Monday, September 30, 2019

“Fly out of Ethiopia while you can.” ማለትስ አሁን ነው አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) Ethio Semay


“Fly out of Ethiopia while you can.” ማለትስ አሁን ነው
አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) Ethio Semay

ከተማ ይፍሩ የተባሉ ደርግ ሥልጣን በያዘበት ሰሞን የአፄ ኃይለ ሥላሤ ዘመነ መንግሥት የመጨረሻው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር(?) ለሥራ ጉብኝት ወደ ውጭ ሄደው በዚያው ቀሩ አሉ፡፡ ለምን እንደቀሩ ሲጠየቁ በርዕሴ የጠቆምኩትን የእንግሊዝኛ ዐረፍተ ነገር እንደተናገሩ ይወሳላቸዋል - “አጋጣሚ ባገኘህ ጊዜ (ሁሉ) ከኢትዮጵያ አጥብቀህ ሽሽ!” ተብሎ ቢተረጎም ያስኬዳል-  ህልምና እንግሊዝኛ ደግሞ እንደፈቺው ነው እሚባለው፡፡

ሀገራችን ካለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ወዲህ በተለይ ለይቶላት ባለቤት አልባ ሆናለች፡፡ አሁን ያለው የዶ/ር አቢይ መንግሥትም ምን እያደረገ እንደሆነ እንኳንስ ሌላው ራሱ አቢይም የሚያውቅ አይመስልም፡፡ ሀገሪቱ መሽቶ ይነጋላታል እንጂ ያለመሪና ምናልባትም ያለ ሕዝብ በደመነፍስ እየተውገረገረች ነው - አለች ለመባል ያህል፡፡
ይህን የሚያስብሉ ጥቂት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

1.     የኑሮ ውድነት - ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ኑሮ  ከመንኮራኩር በሚልቅ ፍጥነት ወደ ሰማየ ሰማያት ሲመጥቅ “ይህ ሕዝብ የኔ ሕዝብ ነው፤ በኑሮ ውድነት ሲጠበስ፣ ከገቢው ጋር በማይመጣጠን ሁኔታ ኑሮው በእሳት አለንጋ ሲገርፈው እኔን በዋናነት ይመለከተኛልና ገበያውን ላረጋጋ፤ ንግዱን ልቆጣጠር፤ የንግዱን ማኅበረሰብም ንቃተ ኅሊናውን አሳድጌ ተመጣጣኝ ትርፍ እንዲያገኝ ላስችል፤ ኢኮኖሚውና ሕዝብ እንዲገናኙ ላድርግ....” የሚል መንግሥትም ሆነ የመንግሥት አካል አልተገኘም፡፡ ሁሉም ሩጫው የራሱን ኑሮ ለማመቻቸት ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ሕዝቡም ሆነ ሀገሪቷ የኔ ናቸው የሚላቸው አካል አለመኖሩን ነው፡፡ ለአብነት ያህል የመኪና ባትሪ በ10 ዓመታት ውስጥ ከብር 200 እና 300 አሁን ወደ ብር ራት ሽህና አምስት ሽህ ሲገባ፤ አንድ ዕንቁላል ከስሙኒ ወደ 6 ብር ሲገባ፤ ኩንታል ነጭ ጤፍ ከብር 1000 ገደማ ወደ ብር 4000 ሲጠጋ፣አንድ ሊትር ዘይት ከብር 12 ወደ ብር 90 ሲሽቀነጠር፣ የ20 ብር የቀን ሠራተኛ (ወዛደር) ወደ ብር 400 እና ከዚያ በላይ ሲመነደግ፣ የቤት ሠራተኛ ከ50 እና 60 ብር ወደ ብር 2500 ሲያሻቅብ፣ ለትንንሽ የመኪናም ሆነ የቤት ጥገናዎች ይወጣ የነበረው ብር 300 እና 500 አሁን ከአሥር ዕጥፍ በላይ አድጎ ብር 3000 እና 5000 ሲገባ (በጣም ትንሽ ጥገና ነው! ሞተር ላውርድ ካልክ የዛሬ 10 ዓመት መኪናውን የገዛህበትን ዋጋ የሚያስከነዳ ዋጋ ትጠየቃለህ፤ የቀን ጅብ ሆኗል እያንዳንዱ ባለሙያና የንግድ ድርጅት፡፡ አቢይ ሲያቀብጠው “የቀን ጅብ” አለ ያኔ፡፡ እነዚያኞች መቀሌ ሲመሽጉ ሌሎች የቀን ጅቦች በየቀኑ እዚሁ ይፈለፈሉ ገቡ)..... ይህ ሁሉ ምስቅልቅል በሀገር ላይ ባልተለመደ ሁኔታ ሲከሰት ታዲያ የኢትዮጵያ መንግሥት ነኝ ባዩ የአቢይ መንግሥት እየታዘበ ቁጭ ከማለት ወይም ምናልባትም ለተለዬ ውስጣዊ ተልእኮ ሲባል ለኑሮው መመሰቃቀል የበኩሉን አስተዋፅዖ ከማድረግ ውጪ ሊያደርግ የሞከረው አንድም ነገር የለም፡፡ “የኔ ነው” የምንለው መንግሥት እንደማጣት ያለ ቁጭት የሚለቅ ነገር ደግሞ የለም፡፡ እኔ ቤተሰቤ ሲራብና ሲጠማ የማይሰማኝ ከሆነ ደደብና ደንቆሮ ነኝ ማለት ነው፡፡ ኃላፊነቱን የማያውቅ ወላጅና መንግሥት አንድ ናቸው፡፡ ስለሆነም ነው የአቢይ መንግሥት የኔ መንግሥት የማይመስለኝ፡፡ ደንቆሮና ዕውር መንግሥት ካላቸው ሀገሮች ቀዳሚዋና ምናልባትም ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ናት - “አክሰሱ” ያላችሁ አንድ ዜጋው እንዲህ ማለቴን ንገሩት፡፡ ይሄ ነገር በጣም ይገርመኛል፡፡ በርሀብና በርዛት፣ በበሽታና በቄሮ ማለትም በህግ-አልባዎች የዝርፊያና ግድያ ቡድን አንቀጥቅጦ መግዛት ወንጀል ነው፡፡ ኋላ ማጣፊያው እንደሚያጥረው ሳይታለም የተፈታ ቢሆንም አሁን ሀገርና ሕዝብ ክፉኛ እየተሰቃዩ መሆናቸውን በመገንዘብ መፍትሔ መሻት ጊዜ የማይሰጠው ነው፡፡

2.    ሥርዓት አልበኝነት - አሁን ይህችን ማስታወሻ እየጻፍኩ እንኳን በመስኮት መንገዱን ስመለከት መሀል አዲስ አበባ ላይ ወጣቶች መንገዱን ዘግተው በኦሮምኛ ቋንቋ እየዘፈኑና እየጮኹ ነው፡፡ መጮኻቸውን አልቃወምም፤ መብትም የለኝም፡፡ ግን መንገድ እየዘጉና የትራፊክ እንቅስቀሴን እያወኩ በሥራ ሰዓት እንዲህ መሆን አግባብ አይደለም፡፡ ይሄ “ጊዜው የኛ ነው!” የሚሉት ዘመን አመጣሽ ፈሊጥ ሀገራችንን የለየላት ሦርያና ሶማሊያ ሳያደርጋት በሀገራችን ህጋዊና ብሔራዊ ስሜት የሚሰማው ሕዝባዊ መንግሥት መቆም ይኖርበታል፡፡ በየክልሉ ሄደን ብናይ መንግሥት ያለ አይመስልም፡፡ ሁሉም ባፈተተው ይጓዛል፡፡ የማኅበረሰቡ ሕይወት በጎረምሦችና በወጠጤዎች የምሕረት እጅ ውስጥ ነው፡፡ አዲስ አበባም እንደዚሁ ናት፡፡ በህጋዊ መንገድ ጉዳይን ማስፈጸም ታሪክ ሆኗል፡፡ ጉቦና ሙስና ጫፍ ወጥተዋል፡፡ በሰላም ከቤት ወጥቶ በሰላም መመለስም ብዙዎች የሚናፍቁት እየሆነ ነው፡፡ በጠራራ ፀሐይ በሚደረግ ዝርፊያና ንጥቂያ የብዙ ሰው ሕይወት እየጠፋ ነው፡፡ ለሀገርና ለወገን ማሰብ ዕርም በመሆኑ ሥራንና የሥራ ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ቀርቷል፡፡ ሙስና የደም ሥር ከሆነ ሰነበተ፡፡ ምናልባት ሰዎች በእውነተኛ ገቢያቸው መኖር አለመቻላቸው ለዚህ ዓይነቱ ህገ ወጥ ድርጊት ዳርጓቸው ሊሆን ይችላል፡፡ መንግሥት ቢኖር ይህን ጉዳይ ግምት ውስጥ በማስገባት ከኑሮው ጋር የሚመጣጠን ደሞዝ እንዲከፈል ህግ ያወጣ፣ አዲስ የደሞዝ አስኬልም ይቀርጽ ነበር፡፡ አሁን ግን ሀገራችን ባለቤት ስለሌላት እንዲያውም ይባስ ብለው ካለችንም ትንሽዬ ገቢ እንዴት እንደሚዘርፉ አዳዲስ ሥልቶችን ያውጠነጥናሉ እንጂ ለኛ ኑሮ ግዴላቸውም፤ ባልተወለደ አንጀት ይገርፉን ይዘዋል፡፡ በዚህ ረገድ ነጋዴው በዓመት በሚሊዮኖች ለሚያስገባበት ንግድ በሙስና ትስስር ጥቂት ሽዎችን እንዲከፍል ሲደረግ የኔ ዓይነቱ ምሥኪን ደሞዝተኛ ላይ ቫትን ጨምሮ ከ50 በመቶ በላይ ከደሞዛችን ይቆረጣል፡፡ ጊዜው ሲደርስ የምናወራው የገቢዎች ሚኒስቴር በተለይ በሠራተኛው ላይ የሚፈጽመው ግፍና በደል እጅግ ብዙ ነው፡፡ ገና ለገና የመንግሥትን ገቢ አሳደግን ብለው የቅጥር ሠራተኞችን ደሞዝ ከየትኛውም የዓለም ሀገር በማይወዳደር የቀረጥ ዓይነትና የአቀራረጥ ሁኔታ እየመዘበሩንና ኑሯችንን መቅኖ እያሳጡት ይገኛሉ፡፡ ለነገሩ ቀረጥና ግብሩ እነሱን ስለማይነካ ምን ያድርጉ፡፡ እነሱ እኮ ደሞዝ የሚከፈላቸው ለስሙ እንጂ የኑሯቸው መሠረት ሌላው ቀርቶ አንዱ ነጋዴ ብቻም ሊሆን ይችላል፡፡

3.    የባለሥልጣናት ድንቁርና -  ልብ አድርጉ፤ አጎቴና አክስቴ በባዶ እግራቸው የመሬት እሾህና የዛፍ ላይ ቆንጥር እያሰቃያቸው ተርበውና ታርዘው በሚከፍሉት ግብር በስምንትና አሥር ሚሊዮን ብር ቪ-8 መኪና መንግሥት ይገዛና ለየባለሥልጣናቱ ያድላል፡፡ እነሱም በነዳጁ፣ በአበሉ፣ በምኑም በምናምኑም የዚህን ምሥኪን ሕዝብ ገንዘብ ያሟጥጡታል፡፡ ለሕዝቡ ግን አንድም ነገር አይሠሩለትም፡፡ አብዛኛው ሕዝብ ውኃ የለውም፤ መንገድ የለውም፤ ትምህርት ቤት የለውም፤ ህክምና የለውም - (“ነቲንግ!” አለ ያ መንጌ በአንድ ንግግሩ - በጣም ተናዶ )፡፡ ገበሬው ከዛሬ 100 ዓመት በፊት የነበረውን ጎስቋላ ሕይወት እየመራ ባለሥልጣናቱ ግን የ21ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን ቅንጡ አውሮፓዊ ሕይወት ይቀጫሉ - ቀንቼ እንዳይመስላችሁ - ነገረ ሥራቸው ስለሚያናድድ እንጂ፡፡ በዚህም ቅንጣት አይሰማቸውም፡፡ ምክንያቱም ተፈጥሯዊ ድንቁርና ጆሯቸውንም ልቦናቸውንም የፊጥኝ አስሮታልና፡፡ ትንሽ መልካም ሥራ ቢሠሩ እንኳን እሰዬው ነበር፡፡ ግን አንዳችም የለም፡፡ ቢሯቸው እንኳን የሚገኙት ከስንት አንድ ናቸው፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ የሚባክነውን ገንዘብና ሀብት ስታዩ፣ ላልተሠራ ፕሮጀክት ሳይቀር ብዙ ሚሊዮን በብድርና በምጽዋት የተገኘ ገንዘብ በሀሰት ሠነድ እየተወራረደ የሚጠፋውን የገንዘብ መጠን ስትሰሙ እንደ ኢትዮጵያዊ ከማሣፈሩም በተጨማሪ እንደ አንድ ጤናማ ዜጋ ያሳብዳችኋል፡፡ ይህን ኢትዮጵዊነት ምን እናድርገው ይሆን?


4.    የመንጋ ፍርድ - በየአካባቢው የሚታዬው የመንጋ ፍርድ ኢትዮጵያ ውስጥ ለአንዲትም ደቂቃ ቢሆን እንድትኖር አያደርግህም፡፡ መውጫ ቀዳዳ ቢኖር ብዙ ዜጎች በአንድ ጀምበር ከኢትዮጵያ ውልቅ ብለው በተገላገሉ ነበር፡፡ በየትም ሥፍራ ብትሄድ እንደ ዘመነ ክርስቶስ “ስቅሎ፣ስቅሎ” ነው መመሪያው፡፡ ሰውን ዘቅዝቆ መስቀል፣ ሰውን ገድሎ ሬሣን ዘመድ እንዳይወስድ በመከልከል የግፍ ግፍ በጀብ ማስበላት፣ አባትን ከቤት ጠርቶ በልጆች ፊት መሀል አናትን በጥይት መፈጥፈጥ፣ ልጅን ገድሎ በሬሣው ላይ እናትን ማስጨፈር፣ ተደራጅቶ ገንዘብና ንብረት በመቀማትና በመዝረፍ የራስን ኑሮ ማበልጸግ፣ ጭቁን ዜጋ በላቡ የሠራውን ኮንዶምንየም ቀምቶ ለራስ ጎሣ ማደል፣ ከአንዱ አካባቢ ወደሌላው አካባቢ እህልና ጥራጥሬ እንዳይገባ ማገድ፣ “ይህ የኛ ቦታና መሬት ነው” በሚል ነባር ባለይዞታን ከኑሮውና ከይዞታው ማፈናቀል፤ በዘር ተሰባስቦ ከተሞችን መውረር፣ የሰይጣን ኮከብ የሌለበትን ንጹሕ የቀደመ የሀገር ባንዲራን ከሃይማኖት ማክበሪያ ሥፍራዎች ከየሰውና ከየካህናቱ በግዳጅ እየነጠቁ ማቃጠል፤ ካህናትን ማረድና ቤተ ክርስቲያናትን ማቃጠል፣ የሃይማኖት አባቶችን ማሰር ወይም ማንገላታት፣ ወዘተ. የሀገራችን ዘመናዊ ባህል ከሆኑ ሰነበቱ፡፡ ይህም የመንግሥትን ደካማነት ወይም ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት የወንጀል ተባባሪነት ከማሳየት ባለፈ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡ ይህችን የመሰለች ሀገር እየመራሁ ነው ማለትም በእጅጉ ያሣፍራል፡፡ እኔ አቢይን ብሆን በሚደረግልኝ የዲፕሎማሲ ፕሮቶኮል እሸማቀቅና ደብቁኝ እል ነበር፡፡ የዚህች ሀገር መሪ መሆን በምንም መንገድ ሊያኮራ አይችልም፤ አይገባምም፡፡ ኢትዮጵያ ያለች የምትመስለው አርትስ ቲቪን በመሳሰሉ አንዳንድ ገራገርና ጥሩ የሚመኙ ሚዲያዎች ውስጥ ብቻ እንጂ በእውን ኢትዮጵያ በቀደመው ይዘቷ አለች ማለት በፍጹም አንችልም፡፡ ልቀጥል? ጊዜ የላችሁም መሰለኝ ... መልስ ለመስጠት ኮራችሁብኝ፤ ስለዚህ ይቅርብኝ፡፡ ... ግን ሀገራችን እንዳለች የማትቆጠር መሆኗን ያዙልኝ፡፡
 Ethio Semay

Friday, September 27, 2019

ስደንጋጭ ሚስጥራዊ መረጃ፦ በህወሓቱ ጌታቸው ረዳ እና በግብፁ የደህንነት ኃላፊ የተዘጋጀው ፕሮፖዛል! (ስዩም ተሾመ) September 27, 2019 (posted -Ethio Semay)


አስደንጋጭ ሚስጥራዊ መረጃ፦ በህወሓቱ ጌታቸው ረዳ እና በግብፁ የደህንነት ኃላፊ የተዘጋጀው ፕሮፖዛል! (ስዩም ተሾመ)
September 27, 2019 (posted -Ethio Semay)
The mercenary TPLF fool Getachew Reda conspiring with Ethiopia's enemies with the Arabs and Egypt in particular


The mercenary TPLF fool Getachew Reda conspiring with Ethiopia's enemies with the Arabs and Egypt in particular

በምስሉ ላይ የሚታዩት አራት ሰዎች ስም፤ ከግራ ወደ ቀኝ፡-

1- የግብፅ ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ ካሊድ ፋውዚ (khalid Fawzy)

2- ፍልስጤማዊው መሃመድ ዳህላን (Mohammed Dahlan)

3- ለግዜው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ፣

4- የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆነው አቶ  ጌታቸው ረዳ ካሕሳይ ናቸው።

መሃመድ ዳህላን የግብፅ ድህንነት መስሪያ ቤት ቅጥረኛ ሲሆን ነዋሪነቱን በተባበሩት አረብ ኢሜሬት ነው። ይህ ግለሰብ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበረበት ወቅት አደራዳሪ መስሎ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ነበር። በዚህ አጋጣሚ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የፈጠሩት ወዳጅነት ከዱባይ ከተማ እስከ ካሪቢያን ደሴቶች ድረስ ለሽርሽር እስከመሄድ አድርሷቸዋል። በሁለቱ መካከል ያለው ወዳጅነት ከራሳቸው አልፎ በምስሉ ላይ ከምታዩት የግብጹ ደህንነት ኃላፊ ካሊድ ፋውዚ (khalid Fawzy) ጋር ወዳጅነት እንዲመሰርቱ አስችሏቸዋል። የአራቱ ሰዎች ምስል ያለበት ፎቶ የተነሳው እዚሁ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ውስጥ ነው። …….

…..ከጥንት ዘመን ጀምሮ አንድ ያልተቀየረ የግብፃዊያን ታሪክ ቢኖር ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ያደረጉት ሙከራ በሙሉ በሽንፈት መጠናቀቁ ነው። ህወሓቶች ከግብፃዊያን ጋር በመመሳጠር የኢትዮጵያን ጥቅምና ሉዓላዊነት የሚፃረር ፕሮፖዛል ማዘጋጀታቸው ግን ሀገርን ከመሸጥ ተለይቶ አይታይም። በተለይ የህወሓት/ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆነው አቶ ጌታቸው ረዳ ከውጪ ሀገር ደህንነት ኃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ለፈጸመው አሳፋሪ ድርጊት በሀገር ክህደት ሊጠየቅ ይገባል።(ስዩም ተሾመ)

Wednesday, September 25, 2019

አየ መምህርት መሰረት አበራ! ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)


አየ መምህርት መሰረት አበራ!
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)
የግብጾቹ የነ ጃራ የነ ኦነግ ባንዴራና ምስል ለብሰሽ ላማረብሽ መሰረት ሆይ!
የፌስ ቡክ ተከታዮቼ መልስ ከመጻፌ በፉት እኔ የአብንም ሆነ ያማንም ፓርቲ/ድርጅት አባል እንዳልሆንክ ይታወቅልኝ። አሁን ወደ ፀሓፊት መሰረት አበራ (አዲስ አበባ) ጥቅጥቅ ጽሑፍ ልውሰዳችሁ። በፌስ ቡክ ለማግኘት ጌታቸው ረዳ ብላችሁ ፕሮፋይል ጉግል ብታደርጉ ታገኙኛላችሁ። ድረገጼም ኢት ሰማይ ብላችሁ ማየት ትችላላችሁ።

“የአማራ ብሄርተኝነት ስንክሳር እና ያዘለው አደጋ (በመስከረም አበራ)September 25, 2019” በሚል ጽሑፍ ሳተናው ላይ ወጥቷል። የኔ ጽሑፍ በሳተናው ስለማይወጣ በራሴው ነፃ መድረክ ላይ ወጥቷል። መሰረት አባራ በብዙ መልኩ ታስገርመኛለች።
“የአማራ ብሄርተኝነት ስንክሳር እና ያዘለው አደጋ (በመስከረም አበራ)September 25, 2019” በሚል ጽሑፍ ላይ
እንዲህ ትላለች:-

“የአብን በአማራ ምሁራን ዘንድ ሞገስ ማጣት፡የአብን ቁጥነትና ፖለቲካዊ ክህሎት ማነስ…” እያለች የምታሳምረው ግሩም አማርኛዋ/ ተችትዋ/ ግራ ያጋባል።

ለመሆኑ የአማራ ምሁራን የምትያቸው ከቁጥነት የተቆጠቡ ትሁት አንደበቶች 28 አመት ሙሉ በትሁትነታቸው የማን ጸጉር ሲያበጥሩ ነበር? መልስ ቢኖርሽ ብትነግሪኝ ደስታውን አልችለውም። አንቺ እኔን ላታውቂኝ ይሆናል፤ 28 አመት ሙሉ ከቁጣ የራቁ እና በፖለቲካ የተካኑ ጠበብቶች (ላንቺ ደስ እንዲልሽ) ያንቺው ባለ ለዛዎቹ ምሁራን አማራ ‘እባካችሁ ሕዝባችሁ ችግር ላይ ነው ተንሱ ‘ ብየ ብኮርኩር ብኮረኩር ጀሮ ዳባ ብለው ሲያንኮራፉ የነበሩ ያንቺው “ምሁራን አማራ”  ኦነግን እና የግንቦት 7 መሪዎች ሲያቆለጳፕሱ“ ነበር የዘበኑት።  የምሁራን አማራ ሞገስ ያጣ ብለሽ የምታንኳስሺያቸው የአብን መሪዎችን ከመጠበቅ “ቁጡ ያልሆኑ ባለሞገስ አማራ ምሁራኖችሽ” ሜዳውም ፈረሱም ይኼው ክፍት ነው ለምን ባለ ሞገሶቹ ምሁራን “አብን እንዲታሰርላቸው እና እንዲከላከልላለቸው ይጠብቃሉ?“

ብስለት የሌላቸው ቁጡዎች” ብለሽ የምታበጥሪያቸው “የአብን ወጣቶች” የሚመራቸው ምሁር አማራ ስላልነበረ ራሳቸውን ማደራጀት ጀምረዋል። ይሰንፍጣቸው ይምረራቸው ሜዳው ክፍት ስለነበረ ያንን ሜዳ ይዘውታል። አንቺ ምሁራን አማራ የምትያቸው አብን ማበረታታት እና መምከር፤ማገዝና ማረም ካልቻሉ አንቺ እንደምትይው ‘አማራጭ’ ብለው ወደ ደመቀ መኮንን (የወያኔና ኦነግ አሽከር) ከሄዱ ተወቃሹ እንዴት አብን ሊሆን ይችላል? 


ልጥቀስ እንዲህ ነበር ያልሺው፦

“በዚህ መሃል ከኦሮሞ ብሄርተኝነት መጦዝ የተነሳ የአማራ ብሄርተኝነት እንዲኖር የሚፈልገው የተማረውን ጨምሮ በርካታው የአማራ ብሄር ተወላጅ ወደ አዴፓ እንዲያዘነብል እያደረገ ነው ፡፡”

አብን ጠልቶ ወደ ኦነግ አገልጋይ መሄድ ከመረጠ ድሮም ከእጅ የማይሻል ዶማ ስለነበር የሚያመጣው ለውጥ የለም። አንቺ የምታሞግሺያቸው አማራ ምሁራን “የአብን ቁጥነት ጠልተው፤ ችለታቸው መዝነው ” አዴፓ ጋር ሆነው ከነ አበራ አዳሙ ጋር ሆኖ  አማራውን ማሰርና ማሳሰር ካማረው ምሁሩ መንገዱ ጨርቅ ያድርገለት እላቸዋለሁ።”

አስገራሚ የሚያደርገው ጽሑፍሽ ደግሞ የሚከተለው ነው።-

“….ይህ ሳይሆን ቀርቶ ውህዱ ፓርቲ በሲቪክ ፖለቲካ ስም ለተረኛ ነኝ ባዩ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ሸብረክ የሚል ከሆነ የአማራ ምሁራንም ሆኑ ሌላው አብንን ለመቀላቀል እየተሸኮረመመ ያለው አማራ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ አክራሪ ብሄርተኝነት መንጎዱ አይቀርም፡፡” ብለሻል

አብን አክራሪ ነው በለሽ ስትከሺ በሽብረተኝነት /አክራሪነት/ ስም እየለጠፈ በየ ጨለማ ማጎርያ ቤት እያሰቃያቸው ያሉትን የአብን አመራሮችና አባላት “አክራሪዎች” ናቸው ብለሽ በይፋ ስለወነጀልሺያቸው ሰሞኑን ያመሰገንሺው “ያንቺው ሰዋዊ፤ሰዋዊ የሚሸትሽ አብይ አሕመድሽ” ስለ አብን አክራሪነት የምታውቂውን ለፍርድ ቤት ለምስክርነት ሊጠራሽ ስለሚችል ተዘጋጂ።

“ይህ ደግሞ የአማራ ክልልን ምናልባትም ታጣቂ ሸማቂዎች ጭምር የሚንቀሳቀሱበት ግልፅ የአመፅ ቀጠና ሊያደርገው ይችላል፡፡” ብለሻል

በፋሺሰቶች ላይ የትጥቅ ትግል አመጽ ማድረግ በየትኛው መጽሐፍ ያገኘሺው ሕግጋት ነው አንቺ አመፅን የምታወግዢው? 

መልካም የፍርድ ቤት ምስክርነት እንዲሆንልሽ እመኛለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

Tuesday, September 24, 2019

በፋሺሰቶቹ ወያኔዎች ሥርዓት የስለላና የጠለፋ ዋና መሪ የነበረው ኮሎኔል አብይ አሕመድ ዓሊ እስር ቤት ውስጥ ግፍ የፈጸሙ ግለሰቦች እንጂ አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሕልሙም በውኑም አልሞት አያውቅም ሲል እራሱን ነፃ ለማውጣት ሲያጭበረብር ይኼው። ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)


በፋሺሰቶቹ ወያኔዎች ሥርዓት የስለላና የጠለፋ ዋና መሪ የነበረው ኮሎኔል አብይ አሕመድ ዓሊ እስር ቤት ውስጥ ግፍ የፈጸሙ ግለሰቦች እንጂ አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሕልሙም በውኑም አልሞት አያውቅም ሲል እራሱን ነፃ ለማውጣት ሲያጭበረብር ይኼው።
 ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)

ዛሬ የምንነጋገረው 4 ወር ሥልጣን ላይ ከወጣ በተለጠፈው የቪዲዮ ሊንክ በምሥጢር የተቀዳ ኢሕአዴጋዊ ስብሰባ ላይ የተናገረው ንግግሩ ነው። ከእዚህ ጽሑፍ ተያይዞ የምታደምጡት ሥዕለ ድምፅ ከድምጽ ፋይሎቼ ያስቀመጥኩት አንዱ ‘አናርኪያዊ ፋሺሰቱ አብይ አሕመድ” እንዲህ ይላል።


“በምርማራ ቦታ ፤ፖሊሶች ወንድ ታስሮ አፉን እንዲከፍት አድርገው ሽንት ሲሸኑበት ነበር።በዚህ ደረጃ የሚያዋርድ ሥርዓት ኢሕአዴግ አስቦም አልሞም አያውቅም።” ሲል መርማሪ ግለሰዎች የፈጸሙት እንጂ በመንግሥት ደረጃ አልተፈጸመም ይለናል።


ልብ በሉ! ይህ ግፍ የተፈጸመባቸው እስረኞች “አማራዎች ናቸው (እነማን እንደሆኑ ለብዙዎቻችሁ ግልጽ ነው ብየ አምናለሁ። እስረኞቹ በአማርኛ የእጅ ጽሑፍ የላኩት ሰነድ በታይፕ በወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ በወቅቱ ተሰራጭቶ ስለነበር ስማቸውን ታገኙታላችሁ)።


እንዲህ ያለ ግፍ የተፈጸመባቸው አማራዎች እንጂ ትግሬዎች ወይንም ኦሮሞዎች አይደሉም። አማራ ደግሞ በወያኔ/ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ /በወያኔ/በኢሕአዴግ/ በወያኔ/ በመንግሥት ፖሊሲ የአማራን ህይወት ሰላም እንድታጣ እናደርጋለን’ ብሎ በፕሮግራሙ ቀርጾ “ኦርቶዶክስን፤ ሰንደቃላማችንን እና አማራን/ኢትዮጵያን” ሦስቱ/አራቱ/ በጠላትነት ፈርጆ ወደ ሥልጣን በመምጣት “ነፍጠኛ በሚል ስም” ሰይሞ ከፕሮፌሰር አስራት ጀምሮ እስከ አሳምነው ጽጌ እና ኣእላፍ አማራዎችን ከምድረገጽ እንዲጠፉ ያደረገ ሥርዓት መሆኑን ልብ በሉ።


አብይ እራሱም የአማራ ጥያቄዎችንና እሮሮዎችን እንዴት እያሳነሰ ወደ ታች እያወረደ፤ በአደባባይ ወጥቶ በግልጽ ሲናገር እንደነበር ከመጀመሪያ አገራዊ ጉብኝቱ ከመቀሌ ጀምሮ ወደ ባሕር ዳር መጥቶ ቆይቶም እስከ ደሴ እና አዲስ አበባ መድረኮች ንግግሮቹን ማስረጃዎች ናቸው። እነዚህ ለማንበብ በራሴው ኢትዮ ሰማይ ድረግጽ ታገኝዋቸዋላችሁ።


ስለዚህም የአብይ ቅጥፈት እና አጭበርባሪ ልሳን መመክት አስፈላጊ ነው እና ተከታተሉኝ።  የአብይ አድናቂዎች እና ተከታዮቹ ላያምኑ ይችላሉ። ሳይወዱ ባርያ ከሆኑ ሰዎች ይልቅ ወድደው ባሮች የሆኑ እነዚህ የሕሊና ባርያዎች ከባርነት የወጡ የመሰላቸው አሳዛን ባሮች ስለሆኑ ከነሱ የሚጠበቅ የለምና ወደ እውነታው እንሂድ።


“በምርማራ ቦታ ፤ፖሊሶች ወንድ ታስሮ አፉን እንዲከፍት አድርገው ሽንት ሲሸኑበት ነበር።በዚህ ደረጃ የሚያዋርድ ሥርዓት ኢሕአዴግ አስቦም አልሞም አያውቅም።


የሚለው አጭበርባሪው አብይ አሕመድ ግን በራሱ ፓርላማ ላይ ቀርቦ “በዜጎች ላይ ግፍ የፈጸመው መንግሥት ነው”፤“መንግሥት አሸባሪ ነው፡ እኛ አሸባሪዎች ነን!!” ሲል ይቅርታ የጠየቀበትን ንግግሩን ለውጦ በግል አቻዎቹን ጠርቶ ሲናገር ግን “እስር ቤት የተፈጸመው ኢሰብኣዊ ድርጊት አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚመራው ኢሕአዴግ ሳይሆን ‘ግለሰቦች’ የፈጸሙት ነው” በማለት “ኢሕአዴግ በሰብኣዊነትና በሕግ የሚመራ ሥርዓት ነው” ሲል ፋሺሰታዊው የህወሓት ዲሞክራሲያዊ አብዮትን ያሞካሻል።


ታስታውሱ እንደሆን ግብረሰዶም የተፈጸመበት አንድ እስረኛ እና ተፈጽሞብኛል ብሎ ለተናገረው ለአንድ ታሳሪ እስረኛ አባይ ፀሃየ እና አዲሱ ለገሰ በሰላዮቻቸው በኩል ምስጢሩን ካወቁት በሗላ ‘ወደ እስር ቤት በመሄድ “ምስጢሩን” ለማንም ሰው ነግራችሁ ብትገኙ “በህይወታችሁ እንደፈረዳችሁ ቁጠሩት” ብለው  እነዚህን ሁለት ሰዎች እንዳስጠነቀቅዋቸው ታሳሪው ምስክር ከተፈታ በሗላ የተናገረውን በዩቱብ እንዳደመጣችሁት ተስፋ አለኝ።

የግለሰቦች ተግባር ቢሆን ኖሮ፤ እነዚህ የሥርዓቱ መሪዎች ግለሰቦቹን በይፋ ፍርድ ቤት ቀርበው ያስቀጥዋቸው ነበር። ሆኖም “አብይ” የሚመጻደቅበት “የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ድርጅት” መሪዎች ግን በረሃ እያሉ “ሰው ሲገድሉ፤ ሰው በእሳትና በፈላ ዘይት እያቃጠሉ ሲመረምሩ፤ ብዙ ግፍ ሲፈጽሙት የነበሩ ግፈኞች ስለነበሩ፤ እስር ቤት ውስጥም እንድያ ያለ ዘግናኝ ግፍ በራሳቸው አመራርና ትዕዛዝ የሚካሄድ ዘግናኝ ግፍ መሆኑን ስለሚያወቁ በተገላቢጦሽ “ተጠቂዎችን ነበር በተቃራኒ ምስጢሩን እንዳያወጡ  ያስጠነቀቅዋቸው”።


እነዚህ ሁለት ሰዎች በተለይ አባይ ፀሐየ የኢሕዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ (ፋሺዝም ማለት ነው) ከሚመሩ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ከፈጠሩት አንዱ እና ቁንጮ የፖሊሲ እና የፖለቲካው ሞተሩ ነው። አብይ አሕመድ ግን የዚህ ፋሺሰት ሥርዓት የስለላና የደህንነቱ መዋቅር ዋናው አንቀሳቃሽ እና ምስጢር ጠላፊ በነበረበት አሳፋሪ አገልግሎቱን ለመደበቅ ሲል የተፈጸሙ ወንጀሎች ሁሉ “ተራ ፖሊሶች/መርማሪዎች የፈጸሙት እንጂ መንግሥት አይደለም እያለ የምርመራው ክፍል “መንግሥታዊ መዋቅር” እንዳልሆነ እና መዋቅሩ ከላይ ሳያዛቸው ማንኛውንም ግፍ በራሳቸው እንደሚፈጽሙ አድርጎ ለማቅረብ የወንጀል ታሪክ ለመደበቅ ሞክሯል።


ኢሕዴግ ብሎ ራሱን የሚጠራ የፋሺሰቶች ጥርቅም “አዲስ አበባ እና ሌሎች ቦታዎች” እራሱ ቦምብ እያጠመደ ሲያጋይና ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድል እንደነበር ጃፓናዊ አሜሪካዊው የመለስ ዜናዊ ወዳጅ አምባሳደር ያማሜቶ ለዋሺንግቶን ያስተላለፈው ምስጢራዊ የፋክስ ምስጢር ‘በዊኪ ሊኪ’ ተጠልፎ ይፋ መሆኑን እናውቃለን።


 አጭበርባሪው አብይ አሕመድ ግን ህወሓት/ኢሕአዴግ በእንዲህ ያለ የሽብር ስራ ተጠምዶ ሲፈጽም እንደነበር እያወቀ፤ ዛሬ ያንን ድብቅ ሽብሩን እና ሰብኣዊ ጥሰቱን ለመደበቅ እንዲያመቸው “የግለሰቦች (ፖሊሶች/መርማሪዎች) በራሳቸው ተነሳሽነት የፈጸሙት ድርጊት እንጂ “ኢሕአዴግ አያደርገውም ብሏል።

 አዎ ሊያምን አይችልም። ምክንያቱም እሱም የስለላውና የጠለፋው የማሰቃያ ቅርንጫፍ ክፍል አንደኛው ቅርንጫፍ መሪ ነበርና ራሱን ነፃ ለማውጣት ነው “የምርመራ ግፎች የመርማሪ ግለሰቦች እንጂ ኢሕአዴግ በውኑም በሕልሙም አያደርገውም” እያለ ወያኔ /ኢሕዴግ የፈጸመው ወንጀል ነፃ ሊያደርገው እየሞከረ ያለው። ለዚህ ነው ባለፈው ሰሞን ኦርቶዶክስን ይቅርታ አልጠይቅም የሚለው።


 አሜሪካ አገር ውስጥ አንድ ሰራተኛ በሌሎች ተገልጋየች ላይ ጥፋት ከፈጸመ “የኩባንያው አስተዳዳሪዎች/ መሪዎች/ ባለቤቶች” በኩባንያው ስም ይቀርታ ይጠይቃሉ። አጭበርባሪው አብይ ግን እኔ ቤተክርስትያን አላቀጠልኩም ከሕናት አልገደለኩም ስለዚህ ይቅርታ አልጠይቅም ብሏል። የሠለጠነ የተደመረ ጭንቅላት የወያኔዎች ኢሕአዴግ ምሩቅ ተማሪ ማለት ይኼ ነው!


ከዚህ ሌላ በዚህ ቪዲዮ ውስጥ- ትግሬዎች ተጠቃሚ ነበሩ የሚለው “ውሸት’ እንደነበር እና ዛሬ ያንን ውሸት ቦታ እንደሌለው በከንቱ ሲዘባርቅ ታደምጡታላችሁ።


እውነታው ግን እኔም ሆንኩ ጥቂት ጓዶቼ “ትግሬዎች ተጠቃሚዎች ነበሩ ብለን በግሃድ ተከራክረናል፤ዛሬም ተጠቃሚዎች ናቸው። ያ ካልሆነ ሌላውን ማሕደር ወደ ሌላ ቀን አቆይተን “የወልቃይትና የራያ ሰፋፊ ለም መሬቶች በጠብመንጃ ሃይል ወደ ትግሬ ቀላቅሎ የነጠቃቸው ለም መሬቶች ለማን ነው የሰጠው? ትግሬዎች የበላይነትን ተጎናጽፈው እዛው የነበሩ ነባር ኗሪዎችን አፈናቅለው፤ ገድለው፤ ገርፈው፤ አስሰድደው፤ ሴቶችን ዘርፈው (ሬፕ በማድረግ) የትግራይ ታጋዮቹ እና አዳዳዲስ ሰፋሪዎች በማስፈር በሺዎቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገው ለማን ጥቅም ሲባል ነበር? ለትግሬዎች ነው፤ አይደለም እንዴ?


የፋሺሰቶች ስነ ምግባር “አሞጋሽ” የሆነው አብይ አሕመድ ትግሬዎች በህወሓት ሥርዓት አልተጠቀሙም ብሎ ሲል ይህን በምን ሊመልሰው ይቻለዋል? ለማንኛውም በምስጢር የተቀዳው የአብይ አሕመድ አጭበርባሪ ልሳን አድምጡ። እነሆ። አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
  ዶር አብይ አህመድ አስደንጋጭ ትእዛዝ ሲሰጡ በድብቅ የተቀረፀ ቪዲዮ ይፋ ሆነ


Monday, September 23, 2019

በእውኑ ኢትዮጵያ መንግሥት አላትን? ብሥራት ደረሰ (posted on Ethio Semay)


በእውኑ ኢትዮጵያ መንግሥት አላትን?
ብሥራት ደረሰ (posted on Ethio Semay)

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት መንግሥት አላት ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ በተሳሳተና ወደ አንድ ወገን ባጋደለ የኦነግ/ኦህዲድ ቅኝ ግዛታዊ አገዛዝ ሥር ወድቀናል፡፡ ይህን ገሃድ የወጣ ሀገራዊ እውነት በምንም መንገድ ለመደበቅ ወይም ለማስተባበል መሻት የኦነግ/ኦህዲድን የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ ወዶና ፈቅዶ ለመቀበል እንደመዘጋጀት ይቆጠራል፡፡ በዚህ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ስም እየማላችሁና እየተገዘታችሁ በሥውርና በግልጽ ግን ኢትዮጵያን እያወደመ ከሚገኘው ኦነግ/ኦህዲድ ጋር የምትሞዳሞዱ ተቃዋሚ ተብዬዎች እጃችሁን ከዚህች ቅድስት ሀገር እንድታነሱ ማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡  የብዙኃን ዕንባ የሚያስከትለውን የቅጣት ዶፍ በሚገባ የምንረዳ ወገኖች መጪው ዘመን ለማን ምን ይዞ በመገስገስ ላይ እንደሆነ መገመት አይከብድምና ለሌላ ሳይሆን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡

በኢትዮ - ኦሮ እና በፊንፊኔ - አዲስ አበባ ተወጥራ ልትፈነዳ የደረሰች ሀገር ውስጥ መኖር ከጀመርን አንድ ዓመት ከመንፈቅ ሆነን፡፡ እመለስበታለሁ፡፡

በዜጎችና በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ በትናንትናው ዕለት በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች የተደረገው ሰላማዊ ሠልፍ እጅግ ደማቅና የሀገራዊ ትንሣኤያችንን ጅማሮ አመላካች ነበር፡፡ በሕይወቴ ከተደሰትኩባቸው ቀናት አንዱ ትናንት ነበር፡፡ምንም እንኳን የመንግሥት ሚዲያዎች ተኩረት በሌላ ግንጥል ጌጥ ላይ ሆኖ ይህ ክስተት በነሱ በወጉ ባይሸፈንም ባሉን ሌሎች አማራጭ የዜና አውታሮች እንደተከታተልነው የሕዝባችን ተነሳሽነት በእጅጉ አበረታች ነው፡፡ ይህን የሕዝብና የሀገር ጩኸትና ዋይታ የራሔልን ዕንባ ከጽርሐ አርያም ሰምቶ በሕወሓት-ኦህዲዳዊ የፈርዖን አገዛዝ ሥር ለነበሩ እሥራኤላውያን ሙሤን የላከላቸው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይሰማል፡፡ ሰምቶም ዝም አይልም፡፡ ሁነኛ መሢሑን ይልካል፡፡ በዚህ ጥርጥር የለንም፡፡

በተመሳሳይ ወቅት በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ ላይ የተካሄደው የኢሬቻ ሩጫ ግሩም አጀማመርና አጨራረስ ነበረው፡፡ በሰላም ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁ አስደሳች ነበር፡፡ የአዲስ አበባና (የፊንፊኔ ለማለት ነው) የ“ኦሮሚያ ክልል” ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሣ በኦሮምኛ የተናገሩትን ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ስሰማው ግን አስከፍቶኛል፡፡ “አበበ ቢቂላና ደራርቱ ቱሉን የመሰሉ የኦሮሞ ልጆች በጨለማው ዘመን የብሔራችንን ስም ከፍ ብሎ እንዲጠራ የድርሻቸውን ተወጥተዋል....” ዓይነት ንግግር ማድረጋቸው ነውር ነው፡፡ የጨለማ ዘመን ያሉት ለኦሮሞ ብቻ ከሆነ በተለይ ትልቅ ነውር ነው፡፡አላልኩም ካሉም ማስተባበያቸውን ይንገሩን። 

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ኦሮሞ ነበሩ፤ ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ኦሮሞ ነበሩ፤ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ኦሮሞ ነበሩ፤ ደበላ ዲንሣ፣ ጄኔራሎች ጃጋማ ኬሎ፣ ደምሤ ቡልቶ፣ ... እነዚህና ሌሎችም ኦሮሞ ነገሥታት፣ የሀገር መሪዎችና የጦር አበጋዞች ከጃዋር ሞሀመድ የበለጡ ኦሮሞዎች ነበሩ፡፡ እርሳቸው ግን ከቋንቋው በስተቀር አንድም የኦሮሞ ደም ከሌለበት ከፊል የመናዊ ሰው አጠገብ ቀምጠውና ከዚህ ኦሮሞ ያልሆነ ሀገር ሻጭ የዐረብ ደላላ ጋር እየተቃቀፉ የኦሮሞዎችን ሀገር የአማሮች ለማስመሰል ባደረጉት ከንቱ ሙከራ አሁን ላይ ሆነን የኋሊት ስንመለከተው ለኛ ለጭቁኖች ወርቃማና ብርሃናማ የነበረውን ዘመን “የጨለማ ዘመን” አሉ፡፡ ፈጣሪ ፍርዱን ይስጣቸው፡፡ ለዚህ ጀብደኛ አነጋገር ያበቃቸው ራሱ አዴፓን ወይም ብአዴንን ተመስሎ በአማራው ሕዝብ ስም የሚንቀሳቀሰው የሠርጎ ገቦች ጥርቅሙ ድርጅት መሆኑን ሊረዱ በተገባቸው ነበር፡፡ ቀሪውን የንግግራቸውን ስህተት በጊዜ ሂደት ያወራርዱታል፡፡ አንቸኩልም፡፡

እመለስበታለሁ ወዳልኩት ተመለስኩ፡፡ አዲስ አበባን የተቆጣጠረ ኢትዮጵያንም እንደሚቆጣጠር የታመነ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከአሥመራ ተለምኖ ከአንድ ሽህ ሁለት መቶ ጥገኛ ወታደሮቹ ጋር ወደ መሀል አገር የገባው ኦነግ ዕድሜ ለልጆቹ ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖለት አዲስ አበባን ብቻ ሣይሆን መላዋን ሀገራችንን በሚገባ ተቆጣጥሯል፡፡ ይህን ሃቅ መካድ የኅሊና መታወር ነው፡፡

ከሞላ ጎደል ሁሉንም የ“ፌዴራል” የሥልጣን ቦታዎች በቀጥታና በተዛዋሪ የተቆጣጠረው ኦነግ/ኦህዲድ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ኦሮምያ የሚባለው ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ አዲስ አበባ እንደመሆኑ የፌዴራል ተብዬው መንግሥት በዚህ ክልል መንግሥት ተፅዕኖ ሥር ወድቆ አዲስ አበባ የሁለት መንግሥታት ተዕዛዛት ፈጻሚና አስፈጻሚ ሆናለች፤ ልትፈነዳ የቀራት አንድ እሬቻ ማነው አንድ ሐሙስ ቢሆን ነው፡፡ በምሣሌ ላስረዳ፡፡ አ.አ የሚል የመኪና ታርጋ አለ፡፡ ኢትዮ የሚል የመኪና ታርጋ አለ፡፡ ኦሮ የሚል የመኪና ታርጋ አለ - መኪናና ሌላው ንብረትም በጎሣ መጠራቱን ልብ በሉ በዚህ አጋጣሚ ታዲያ፡፡ ደሕ፣አማ፣ሱማ፣ትግ፣... የሚሉም አሉ፡፡ ልብ አድርጉ! በአዲስ አበባ አ.አ የሚልና ኢትዮ የሚል ታርጋ ነበሩ እንደልባቸው የሚንቀሳቀሱት፡፡ ሌሎች እንደ ደሕ. (ደቡብ ሐዝቦች) ያሉት እንደተላላፊ ወይም እንደ አድሮ ሂያጅ እንግዳ ነበር እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቀድላቸው - ከተሳሳትኩ እታረማለሁ፡፡ አሁን ባለው የመንግሥት አወቃቀር ግን አዲስ አበባ ራሷ በፊንፊኔ የዋቄ ፈታ ስም በጉልበትና በማን አለብኝነት የዘረኝነት ጥልፍልፎሽ የፌዴራልና የኦሮምያ ዋና ከተማ ሆናለችና ኦሮ. የሚል ታርጋ አዲስ አበቤ ሆኗል፡፡ 

አ.አ የሚል ታክሲም ሆነ የቤት መኪና የሚተዳደረው በአዲስ አበባ የክልል መስተዳድር ፖሊስና የመንገድ ባለሥልጣን ሲሆን ኦሮ. የሚል ማንኛውም ተሸከርካሪ የሚተዳደረው ደግሞ በዚችው ከተማ በሠፈረው  የኦሮምያ ክልል ፖሊስና የመንገድ ባለሥልጣን ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች ባመቻቸው ቢሮ እየሄዱ ይስተናገዳሉ - በተለይ ኦሮምኛ የሚችል እልል በቅምጤ እያለ ነው፡፡ ዜጎች የአዲስ አበባው ሲጠብቅባቸው ወደፊንፊኔው ያመራሉ፡፡ የፊንፊኔው ያዝ ሲያደርጋቸው ወደ አዲስ አበባ ይሄዳሉ -  በዓለማችን የመጀመሪያዋ የሁለት መንግሥታት ዋና ከተማ - አዲስ አበባና ፊንፊኔ - አንድም ሁለትም፡፡ ዕርግብም እባብም፡፡ ቫቲካን እንኳን ለራሷ ተከልላ በሊቀ ጳጳሱ ሥር ነው የምትተዳደረው - መሀል ሮም፡፡ የኛ ግን ፊስቱላ ገጥሟታል - መደበላለቅና የለዬላት ባቢሎን መሆን፡፡ 

በምሣሌ ላይ ሌላ ምሣሌ ልስጥና - ለምሣሌ አንድ ቁጥር ታክሲ በአዲስ አበባ ቀርቷል - ፈቃድ አይሰጥም፡፡ በሌላዋ አዲስ አበባ ማለትም በፊንፊኔ ግን አለ፡፡ ስለዚህ 20ሽህ ብርና ከዚያ በላይ ጉቦ እየከፈሉ በዚያኛው መንግሥት ፈቃድ በማውጣት በአንዲት ከተማ የሁለት “ሀገራት” ታክሲዎች ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም - ሌላው ነገር ሁሉ ልክ እንደዚህ ነው፤ የጨረባ ተዝካር፡፡ አዲሶቹ ገዢዎች ደግሞ ጉቦ ሲጠይቁ ዐይን የላቸውም አሉ - አምስት ሽህ ብር ለምታገኝበት ጉዳይ ሃምሣ ሽህ ብር ጉቦ ሊጠይቁህ ይችላሉ - ጉቦም እኮ ዕውቀት ይጠይቃል ወንድሜ፡፡ እነሱ ግን ምን ገዷቸው! እከሳለሁ ብትል “ሰባራ ዶሮ ሳቲቃድሚህ ወደፈለካው ሄዴ ኪሰስ፤ ኢልማ ሃጥራው!” ቢሉህ እንዳይደንቅህ - ከየወረዳውና ክፍለ ከተማው የምንሰማው ጉድ ይሄንኑ ነውና በዚህ አልኮነንም፡፡ ወይ ጊዜ መስታወቱ!... (የምን ዝምታ ነው? ትንሽ ፈገግ በሉ እንጂ! እነአባ ጫላና ገመዳም የዲጂታል ኦህዲድ ጦራችሁን ምዘዙና እንደለመደባችሁ የክት ስድቦቻችሁን ዘክዝኩ፤ ወገናዊነት ለመቼ ሊሆናችሁ ትቆጥቡታላችሁ? አይዟችሁ እንጀራችሁ መሆኑን ስለምናምን ከፈገግታ በስተቀር አንከፋባችሁም፡፡ ለምኑ ብለን?)

  በዚህ መንገድ አዲስ አበባ እንደፉክክር ደጃፍ ሳትዘጋ እያደረች ለማንም ቀማኛና ወሮበላ ምቹ እንደሆነች አለች፡፡ እኛም ኤሎሄያችንን ቀጥለናል፡፡ መልስ የምናገኝበት ጊዜም በጣም ቅርብ ነው፡፡ ተስፋህ ሲጨልም ከወዲህ፣ ሌላ ተስፋህ ይፈነጥቃል - ከወዲያ፡፡ አይዞን!



Thursday, September 19, 2019

ኢሬቻ የኦሮሞ ብሔርተኞች «መንግሥት» እና ሃይማኖት አንድ መሆናቸው ማሳያ! (አቻምየለህ ታምሩ) Posted on Ethio Semay (Important document –a must read!)



ኢሬቻ የኦሮሞ ብሔርተኞች «መንግሥት» እና ሃይማኖት አንድ መሆናቸው ማሳያ! (አቻምየለህ ታምሩ)

Posted on Ethio Semay (Important document –a must read!)

የኦሮሞ ብሔርተኞች በዐፄዎቹ ዘመን ነበር የሚሉትን  የመንግሥትና ሃይማኖት አንድነት ለማስቀረትና መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩበት አገር እንዲፈጠር ጫካ ወረድን ቢሉንም ስልጣን ሲይዙ  ግን መንግሥትና ሃይማኖትን አንድ አድርገው ሃይማኖታዊ በዓል ለማክበር ሽር ብትን እያሉ ናቸው! ሃይማኖት  የሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር  ግንኙነት የሚያደርግበት ሥርዓት ነው። ክርስትና፣ እስልምና፣ ዋቄፈታ፣ ወዘተ አማኞች እንደየቤተ እምነታቸው አማኞቹ ከፈጣሬያቸው ጋር ግንኙነት የሚያደርጉባቸው የአገራችን ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ናቸው። ኢሬቻ የዋቄፈታ እምነት ተከታዮች ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙበት ሃይማኖታዊ በዓል ነው። እሬቻ  ሃይማኖታዊ  በዓል እንደመሆኑ መጠውን እውነተኛ  የክርስትናና  የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ሃይማኖት የሌላቸው ኢትዮጵያውያን የሚያከብሩት በዓል አይደለም። አንዳንዱ ኢሬቻን  ሃይማኖታዊ በዓል ሳይሆን  ባሕል ሊያደርገው ይፈልጋል። ሆኖም ግን  ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው።

ሊቁ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን  ከጦብያ መጽሔት ጋር በ1990 ዓ.ም. ባደረገው ቃለ ምልልስ ስለ ኢሬቻ ሃይማኖታዊ በዓልነት የሚከተለውን ተናግሯል፤ «በኦሮሞ ዘንድ በገዳ ትዛዛት እየተመሩ የሁሉን ፈጣሪ አንድ አምላክ ዋቃን ማምለክ ዋቄፈና ይባላል። ዋቄፈና  ይማኖት ነው። እሬቻ ደግሞ የዋቄፈና እምነት  አካል ነው። ምዕመኑ  ተሰብስቦ ለምለም ቄጠማ፤ አረንጓዴ ቅጠል፤ አበባ…ይዞ ፤ዋቃን በወንዝ ወይም በሐይቅ ዳርቻ ወይም በተራራ ላይ የማመስገን፤ የማክበር ፤የማምለክ በአል ነው – ኢሬቻ፤ የፀሎት ቀን ነው እሬቻ። ኢሬቻ ብዙ አይነት ቢሆንም ዋናዎቹ ሁለት ናቸው፤ ኢሬቻ መልካ  እና እሬቻ ቱሉ። ኢሬቻ መልካ በውሃ ዳርቻ ክረምት እንደወጣ ይከበራል። ይበልጡን ምድርን በዝናብ ያጠገበውን ዋቃ በምስጋና የመዘከር በአል ነው። እሬቻ ቱሉ ደግሞ  በተራራ ጫፍ ላይ በበጋው መሀል ይከበራል። ዝናቡ እንዳምናው በወቅቱ እንዲመጣ ዋቃ ይለመናል። ይበልጡን የፀሎት በአል ነው። ቢሆንም…ቡራኬው፤ምስጋናው፤ ፀሎቱ በሁለቱም ኢሬቻ አይቀርም። ለተራራው ወይም ለወንዙ አይሰገድም። እነሱን ለፈጠረ ፤ አምላክ ነው የሚሰገደው። በእምነቱ ልምላሜ እና ውሃ የአምላክ መንፈስ ማደርያ፤ ንፁህ የአምልኮት ስፍራ ነው። ለፀሎት ምቹ እና ሰላማዊ ቦታ ነው። እናም በኢሬቻ መልካ በአል የተፈጥሮን ኡደት ሳያዛባ ያስቀጠለ ዋቃ ይመሰገናል። ዋቃ ይከበራል። ዋቅ ይመለካል።» [ምንጭ፡ ጦብያ መጽሔት፣ ቅጽ 5፣ ቁጥር 11፥ 1990 ዓ.ም.፤ ከገጽ 8-12] ይህ የሎሬት ጸጋዬ ገለጻ በግልጽ እንደሚያሳየው ኢሬቻ የዋቄፈታ ሃይማኖት በዓል ነው። 

ሰው ከፈጣሪው ጋር የሚገናኝበትና ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ማናቸውም  ስርዓት ሃይማኖታዊ እንጂ ባሕል ሊሆን አይችልም። ኢሬቻ  የጥምቀት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እንደሚከበረው ሁሉ በዋቄፈታ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር ሃይማኖታዊ በዓል ነው። ኢሬቻ ባሕላዊ እንጂ ሃይማኖታዊ አይደለም የሚል ቢኖር አንድ የኦሮሞ ኡስታዝ ወይም ሼህ ቄጠማ ይዞ፣ ወንዝ ዳር ወሮች ኢሬቻን ሲያከብር ያሳየን!

የኢትዮጵያ ነገሥታትን ሃይማኖትና መንግሥትን አንድ አድርገዋል በማለት ሲያወግዙ የኖሩት የኦሮሞ ብሔርተኞች መንግሥትና ሃይማኖት እንዲለያዩ ታግለናል ሲሉን  እንዳልኖሩ ሁሉ  ዛሬ በመንግሥትነት ሲሰየሙ ግን  የዋቄፈታ ሃይማኖት በዓል የሆነውን ኢሬቻን በመንግሥት ደረጃ ለማክበር  ዝግጅት ማድረጋቸው የኦሮሞ ብሔርተኞች የታገሉት ኢፍትሐዊነት እንደሌላቸው ነው። የኢትዮጵያ ነገሥታትን መንግሥትና ሃይማኖትን ሳይለያዩ ቤተክርስቲያን ይተክሉ ነበር በማለት ሲያወግዟቸው እንዳልኖሩ ሁሉ ዛሬ እነሱ ግን ዛሬ በመንግሥትነት ሲሰየሙ መንግሥትና ሃይማኖትን አንድ አድርገው በመንግሥት በጀት የሃይማኖት  በዓልን በመንግሥት ደረጃ እንዲከበር የዋቄፈታ ሃይማኖት በዓል የሆነው ኢሬቻ የሚከበርበት ወንዝ ይቆፍራሉ፣ በመንግሥት ደረጃ የኢሬቻ ሩጫ ያዘጋጃሉ።

 ኦነጋውያን በየመድረኩ እየተገኙ ሕገ መንግሥት ተብዮው ካልተከበረ ሞተን እንገኛለን  እንዳላሉን ሁሉ  እነሱ ግን «መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው» የሚለውን የሕገ መንግሥታቸውን አንቀጽ ጥርሱን እያራገፉ ኦሮምያ  የሚባለው ክልል መንግሥታቸው ከመንግሥት ካዝና ብዙ ሚሊዮን ብር መድቦ በመንግሥት ደረጃ  በዓሉን የሚያስተናብር አካል  በማቋቋም ሃይማኖታዊውን በዓል ኢሬቻን  ለማክበር ሽርጉድ እያሉ ናቸው። ለዚህም ነው የኦነጋውያንን ፖለቲካ በቅርበት ያጠናን ሰዎች  ኦነጋውያን  የታገሉት ጭቆናን ጠልተው ለዲሞክራሲ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወግተው ኦሮምያ የምትባል አገር ለመፍጠር ብቻ ነው የምንለው። ኦነጋውያን መንግሥትና ሃይማኖትን አንድ እያደረጉ ጥርሱን የሚያረግፉትን «ሕገ መንግሥት» ካላስከበርነው ሞተን እንገኛለን የሚሉን የሕግ መጣስ አሳስቧቸው ሳይሆን  «ሕገ መንግሥቱ» በኢትዮጵያ መንበረ መንግሥት ተሰይመው  የሌላውን ሀብትና መሬት እየዘረፉ ለመመስረት የሚያስቡትን የተስፋ አገር ለማበልጸግ የሚያስችላቸውን  የአፓርታይድ ስርዓት ለመዘርጋት  የሚያስችል አይነተኛ መሳሪያ እንደሆነ ስለሚያውቁ ነው። የኦሮሞ ብሔርተኞች በመንግሥትነት ከተሰየሙ በኋላ  ያስቀጠሉትን የአፓርታይድ ዓለም ሕጋዊ ለማድረግ  ሕገ መንግሥት ተብዮው የማይጠቅማቸው ቢሆን  ኖሮ ከሁሉ በፊት ሕገ መንግሥቱ ካልተቀየረ ሞተን እናድራለን ብለው  መንጋቸው ሰልፍ እንዲወጣ የሚቀሰቅሱ  እነሱ ነበሩ።
Posted on  Ethio Semay