ትችቴ ለታማኝ በየነ
ጌታቸው ረዳ የኢትዮያ ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay
ይህ ፎቶ ታማኝ በየነ ከጸረ ኢትዮጵያ ከኦነግ ጀሌዎች ጋር የተነሳው ነው። ይህች የኦነግ ባንዴራ በወለጋ በአርበባ ጉጉ ወዘተ…. አማራዎች ሲጨፈጨፉ በደስታ የተሰቀለች የፏሲስቱ የጸረ አማራዎች የኦነግ የባንዴራ ነች። |
ባለፈው ሰሞን ዋሺንግተን ከተማ ውስጥ “Tamagne Beyene’s speech at Gondar solidarity protest in Washington DC” https://youtu.be/ZLPCTKV5nHI በሚል ርዕስ በድረገፆች የተለጠፈውን ስዕለ ድምፅ/ አውድዮ ቪዲዮ/ ስመለከት አንድ ያስገረመኝ የታማኝ በየነ ንግግር አደመጥኩ።
እንዲህ ይላል፦
“በአማራ ስም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ በኦሮሞ ስም
የተደራጃችሁ ድርጅቶች፤ በሌ፤በሌላም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች በእውነት ይኼን ሕዝብ የምትውዱት እና የምትደክሙለት ከሆነ
ከራሳችሁ ኢጎ/Ego/ ዝቅ ብላችሁ መነጋገሪያ ሰዓቱ ዛሬ ነው!” ይላል አቶ ታማኝ። ተሰብሳቢውም በተለመደው ስሜት ጭብጨባውና
ፏጨቱ አስተጋባው።
ታማኝ የታወቀ የመድረክ ሰው በመሆኑ የሚናገራቸው ቃላቶች የሚያበጥራቸው
የለም። ሕብረተሰቡ የሊሂቅ ሙርከኛ ስለሆነ፤ የጌታ ቃል ይመስል ከነገለባው መቀበል ነው። በየስብሰባው እየተገኘ የሚያደርጋቸው አንዳንድ
የታሪክ ውሸቶች ተከታትሎ የሚያበጥራቸው የለም። ለምን ጌታቸው ረዳ
ብቻ የሚለው ጠያቂ ሊኖር ይችላል። ጌታቸው ረዳ ለተቃዋሚም፤ለጮሌ የመድረክ ሰውም ሆነ ለወያኔ አቃጠሪና እግር አጣቢ ድጋፍ የቆምኩ
ሰው አይደለሁም። እኔ የቆምኩት በዚህ አደገኛና ፈታኝ ዘመን ውሸት እያደገች በሄደችበት ዘመን እውነት እንዳትደበቅዘብ የቆምኩ አንድ
ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ስለሆነም፤ ማንም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በሚከተለውና በሚሰብካቸው ንግግሮቹ እውነትና ውሸት ለይቼ ሕዝብን
ማስተማር ከወጣትነቴ የጀመርኩት መርህ ነው።
አንድ የራዲዮ ጋዜጠኛ እንዲህ ሲል ጠይቆኝ ነበር። “ስታዘብህ
እጅግ የተለየህ ሆኜህ አግኝቼአለሁ።” እንዴት? ብዬ መልሼ ጠየቅኩት። “ልጠይቅህ፡ ግፍ በሚፈጽሙ ላይም ሆነ ተቃዋሚዎችም ያለሆነ
ነገር ሲያደርጉ ቀድመህ ትችት በመሰንዘር ትታወቃለህ፤ በተለይ አማጽ በማንም ይሁን በማን ወገን ሲፈጸም ጮሕ ብለህ በማስተጋባት
በዚህ ባሕሪ እንዳለህ ታዝቢኤለሁ። ይህ ባሕሪ እንዲኖርህ ያሳደረብህ ተጽእኖ ምንድነው ትላለህ? የሚል ነበር። አመጽን እንድቃወም
መሰረት የሆኑኝ ሕሊናየየ ውስጥ የሰረጹብኝ ሁለት ነገሮች ልንገራችሁ።
እንአቴና አባቴ እጅግ ሲበዛ ይዋደዱ ነበር። ሆኖም አባቴ በደጅም በውስጥ ቤትም
ሃይለኛ ስለነበሩ፤ በሆነ ነገር ሲቆጡ እናቴን ለመደብደብ የሚቃጣቸው
ስለነበሩ፤ ህፃን ሆኜ ከእናቴ ጋር ወግኜ ከአባቴ ጋር ብዙ ንትርክ የፈጠርኩበት ጊዜ ብዙ ነበር። እናቴ ለውጭ ሰው ሃይለኛ ብትሆንም
ለአባቴ ረጋ ያለች አስተዋይ ስለነበረች፤እጅግም ስለምወዳት፤ የሚደርስባት የአባቴ ቁጣ “ከወስጥ ስሜቷ እንዴት እንደሚያሰቃያት እታዘብ
ስለነበር እሷን ስመለከት አንጀቴ ሁላ ይንሰፈሰፋል፤ ይበሳጫል፤ እቃጠላለሁ፤ እምባዬ ይተናነቀኝ እንደነበር ትዝ ይለኛል። በዚህ
ተቃውሞዬ ምክንያት አባቴ በመጨረሻ ባስገራሚ ቀጽበት ፍጹም ወደ ረጋ እና ወደ የመከባበር መንፈስ እንደተለወጡ አስታውሳለሁ። እውጭም፤
በትምህርት ቤትም ጉልበተኛ ሰው አቅም የሌለውን ሲያጠቃ አንጀቴ አያስችለኝም አንጀቴ “ይንቀሳቀሳል”።
ሁለተኛው ሌላው የግፍ ምንነት የተመለከትኩበት
ወቅት፤ ሰለኽለኻ ከቤተሰብ ጋር ትንሽ ሆኜ ለጥቂት ወራቶች ኖሬአለሁ።
“ሰለኽለኻ” ተብላ በምትጠራ ከአክሱም ከተማ 40 ኪ.ሜ (?) ራቅ ብላ በምትገኝ ትንሽ ከተማ አንድ የከተማው ገዢ የነበሩ “ፊታውራሪ
ማዕረግ የነበራቸው (ካልተሳሳትኩ ስማቸው ፊተውራሪ ታፈረ የባላሉ መሰለኝ”) አምባገነን ሰው፤ ልጃቸው ለመዳር ወዲያ ወዲህ ሲሉ
፤ ለድግሱ/ለሰርጉ የሚሆን “ዳስ’’ ለማሰራት በጥዋቱ 3 ሰዓት በአሽከሮቻቸው ታጅበው ወደ ከተማዋ ፒያሳ በማምራት የዕለት እንጀራቸውን
ፍለጋ ለሸቅል ቆመው የነበሩ ምስኪኖች ሰብስበው ለ“ዳስ” ስራ ወደ ፊታውራሪው ቤት እንዲሄዱ በትእዛዝ ሲነገራቸው፤ ከሸቃዮቹ አንዱ
“ጌታዮ ሆይ! ሚስቴ ታምማብኝ፤ከአልጋ አትነሳም፤ የምንቀምሰው እህል ውሃ የለንም ሸቅል አግኝቼ “ሕርካም” (ሱሙኒ/ሃያ አምሰት ሳንቲም) ባገኝ፤ እሷን እንደሰራሁ፤
ጉልበቴን ለጌታዬ በደስታ አበረክታለሁና አሁን ግን ይማሩኝ፡ ብሎ ሲላቸው፡ በያዙት ከባድ ከዘራ ግምባሩና ጭንቅላቱ ላይ ተርትረው
ሲጥሉት፤ አወዳደቁ ልክ አንደ ባሕር ዛፍ “ጅው” ብሎ ሲወድቅ አካባቢው ላይ ቆሜ ስለነበር ይህ ግፍ ድንገት ሲከሰት አይቼ “ህሊናዬ”
“በጭለማ” ተውጦ ዓይኔ ታውሮ ማየት እስኪያቅተኝ ተንደርድሬ ወደ እሳቸው በማምራት እንደጮኹኩባቸው የተሰማኝ የግፍ ገጽታ” በ8
አመቴ ያየሁት ነበር። ያ ሁኔታ አሁንም ሳስታውሰው ይረብሸኛል።
እነዚህና የመሳሰሉ ግፍ እንድጠላና እንድቃወም አድርገውኛል
የሚል ግምት አለኝ። ስለሆነም፤ ያን ያለፍኩበት በሕሊናዬ ውስጥ በሕጻንነቴ የተቀረጸው ግፍን የመቃወም አጋጣሚ ዛሬ አድጌ፤ ግለሰቦች
ባላቸው “ማዕረግ”/ስታተስ/ እንዳልምበረከክ አድርጎኛል። ስለሆነም፤ ታማኝ በየነ ለአገሩ ያለው ሁነኛ ፍቅር እንደተጠበቀ ሆኖ፤
የፖለቲካ ብስለቱና በንግግሩ ውስጥ የሚዘባርቃቸው ነገሮች የሰዎችን አመለካከት የሚያዛቡ ሆነው የታዘብኳቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው።
በዚህም ተደጋጋሚ በማስረጃ መተቸቴ ታስታውሳላችሁ። ከተቸኋቸው ትችቴ አንዱ በእስላሞች ስብሰባ
ላይ ሄዶ የሰነዘረው ንግግሩ ነበር። በዚህም “በሃይማኖትና በፖለቲካ የማሻኾር ባሕሪ” በሚል ተችቼዋለሁ። ዛሬ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው
ስብሰባ ተገኝቶ፤
“በአማራ ስም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ በኦሮሞ ስም
የተደራጃችሁ ድርጅቶች፤ በሌ፤በሌላም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች በእውነት ይኼን ሕዝብ የምትውዱት እና የምትደክሙለት ከሆነ
ከራሳችሁ ኢጎ/Ego/ ዝቅ ብላችሁ መነጋገሪያ ሰዓቱ ዛሬ ነው!” ይላል። ምን ማለት ነው? ሁለት ነገሮችን ላስቀምጥ።
ወንድም አቶ ታማኝ አማራና ኦሮሞ እንዲሁም ሌሎቹ የተደራጁበት
ዓላማ አንድ አይደለም። አማራው የተደራጀው (ስለ ድርጅት ሳወራ የሞረሽ ወገኔን ነው፤ስለ ሌሎቹ አላውቅም።) ከሃያ አምስት አመት
ሰቆቃና እንቅልፍ ነው። ሞረሽ ወገኔ ምስጋና ይድረሰውና፤ በአርበኛው አቶ ተክሌ የሻውና የድርጅቱ አርበኞች አባሎች ምክንያት ከውስጥ
አገር ከሚገኙ የአማራ መገፋት ያስቆጣቸው ግለሰቦች ጋር ተገናኝተው ግፉ “በቃን” ብለው የተነሱ አማራን ከጨርሶ መጥፋት ለመታደግ
የተነሱ የአማራን ብሶት ለሕዝብና ለሕግ ለማስሰማት የሕልውና ጭኸት ከሚያስተጋቡ አማራ ድርጅቶች አንተ “ኦሮሞ እና ሌሎች ድርጅቶች”
ከምትላቸው እስከ መገንጠል ድረስ እና የኮሎኒያል ጥያቄ ከሚያነሱ
ወደ “ራሳቸው ያተኮሩ” ሰልፍ ሰንተርድ/“ኢጎዎች” ጋር “አማራን” ልክ እንደ ወያኔ በነፍጠኛነትና በትምክሕተኛነት የሚከሱና
የሚዘልፉት ድርጅቶች ጋር እኩል በማየት፤ ሰልፍ ሰንተርድ/ኢጐይስቲክ መስመራችሁ ውጡ ማለት ምን ማለት ነው?
ለመሆኑ ከዚህ በታች የሚታዩት ሙታን እነማን ናቸው? ማንስ
ጮኸላቸው? አማራ በገዛ ልጆቹ የተከዳ ማሕበረሰብ ነው። አይደለም እንዴ? እንነጋገር አንጂ! እነዚህ ምስኪን ሙታን እነማን ይመስሉሃል?
በምንስ ምክንያት ተገደሉ?
“የአመቱ ከፍተኛ ሐዘናችን” በሚል ርዕስ በጋምቤላ/ጉምዝ ውስጥ
ስጋቸው በተበሉ እነዚህ አማራዎች ምክንያት የጻፍኩትን ለአንባቢ ላስታውስ፦
“መስከረም 1/ 2008 ዓ.ም። የተወለድንባት ምድር ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ታይቶ ተስምቶ በማይታወቅ ብሔራዊ ሐዘን ውስጥ ተወጥራ በምትገኝበት በዚህ “አዲስ አመት” የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ ፤ እንደወትሮው እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እንዳይል የአማራው ሕብረተሰብ በወያኔ ትግራይ መሪነትና ሥልጣኑን ለማቆየት በየቦታው ባሰማራቸው ተባባሪ “የሰው ጅቦች” በአማራው ላይ የዘር ማጽዳት/በጀነሳይድ ጥቃት ከመቸውም በተጠናከረ በስፋት በከፍተኛ ሂደት እየተስፋፋና እየተፈጸመ ነው። ስለሆነ አዲሱ አመት ብሔራዊ ሐዘን እንዲሆን “ይህ ጥቃት በቁጭት የሚሰማው” ዜጋ ሁሉ፤ በጥቃቱ የተጠቁትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ ወጣት ገበሬዎች፤ እናቶች፤ህጻናትና
አረጋዊያን አባቶች ነብስ ለመዘከር በየድግስ ቤቱ/ኮንሰርት የሚገኝ ወጣት ብሔራዊ ሰንደቃላማውን ዝቅ አድርጎ ሐዘኑን ለመግለጽ የደቂቃ ጸሎት በማድረግ አንዲያስባቸው ጥሪ አቀርባለሁ። ከፍተኛ ውርደትና ሐዘን የደረሰባቸው በሚሊዮኖች የሚጠቆጠሩ የአማራ ገበሬዎች በዚችው የመጀመሪያዋ ቀን በሐዘን ተኮማትረው ይገኛሉ። ልጆቻቸው ተበታትነዋል፤ተገድለዋል፤ ምስቶቻቸው ተነጥቀዋል፤ ገሚሶቹም ታስረው እየተደበደቡ “ሽንታም አማራ ምን ታመጣለህ” ተብለዋል። በቆጨራ ፤በጥይት፤በቢላዋ ሰውነታቸው ተዘልዝሎ በየጫካው የተጣሉ አማራዎች ሬሳቸው የትም ወድቆ የቀባሪ ያለህ ይጮሃል። አማራው “ሽንታም አማራ” ተብሎ ተሰድቦ ተዋርዷል! ይህ ውርደት ያልተሰማው ምሁር ክፍል በተለይም የአማራው ምሁር፤ ውርደት ለምን አንዳልተሰማው ደግሜ ደጋግሜ ብጠይቅም፤ እስካሁን ድረስ መልስ ያልተገኘለት “ዝምታ” ሆኖ አግኝቼዋለሁ።” (ምንጭ፡-
“የአመቱ ከፍተኛ ሐዘናችን” ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
እንግዲህ በጸረ አማራ የሚታወቀው የግንቦት 7 ድርጅት አድናቂና
ሸላሚ፤ የኢሳት የፖለቲካ ተንታኝ እና አምደኛ አቶ ታማኝ በየነ በምን መለኪያ ነው የእነዚህን ሙታን ጩኸት ለማስተጋባት የተደራጁትን
“በኢጎቲስቲክ/ሰልፍ ሰንተርድ/ትምክሕት/ጥበት/ደንቃራ-ባሕሪ… እያልክ የምትከሳቸው? አማራን ከጨርሶ ማጥፋት ለመታደግ የተመሰረተው
ድርጅት “ሰልፍ ሰንተርድ/ጠባብ” ብሎ መክስ ካንድ የሰብአዊ መብት ቆሜአለሁ ከሚል ሰው ንግግር የሚጠበቅ ሕዝባዊ ንግግር ነው?
አገር ውስጥ ያሉ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ያንተን ዲስኩር እና ዘለፋ
ሲሰሙ አማራ ድርጀቶችን “በኢጎ” ስትከሳቸው እንዴት አንደሚመለከትዋቸው ትገምታለህ? አማራ ድርጅቶችና አማራ ምሳር የበዛበት ነው።
‘እንኳን ዘንቦብሽ ድሮውም ጤዛ ነሽ?” ያንተም ተጨምሮበት! ?
አማራዎች ለምን ተደራጁ? ስለ “በኢጎ/በደንቃራ ባሕሪያቸው”
መነሻ ነው? ምንድነው ጉዳያቸው?
“መሬታችን ተነጥቆ ለትግሬዎች በመስጠት እህቶቻችን፤ ሚስቶቻችን፤ልጆቻችን፤በሚያመክን
መርፌ እየተወጉ አማራ እንዳይራባ ወንጀል ተፈጽሞብናል። ማንም ሊደርስለን አልቻለም። ነው እያሉን ያሉት። ዓለምም ሆነ ምሁራን እንዲሁም
ፖለቲከኞች “ጀሮ ዳባ” ያሉበትን የዘር ማጥፋት በኦሮሞ ድረጀቶች በወያኔ/ሻዕቢያ/ኦነግ/ኦፕዲኦ/ ወንጀል ተፈጽሞብናል ብለው ስለጮኹና
ያንን ብሶታቸው የሚያስጋባላቸው ምሁር ስለታጣ ((አማራው በራሱ ልጆች ሳይቀር ኦሮሞዎችን ይቀርታ ይጠይቅ፤ የሚሉ አማራዎች እንደ
“ዘላለም እሸቱ” የተባለው በዘሐበሻና ኢትዮ ሚዲያ የለጠፈውን
አስታውሱ) ዘመዶቻቸውና እና እራሳቸውንም መጠቃታቸውና በብዙ ጠላት
መከበባቸው ያንገበገባቸው አማራዎች፤ ተሰባስበው ብሶታቸውን ለማስተጋባት ፤ትግላቸውን ፈር ላመስያዝ የተደራጁትን አመራዎች “በኢጎቲስቲክ/ሰልፍ
ሰንተርድ” መክሰስ “ጠባቦች” ብሎ መዝለፍ ሳያገናዝቡት ጸረ አማራ
መሆን ነው፤ ወይንም ወንጀል ነው።
ያንተው ኢሳት/ግንቦት7 ጋዜጠኞች እንደ እነ ፋሲል የኔዓለም የመሳሰሉት ጸረ
አማራ ጋዜጠኞች በሞረሽ ሊቀመንበር በአቶ ተክሌ የሻው ላይ ያሳዩት ነውራማ ጋዜጠኛነት ሁሉም የሚዘክረው ነው። የፋሲል ባለቤት ሳትቀር
ለባልዋ ቅሬታዋን መግለጽዋ እራሱ ነግሮናል (እውነት ጨዋ ሰው ነች። አምላክ ይባርክሽ! God Bless You!)። ያንተ ደግሞ
ዛሬ በሕዝብ ፊት “ሰማይ የሰቀላችሁት ደንቃራ ባሕሪያችሁ /ኢጎ” ብሎ መሳደብ ደግሞ “በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ” መሆኑ ነው።
አማራን ያልተተናኰለ ማን ነው? ስለ ወያኔም ሆነ ኦሮሞ ድርጀቶች
(ደደቦቹ የተቃውሞ ደርጅቶች ሳይቀሩ የቆሙለትና የሚያንጨበጭቡለት ጠባብ ብሔረተኛው ኦሮሞው “በቀለ ገርባም” ጨምሮ “አማራ ኦሮሞን
ይቅርታ ይጠይቅ” ብሏል፤ በራስህ በኢሳት ሚዲያ ለኢትኦጵያ ሕዘብ የተላላፈ!) አማራ ይቅርታ ይጠይቅ የሚሉና አኖሌ ሃውልት የገነቡና
የሚያደንቁ ጠቅላላ የኦሮሞ ሕዝብና ድርጅቶቻቸው ጋር በማነጻጸር “ከ3 ሚሊዮን በላይ የአማራ ሕዝብ ከዓለም ምድር ከተሰወረበት፤
(የዶ/ር ብርሃኑ አበጋዝ የሕዝብ ቆጠራ ትንታኔ በ “ወልቃይት.ካም
welakit.com” ያንብቡ) ሕልውናው አጠያያቂ ከሆነበት የአማራን ሕዝብን ከጨርሶ መጥፋት ለመታደግ የሚታገሉ አማራዎችን
እላይ የተወጠረው “ሰልፍ ሰንተርድ” ባሕሪያችሁ ዝቅ አድርጋችሁ እራሳችሁ ከሰቀላችሁት ሰንቃ አውርዳችሁ ዝቅ በሉ፤ ማለት
“ትምክሕተኞች ወይንም ጠባቦች” ብሎ መዝለፍ እጅግ አስገራሚ ነው (ለኔ)። “እላይ ከሰቀላችሁ ትምክህት/ጠባብነት/ ዝቅ
ብላችሁ እራሳችሁን አውርዱ” ማለት አማራን በትምክሕት ከሚከስሱ ከወያኔዎች ፤ከበቀለ ገርባዎች ፤ከኦነጎች/ኦፒዲኦዎች/ከሻዕቢያ ዘለፋዎች
ምንም አይለይም። እንዲህ ያለ ፖለቲካ ያለመብሰል ወይስ በስሜት ተወጥረው
ነገሮችን ሳያገነዝቡ መዘላበድ ፤እኔ ሊገባኝ አልቻለም። የኛ ፖለቲካ ምስቅልቁሉ የወጣ የተፈረካከሰ መያዣ የሌለው ስሜት የወጠረው
ጉደኛ ዘመን ነው ያለነው እና ይህ አማራንና የአማራን ድርጅትን መዝለፍ፤በጠባብነት መክሰስ እንዴት እንደሚቆም መፍትሔ ፈልጉለት።
ለመሆኑ ታማኝ በኢጎ የሚዘለፍው የእራሱን “ኢጎ” ማሕደር ያውቀዋል?
እስኪ ስለ ራስህ ‘ኢጎ’ ላስታውስህ አቶ ታማኝ ። በዚህ ልጀምር።
https://ethiopiansemay.blogspot.com/2011/12/to-see-pagefont-with-wider-range-please.html
አንብቡ። ይህ ትችቴ በ2011 (ከ 5 አመት በፊት) “ወደ ዘረኞቹ ወደ
“እናት ክፉሉ” የተመለሰው ወታደር ታማኝ በየነ” በማለት የተቸሁትን “ካረንት አፈይረስ/ኢካዴፍ” ተብሎ
በሚታወቀው የግንቦት 7 የፓልቶክ ክፍልና ድረገጽ ቀርቦ ከትግሬ ጋር እንዳትጋቡ በሚል ሰፋ ያለ ለበረካታ ተደጋጋሚ ጊዚያት ቅስቀሳ
ሲደረግበት ወደ ነበረው ወደ ዘረኞቹ ካረንት አፈይረስ ተጋብዞ በአድናቆት ሲያሞግሳቸው የተናገረው ንግግር ነው።
የክፍሉ አዘጋጅ ሙያዬ ምስክር አንዲህ ስትል ትጠይቀወላች፤
“ወደ ኢትዮጵያውያን ካረንት አፈይርስ የመወያያ መድረክ አንኳን ደህና መጣህ ይላሉ። አንተ ምን ትላለህ?” ብላ ዘረኛዋ የመድረኩ ዋና መሪዋ ስትጠይቀው፤
“በጣም አመሰግናለሁ።
ከረዥም ጉዞ እና አገልግሎት በኋላ ወደ እናት ክፍሉ ወታደር እንደተመለሰ ወታደር ይሰማኛል።” እንዲህ ዓይነት ንግግር ለእኛ ለትግሬዎች ጀሮ በጣም አስቀያሚ መልስ ነው።
ይህ የፓል ቶክ ክፍል የግንቦት 7ና የኢሳት የፕሮፓጋንዳ አሰራጭ ጭፍራ/ቻርተር/ እንደሆነ ብናውቅም፤በኛ
በትግሬዎች ላይ ያለው ጥላቻ በደምብ እንገነዘባለን። ይህ ክፍል ጸረ ትግሬ ብቻ ሳይሆን፤ ክፍሉ ጸረ ትግሬዎች የሚሰበክበት ከመሆኑ
በላይ፤አማራን በነፍጠኛነትና በትምክሕተኛነት የሚዘልፉ የግንቦት 7 አመራሮች እንደ እነ ኤፍሬም ማዴቦ የመሳሰሉ አወዳሽ ክፍል የሆነ
የግንቦት ሰባት ጭፍራ/ሚዲያ ነው። ስለሆነም አቶ ታማኝ “ከረዥም ጉዞ እና አገልግሎት በኋላ ወደ እናት ክፍሉ ወታደር እንደተመለሰ ወታደር’ ለምን እንደተሰማው ጥያቄ አቅርቤለት መልስ
ሊሰጠን አልቻለም።
ይህ ክፍል ‘ሙያየ ምስክር” (እውነተኛ ስሟ ብዙ ወንድማገኝ)
ተብላ በደርግ ዘመን፤ ማሕበበራዊ ጋዜጠኛ አዘጋጅ ነበረች የሚባልላት “ጸረ ትግሬ” ቅስቀሳ ሳትደብቅ በግልጽ በተደጋጋሚ ስትናገር
የነበረችውን በቴፕ የተቀዳውን አውድዮ ደጋግሜ ሰዎች እንዲያደምጡት የላኩትን አስታውሱ! አማራ እንዳልሆነችም በራስዋ አንደበት ነግራናለች(ድምጿም ተቀድቷል)። በዚህ
ላይ ጸረ አማራነትዋን በአቶ ተክሌ የሻው ላይም ሆነ በሌሎች ንግግሯ ላይ የተቀዱት ጸረ አማራና ጸ ትግሬ ንግግሮቿ የታወቀች የተኮነነች
ሰው ምታዘጋጀው የፓልቶክ ክፍል ነው። አቶ ታማኝ ግን ይህ ክፍል
“እናት ክፍሉ ነው”። አስገራሚው ደግሞ ይህ ክፍል/ፎረም “ዛንዜራ” በሚል ቅጽል ስም የሚጠራ ሻዕቢያ ያሰማራው
ካድሬ በዚህ ክፍል ከፍተኛ ቅስቀሳና ቦታ ተሰጥቶት አማራዎችን፤ትግሬዎችን
ሌት ተቀን እንዲዘልፍ የፈቀደ ክፍል ነው።
አቶ ታማኝ በየነ ባድናቂዎቹ የተሸለመው “ሽልማት” ለጸረ አማራ
የሆነውና ጸረ አማራ መጽሐፍ የጻፈ ፤እሱን አምነው ለትግል ወደ ኤርትራ የሄዱትን ኢትዮጵያዊያንን ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት ያስገረፈ፤ ያስገደለ፤ ያሳሰረ፤ እንዲሰወሩ ያደረገ አንዳርጋቸው ጽጌ መሆኑ እየታወቀ፡ አንዳርጋቸው ከራሱ ሃጥያት ባሻገር “ምን
ታመጡ” ብሎን እስካሁን ድረስ አማራዎችን በባርነት የያዘ፤ አማራ ወታደሮችን እየለየ የረሸነ፤ ጸረ አማራ የሆነው ወንጀለኛው ኢሳያስ
አፈወርቂን ለኢትዮጵያ ገዢነት የተመኘልን (ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ምሳሌ የሚሆን አርአያ መሪ መሆኑን የነገረን)፤ ቅጥረኛና
አደገኛ ሰው ሽልማቱን አሳልፎ “አምበሳየ” በማለት ለግንቦት ሰባት ምክትል ጸሐፊ ለአንዳርጋቸው ጽጌ አሳልፎ ካንገቱ አውጥቶ ሽላመቱን
ሰጥቶ የሸለመ ባለ “ኢጎው” ታማኝ በየነ ከቶ ማሕደሩ እኛም አንረሳውም።
ሰልፍ ሰንተርድ ምን ማለት ነው? በሚያስገርም ሁኔታ ደግሞ
አንዳርጋቸው ‘ጸረ አማራ መጽሐፍ መጻፉን” እስካሁን ድረስ የምኮራበት መጽሐፍ ነው” ብሎ ለታመኝ በየነ በኢሳት ቃለ መጠይቁ ሳያፍር፤ሰያቅማማ አፉ ላይ ሲነግረው
በንግግሩ “ቦይ ኮት አላደረገም”። ዛሬ ታማኝ ሌላ አንበሳ ስለማያውቅ “ጸረ አማራ መጽሐፍ በመጻፉ የተኩራራና በድብደባና በግድያ
ወንጀል የሚከሰስ፡አንዳርጋቸው ጽጌ “የታማኝ አምበሳና ተሸላሚ ነው”። እንዴ ሂሳብ እናወራርድ ከተባለማ ሂሳባችን እናወራርድ እንጂ
ይላል አቶ ታማኝ በተደጋጋሚ ንግገሮቹ። እንዴታ! መተሳሰብማ ከመጣ እንተሳሰብ እንጂ? በአማራ ድርጅት የተደራጃችሁ ድርጅቶች ራሳችሁ ከሰቀላችሁበት ኢጎ አውርዳችሁ! ኦ ሆ ሆ ሆ፤ ጉድ
እኮ ነው። ምን ማለት ነው?
ታማኝ “ሰልፍ ሰንተርድ/ኢጎኢስቲክ” የግንቦት 7 ሰውና አድናቂ/አጋፋሪ መሆኑን ምን የሚያጠያይቅ ነገር አለ? አንዳርጋቸው ጽጌ፤ኤርትራ በረሃ እያለ በእራሱ አባሎች ላይ “ግርፋት እና እስራት” አንዲፈጸም ያደረገ መሆኑን ከሰለባዎቹ አንደበት በማስረጃ እየተነገረውም ቢሆን ፤እሱ በሚመራውና በሚያደራጀው
ኢሳት ሚዲያ ላይ ቀርበው ካንዳርጋቸውም ሆነ ከግንቦት 7 መሪዎች ስለ ደረሰባቸው ግፍ እና የግንቦት 7 ጸረ አማራነት ከአመራሮቹ
በጆራቸው በስብሰባቸው ላይ የሰሙትን፤የደረሰባቸውውን በደል ለሕዝብ ቀርበው ከግንቦት መሪዎች “ለውይይት” አንዲያቀርብዋቸው ለታማኝ በየነ ሚዲያ ለኢሳት
በደብዳቤ ቢያሳውዩትም ጀሮ ዳባ ተብሎ መኖሩን እናውቃለን። ታማኝ ለሰበብአዊ መብት ቆሚያለሁ ካለ የግንቦት 7 አምባገነን መሪዎች
ሰላባ የሆኑ ያሰተጋቡት እሮሮ እምባ አንዲታፈን ታማኝ ለምን ጀሮ ዳባ አለ፤ ወይንም ለምን ተባባሪ ሆነ? መልስ አላገኘንም።
አቶ ታማኝ እኒዚህ ሰዎች ጋር ደርሰህ “ዝምታ መምረጥህ” ድርጅትህ ላለማጋለጥ ነው? ከዚህ ወዲያ “ኢጎ”/ስልፍ ሰንተርድ/እና
ጸረ ሰብአዊ እሮሮ መቆም ምን አለ? ሌላውን ስትከስ እኔም ኢጎየን ልግለጽ ብለህ ታውቃለህ? You a hypocrite at
its worst. ኢጎቲስቲካል/egotistical/ ማለት ምን ማለት ነው? Excessively conceited or absorbed in oneself; self-centered.
ይህ ማለት ቃላቱ ቀፋፊ መሆኑን ባንድ ምሳሌ አጠቃቀም
እንዴት ተን እንመለክት "he's
selfish, egotistical, and arrogant" ሚል
ትርጉም የቃላቱ ምንነት ይገልጻል። ታማኝ ይህንን ቃል ሲጠቀም በቀጥታ የሚያሳየው ምንድነው?
ካሁን በፊት “በፖለቲካና በሃይማኖት የማሻኮር ባሕሪ” በሚል በሜይ 2013 ታማኝ አስመልከቼ
የጻፍኩትን አስታውሱ።ታሪካችን እንደ ፋሲካ በግ ለእርድ የሚያቀርቡ ግልብ ግለሰቦች ብዙ ናቸው።፡ብዬ ነበር። ባንት በእስላሞቹ ስብሰባ ጃዋር መሓመድ “የሜንጫ ንግግር ሲያደርግ” ታማኝ ደግሞ እዛው ተገኝቶ
የሚከተለውን
ተናግሮ ነበር፦
1) ኦነግ ኢትዮጵያዊ አልነበረም”
ብለው የሚያምኑ
አክራሪዎች አሉ።
(2) ኢትዮጵያ የክርስትያኖችን
በዓል ስታከብር
የእስላሞችን አታከብርላቸውም ነበር።(
3) “ኦነግ ኢትዮጵያዊ አልነበረም” ብለው የሚያምኑ አክራሪዎች አሉ።
4) የኢትዮጵያ ሙስሊም ‘አክርሮ’ ጐራዴ ይዞ ቢመጣ ከወያኔ ጥይት ይልቅ የሙሲሊሙን ጐራዴ እመርጣለሁ እኔ።”
አላህ ወ አክበር!
ተክቢር! ተክቢር!
ተክቢር! ሲል ነግሮናል።
ምናልባት ትንተናዬ ያላነበባችሁ ሰዎች ጽሑፌን በሰጠሁት ርዕስ ጉጉል አድረጋችሁ
ግቡና አንብቡት። በመጀመሪያ ነገር “የማሿኮር” ባሕሪ ካልሆነ በስተቀር አስላሞች ኢትዮጵያን በገዙበት ዘመን ወቅት፤ እንኳን
ክርስትያን በዓል እንዲከበር ቀርቶ ሊፈቅዱ ክረስትያኖች እያረዱ በሰይፍ በሃይል ወደ እስልምና አንዲለወጡ አድርገዋል።
ብዙዎቹ የዛሬዎቹ እስላሞች ወንድሞቻችን የዛው ውጤት ናቸው። አልተከበረላቸውም የሚለው ውሸት ግን እንዳለ አንቀበለውም። ታማኝ
በነበረበት ስርዓት በደርግ ጊዜ አስላሞች በዓላቸው እንዲከበር ተደርጓል። ታሪክን መዳሰስ ነው። በሃይለስላሴም ጊዜ “ዒድ” ነው
ብሎ የቀረ እስላም ተማሪ ለቅጣት ሲዳረግ እኔ እስከማውቀው አልነበረም። የወቅቱ መምህራኖች እስላም ውንድሞቻቸውን እኩል
ሲመለከቱ እንጂ እሱ እንደሚያሻኩረው አልነበረም። እስላም ነሽ ተብላ በሆስፒታል የወሊድም የጤና ምርመራም ሆነ ትምህርትም ስራም
የታገደ ዜጋ የለም/የለችም።
** ኦነግ
ኢትዮጵያዊ አልነበረም”
ብለው የሚያምኑ
አክራሪዎች
አሉ።**
የሚለው ዲስኩሩ ደግሞ፤ ፍጹም የተዛባ ስብከት ነው። ኦነግ ኢትዮጵያ አልነበርም ያለ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የለም። አይደለም ብሎ
በፖሊሲው የጻፈና የተከራከረ ኦነግ እራሱ ነው። ዛሬም ፖሊሲያቸውና እምነታቸው “ያንኑ ያንጸባርቃል” (ስማቸው
ቢቀያይሩም ያው ታጭቦ ጭቃ ናቸው)። ስለዚህ አክራሪነቱ ለኦነግ መስጠት ሲገባው ለሌሎች ዜጎች መለጠፍ የማሻኮር ባሕሪ ነው።
**የኢትዮጵያ ሙስሊም ‘አክርሮ’ ጐራዴ ይዞ ቢመጣ ከወያኔ ጥይት ይልቅ የሙሲሊሙን
ጐራዴ እመርጣለሁ እኔ።” አላህ ወ አክበር! ተክቢር! ተክቢር! ተክቢር! መፍከሩ ስንመለከት ሰውየው የአክራሪ አስላሞች ጎራዴ ከጥንት ጀምሮ ምን ያህል
(ከአክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ) ኢትዮጵያን እንዳጠፋ፤ አሁንም በወያኔ ዘመን፤ “አክርረው” የመጡ የአክራሪ አስላሞች
ጎራዴ ስንቱን ክረስትያን እምባ በጅማ፤በሐረርጌ በትግራይና በመላው አገሪቱ እንዳስለቀሰ ወንድማችን ታማኝ በየነ
የሚዘነጋው አይደለም። ሆኖም የማሻኮር ባሕሪ አደገኛ ነውና አስላሞችን ለመሳብ ታሪክና ነባራዊውን ገጽታ በመደበቅ ዲስኩር
እየነፋ “አክራሪ አስለካምን ከወያኔ ጥይት መምረጥ” አስገራሚ ነው። በመሰረቱ ምርጫው ያልበሰለ የመድረክ ሰው የሚዘባርቀው
አባባል አንጂ፤ ከወያኔ ካክራሪ አስላም ምረጡ ብንባል የሚባል ምርጫ ለኔ ምን ማለት አንደሆነ አይገባኝም። በየመድረኩ ለፖለቲካ
ዝና ተብለው የሚሰበኩ የተዛቡ ሰበካዎች መበጠር አለባቸው። የፖለቲከኞች ባሕሪ ለመለየት ስትፈልጉ የሚናገሩት ንግግር ማበጠር (ጠለቅ ብሎ የብዙ ጊዜ
የንግግር ማሕደራቸውን መመርመር) ማንንታቸው በግልጽ ይነግረናል። እነዚህ የመድረክ ዝና የተጠናወታቸው የዝና ሱሰኞች በፖለቲካውን
ሊያዛቡት የሚችሉበት ችሎታና መድረክ አላቸው። ትግሉ
የሚኮላሽበትም ከብዙዎቹ አንዱ ምክንያት መድረኩ በነዚህ “ሂፕክሪቶች” ስለታመጸ ነው።
አንድ ምሰሌ ልስጣችሁና ወደ ሌላው ነጥብ ልዙር፤ኦነግን በሚመለከት የታማኝ በየነ የማሻኮር ፖለቲካ ስራ በእሱ ብቻ አልተጀመረም።ከእርሱ በፊት
የዶክተር ማዕረግ ያላቸው ብዙ ሞኞች እና አሳባቂዎች የጀመሩትየፖሊቲካ ሴራነው።
ለምሳሌ ዶ/ር ዜሮ የሚል የተጸውኦ/የቅጥያ ስም የተሰጣቸው ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው እንዲህ ይላሉ
(2) ኦነግ“ኢትዮጵያዊአይደለሁም”ብሎአያውቅም።
(3) ኦነግ “የመገንጠል ጥያቄ ጠይቆ አያውቅም ሲሉ ባደባባይ ተናግረዋል።
በዚህ የውሸት እና የደላላነት ፖለቲካ ንግግራቸው
ደ/ር ጌታቸው ጋሻው
“ዶ/ር ዜሮ” የሚል መጠሪያ ተሰጥቷቸዋል። ፖለቲከኞችም ሆኑ የመድረክ ሰዎች ካንደበታቸው የሚሰነዘሩ ቃላቶች ማሕበረሰቡን የማናጋት
ችሎታ ስላላቸው በጥንቃቄ መበጠር አለባቸው የምለው ለዚህ ነው።
ታማኝ አማራውን/አደራጂዎችን “ከሌሎች ጋር ደምሮ” ሰማይ የተሰቀለ “የግል
ኢጎአችሁ” ከራሳችሁ አውርዳች ዝቅ በማለት አውርዱት ብሎ ሕዝብ በተሰበሰበበት እና መላ ኢትዮጵያ በ ያዳምጥበት መድረክ፤
አማራዎች የሆኑ አማራን ድረጅት የሚመሩ በኢጎትስቲክ ሲከለስ፡ ታማኝ የሚናገራቸውን ቃላቶች እንደ አምላክ ቃላት
የሚቀበላቸው ተራው አድማጭ “አማራን ከፈጽሞ ከጥፋት ለመከላከል” የተደራጁ ድርጅቶችን በጠባብነት/ በትምክሕተኛነት እንደሚተቻቸው
የሚያጠራጥር አይደለም።፡ምክንያቱም የመድረኩ ሰው ታማኝ ነግሮአቸዋል እና። ያውም አገር ያለው ሕዝብ እማ ጭራሹኑ ስለ አማራ
መጨፍጨፍ ጀሮም የለውም የዛሬውን የጎንደር “መብረቃዊ አብዮት” ከተኛበት ከተነሳ በኋላ ሳይጨምር
ማለቴ ነው) ።
ምሳሌ ልስጥ
ኢንጂኔር ሃይሉ ሻውል ከመሳይ/ኢሳት ያደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዲህ ይላሉ፤
“የወደፊት ትውልድ እኮ እያለቀ ነው! እዚህ እኮ እከተማው ውስጥ “የተፈናቀለው ሕዝብ አጠገቡ ቁጭ ብሎ እያለ፤ “ሰው እኮ አለቀ” ብለህ ሰውን ስትነግረው “የት?” ብሎ ይጠይቅሃል። አያውቅም፤ ምንም! ይህ ሁሉ “ሁማን ራይት ድርጅት” ምነው ዝም አለ? ሰው ሳይነግረው ቀርቶ ነው? ወይንስ እምቢ አንተባበርም አንጮህላችሁም ብለውን ነው? አሁን ለምሳሌ ሰልፍ ይደረጋል ይባላል። አማራ አለቀ ተብሎ ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጎ ያውቃል? የሰማሁት አለ? ዋሽንግተን ተደርጓል? ፍራንክፈርት ተደርጓል? ብርሊን ተደርጓል? የለም! ለምንድነው ይህ ሕዝብ በራሱ ሕዝብ የተጠላው?
አማራው የሌላው ጉዳይ ሲመጣ አብሮ ይሰለፋል፡ አብሮ ያለቅሳል፡ የራሱን ጉዳይ ግን፤ ማንም፤ምንም፤ማንም አንድ ፋይዳ አድርጎለት አያውቅም።የተጠናከረው ጠንካራ ረዚስታንስ ቆሞ አምቢ የሚል ስለጠፋ ነው። አንድ ሰው ከቤቴ አልወጣም ሲል ሚሊሺያ መጥቶ ደብድቦ አጎሳቁሎ፤አቁስሎ፤ ከቤቱ አስወጥቶ ሜዳ ላይ ይጥለዋል። ማን መጥቶ ይከላከልለት? መንግሥት የለ፤ የሌላ ብሔረሰብ መጥቶ አይረዳውም፤ ብቻውን አማራ የሚባለው “በሽታ ይመስል” ሁሉም ….ሌላ ቀርቶ የአገር ውስጥ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች እንኳ ሁሉም የአማራ ጉዳይ መስማት አይፈልጉም!” በቃ እውነቱን መናገር ነው፡ አይፈልጉም! በቃ መስማት አይፈልጉም!” ሃይሉ ሻውል።
የፖለቲካ ተቃዋሚዎች የአማራን ጉዳይ መስማት ባልፈለጉበት ወቅት
ጥቂት አማራዎች/ወልቃይቴዎች ተሰባስበው ስለ ብሶታቸው ለማስተጋባት ሲደራጁ
አቶ ታማኝ በየነ “ባጎይስቲክ” ይከሳቸዋል። ይኼ አስገራሚ ነው።
በኔው እና በሌላ አርበኛ ወጣት ጽሑፌን ልደምድም።
አቶ ታማኝ በየነ በ2014 ካሊፎርኒያ/ሰናሆዘ ከተማ የኢትዮጵያዊያን የአመቱ
የስፖርት በዓል በተከናወነበት ወቅት ‘የሞረሽ ወገኔ አማራ ድርጅት’ መሪዎች ባዘጋጁት ሕዝባዊ ስብሰባ/ኮንፈረንስ በእንግዳ
ተናጋሪነት አኔ እና እውቁ የታሪክ ምሁር ዶ/ሃይሌ ላሬቦ፤ዶ/ጌታቸው ሃይሌ ተጋብዘን ነበር። በወቅቱ እኔ ያቀረብኩት ጥናት “የትግሬ
ልሂቃን በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? “በሚል ርዕስ ለጉባኤው አቅርቤ ነበር። በወቅቱ የታማኝ በየነ
“አንበሳ” የግንቦት 7 መሪው አማራ የሆኑ ወታደሮችን በመምረጥ ሲገድል የነበረው ኢሳያስ አፈወርቅ አሞጋሽ
አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ታፍኖ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ ተወስዶ በነበረበት ወቅት ስለነበር፤ ግንቦት7/ ኢሳት
ባዘጋጀው ሕዝባዊ ጉባኤ ለመሳተፍ አቶ ታማኝም በጉባኤው አዳራሽ ተገኝቶ ነበር።
በወቅቱ ታማኝ በየነም ሆነ የታማኝ በየነ ኢሳት “ሚዲያ” ለነብርሃኑ፤ ለነ አንዳርጋቸው፤ ለነመሳይ ከበደ….ለነ…ለነ….. ጉባኤ እየጠሩ ሕዝብ ሰብስበው ሲጮሑ ፤መድረክ ሲከፈትና በየአገሩ ተደጋጋሚ መድረክ ሲዘጋጅ፤ ስለ አማራ ጉዳይ የተዘጋጀ መድረክ አላየንም። ያውም እዚህ ሳንሆዘ ካሊፎረኒያ ውስጥ፤ ስለ አማራ ጉዳይ ሞረሽ ያዘጋጀውን መድረክ አማራዎቹ እነ ታማኝ በየነ እና የመሳሰሉ ታዋቂ የኢሳት ሰዎች የአማራውን መድረክ ለመነጋጋር የተዘጋጀውን አዳራሽ እየረገጡ፤ በጎሪጥ አዳራሹን እያዩ በማለፍ ኢሳት ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ አዘጋጀው መድረክ እና አዳራሽ ነበር የሄዱት።ያውም፤ ሆን ብለው ኢሳቶች የአማራውን መድረክ ሰው እንዳይገባበት ሞረሽ ባዘጋጀው ሰዓት፤ቀን እና ቦታ አዘጋጅተው፤ ሕዝቡ ጎን ለጎን በሁለት አዳራሽ ባንድ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ
ቅጠር ግቢ ውስጥ ለየቅሉ ተከፍሎ ነበር የተሰበሰበው። በዚህ ላይ እኔ የሞረሽ ተናጋሪ አንግዳ ሆኜ ተጋብዤ ስለነበር፤ በጉዳዩ ልዩ ትችት ለኢሳት አዘጋጆች…በታማኝ፤ በአበበ ገላው (አበበ በላው ኢትዮጵያዊ እንጂ “አማራ” አይደለሁም ብሎ ኢመይል ቢያደርግልኝም ) እና በመሳሰሉት ላይ በማግስቱ ትችት ጽፌ እንደነበር አንባቢዎቼ የምታስታውሱት ነው። ታማኝ በየኔ ያኔ ላንድ ግለሰብ ለጸረ አማራው እና በሰብአዊ መብት ረገጣ
በሚከሰስ ለአንዳርጋቸው ጽጌ ጩኸት ለማስተጋባት ወደ አዳራሹ ሲያመራ፤ የሚጮኽለት ያጣው ለሚሊዮኖች የሚቆጠር አማራ ሕብረተሰብ የተዘጋጀው ሕዝባዊ ጉባኤ እንደጠላት ጉባኤ በጎሪጥ ዓይኑ ሰረቅ አድርጎ
እያየ ረግጦት ነበር ወደ አንዳርጋቸው አዳራሽ ሄዶ ንግግር ያደረገው። ዛሬ “ለማያውቅሽ ታጠኚ” ሆነና፤ ታማኝ ስለ አማራ እጮሃለሁ
ብሎ፤ “ካሁን በፊት እየረገጣቸው ሲሄድ በነበሩት ላይ በቁስሉ ላይ ጨው ጨምሮ” “ሰማይ ከሰቀላችሁት” “ኢጎአችሁ “ “ውረዱ” ብሎ መዝለፍ እንደገና አስገርሞኛል። አንዳርጋቸው
ጽጌ ለታማኝ በየነ አፍሪካ ምድር ውስጥ ያልታየ የዘር ማጽዳት ከተካሄደበት እልፍ አማራ ሕዝብ በልጦበት ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲያለቅስ
ሲሸልም በኔ በጌታቸው ረዳ በኩል ታሪክ ዘግቦታል። አጎብዳጅ ሁላ፤ተታዋቂ ፖለቲካ መሪ፤ ታዋቂ ድርጀት፤ታዋቂ ሚዲያ፤ ዝነኛና የመድረክ
ሰው መንካት/መተችት አይገባም ብለህ የምታነፈንፍ የሊሂቃን እግር አጣቢ ሁላ ከዚህ ባሕሪ ውጣ።
ይህ ፎቶግራፍ አማራ ነብሰጡሮች፤አረጋዊያን ፤ወጣቶች፤ህጻናት፤ሴቶች፤ወንዶች፤እየተገፈተሩ ያለቁበት ገደል ነው። ወጣቱ አርበኛ ሙሉቀን ተስፋው ገደሉን በዘገበው ጥናት ላይ የተካተተ ፎቶ ገደሉን ምን አንደሚመስል ሲያሳይ ነው። |
ወጣቱ ሙሉቀን ተስፋውእና የአማራን ግፍ
ማሕደሮች በስንት መከተራና ትግል እየተሰቃየ እየዘገበ ለታሪክ እና ለሕግ ያቆየልንን ማሕደር ደብቆ ወደ ውጭ አገር በማስወጣት
የታወቀው ይህ ወጣት ለእነ ታማኝ በየነ እና አማራን በጠባብነት/በትምክሕተኛነት ‘ኢጎ’ ለሚከሱ እንዲህ ይላል።
ዘረኝነት ምነድ ነው? በሚል በሰሞኑ የጻፈው
ጽሑፍ ፤ልጥቀስ፦
“ሁሉም የዐማራ ወጣቶች እንዲገነዘቡት የሚያስፈልግ ነገር አለ፤ስለዐማራ ስትናገሩ አንገታችሁን እንድትደፉ የሚፈልግ ቡድንና ሰው ብዙ ነው፡፡ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የዐማራውን መደራጀት ብሎም ለመብቱ መቆም የሚደረገውን ተጋድሎ የሚቃወም ቡድን ወይም ሰው ሁሉ ከወያኔ ጋር እኩል ጠላታችን ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ወገኖች የእኛን መኖር አይሹምና፡፡ ወይም ነባራዊውን ሁኔታ ያልተገነዘቡ በምኞት ዓለም ውስጥ የሚዳክሩ ናቸውና፤ ትግላችንን ወደ ኋላ የሚጎትቱ ዘገምተኞች ናቸውና፡፡…………… ይህን ስትናገሩ የነፍጠኛ ልጆች ናችሁ የሚሏችሁ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ይህን ስትናገሩ ትህምከተኛ ናችሁ የሚላችሁ ይበዛል፡፡ አዎ ይህን ስንል፤ ስለዐማራ ሕዝብ ስንናገር የሚያመው ብዙ ሰውና ቡድን ነው፤ ግን ገና እንናገራለን፡፡ ስንጽፍ የሚያቅለሸልሸው ሰውና ቡድን የትየለሌ ነው ግን ገና ገና እንጽፋለን፡፡ ምክንያቱም ያገባናልና፡፡ ስለዐማራ ሕዝብ መናገር ከሚገባን አንጻር ካየነው ገና አልተናገርንም፤ ይህን ያክል በመቶኛ ከማለት ምንም ብንል ፡ ገና አልተናገርንም አልጻፍንም፡፡ የዐማራ ሕዝብ የሠራውን ታሪክ ለመክተብ ሰማይ ብራና ዝናማትም ቀለም ሆነውይሻ ላል፡ ቢያገለግሉ አይበቁም፡፡
በተቃራኒው በዐማራ ሕዝብ ላይ የደረሰውን ዕልቂት ለመግለጽ እንዲሁ፡፡ ስለዚህ ነው የምንናገረው፤ ስለዚህ ነው የምንጽፈው፡፡ የዐማራ ሕዝብ ላይ የደረሰው ፍጅት፤ የታቀደው የዕልቂት ድግስ እስኪቆም ደረስ፣ የዐማራን ሕዝብ ሕልውና በሚገባ እስክናረጋግጥ ድረስ እንናገራለን፣ እንጽፋለን፤ ይህ የእኔ ቃል ብቻ አይደለም፤ የብዙ ሚሊዮን ዐማሮች ሐሳብ እንጅ፡፡
No comments:
Post a Comment