል የነበረው፤የሁለት አለም ሰው ሰላይ አብይ አሕመድ “ልደቱን” በኢሳያስ ትዕዛዝ ለመግደል ሲሞክር ‘ትንታጉ” ልደቱ ተሎ ስለነቃ የተከታታዮቹን የመኪና ታርጋ ጽፎ እየተከታተሉት እንደሆነ ለሕዝብ ግልጽ በማድረጉ ሳይገድለው ሲቀር ለእስር ዳረገው።


ለዚህ ሁሉ በር ከፋቾችና ትግሉን ያስጠለፉት “ተደማሪ ተቃዋሚ የሚባሉት” የነልደቱን መታሰር ለአፓርታይዱ መሪ፤ ለአብይ አሕመድ “መደላድል ማዳበሪያ” እንዲሆነው ድጋፍ እየሰጡ አብይ አያስርም አይገደልም ሲሉ የነበሩት ቀንደኛ ተጠያቂዎች ናቸው።


 በድፍኑ ከመሄድ ለአንባቢዎቼ  መጥቀስ ስለሚያስፈልገኝ  ከተደማሪ ተቃዋሚ የአብይ አሕመድ አዲሱ “መናፍህ’ ከሆነው አንደኛው “አማራ ለብቻ ተለይቶ የተጠቃበት ጊዜ የለም” እያለ በዋሾነቱ ለሚታወቀው “የብርሃኑ ነጋ” አዳማቂ የኢዜማው “አንዱአለም አራጌ” የመሳሰሉትን በዚህ ወቅት መጥቀስ አስፈላጊ ነው።


አንዱአለም  አገዛዙን የደገፈበትን አሳፋሪ ቃለ መጠይቁን ልጥቀስና ልደቱ እንደ አንዱአለም አራጌ “የአፓርታይድ መናፍህ” ባለመሆኑ ለእስርና ለግድያ ሴራ ተዳርጓል። አንዱአለም አብይን ብቻ ሳይሆን ጸረ አማራው ኦነጉ የኦሮሞው ክልል መሪ ሽመልስ የተባለውንም ሲደግፍ አድምጠናል።
'

 ብርቱዎቹ ዜጎቻችን ይህንን “የኦሮሙማው አፓርታይድ” ሲጋፈጡ ተደማሪው አንዱአለም አራጌ የሚከተለውን መናፍህ ሲያቦካ ነበር፡

አንዱአለም አራጌ እንዲህ ይላል፦

“ድሮ የነበረው ሰራዊት ፤ ፖሊስ እንዳለ አለ፤ “ስትራክቸሩ” አለ፤ ነገር ግን ሰዎች እንደፈለጉት ሃሳባቸውን በነፃ ይገልፃሉ፤ እንደ ድሮ የሚገድላቸው የለም፤ የሚያስራቸው የለም።”” እያለ ከዋሸ በሗላ ሕዝቡን እንዲህ ሲወነጅል ላስሰማችሁ እና ወደ ሚቀጥለው ልግባ፤
አንዲህ ይላል፡

“አንገቱን ለገዢዎች ጫማ የሚያመቻች ሕዝብ ባለበት አገር ነፃ መንግሥት ሊኖር አይችልም።” 
እንግዲህ ይህ ማፈሪያ ከድሮ ጀግንነቱ ተለውጦ ወደ ሎሌለነት ተገልብጦ “አንገቱን ለገዢዎች የሚያመቻች ሕዝብ ስላለ እንጂ የአብይ አሕመድ ጥፋት አይደለም” በማለት ጥፋቱ የሕዝብ መሆኑን ይጠቅሳል። ንግግሩ ልክ ቢሆንም፤  ልደቱ፤ ይልቃል፤ አስቴር፤ እስክንደር… ወዘተ,፣ ወዘተ, የመሳሰሉ ዜጎች  “አንገታችንን ለገዢው ለአብይ አሕመድ ጫማ አናመቻችም ስላሉ ይኼው “አብይ አሕመድ” አስሮ እየደበደበ ፤ በርሃብ እያሰቃየ ፤ ከኮረና ቫይረስ ታማሚ እስረኞች ጋር አስሮ ሊገድላቸው ወስኗል።

እንግዲህ “አንገቴን ለአብይ አሕመድ እና አንደኛ ደረጃ ጠላት ለሆነው ለኢሳያስ አፈወርቂ ጫማ አላመቻችም ብሎ በግልጽ “የኩሊው የአብይ አሕመድ” አለቃ “ኢሳያስ አፈወርቂን” በመቃወሙ “አለቃየን ደፍርክ” ብሎ “አዲስ አባባ ውስጥ እንደ “አሸን የፈሉት የኤርትራ አፋኝ ነብሰ ገዳዮችን” አሰማርቶ ልደቱ አያሌውን ሊያስገድለው ሲከታተለው እንደነበረና “ልደቱም የተከታታዮቹ ዕቅድ ወዲያውኑ ስለደረሰባቸው “የመኪናዋ መለያ ቁጥር”  መዝግቦ ልደቱ ለሕዝብ ይፋ አድርጎ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የነብሰገደዳዮች ስብስብ ጠ/ሚኒሰትር ነኝ የሚለን አብይ አሕመድ “አለቃውን ኢሳያስን” ስለተቃወመበት “በክርክር የማይችለውን” ልደቱ አያሌውን “እስር ቤት” አስገብቶ ምክንያት እያሳበበ በተፈጥሮም ሆነ በመርዝ ወይንም ልክ እንደ ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት “በኮረና ቫይረስ” እስረኞች እንዲገናኝ በማድረግ ባጭር ዐድሜ ይህ ወጣት ፖለቲከኛ ሊቀጨው ይችላል። በዚህ አጋጣሚ ይኼው “ልደቱ አያሌውም ይታሰር እንጂ ጠበሉን ይድረሰው” እያሉ በየፌስ ቡክ እየለጠፉ “ልደቱን የሚያክል ወጣት ፖለቲከኛን በፋሺስቶች እጅ እንዲወድቅ” መሪያቸውን አብይ አሕመድን ሲወተውቱት የነበሩ ሻዕቢያዎች እና የአብይ ተከታይ ኢትዮጵያዊያን አነሆ መሪያቸው የሎሌዎቹን ውትወታ ሰምቶ ልደቱን አስሮታል። የልደቱን መታሰር የኛ መታሰር ነውና በመታሰራችን እነሆ “አንኳን ደስ አላችሁ” እላችሗለሁ።

እንደምታውቁት ‘ጥርቅም የነብሰገዳዮች መንግሥት’ የኮሮና ቫይረስን ለመጋፈጥ ሰፊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅእና “የመግዛት ሀይል” እንዲሰጠው በአባላቱ አማካይነት በህግ አውጪ ሎሌዎቹ በኩል ሰፊ ዕድል ካገኘ ወዲህ የመብት ተሟጋቾች፤ፖለቲከኞችና የተቃዋሚ አባሎች ለመቅጣትና “የሕዝብ ሚዲያ/ቲቪ/ቴሌፎን መስመሮችን” በበላይነት ተቆጣጥሮ ያሻውን መናፍህ (ቅስቀሳ) እያሰራጨ  ይገኛል። አሻንጉሊቱ የሕግ አውጭውና የሕግ ተቀወዋም ተብየው አካልም እንዲሁ “ከአፓርታይዱ ስርዓት ጋር ወግኖ የውሸት መረጃ አስደግፎ”፡የሀሰት ውንጀላ በማሰራጨት በልደቱ ላይ ዘምቷል።

አብይ ወደ አገር አስገብቶ ለስሙ “ሂዩማን ራይትስ” ጉዳይ ተከታተሉ ብሎ በሹመት ወደ አገር ያስገባቸው እንደ እነ “ዶ/ር ዳኒኤል በቀለ” የመሳሰሉ ማፈሪያዎችም ሁለት አመት ሙሉ የገዢው መገልገያ ከመሆን አልቦዘኑም፡፡ሥልጣናቸው ወርውረው ወደ ነበሩበት ውጭ አገር ተመልሰው “ለዓለም ሕግ ጽ/ቤቶች የኮለኔሉን አፓርታይዳዊ ጭካኔ” ለማጋለጥ  ፍላጎት አላሳዩም። አሁንም ቅምጦች ሆነው ሲዘባርቁ እያደመጥን ነው።

“የነብሰ ገዳዮች ስብስብ” ጠ/ሚኒስትር ድምፅ በመሆን የሚያገለግሉ ውጭ አገር የሚገኙ ደጋፊዎቹም በመሪያቸው አብይ አሕመድ ላይ ትችት ወይንም ምላሽን የሚሰነዘር ጋዜጠኛም ሆነ የፖለቲካ መሪ  በሓሰተኛ ወንጀል ተከስሶ ሲንገላታ/ስትነገላታ/ አይተው “ደስታቸውን የሚገልጹ ድኩማን ፍጡራን እየተባዙ ነው።

ብልጽግና ብሎ ራሱን የሰየመው ይህ የወንጀለኞች ስብስብ ፓርቲ “አገሪቱን በቁጥጥር ስር አውሏታል” ፣ ይህም ማለት የተቃዋሚ ዕጩ ዘመቻ ማካሄድ አይችልም ፡፡ ነገር ግን በቁጥጥሩ መዳፍ የበሰባቸው የአፓርታይዱ የሕግ እና የፍትህ ዘርፎችን ፤ የዜና ማሰራ የቴሌቪዥን ስርጭቶችና ቴሌፎን መልዕክቶችን እየተጠቀመ የፓርቲው ‘መናፍህ’ በስፋት እያካሄደ ነው፡፡


የአብይ አሕመድ የክፉ አዕምሮን ውስጣዊ ስራዎች ልደቱን የሚያክል ወጣት በማሰር አብይና ሥርኣቱ የወሮበላዎች የዱርየዎች የመንጋ ሥርዓት መሆኑን አሳይቷል። በ 1970 ዎቹ አመተምህርት ወቅት የኡጋንዳ ጨካኝ መሪ የነበረው ኢዲ አሚን ዳዳ ፣የገደላቸው የፖለቲካ ጠላቶቹ ጭንቅላቶች “በማቀዝቀዣው” ውስጥ እንደቆየና “የሰውን ሥጋ ለመብላት እንደሞከረ” ተናግሯል፡ ሲቀምሰው ግን “በጣም ጨው ጨው” የሚል “ጫውማ” ሆኖ  ማግኘቱን ሲናገር ዓለምን ሁሉ በድንጋጤ ያስገባ ክስተት አንደነበር ያነበብኩት መጽሐፍ  ይገልጻል፡፡ አብይ አሕመድ እንደ እነ ኢዲሚን ባይሆሆንም የተቃወሙትን ሰላማዊዎችን በማሰር በኮረና በሽታ እንደለከፉ በማድረግና የሰው ስጋ የሚበሉ ግብረሰዶማውያን የኦነግ ተዋጊዎችን ያለ ምንም የመቆጣጠሪያ ውል “ወደ አገር አስገብቶ” ኦነግን የሚቃወም ሰው “ግብረሰዶም እንደሚፈጸምነትና “የገዛ ሥጋው” ተቆርጦ በማስገደድ  እንዲበላ ተደርጓል የሚል ከአፓርታይዱ የኦሮሞ ክልል ባለሥልጣኖች  ሲናገሩ አድምጠናል (አውድዮውም አለ)። ሥጋታችን የከፋ የሚያደርገው የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ወኪል በሆነው አብይ አሕመድ ትዕዛዝ ኦነጎች በሚያስተዳድሩት የፍትሕ ተቋማትና በሚቆጣጠርዋቸው እስርቤቶች ውስጥ የተወረወረው  “ኢትዮጵያዊው ዜጋችን ልደቱ አያሌው” ከዚህ በሗላ ምን እንደሚደርሰው ስጋታችን እጅግ ይጨምራል። ተቃውሞኣችን ግን ይቀጥላል!
ትንታጉ ወንድሜ ልደቱ አያሌው ዛሬ ግን ከጎንህ ቆሜአለሁ!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ የኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ




Thursday, July 23, 2020


በዚህ ርዕስ ሁለት ርዕሶችን ታያለችሁ፤
Frids, July 23, 2020
ከ Ethiopian Semay አዘጋጅ ክፍል የሚከተሉትን 2 ጉዳዮች እንድታነቡ ይጋብዛል።

(1ኛው) ትችት-- “እንዲህ ማለት ከቀጠላችሁ ካላችሁ” .. “ሳንወድ ወደ ወያኔ እገባለሁ” እያለ የሚዝተው “የፈንቅል ሊቀመንበር ተብየው በአብይ አሕመድ የፕሮፓጋንዳ ችሮታ ሥር የተጠለለው ታሪክ ዘባራቂው “የማነ ንጉሡ” ስለ አጼ ምንሊክና ዮሓንስ (አሉላ) እያነጻጸረ የዘባረቀውን የተምታታ የታሪክ ትንተና መልስ የተጻፈ በትዕግስት አንብቡት’
(2) ትችት= ታዋቂው ወዳጄ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ ሞቷል ተብሎ በሃሰት በዘሓበሻ ድረገጽ የተለጠፈው ጉዳይ፤ ከዚያም የድረገጹ ባለቤት ፤”አንሳው” ሲባል ባለማንሳቱ ተለጥፎ እስከ ዛሬም እየተነበበ እንደሆነ ወዳጄ “ዳግማዊ ጉዱ ካሳ” ይህንን እንድለጥፍለት አስቸኳይ ጽሑፍ ልኮልኛል። አነብቡት!

አፄ ምኒልክንና አማራን መሳደብና ማዋረድ - የዘመናችን ፖለቲካ የይለፍ ቃል!
ጻሐፊ
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

በተለይ ካለፉት 30 ዓመታት ወዲህ ያለውን የሀገራችንን ፖለቲካ በጥልቀትም ሆነ በግርድፉ ለሚመለከት ታዛቢ በዚሁ በተግማማው ፖለቲካችን ውስጥ ለይስሙላም ቢሆን “ኢትዮጵያ” እየተባለች በምትጠራው ሀገራችን ግዘፍ ነስቶ የምናየው ትልቅ ነገር በፓርቲዎችና ድርጅቶች ማኒፌስቶና በአቋም ደረጃም ጭምር አማራን ከኢትዮጵያ ጋር ደርቦ መጥላት፣ መሳደብና ማንቋሸሽ ነው፡፡ ይህን ፋሽን ያልተከተለ ፖለቲከኛ የሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ አድባር አትቀበለውም (ይመስለኛል)፡፡

ይህን እንድል በሩን ወለል አድርጎ የከፈተልኝ አንድ በፍጹም ያልጠበቅሁት ሰሞነኛ ጉዳይ ነው - በጣም እወደውና እንዲቀናው እመኝለት እጸልይለትም ከነበረ ብላቴና የወጣ አስጸያፊ ቃል ፖለቲካን በጥቅሉ ይበልጥ አምርሬ እንድጠየፈው ማድረጉን የምገልጽላችሁ በከፍኛ ሀዘን ነው፡፡

መሬት ትቅለለውና ፀረ-ኢትዮጵያው መለስ ዜናዊ አንድ ወቅት “የአማራ ተረትና የሶማሌ በጀት ነው የበጠበጠኝ” ብሎ እንደቀለደ በወቅቱ ሰምተናል፡፡ ያሻችሁን በሉኝ እንጂ እኔም  ልተርት ነው፡፡ “ ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ” እንላለን፡፡ “መቼ መጣሽ ሙሽራ፣ መቼ ቆረጠምሽ ሽምብራ”ም እንላለን፡፡ ነገር በሦስት ይጸናልና “በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም” ብዬ ልሰልስና ወደመነሻየ ልግባ፡፡
የፈንቀል ተብዬው እንቅስቃሴ መሪ የተባለ ከወያኔ ኮረጆ የወጣ ደቀ-ሕወሓት አንድ የሚዘገንን ነገር ሲናገር በዐይኔ በብረቱ እየሰማሁ በጆሮየ በታምቡሩ አዳመጥኩት፡፡ ዲጂታል ወያኔ አመሳስለው ያን መልእክት አስተላልፈውት እንደሆነ ብዬም ደጋግሜ በመስማትና በማየት ለማጣራት ሞከርኩ፡፡ የልጁ የራሱ ነው፡፡ በከንፈር እንቅስቃሴና በድምፁ መለየት ይቻላል፡፡

ይህ ልጅ የሚለው አፄ ምኒልክ ኢትዮጵያን ለባዕዳን የሸጡና ሀገርን የከፋፈሉ ባንዳ ናቸው ነው - በአንተታ እየዘረጠጠ ለዚያውም  - የስሜት ሕዋሳቴን ተጠራጠርኳቸው፡፡ በርግጥም በዚህች ሀገራችን የገባ ሾተላይ ሥር የሰደደ መሆኑ ገባኝ፡፡ ይሄ አንድ መስከረም ሳይጠባ ስንቱን ጉዳጉድ እያሰማን እንደሆነ እንግዲህ ልብ በሉ፡፡ እነዚህን የየብሔር ብሔረሰቡን ልጆች ምን እየጋቱና እየቀለቡ እንዳሳደጓቸው ግልጽ ሆነልኝ፡፡ የዚህች ሀገር በሽታዎች መፍትሔ በእግዜር እጅ ብቻ መሆኑንም ተገነዘብኩ፡፡

ዝርዝሩን ለመመልከት ዩቲዩብ ወይም ፌስቡክ ገብታችሁ እዩት፡፡ የማነ የሚሉት ሣልሣዊ ወያኔ አፄ ምኒልክን  ቂጣ በቆረጠ  ስድ አፉ ሙልጭ አድርጎ ይሳደባል፡፡

የማያድግ ልጅ በአባቱ ብልት ይጫወታል ይባላል - መግቢያየ አካባቢ ዘንግቼያት ነበር አንተዬ! እኔ ስጠረጥር “ወደ ሀገር እንድትገባና ትግሉ እንዲሰምርልህ ከፈለግህ በአማራ ታርጋ የሚታወቀውን ምኒልክን አጥረግርገህ ስደብ፤ አማራንም በእግረ መንገድ ፈሪና ቦቅቧቃ እያልክ ሞልጨው፡፡ ከዚያ በኋላ እኛ እንደግፍሃለን...” ያለው ወገን ሳይኖር ልክ እንደዚህ ደረቱን ነፍቶ የጥቁሮችን አባት ባልተሳደበ ነበር፡፡ የሚገርመኝ ሌላው ቢቀር አማራን እወክለዋለሁ የሚለው በቁልምጫ ስሙ አዴፓ የሚባለው ነፈዝ የሆዳሞች ጥርቅም አንድም ነገር ትንፍሽ አለማለቱ ነው፡፡ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን አፉ ተለጉሞ ከጡት አባቶቹ የሚጣልለትን ፉርሽካና ‹አልፋ-አልፋ› በማሞስካት ሥራ ላይ ተጠምዷል ማለት ነው፡፡ እንዲህ ያሉ ስድ አፎችን ከአለቃው ጋር በመመካከር ጭምር - ለራሱ ፖለቲካዊ ቅቡልነትም ሲል ቢያንስ አነስተኛ መግለጫ ቢያወጣና “አለሁ ወንዱ! ማናባቱ ነው አማራን የሚነካ!” ቢል ከዘመኑ የዘረኝነት ቅኝት አኳያ መልካም ነበር፡፡ ዳሩ የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም - ሞኝነቴ፡፡

ሀጫሉና የማነ ኦነግንና ሕወሓትን በመወከል እንዲህ እያሳቁን ነው፡፡ ተራው የትግራይና የኦሮሞ ሕዝብ ግን ይህን መሰሉን ቅዠትና የባለጌዎች ዘለፋ እያዬ ጉድ ከማለት ውጪ የአብዛኛውን ድጋፍ ይሰጣል ተብሎ አይገመትም፡፡ የሞተ ሰው ዕረፍት በሚያጣባትና ዐፅም እንኳን በመቃብሩ አርፎ እንዳይተኛ በሰላማዊ ሰልፍ ሳይቀር ደጋግሞ በሚገደልባት ሀገር መኖር አሳፋሪም፣ አስደንጋጭም ነው፡፡ አክራሪ ኦሮሞዎችንና ብልጣብልጥ ወያኔዎችን ለማስደሰት ሲሉ አፄ ምኒልክ አንዴ ተነስተው ለሁለተኛ ጊዜ ቢሞቱ እንዴት በተገላገልን ነበር!

ለማንኛውም የማነ ንጉሱ የተባልክ የወያኔ ጥርብ ድንጋይ ይቅናህ፡፡ በርታ፡፡ ቃላትን እየተበዳደርክና እየተዋስክም ቢሆን በጀመርከው መንገድ ንጉሥ ምኒልክንም ሆነ አማራን ሞልጫቸው፡፡ ምን ያመጣሉ? ለጊዜው ሁሉም አልጋ ባልጋ ነው፡፡ ከቤተ መንግሥት እስከ ደደቢት ያንተን ሃሳብ የሚጋራና አይዞህ የሚል ነው፡፡ ቀን እስኪዘምብህ በርታልን፡፡ ወፌ ቆመች ስንልህ ባንዴ ዘጭ በማለትህ ግን አሁንም ልተርትልህ “የማያድግ ልጅ ካካው ብዙ ነው” እንዲሉ ሆነሃልና ለፓምፐርሱ ኦነግንና ሕወሓትን በደምብ ጠጋ በል - ያምበሸብሹሃል፡፡

በመጨረሻም፡-

ከመቼው ነግቶልኝ ይህችን ማስታወሻ ጽፌ በላክሁ ብዬ አሥሬ ሰዓቴን ሳይ እንደተለመደው ድረ ገፆችን መጎብኘት ጀመርኩ፡፡ ዘሀበሻ ላይ ስደርስ ባየሁት አንድ ዜና ፈገግ አልኩና እንደመሳቅ ሲቃጣኝ ባልተቤቴ “ምን ሆንክ?” አለችኝ፡፡ እኔም “ባለቤትሽ ሞቶ አንቺ እዚህ ተጋድመሽ እንቅልፍሽን ትለጥጫለሽ!” ስል አፌዝኩባት፡፡ አልገባትም፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- በአባቴ ስም በ“ጉዱ ካሣ” የብዕር ስም ይጠራ የነበረ አለማየሁ በላይነህ የሚባል ወንድማችን ሰሞኑን ከዚህች ዓለም ተሰናብቷል፤ ያም ዜና በኢካድፍ ወጥቷል፡፡ ያንን ዜና ቀደም ሲል ከኢካድፎረም አንብቤ በአስተያየት መስጫውም የተሰማኝን ገልጬ አልፌያለሁ፡፡ ዛሬ ግን የዘሀበሻ ድረ ገፅ አዘጋጆች ያ ሰው እኔ መስያቸው የሀዘን መግለጫ አውጥተው አየሁ - ያቀንየለይ፤ ገለቶማ፤ አመሰግናለሁ - ብሞትም እንዲሁ ነበርና ሳልሞት “ዓለሜን አየሁ”፡፡ አንድ ሰው ሳይሞት የሀዘን መግለጫዎችን የማየት ዕድል ካለው አንዱ እኔ መሆን አለብኝ፡፡ በአንድ በኩል ደስ አለኝ፡፡ በሌላ በኩል ... የምን በሌላ በኩል ነው ... ኧረ ምንም አልተሰማኝም በሌላ በኩል፡፡

ወንድሞቼ እነ አባዊርቱና ገብረ ሕይወት እነኩኒ ያደረሱኝን የሀዘን መግለጫ አንብቤያለሁ፤ በገነት ወይም በገሃነም ሆኜ ሳይሆን እዚችው ጉደኛዋ አዲስ አበባና ፊንፊኔ ውስጥ ሆኜ፡፡ ምሥጋናየ እጅግ ላቅ ያለ ነው፡፡

ለፈገግታ ያህል፡- አንድ ክፉ ፊታውራሪ ይሁኑ ደጃዝማች ነበሩ አሉ፡፡ ከክፋታቸው የተነሣ ቀብራቸው እንደማያምር ይጠራጠሩ ነበር አሉ፡፡ አንድ ወቅት ታዲያ “ማን እቀብሬ ላይ እንደሚገኝ፣ ማን እንደማይገኝ፣ ማን ከልቡ እንደሚያለቅስ... ለማወቅ እፈልጋለሁና አሁን ሞቻለሁ አሉ ... እንደሞትኩ ቁጠሩና አልቅሱ፤ ከፍኑኝናም ወደ መቃብር ውሰዱኝ፡፡ በደምብ መመልከት እንድችል ታዲያ ለዐይኖቼ ቀዳዳ ነገር አብጁልኝ፡፡ ሳትቀብሩኝ ግን የውሸት መሆኑን ነግረን ለቀስተኛውን እናሰናብታለን፡፡” ብለው ለቤተሰባቸው ነገሩ አሉ፡፡ እንዳሉት ሁሉ ሆነ፡፡ ሰውዬው እንደጠረጠሩት የተገኘው ለቀስተኛ በጣት የሚቆጠር ሆነና የራሳቸውን ዕርም አወጡ ይባላል - የቁም ሞቸታውን፡፡

አንድ ልጨምር፤ በኮሮና ጊዜ የት ትሄዳለህ ዐርፈህ አንብብ፡፡ ... አንድ መንደር ውስጥ እንደዚሁ አንድ እጅግ ክፉ ሰው ነበር፡፡ መንደርተኛው ሁሉ አደመበትና ሳይሞት እንደሞተ ተቆጥሮ ተከፍኖ እንዲቀበር ተወሰነ፡፡ ልቅሶው ተጀመረ፡፡ የሌላ መንደር ሰው ወደ አስከሬን ዝር እንዳይል ሠፈርተኛው ቃል ተገባብቶ እየጠበቀ ነው፡፡ መንደርተኛው ብቻ አስከሬኑን እየተቀባበለ ይዞት ወደ ቤተ ክርስቲያን ነጎደ፡፡ ሰውዬው ሣጥኑ ውስጥ ሆኖ እንዳልሞተ ቢጮህ ቢያጓራ ማን ሰምቶት፡፡ ተስፋ ቆርጦ ዝም ብሎ ሳለ በምክክሩ ያልበሩ አንድ የሕግ ጠበቃ አስከሬን ሸክሙን ለማገዝ ሲቀበሉ ይሰማል፡፡ ያኔ እርሳቸው ቢረዱኝ ብሎ ስማቸውን በመጥራት “ኧረ አያ እንቶኔ፣ መንደሩ አድሞብኝ በቁሜ ሊቀብረኝ ነው፤ ውሸታቸውን ነው አልትሞኩም...” ቢላቸው ሬሣውን ለሌላ ሰው ቀበል ያደርጉና የሕግ ማስታወሻና ብዕር ከኪሳቸው በማውጣት “ምሥክር አለህ?” ብለው ይጠይቁታል፡፡ ማንን ያምጣ! ተቀበረና ዐረፈው፡፡ ...

እንዲህ ያለ ነገር ያጋጥማል፡፡ ከመዝነኛነት ግን አያልፍም፡፡ ላዘናችሁልኝ እግዜር ይስጥልኝ - ክስተቱ “ውለታ መላሽ ያድርገኝ” የማያስብል በመሆኑ “በደስታ ልመልሰው” ልበል፡፡ ለተደሰታችሁ ግን ምንም ማድረግ አልችልም፤ አልሞትኩም፡፡ ሞት ደግሞ የሁላችንም ርስት ናትና መቼ እንደምትመጣ ሳታሳውቀን አንድ ቀን ላፍ ታደርገናለች፡፡ መጽሐፉም “በጧት አመጣ፣ በቀትር እመጣ፣ በማታ እመጣ አታውቁምና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ” ነው የሚለው፡፡ ስለዚህ የኛ ፋንታ ተዘጋጅቶ መጠበቅ ነው፡፡ በሰው ሞትም መደሰት ከንቱነት ነው፡፡ ማንም ለማይቀርበት ነገር ትርፉ ትዝብት ነውና በቁም እያለን ለመማማር መትጋት ጥሩ ነው፡፡        

ከዚህ በታ ያስቀመጥኩት አስተያየት ኢካድፍ ላይ ያስቀመጥኩትና በድረገፁ አዘጋጆች ከፀደቀ በኋላ የተለጠፈ ነው፡፡

https://secure.gravatar.com/avatar/791b32d5d0efef60a0a2ab12c4096e1f?s=45&d=https%3A%2F%2Fecadforum.com%2FAmharic%2Fwp-content%2Fuploads%2F2015%2F11%2FECADF_Gravatar.png&r=g     ዳግማዊ ጉዱ ካሣ


ነፍሱን በገነት ያኑርልን፤ የልፋቱን ውጤት ሳያይ መሰናበቱ ቢያሥከፋም ሁላችንም ወደማንቀርበት ቀድሞን መሄዱ እንግዳ ነገር ባለመሆኑ ለቤተሰብና ዘመድ አዝማድ እንዲሁም ጓደኞቹና የሙያ አጋሮቹ መጽናናትን እመኛለሁ።

“ጃዋርና እስክንድር እየተናበቡ ሀገር ለማተራመስ ይሠራሉ” - ወ/ሮ ዐቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Posted - Ethiopian Semay


ጃዋርና እስክንድር እየተናበቡ ሀገር ለማተራመስ ይሠራሉ” - ወ/ሮ ዐቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
Posted - Ethiopian Semay
የወ/ሮ አዳነች ይህን ዓይነቱ መንግሥታዊ ንግግር የዶ/ር አቢይን ከባልደራስ ጋር የሚያደርገውን ጦርነት ያወጀበትን የቁጣ ንግግር የተንተራሰ ለመሆኑ ዋቢ መጥቀስ አያሻም - እየተናበቡ ሀገርን በማፍረስ ላይ የሚገኙትስ እነሱ ራሳቸው ናቸው፡፡ ይህ ንግግር በተውኔቱ ዓለም ቢገለጽ ደምበኛ ሼክስፒራዊ ትራጂ ኮሜዲ ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሽል መንጣሪዎች እየመሯት ሀገራችን ወደገደል እንጂ ወደ ብልጽግናና ዕድገት አታመራም፡፡ ምኞት ግን አይከለከልም - ሊያውም ከማስመሰል የራቀ ቀናና ትክክለኛ ምኞት ካለ፡፡

ጥቅምት 2012ዓ.ም ከ100 በላይ ንጹሓን አማሮችንና ለዘብተኛ የኦሮሞ ክርስቲያኖችን እንዲሁምና ምናልባትም ከሌሎች ነገዶችም የተወሰኑ ዕድለቢሶችን  ያስጨፈጨፈው በወቅቱ “ሁለተኛው የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር” ጃዋር መሀመድ በመንግሥት ዕቅፍ ውስጥ ሆኖ ያሻውን ሲያዝዝና ሲናዝ ለተመለከተ ቅን ታዛቢ በቅርቡ የአክራሪ ኦሮሞዎች አማራ ላይ ባደረሱት ዕልቂትና የንብረት ውድመት ሳቢያ “ራሳችሁን ጠብቁ፤ ተደራጅታችሁ አካባቢያችሁን ከጥቃት ታደጉ...” ብሎ አዲስ አበባን ከውድመት ለመከላከል የሞከረን አንድ ዜጋ በመናጆነት ማሰር በርግጥም የክፍለ ዘመኑ ቧልታይና ድንቃይ የልጆች ትያትር የሚመስል አስቂኝ ግን  መራር ቀልድ ነው፡፡ እንደዚህ ያለ ዐይን ያወጣ መድሎና ወገንተኝነት በመንግሥት ደረጃ ከታዬ በግልማ እንዴት የባሰ አይሆን! ሀፍረትን መሸጥ እንደዚህ ነው፡፡

እንደ አንዳንዶች ግንዛቤ እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ባያስጠነቅቅ ኖሮ ከተማችን ይሄኔ ከገጠር በአይሱዙ ተጭነው በመጡ የጥፋት ኃይሎች እንደ አሌፖና ደማስቆስ የዶግ አመድ ሆና ነበር፡፡ ይህን የንጹሓን ዜጎች ዕልቂትና የንብረት ውድመት መከላከልም እንደወንጀል ተቆጥሮ ወጣቱን “ራስህን ተከላከል፤ አካባቢህንም ጠብቅ” ብለው ያነቁ ከእስክርቢቶም በስተቀር አንድም የጦር መሣሪያ የሌላቸው ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸውና በዘር ሐረጋቸው ምክንያት ብቻ ለእስርና እንግልት ተዳርገዋል፡፡ ይህን መንግሥት የሚመራው ደግሞ እንደዓሣ በባህር እንደሰው በምድር ነዋሪ የሆነው ዶክተር አቢይ ነው፡፡ የሚገርም ተፈጥሮ፡፡

በበኩሌ ከአቢይ መንግሥት ምንም አልጠብቅም፡፡ ተስፋችንን ሁሉ እያሟጠጠው ነው፡፡ ሰውዬው እጅግ አደገኛ የጭቃ እሾህ መሆኑን በተደጋጋሚ በተግባር በማሳየቱ ከእንግዲህ አቢይ ኢትዮጵያን ወደ ወርቃማ ጊዜዋ ያሻግራታል ብሎ ራስን ማታለል ሲበዛ የዋህነት ነው፡፡ ልጁ በነገሮች መሳከር ሳቢያ ድንገት እጁ የገባችዋን ዕድሜ ልኩን ሲቃዥባት የኖረውን የሰባተኛ ንጉሥነት ሥልጣን ላለማጣት ሲል የማይቀጥፈውና መስሎ ለመገኘት የማይጥረው ነገር የለም፡፡ ይሉኝታን ባወጣ ሸጦ ስለበላ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው በአንድ ጊዜ ጅብም አህያም፤ እሳትም ውኃም ለመሆን ከመሞከር አይመለስም፡፡ ይህን ቦታ ከመያዙ በፊት እርግጥ ነው ጥሩ ሰው ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ወንበሩን ከያዘ በኋላ የሚታይበት ጠባይ ግን እጅግ የተለዬና አስመሳይነት የበዛበት ለመሆኑ የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በግልጽ የሚናገረው እውነት ነው፡፡ ለዚህም ነው የተበደለ ሲያይ አብሮ እያነባና ዕንባም ከጉንጭ እየጠረገ፣ የኦርቶዶክስ መስቀልንም ከሙስሊሙ ክታብና ሙስባሃ አጣምሮ እየሳመ፣ የጴንጤን መዝሙር ከማጀት እስካደባባይ እየዘመረና እያዘመረ፣ ምናልባትም ታልሙድንና ቶራን ከጽዮናውያን ምኩራቦች እያስተረጎመና እያስነበበ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ተከላም የዋሃንን እያነሆለለ፣ ... በየሥነ ግጥም ምሽቶችና የድርሰት ምርቃቶችም በመገኘት የአርት ሰዎችን እየቀፈለ ... በሌላ በኩል ደግሞ የሥልጣን ተቀናቃኞችን በሥውር እየገደለና እያስገደለ፣ በዘር ልክፍት የደዌ ግርሻ አክራሪ ወጣት ኦሮሞዎችን በየሥልጣን ቦታው እየመደበና ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸቱ ጥሩ ጥሩ ዜጎችን ግን ከጥቅምም ከሥራም እያገለለ፣ አዲስ አበባንና ሀብቷን ከየገጠሩ ተጠራርቶ ለመጣ የቄሮና አባገዳ ግሪሣና መንጋ እያከፋፈለ... አማራን ግን ከነስሙም አታንሱብኝ እያለ፣ የአማራን ክልል ሀብትና ሥልጣን ለታማኝ አሽከሮቹ እንደራሴዎች እያቃረጠ ... አይሆኑ ሆኖ የምናየው፡፡ ልጁ አስገራሚ ተፈጥሮ ያለው ሰው ነው፡፡ ሰይጣን ለተንኮሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ መጥቀሱን የማያምኑ የዋሃን ዜጎች በአቢይ የማስመሰል “ጥበብ”ና በሚያሣየው የሃይማኖተኛነት ውስጠ-ወይራዊ ስብዕና በመማለል በኔ እንደሚፈርዱብኝ አውቃለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ከጥቂት ጓደኞቼም ጋር ስከራከር ባለመስማማት ራሴን ከክርክሩ አገልላለሁ፡፡ የወደደ ሲጠላ እንዲህ ነው፡፡

በመጀመሪያው አካባቢ እርግጥ ነው እኔም መስሎኝ ተታልዬ እንደነበር አልደብቅም፡፡ እየቆዬ የተረዳሁት ግን አቢይ ማለት የጨለማው ገዢ ሊቀ ሣጥናኤል ዓላማውን እንዲያስፈጽሙለት ከልጅነታቸው ጀምሮ አርሞና ኮትኩቶ ለቁም ነገር ካበቃቸው ምድራዊ ሰብኣውያን ፍጡራን መካከል አንዱ መሆኑን ነው፡፡ እኔ ይህን እውነት በሚገባ አምኜበታለሁ፡፡ ምናልባት ይህን የኔን እውነት ከሰይጣን ከራሱና ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ ሰው አያውቀው ይሆናል - ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የአቢይ ልዝብ ሰይጣናዊ አንደበት ሌላውን ሁሉ ተውትና ፕሮፌስር አለማየሁ ገ/ማርያምን ሳይቀር አንበርክኳል፤ ምትክ የለሹን ለሀገር እንስፍስፍ ታማኝ በየነን በፍቅሩ ጫማው ሥር ጥሏል፤ ፕሮፌሰር እንደሻው ነጋን የመሰለ አክሮባቲስት አሽከሩ አድርጓል፤ በርካታ የተቃውሞው ጎራ ሚዲያዎችን አፍ አሲዞ በራሳቸው ጊዜ እንዲዘጉ አድርጓል፡፡ ብዙዎችን አሁን ድረስ በፍቅሩ እያማለለ እንዲያለቅሱለት በማድረግ ላይ ነው፡፡ ሰይጣን እስከዚህ ድረስ ሰውን ያጃጅላል፡፡ ለእግዚአብሔር ብቻ አይደለም - ለሰይጣንም የሚሳነው የለም! ዋናው እምነት ነው፡፡ ካመንክበት እንኳንስ ሰይጣንና አቢይ ድንጋይም ብዙ ተዓምር ይሠራልሃል፡፡ እውነት ነው፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ እውነቶች በገሃድ እስኪከሰቱ ጊዜ ይወስዳል፡፡

ኢትዮጵያ የተደገሰላት የመከራ ድግስ ቀላል እንዳይመስለን - የቆማጢት ልጅ “እማዬ እጄን አሳከከኝ” ብትላት “ልጄ እኔም በአንድ ቀን አልተቆመጥኩም!” ያለችው ሦርያንና ሩዋንዳን ለኛ ለጀለንፎዎቹ ለማስታወስ ፈልጋ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከሆነ በኋላ እዬዬ ዋጋ የለውም - ለዚያም ከበቃን እንዲያውም፡፡ አንድ መራር እውነት ላስታውስህ፡- የፌዴራል ተብዬውን ዋና ዋና የፈላጭ ቆራጭ የሥልጣን ቦታዎች የተቆጣጠረው ኦህዲድ/ኦነግ ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት አማራና ኢትዮጵያ ላይ የዘረኝነት የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሲነዛበት በነበረው ወጣት ኃይል ነው፡፡ ታከለም በለው ሽመልስ፣ አቢይም በለው ደቻሣና ቀልቤሣ .... ሁሉም የዚያን ወያኔ ወለድ የአኖሌ ትርክት እየተቀለበ የበቀል ጥማቱን ለማራገፍ ጊዜ ይጠብቅ የነበረና በአማራው ላይ ታሪክ ለመሥራት ያቆበቆበ ትውልድ ነው፡፡ ልዩነቱ አንዱ ወለጋ ጫካ ውስጥ ሲሆን ሌላውና ጓዳችን ውስጥ በራሳችን ስንቅና ትጥቅ እየተዋጋን ያለው ኃይል አዲስ አበባ ላይ የፌዴራል ተብዬውን መዋቅር ይዞ እንደልቡ የሚፏልል መሆኑ ነው፡፡ ይህ የምለው ነገር ውሸት በሆነና እኔ ቀጣፊ በተባልኩ፡፡ ኢትዮጵያ ሲባል እንደኮረንቲ የሚነዝረው፣ አማራ ሲባል እንደ ዛር አዶ ከብሬ የሚያስጓራው ትውልድ ሥልጣን ይዞ ኢትዮጵያም ሆነች አማራ ሰላም ያገኛሉ ብሎ ማሰብ ደግሞ በትንሹና በተለመደው አገላለጽ ከእባብ ዕንቁላል የዕርግብ ጫጩት ይፈለፈላል ብሎ  እንደመጠበቅ ነው - ትልቅ ጅልነት፡፡

እነሱሴም ሆኑ እነ “ስንኖር ኢትዮጵያ፣ ስንሞትም ኢትዮጵያ” ነገረ ሥራቸውን እያየናቸው ነው - እነሱም ብልጥ ሆነው ሞተው እንዴት ሕዝብን እያታለሉ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት አይከብድም፡፡ የ30 እና የ40 ዓመት ውርጋጥ የሦስት ሽህ ዘመን የጋራ የአብሮነት ታሪክ ያለውን ያንቀላፋ ግን ያልሞተ ሕዝብ ለማሞኘት የተጓዙትን ርቀትና ያስመዘገቡትን ስኬት ስንመለከት በርግጥም ዕድል ሲሰምርና ዕድል ሲያንጋድድ ልዩ ምስል  ሊፈጠር እንደሚችል ከሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ መረዳት አያቅተንም፡፡ ሆኖም ሁሉም ነገር አላፊ መሆኑ ያጽናናናል፡፡ እንደመጽሐፉ - ለመትከል ጊዜ አለው፤ የተተከለውን ለመንቀልም ጊዜ አለው፡፡ ለመነሣት ጊዜ አለው፤ ለመውደቅም ጊዜ አለው፡፡ ሮም በአንድ ቀን እንዳልፈረሰች ሁሉ በአንድ ቀንም አልተገነባችምና የሞኞች ግዝፈት ብልኆች ከዳተኝነታቸው እስኪላቀቁ ድረስ ነው፡፡  የሚያዋጣው በፋሲካ ሰሞን ከተቀጠረችዋ የቤት ሠራተኛ ትምህርት መቅሰምና ራስን ከታሪክ ሂደቶች ጋር ለማስተካከል መሞከር ነው - ብዙም ሳይረፍድ፡፡ ታሪክ ጨካኝ ነው - ምሕረትን አያውቅም፡፡ ከአጼ ኃይለ ሥላሤ፣ ከደርግና ከወያኔ ያልተማረ ንክር ያለ ደንቆሮ ነው፡፡ መለስና መንግሥቱ ኃ/ማርያም በተሰሚነታቸውና ጠርዝ ባልነበረው ዐረመኔያዊ አምባገነንነታቸው ያልቻሉትን የታሪክ ዱላ ጮርቃው አቢይ ይችለዋል ብሎ ማሰብ አነሰ ሲባል ሞኝነት አሊያም ካድማስ ወዲያ ማዶ አገር እንደሌለ የሚያስቆጥር አላዋቂነት ነው፡፡

እነዚህ በሥልጣን አራራ ያበዱና በፍቅረ ንዋይ የሰከሩ ዘረኞች የዘመናችን ጴጥሮሶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ከመፋፈራረሷ በፊት ከሦስት ጊዜ በላይ ይክዷታል፡፡እጅግ አስፈሪ ኃይል ማዕከላዊ መንግሥቱን ተቆጣጥሯል፡፡ ሀገራችን በሰሜንም በደቡብም በምሥራቅም በምዕራብም እንደሌጦ ተወጥራ ትገኛለች፡፡ እነጃዋርና እነአቢይ የሥልት እንጂ የዓላማ ልዩነትና የጠብ መንስኤ የላቸውም - ጥላቸው የሥጋ ጥል ነው፡፡ ዓላማቸው አንድና አንድ ነው - እሱም በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ሌሎችን በገዳ ሥርዓት የሚያንበረክክ ታላቋን ኦሮሚያ መመሥረት ነው፡፡ ልዩነት ካልነው ሌላው ልዩነት አንዳቸው ዓላማቸው በፍጥነት እንዲሳካ ሲፈልግ ሌላኛው በእርጋታና በዘዴ እንዲሆን መፈለጉ ነው፤ ሌላው ልዩነት የሥልጣንና ሀብት ክፍፍል ነው፡፡ እንጂ እዚያም ውስጥ ያሉት እዚህኛው ውስጥ አሉ፡፡ እዚህኛው ውስጥ ያሉት እዚያኛውም ውስጥ አሉ፡፡ አባተ ኪሾ እውነቱን ነበር፤ “ኤርትራውያንን ጭነህ ላክ” ቢሉት “እናንተው ለዩዋቸው እንጂ እኔ በምን አባቴን አውቃቸዋለሁ” ብሎ ትግሬዎቹንም ከአዋሣ ጠፍንጎ ለወያኔ ላከላቸው ይባል ነበር ያኔ፡፡ አሁንም እንደዚያ ነው፡፡ ነገር ይደጋገማል - ኦነግ ሸኔን ከኦነግ ኦህዲድ መለየት የሚችል ማሽን ተፈጥሮ ከሆነ የቸርች ኦፍ ሴተን መሥራች የቀሲስ አንቷን ሌቪ ሙት-መንፈስ ይንገረን፡፡


ልድገመው - በወያኔ ተንኮልና ሤራ የኦሮሞና የትግሬ ወጣት ሲኮመኩም ያደገው አማራን አምርሮ እንዲጠላ የሚያስችል የዘረኝነት መርዝ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ፈርዶባት ከአማራ ጋር አያይዘው እንድትጠላ ስላደረጓት ወጣቶቹ ለዚህች ጥንታዊት ሀገር ያላቸው ጥላቻም የዚያኑ ያህል ነው፡፡ መፍትሔው ለሰማይ ለምድር የከበደ ይመስላል፡፡ በኪነ ጥበቡ ውለን እናድራለን እንጂ እንደነዚህ ሰዎች ሁኔታ ቢሆን ኖሮ አዲስ አበባ በደም ባህር ላይ የምትንሣፈፍ ፍርስራሽ ከተማ በሆነች ነበር፤  አንድም ፎቅ ቆሞ ባልተገኘ፡፡ ይህን መከላከል ወንጀል የሆነው እንግዲህ በፌዴራል መንግሥቱ ውስጥ በተሰገሰገው አፍቃሬ ኦነግ ሸኔ ቲም ለማ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እጅግ ይገርማል፡፡

ኦሮሚያ በሚባለው አካባቢ ሲሰለጥን የነበረው ያ ሁሉ ለመቁጠር የሚያስቸግር ሠራዊት ለምን ዓላማ እንደሠለጠነ ሰሞኑን ትልቅ ፍንጭ እየሰጠን ነው - ቤተ ክርስቲያን ሲያቃጥሉ የነበሩት እነዚሁ ሥልጡኖች እንደነበሩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ አማራ ራሱን እንዳይከላከል በበጀትና በተላላኪ ምስለኔዎች እያሽመደመዱ ኦሮሚያ ተብየውን ክልላዊ መንግሥት ግን ልክ እንደ አንዱ አውሮፓዊ ኃያል አገር ለማድረግ ምን ያህል የተናበበ ሥራ ይሠሩ እንደነበር የምናውቀው ነው - ይህንን እውነት የሚክድ በርግጥም አድርባይና ሆዳም ነው ወይም ከዕውቀት የፀዳ እልም ያለ ደንቆሮ፡፡ ሁሉም ፈዞና ደንግዞ እያየ ያለው ይህ ድራማ መጨረሻ ምን ሊሆን እንደሚችል ሰሞኑን በቂ ምልክቶችን ስላየን ሌላው ቆሞ ከማየት ተቆጥቦ ራሱን መከላከል ወደሚያስችለው ዝግጅት መግባት እንዳለበት በዚህ አጋጣሚ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ራስን ከጥቃት መከላከል በአሁኒቷ የኦህዲድ ኢትዮጵያ ወንጀል ቢሆንም ሜዳ ላይ ተገትሮ አንገትን ለግብጽ ገጀራ መስጠት ግን ለማንም አይመከርም፡፡ አልሞት ባይ ተጋዳይነት በወንበዴ መንግሥት ሲጨፈለቅ ራስን ከዕልቂት ለማዳን ሥልት ነድፎ መንቀሳቀስ ቢያንስ ዘር ለማትረፍ ይረዳልና ሁሉም በዚህ ረገድ ማድረግ ያለበትን ብዙ ሳይረፍድ ያድርግ፡፡ ከሩዋንዳ እንማር፡፡ አሁኑኑ!! 

እርግጥ ነው ከፍ ሲል እንደተገለጸው የኦሮሞው ማዕከላዊ መንግሥት ራስን መከላከልን አይፈቅድም፡፡ ሰሞኑን አየነው፡፡ “ዝም ብላችሁ ታረዱ እንጂ መሸሽም ሆነ ንብረት እንዳይቃጠል መከላከል አትችሉም” የማለት ያህል አስገራሚ ትዕዛዝ ሲሰጡ ታዝበናል፡፡ ቄሮዎች አማሮችን ሲያርዱና ንብረታቸውን ሲዘርፉና ሲያቃጥሉ የሚሸሸውን ሰው የሚያግዱና ከዘረፋ ለማስጣል የሚሞከረውን ሀብት ንብረት እንዳይወጣ ሲከለክሉ የነበሩት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት እንደነበሩ በስፋት ተነግሯል፡፡ የመንግሥትን ቅርጽ ከያዘ የዘር ፍጅት ለማምለጥ ደግሞ ዕድሉ በጣም ጠባብ ነው፡፡ የኔ ነው ብለህ የምትጠጋው ኃይል ከሸሸኸው ኃይል በባሰ ወይም በተካከከለ ሁኔታ ሕይወትህን ሲቀጥፍ ወይም ሲያመናጭቅህ መፈጠርን ያስጠላል፤ የፈጣሪንም ኅልውና እስከመጠራጠር ሳይቀር ይፈታተናል፡፡ ሰሞኑን የሆነው ይሄው ነው፡፡ የነገው ደግሞ ከዚህ የከፋ መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ አማራነትና ኢትዮጵያዊነት ወንጀል ሆነዋልና ለመጨረሻው የአልሞትባይ ተጋዳይ ፍልሚያ እንዘጋጅ፡፡ ቁርጡን ካወቅነው የትግሉ ውጤት የሚያዘነብልበትን አቅጣጫ ለመተንበይ ቀላል ነው፡፡ 

ራስን ከጥቃት መከላከል ወንጀል የሆነባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ ከአሁን በኋላ ይህን መንግሥት ማመን አስቸጋሪ ብቻ ሣይሆን በፍጹም የሚቻል አይደለም፡፡ ቄሮ ሲመጣብህ መሸሽና አንገትን ከቆንጨራ ለማዳን መሞከርም በህግ የሚያስቀጣ አንቀጽ የሌለው ወንጀል ሊሆን ነው፡፡ አክራሪ ኦሮሞ ሲመጣብህ ቆሞ መጠበቅና የሚደርስብህን በጸጋ መቀበል ህግን እንደማክበር ከተቆጠረ ከእንግዲህ አገር አለኝ ማለት አንችልም፡፡ መንግሥት እነጃዋርን አሰራቸው ማለትም አይቻልም፡፡ የሚደረግላቸው ክብካቤ ልዩ እንደሆነ እየሰማንና እያየን ነው - ከርቸሌ ገብቶ ያልታሰሩ የቅንጅት አባላትን ሲሾም ሲሽር እንደነበረው እንደኢንጂኔር ኃይሉ ሻውል ጃዋር እስር ቤት ውስጥም ሆኖ የመንግሥትነት ጠባዩ የለቀቀው አይመስልም - እንደምናየው ከእስረኛ ዓለም አቀፍ አያያዝ በተለዬ ሁኔታ በቪ8 እና በተለዬ አክብሮትና አጀብ ነው ወደ ፍርድ ቤት እንኳን የሚመላለሰው፤ ተፅዕኖው ቀላል አይደለም፤ በዚህ አኳኋን በቅርብ እንደሚፈታም መገመት አይከብድም፡፡ ለምሣሌ በበቀደም አንድ የጊዜ ቀጠሮ ለነእስክንድር ተጨማሪ ምርመራ 13 ቀን ሲፈቀድ ለነበቀለ ገርባ ግን 11 ቀን ነው፡፡ ምን አለፋችሁ - ይህን በዘረኝነት የጠነባ የአቢይ መንግሥት በሰላም ካልተገላገልን የኢትዮጵያ ትንሣኤ መቼም እውን አይሆንም፡፡


ይልቁንስ ትንቢትን ማክሸፍ የሚቻል ከሆነ በየሃይማኖታችን አጥብቀን እንጸልይ፡፡ መጪው ጊዜ ካለፈው እጅጉን ከባድ ነው፡፡ ትልቅ ሰውም የለም፤ ሃይማኖትም የለም፤ ሃይማኖተኛም የለም፡፡ በሁሉም ከስረናል፡፡ አንድ ነገር ቢነሳ ማንም አያድነን፡፡ ዓለም ደግሞ የባለጌዎች መናኸሪያ ከሆነች ቆየች፡፡ እንጂ የንጹሓንን ደም ለማፍሰስ አውስትራሊያና አሜሪካ መሽገው ጃዝ የሚሉ ተኩላዎችን ለማስቆም የሚከብድ ሆኖ አልነበረም፡፡ ዘመኑ የመጨረሻው መሆኑን እንድናምን የሚያስገድደንም ይሄው የጭካኔ ትስስር ነው፡፡

ማኅበረሰቡ በሞራል ላሽቋል፤ በሃይማኖት ወድቋል፤ ባህልና ወጉን ተነጥቋል፤ ማኅበራዊ ወግ-ሥራታዊ ተራክቦው ከሞላ ጎደል ተበጣጥሷል፡፡ በቀደምለት ዮንሐስ አካባቢ ገዳም ሰፈር በሚባለው ልዩ ቦታ የታዘብኩት ክስተት ኢትዮጵያ እንደሀገርም እንደህዝብም  ትልቅ ችግር ላይ መውደቋን አጉልቶ የሚያሳይ ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው - እኔ በራሴ ተሸከርካሪ ቀስ ብዬ እያለፍኩ ነው፡፡ አንድ የቆመ ዲኤክስ መኪና ተነስቶ ሊሄድ ማርሽ እያስገባ ነው፡፡ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ሁለት የጉሊት ሴቶች ተንደርድረው ሲመጡ አያለሁ፡፡ ሣር ቢጤ ይዘዋል፡፡ አንደኛዋ ማንም ሳይነካት ከመኪናው የኋላ ኮፈን ጋር በዘዴ ተጋጨችና ተምበልብላ ወደቀች፡፡ መኪናው አልገጨም፤ የጀመረውንም እንቅስቃሴ ወዲያውኑ አቆመ፡፡ ትያትር የማይ መሰለኝ፡፡ ይህንን የአጭበርባሪዎች ዘዴ በፊትም አውቀዋለሁ፡፡ እንደዚህ ሲገጥመኝ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ያቺ በራሷ ጊዜ ጎማው ሥር የወደቀችው ሴትም ጓደኛዋም ያገር ያለህ እያሉ ጩኸታቸውን ማቅለጥ ጀመሩ፡፡ ሹፌሩ ደነገጠ፡፡ ሕዝብ መሰባሰብ ጀመረ፡፡ እኔ ንዴት ብልጭ አለብኝና ከራሴ መኪና ወርጄ በጩኸት ወደ ጀማው ተቀላቀልኩና ሕዝብና መንግሥት ህግና ሥርዓትም ያለ መስሎኝ “እነዚህን ሴቶች ከመነሻው አይቻቸዋለሁ፡፡ ትያትር እየሠሩ ነው፡፡ ልጁ አልገጫቸውም፡፡ ...” እያልኩ ምስክርነቴን ባደባባይ መስጠት ጀመርኩ፡፡ ፖሊሶችም ነበሩ፡፡ የአካባቢው ሰው ግን እኔን ሳይሆን ሴትዮዋን ደግፎ ይንጫጫ ጀመር፡፡ ትያትሩ መንደር አቀፍ መሆኑ ገባኝ፤ እርግጥ ነው ሰፈሩ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች መኖሪያ ይመስላል - ያን ያህል የሞራል ዝቅጠት ይኖራል ብሎ መገመት ግን ይከብዳል፤ እየሆነ ያለው ግን ሌላና አስደንጋጭም ነው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም በኔ ይዝቱ ገባ፡፡ ሁኔታው ሳያምረኝ ሲቀር እያበድኩ እየተከንኩ አካባቢውን ለቅቄ ሄድኩ፡፡ ራቅ ብዬ ስከታተል የተወሰኑ ሰዎች ተገጨች የተባለችውን አጭበርባሪ በመኪናው ጭነው ሄዱ፡፡ ቀጥሎ የሚሆነውን መገመት ቀላል ነው፡- መንገድ ላይ ይደራደሩና “ማገገሚያና መታከሚያ ጥቂት ገንዘብ ስጣትና እዚሁ ተስማሙ” ይባልና ገንዘብ ተቀብለው ባለመኪናውን ይሸኙታል፤ “ገጪው”ም ከህጋዊና ህክምናዊ ውጣ ውረድ በመገላገሉ ያላመነበትን ነገር አድርጎ ከውጣ ውረድ ይድናል፡፡ እስከዚህ በስብሰናል፡፡

በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየእምነት ቤቱ፣ በየምናምኑ ... ሁሉ እንደዚህ ያለ ንቅዘት በስፋትና በጥልቀት ይታያል፡፡ ይህን መበስበስ ለማስወገድና ወደ ትክክለኛው ስብዕና ለመምጣት ራሱ ብዙ ጊዜንና ብዙ ትግስትን፣ ብዙ የተማረ የሰው ኃይልንና በጀትን፣ ብዙ ቆራጥነትንና የሀገርና የወገን ፍቅርን፣ ... በጣም ብዙ ብዙ ነገርን ይጠይቃል፡፡ አቢይም የዚህ የበሰበሰ ማኅበረሰብ ውጤት ነውና በውሸታምነቱ የተቆራኘው የአጋንንት መንፈስ ከየትም እንዳላመጣው በዚህ አጋጣሚ መመስከር ይቻላል፡፡ በወለድነው እንጦራለን፤ የዘራነውንም እናጭዳለን ... በዚህ መሀል ግን አዲዮስ ሀገር፤ አዲዮስ የመንግሥት ህዝባዊ አገልጋይነት፤ አዲዮስ የሞራልና የሥርዓት ዕሤቶች.... አዲዮስ ህግና መንግሥት ... የአሥር ዓመት ሕጻን ልጁን የደፈረና የደበደበ ዋና ሳጅን የዘጠኝ ዓመት እሥራት ብቻ የሚፈረድባት ሀገር ዱሮውንስ ምን ሀገር ሆነች .... ውይ ኢትዮጵያ! ቺድ! በቃኝ እባክህን፡፡ ሳይጠጡ የምታሰክር፣ ሳይኖሩባት የምታስረጅ ሀገር!!
ma74085@gmail.com

Tuesday, July 21, 2020

ይድረስ ለጀርመን ድምፅ ያማርኛ አገልግሎት ቦን/ጀርመን 21.07.2020


ይድረስ ለጀርመን ድምፅ ያማርኛ አገልግሎት
ቦን/ጀርመን
21.07.2020          
በሐምሌ 12 ቀን 2012 . ዕለተ እሁድ እንወያይ ሳምንታዊ ዝግጅት ሦስት ሰዎችን አቅርባችሁ በአቶ ነጋሽ መሐመድ አዋዋይነት የተደረገዉን ሰምተን ምላሹ ይኽዉ።

የጀርመን ድምፅ ራዲዮ ተብየዉ ከሁሉ በተቀዳሚ አንድን  ፀረ ዐማራ ለዘር ማጥፋትና ማፅዳት ግልጽ የጥላቻ ቅስቀሳ ዋና አቀንቃኝ የሆነዉን ራሱን ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኒ ብሎ የሚጠራዉን፣ 16ኛዉ ሁለተኛ አጋማሽ (1665) ከግራኝ አሕመድ ጅሃዳዊ ወረራና ፍጅት በኍላ በተከተለዉ የጋላ ነገድ ወረራና በሸዋ ምድር መጤ ሠፋሪ ሆኖ ከቀረዉ የጋላ ቱላማ ጎሣ ዉላጅ የአቢቹ  ዘርያ ነኝ ያለዉ ዓይኑን በጨዉ አጥቦ ጥንታዊት በራራ እንዶጥና የቀዳማዊ አጤ ዳዊት(1382-1411) መናገሻ በነበረችዉ ሥፍራ ገናና ሰመ ጥሩዎች በሆኑት እቴጌ ጣይቱ ብጡልና ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ዳግም በተመሠረተችዉና አዲስ አበባ ብለው በሰየሟት መዲናችንና ዙሪያ የአቢቹ ወረሞ ጎሣ ብቸኛ መኖሪያ ነበር ብሎ እራሱን የኦሮሞ ነጻ አዉጭ ግንባር (ኦነግ) የሚለዉ ያልታጠቁ ሰርቶ አደር ገበሬዎችን ነጋዴዎችንና ሠራተኞችን ዐማራ ኢትዮጵያዊ እስላምና ክርስቲያን በመሆነናቸዉ ብቻ ለይቶ ነፍጠኛ እያለ ፈርጆ በአሰቃቂና አረመኔያዊ ድርጊት የፈጀና የሚፈጅ፣ ያፈናቀለና የሚያፈናቅል የወንጀለኞች ቡድን የፈጠራ ትርክትንና ፀረ ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳ በቅጥረኝነት ልክ እንደ ሻዕቢያ እና ትሕነግ ወያኔ ሲያደርጉት እንደነበረዉ ለኦነጉ ብርሃነ መስቀል እንዲያነብንብ የጀርመን ድምፅ ራዲዮ ነፃ መድረክ ሆኖታል። 

ምን የጀርመን ድምፅ ብቻ ያሜሪካኑም ቪኦኤ የተሰኘዉ ለብርሃነ መስቀል አበበ የዉሽት በሬዉ ላም ወለድ ትረካ እንዲያናፋ ሰለሞን አባተ የተባለዉ ድንብርብር ተከታታይ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግለት ተደምጧል። ወደ ዋናዉ ቁም ነገር ተመልሰን የነጋሽ አሕመድን ቅሌቱና ወንጀሉ ለብርሃነ መስቀል አበብ ዐማራን በስም ለይቶ፣ ነፍጠኛ በሚል ምልከታዉ፣ የጥላቻ ቅስቀሳ በማነሳሳት በጀርመን ድምፅ ራዲዮ በስፋት እንዲያሰራጭ አስችሎታል። ብርሃነ መስቀል በሚረጨዉ የፈጠራ ወሬ ማለትም አዲስ አበባና ዙሪያዋ የአቢቹ ጎሣ መኖሪያ ነበር እያለ አዲስ አበባን በአረመኔ የቄሮ መንጋ ለማስጨፍጨፍ፣ ለማዉደም በጀርመን ድምፅ ራዲዮ መርዙን ረጭቷል።

የአቢቹን ጎሣ በተመለከተ ሐቁ ግን ሌላ ነዉ። ይህ ጎሣ የሚኖረዉ ባማራዉ ምድር በወግዳ ነዉ። ያቢቹ ዋና ጠላት ገላን የተባለዉ ከአዋሽ ወንዝ በሰተሰሜን ከወጨጫ ተራራ በመለስ ከእንጠጦ ተራራ በስተደቡብ ከየረር ተራራ በሰተምዕራብ ባላዉ አካባቢ የሚኖረዉ። በሸዋ ከግራኝ አሕመድ ወረራና ከተከተለዉም የጋላ ወረራና ቇሚ ሠፈራ ሳቢያ ተለያይቶና ተነጥሎ የቆየዉን በጋላ ጎሣ የተያዘዉን ያማራዉን ምድር ለማስመልስ ያጤ ልብነ ድንግል ተወላጆች እነ ያዕቆብ፣ ነጋሢ፣ መርድ አዝማች ስብስቴ፣ አብዬ፣ አምሃ ኢየሱስ፣ አስፋ ወሰን፣ ራስ ወሰን ሰገድ፣ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ፣ ኃይለ መለኮት ተከታታይ ዘመቻ አድርገዋል። የሸዋዉ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ እስከ ጉራጌ እና አባይ ወንዝ በመለስ ያለዉን አገር አስመልሰዉ አቅንተዋል። በዛሬዉ አዲስ አበባ በጥንቱ በራራ የአቢቹ ጎሣ ስፋሪ በጭራሽ አልነበረም። ለዚህም ዋናዉ ሰነድ የእንግሊዝ ንግሥት ቪክቶሪያ መልክተኛ መሪ የነበረዉ ሻምበል ዊሊያም ሃሪስ ያይን ምስክር ሆኖ ያዘጋጀዉን መጽሐፍ መመልከት ነዉ። ከዚህም ሌላ አፍቃሪ ጋላ የነበረዉ የጀርመኑ የወንጌል ሚሲዮን ተብዬዉ ሰላይ ዮሓን ሉድቪኽ ክራፍ ከሰሜን ኢትዮጵያ ሲባረር በታጁራ በኩል ወደ ሸዋ ገብቶ ሁለት ዓመታት ቆይቶ ሸዋን ዋና ማዕከሉ አድርጎ አእዋሚ ጋሎችን ሁሉንም የፕሮቴስታንት ክርስትናን ሰብኮ ከሸዋ በስተደቡብ ያለዉን አገር ልክ እንደነ ታንጋኒካ፣ ካመሩን፣ ቶጎና ናሚቢያ ያፍሪቃ ጀርመን ቅኝግዛት መስፈሪያ ለማሰደርግ አቅዶ ባዘጋጀዉ ትረካ አቢቹ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንደማይኖር ያረጋግጣል።

ሌላዉ የነጋሽ አሕመድ በጣም አሳፋሪ ቀልባጣነት "ኢትዮጵያ እንዴት ትፍረስ?" እያለ ማሟረቱ ነዉ። በእዉነትና ብርግጠኛነት እንላችኍላን እናት ሀገር ኢትዮጵያ አትፈርስም። ሊያፈርሷት የሞከሩ ጠላቶቿ ሁሉ ፈርሰዉ ትቢያ ሆነዋል፣ ይሆናሉ።

 የጥላቻ ቅስቀሳ የሚያነሳሱ፣ የሚያደራጁ፣ የአንድን ማኅበረሰብ ለይተውና ምልከታ ሰጥተዉ፣ ሰባዊ ክብሩን አዋርደዉ ለዘር ፍጅት(Genocide) እና  ዘር ማፅዳት (Ethnic cleansing ) ዘመቻ ከሚያደርጉና ካደረጉት ጋራ በግልጽና በስዉር የሚተባበሩትን ሁሉ በጥብቅ እንቃወማለን። እነዚህ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን::
ኢትዮጵያ በልጆቿ መስዋዕትነት በነፃነት ትኖራለች!!!!

ቶሚ ገሞራው       

 የዉብዳር ዘለቀ/ዶክተር             
 ገለበዉ ሰንጎጎ          
ገብሬ ጉልቱ /ዶክተር
ሞገስ  ገብረ እግዚአብሔር 
21.07.2020