Sunday, April 7, 2019

በዕድሉ ዋቅጃራ ሆይ ቴድሮስ ጸጋየን ለቀቅ አርገው! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)


በዕድሉ ዋቅጃራ ሆይ ቴድሮስ ጸጋየን ለቀቅ አርገው!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)

ሰሞኑን የርዕዮት የዜና ማዕከል ዋና አዘጋጅ ለሆነው ለቴድሮስ ጸጋየ የጻፍከውን ደብዳቤ  እና አብይ አሕመድን ለቀቅ አድርገው የሚል መልዕክት ያለው ‘የደላላ መልዕክት’ ያዘለ  ደብዳቤህን “ቴድሮስ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳህን ተው” በሚል ርዕስ “መረጃ ዩቱብ” በተባለ የተላለፈው የድምጽ ንባብ አድምጬዋለሁ። ምንም እንኳ ደብዳቤህ በምሁራዊ ብዕር ቀባብተህ ለአንባቢ ለመሸጥ ብትሞክርም ዓይነተኛ መልዕክትህ እየነገረን ያለው “የመንጋ ፖለቲካውን ተቀላቀሉ” እያለከን ነው። የአብይ አሕመድን ጭራ ይዛችሁ የምትሄዱበትን አቅጣጫ በቅጡ ሳታረጋግጡ የምትከንፉ አንተ እና “የአላይቼው አልሰምቼው! ባዩ የአብይ አሕመድ ተከታዮች ምንም እንኳ ምጡቅ ምሁራን ብትሆኑም አንተ እና መሰል ምሁራን “የባርያ ስብስብ አባል” አበረታቾች መሆናችሁን ደብዳቤው ያስረዳል። ዛሬም የምትወቅቱት ውሃውን ነው። ከድሮው አልተሻላችሁም!

 “ብዙዎቹ” የሚዲያ ሰዎች እና “የተብየ- ምሁራን” ስበስቦች “እንዴ! ይህንን ሚሊየነም አዳረሽ የተንጨበጨበለትና ይህንን መሳይ ግምቱ ምሁር እንዴት ትነካዋለህ?” በሚል ትችቴን እንደሚያጣጥሉት አውቃለሁ። ይህ ለኔ አዲስ አይደለም ፡ ለ27 አመት የፈተንኳቸው እና በተግባር “ተፈትነው የወደቁ” የተቋቋሙኩዋቸው የመንጋ ስበስቦች ስለሆኑ አይገርመኝም።መንጋን የሚከተል ደግሞ “ራሱን ነፃ ያላወጣ “ባርያ” ማለት ነው። ከክራውድ/ከመንጋ/ ጋር አብሮ የሚጓዝ በራሱ ማሰብ ያቆመ መሪውን መተችት፤ መወንጀል፤ መክሰስ፤መውቀስ፤ማጋለጥነውር” አድርጎ የሚያይ ወዴት እንደሚጓዝ እንኳ ሳይጠይቅ የሚደመር የኢትዮጵያ ምሁር ደምበኛው የባርያ ምሳሌ ነው። እነኚህ ባርያዎች “ባርያነታቸው እንዳይታወቅባቸውም” ከሽነው በመኳኳል የሚያቀርቡት ምሁራዊ ስነ ጽሑፍ በደምብ ላላወቃቸው ሰው “ነጻ” ሰዎች ይመስለዋል። ሓቁ ግን ነፃ ያልወጡ ከደራሽ ወንዝ ጋር አብረው ሚፈሱ ተንጋጊ “ባርያዎች” ናቸው።

 አንባቢዎችን ለማስገንዘብ የምሻው አንድ ነገር አለ።፡ይህ ደብዳቤ ስጽፍ በዕድሉ ዋቅጅራን ማንነት ስቼው አይደለም። ከ 17 አመት በፊት በጻፍኩት “የወያኔ ገበና ማሕደር” መጽሀፌ ውስጥ በዕድሉ ዋቅጅራ ስለ ገጠመው “ሀገር ማለት የኔ ልጅ” የሚለው በ1999 ፍካት ናፋቂዎች በሚለው መጽሐፍ የተገኘውን ግጥሙን ስለሳበኝ ስለ ሀገር ምንነት ለመግለጽ ቀላል እና ጥልቀት ያለው ግጥም ሆኖ ስላገኘሁት አንባቢዎች እንዲመለከተቱት አድርጌኣለሁ። ስለዚህ የበዕድሉን የምሁራዊ ጥልቀቱ አላጣሁትም ለማለት ነው።

ችግሩ ያለው በዕድሉ ዋቅጅራ እራሱስ ነጻ ነው ወይ? ለልጆች የመከረውን “አገር ማለት” ትርጉምስ እራሱ ገብቶታል ወይ ነው እየጠየቅኩ ያለሁት። ቴድሮስ ጸጋዬ እንደኔው የትግራይ ትውልድ ያለው አርበኛ ኢትዮጵያዊ ነው። ቴድሮስ በሚሰነዝራቸው አስተያየት ልትስማሙም ላትስማሙም የምትችሉ ሰዎች አላችሁ። ይህ የሚጠበቅ ነው። ነገር ግን እንደ በዕድሉ ያለው ምሁር ሰው ቴድሮስ ጸጋየን “አገር አፍራሽ ፕሮፓጋነዳህን ተው” ብሎ የሚል እራሱ አገር የሚያፈርስን አብይ የተባለው “የኦሮሞ መሪ” መደገፍ አፍራሽ መሆኑን ያለመረዳት የሚያሳየው እራሱ አገር ገንቢ ቴድሮስ ጸጋየ አገር አፍራሽ አድርጎ የሚተች ሰው ለምልክት እንኳ አንዲት የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ባልታየበት (የፋሺስቶቹ መሪ መለስ ዜናዊ የተወለትን አብይ አሕመድ ሚያመልካት ባንዴራ ለሽታ ተብላ በጥ (ኮርነር) ተጋድማ አይቻለሁ) የሚሊየነም አዳራሽ አብይ አሕመድ በተገኘበት የአንድ አመት ንግሥናው ለማክበር ዶ/ር በዕድሉ ዋቅጅራ “ተመርጦ” የደሰኮረብትን አንደበቱ የሚጣረስ ነው።


በዕድሉ ዋቅጅራ በደሰኮረበት ንግግሩ ጥቂቶቹን አንዱን ልጥቀስ፡

“አንደማመጥም፤ የሌለውን ሃሳብ አናከብርም” ይላል።

እራሱ የተናገረበትን አንደበት ዶ/ር በዕድሉ ዋቅጅራ ቴድሮስ ጸጋየን “አገር አፍራሽ” እያለ ሲተቸው እራሱ ዶ/ር በዕድሉ ስለ አገር ተቆርቋሪነቱ የምናውቀውን ቴድሮስን ግን አገር አፍራሽ አድርጎ ሲተች የምሁራን ምላስ ሁለት መሆኑን በዶ/ር በዕድሉ ማየት ትችላላችሁ። ፈረንጆች ‘ሂፕክሪት” የሚሉት ዓይነት!

በዕድሉ ዋቅጅራ “ሌሎችን በያዝነው መስመር አንደራደርም” በሚሉ ላይ በዛው አዳራሽ ክፉኛ ይተቻል። ትችቱ ልክ ቢሆንም፤ የምትደራደርበት እና የማትደራደርበት መስመር እንዳለ ግን ሂፒክሪቱ ዶከተር ለይቶ አላስቀመጠም።በባሕር ወደብ፤በሃይማኖት፤በሰንደቃላማ በሰብኣዊነት ላይ ‘ድርድር አይደረግም”! በዕድሉ ይህንንም ጭምር ተደራደሩ እያለን ነው።መጽሐፍ ቅዱስም በዚህ “በሰለጠነው ዓለም” አየተከለሰ መሆኑንንም ጭምር ነካ ነካ በማድረግ በመጽሐፍ ቅዱሳችንም እንድንራደር አይነቱ የብቃጥ መርዝ ፖለቲካውን አስታክኮ ረጭቷል። በዚህ ላይ ቄሶቹ ምን እንደሚሉ አላውቅም! 

አብይ የሾማት የአገራችን ፍረድቤቶች ዋና ሹምም “የፍናፍንቶች/የሌዝብያን” መብት ቢከበር በበኩሉዋ ችግር አንደሌላት ሕገመንግስት ተብየውም ሆነ የአገሪቱ እስላማዊ እና ክረስትያናዊ ሕጎችና ባህል የሚጻረር ንግግር ነግራናለች። እንግዲህ ስልጣኔ ማለት “መደራደር” ነው ብለውናል። እንደግዲህ የአገራችን ምሁራን (ጋዜጠኞችም አሉ ይባላል)የመጽሐፍ ቅዱስ ክለሳ እና የፍናፍንት መብቶች ለማስከበር ፖለቲካውን አስታክከው ‘በድርድር’ እንድንለምደው እያስተማሩን ነው።

የበዕድሉ መሪ የሆነው አብይን ልጥቀስ።“ከሁሉም በላይ እኔ የማከበርው ኦዲፓ (ኦ ፒ ዲ ኦ)ነው” እያለ የስንቱን ሰው ደም ያፈሰሰው ፋሺስታዊ ድርጅትን ከማንም በላይ አከብረዋለሁ ብሎ የነገረን አብይ አሕመድ “ፍንፍኔ እንትሮስፔክት” በታበለው ድረገጽ ላይ የተለጠፈውን ስንመለከት ‘አብይ አሕመድ በኦሮምኛ ቋንቋ “ፍንፍኔ የኦሮሞ ነች” ሲል የተናገረበትን ቪዲዮ ተልጥፎ ይፋ ሆኗል። ቴድሮስ በዚህ ላይ እንዳልተስማማ እና አብይን አንደተቃወመው ሁሉም ያወቃል (ቴዲ የተጠቀመበት የቆየ ቪዲዮ ነው የቅርብ አይደለም የሚለው የመንጋዎች የማምለጫ ክርክር ወደ ጎን ትተን!)፡ ያ እንዳለ ሆኖ:: 

እንደገና  ለማ መገርሳም “ስለ ኦሮሞ ዲሞግራፊ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ስለ መቀየር ” የሰራው ተያያዥ ሴራ እና  ስለተናገራቸው ሁሉ “አላላልኩም በቆርጦ ቀጥል የተሰራ ውሸት ነው” እያለ የዋሸውን ውሸቱን ቴድሮስ ጸጋየ በማስረጃ ተቃውሞኣቸዋል። እንዲህ ያለ ማጭበርበር መሪዎች ሲፈጽሙ እንደ በዕድሉ ዋቅጅራ የማሳሉ የአብይ አሕመድ ደጋፊዎች ደግሞ ቴድሮስን “አገር አፍራሽ” እያሉ  ሲከስሱት በዕድሉ ሂፒክሪት መሆኑን እንደረዳለን።

አንድ የአገር መሪ ነኝ የሚል፦ አዲስ አበባን መቀመጫው ያደረገው ዓለም በሙሉ ‘በአዲስ አበባነት” የሚጠራትን የአፍሪካ መዲናን “ፍንፍኔ” እያለ ሲጣራ ዝም በሉ የሚሉ ባርያዎችንም “አደብ” አድርጉ የማለት መብታችንም ጭምር አክብሩልን።

አሁንም ወደ በዕድሉ ዋቅጅራ ንግግር እና እራሱ የተናገረውን የሚጣረስበትን ነጥብ ንመልከት፡
እዛው ሚሊየነም አዳራሽ በሚባለው የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በማይታይበት አዳራሽ እና አረባዊ ሰንደቃላማ የሚመስለው የኦነግ/ኦፒዲኦ ባንዴራ የተጠለፈበት ዙርያ የለበሰች ህጻን ልጅ “/ኦነጋዊ/ፊንፊኔኣዊ ፕሮፓጋንዳ” ለማድመጥ በተሴረ ሴረኛ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የደሰኮረውን የዶ/ር በዕድሉ ዋቅጅራ ንግግር 

አንዲህ ይላል፡-

“አስመሳዮች ነን፤ አስመሳይነት እና ባደባባይ ያወገዙትን ተደብቆ መስራት የነብስን ፉንጋ ምስል ለማቆንጀትን ይመሳሰላሉ። በምላስ የቃላት ውበ አሰውቦ ማሕበራዊ ተቀባይነት ለማግኘት መሞከር የማሕበረሰባችን መገለጫ እየሆነ ነው።” ይላል።

ይህ ልክ ነው። ነገር ግን ቴድሮስ ጸጋየም ይህንኑ ነው ያወገዘው እና የተቃወመው። በአደባባይ ያወገዙትን ተደብቀው እየሰሩ/ እየተናገሩ/ እያስፈጸሙ/ እየተባበሩ/ ችላ እያሉ… ያየናቸው እንደ አብይ አሕመድ፤ ለማ መገርሳ፤ ታከለ ኡማ እና በጠቅላላ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ነው ቴድሮስ በማስረጃ እየተቃወማቸው ያለው። ታዲያ አገር አፍራሽነትህን አቁምን ምን አመጣው? በዕድሉ ቴድሮስን ከመደገፍ ይልቅ አስመሳዮችን መደገፉ የመንጋ አጃቢነቱን እና ሂፒክሪትነቱን ማሳያ ነው።

ዶ/ር በዕድሉ በዛው አልተገታም፡ እንዲህም ይላል፡

“በወንበር መቆየት የማይገባቸውን በወንበር እንዲቆዩ ማድረግ ሕዝብን እንዲያሰቃዩ ማድረግ ነው!” ባለበት አንደበቱ ቴድሮስ ጸጋየ ግን “ቤት በማፍረስ ፤ ሕዝብን በማፈናቀል፤ ዲመግራፊን ለማስቀየር ኦሮሞን የበላይ ለማድረግ የሚሯሯቱትን ጎጂ እርምጃዎች እና ወንጀለኞችን በጊዜው ማቆም ያልቻለ መንገሥት ነው። እነዚህ በርካታ ወንጀሎች ሊፈጸሙ የቻሉበት ምክንያት መቆየት የማይገባቸውን ባለሥልጣኖች  ወንበር ላይ እንዲቆዩ በመደረጋቸው ነው…።” ነው እያለ ያለው ቴድሮስ። ይህ ሕጋዊ ተቃውሞ ግን በዶ/ር በዕድሉ ዋቅጅራ “አገር አፍራሽነት” ተደርጎ የመተርጎሙን አባዜ ስንገመግም “ዶክተሩ የተናገረውን እራሱ የሚቃወመው “ሂፒክሪት’ ነው ማለት ነው።

የዶ/ር በዕድሉ “ሂፒክሪት” በዚህ አላቆመም።

እንዲህ ይላል፡

"አጥፊዎችን በአደባባይ በስም ጠርቶ ያለመገሰጽ፤ በሕግ ፊት አቁሞ ያለመቅጣት፤ወንጀልን ያበራክታል፤ ያበረታታታል፡ ሌሎችም የግፍ እና የወንጀልን ፍሬ እንዲመኙ ያደርጋል” ይላል ሂፒኪሪቱ በዕድሉ ዋቅጅራ።

ቴድሮስም እኮ አጥፊዎችን በአደባባይ በስም ጠርቶ ያለመገሰጽ፤በሕግ ፊት አቁሞ ያለመቅጣት፤ወንጀልን ያበራክታል፤ ያበረታታታል፡ ሌሎችም የግፍ እና የወንጀልን ፍሬ እንዲመኙ ያደርጋል፡ ይህ ደግሞ የአብይ መንግሥት አይነተኛ ማሳያ እና ተወቃሽ ነው” ብሎ በመቃወሙ ዶ/ር በዕድሉ ዋቅጅራ ግን የተገላቢጦሽ ቴድሮስ ጸጋየን “አገር አፍራሽ ብሎ ይኮንነዋል። እኛ እኮ የምንለው አብይ አሕመድ “የሚጥሙ ቃላቶች ከማሽሞንመን ውጪ ምንነቱ አልተለየም” የበዕድሉ መሪ አብይ አሕመድ “ግልጽ” ሰው አይደለም ነው ክርክራችን። በአክራሪ ኦሮሞ አስላም ሴት ከንቲባዎች በሺዎቹ ቤቶቻቸው በላያቸው ላይ በቡልዶዘር እያፈረሱ ሲደበድቡዋቸው ለምን በጊዜው አላስቆምከውም ሲባል “አልሰማሁም” ይላል። የጉጂ እና የገዴዎን ርሃብ፤እርዛት እና ሞት ለምን ተሎ ደርሰህ አላስቆምክም ሲባል ‘ገና መጋቢት 1 አሁን ነው የሰማሁት ይላል’። የሞቱት ወይንም በረሃብ የሰቃዩ ህጻናትንም ፎግራፍ “የፌስ ቡክ ቆርጦ ቀጥል” ነው እያሉ አውነታውን የሚያጣጥሉ እነ ለማ መገርሳ የራሱ ሹማምንቶች ወዴት እየመሩን እንደሆነ ግልጽ አይደለም ብለው ለሚተቹ እነ ቴድሮስ ጸጋየም የመሳሰሉ ሰዎችን አፍራሾች የሚል ስም ተለጥፎባቸዋል። እና አብይን መስመሩ እንዲያስተካክል በሚጮኹት በነ ቴድሮስ ጸጋየ ላይ መቦረቅ እና “ቴድሮስ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳህን ተው” ብሎ ምን የሚሉት ምሁራዊ ደብዳቤ ትርጉሙ ምንድ ነው? ተማሪው አስተማሪውን በጭምትነት በልጦ ሲልቀው፤ “ሂሚሊየሽን” ውስጥ ግብቶ “አትብለጠኝ” ነው? የደብዳቤው ዓላማ ወይስ እውን ዶክተር በዕድሉ ቴድሮስን በአገር አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ መክሰሱ የምሩን አምኖበት?

ባለፈው ጊዜ የገረመኝ አንድ ነገር አለ። አንዱ የሕግ ምሁር ከቴድሮስ ጸጋየ ጋር በ ቪ ኦ ኤ የአማርኛ ክፍለጊዜ ሲወያዩ ቴድሮስ “አብይ አሕመድ ዘሎ ወደ ኤርትራ ሄዶ “የአልጄሪስን ስምምነት ተቀብያለሁ እውን አደርጋለሁ ማለቱ ኢ-ሕጋዊ/ ኢ-ፍትሓዊ/ የሆነውን ኢትዮጵያ ተወካይ ባልነበረበት የተወሰነውን የፍርድ ውሳኔ ‘መቀበል’ “የራሳችን የሆነውን የባሕር ወደብ” እንኳ ለዘላለሙ የሚያግዳት አደገኛ ውሳኔ ነው” ብሎ በማለቱ፦ ያ የሕግ ምሁር ተብየው “ገዜው አሁን አይደለም” ብሎት “ቁጭ!”። እንዲህ የሉ ምሁራን የሚርመጠመጡባት አገር “ያ ድሃ ገበሬ” ሞቶ ቆስሎ ያቀናትን አገር “ጊዜው አሁን አይደለም፤ ጊዜው ስለ ዲሞከስራሲ ማሰብ ነው…” እያሉ ሕዝቡን የማጃጃላቸውን ቸልተኛነት ከቀጠሉ (የሚቀጥሉም ነው የሚመስሉት) አገሪቷ መወጣጫ የላትም።

 “ብዙዎቻችሁ” የኢትዮጵያ ምሁራን እንዴት አንዳስጠላችሁኝ በአውነት በቃላት መግለጽ ልነግራችሁ አልችልም። ለምን ምሁራንን ጠላህ ብሎ አንድ ምሁር ሲጠይቀኝ፡ “አንዱ አንተ ነህ” ስለው እንዲህ ስላልኩኝ የወያኔ አገልጋይ የነበረው እና “ሳልሳይ ወያኔ” ይመስረት እያለ የሚዳክረው መስመረ-ቢስ ‘የዓይጋ ፎረም አምደኛው እና ብሔረተኛው’ ፕሮፌሰር ተኮላ ሓጎስ ጋር ሰሞኑን የኢመይል አታካራ ገጥመን ነበር። እውነት ምሁራን ይህን ድሃ እንምራህ ባትሉት እራሱ መምራት ይችል ነበር። እናንተ በምትበጠብጡት መርዝ ግን ለዘመናት ተበጥብጧል። አሁንም ወንጀለኞች ለፍረድ ከማቅረብ ይልቅ እንደገና ወንጀል እንዲፈጽሙ ዕድል ተሰጥቶአቸዋል። ወንጀል ፈጽመው “ምነው?” ተብሎ እነ አብይን ስንጠይቅ “ዲሞክራሲ ተሰጥቶአቸው ስላማያውቅ ‘አዲስ ዲሞክራሲ እየተለማመዱት’ ስለሆነ ቸል በሉዋቸው” ይለናል። በንግግሩ ገርሞን ስንተችም ‘የምሁራኖቻችን መልስ ‘እውነቱ ነው “ዓብይን” አትበጥብጡት ዲሞክራሲን እያለማመደን ነው እያሉን ነው።በሰው ልጆች ህይወት የሚያሾፉ ‘መሳቂያዎቹ!’ 

 ይህንን ልበል እና ላሳርገው።

ምሁራን ሆይ መቼ ነው እራሳችሁን “ነፃ” ሰው አድርጋችሁ መንግሥትን እና ወንጀለኞችን ያለምንም ይሉኝታ እየተቋቋማችሁ ባርያ ከመሆን የምታላቀቁት? ዑሾ የተባለ “ህንዳዊ ፈላስፋ” በድምጽ የተናገረውን ወደ ጽሑፍ የገለበጥኩት “ትራንሰክራይፕ” ያደረግኩትን እንደህ ሲል ያለውን ትምህርታዊ ምክሩ ጠቅሼ ልደምድም’፦

“…Do not follow the crowd. Be individual. Only then you can be a master. Only individuals can be masters. In the crowd you have to be a slave.  The crowd consists of slaves. All the politicians, all the leaders want you to remain slaves. Only then፣ they can be great leaders and great priests. Otherwise who will follow your stupid leaders? Who is going to follow Adolf Hitler or Josef Stalin…? Who is to follow these people? Only slaves! Only people who do not know what they are doing. “Following them will be following ditches!”  

በማለት ሁሉም እየተከተለው ነው ተብሎ በመንጋ ጋጋታ እና ጭብጨባ እኛም እንከተለው እያለ የሰከረ ማሕበርን “አልከተልም” ፤ “ይህ መሪ ወንጀልን መቆጣጠር አልቻለም”  “አናርኪ/ ስርዓተ አልባን/ አንግሷል”፤ “ሉኣላዊነትን የሚያከብር አይደለም” “የቃላት አሽሞንሟኝ እንጂ የግብር ሰው አይደለም” ፡ ለሚል ነጻ ሰው  “እንደ አፍራሽ” እየተከሰሰ ያለው “ቴድሮስ ጸጋየን” መውቀስ አግባብነት የለውም!

ቄሮ ተብሎ ስም የተሰጠው “አደገኛ” የኦሮሞ ወጣት የተሰዋው “ለኢትዮጵያ አንድነት” ተብሎ ነው መስዋዕት የሆኑት ብሎ የሚዋሸን ዶ/ር በዕድሉ ዋቅጅራ “የጃዋር ቄሮ” አሞጋሽነቱን ሳይመረምር ዛሬ ቴድሮስ ጸጋየን ከመወረፍ “መቈጠብ” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እወዳለሁ። ቄሮ በማን እና ለምን ግብ እንደተዋቀረ ስልጠናስ ማን ይሰጠው እንደነበረ “ቄሮን ያሰለጠኑት” እና “የመለመሉት” አሰልጣኞቹ እና መልማዮች የሆኑት እነ ጃዋር እና እነ ዳውድ ኢብሳ በአንደበታቸው የመሰከሩትን ‘ማስረጃ’ ሕዝቡ ሰለ ቄሮ ያለው ግንዛቤ እንዳይኖሮው ከመጣው ጋር የማንጨብጨብ አመል ካንድ ምሁር አይጠበቅምና ቃላቶችን እያቆነጃጁ (ሮማንትሳይዝ እያደረጉ) ሕዝብን ማስከር ይቁም! የቴድሮስ ጸጋየንም ነፃነት ሳትጋፉ “አፍራሽ” የመትለዋን የማምለጫ ቃላት ወደ እናንተው ዋጥዋት እና “ነጻው ሰው” ግን ለቀቅ እንድታደርጉት እንጠይቃለን!   
 አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)



No comments: