“ቪዥን ኢትዮጵያ”
ለኤርትራ ጥብቅና!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ- Ethiopian Semay blogspot.com)
ወደ ኋላ
ታሪክ ስንፈትሽ፤ከሰማይም የተምዘገዘጉ፤ በምድርም የተወረወሩ የሙሶሎኒ ቦምቦች የብዙ ሺሕ ጀግና ሕዝባችን እና የሴት ዘማች አርበኞች
ሕይወት ቀጥፈው እራሳቸውም ተቃጥለው ወደ አመድነትና ጭስነት ተለውጠው በንነው ታሪክ ሆነው የቀሩ ዳግም ላይመለሱብን ነበር የመሰለን።
አጥፍተውን ጠፍተዋል ያልናቸው የተቃጠሉ የሙሶሎኒ ቦምቦች ከአፈሩ
ጋር በመዋሃድ ቀስ በቀስ በቅለው ሕይወት ዘርተው ወደ ሰውነት የመለወጣቸው አስገራሚ ሂደት ሳስበው እጅግ አስገራሚ ተፈጥሮ ሆኖ
አግኝቸዋለሁ። ይህ ህልም ወይስ እውነታ?
በ 1928 ዓ.ም ሰለኽለኻ/ትግራይ
ውስጥ በተካሄደው ውግያ በደጃች አያሌው ብሩ ሲመራ የነበረው ጣሊያንን “ማማ ሚያ” እስኪል ያስጮኸው እጅግ አስገራሚ ጀግና የነበረው ተዋጊ ጦር፤ አላስጠጋ ብሎ ሽብር ሲለቅባቸው ከነበሩት የጠላት መሳርያዎች
ክፉዎቹ “የእጅ ቦምምቦች” ነበሩ፡ በምትኩ ጣሊያኖችን ሽብር ሲለቅባቸው የነበረው ባሕላዊ ኢትጵያዊያ ስሪት መሳሪያ ድግሞ “ጎራዴ”
ነበር። ታዲያ እነኛ ጀግኖች ብዙ ሕዝብ የፈጁ የጣሊያን ቦምቦችን “የሙሶለኒ ወንበዴዎች”
በሚል የቅጥያ ስም ይጠሯቸው ነበር።
በእዛው አስጨናቂ የቦምብና የጎራዴ፤የእጅ
ለእጅ የጨበጣ ውጊያ የተከሰተ አስገራሚ “ጽናት” እና “አደራ ተረካቢነት” አሁን ላለነውና ለወደፊት ለሚመጡ ትውልዶች የማይረሳ
አንድ ትምህርት ትተውልን ሄደዋል። ቀኑን ሙሉ እስከ ማታ ድረስ ውግያው አልቆመም። ጣሊያኖች በብዛትና በመሳሪያ እጅግ 10 እጅ
አጥፍ ናቸው። አበሾቹ በቦምብ መርዝ ጣይ አይሮፕላኖችና በእጅ ቦምቦች እየተደበደቡ ሞራላቸው ጽናት ቢኖሮውም፤ እልክ ውስጥ ገብተዋል፤
ጭንቅ ውስጥ ገብተው እየተዋጉ ቁጥራቸው ቢመናመንም፤መርዙ ዓናቸውና
ቆዳቸው እያቃጠለ፤አላላውስ ቢላቸውም፤ ጣሊያን ካለበት ቦታ ገትረው በመያዝ እንዳይንቀሳቀስ አድርገው እስኪ መሽ ድረስ በጀግንነት መክተውታል ። ታዲያ በወቅቱ የደጃዝማች አያሌው
መድፎች ስልሳ ጊዜ ከተኮሱ በኋላ እኩለቀን ላይ ድምጻቸው ጠፍቷል።
የጣሊያን አይሮፕላኖች የአየር ድብደባ
የመድፎችን ተሸካሚ ተሽከርካሪዎቻቸውን ሰብሮታል። የአንደኛው አንዱ ሲሆን፤ የሁለተኛው ሁለቱንም ነበር። መድፎቹ የተማረኩት ቀደም
ብሎ ከተሸነፈው የዓድዋ የጣሊያን ወረራ ውቀት ነበር። መድፎቹ ማራኪዎቻቸውን ለ40
አመት በታማኝነት ካገለገሉ በኋላ፤ጣሊያኖቹ የመድፎቹን ከሃዲነት ያን ቀን በመበቀል ለዕድሜ ልክ ጸጥ እንዲሉ አድርገዋቸዋል።
አስገራሚው ነገር፤ የመድፎቹ ስባሪ
ተይዞ፤ተለቅሞ ከኛ ጋር (ከጦሩ ጋር) አንዲጓዝ ተደርጓል። ምክንያቱ አልገባኝም።” ይላሉ የተደበቀው ማስታወሻ ደራሲ ዶ/ር ሀራልድ ናይስተሮም (መጽሐፉን ወደ አማርኛ የተረጎሙት ደ/ር ገበየሁ
ተፈራ እና ደስአለኝ አለሙ።)
ደራሲው አማርኛ ቋንቋ የሚያውቁ
ሓኪም ሆነው ከደጃዝማች አያሌው ብሩ ጋር እንዲዘምቱ/ (ደጃዝማችን ለማከም ) በአፄ ሃይለስላሴ ተልከው በጦርነቱ ወቅት አብረው
የዘመቱ ስውዲናዊ ነበሩ።
እዚህ ላይ ደራሲው፤ በድካምና በቦምብ
ናዳ የደከመ ሠራዊት፤ ከጥቅም ውጭ የሆኑ፤ የተጎዱ መድፎችን፤ ስብርባሪው ሳይቀር ለቃቅሞ ይዞት እንዲያፈገፍግ ለምን አንደተደረገ
ምክንያቱ አልገባኝም የሚሉትን ምክንያት ላብራራ። እሳቸው የተመለከቱት የተሰበረን መድፍ እርባና የለውም፤ ስለዚህም መሸከሙ ምን
ይረባል? ነው መልስ ያላገኙበት ጥያቄአቸው።፤ ግን ከበስተጀርባው ለደራሲው ያልተገለጸላቸው የጀግኖች ወላጆቻችንን ምስጢር አለ።
እሱ ምንድነው?
ይኼውም፤ ወላጆቻቸው፤የህይወት መስዋእት
ከፍለው፤ ከወራሪ ጣሊያን በውግያ የማረኩዋቸውን ትጥቆች፤ መልሰው አንዳያስነጥቋቸው፤ በክብር ጠብቀው በባለቤትነት ያስረከቡዋቸውን
‘’አደራና ቃል ከዳን” ፤ ቀን ቢሸሸን፤ ወቅቱ አስከፊና ቀውጢ ሆኖ ዓለም ብትከዳንም፤ በምንም ታምር እስካልሞትን ድረስ የተረከብነውን
የወላጆች አደራና ንብረት ‘ቅንጣት” ታህልና ሰባራ ንብረትም ብትሆን፤
እዚህ ሜዳ ላይ ትትን ለጠላት መልሰን አናስረክብም! በማለት ነበር
ተዋጊውን ሠራዊታቸው “ወላጆቻቸው ደም ገብረው ያስረከቧቸውን የሉዓላዊነትን እና የቅርስ የባለ አደራነት ትርጉም” ነበር ተዋጊውን
ሠራዊት በተግባር በዛው ፈታኝና አስቸጋሪ ሰዓት ለማሳየት የጣሩት።
አሁን ወደ እኛው ትውልድ እንመልከት። የዛሬ የምሁሩ ትውልድና የፖለቲካ መሪዎች
የባለ አደራነት ሃላፊነት ትርጉም ገብቶአቸዋል? የሚለው ጥያቄ ላስቀድም።
“አብዛኛው ምሁር” አልገባውም። አልገባውም ብቻ ሳይሆን፤ ሆን ብሎ የጠላት ቅስቀሳ እና አጀንዳ/ፍላጎት ተቀብሎ ሕዝባችን አንዲቀበለው
በማድረግ በማጃጃሉ ስራ ተጠምዶ፤ አዲስ አስተሳሰብ ለውጥ እንዲከተል በማድረግ፤ ሕዝባችን ለጠላት የተመቸ እንዲሆን በማንንቱና በከፍተኛ
እሴቶቹ በሚጎዳ ቀረጻ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ።
ለአገራቸው ሉዓላዊ ክብርና ዳር ድምበር ሲሉ ሕዝባችንን በማስተማር በጽናት
ቆመው አንምበረከክም ብለው ባደባባይ የሚሞግቱ ጥቂት አርበኞች ኢትዮጵያዊያን ላይ ዘመቻ ከፍተው፤ “የትምክሕት ሃይል፤ የ14 ክፍለሃገሮች
መዝሙር ዘማሪዎች፤ አማራዎች፤ ጦርነት ናፋቂዎች፤ ነፍጠኞች፤ የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች ወዘተ…..ወዘተ…. የሚል ‘የተለያዩ የቅጽል
ስሞችን” በመስጠት፤ጥላሸት በመቀባት፤ሕዝባችን የሉአላዊነት ጉዳይ አሳንሶ እንደ ወረት፤ እንደ ሸቀጥ ዕቃ እንዲመለከተው እያደረጉ
ናቸው። እነኚህ ዘለፋዎች፤ በወያኔ ብቻ ሳይሆን የሚነገሩት፤ ‘ወያኔን” አንቃወማለን ከሚሉ ተቃዋሚ ሃይሎች ጭምር የሚሰነዝሩብን
ዘለፋዎች ናቸው።
ጭራሽኑ፤ ተተኪው ትውልድ የማንነቱን
እሴቶችና የወላጆቻችን ገድል አራክሶ ቸል እንዲላቸው በመቀስቀስ ፤ “በሴራ”
የተጎዳውን የኢትዮጵያ ሉአላዊ ድምበር፤አገራዊ ሰንደቅና ቅርጽ “በሕግ፤በፖለቲካና በጉልበት” እንዲከበር ከማስተማር ይልቅ፤ ጉዳዩን
ለመፍታት “ሕዝቦች አብረው በመብላት በመጠጣት፤ በመጫወትና እስክስታ በመርገጥ” ፖለቲካ የተበተባቸው ችግሮች በዚህ መልክ ይፈታል
እያሉ ከፍተኛ የሕሊና ማጃጃያ በመዘርጋት “የሳብቨርዢን/የአጥቂዎች ዘመቻ ዘርግተው፤ በሕዝባችን ሕሊና የአመለካከት ለውጥ/ አንዲያደርግ
በአፍራሽ ዘመቻ ለይ የሚንቀሳቀሱ ምሁራን ተበራክተዋል።
በዚህ ሥራ ላይ ወጣ፤ወጣ ብለው
የሚታዩ አንዳንዶቹ አዳዲሶች ናቸው። አንድ ስመ ገናና የሆነ ምሁር ታዋቂ ወዳጄ “ቪዥን ኢትዮጵያ” ስለሚባለው ኢትዮጵያዊያን የሚያካሂዱት
ስለ ኤርትራዊ ጥብቅና እና ሙገሳ የሚሰራ ድረጅት አዘጋጅ ስለሆነው አንድ ሰው ማንንቱን እንዲነግረኝ በኢመይል ጠይቀው፤ “ (I
do not know or heard or saw this individual before) In present day Ethiopian politics, all kinds of characters are
emerging out of no where thanks to some groups who have been able to control
the media in the diasporic space” ብሎ እንዳለው፤ ማንነታቸው ብዙም የማናውቃቸውና ታይተው የማያውቁ ሰዎች/ካራክተሮች/
በየ መድረኩና በየድረገጾች እንዲሁም በየፓልቶክ ክፍሎች፤ በግንቦት 7 አስተባባሪነት ብቅ እያሉ የሚናገሩትና የሚጽፉት ሁሉ፤ ለኢትዮጵያ
ሳይሆን ለኤርትራ ጥብቅና እና ሙገሳ ነው። በሚገርም ሁኔታ እነኚህ ምሁራን፤ “ስለ ኤርትራኖች ቀናነትና ውሸት የማይናገሩ ስለመሆናቸው፤
በጽሁፍ ዘርግተዋል።
አንዳንዶቹም በሚያስገርም ሁኔታ
ስለ ኤርትራኖች ተክለ ሰውነት እያወሱ፡መልካቸው፤ ንግግራቸው፤ ቄንጠኛነታቸው ከትግሬዎች እጅግ እንደሚያምሩ” ሁሉ የሚሰብኩ ብዙ
“በሽተኞች” ተበራክተዋል። ያለ ማፈርም “ቪቫ ግንቦት7 እና ኤርትራ! ሻዕቢያ ያሸንፋል!” የሚሉ የግንቦት7 ደጋፊዎች ኢትዮጵያዊያን
ያስተጋቡትን ድምጻቸው በድምፅ መቅረጫ ተቀርጸዋል።
ኢትዮጵያዊያን እራሳቸው በተኮሱት
የገዛ ጥይታቸው፤ ተመልሶ እራሳቸውን እያቆሰለ ነው። ለጠላት ተመቻችተናል። ጠላቶቻችን በሞኝነታችን ካለፈው መማር ባቃተን እንዝህላል
ባሕሪያችን ይስቁብናል፡ ሕዝባችን የጠላቶቻችን ወዳጆች በሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ አዘጋጁለት “የወደቀ ሞራልና ተምበርካኪነት” ቀስ
በቀስ እንደገና በማዝገም ላይ ይገኛል። አዲስ/ፓራዲግም/ ስር ነቀል የሆነ በሂደት ላይ እያዘገመ ያለው የአስተሳሰብ ባሕሪ በሕዝባችን
ላይ ቀርጸናል በማለት፤ “ኤርትራዊ አጀንዳ” እያስተጋቡ፤ ከጥዋት እስከ ማታ፤ ጸሃይ እስክትጠልቅ “በሳብቦታጅ/ሴራ” ስራ ተጠምደው፤ አሳፋሪው የእንዝህላልነትና ታሪክ የመዘገበውን መጠን ያለፈ
ተጠራጣሪ ያለመሆን፤ ገደብ የሌለው ተንኮለኞችን በወንድማማችንትን የማመናችን የዋህነታችን ራሳችንን ተመልሶ የጎዳን፤ ታሪክ እራሱ
እየደገመ በማየት ሂደት ላይ እንገኛለን። ይህ ህልውናችን ከጎዳን አንደኛው የባህሪያችን ዘርፍ ነው።
ቀደም ብዬ ከላይ የገለጽኩዋቸው
ወላጆቻችንን ሲያስጨንቋቸው የነበሩ አሸባሪ የሙሶሎኒ ቦምቦች ወደ ሰው ፍጡርነት ተቀይረው “የሙሶሎኒ ወንበዴዎች” የሚባሉ ፍጡራን ተከስተው፤ባስገራሚ ክስተት ዛሬ ተራብተው ባንዳዊ
ስራ እንዴት እየተካኑበት እንዳሉ በግልጽ እንነጋገር።
የድሮ ባንዳዎች ያልተማሩ ነበሩ።
የዛሬዎቹ በዘመናዊ ትምህርት እጅግ የመጠቁ እና፤ እጅግ በረቀቀ የሕሊና አጣባ የተካኑ አደገኛ ሴረኞች እና ጎጆዎች ናቸው። የድሮ
ባንዳዎች ስንመለከት ተጸጽተው ወደ እናት ገራቸው ተሎ ይመለሱና ጠላትን ይመክቱ ነበር፤ እነኚሆቹ ግን፤ እስከ መጨረሻ ድረስ ጥፋታቸውን
ለማከናወን የሚዘልቁና አልፎም፤ ጠላትን በማሞገስ እና ለጠላት ጥብቅና በመቆም ሽንጣቸው ገትረው በቀጣይነት ያለ ሓፍረት ባደባባይ
ቆመው በግልጽ ይሞግታሉ።
ዛሬ ከሕግ ውጭ “በሙሶሎኒ ወንበዴው”
በኢሳያስ ሻዕቢያ የምትረገጠው ጣሊያን የሰየማትን “ኤርትራ” ተብላ የምትጠራዋ ‘ባሕረ ነጋሽ’ የተባለቺው ሉአላዊ የአገራችን ክፍልና
ሕዝብ፤ ኢሳያስና የመሳሰሉ ተገንጣይ ግልገሎች ጋር ወዳጅነት በማበጀት
የኢትዮጵያን ሉአላዊ እና ሕጋዊ ጥያቄዎቻችንን ለማስረሳትና ለመጉዳት “ቪዥን ኢትዮጵያ” “ፒፕል ቱ ፒፕል” “future of Ethiopian and
Eritrean relationship” ኤርትራ ኢትዮጵያ ወንድማማችነት…..ወዘተ ወዘተ…..
እየተባለ የሳብቨርዢኑ/አፍራሽና ጎጂ ቡድን በሕዝባችን ላይ “ስር
ነቀል የአመለካከት ለውጥ” በማጧጧፍ ላይ ይገኛል።
ይህ ሁሉ ስም እየቀያየሩ በቅጥረኛነት
ከጠላት ጋር ዶልተው የጠላት ቅስቀሳ እያራገቡ፤ ሕብረተሰቡን በማሳሳት የሚዘምቱብን እነማን ናቸው? ለዛሬ የመረጥኩላችሁ ግለሰቦች
የቪዥን ኢትዮጵያ ሰው የሆነው ደ/ር አሰግድ ሀብተውልድ፤ ንአምን ዘለቀ እና ብቅ ጥልቅ የሚለው ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ናቸው።
አሰግድ የተባለው ለእይታችን አዲስ የሆነ ይህ አዲስ ወጣት አገር ውስጥ የ CUD ተቀዋሚ የፖለቲካ ተዋናይ ነየነበረ ነው ይባላል።
ይህ እጅግ አደገኛ ወጣት ልብ ብሎ ላጠናው “በሳብቨርዢኑ” ዘመቻ የተሰለፈ “ሊደርሺፕና/ ቪዥን” (አመራርና ራዕይ) የሚል ኤርትራዊነት
ያጠበቀ ራዕይ የተካነ ሰባኪና ሕገ ወጥ የሆነው የኤርትራን ሉኣላዊነትን የተቀበለ፤ በየፓልቶኩ ተጋብዞ በግልጽ አቋሙን ያስታወቀ፤
“ከሳብቨረሲቮቹና ተምበርካኪነትን” ከሚሰብኩት ቡድኖች ውስጠጥ አንዱ ነው።
አሰግድ ሃብተውልድ ምን እንዳለ
ከመነጋገራችን በፊት ግን መጀመሪያ አብሮ በግምባር ተሰልፎ የሳብቨርሲቩ ዘመቻ መሪ የሆነው አቶ ንአመን ዘለቀ የተባለው የግንቦት7
አመራር አባል፤ በሕዝብቻን አስተሳሰብ ውስጥ ኤርትራዊነት አመለካከት ለማስረጽ፤ ብዙ አርበኞችን አርዶ ለሞት የዳረገ መሰሪው ሻዕቢያን
በማሞገስ የታወቀው ንአመን ዘለቀን እንመለክት።
ኤርትራ ሕጋዊ አገር አይደለችም፡ የሚለው አሮጌ አመለካከት እንቀይራለን ብሎ
የተነሳው ንአመን እና ድርጅቱ፤ ኢሳያስ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ተቆርቋሪ ነው የሚል በሕዝባችን ሕሊና “አዲስ የአመለካካት ለውጥ”
አንደመጣ እንደ አውሮፓ ዘመን አቆጣጠር በ2009 እንዲህ ሲል “የሳብቨርሲቭና ዲሞራላይዘሺን” ዕቅድ ዘርግቶ የማጧጧፍ ዘመቻ ለማካሄድ ሲጀምር ‘አዲስ ራዕይ’ በማለት አንዲህ ሲል ነግሮን ነበር፦
“There is a fundamental change in our thinking
process. There is a shift of attitude among Ethiopians. A positive and
essential change. Fuzziness of thought is giving way to clear thinking.” Neamin Zeleke - The need for
Ethiopians to work with Eritrea “Ethiomedia June 12, 2009
ትርጉም
“በማሰላሰል
ሂደታችን መሰረታዊ ለውጥ አለ። በኢትዮጵያዊያን ዘንድ (አዲስ) የባሕሪ ለውጥ አለ። አስፈላጊ የሆነ። ውዥምብር አመለካካት
ለጠራ አመለካከት ቦታው እየለቀቀለት መጥቷል።” - ይላል የግንቦት7 አመራር አባል አቶ ንአምን ዘለቀ።
እዚህ ላይ ርዕሱን ተመልክቱት።
ኢትዮጵያዊያን ናቸው ከኤርትራኖች ጋር የአብሮ መስራት ፍላጎት አስፈላጊነቱ የፈለጉት እንጂ ኤርትራኖች አይደሉም። አንዲህ ያለ
ስብሰባ ሲአደርጉም አልታዩም። ‘የኢትዮጵያዊያን ከኤርትራኖች ጋር
አብሮ የመስራት አስፈላጊነት’ ለምን? የሚል ጥያቄ ብታቀርቡ በጽሑፉ ላይ እየነገረን ያለው፤-
“ኢትዮጵያን ነጻ ላማውጣት ፤ጸረ ኢትዮጵያ የሆነው የትግሬው የወያኔ ማፊያ መንግስት ለመጣል መፍትሄው፤ ኢትዮጵያዊኖች በዓላማ የተደገፈ
ወዳጅነት ከኤርትራ መንግሥት ጋር በመፍጠር ነው” ይለናል አቶ
ንአምን ዘለቀ። ወዳጅ እያለ ያለው “ሰይጣናዊው ኢሳያስ አፈወርቂን/ሻዕቢያን ነው” (ሻዕቢያን በመቃወም ላይ ያሉትን ኤርትራኖች
እየፈጠረ ያለው ግንኙነት እዚህ ላይ የሚለው ነገር የለውም) ወዳጅነቱ ከሻዕቢያ እንጂ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር አይደለም። ስለዚህም
ከኤርትራ “ሕዝብ” የሚለው እንዲገባችሁ አስምሩበት።
ሰትራተጂክ አላያንስ የሚለው ግብ ደግሞ
አሁን በየአዳራሹ እየሰበሰበ ስለ ኤርትራ “ሉአላዊ እና ሕጋዊ አገርነትን” በመስበክ በኢትዮጵየዊያን ዘንድ እውቅና በመስጠት የተደገፈ ትብብር ነው፤ “ስትራተጂክ
አላያንስ” የሚለው። ለምን? ቢሉ
“A paradigm shift is taking place, a shift
towards the view that in order to liberate Ethiopia from the anti-Ethiopia
ruling Tigrayan mafia, Ethiopians need to make a strategic alliance with the
State of Eritrea. The Rubicon has been crossed.”
ለምን ቢሉ
እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን፤ አዲስ
አስተሳሰብ፤ አዲስ ሞዴል፤ አዲስ ጉዞ፤አዲስ የአሰስተሳሰብ ለውጥ ሂደቱ እየለወጠው ነው። የሳብቨረሲቭ አፍራሽ ሃይላት አዲስ ክስተትና አመለካከት ምንድነው?
“ኢሳያስ አፈወርቂን አና ኤርትራን ሕጋዊ መሪ እና ሕጋዊ አገር” አድርገው ኢትዮጵያዊያን እየተቀበሉት ነው ይለናል። ስለሆነም፤
ቢዚህ ሂደት እና ያስተሳሰብ ለውጥ ከተደረገ ወዳጅነታችን በማጎልበት ወያኔን ማስወገድ አንችላለን። ይላል ንአምን። ኤርትራኖች
ለብዙ ዘመን የጠየቁትም ይህንኑ ነበር።
ምንም አንኳ ዓለም ያወቀው ንትርክ
ቢኖራቸውም። ጥለኞች ቢሆኑም። ሻዕቢያ በመሰረተ ፍላጎቱ ወያኔ እንዲወድቅ አይፈልግም። የወያኔ መውደቅ ‘የኤርትራን ኢ-ሕጋዊ
አገርነትና በአመጽ ባሕርን ነጥቆ የመዝጋት ሂደት” ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ከመጣ ለረዢም ጊዜ የሻዕቢያ አመጽ ሊቀጥል እንደማይችልና ‘ነፃነታቸውንም” ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ክስተት አንደሚከተል
ያውቃሉ። ይህነን ለማለዘብ፤ በሆነ ሃይል ወያኔ ሥልጣኑ ቢለቅ፤ እነ ንአምን “ፓትርዮቲክ/አርበኛዊ’ ጥያቄ የሚያነሱትን
ኢትዮጵያዊያን ለማለዘብና ቦታ ለመዝጋት አንዲጠቅሙት ነው አሁን እነሱን በግምባር ቀደም እረዳችኋለሁ እያለ እነ
ግንቦት 7ም የኤርትራ አገራዊነትን ተቀብለው አርበኞች ቦታ እና ሰሚ እንዲያጡ በመጣር ላይ ያሚገኙት።
ተገንጣይ ቡድኖችንም ለምን እየረዳ እንዳለ የምናውቀው ነው። የኤርትራ ሉአላዊነትን ለማስጠበቅ ይረዳው ዘንድ
ኢትዮጵያ ሰላም እንድታጣ አንድትወጠር ተገንጣዮችና አክራሪ
ሃይላት፤ በዚህም በዚያም እንዲወጥሯት የታቀደ ጥንት ጣሊያኖችና ዓረቦች ያቀዱት አጀንዳ ነው ኢሳያስ ተከትሎ እየሰራልን ያለው።
አዲሱ “የሳብቨርሲቭ” ቡድን አባሎች የሚሉን “ኢሳያስ ወዳጃችን ነው” ይሉናል። “ሰትራተጂክ አላያንስ” የሚሉት ወዳጅነትም
ይህንኑ የኤርትራ አጀንዳ አሁን እንዳለው ሉአላዊነት ‘ሰታተስ-ኮ’
እንዳለ ለማቆየት ነው።
በኛ በኢትዮጵያዊያን በኩል ያለ አቁዋም
ደግሞ ሕጋዊነት ያልተላበሰ፤ ኢትዮጵያዊያንን ያላካተተ ነፃነትና ሬፈረንደም/ምርጫ ፤ሕዘብን ለሁት የከፈለ፤ ቤተሰብ ያራራቀ፤ ኢትዮጵያን
የጎዳና “ኮሎኒያል ትሪቲ/ስምምነት ብለው የተፈራረሙበት ሰነድም ፤በሕግ ፊት እርባና ሌለው የተቃጠለ፤ ጊዜው ያለፈበት የተጣሰ በአመጽ
የተከናወነ እረምጃ ስለነበር ሕጋዊነቱን አንቀበልም ነው እስካሁን እየታገልንበት ያለው መስመር። ይህ መስመር እኛ ከመወለዳችን
በፊትም ቢሆን ወላጆቻቻችንም ታሪካዊ ደም የገበሩበት፤ጉልበትና ጊዜ አፍስሰውበት፤ ወልደው ተዋልደውበት በዓለም መድረክ
የሞገቱበትን የይገባናል ጥያቄአቸውን ያሰመሩበት የሙግት መስመርን ነው ምጉታችን። ልዩነታችን እዚህ ላይ ይጀምራል። ሲፈልጉ ይሂዱ፤ ግን በሉአላዊነታችን ኪሳራ እንዲሆን ግን አንፈቅድም።
ትግሉ ቀጣይ ነው! 40 አመት ግዝተውናል፤ ቅኝ ገዢዎችና ባዕዳን ናቸው ብለው ካሉንም፤ የቅርብ ገዢዎቻቸው ነበርንና እኛ
ያሰመርንላቸው የኮሎኒ/የቅኝ ግዛት ካርታ እና ድምበር ተቀብለው ወደ ሗሊት ዞሮው መሄድ ነው!!!!! የካይሮ ስምምነቱም ያንኑ
ነው የሚያውቀው።
እኛን እያስቸገሩን ያሉት፤ የምናውቃቸው
ተቀናቃኞቻችን ሳይሆኑ፤ የኛ የምንላቸው ወገኖቻችን ልክ ወያኔ ሲያደርገው እንደነበረው ለጠላቶቻችን ጥብቅና መቆማቸው
ጥያቄያችንና በሕብረት የመራመዳችን አስቸጋሪ አድርጎታል። እንደ ምሳሌ ከላይ እየጠቀስኩት ያለውን አቶ ንአምን ዘለቀ “ወያኔን ለማስወገድ” በሚል ሽፋን ልክ ወያኔ እንዳደረገው “የኢትዮጵያን
ሉአላዊነትን በሚጎዳ እና በሚጻረር መልኩ በመቀበል ነው” ይለናል።። እዚህ ላይ ግልጽ አድረጎልናል፤
“if Woyane allied itself with EPLF to promote its
strategic interest, why can’t the current Ethiopian opposition do the same?”
ወያኔ ለጠቀሜታው ሲል ከሻዕቢያ ጋር
ወዳጅነት ካደረገ፤ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይላት በተማሳሳይ መልኩ ልክ ወያኔ እንዳደረገው ከሻዕቢያ ጋር ወዳጅነት ለምን አያደርጉም? ሲል ወያኔ የተከተለው ስታረተጂ “same
interest/strategy” መከተሉ ነውር የለበትም ይለናል አቶ ንአምን ዘለቀ። ንአምን የወያኔን መንገድ በመከተል ግልጽ
አድርጎታል፤ ከሻዕቢያ ጠቀሜታ ለማግኘት፤ በአንጻሩ የሻዕቢያን ጠቀሜታ /ሰተራተጂ/ መጠበቅ የግድ መሆኑን ገልጾ፤ በተጨባጭ
ደግሞ “ይህ አዲስ የፓራዲግም ሽፍት” እያለን ያለው በተግባር “ከአንዳርጋቸው ጽጌ” ጀምሮ እስከ ንአምን ዘለቀ እና ቪዥን
ኢትዮጵያ፤ እንዲሁም በኢሳት/ግንቦት7 ጋዜጠኞች በኩል ግልጽ የሆነ ለኢሳያስ ጥብቅና ቆመው ዘመቻ ሲያካሂዱ በተጨባጭ አይተናል።
ይህ ነው A paradigm shift is taking place የሚለው። “There is a shift of attitude among Ethiopians የሚለው፤ Fuzziness of thought is giving way to clear
thinking.” ወያኔ ከሻዕቢያ
ጓዳ ሲለቅ፤ የወያኔ እግር ተከትለው ሻዕቢያ ጓዳ ስር በመግባት የኤርትራን ኢሕጋዊ አገርንትና በአለም መንግሥታት ሴራ፤ በአሜሪካኖች
የተፈጸመብንን ሴራ እና ውንብድናን አክብረው በመቀበል አስገራሚና አሳፋሪ የሞሶሎኒ ቦምቦች በሕዘባችን ላይ ካደረሱት የአካል
ጥቃት በላይ እነኚህ አዳዲስ “ባንዳ ምሁራን” በመጻኢ የሕዝባችን ላይ እና አሁን ባለው ትውልድ፤ ሕሊና የማይሽር ተጨማሪ ጥቃት
በማድረሰ ላይ ናቸው። ይህ የሕሊና አጠባ ውጤት ደግሞ በየመድረኩና በየፓልቶኩ የሚደመጡት የሕብረተሰቡ አንድበቶች ምንኛ ስር
እየሰደደ እንዳለ ሌላ መረጃ ማምጣት አያሻንም።
የቭዢን ኢትዮጵያ እና የግንቦት 7 አመራር አባል “ንአምን ዘለቀ”
የዋሃንን ሲያታልል “እኛ እና ወያኔ ከሻዕቢያ ጋር የሚያገናኘን ልዩነት አለን”
ሲል እንዲህ ይላልጸ፤-
‘’But the differences
between what the TPLF stood for then and what the Ethiopain patriotic and
democratic forces stand for now is like that of light and darkness”
እኛ አርበኞችና
ዲሞክራት ኢትዮጵያዊያን ሃይሎች ከወያኔ ጋር ያለን ልዩነት የብርሃን እና የጭለማ ያህል ነው” ይላል። በዚህ ማሳሳቻ ምላስ
ያመኑ የዋሃን ብዙ ናቸው። ሃቁ ግን ወያኔም ግንቦት 7ም በእምነት፤በአሰራር እና “በካራክተር” አንድ ናቸው። ወያኔ የተከተላቸው
‘ትሬንዶች” አማላካች ፈለጎች ግንቦት7 ተከትሎአቸዋል።
ወያኔ
የተናገራቸው በአማራው ላይ ያወረደው ዘለፋ የግንቦት 7 መሪዎች በይፋ በስብሰባ ከሻዕቢያ ጋር ሆነው ካሊፎርኒያ ኦክላንድ ከተማ
አዳራሽ ውስጥ ተገኝተው (በወኪላቸው በኤፍሬም ማዴቦ አማካይነት)
አማራውን “ሲዘልፉ” ኢትዮጵያ በኤርትራ ለይ የግዛትም፤የቦታም፤ የወደብም የምንም ጥያቄ የላትም”፤ ኤርትራ ራሷን
የቻለች አገር ነች፡……..ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ 14 ክፍለሃገር…..የሚሉ
ጥቂት ነፍጠኞች በቁጥጠር ስር አድርገንላችኋል፤ ዓሰብ ዓሰብ
የሚሉ ነፍጠኞች…..” በማለት ወያኔዎች ሲናገሩት የነበሩትን አንድ ባንድ ቃላቶቹ፤ ፊደሎቹ፤ ድመፆች ሳይቀሩ/ቶን/ ትክክለኛ
ቅጂውን አስተጋብተዋል። ለዚህም በሻዕቢያ ተሰብሳቢዎች የቀለጠ ጭብጨባ ተለግሶላቸዋል። ወያኔና ሻዕቢያ ቀርጸው ለዓለም
የለጠፉትን ኢ-ሕጋዊ ካርታ የግንቦት 7 መሪዎችም ሆኑ ራዲዮ እና ቲቪአቸው ተቀብለውታል። መሪዎቻቸው በየመጽሐፋቸው የለጠፉትን
ካርታ መመለክቱ በቂ ነው። የብርሃኑ ነጋ ‘ጎህ ሲቀድ’ የመጽሐፍ ሸፋንን ተመልከቱት።
የጭለማ እና
ቀን በርሃን ልዩነት አለን ብለው የሚሉት ልዩነታቸው የቱ ላይ ነው? እስካሁን ድረስ ይህንን
ሊደብቁት አልቻሉም፤ ሊደብቁትም አይቻላቸውም። አውድዮ የተቀዳ፤ በዩቱብ ተቀርጾ የሚገኝ ነው። የሚገርመው ደግሞ President of Eritrea has
made it public that his country has no intention of working against Ethiopia’s
unity. የኤርትራ ፕረዚዳንት የኢትዮጵያ አንድነትን
ለመጻረር ፍላጎት እንደሌለው በሕዝብ ፊት ይፋ አድርጓል” ሲል
ጥብቅና ይቆምለታል።
ምን በወጣው
ብሎ? እራሳቸው ኢትዮጵያዊያን እነ ንአምን እና እነ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ……ኢሳያስን ሕጋዊ ፕረዚዳንት፤ ኤርትራም በሕግ
የጸደቀች ሕጋዊት አገር፤ እያሉ፡ ኤርትራ አሁን የያዘቺው “የኮሎኒያል -ካርታ” ብሎ ወያኔ ያስረከባት ሕጋዊ ያልሆነ መልክኣ መሬት ሕጋዊ
አድርገው በማራገብ፤ በየመድረኩ እየተናገሩለት እያወቀ፤ ምን ሲያሳብደው ብሎ ነው “ስለ ኢትዮጵያ አንድነት በቃሉ
መጥፎ ነገር ሊወጣው የሚችለው?” በግብር ጸረ ኢትዮጵያ የሽምቅ ሃይል ተዋጊዎችን እያሰለጠነ ፤ለግንጠላ የተሰማሩና አማራን
የፈጁ ወንጀለኞችን እየመለመለ፤ እያሰለጠነ እና በፊትም ያሰለጠነ እና እስከ “አዋሳ” ድረስ ተሻግሮ ሠራዊቱ አሰማርቶ የአማራን
ሕዝብ የፈጀ ወንጀለኛው ኢሳያስን ላገራችን አንድነት በጎ አሳቢ ነው ሲሉን ”አዲስ መልአክ” አድረገው በመሳል ሊያጃጅሉን
ሲሞክሩ “ጤና ላለው ሕሊና” እጅግ ያሳምማል።
“ከተሞክሮ
የማይማሩ፤ በወያኔ ብቻ ጠጠር ይወርውር እንጂ፤ ሰይጣንም ቢሆን አንረዳለን” የሚሉ በውጭ ተቃወሚዎች ዘንድ ተቀባይ አግኝተዋል። የህ ግን
ከነባራዊ እውነታው እጅግ የራቀ ያልጠወተ/ያልበሰለ አስተሳሰብ ነው።
ይህ የሕሊና አጠባ አስቀድሞ በነ
ሻለቃ ዳዊት ተሞክሯል።
The Free Ethiopian
Soldiers Movement ከሚለው ጀምሮ ሻለቃው ቢያንስ አራት አምስ ጊዜ የሻዕቢያን ውሸት እያቀፈ ወያኔን ከሻዕቢያ ጋር
ለማደራደር ሙከራ ድርጌአለሁ ይላል። ወያኔ ጥቂት ወራት አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት በሽግግር መንግሥት ተብየው በወያኔ ስርዓት
ውስጥ ሻዕቢያን ለማስገባት “ፕሮፖዛል” ተጽፎ (ፕሮፖዛሉ ምን አንደሚል አይገልጽም) ወያኔ አልቀበልም አለ፡ ይላል ሻለቃው።
አስገራሚው ግን፤ ሻዕቢያ እውነት የግዛት አንድነታችን የማይጻረርና አንድነት ፈላጊ ሆኖ ለመቅረብ “ፈዴረሽን” ሲለው የነበረው
የማጃጃያ የኢሳያስ ተደጋጋሚ ልፍለፋ እውነት ቢኖሮው ኖሮ፤ ፕሮፌሰር አስራት ላይ ሲያሾፍ የነበረውን እስኪ አስታውሱ!
ዛሬ እነ ዳዊት እና እነ ንአምን ስለ ኢሳያስ ላገራችን በጎ
አሳቢነት ተናግሮናል እና እመኑት እያሉ ሕዝባችን ለዳግም ክፍተትና ጥቃት እያዘጋጁት ነው። ዳዊት እንዲህ ይላል፤- EPLF agreed that it will unilaterally implement a cease fire and
participate in the transitional government to negotiate the future
of Eritrea. After this attempt failed, I was again involved in another similar
effort. The EPLF’s position was unchanged.
The EPLF was willing to participate in a
transitional government of Ethiopia. And this was only a few months before TPLF
marched into Addis. We were about to try once again, but the TPLF rejected the
proposal and the attempt was aborted.
Throughout these activities against the Derg,
my colleagues and I worked very closely with the EPLF leadership.
Despite the fact that I was an ardent
supporter of unity, an officer who fought them, a governor who condemned them
at every available opportunity, my relationship with the EPLF leadership was
cordial and constructive.” ይላችኋል!!!!! ሻለቃው!!!
ሻዕቢያና ወያኔ ውስጥ ለውስጥ በነዚህ ኢትዮጵያዊያን (በነ
ዳዊት) እንዴት እየተጫወቱባቸው እንደነበረ ከላይ በቀላሉ ማየት እና ያለ እነ ሻለቃ ዳዊት አደራዳሪነትና
ደላላላነት፤ በኋላ “ሻዕቢያና ወያኔ” መንግሥት
መስርተው እነ ዳዊትን ወደ ጎን አግልለው፤ እንዴት እጅና ጓንቲ ሆነው ቢያንስ ለ7/10 አማታት ኢትዮጵያን እንዴት ይበዝብዟት
እንደነበሩ ሁላችሁም የምታስታውሱት የቅርብ ትውስታ ነው።
እነ ሻለቃ ዳዊት እመሃል ሆነው ወታደሮቹን “በሳብቨርሲቭ እና
የሳብቦርተር” ሚና እየተጫወቱ ስያጃጅሉዋቸው፤ “ሻዕቢያና ወያኔ”
ወታደሩን እመሃል አስገብተው “ሳንድውች” አድረገው ሶቭየቶችን ከቀይ ባሕር አካባቢ ለማስወጣት ሲሉ፤ ከሰማይ በሚላክ
የአሜሪካኖች የስለላ ወታደራዊ ጠቋሚ ፎቶግራፎችንና እንቅስቃሴዎችን በሳተላይት መረጃ ለሁለቱ “የሙሶሎኑ ወንበዴዎች” እየሰጡ ወታደሩን አስበሉት። ካሁን በፊት በራሴው ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ ላይ ሰው ከአስመራ ይዞልኝ
የመጣው “ዕጠቕ” የተባለ የትግርኛ ወታደራዊ የሻዕቢያ መጽሄት “ወዲ ኤፍሬም” (ጀኔራል ኤፍሬም የሚባለው ሻዕቢያ) የሰጠው ቃለ
መጠይቅ ስለ ወታደሮቹ መፈንቅለ መንግስት እና ሻለቃ ዳዊት የሚናገረው ልዩነቱ ነግሮን እንደነበር ታስታውሳላችሁ።
ዛሬም ገና ከዚህ ሳይማሩ የእነ ሻለቃ ጋደኞች ጀግኖች ወታደሮች
ደማቸው፤ጉልበታቸው፤ጥረታቸው ያፈሰሱባትን ኤርትራ የምትባለው
“የደም መሬት” ዛሬ ሻለቃ ዳዊት ሁሉም በመርሳት “ የኤርትራን ኢ-ሕጋዊ አገራዊነት ሕጋዊ ነው ተቀበሉ” በማለት ንአምን
ዘለቀና ግንቦት 7 አንዲሁም መሰል ምሁራኖችን ያካተተ ቡድን ቀደም ብሎ ለማስፋፋት የታጠቁበት “ስር ነቀል አዲስ
ያስተሳሰብ ለውጥ በኢትዮጵያዊያን “ ላይ የሚለው ዘመቻቸው፤ ሻለቃ ዳዊትም ያሰንን በማስረገጥ እንዲህ ብሏል፡-
“Assab is negotiable. Badme is negotiable. As President Isaias stated, “the sky is the limit.” Knowing how
the Eritreans are straightforward and consistent in their words and deeds,
there is no reason to suspect that his statement is one of a political
gimmick.” ……
ዳዊት ምንድነው እዚህ እየነገረን ያለው?
“ኤርትራኖች የሚሉንን አምነን መቀበል
አለበን፤ ምክንያቱም ኤርትራኖች የተናገሩትን በቀጣይነት ተግባራዊ የሚያደርጉ ፊት ለፊት የሚናገሩ ግልፆች ናቸው።” ነው እያለን ያለው። ሻለቃ ዳዊት በተለይ “ፕረዚዳንት” እያለ
የሚጠራው “የሙሶሎኒው ወንበዴውን” ኢሳያስ አፈወርቂን “ባድሜ ሊደራደር ዓሰብ ሊደራደር የሚችል ግልጽ ሰው ነው፤ ቃሉ
አያጥፍም፤ አይዋሽም፤ እያለ ኢትዮጵያየዊያንን ለማጃጃል እየሞከረ ያለው ዳዊት እስኪ ኢሳያስ ማን ነው? እሰኪ ከቃሉ ካንደበቱ
አናዳምጥ፤
በ2010 አልጀዚራ የተባለው ዓለም አቀፍ ቴ/ቪዥን ሚዲያ ስለ
ገደብ የለሹ አገራዊ ወትድርና አገልግሎት ተጠይቆ ሲመልስ “ወታደራዊ አገልግሎት የሚባል የለንም፤ የውሸት ክምር ነው” በማለት
እንዲህ ሲል ‘አሌ’ ይላል፡’ These
are lies,” “it is a pack of
lies,” and “it is lies that do not exist in the real world.”
ሰለ ኤርትራ ስደተኞች ወደ እየ ዓለማቱ መጉረፍ ሲጠየቅ፤
‘ከኤርትራ የሚሰደድ ስደተኛ የሚባል የለንም” “ይህ ለኔ አዲስ ዜና ነው”
ይላል። አንዲህ ይላል፡=
“this was news to me,” “people who said this were “crazy” and “out of
their minds.” “Slander against Eritrea.” “Anyone can leave this country
anytime,” ““fantasy,” “lies,” “imagination,”
“insane,” “boring” and a “joke.”
ሲል ስደተኛ የሚባል የለም ጥያቄአችሁ
የውሸት እና ግምት ነው፤ አለፍ ሲለም “ቀልድ ነው” ሲል በጋዜጠኛዋ ላይ ሲያሾፍ አድምጣችኋል።
ስለ ጋዜጠኞች መታሰርም “የታሰሩ ጋዜጠኞች አሉ፤ መች ነው ወደ ፍርድ የሚቀርቡት? ብላ ጄን ስትጠይቀው
እንዲህ ሲል ይዋሻል፦
“these
are lies,” ይሄ
ሓሰት ነው! ይልና፤- የአልጄዚራ ጋዜጠኛዋን ተመልሶ በመወንጀል እንዲህ ሲል ይወነጅላታል
“…using these lies to destabilize this region to serve
someone’s agenda.”
በማለት
እጅግ በጣም አስገራሚ እና ደረቅ ውሸት ሲወሽ ሻለቃ ዳዊት አወድሶ ለአወዳሽ የሰጠውን የማይዋሸው ኢሳያስ እና የኤርትራዊያን
ግልፅ እና የማይዋሽ በሕሪያቸው በዓለም ፊት ሲዋሹ ግን መረጃው ዳዊት ከሚነዛው “የሳብቨርሲቭ ፕሮፓጋንዳ” ቅስቀሳ የተለየ ነው።
እንዲህ ያለው ውሸታም እና እስስት ባሕሪያቸውን
ስለ ኢትዮጵያ የሚናገሩት ንግግር በሙሉ እመንዋቸው። ሲል አስገራሚ “ቃለ አጋኖ” እየቀጠሉ ለጊዜየዊ ስም እና ዝና (በባንዳነት
ዝና እየተጠቀሱ፤ ምን አይነት ዝና አንደሚገኝበት ባይገባኝም) ምሁራኖቻችን
እና አንዳንድ ወታደራዊ ከፍተኛ መከንኖች የነበሩ የሕዝባችን ጠላቶች የሆኑትን “እውነተኞች ናቸው እያሉ በማሞካሸት” በጎጂ ስራ
ላይ ተጠምደዋል። እነዚህ “የተበከሉ ምሁራን” (ኮንታሚኔትድ
ኢሊት) ለሕብረተሰብ ጠንቅ ናቸውና ከቶ ካለፈው ታሪክ የሚማሩ
አይደሉም።
በመጨረሻ ላይ ዳዊት ይህ ሁሉ የጠላት
ሙገሳ፤ሀቀኛነት እና ፊት ለፊት ግልጽነት ወዘተ…. ወዘተ….ፕሮፓጋንዳው ከዘረጋ በኋላ “Eritrea is now independent. That reality cannot be
reversed by force” ሲል አዲስ ለውጥ በኢትዮጵያዊያን በስር ነቀልነት
እየጎለበተ ፤ለውዥምብራሞቹ ግልፅ አስታሰቦች ለያዙ ቦታ እየለቀቁ ነው፤ ያለውን የግንቦት 7ቱ የንአምን ዘለቀ “የዲሞራላይዘሽኑ/አፍራሽ”
ዘመቻ “ሻለቃ ዳዊትም “ኤርትራ አሁን ነፃ አገር ናት፤ ሀቁ ይሄ ነው፤ በጉልበትም የሚቀለበስ አይደለም!” ብሏል።
ነብሳቸው ትማር ኢትዮጵያዊው ትግሬው
ዓድዋዊው በንጉሱ ዘመን አገራቸውን በመኒስቴር ማዕረግ ያገለገሉ የሃርቫርድ ምሁሩ “አቶ በላይ አባይ” ከሞታቸው በፊት
“ኢንተርናሽናል ትግራያን ሶሊዳሪቲ” ሲባል በነበረው ተቃዋሚ ትግሬዎች ስለ ኤርትራና ሉኣላዊ ጉዳይ ለመነጋጋር በጠሩት ስበሰባ
ላይ ፕሮፌሰር ተኰላ ሐጎስና አቶ በላይ አባይ ተጋብዘው ንግግር አድርገው ነበር። አቶ በላይ ዓባይ የተናገሩት ንግግር ሌላ
ቀን በታይፕ ጽፌ አቀርብላኋችለሁ፤-
ያኔ ምንድ ነው ያሉት፦
“ኤርትራኖች ከፈለጉ መሄድ ይችላሉ፤
ሲሄዱ ግን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትን በሚጎዳ መልኩ አንዲት “ቅንጣት ኢንች” የምታክልም ብትሆን አፍርሰው አይሄዱም። እኛም
መጪው ትውልድም መፍቀድ የለበትም።” (በላይ ዓባይ)
አዎን ዳዊት እና የመሳሰሉ የሳብቨርሲቩ ቡድን
“ጉልበት” አይሰራም ሲሉ ይዋሻሉ። ኤርትራኖች የነገሩን
ኢትዮጵያዊያን ኤርትራንን ከእጃቸው ነጥቀን የባሕር በር አንዲያጡ ያደረግናቸው “በጉልበታችን ነው” ብለውናል (ኢሳያሰን ነጻነታችን በጉልበት እንጂ
‘በብሩር ሳህን’/ሲልቨር ፕሌት ተጠቅልሎ አልተሰጠንም ብሎናል)። ዳዊት እዚህ ላይ እንዲረዳልን የምንፈልገው፤ ወደ ኮሎኒያሊዝም እና የካርታ ትንተና ሳልገባ፤
ኤርትራ በሕግ አልሄደችም፤ ፍች ከተባለም ሕጋዊ ፍች አልተደረገም፤ የተከለለ ካርታ የለም፤ ኢትዮጵያን ወክሎ
የተደራደረ መንግሥት የለም፡ (ሁለቱ ወያኔ እና የሻዕቢያ ተደራዳሪዎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው፤ከሳሽና ሰሚ ቢገኝ፤ ዓለም
ዓቀፍ ሕጉም ይጻረራቸዋል።)። ሕገ ወጥ አርምጃውን ለማስቆም፤ ሁለት ነገሮች መደረግ አለባቸው። አንዱ ሕጋዊ አርምጃ ነው። ያ
ካልሰራ “ጉልበት” ነው። ጉልበት ሕግን ያስከብራል። ይህ የትግሬው የጌታቸው ረዳ ቃል ነው፤ ክቡር ሻለቃ!
አዲስ “የቪዥን ኢትዮጵያ” ወጠጤው ወጣት ደ/ር አሰግድ አብተወልድ የተባለው ደግሞ እንዲህ ሲል የኤርትራኖችን አገራዊነትና
ቅስቀሳ ደጋፊዎች በሚበዙበት በግንቦት 7 የፓልቶክ ክፍል ውስጥ ዘነበ በተባለ የግንቦት 7 አባል እና የክፍሉ
አዘጋጅ አሰግድ ሃብተወልድን ‘ቃለ መጠይቅ ለማድረግ’ በእንግዳነት ቀርቦ ስለ ኤርትራ ሕጋዊነት ሸንጡን ገትሮ የተበደለቺውን አገራችን
አንገት ላመስደፋት እንዲህ ሲል ስለ ኤርትራኖች ጥብቅናው በማያወላዳ ንግግር ግልጽ አድርጎልናል።
እንዲህ ይላል፤-
“ የኛ “ስኮፕ” ፒፕል ቱ ፒፕል
people to people ነው፡ በሁለቱም አገሮች (ኤትራ/ኢትዮጵያ)
ግንኙነት ምንድነው መሆን ያለበት? ፖለቲካ ሳይዱ side ሳናነሳ ምንድ ነው ሪለሽን ሽፑ /relationship መሆን ያለበት?
ኤርትራኖች በራሳቸው ምርጫ ኢንደፔንደንት/independent ናቸው፤
የራሳቸው ኢንድፔንደንት/ independent አገር አላቸው፤ ዓለም ሬኮግናይዝድ/recognized ያደረገውን አገር ለመጨፍለቅ ወይንም በተለይ እነሱ (ኤርትራኖች) በማያምኑበት መልኩ ወደ ኋላ እንመለስ (አንድ አንሁን)ብሎ
ዓይነት ሪለሸን ሺፕ/relationship የመፈለግ ነገር ቦታ የለውም።
እኛ የምናደርገው ከምንራራቅ ይልቅ ብንቀራረብ ፤አብረን ‘commen” በሚያደርገን ዙርያ ላይ ብንሰራ የሚል ነው።ኮነፈረንሱ
conference ላይ የተካፈሉት Professor/ፕሮፌሰርመስፍንም፤
ዶ/ር ካሳ ከበደም ሌሎችም አንስተውታል። “ኤርትራ ራሷን የቻለች ሉዓላዊት አገር ናት”
ብለዋል። የሚደረገው ግንኙነት እንደገና ሁለቱም አገሮች በጉልበት አምጥቶ
የማጨፍለቅ ዓይነት ኢንቴግሬሽን integration አይደለም
እያወራን ያለነው።” እኛ እያወራን ያለነው “ፒፕል ቱ ፒፕል ነው/ people to people ” ዶ/ አሰግድ
ሃብተወልድ (ቪዥን ኢትዮጵያ መስራች አባል)።
የህ ምንን ያመላክታል? የጉልበት
ብቻ ሳይሆን የሕሊና ተምበርካኪነትና የሞራል ተሸናፊነትን መልእክትነትን የያዘ መሰመር መሆኑን ያሳያል! ኢትዮጵያን ለማፍረስ ኢትዮጵያ
ምሁራን ብዙዎቹ የጠላትን ፕሮፓጋንዳ ተቀብለው፤ እራሳቸው ሞራላቸው ላሽቆ፤ ጀግናው ህዝባችን ሞራሉ እንዲላሽቅ እና እጅ ሰጥቶ የዓረቦችና
የአክራሪ እስላሞች ስትራተጂ ከጥንት የቆየ ያልበረደ ዒላማ ጥቃት አንዲፈጸምባት በቀጥታም በተዘዋዋሪም አስተዋጽኦ የሚያደርግ መስመር
ነው። አማራርና ራዕይ/ ሊደርሽፕ እና ቪዥን’ በሚለው በተመረቀበት ሙያው ሕዝባችንን እያስተማረ ያለው ይህ “ተምበርካኪ ወጣት”
፤ ተምበርካኪ ራዕይ የሚከተል የሊሂቅ ቡድን፤ በሕዝባችን አስተሳሰብ ሕሊና “እጅ ሰጪነትን” የሚቀርጽ፤ ተአማኒነት የጎደለው ወጣት
ነው።
ኤርትራ ሉዓላዊ ያደረጋት ማን ነው?
አሰግድ ሊመልሰው ይችላል? መለስ ዜናዊ/ወያኔ!!!!!!! አልፎም ሲአይኤ!!!!!!!!! ቀጥሎም “ዩ ኤን’
የተባለ የአራዊት መንጋ መሰብሰቢያ የሆነው ሰረንገዲ” (የፕሮፌሰር ተኮላ ሐጎስ አገላለጽ ልዋስ እና) ነው። እነኚህ
ሁሉ የበሰበሰ፤የተሻረ፤ በሕግ ፊት ተቀባይነት የሌለው፤ የኮሎኒ ካርታ ተጠቅመው፤ ኢትዮጵያ ያለ ተወካይና ጠበቃ አስቀርተው “ኢትዮጵያን
የባሕር ወደብ እንዳይኖራት” ሴራ አድርገው “የተዋለዱትና አንድ ጎሳ ለሁለት ከፍለው/አንዱ ወደ ኢትዮጵያ አንዱ ወደ ኤርትራ ያለምንም
ሕጋዊ ሬፈረንደም አስገድደው “ባርነት ወይስ ነፃነት” ምረጥ ተብሎ የተፈጸመ የአመጽ ነፃነት ነው ሉዓላዊ አገር ነው ተቀበሉት
ብለው ሕዘባችንን እየሰበኩት ያሉት።
አስገራሚው እና አሳዛኙ ደግሞ፤
አሰግድ ሃብተውልድ የተባለው ይህ ወጣት አገር ውስጥ እያለ የCUD አባል አንደነበረ ነው የሰማሁት። እራሱም የየትኛው ፓርቲ አባል
እንደነበረ ባይናገርም እንደነበረ እና በቅርብ ጊዜ እንደመጣ ይናገራል። CUD የተባለው በእነ ልደቱ እና በመሳሰሉ ተቃዋሚዎች በጠቅላላ
5 ተቃዋሚዎች የአልጀሪሱ ሰምምነት የሚባለው ኢትዮጵያን የጎዳ የሙሰሎኒ ወንበዴዎች ስብሰብና ፌርማ በመቃወም፤ “ከሦስት መቶ ሺሕ
እስከ ግማሽ ሚሊዮን” ሕዝብ በላይ አስቸኳይ የተቃዉሞ ፌርማ አሰባስበው “ወደ የተባበሩት መንግሥታት” የተቃውሞ ፌርማ/ፔቲሽን/
አንደተላከ ሁላችሁም የምታስታውሱት የቅርብ ጊዜ ታሪካዊ ትግል ነው።
የዛሬ ቡድኖች ያ ተቃውሞ ከንቱ
አንዲቀር እየጣሩ ናቸው። ፌርማው እና ተቃውሞ ድምፅ በከንቱ የተፈረመና የተጠራ ጥሪ አይደለም። የኛ የምንለው መንግሥት ሲመጣ በሕግ
ቀስቅሰን በአገራችን ላይ የተፈጸመው ደባ እንደገና ማሕደሩ እንዲታይ፤ በሕግ አንዲቀሰቀስ እና ጉዳዩ እንደገና ለፍርድ እንዲቀርብ
ለማድረግ የተደረገ የሕግ ባለሞያዎች ያጠናቀሩት የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያዊያን አቤቱታ ነው። ያ አልሆን ሲል ወደ ጉልበት ይገባል።
ጉልበት እምቢተኛ ተቀናቃኝን ወደ ጠረጴዛ እንዲመጣ የሚያስገድድ የመጨረሻ ማስገደጃ መሳሪያ ነው። ነው እያልን ያለነው።
ኢሳያስ ከባድሜ ውጣ ተብሎ “ከባድመ
ወጣሁ ማለት ፀሐይ በምስራቅ ትጠልቃለች” ማለት ነው ሲል ያሾፈበትን ንግግሩ፤ “ቁጭትና ውስጠዊ ንዴት እና ቂም ይዞ የነበረው ኢትዮጵያዊ
እልክ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ከሶማሌ ሳይቀር ጫፍ እስከ ጫፍ ዘምቶ “ግማሽ ኤርትራ መሬት ጥሶ በመቆጣጠር” ገብቶ፤ ኢሳያስ በፍርሃት
ተንቀጥቅጦ፤ የመረጃ ሰነዶችን ከአስመራ ወደ ናቅፋ በረሃ እንዲጋዝ አዘጋጅቶ፤ ጊዜ በማጣቱ አንዳንዳንድ ፀጥታዊና ወታደራዊ ምስጢር
አዘል ማሕደሮችን ተሎ አንዲቃጠል አድርጎ፤ ‘ወደ ፕረዚዳንት ክሊንትን ስልክ ደውሎ እባካችሁ ጦሩነቱን አስቁሙልኝ እሺ እፈረምላሁ”
ሲል ሊፈረጥጥ ሲዘጋጅ፤ ወዳጁ “መለስ ዜናዊ” ሳይታሰብ ድንገት ጦርነቱን አስቆመለትና ኢሳያስን ከፍርጣጣ ገላግሎ ትንፋሽ ዘራለት።
ጉልበት ይህን ያህል ታምር አለው። ጉልበት! ጉልበት! ጉልበት! ተቀናቃኝን ወደ ሕግ አንዲመጣ ያስገድዳል፤ጉልበት!
ዛሬ እነ አሰግድ እና የመሳሰሉ
አዳዲስ የሳብቨርሲቭ ዘመቻ አስፋፊዎች፤ ሕጋዊ አገር ለመጨፍለቅ፤ ላለመጨፍለቅ እያሉ ጥብቅና ቆመው አገራቸውን ከድተው፤
ገራገሩን በማሞኘት ላይ ይገኛሉ። ኢሳያስ እንዳለው “እኛ እስካወቅነው ድረስ የኤርትራ ፋይል ላንዴና ለመጨረሻ የተዘጋ አጀንዳ ነው፡ ለወይይት የሚቀርብ አይደለም” አንዳለው ሳይሆን
ወዶ ሳይወድ ተገድዶ “ፀሓይዋ በምዕራብ እንጂ በምስራቅ እንደማትጠልቅ እንዲያምን ይገደዳል።” የኢትዮጵያ
አርበኞች የጊዜ ጉዳይ አንጂ “ፀሐያቸው ትወጣለች! የባንዳዎችም ፀሐይም
አብራ ከባንዳዎች ጋር ትጠልቃለች። አመሰግናለሁ፡
ጌታቸው ረዳ (Editor
Ethiopian Semay) getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment