ግንቦት 7 “የቀድሞ
የኢትዮጵያ መከላከያ
ጦር ሃይሎች ሲቪኽ ማሕበርን” ለሻቢያ ገጸበረከት ለማቅረብ ያደረገው ሙከራ
ጌታቸው ረዳ
(የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)
ይህ ፎቶግራፍ ሻምበል አሸብር ገብሬ ናቸው። ሻምበል አሸብር ገብሬ በስደት በውጭ አገር የሚገኘው “የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ዓለም አቀፍ ማሕበር” ሊቀመንበር ናቸው።
ስለ እኚሁ ጀግና መኮንን የሚመሩት ማሕበር ከመተቸቴ በፊት፤ ስለ ግንቦት 7 ጋዜጠኞች ለመግቢያ አንድ ልብል።
መቸም ግንቦት 7 እና ኢሳት የተባለው
የግንቦት 7 ልሳን በተነሳ ቁጥር “ወያኔ” እና “ወይን” / “ኢሕአዴግ” እና “ኢቲቪ” በተመሳሰለ መልካቸው ያስታውሱናል። ከሞላ
ጐደል በግብርም፤በሰላቢነት፤በርካሽ ፕሮፓጋንዳ አሰራጪነት፤በውሸት እና ለኢትዮጵያ ጠላት ለኤርትራው ሻዕቢያ በቅጥረኛነት ማጎብደድ
እና ማደር ኢሳት እና ግንቦት 7 የወያኔ ባሕሪ “ከች” አድርገው ቀድተው በግብር እያሳዩን ነው።
2ቱ አድርባይ ጋዜጠኞቹን ሻዕቢያ
ወደ እሚቆጣጠረው “መረብ ምላሽ” ልኮ፤ ሲመለሱ ባልመጠቀ ሕሊና ለሚጓዙ
ተከታዮቻቸው ይዘውላቸው የመጡትን በዓይነቱ እጅግ በጣም የወረደ ርካሽ “ሻዕቢያዊ ፕሮፓጋንዳ” ፤ በየአገሩ በመዞር ገንዘብ እያስከፈሉ
በየአዳራሹ እየሰበሰቡ ስለ ኢሳያስ “ያለጠባቂ መጓዝ” እና “መናኛ ልብስ መልበስ” የሰሩትን
(“ሲምፕሊሲቲ” ይሉታል ኤርትራኖቹ በኢሳያስ ሲያላግጡ፤ ስለዚህ በሚቀጥለው ሳምንት ርዕሴ የኢሳያስ “ሲምፕሊሲቲ”
፤የውሸት መሆኑን እና ትክክለኛ ታሪኩን ግን በቃለ መጠይቅ ከአንድ ኤርትራዊ የእህቱ ልጅ እና የሻዕቢያ ታጋይ የነበረ ሰው አቀርብላችሗለሁ።
ያኔ እውነታው ታያላችሁ።)
ስለ ኢሳያስ
ልብ ወለድ ሥራ ፤ “ለአማርኛ ተናጋሪ አምቼ ሻዕቢያ ኤርትራኖች እና ኢትዮጵያዊያን ጌኞዎቻቸውን” በየአደራሹ ጠርተው ፤ ‘ዳዊት’ የተባለው የሻዕቢያ ሻለቃ”፤ “በትንሽ የእግር ጉዞ ምክንያት፤ቆስሎ፤
ውሃ የቋጠረውን የግንቦት 7ቱ ጋዜጠኛው የመሳይ መኰንን እግር” “ውሃ አሙቆ” “ ጐምበስ ብሎ” “እግሩን ለማጠብ” ያደረገውን እጅግ
አስገራሚው ሻዕቢያ “የተካነበት ትያትር” በአድናቆት ሲናገሩ “የሻዕቢያ ወታደራዊ መኰንኖች” የደከመን እና የቆሰለን የመንገደኛን
እግር በሞቀ ውሃ የሚያጥቡ “ክርስቶሳዊያን መላዕክት” እንጂ ሰውን የሚገድሉ፤ የሚገርፉ እንዳልሆኑ እና በዚህም የሻዕቢያን ስም
ጥላሸት በመቀባት የተሰማራነው “ውጭ/ዲያስፖራ/ ያለነው መሆናችንን ሳያፍሩ የተከራከሩበትን አሳፋሪ ጉዳይ በሚቀጥለው ሳምንታዊ ትችቴ
እመለስበታለሁ። በሚቀጥለው ጉብኝታቸውም እነ መሳይ እራት ሲበሉ ኢሳያስ አፈወርቂ ድንኳኑ ውስጥ “ኩራዝ መብራት” ይዞ ፊቱን ወደ
ግድግዳ አዙሮ ቆሞ እራት እንዳበላቸው ይነግሩን ይሆናል! “የሰው ልጅ” ህይወት ከፍ ያለ “ክብር” በሚሰጥበት “በቅዱሳኖቹ በኤርትራኖቹ”
ምድር “ሁሉም ይቻላል”!
ለዛሬ ግን “ግንቦት 7 የቀድሞ
የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ሃይሎች ሲቪኽ ማሕበር ለሻቢያ ገጸበረከት ለማቅረብ ያደረገውን ሙከራ” እንመልከት። ታሪኩን ከባለቤቶቹ
አንደበት ለማድመጥ http://formerethiopianarmedforceworldwide.org/
ይጐብኙ። አድራሻቸውንም ለማግኘት ለምትፈልጉ፤ Former Ethiopian Armed Forces Worldwide
Organization P.O.Box 703913 , Dallas ,TX 75370-3913 Phone (469)432 2435 ነው።
እኔ ድረገጹን ያወቅኩት በጣም በቅርብ
ነው። ለዚህም ምክንያት፤ የተቃዋሚ ድረገፆች የሚባሉት አብዛኛዎቹ እንደዚህ ያሉትን ኢትዮጵያዊ የጀግኖቻችንን ድረገጾች እና ታሪኮች
ለሚያነቡ ደምበኞቻቸው ድረገፆቻቸውን “ሊንክ” (መስኮት) ከማበጀት ይልቅ፤ እንደ እነ “ኦነግ/ኦብነግ/ሻዕቢያ/…….) እና የመሳሰሉ
ነብሰገዳይ ሽብርተኞች እና የተገንጣይ ድርጅቶች ፤አልፎም መናኛ የሆኑ የግለሰብ ብሎጎችን “በጓደኝነት ሰበብ” “ሊንክ” በማበጀት፤ ተውጠው ሳይታወቁ አንዲቀሩ በመደረጉ ምክንያት ነው።
ይህ ደግሞ አውቀው ካደረጉት ‘ከባድ ወንጀል እና የጠላት ተባባሪነትን’ ያሳያል። ከዚህ ጽሁፍ ወዲህ ኢትዮጵያዊያን ድረገፆች በድረገፆቻቸው
ሊንክ እንዲአደርጉላቸው ግዴታቸው ነው። ባያደርጉት ግን ያው ሆን ብለው ልሳናቸው እንዳይሰራጭ የሚጠቅሙት
“ለሚተባበሩዋቸው ጠላቶቻችን ብቻ ነው ማለት ነው” ። በዚህ ትችት በስፋት አልሄድበትም። ለወደፊቱ እምለስበት ይሆናል።
አላማዬ፤ ድረገጹ ታፍኖ በመቆየቱ፤ ለመስተዋወቅ ነው። ስለሆነም የሚከተለው ሃተታ ባጭሩ አብረን እንመርምር።
ከላይ ከመግቢያ የተመለከተው፤ ፎቶግራፍ ሻምበል አሸብር “የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ዓለም አቀፍ ማሕበር” ሊቀመንበር፤ ስለ
ማሕበሩ የሚሉት ነገር አላቸው።ሻምበሉ፤ ግንቦት 7 የተባለው የሻዕቢያ ተላላኪ፤ ጥቂት አድርባይ የሠራዊቱ አሳፋሪ ግለሰቦችን አስሰርጾ
ወደ ድርጅቱ በማስገባት፤ ድርጅቱ የሻዕቢያ ተልዕኮ ፈጻሚ እንዲሆን፤ ድርጅቱ ለመጥለፍ የሞከሩትን ግለሰቦችን በመጋፈጥ፤ ድርጅቱ
ኢትዮጵያዊ “የስቪክ ማሕበር” ህልውናውን በኩራት ጠብቆ እንዲጓዝ
ካደረጉት ጀግኖች አንዱ ናቸው።
በሻምበሉ አንደበት ድረጅቱ በግንቦት 7 በኩል ለሻዕቢያ መገልገያ እንዲሆን የተደረገው የከሸፈው ሙከራ
ለማድመጥ ከአንድነት ኢትዮጵያ ሲዊዲን ራዲዮ ጋር ያደረጉት በ4 ተከታታይ ክፍለ መጠይቅ ፣የድርጅቱ ዓላማ ምንድነው? ለምን ለሁለት ተከፈላችሁ የሚባለውስ ውዥምብር ከየት የመጣ ነው? በተጨማሪም ለምን ለወያኔና ለሻቢያ የልመና ደብዳቤ ላካችሁ? ተብለው የደብዳቤውን በጎ ተልዕኮ እና መላክ የነበረበት ታሪካዊ ደብዳቤ ለማንኳሰስ ለምን
ተጣምሞ ሊቀርብ አንደተፈለገ ያብራራሉ።
ቪ ኦ ኤ” የተባለው የአማርኛ ክፍል ራዲዮንም፤ የሚያስመሰግን ሥራ የሚሠራ መሆኑን
ባይካድም፤ አንዳንድ ጊዜ “ግራ በሚያጋባ ባሕሪ” አድልዎ በማድረግ ፤ ድርጅቱን ለሻዕቢያ ስጦታ ሊያበረክቱ የሞከሩትን ገለሰቦችን
ሲጋብዝ፤ በሌላ በኩል በእነ ሻምበል አሸብር ግብሬ ብርታት በተደረገው ትግል ድርጅቱን ጠብቀው የቆሙትን አባሎችን ያላቸውን እይታ፤መልስ እና ልዩነት አሰተያየታቸው ለሕዝብ አንዲያቀርቡ
ከማስተናገድ ይልቅ “ላንድ ወገንተኛ ሆኖ” የነ ሻምበል አሸብርን ወገን ሳይጋብዝ ለምን እንደቀረ ቅሬታቸውን በሰጡት በስዊድን የኢትዮጵያ
አንድነት ራዲዮ ታደምጣላችሁ።
ይህ ጽሁፍ ለቪ ኦ ኤ አማርኛው ክፍለ ጊዜ ሓላፊው ለአቶ ንጉሴ/ትዝታ/አዲሱ ……ለመሳሰሉ ሁኔታው እንዲያወቁትና እነዚህንም ጋብዘው ለማነጋገር ለምን ዕድሉ
እንደነፈጓቸው እኛም በእነ ሻምበል አሸብር ገብሬ ጐን የቆምን የማሕበረሰብ ወገኖች ፤ ምክንያቱን እንዲነግሩን ይህ ትችት እንደምልክላቸው
በዚህ አጋጣሚ አንባቢዎቼን ልግልጽ እወዳለሁ።
አብሮ ከዚህ ጋር ሁላችንም መዘንጋት የሌለብን፤ ሻምበበል አሸብር እንዳሉት ኢትዮጵያን
ለማዳን ሲሉ ከመረብ ምላሽ ወዲያ እና በትግራይ ውስጥ ከተገንጣይ እና አስገንጣይ ቡድኖች ጋር ሲዋደቁ አካላቸውን አጥተው ስንኩላን
ሆነው ለመስራት ሳይችሉ ቀርተው የትም ተጥለው ያለ አስታዋሽ የቀሩ እና ፤ ወያኔ እና ሻዕቢያ እንዲሁም ኦነግ በአንድነት በቀየሱት
ጸረ ኢትዮጵያ ሴራ “የሚከላከልላትን እና ቤዛ የሚሄድላትን የቀድሞው ጦር ሃይሎችን በማፍረስ” ያለ ጥሮታና መጠለያ ከነ ቤተሰቦቻቸው
የትም ተጥለው መገኘታቸው ሃቅ ነው።
ለምሳሌ ከዚህ በታች የምታየው ፎቶ በልመና የተሰማሩት
የቀድሞ ወታደር ኰሎኔል ካሳሁን ትርፌ የመሳሰሉ
በየበረንዳው ወቀድቀው የቀሩት
ተራ ወታደሮች እና ከ’ ነ ማዕረጋቸው ወደ ልመና የተሰማሩትን ሕዝብን አስተባብሮ እሮሮአቸውን ለማስተጋባት እና ለመርዳት የተደራጀ
ድርጅት መሆኑን ሻምበል አሸብር ገብሬ በቃለ መጠይቃቸው ታደምጣላችሁ።
ከላይ የሚታዩት ኮሎኔል ‘በረንዳ አዳሪ ሆነው ሕሊናቸው ተቃውሶ በነበሩበት ጊዜ’ በተራድኦ
ድርጅት ዕርዳታ ተደርጐላቸው መጠናኛ የሕሊና መቋቋም ካደረጉ በሗላ ፤ አንድ ጋዜጠኛ ስለ ሁኔታቸው እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል።
“እንዴት ነዎት? ስላቸው ‹‹ወንድሜ አሁን ደህና ነኝ፤ አእምሮዬም በጣም ደህና ነው፡፡ እንደበፊቱ ወደ ንባብና ትርጉም ሥራዬ እየገባሁ ነው›› በማለት እያነበቡት ያለውንና በእጃቸው የያዙትን ‹‹Among the Russians›› የሚል መጽሐፍ አሳዩኝ፡፡ እንዴት ያለ ግሩም መጽሐፍ መሰለህ በሚል የአድናቆት ቃል እያነበቡት ስላለው መጽሐፍም አወጉኝ፡፡
ባለፈው ሳምንት ‹‹አፍሪካን ኔግሮስ›› የሚል አንዲት ከአፍሪካ በባርነት ተሸጠው ከሄዱ ቤተሰብ የተወለደች አፍሪካ አሜሪካዊት ሴት የሕይወት ታሪኳን የተረከችበትን መጽሐፍ በተመስጦ አንብበው እንደጨረሱትም ነገሩኝ፡፡
‹‹ኮሎኔል ካሳሁን በቅርቡ በራሴና በመቄዶንያ ድርጅት ስም የሚታተም መጽሐፍ ለመተረጎም ዝግጅት ላይ ነኝ፡፡ አንዳንድ ነገሮችን እንድታግዘኝ ስለምፈልግ እንዳትጠፋ›› አሉኝ ፈገግ እያሉ፡ አልጠፋም ኮሎኔል ብቅ እላለኹ ብያቸው ተጨባብጠን ተለያየን፡፡ ኮሎኔል ወደፊት የሕይወት ታሪካቸውን ለመጻፍ እንደሚፈልጉና ለዚህም የሌሎች ኢትዮጵያን ወገኖቻቸውን ድጋፍና እገዛ እንደሚፈልጉ ገልጸውልኛል፡፡ ወደፊት ኮሎኔል ካሳሁን የሕይወት ታሪካቸውን የሚተርክ መጽሐፍ ጽፈው እንደሚያስነብቡን አንዳንች እርግጠኝነት በልቤ ውስጥ እየተሰማኝ ተሰናበትኳቸው፡፡”
ሙሉውን ታሪክ ለማንበብ “ፍቅር በፍቅር” ያዘጋጀው “የጎዳናው ተዳዳሪ የወታደራዊ መረጃ
ኮሎኔል” በ04/30/2013 በፈረንጅ Ethiopiansemay.blogspot.com (Ethiopian semay) እንደገና
የታተመውን ታሪክ ለማንበብ ጉጉል ላይ ርዕሱን ብታስገቡ ታሪኩን ታገኙታላችሁ።የታሪኩ አዘጋጅ ኢመይልም ታገኙታላችሁ።
ይህንን የዚህ ጀማሪ ድርጅት በጐ ዓላማ እንዳይሳካ የግንቦት 7 መረዎች መሰሪ እና
ለድርጅቱ ያደሩ ጥቂት የቀድሞ ጦር አባል ወታደሮች ለሻዕቢያና ለወያኔ የማደር ደካማ ባሕሪያቸውን እንዳይደግሙብን፤ ሕዝቡ ዛሬም
ነቅቶ ማስተዋል አለበት።
የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሃይል አባላት አሁን ባለው ሥርዓት የተወሰነ ሴራ እና
አረሜናዊ ውሳኔ በልመና ተሰማርተው ምን ያህል ስቃይ እና ውርደት በህይወታቸው አዲስ አበባ ውስጥ መንገድ ዳር ተጥለው ሕዝቡ እያየ
አንዳሚያልፋቸው የቆጫቸው እነ ሻምበል አሸብር ገብሬ ተረባርበው የወደቁ ጀግኖቻችን በሚመለከት ምን መደርግ አለበት በሚል መፍትሔ
ለማፈላለግ ሲሞክሩ ነው፤ ባንዳው የግንቦት 7 ድርጅት ድርጅቱን ለመጥለፍ የሞከረው። እነዚህ የወደቁ ጀግኖቻችን ምን ብናደርግ ልንደርስላቸው
ይገባል? የሚል ጥያቄ አንገብጋቤ ነው። አሁንም የተጫኑን ፈተናዎች በርካታዎች ናቸው።
በሚቆጭ ሁኔታ ግን፤ ወያኔዎች ለወደቁ አካለ ስነኩላኖቻቸው እና የተሰው ሰዎቻቸው
በትግራዊው ታጋይ “ዓባይ ነብሶ” በተባለው የወያኔ የሕግ አማካሪና የወያኔ ታጋዮች አካለ ስንኩላን ሊቀመንበር እየተመራ፤ ትግሬዎችን
በማስተባባር፤ እርዳታ በማሰባሰብ እና እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት
እና በመሳሰሉ ተራድኦ ሰጪዎች ትብብር የራሳቸው ንግድ፤ መጓጓዣ አብቶብሶች፤ መልሶ ማቋቋሚያ ገንዘብ፤ትምህርት… ወዘተ….. የመሳሰለ ዕገዛ ሲደረግላቸው (ያው
መቀሌ ውስጥ ባለፈው ወር በተጋበዙ የአፍሪካ፤ የአሜሪካ ኣማባሳደሮች እና መሪዎች ፊት ለፊት መቀሌ ስታዲዮም ‘አምረው ተከብረው’
ሰልፍ ሲወጡ ያያችሁት ነው።) በአንጻሩ የቀድሞ የአገሪቱን መከላከያ ሃይሎች በትኖ ወያኔ ስልጣኑን ተቆጣጥሮ ለራሱ ጀግኖች ምን
ዓይነት እንክብካቤ እያደረገ መሆኑን አድላዊ አሰራሩን በትግርኛ የሚሰራጩ ዘገባዎች የሚዘግቡት ሃቅ ነው።
እኔ የምናገረው ሃቁን ነው። ሃቁን ስናገር የማይጥማቸው በግራም በቀኝም አሉ። እስከ
ትናንት ድረስ እየደወሉ “ስለ ድርጅታቸው ደጋፊዎች እና አባሎቻቸው የምጽፈውን ቅሬታቸው ይገልጽሉኛል”፤ ይጠይቁኛል፤ ለመከራከርም
ይከጅላቸዋል። አንዳንዶቹ በጨዋነት ይግባቡኛል፤ አንዳንዱም መያዣ የሌለው ንትርክ ገብተው ለመዳከር ይቃጣቸዋል። ፈለጉም ጠሉትም፤
ሃቁን ከመዘገብ ወደ ሗላ እንደማልል እንዲያወቁት አሁንም ልነገርቻው እፈልጋለሁ። እኔ ታጋይ ነኝ፤ ሞትን የምፈራ አይደለሁም፤ ምቾትም፤ሥልጣንም
አልፈልግም። ሕግን የሚጻረሩ አመጸኞች እና የሰው ልጅ ወደ በረንዳ ከነቤተሰቡ የሚጥሉ ጨካኞች ግን ከማጋለጥና ከመቃወም ወደ ሗላ
አልልም። ይህ ምሬት የኔ አይደለም የብዙ ሚሊዮን ዜጎች ምሬት ነው።
ትግርኛ ለምታነብቡ “ትግራይ ተወላጆችም ለወያኔ አካለ ስንኩላን ታጋዮቻቸው ምን
እንክብካቤ እያደረጉላቸው እንደሆነ “ይኩኖ መስፍን” የተባለ “የኢትዮ ሚዲያ” ወዳጅ እና የወያኔ “ቀዳሽ አወዳሽ” የነበረ ፤አሁን
ተጣልቻለሁ የሚለን (ጥላቻቸው ግን ጅግኖቻችን ለምን በደምብ አትንከባከቧቸውም፤ በሚል እንጂ ወየኔ ከልጅ እስከ አዋቂ የደገፍኩት
እና አሁንም የምኰራበት ነው፤ ባይ ነው)። የጻፈውን ሐተታ ስትመከቱ፤ እርሱ በሚኖርበት አሜሪካ “ቦስተን” ውስጥ እንኳ $50,000.00 በእርሱ አስተባባሪነት፤በአባይ
ነብሶ እና በወያኔው አምባሳደር ፍስሃ አስገዶም ጉብኝት ከትግሬዎችና ደጋፊዎቻቸው ለወያኔ አካለ ስንኩላን መረዳጃ ገቢ ሆኗል። ይህ
የሆነው ምናልባትም ከ6 አመት በፊት በጣም በቅርብ ጊዜ ነው። ይህ ከቦስተን ብቻ የተገኘ ነው። አለም በሙሉ ሲዞሩ ከትግሬዎች፤ከተራድኦ
ያገኙትን ስታሰሉት ምን ያህል እንደሆነ ገምቱ።
አምና በቅርቡ ትግራይ ፌስቲቫል ተብሎ ፤የወያኔ ትግሬ ደጋፊዎች ተጠራርተው ወደ
ትግራይ ሲሄዱ ወደ 8 ያክል መነሻ ነጥቦችን ይዘው ነው የሄዱት። አደረጃጀታቸው የሴት፤የወጣት፤የቤተሰብ፤(ልክ እንደ ኮሚኒሰት ሩሲያ/ቻይና)
ሆኖ የሚዘረዝሩት ዓለማቸው ፈረንሳይ ከሚኖር አንድ አመራራ አባል ሲገልጽ ‘እጅግ ይገርማችሗል። ሌላ ቀርቶ መቀሌ ከተማ የሚገኘው፤
“ፕላኔት ሆቴል” ተብሎ የሚታወቀው ዓለም ዓቀፍ ሆቴል ባለቤት አቶ አርጋው (ስማቸውን ካልተሳሳትኩ) ሲናገሩ፤ መካዝኖቻቸውን የሚጠብቁ
ወደ 12 ጥበቃ ሲቀጥሩ ሁሉም የድሮ ታጋዮች የነበሩ ናቸው። ለምን እነሱን ለመቅጠር ተገደዱ ብለው እራሳቸው ሲመልሱ፤ አንደኛ
“ትምህርት ስለሌላቸው የትም ወድቀው መቅረት የለባቸውም” ሁለተኛ
“ታግለው ለዚህ ፍሬ ያደረሱን እነሱ በመሆናቸው” ቅድሚያ የሥራ ዕድል ይገባቸዋል፡ ሲሉ መልሰዋል። እንግዲህ “ጎሰኛነት”
አደገኛነቱን እዚህ ላይ ተመልከቱ። ትግሬዎች ለትግሬዎች ምን ያህል መተሳሰብ እና መቆርቆር እስከ እዚህ ድረስ ሲያሳዩ፤
የኛው ጉዶች ግን፤ አንድ ማሕበር መመስረት አቅቷቸው፤ ያንንም ለማፍረስ እና ለመጥለፍ
ሲጥሩ ታያላችሁ። የትም ተጥለው የወደቁትን ብሔራዊ የአገሪቱ ወታደሮች በምን መንገድ እንርዳቸው ብለው ድርጅት መስርተው ለማጠናከር
የተነሱትንም ፤ በባንዳነት ለማደር ወደ ሗላ የማይሉ አድርባይ ግለሰቦችን በማሰማራት ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት የእነ ሻምበል
አሸብር ገብሬን የሚያስመሰግን ኢትዮጵያዊ እና አርበኛዊ ሓላፊነት የተሞላበት ድርጅት “ተጠልፎ” ከሻዕቢያ ሥር አንዲወድቅ ሙከራ
አድርጓል። በዚህ መሰሪ ሥራ የተሰማሩ የቀድሞ ወታደራዊ አባሎች ዛሬም
ካልታቀቡ፤ ፎቶግራፎቻቸውን በየሚዲያው በማውጣት በባንዳነት የሚፈረጁ መሆናቸውንና፤ ከግንቦት 7 ጋር ሆነው በመደራጀት እና በመምራት
የሻዕቢያ ተላላኪነታቸው ሥራ ካላቆሙ፤ እኔም ብግሌ የማውቃቸው በግንቦት 7 ሥር ሆነው በየአገሩ እየዞሩ ‘የግንቦት 7 ፕሮፓጋንዳ”
የሚነዙ አሳፋሪ ወታደራዊ ግለሰቦች ስላሉ፤ ጥረታቸውም በሻዕቢያ ግፍ የተፈጸመባቸው ወታደሮቻችንን ታሪክ አዲሱ ትውልድ እንዳያውቀው
“ከተፈላጊው ወንጀላኛው ሻዕቢያ” በላይ “ሻዕቢያ ሆነው” የሚጥሩ ስለሆኑ፤
ፎቶግራፎቻቸው በማውጣት በአዲስ መጤ ባንዳነት የሚተቹ፤ መሆናቸውን እንዲያውቁት። በመለዮው ሥር “ባንዳዊ ተልዕኮ” ላንዴ
እና ለመጨረሻ ከ1983 ዓ.ም በሗላ መቆም ነበረበት። ሆኖም አሁንም ለዳግማይ የተከሰተ ይመስላል።
አይ ምፅዋ! ከሚለው ታሪካዊ ሰነድ ተነብቦ፤ እንደዚያ ያለ ኢትዮጵያዊነት መስዋዕት
ምፅዋ ላይ ከተደረገ በሗላ፤ ባንዳዎች በግንቦት 7 በኩልም ሆነ በስቪል ተዋጊ ሃይላት መረብ ምላሽ ድረስ ተሻግረው ስለ ኢሳያስ
መልአካዊ ተክለሰውነት የሚያሞግሱ ኢትዮጵያዊያን ይፈጠራሉ የሚል ሕልም ከቶ ነበራችሁ? እስኪ እንደገና ታሪክን መለስ ብለን ለመደምደሚያ
ጽሑፌ ልጋብዛችሁ እና የግንቦት 7 የዜና ማዕከል አሰራጭ የሆነው ኢሳት ጋዜጠኞች እየዘረጉት ያሉትን ባንዳዊ ቅስቀሳ የሻዕቢያ የምፅዋን
ጭካኔ እና ወንጀል እንዲሁ እንደዋዛ በሁለት ሦሰት/አራት ሆድ አደር ጋዜጠኞች ደላላነት የሚረሳ ወንጀል ከሆነ እንደገና የሚከተለውን
የምጽዋ ታሪክ ቀንጨብ አድርጌ ላስታውሳችሁ? አስታውሱ! ምፅዋ ውስጥ የወደቁ ጀግኖች ፎቶ በጥቂቱ
ከላይ የሚታዩት ኮሎኔል የምፅዋ አምበሶች እና አናብስት መርተው ከተሰውት
መካከል አንዱ የሆኑት ኮሎኔል ተሾመ ተሰማ ናቸው። The Lion of Massawa
Birgadier General Teshome Tesema፤
አብረው የተሰውት ከታች የሚታዩት መኰንን ደግሞ ሻምበል ሸዋን ታዬ ዓለሙ ይባላሉ።
Captain (Shambel) Shewantaye Alemu-the Lion of
Massawa
ፎቶግራፋቸው ያላገኘሁት የምፅዋ አናብስትና አንበሶች ታሪክም እንዲህ ተዘግቦላቸዋል፦
“…….ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ለብሰዉ ከቀይ ባሕር ሆቴል በረንዳ ላይ በአንዲት ጥልፍልፍ የቃጫ ወንብረ ላይ ተቀምጠዉ አጠገባቸዉ ለነበሩት ጥቂት አባላት መልዕክት ያስተላልፋሉ። “ጀግና ቢሞት በእልፍ እአላፍ ጀግና ይተካል።የእኔ ታሪክ ለትዉልድ ይቀራል። ታሪክ ይናገራል እንጂ እኔ አልናገርም።” የምትል መልዕክት ነች። መልዕክታቸዉም አንደጨረሱ ፊታቸዉን ወደ ምፅዋ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስትያን አዙረዉ አማተቡና የክላሽንኮቭ ጠመንጃቸዉን አፈሙዝ ጎርሰዉ ቃታዉን ሳቡት። ለጥቂት ሰኮንዶች አዉቶማቲክ ክላሽንኮቭ ድመፅ አስተጋባና ፀጥታ ሆነ።
ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ ክላሽንኮቭ ጠመንጃቸዉ እንደያዙ ወንበር ተደግፈዉ ተዝለፍልፈዋል። የለበሱት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ባንዴራ በላያቸዉ ላይ ደምቆ ይታያል።ይህነን ትዕይንት ሻዕቢያ በፎቶግራፍ አንስቶታል። በቪዲዮ ካሜራም ቀርጾታል፡ የወታደዊ ሸሚዝና ሱሪያቸዉን ኪስ ሻዕቢያ ሲበረብርም ከንጽህና ወረቀት በስተቀር ምንም አላገኘም። አንድ የሻዕብያ ተዋጊ ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ ለብሰዉ የተሰዉትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ባንዴራ ካላያቸዉ ላይ ገፈፈና ክብሪት ጭሮ አቃጠለዉ። የኮሎኔሉ አስከሬን ከወንበሩ ላይ ገፍትሮ በመጣልም በደም የተጨማለቀዉን ወንበር በአንድ እጁ ወደ ላይ አነሳዉ። ይህ ድርጊት ጋብ ያለዉን ተኩስ በመጠኑ ቀሰቀሰዉ። ከአንድ አቅጣጫ የተተኮሰች ጥይት ያን የሻዕቢያ አባል ከወንበሩ ጣለችዉ።ከዚያ በሗላም የሻዕቢያ ተዋጊዎች ተደናግጠዉ አካባቢዉን ማሰስ ጀመሩ።ፎቅ ላይ እየወጡና ምድር ቤቱን አሰሱ ቁስለኛም ይሁን ጤነኛ በየቤቶቹ ፍርስራሽ ሥር ተደብቆ ያገኙትን የአብዮታዊ ሠራዊት አባል ጭምር በየቦታዉ መረሸን ጀመሩ። የአብዮታዊ ሠራዊት አባላትም ሻዕቢያን ገድሎና የራሳቸዉን ጥይት እየጠጡ ሞቱ። “ኢትዮጵያ ወይም ሞት! ቀይ ባሕር የ ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ባሕር ነዉ!”። እያሉ መፈክር በማሰማት የክላሽ ጥይት እየጠጡ የተሰዉም ብዙ ናቸዉ።…….” አይ ምፅዋ ደራሲ ታደሰ ተሌ (ከሞላ ጐደል ታሪኩን ላምነበብ Tuesday, November 11, 2008 (Ethiopian Semay) የታተመወን ታሪክ ያንብቡ)
ይህን ለሚያስታውስ ሕሊና ላለን ኢትዮጵያዊያን እውን ለሻዕቢያ ባደሩ በሁለት ሦሰት
ባንዳ ጋዜጠኞች ደላላነት የሚደመሰስ ትውስታ ነው ያለን!!!??
በመጨረሻ፤“የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ዓለም አቀፍ ማሕበር” ዐላማ ምን አንደሆነ በድረገጹ የተለጠፈ ያስቀመጣቸው 8 ዘርዝር ነጥቦች ምን እንደሆኑ
በመግለጽ ጽሑፌን ልደምድም። እንዲህ ይላል-
አላማችንን ባጭሩ ለማስጨበጥ ያህል ፡-
1ኛ, ያልተፃፈና ያልተነገረ ታሪካችንን በእኛ በታሪኩ ባለቤት በአንድ ላይ ሁሉንም የሙያ ክፍል አካቶ እንዲፃፍና እንዲነገርና ለአሁኑም ይሁን ለመጪዉ ትዉልድ የዚህን ሠራዊት ገድልና ታሪክ ለማሳወቅ፣
2ኛ, ያለስራችን ስራ ፣ያለስማችን ስም ተሰጥቶን እኛ የደርግ ሠራዊትና ጨፍጫፊ ሆነን ከደርግ ጋር አብረን እንደከሰምን ተደርጎ የሚወራዉን የተሳሳተ አመለካከት ለኢትዮጵያ ህዝብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣
3ኛ, ደርግ ከጦሩ የተዉጣጣ የመለዮ ለባሾች ስብስብ እንጂ ሠራዊቱን ያልመሰረተ , ይልቁንም ሠራዊቱ ከመቶ ዓመታት በላይ ያስቆጠረና ረጂም እድሜ ያለዉ መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣
4ኛ, ለሀገር ዳር ድንበር, የአየር ክልልና የባህር በር መስከበር ሠራዊቱ የከፈለዉ መስዋዕትነት ለእናት ለሃገር ኢትዮጵያ እንጂ ለአንድ መንግስት ብቻ ያደረገዉ ባለመሆኑ ሊያስከበር ሲገባዉ በዓለም ላይ በማንኛዉም ሀገር ታሪክ ዉስጥ ባልታየበት ሁኔታ ሰራዊቱንና ቤተሰቡን ያለምንም የጡረታ መብትና ደመወዝ በመበተኑ ፤እነኚህ የስራዊቱ አባላትና ቤተሰቦች ለደረሰባቸዉ ጉዳት መንግስት ካሳ እንደከፍልና የጡረታ መብታቸዉ እንዲያከብር ፣አቅምና ችሎታ የፈቀደላቸዉን እንደገና ወደ ሠራዊቱ ገብተዉ የማዕረግ እድገታቸዉ ተጠብቆ እንዲያገለግሉና እንደማንኛዉም ሀገር ለዚህ ሠራዊት የመታሰቢያ ቀን እንዲኖር ለማስደረግ፤
5ኛ, በ17ቱ ዓመታት ዉግያ ከመቁሰል ተርፈዉ በጀግኖች አምባ ይኖሩ በነበሩ ጀግኖቻችንን ከጀግኖች አምባ ያለምንም ርህራሄ አዉጥቶ በማባረር ለሞትና ለአደጋ ከማጋለጥም በላይ በህይወት የተረፉት በልመና በየጎዳናዉ አሁንም ስላሉ ፣ በእነዚህ ጀግኖች ላይ የተፈጸመዉን ኢሰባዊ የሆነ ድርጊት ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም ህብረተሰብ ማጋለጥ፤
6ኛ, በተለያየ ሁኔታ ከጄነራል እስከ ወታደር ያሉ የቀድሞ ሠራዊት አባላት በተለያዩ የአፍሪካና መካከለኛ ምስራቅ አግሮች በስደት ካምፕና እስር ቤት የሚሰቃዩ ስላሉ ፣እነኚህ አባሎቻችን ቢቻል ወደሌላ ሦስተኛ ሀገር እንዲሄዱ አልያም መብታቸዉ ተከብሮ ወደ ሀገር በሰላም እንዲመለሱ በአስፈላጊዉ ሁሉ መርዳት፤
7ኛ, በተለይ በአሁኑ ሰዓት በኤርትራ በረሃ ዉስጥ ከምድር በታች ሲኦል በሆነ ሁኔታ የኤርትራ መንግስት የቀድሞ ጦር ኃይል አባላትን በማሰቃየት ላይ ስለሚገኝ ፣ እነኚህ አባሎቻችን ያለምንም ቅድመሁኔታ እንዲለቀቁ መጠየቅና ለዓለም መንግስታት ማሳወቅ፣
8ኛ, ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን ዳርድን በርዋን ብሎም ማንኛውንም ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ማስከበርን አስመልክቶ ፡ ከዚህ በፊት በታሪክ እንደታየዉ አባት ጦር ከመደበኛዉ ሠራዊት ጎን ሆኖ ግጋጃቸዉን እንደተወጡት ሁሉ አሁንም አገራችን ኢትዮጵያ የእኛ የልጅዎችዋ እርዳታ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የዜግነት ግዴታችንን ለማበርከትና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ፤ ሲሆን ይህንን ዓላማችንን ከግብ ለማድረስ የሁሉም አባሎቻችንንና ቤተሰቦቻችንን ያልተቆጠበ ጥረት እንጠይቃለን።
በመጨረሻም ማሳሰብ የምንወደው ይሄንን ማሕበር ስናቋቋም እንዲያው በቀላሉ ሳይሆን ያልጠበቅናቸውና ያላሰብናቸው የተለያዩ እንቅፋቶች አጋጥመውና ል ። ይህንን ትልቅ የተቀደሰ ዓላማ ይዘን ስንነሳ ውጥናችንን ፡ የአንድነት ጥሪያችንን ፡ በማጣመም በተለመደው ዘዴ የኛንም ጥረ ት ጠል ፈው ለመውሰ ድና ከታሰበበት ትልቅ ቁምነገር መንገድ አስወጥተው ለግል ጥቅማቸው የሠራዊቱን ስም መጠቀሚያ ለማድረግና እንደለመዱት ከሕዝብ ለሚሰበሰቡት ገንዘብ መሰብሰቢያ አዲስ ምዕራፍ ለማድረግ ያልሄዱበት የመከፋፈያ መንገድ አልነበረም። ይሄም ሳያንስ እነሱና መሰል ድርጅታቸው በሕብረት እንዳ ቋቋሙን ለማስመስል ጭምር አብረውን እንዳሉ በማስመሰል በመሃላችን ጣልቃ ገብተው ያስቸገሩን ግለሰቦችና ድር ጅት ነበር። እነዚህ በድርጅቱ የገንዘብ ጉርሻ ወይም በደመወዝ የሚሰሩ ግለሰቦች ከመሃላችን ተባባሪ ሆነው እንዳገኘናቸው ለምንወደው ለምናከበረው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለመላው የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ልናካፍላችሁ እንወዳለን ። ሆኖም ግን ጥረታቸውን ደርሰንበት በሃቀኞች ወንድሞቻችን ትብበር በመጨረሻ ማህበራችንን ልናቋቁም ችለናል ። ኢትዮጵያ በአንድነትዋ በሃቀኞች ልጆ ችዋ ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!!!” ይላል።
አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ geachre@aol.com )
ግልባጭ፦ ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ክፍል ዋና አዘጋጅ፤ horn@voa.com
1 comment:
ይድረስ ለወንድማችን አቶ ጌታቸዉ ዛሬ እማማ ኢትዬጲያ እያለቀሰች እነኝህ ሸጠዋት የመጡ ዛሬም ሱቅ ከፍተው በስሟ መነገድ ስራዬ ብለዉ ተያይዘውታል ቆራጥ ልጆቿን እንዳይደርሱሳት የውሸት ወሬ በማውራት በማስወራት ሀዘኗን እያራዘሙ አሉ ግቡ ለከፈቱት ሱቅ ከስደተኛው ወገኔ ገንዘብ መሰብሰብ ነው ።
እኛ እና አንተ በቆራጥነት ለወገን ለመድረስ የሚጥሩትን የማማ ኢትዬጲያ የቀኝ እጆቿን እንዲሰሩ በጋራ እንቁም
በቅርቡ አብረን መስመር ላይ እንገናኛለን አመሰግናለሁ
እዝራ
Post a Comment