Sunday, August 21, 2022

የአሸንዳ/አሸንድየ ሰርዓት እና የወያኔ ትግሬዎች ፓለቲካዊ ጣልቃ ገብነት (ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)





አብይ አሕመድ የግንቦት 7 የመረጃ አቀባይ እንደነበር ሰማችሁ? ይህንን ጉድ አድምጡ ! (ጌታቸው ረዳ Ethio Semay)
Ethiopia |ዋልያ ኢንፎርሜሽን | ያልተነገረው የአቶ አንዳርጋቸው ንግግር በቶሮንቶ


የአሸንዳ/አሸንድየ ሰርዓት እና የወያኔ ትግሬዎች ፓለቲካዊ ጣልቃ ገብነት
(ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
ይህች ልጅ የኔ ልጅ  ናት። ባለሽበት ትግራይ ውስጥ መልካም አሸንዳ ይሁንልሸ! (Ethio Semay)

ልጄ 3 አመት በፊት ጦርነቱ ከመከፈቱ በፊት መቀሌ ትግራይ  አሸንዳ ስታከብር የተቀረጸ የማስታወሻ ፎቶ ነው።

እንኳን ለአሸንዳ በዓል አደረሳችሁ!

ይህ ጽሑፍ “የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው የጥላቻ መነሻ ምንድነው?” ከሚለው ከራሴው መጽሐፍ “የትግሬዎች ፋሺዝም” ከሚለው ንኡስ ምዕራፍ የተወሰደ (ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay)

ማሳሰቢያ

ካለፈው ክፍል 2 የቀጠለ ክፍል 3። (የመጨረሻ ክፍል)
በክፍል፤ በክፍል የተጠቀሰበት  ምክንያት አምና በትግራይ በመቀሌ ከተማ ሲካሄዱ የነበሩ ስብሰባዎች ሲደመጡ የነበሩ ጸረ አማራ እና ፋሲስታዊ ትምክሕት እንዲሁም ስለ አሸንድየ/አሸንዳ/ በዓል አስመልክቶ  “ሃይማኖታዊ-በዓል ነው” ተብሎ በሚነገርለት በዚህ በዓል ላይ ወያኔዎች ፋሺሰታዊ ባሕሪያቸው ተሞርኩዘው ፖቲካዊ እንዲሆን በማድረግ በመድረኩ ላይ በሺዎች የሚቀጠሩ ሕፃናት ልጃገረዶች እና ወንዶች በሚጨፍሩበት መጨፈሪያ ቦታ የወያኔ የኪነት ቡድኖችን በማሰማራት ፖለቲካዊ አዘል ዘፈኖችን በመዝፈን በዓሉን ፖለቲካዊ እንዲሆን ያደረጉትን ሁኔታ በመቃወም ያንን ለማጋለጥ በትግርኛ ጽፌ በኢንተርኔት ተለጥፎ የነበረ ነው። ለዚህ ነው ከላይ ክፍል 2- ክፍል 3- የሚለው። አማርኛው ትርጉም እንዲህ ይቀጥላል፡


ጽሑፌ ከመጀመሬ በፊት ስለ አሸንዳ ትንሽ ልበል። ‘ራያ ቱብ’ ከሚባል ፌስ ቡክ ከ4 አመት በፊት ስለ አሸንዳ ያገኘሁትን አጭር አገላልጽ ስለ አሽንዳ እንዲህ ይገልጸዋል።


“አሸንዳ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ የጾመ ፍልሰታ ፍጻሜን ተከትሎ ከነሐሴ 16 ጀምሮ በሰሜን ኢትዮጵያ ከሚከበሩ መንፈሳዊ በዓላት መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ የአሸንዳ በዓል በክረምት ወቅት ከሚበቅለው ቁመቱ ከ80 እስከ 90 ሣ.ሜ የሚሆን የአሸንዳ ተክል ስሙን የወረሰውና በአብዛኛው ልጃገረዶች አሸርጠው የሚጫወቱበት የአሸንዳ በዓል አከባበር በዋናነት ሴቶች በዕድሜ ደረጃቸው ተቧድነው የሚያከብሩት ትልቅ በዓል ሲሆን ወንዶችም ያጁቧቸዋል።” እንግዲህ ስለ አሸንዳ ባጭሩ ካወቅን ወደ ወያኔ እና አሸንዳ ግንኙነት በሰፊው ከመመለክታችን በፊት ወያኔዎች ለምን ሃይማኖታዊ በዓላትን መጠቀሚያቸው እንዳደረግዋቸው የመነሻ ባሕሪው ምን እንደሆነ እንመልከት።

ደጋግሜ እንደገለጽኩት የትግሬዎች አብዮት ‘ፋሺስታዊ ርዕዮት ነው” ብለን እኔም ጥቂት ጓዶቼም ተከራክረናል። ስለሆነም እንደ ማንኛውም ፋሺሰት ቡድን የወያኔ ፋሺቶችም የሕዝብ በዓላትን ለፖለቲካው መገልገያ እያደረጋቸው እንደቆየ መሪዎቹ በየዓላቱ እየተገኙ በቪዲዮ የተቀረጹ ማዛግብቶች የሚናገርዋቸው እና የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነታቸውን ማስረጃዎች ናቸው። ስለሆነም የትግራይ ፋሺሰቶች በዓላቱ ወደ ፖለቲካ የመለወጥ እንቅስቃሴ ከማሳየቴ በፊት አንባቢዎቼ ስለ ፋሺዝም በቂ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ ያስፈልጋል።


የማከብረው ወዳጄ የስነ ኣእምሮ ሓኪም ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ፋሺዝምን ካጠኑ የውጭ ምሁራን መዛግብት በመመርመር ደጋግሞ በጥልቅ የጥናት ጽሑፉ ውስጥ እንደገለጸው ‘ፋሽዝም በአንድ ምርጥ ሕዝብ ማንነት ላይ ተመስርቶ የቆመና የአንድን ምርጥ ሕዝብ የበላይነት የሚሰብክ የአክራሪ ብሄረተኛነት (ultranationalism) ፍልስፍና’ መሆኑን ነግሮናል። የኢትዮጵያ ፋሺስቶች (ኦነግ ወያኔ ወዘተ…) የሚያቀንቅኑት የአንድን ምርጥ ሕዝባቸው ማንነት ለማረጋገጥ በማያቋርጥ አብዮታዊና ስር-ነቀል በሆነ መንገድ መጓዝ ነበረባቸው። ‘ብሄራችን’ የሚሉትን ክፍል በመለወጥ አንድ-ወጥ አስተሳሰብ ያለው ክፍል ፈጥረዋል።  ያራመዱት ፖለቲካ “አንድ ወጥ” የሆነ አስተሳሰብ እንዲከተል ማድረግ ነበር እና አድርገውታል።


 ብሔራችን የሚሉትን ክፍል ሃይማኖትህ ፤ ቋንቋህ ፤ ድምበርህ እና ማንነትህ ተጨፍልቋል በማለት የሰበኩትን ክፍል በዳግማይ ልደት ምርጥነቱን ተመልሶ ለማረጋገጥ አዲስ በሆኑ የሞራል እሴቶች የታነጸ አዲስ ሰው መፍጠር ነበረባቸው እና ፈጥረዋል። አዲስ ታሪክ ሰሪ ነህ ብለው ሃይሞኖቱን፤ቋንቋውን፤ባሕሉን የፖለቲካ መጠቀሚያ ድልድይ እንዲሆኑ በማድረግ ከሌላው ብር እንዲለይ ብቻ ሳይሆን አገር ከምትባለዋ ዋናዋ አገር የነበራቸው ትስስር ባሕል እንዲበጠስ ጉልህ ‘ሴራ አድርገዋል”፤ ይህ የኛ ባህል እንጂ የማንም አይደለም በሚል ምርጥ ልዩ የሆነ የማንነት ማዕረግ ለመላበስ ትግሬዎች (የወያኔ ፖለቲከኞች) አክሱም ከነበሩት ጥንታዊ አገዎች ጋር ፉከክር ገብተዋል (በታሪክ አንደምታውቁት ትግሬ/ትግራይ የሚል ስም ወይንም ትግርኛ ቋንቋ በአክሱም ዘመን አልነበረም ። የተከሰተው “ቤጃውያን አክሱምን ከወረሩ እና ካፈረሱት ወዲህ ነው። የትግርኛ አስክስታ “ሲደረብ” (ውረድ ሲባል) አንገት ወደ ሰማይ አንቃርሮ አነገትን የማንቀሳቀስ ጨዋታ ከቤጃዎች ጋር ይመሳሰላል።ከበሮ መቺዎችም ወደ መሬት ወርደው ሁለቱ እግሮቻቻው ወደ ሗላ አንደ ‘ግመል’ በማጠፍ ወደ ሰማይ አንቃረው ሲመቱ የቤጃዎችን ባህል ይመሳሰላል)። አገዎች ትግርኛ ወይንም ትግሬ ከሚባለው ክፍል አስቀድመው እዛው አክሱም የነበሩ፤ሰማቸውም በዛው ስም በጥንት ሃውልቶች ጽሑፍ ይጠቀሱ የነበሩ ናቸው)። የዛሬ ትግሬዎች (ወያኔዎች) ከሰቆጣ ዋግ አገዎች/አማራዎች ጋር (በትግርኛ ተነጋሪ ትግሬዎች አባባል- “አሸንዳ” በሰሜን ወሎ ቆቦ (ሶለል)፣በአማራዎች/አገዎች ፤በሰሜን ጎንደር አካባቢ በዋግ ህምራ ሰቆጣ (ሻደይ) በላስታ ላሊበላ (አሸንድዬ)፤ በአክሱም (ዓይኒ ዋሪ) ተብሎ በሚታወቀው ጥንታዊ ሃይማኖታዊ የጨዋታ በዓል የዛሬ የወያኔ ትግሬዎች ወደ ፖለቲካ መጠቀሚያቸው በማዞር ሕዳጣንን ከሕዳጣን ለማጣላት በረቀቀ ፋሽታዊ የማንነት ውዝግብ  እንደገቡ የምታውቁት ታሪክ ነው። በየፌስቡኩ የምታዩት የትግሬዎች አሸንዳ ባለቤትነት “አማራዎች/አገዎች” ነጠቁን የሚሉት ማንበብ ፋሺስታዊ ገጸ ባሕሪያቸውን ያመላክታል። ፋሺሰቶች መጋራትን ሳይሆን “የሁሉም ነገር ፈጣሪዎች እና አለቃዎች መነሻዎች እኛ፤ በሁሉም “የኛ” በሽታ የተጠቁ ናቸው።


ዶክተር አሰፋ እንደገለጸው ብዙዎቹ የፋሺስት አቀንቃኞች፤


) በአፈ-ታሪክና በአብዛኛው በውሸት ላይ የተመሰረተ አዲስ ታሪክ በመፍጠር አንድ ሕዝብ እጅግ ደማቅ የሆነ በእጅጉ ገናና የሆነ ታሪክ ባለቤት እንደነበረ ይተርኩለታል።

- ይህ ትላንት በታሪክ የደማቅና ገናና ታሪክ ባለቤት የነበረ ሕዝብ በዛሬው ዘመን እየተፈጸመበት ያለውን በደል፤ ወርድትና ብሶት ያስተጋቡለታል።  

- ይህ ትላንት ደማቅና ገናና ታሪክ የነበረው ዛሬ ደግሞ የውርደት፤ የበደል ሰለባ የሆነ ሕዝብ ራሱን እነዚህን አዲስ የነጻነትና የአክራሪ ብሄረተኛነት ዜማ የሚያዜሙ መሪዎችን ቢከተል ሊያገኝ የሚችለውን ሲሳይ ይተርኩለታል። ከዚህም በላይ ብሄረተኞች ወገናችን ነው የሚሉትን አንድ ምርጥ ሕዝብ አንተ የእኛን መሪነት ተቀብለህ በስራችን ታቅፈህ ከታገልክ ምድራዊ ገነት እናወርስሃለን፤ ከችግርና ከጉስቁልና እናወጣሃለን ብለው የተስፋ መና በማስጨበጥ አንድን ምርጥ ሕዝብ ወይም ነገድ በአዲስ ተስፋ ለትግል ያነሳሱታል።እነዚህ ሶስት የብሄረተኝነት ማጠንጠኛ ድርና ማጎች በመከተል።ባህልን ሃይማኖትን እና በዓላትን በመጠቀም የተከታዮቻቸውን አመለካከት ለመቅረጽ ይጠቀሙባቸዋል።


አሁንም ዶ/ር አሰፋ እንደገለጸው “ባህልና ከባህል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አፈታሪኮች፤ ባህላዊ ስነስርዓቶች፤ ዘፈኖች፤ ባህላዊ ፉከራዎች/ሽለላዎችን ወዘተ በመጠቀም አንድ የፋሽስት ቡድን ህዝብን በስሜታዊነት በማነሳሳት የባህልን ውጤቶች የፋሽስት የፓለቲካ ዓላማ ማሳኪያና ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ያደርጋል። ባህላዊ ምስሎችና ምልክቶች (cultural images and symbols) ሰዎችን በስሜት አነሳስተው የማሳወር አቅምና ችሎታ አላቸው።” ይላል።


እኔም ካሁን በፊት ይህንን ለማብራራት የጠቀስኩትን ትግሬዎች በሙዚቃ እየታጀቡ የትግራውያን ፉከራ ይዘት ምን የገለጽኩት የአንድን በፋሽስት አስተሳሰብ ያበደ ሕዝብ አመለካከት ፍንትው አድርጎ ስለሚያሳይ ነው። ለዚህ ነው ወዳጄ ዶከር አሰፋ “የትግራይ ሕዝብ ተነስቶ ወያኔን ይጥላል ማለት ቅዠት ነው” በማለት ድምዳሜ የደረሰው። አሁን እውነታው እያየነው ነው። ትግሬዎች እና ወያኔዎች ያላቸው ግንኙነት እና ቃልኪዳን የዶከተር አሰፋ ክርክር እውነታ ትክከለኛነት ያረጋግጣል::


ኪነጥበብ፤ክብረበዓላትና ባሕላዊ ምልክቶች የፋሲስቶች እምነት ማስፋፊያ መሳሪያዎች” የሚሆኑበት ምክንያት ፋሽስቶች እነዚህን በአንድ ሕዝብ ውስጥ ጥልቅ መሰረት ያላቸውን ምልክቶች፤ ልማዶችና ክብረ በአሎች ህዝብን በስሜታዊነት ለማነሳሳት ለሚያደርጉት ያላቋረጠ ትግል በመሳሪያነት ቀላል እና ሃይለኛ መጎተቻ ገመድ ናቸው።


አሁንም ዶ/ር አሰፋ “የትግራይ ህዝብ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት አማካይነት የራሱን ነገድ ማንነትና ታላቅነት እንዲያመልክ ተደርጎ ለብዙ ሺህ ዘመናት አብሮ ከኖረው የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስነልቦናም ሆነ በእለታዊ ህይወቱና ማህበረሰባዊ ተራክቦው (social interaction) እየተለየ መጥቶአል። ዛሬ የትግራይ ህዝብ ራሱን ኢትዮጵያውያኖች በጋራ ከሚጋሩዋቸው ብሄራዊ እሴቶች በተቃራኒ የቆሙና ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ፤ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት የተቃኙ ፋሽስታዊ እሴቶች ባለቤት በማድረግ ጨርሶ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ወጥቷል ማለት ይቻላል። የኪነጥበብ ስራዎች፤ ዘፈኖች፤ ትያትሮች፤ ፊልሞች ወዘተ የህዝብ መዝናኛዎች መሆናቸው ቀርቶ ጦረኝነትን፤ የትግራይን ሕዝብ የበላይነት፤ ምርጥነት፤ የንጹህ ዘር፤ የንጹህ ደም ባለቤትነት፤ ልዩና ወደር የሌለው የታሪክ ባለቤትነት፤ የሥልጣኔ ባለቤትነት፤ ጀግንነት፤ አዋቂነት፤ ወዘተ አጉልተው የሚያሳዩ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎች ሲደረጉ በሌላው በኩል ዘፈኖችን፤ ፉከራዎችን፤ ትያትሮችን፤ ፊልሞችን የመሳሰሉ የኪነት ስራዎች ከምርጡ የትግራይ ሕዝብ ወይም ጎሳዎች ወይም ሕዝቦች ውጭ ያሉትን የሌሎችን ፈዛዛነት ትንሽነት፤ ፈሪነት፤ ድንቁርና፤ ኋላቀርነት፤በአይምሮ ዘገምተኝነት” (Retards የሚለውን የአንዲት እብሪተኛ የትግራይ ብሄረተኛ ሴት (ወ/ሮ ከበደሽ የተባለች የገዛ ተጋሩ ፓልቶክ አስተዳዳሪት የሆነች ሴት አማረውን ጎጃሜውን ጎንደሬዎን Retards ብላ መሳደብዋን በድምፅ መቅጃ የተቀዳ ማስረጃ ልብ ይለዋል) የመሳሰሉ ስድቦች እና ንቀቶችን የሚደመጡባቸው እብሪቶች ጉልተው የሚያሳዩ የእብሪት መገልገያ ይሆናሉ። ዛሬ በርካታ የትግርኛ ዘፈኖችን ይዘት ብታዳምጡ የሚያሰሙት ፉከራ ስለ ትግራይ ሕዝብ ልዩ ጀግንነት፤ አልበገሬነት፤ (ለምሳሌ የሟቹ ብ/ጀኔራል አብርሃ ኳርተር ከመሞቱ በፊት የተናገረውን አስታውሱ “የዛሬዋ ትግራይ አንኳን በጥፊ የሚያጮላት ቀርቶ ጫፍዋን የሚነካ በዚህ ምድር ከቶ እንደሌለ ዓለም ሁሉ የሚያውቀው ሃቅ ነው” ብሎ ነበር።) ታላቅነት ሲያወሩ ስለሌላው ነገድ ግን ደካማነትና ፈሪ መሆኑን ይሰብካሉ። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድ ሕዝብ እንደዚህ ይሉኝታን ባጣ መንገድ ታላቅነቱን፤ ብቸኛ ጀግንነቱን፤ አልበገሬነቱንና በሌሎች ላይ ያለውን የበላይነት የሰበከበት ወቅት ተከስቶም አይታወቅም።


በአንድ ሕዝብ ማንነት ላይ ተመስርቶ በመሆን ወደፊት ብቅ ያለው ፋሺዝም የተባለውና የአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት መገለጫ የሆነው አዲሱ የፓለቲካ ኃይማኖት ከእሱ እንደሚቀድመው የኢጣሊያን የፋሽስት ስርዓት አዲስ ምድራዊ የፓለቲካ ሃይማኖት እምነትን (አክራሪ ብሄረተኛነትን) እያስፋፋ ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በመንግስትነት ሰይሞ በኢትዮጵያሕበረሰብ ላይ ራሱን በኃይል በመጫን ለትግራይ ሕዝብ የደስታን ዘመን ከትግራይ በታች ላለው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጭለማና የመከራ ዘመንን አብስሯል ።ይህ የትግራይን ህዝብ የወል ማንነት (በወያኔ ቋንቋ የትግራይ ብሄር) እንደ ሃይማኖቱ አድርጎ የሚያየው፤ የትግሬነትን የወል ማንነትንና የትግራይ ብሄረተኛነትን መመሪያው ያደረገ ፋሽስታዊ ፍልስፍና የትግራይን ሕዝብ የወል ማንነት የተቀደሰ አድርጎ ከማየቱም በላይ የትግራይ ተወላጆች ይህንን በወያኔ መንግሥት ቅድስና የተሰጠውንና ከሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች ሁሉ በላይ ወርቅ አድርገው ራሳቸውን እንዲያዩ ያደረጋቸውን አዲሱን ማንነታቸውን ህይወታቸውን ጭምር መስዋእት አድርገው እንዲጠብቁትና እንዲከላከሉት ያስተምራል።


የወርቅ ማንነቱን ለማክበር በየጊዜው የሚያከብራቸው አዲሱ ባዓላቶቹ ስትመለከቱ ይላል ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽጊዜውን አግኝቶ የትግራይን ቴሌቪዥን በየጊዜው ለሚከታተል ሰው የትግራይ ህዝብ በልማት ስራ ላይ ብቻ አለመጠመዱን ይመለከታል። የትግራይ ህዝብ ልጆቹ ምስጋን ይግባቸውና ታጋዳላይ ጀግኖች ልጆቹ ያጎናጸፉትን አዲሱንና አኩሪ የወርቅ ማንነቱን በየጊዜው በሚያከብራቸው አዲስ በዓላቱ (የየካቲት 11 የግንቦት 20 የአሸንዳ የሰማእታት ቀን፤ የሰራዊት ቀን፤ የሴቶች የወጣቶች ቀን፤ በጦርነት የተጎዱ አካል ጉዳተኞች በዓላት ቀናት ወዘተ… በስሜት ሰክሮ፤ ከበሮ እየደለቀ፤ በኦርቶዶክስ ቀሳውስትና ታቦት ታጅቦ ታላቅነቱን፤ ልዩ ጀግንነቱን ጠመንጃ ይዞ በቀረርቶ፤ በፉከራ ጭምር ያስተጋባል። በቴሌቪዥን መስኮቶች የትግራይ ህዝብ ልዩ ጀግንነት በእነ አሉላ አባነጋ፤ ዐጼ ዮሃንስ፤ ኃያሎም ዓርዓያ፤ አሞራው ወዘተ ምስሎች ታጅበው ይቀርባሉ። እነዚህ ዓይነት ያንድን ህዝብ ታላቅነት የሚዘክሩ ትዕይንቶች ወያኔዎች ከደርግ ጦር ጋር በተደረጉ የእርስ በርስ ውጊያዎች በጦር ሜዳ የበላይነት ባገኙባቸው ምስሎች ታጅቦ ይቀርባል። በእነዚህ የጦር ምስሎች ታጅበው የሚቀርቡት የቴሌቪዥን ዝግጅቶች የትግራይን ህዝብ የህዳሴ ጉዞ (renaissance) የዳግም ልደት (rebirth) የሚያሳዩ፤ የትግራይ ህዝብ ከመቶ ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ ነበሩ በሚባሉ የአማራ ህዝብ መሪዎች ተቀብሬ ነበር ብሎ ከሚያምንበት መቃብር በጀግና ልጆቹ መስዋእትነንትና ሰማእትነት በትንሳዔ ተነስቶ አዲስ ታሪክ እየጻፈ መሆኑን ያስገነዝቡናል
<ለፋሽስቶች ዋነኛና ተመራጭነትና ዋጋ ያለው ችሎታ እውቀት ሳይሆን ጭፍን እምነት ነው። ፋሽስቶችን ለቆሙሉት ዓላማ በቆራጥነት እስተመጨረሻው እንዲዋጉ የሚያደርጋቸው ጭፍን እምነታቸው ነው>


በደንብ ያላጤናቸውና ያላስተዋልናቸው የትግራይ አክራሪ ብሄረተኞች  ሲያስተጋቡዋቸው የነበሩት የእነ ሙሶልኒ ፋሽስታዊ አስተሳሰቦች ምን ይመስላሉ?


ብስራት አማረ የሚባል የወያኔ ካድሬና የወያኔ ዋና የመግደያና የማሰቃያ እስር ቤት ኃላፊ በመሆን ለብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን፤ በተለይም ለአማራ ተወላጆች ህይወት መጥፋት ተጠያቂ የሆነ ግለሰብፍኖተ ገድልበሚል ርዕስ ስለ ወያኔ ሓርነት ትግል በጻፈው መጽሃፉ ውስጥ የትግራይ ሽማግሎች ለወያኔ ተዋጊዎች የሰጡትን ምክር እንደሚከተለው አስፍሮአል።


<ዮሃንስ አራተኛ ከሞቱ ልክ ከአንድ መቶ አምስት አመታት በኋላ መጋቢት 1981 .. ህውሃት መላውን ትግራይ ነጻ አውጥቶ መቀሌን ተቆጣጥሮ ወደ ማእከላዊ ኢትዮጵያ ሲገሰግስ በእድሜ አንጋፋ የሆኑት ትግራውያን እነሱና አያቶቻቸው የከፈሉትን ታሪካዊ ሰቆቃ አስታውሰው በታላቅ ክብር ለታጋዮቹ  ሲመክሩኢትዮጵያ የናንተ ናት። አሁን የሚያቆማችሁ ኃይል የለም። ልጆቻችን ከእነሱ ይበልጥ ጠቢብና አሳቢ እንደሆናችሁ የንጉስ ምንሊክ ሰዎች አሁን ይማራሉ። እናንተን ለማሸነፍም ሆነ ለማስቆም የሞራል ብቃት የላቸውም። ትግራይ አንዴም ተሸንፎ አያውቅም። ምንሊክ የትግራይን ህዝብ እንደ ጠላት ቅልስልስ አደረጋቸው። እግዚአብሄር ይባርካችሁና በአባቶቻችን እና በራሳችን ስም እናመሰግናችኋለን ብለው ምንሊክ ባንድ ወቅት ታላቅ ለነበረችው ሀገር የተወላት ብልሹና ከፋፋይ አስተሳሰብ እንደ ነበር አስገንዝበዋል (ለዝርዝር መረጃ የብስራት አማረን -
ፍኖተ ገድልየተሰኘ መጽሃፍ ገጽ 41 ላይ ይመልከቱ) (ዘኒ ከማሁ (/ አሰፋ ነጋሽ 118)
መለስ ዜናዊ በየካቲት 1984 . መቀሌ ላይ ለአስራ ሰባተኛው የወያኔ ምስረታ በዓል ላይ አንድ ሚሊዮን ለሚሆኑ በቦታው ለተሰበሰቡ የትግራይ ተወላጆች ያደረገው ንግግር።



ይህ ሕዝብ እንኳን የሌሎች/የባእዶች አልሆነ። እንኳን ከእናንተ ተፈጠርን። ይህ የእያንዳንዱ ታጋይ እምነት ነው። እንኳን ከናንተው ማህፀን ተፈጠርን። እንኳን የኛ ሆናችሁ። እንኳን የባዕድ የሌላ አልሆናችሁ። እንኳን በማዶ እያየናችሁ የምንቀናባችሁ የሌሎች አልሆናችሁ። እናንተ ወጣቶች! እዚህ ያላችሁበት መድረክ እንደትደርሱ ሲባል ታላላቆቻችሁ ላባቸውና ደማቸው አፍስሰዋል፤ ታላላቆቻችሁ በየጉራንጉሩና፤ በየሸለቆው እና ተራራው ቀርተዋል።ታላላቆቻችሁ አጥንቶቻቸው በየተራራው ተበትኗል። አጥንቶቸው  በየተራራው የተበተነበት ምክንያትም ትግራይ እንድትለማ በሚል ነው። እነኚህን አጥንቶች-እንዳትረግጧቸው፤አንዳታራኩሷቸው! ሁኔታውን-ካመቻቹላችሁ በኋላ እንዳትከዷቸው፤ ሌት ተቀን  መጣር ይኖርባችኋል” >>(መለስ ዜናዊ)


(ምስጋና ይድረሰውና ወዳጄ የሆነው፤ ወያኔን በግምባር ቀደምትነት በመታገል የሚታወቀው የአክሱም ተወላጅ አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን እዚህ የጠቀስኩትን በመተርጉም የሁል ጊዜ ትብብሩን አድርጎልኛል)



ከዚህ ቀጥሎ የምትመለከቱዋቸው የተላያዩ የትግራይ ዘፋኞች የሚዘፍኗቸው ዘፈኖች ሲሆኑ፤ ከውስጣቸው እያንዳንዱ ዘለላ ዓረፍተነገር የሚነግሩን ‘በትግራይ ብሔረተኛነት የተቃኘ ፋሺስታዊ ቅንቀናዎች ጎልተው የሚነግሩን የስርዓቱ ምንነትን ነው። በእነኚህ ዘፈኖች ሚሰነዘሩ ስንኖችና መልዕክቶች እንደመብራት ሆነው ብዙዎቻችን ማየት ያቃተንን ‘የትግራይ ብሔረታዊ ፋሺስዝም’ ምንነት ማየት የተሳናቸወ ዓይኖቻችን ላይ እያበሩ ለኛ በጋረደው ዳመና ውስጥ ሰርስረው የሚያሳዩን ፋና ወጊ መብራቶች ናቸው። ከዚህ ቀጥሎ በትግራይ ሙዚቀኞች የተዘፈኑ የያዝዋቸው መልዕክቶች ካስነበብኳችሁ  ኋላ፤ ለወያኔ ፋሺስታዊ ስርዓት ለመፍጠር የተደረጉ የሕሊና ቀረጻዎችና ባገራችን የታየ ፋሺዝም መቸ እና የትኛው ስርዓት ነው ፋሺስት የምንለው፤ ትክክለኛስ ትርጉሙ ምንድነው? በሚል አንባቢዎቼ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ ለዚህ መጽሐፍ ማጠናከሪያ እንዲሆነኝ ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ከሆላንድ/ አምስተርዳም (አውሮጳ) የላከልኝ ጽሑፍ አቀርብላችኋለሁ። አሁን ወደ ትግራይ ወያኔ ወጣት ዘፋኞችና ዘፈኖቻቸውን እነሆ ምን እንደሚል የትርጉሙ ምንነት እንመልከት።

ዑንቂ ባሕሪ (ዘፋኝ ሕሉፍ አለሙ)
ትግረኛው ለአንባቢ እንዳይራዘም ትቼዋለሁ።

ወደ አማርኛ ሲተረጐም
የትግራይ ሕዝብ የባሕር ዑንቅ
ጀግና የትግራይ ሕዝብ ይገባዋል ክብር
በዛ በመራራው በአስራ ዘጠኝ ሰባሰባቱ (1977) ሕዝብ እንዳይበተን ማገርና ቀምበር
ሆኖ የጠበቀን ታጋይ የትግራይ ሕዝብ ይገባዋል ክብር !
የተፈተናችሁ በቀውጥ ቀን በእሳት
በመራራ ትግል እያባረራችሁ አሳድዱት በሉት
ናችሁና ትግሬዎች!
የበረሃ አምበሶች!
በመራራ ትግል እያባረራችሁ አሳድዱት በሉት
የባሕሩ የሉል የዑንቅ ልጆች ድል ተጎናጽፈዋል በአሸናፊነት!
ምነው በሞትኩኝ
ምነው ስስት ያዘኝ
ለመብላት ቸኮልኩኝ
የትግራይ ሕዝብ ስሙን ሳልጠራ ረስቸው ጎረስኩኝ! (በስመ አብ ወወልድ..የሚለው ተክቶ በስመ አብ ወትግሬ” ማለት ነበረብኝ እንደማለቱ ነው ዘፋኙ እየነገረን ያለው)

ትግራይ ዓደይ (ዝዓበኹልኪ መረበተይ)  (ዘፋኝ አበበ አርአያ)
ኣይርስዐክን እየ ዓደይ
ዝዓበኹልኪ መረበተይ
ዓይርስዐክን እየ ትግራይ ዓደይ
ፍርይቲ ዓይነይ
ክሳብ መወዳእታ ምሳኺ እየ ትግራይ ዓደይ
ንዓኺ ዘይኸውን የለን ትግራይ ዓደይ
ወርቂ ተሸለምለይ ጸብቕለይ
ርኢኽዮንዶ እቲ ብርሃን ጅግና
ሳላ ዝወለድክዮ ትግራይ ዓድና
ርኢኹሞዶ ሽዶናይ ወዳ
ወደ ትግራይ ጎሚዳ
ርኢኹማዶ ትግራይ ኩሑሎ
ብመብራሕቲ ትሕሎ
ንዓኺ ዘይኸውን የለን ወርቂ ተሸለምለይ

ወደ አማርኛ ሲተረጎም፤
አልረሳሽም አገሬ
ያደግኩብሽ መንደሬ
አልረሳሽም ከቶ ትግራይ አገሬ መንደሬ
ውብ ዓይናማይቱ ትግራይ አገሬ መንደሬ
እስከ መጨረሻ  ካንቺው ጋር ነው ልቤ
ላንቺ የማይሆን የለም ትግራይ አገሬ
ይማርብሽ ተሸላለሚ ተዋቢ ትግራይ አገሬ
አገራችን ትግራይ የቀን ብርሃን አየሽ
ስለወለድሺው ቆፍጣና ልጅሽ
አያችሁት አይደል መራራ ጀግና
የትግራይ ልጅ ጎሚዳ (ደምሳሽ፤ አርበኛ፤ጀግና፤አሸናፊ ….)
ላንቺ የማይሆን የለም ተሸላለሚሊኝ
በወርቅ አጊጢሊኝ
አያችኋት አይደል ታጀባ በመብራት
ውብ ዓይናማዋ ትግራይ ተኩላ  አምሮባት። ይላል አበበ አርአያ።


በጣም የሚገርመው ዘፋኙ (አበበ አርአያ ኗሪነቱ አሜሪካ ነው።) ይህ ከላይ የተጠቀሰው ግጥም እና ዜማ የዘፈነው በረሃ እያለ ነበር የዘፈነው። ዘፈኑትግራይ የዓይኔ ብሌን፤ትግራይ፤ ትግራይ፤ ትግራይ…) ከሚለው በተጨማሪደርግን፤ ኢሕአፓን፤ኢዲዩን አሸነፍን ወዘተ..ወዘተ እያለ ትግራይን እንደ ልዩ ፍጡር እና አንባሰ በመሳል ሲያሞግስ የገጠመው ነበር: ሆኖም፤ ዛሬ ይህ ፖለቲካዊ ዘፈን 2009 .(2017) ሮማናት አደባባይ መቀሌ ከተማ ውስጥ አመታዊው የአሸንዳ በዓል በተከበረበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የመቀሌ ታዳጊ ንኡሳን ወጣት ሴቶች አደባባይ ተሰብስበው የአሸንዳ በዓል ሲያከብሩ ይህ ፖለቲካ ይዘት ያለው ሙዚቃ እንዲያዳምጡ መደረጉ ባሕላዊ በዓሉን በመጠቀም ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እንዲተላለፉ መደረጉ አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን ወያኔዎች ሕዝባዊ ባሕሎችን እንደ ናዚዎች እና ፋሺስቶች ወደ የፖለቲካ መድረክ መቀስቀሻ ማድረጋቸው፤ ይቅር የማይባል ፋሺስታዊ እና ሕገ ወጥ እንደሆነ የታሪክ ጸሐፍት እንደሚዘግቡት ተስፋ አለኝ። ይህ ዘፍኝ ብቻ ሳይሆን ሰለሞን ባይረ (የለየለት ጠባብ ትግራይ ብሔረተኛ ሙዚቀኛ) እንዲሁም ሕሉፍ አለሙ የተባለው እጅግ፤እጅግ በጣም የከረረ ትምክሕት እና የትግራይ ብሔረተኛነት ስሜት ያንገላታው ሙዚቀኛ (ዑንቅ ባሕሪ፤ደቂ ዑንቂ ባሕሪ-- የዑንቅ ባሕር ልጆች) የሚለው ዘፈኑ እና ብዙዎቹ እዚሁ አደባባይ ተገኝተው ነበር የፖለቲካ አጠባቸውን በጥናት ተጠንቶሆን ተብሎለታዳጊ ህጻናት በአሸንዳ ወቅት ሲያስተላልፉ የነበሩት። እጅግ አሳዛኝ ክስተት! ባሕላዊና ሃይማኖታዊ በዓል ለፖለቲካ መቀስቀሻ መድረክ አድርገው ሲጠቀሙበት ማየት አጅግ አስገራሚ ነው።


ሌላው እጅግ አስፈሪ ፋሺስታዊ የትግራይ ብሔረተኛዊነት ትምክሕት በግልጽ የሚያስተምር ግጥምና ዘፈን በቀዳሚ ምሳሌ የምንምለከተው ሙሉጌታ ካሕሳይ (በቅጽል ስሙወዲ ሮሚጥ”) በመባል የሚታወቅ ትግራዊ ብሔረተኛ ምን እያለ እንደሚዘፍን መልዕክቶቹን ስናጤን። የትግራይ ሰው ከሰው ሰውነት አውጥተው ወደ ፈጣሪነትና ልዩ ፍጡርነት (ፈጣሪ…) አስገብተው፤ የሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ግዑዝ (ዕቃ፤ድንጋይ፤ ዛፍ፤ተራራ፤ነፋሰ…) ሁሉ ሳይቀር በትግሬዎች ተደንቀዋልይላል። ያውም ነጋሽ እና አንጋሽ ነን እንጂ ሥልጣን ከማንም ተቀብለን አናውቅም ይላል ፋሺስታዊ ትምክሕት ያለው የገጣሚው መልእክት። የዘፈኑ ርዐስ
ከመይ ኣለኻ!’
(አንደምን አለህ!?)
ከመይ ኣለኻ?
ዘፋኝሙሉጌታ ካሕሳይ
( ወዲ ሮሚጥ)

ሕዝቢ ትግራይ ክባሃል ውሽጠይ ፍናን፤ፍናን ይወረኒ
ልበይ ታሕጓስ ፍግዕ ይብል አሎየ፤ ልበይ ታሕጓስ ፍንፅሕ ኢሊ
ከመይከ ኣለኻ?
ጥበብ ኮይንካ……..
መዋእልካ
ጻዕዳ ከምፈረስ፤  ኣብ በረኻ ትሕለቕ
ሓንሳብ እውን ሓፂን ፤ሓንሳብ እውን መብረቕ ሕዝቢ ትግራይ ነጋሲን አንጋሲን
አማዕዚንካ መራሕን ገናሕን
እሞድማ ውሑድን ሙሩጽን
እንኳይ ንሰብ ንጉኡዝ ዘህንን
ሕዝቢ ከምሓደሰብ ይጽዋዕ፤
ከም ሓደ ይሕሰብ ከም
ይሕሰብ ማዕርነት ክብሩን
ሕልፊ ዘይደሊ ግን ሕልፊ ገቢሩ
 (ሕልፊ መስዋዕቲ)
ንከይጎብጥ ካን ታአምር
ንዝጎብጦ ግና ሕልፊ እዩ መሪር
ናይ ማዕርነት ብዕሪር፤
ንትንቢተ ኦሪት መላእ እዩ አፉ
ደጊም አይሓልፎን ሕዝበይ ከምሕላፉ
ኣይገድፈናን ሎሚስ ከይተማላኣና
ምን ሒዙ ክኸድ ሰብ ዋና ከለና
ወዲ ትግራይ ክባሃል ከሎ
ፍናን ፍናን ይወረኒ አሎ
ልበይ ብታሕጓስ ፍንጽሕ
ክብል ኢሉ አሎ
ከመይ ከመይ ከምይ ኣለኻ
እንግዳዕኻ ሥልጣነ ፈለማዊ
መቦቆልካ ንግሥተ ሳባዊ
ማይ ፈለግካ ጥበብ ያሬዳዊ
 ፈላስፋዊ ዘርዓ ያዕቆባዊ
ዘረባኻ ይነትዖ ሊቅነት
ማኣድኻ የኩልስ ጅግንነት
ከመይ ኣለኻ?
 2017 በፈረንጅ ዘመን የወጣ አዲስ የትግርኛ ዘፈን።
ዘፋኝሙሉጌታ ካሕሳይ (ቅጽል ስሙወዲ  ሮሚጥ”)

ትርጉም
         
እንደምን አለህ ?
 (የትግራይ ሕዝብ ህልውናውን ሲጠይቅ ነው)
 ሙሉጌታ(በቅጽል ስሙወዲ ሮሚጥ”)
የትግራይ ሕዝብ ስም ሲነሳ ውስጤ
ኩራት ኩራት ይለኛል፤
ልቤ በደስታ ይሰነጠቃል
እንደምን አለህ ጤናህ ህልውናህ
ጥበብ ሆነህ፤ጥበብ አስተምረህ
ጥብቅና ቆመህ
መላ ህይወትህ ሰጥተህ
ለግፉኣን ስትል በረሃ ወጥተህ
ለመሆኑ አንተ እንደምናለህ!
ቁመናህ ያምራል እንደ ነጭ ፈረስ
ትሆናለህ አንዴ እንደ ብረት
አንዴ አንደ መብረቅ
የጀርባ አጥንትህ ሥልጣን ጀማሪ
ሥልጣን አስተማሪ፤ ሥልጣን አበሳሪ
መሰረተ ዘርህ ንግሥተ ሳባዊ
ምንጨ ልሳንህ ጥበብ ያሬዳዊ
ፈላስፋዊው ዘርዓ ያዕቆባዊ
ምድርህ ይረጫል/ያመነጫል ሊቅነት
ማአድህም ያጎርሳል ጀግንነት
የትግራይ ሕዝብ ነጋሽ እና አንጋሽ
በየመአዝኑ መሪና አራሚ
ያውም ጥቂት ሆነህ
ብትሆንም ምርጥ ነህ
እንኳን ለሰው ፍጡር ግዑዝን አስገርመህ።
አንድ ሕዝብ አንድ ነህ
ገስግስ አንድ ልብ አንድ ሃሳብ ሆነህ።
ትርፍ የማይፈልግ
ግን ትርፍ ግብሮ/መስዋእት ከፍሎ/
 የራሱ ያልሆነ ከቶ የማይፈልግ
 መልሱ መራራ ነውለሚቃጣው ሁሉ
 አርማ ነው ይጨሳል
 እንደ ብሪር ዕጣን ይጨሳል ይበግናል
ቢፈታተኑትም እንደማለፉ ያልፋል
ብሎ ቸል አይልም ከእንግዲህ ይበቃል!
 ይኼው ማስጠንቀቂያው
ይሞካክረናል ሥልጣን የሚጋራው
ዛሬስ አይተወንም ይዞን እንዳይጠፋ
ባለቤቶቹ እያለን ነጋሽ እና አንጋሽ
ይምጣ ይሞክረን ማንስ ይበገራል!
ማን ሆኖ ነው ማንስ  ይነጥቀዋል!
(ትርጉም ጌታቸው ረዳ ) (112)

እንዲህ እና የመሳሰሉ በጣም በርካታ የሆኑ የትምክህት ሙዚቃዎችና ግጥሞች እያታተሙ የወጡን አስተሳሰብ  በጎሰኛነት ትምክሕት ተጠምዶ በጉረኛ መንፈስ እየተጓዘ ሌሎችን በመናቅ አገራዊ ማንነቱን እንዲፍቅ፤የትግራይ ሕዝብ ልዩ ፍጡር የሆነ፤ እሱ ነጋሽ እና ሌሎችን  የሚያነግሥ በሚል የተወጠረ ፋሽታዊ ቅስቀሳ እንደሆነ ተመለክተናል።ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ በዓላትን የፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ ወያኔም ፋሺስቶች የሚጠቀሙበትን ዘዴ ትክክለኛ ቅጂ በመቅዳት የኪነት ሰዎችን ወደ ፖለቲካው በማሰማራት በተጠቀሱት በዓላት ላይ ከፍተኛ የሕሊና ብረዛ ሥራ ላይ አሰማርቶ ባሕልን ሃይማኖትን ወደ ፖለቲካ ጠልፎታል።


።ገጣሚዎቹና ሙዚቀኞቹ ሓላፊነት በጎደለው ለገዢው ለፋሲቱ ለወያኔ ቡድን አለጥልጠው የሚሰጣቸው አደገኛ ግጥሞችን ለሕዝብ ጀሮ እንዲዳረሱ በማድረግ ከፍተኛ የሕሊና አጠባ በማድረጋቸው የታሪክ ተጠያቂዎች ናቸው ብየ ሁሌም የምከስሳቸው ከዚህ በመነሳት ነው።

የትግራይ የኪነት ቡድኖች በዚህ ትምክሕትና እንዲህ ያለ ፋሺስታዊ ግጥሞቸን እንዲቀሰቅሱ ያስገደዳቸው ምክንያት ምንድ ነው? ፋሺስቶች እንዲሀ ያሉ የኪነት ሰዎችን እጅጉን ለሚያቀጣጥሉት ፋሺስታዊ ዕቅዶች የኪነት አባሎቹ ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ምቾታቸው የተጠበቀ ሆኖ  የተንደላቀቀ ኑሮ እንዲኖሩ እንክብካቤ ያደረግላቸዋል። ……. ይቀጥላል
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትኦ ሰማይ አዘጋጅ Ethio Semay)

No comments: