የወያኔ “ፍሽስት ዳኞችን” ያንቀጠቀጠ ገጣሚ ወጣት
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ
ብሎግ አዘጋጅ)
December 12/2014
አሁን እየተካሄደ ያለው የፖቲካ
ውጥረት እንድተች ብዙ አንባቢዎቼ በስልክና በኢመይል ወትውተውኛል። ካሁን በፊት ስለ ተቃዋሚው በቃለ መጠይቅም በጽሑፍም ገልጫለሁ።ለጊዜው
ከመታዘብ ሌላ የምለው የለኝም። እንደዘወትሩ ትላልቅ የሆኑ (በአማራ ሕዝብና ገበሬዎች ላይ እየተወረወረ ያለ ዘለፋዊ ንቀት፤ድህነት፤በሽታ፤
እንግልት፤ እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻና ጥቃት፤ የባሕር በር ጉዳይ፤ የድሃ ሕዝብ መኖርያዎችን በቡልደዘር እያፈረሱ ለሃብታሞች
ህንጻ ግምባታ አንዲውል የመደረጉ፤ የሕዝብ መበታተን፤ስደት ፤ውርደት፤ የገበያ ኑሮ መወደድ…) ሕዝብን በፏስቶቹ ላይ አመጽ የሚያስነሱ
አንገብጋቢ ትላልቅ ብሔራዊ እና የዜግንት ጥያቄዎችን ወደ ጎን ትትው በግለሰቦች መታሰር እና በጋዜጠኞች መታሰር ማትኮሩ እሩቅ አንደማያስኬዳቸው
ደጋግሜ ገልጫለሁ። ተቃዋሚዎች አሁንም ኳሷን በመጣል ላይ ናቸው።
ሕዝብን ለአመጽ የማያስነሳ “ስተራተጂ” እየተከተሉ እራሳቸው በፋሺስቶቹ ሰነሰለት ውስጥ አስገብተው በመሰቃየት ላይ ናቸው። በመታሰራቸው፤
በመገደላቸው እና በመንገላታቸው ስቃያቸው የኛ ስቃይ መሆኑን ብናወቅም፤ እየተከተሉት ያሉትን “የ Repression and
Resistance” በጨቋኙ ሽብርተኛው የወያኔ ደብዳቢ ወታደሮች እና በተጨቋኙ ተደብዳቢው ሕዝብ ያለው የጭቆና እና የተቃውሞ ፍትግያዊ
ትግል ስልት ብዙ ብልሽት እንዳለው ካሁን በፊት ስላልኩኝ፤ አሁንም ያንኑ ድክመት እየደገሙ መስዋዕት ብቻ እየሆኑ ናቸው። ዛሬ ከመታዘብ
ሌላ የምለው የለኝም።
ለዛሬ የማቀርብላችሁ ዘገባ፤ “ታለንት ሸው” በመባል የሚታወቀው የወያኔ ቡችላዎች ያዘጋጁት በደቡባዊው ኢትዮጵያ
ክፍለ ግዛት የግጥም ወድድር ላይ በተዘጋጀው በአንድ ስሙ ያልተገለጸ ኢትዮጵያዊ ወጣት ገጣሚ እና በሦስት የወያኔ ፋሺስት ባንዳ
የመድረክ ዳኞች ላይ በተቀረጸው አውድዮ-ቪዲዮ የታየው ታሪካዊ ፍጥጫን በዓይናችሁ አንድታዩ እና በሁኔታው የታዘብኩትን ልገልጽላችሁ
ነው።
አይኩዌይ አርማሕ Ayi
Kweyi Armah (የተባለ ጋናዊ ልብ ወለድ ደራሲ “The Beautiful Ones Are Not Yet Born” በሚል ርዕስ በ1960
ዓ.ም (1968) የተደነቀ አንድ መጽሐፍ አሳትሞ ነበር። መጽሐፉ የሚተርከው፤ ጋናን ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ያወጣት የመጀመሪያው
የጋና መሪ የነበሩት የኮዋሚ ንኩርማ አስተዳዳር የመጨረሻዋ አመታቸው ላይ
እና ኑኩርማን በፈነቀለው ወታደራዊው ቡድን (1966 በፈረንጅ
ዘመን አቆጣጠር) የተከሰተው የተበላሸ፤ የሞራል ንቅዘት እና አስተዳደሩን ተከትሎ ከላይ እስከ ታች የነቀዘው፤ የጋና ማሕበረሰብም
በጉቦ፤ በውሸት፤ በቅጥፈት፤በወንጀል፤ በስግብግብነት እና አገራዊ ስሜትን ወርውሮ በጣለ በተበላሸ ባሕሪ ውስጥ ሲጓዝ በነበረበት
ዘመን፤ ደራሲው “The Man” / ሰውየው/ የሚል መጠርያ የሰየመው በጋና የባቡር መንገድ መ/ቤት ተቀጥሮ የሚሰራ በልብ ወለዱ
መጽሐፍ የተገለጸው ተዋናይ ግን፤ ጉቦም ሆነ አገራዊ ስሜትን የሚገድሉ ማራኪ ስጦታዎችን ከስርዓቱም ሆነ ከዜጎች ሲበረከትለት “እምቢታ”
ብቻ ሳይሆን፤ አገሩ በዛ ደራጃ መዝቀጥዋን ከውስጡ የሚያቃጥለው አገራዊ ቃጠሎ በቁጭት እንዴት ይለበልበው እንደነበረ የሚተርክ አስገራሚ
ድርሰት ነው።
The Beautiful Ones
Are Not Yet Born” ብሎ የሰየመው ልብ ወለድ መጽሐፍ ይሁን እንጂ፤ እውነታነት ያለው አሳዛኙ የአፍሪካ ታሪክ የሚተርክ
ነው። በዛው ትረካ ውስጥ የተዘረዘሩት ንቅዘቶች እና አሳዛኙ አገራዊ ስሜትን ከዜጎች ሕሊና ያስወጣ፤የሥልጣን ጥመኝነትና ስግብግብነት
(Power Greed/corruption) ስንመለከት፤ አሁን የተከሰተው የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ቁርቁዝናን የሚያሳይ ባሕሪያዊ መስተዋት
ነው።
ይባስ ብሎ፤ ብዙዎች የጋና ዜጎች
ብቻ ሳይሆኑ በእዛው የሞራል ቁርቁዝና የተለከፉት፤ ‘የተዋናዩ “የአቶ ሰውየው” የገዛ ሚስቱም ጉቦ እና ማራኪ ስጦታዎች ተቀብሎ
ኑሯቸውን አንዲያሻሽሉ ነጋ ጠባ በሃይለ ቃል ብትገፋፋውና ብትነጫነጨውም፤እስከመጨረሻ
ድረስ ነቀዞች በከበቡት ማሕበረሰብ ውስጥ ቢከበብም፤ እስከ ሕልፈተ ሞቱ ንፁህ ሆኖ ለመዝለቅ ያደረገው የሞራል ግብግብ በሚያስገርም
ሂደት ታግሎታል።
ሆኖም የመንግሥት ባለስልጣኖች እና ማሕበረሰቡ ብቻ ሳይሆን፤ ሚስቱም ጭምር
በእዛው በነቀዘው ማዕበል መጓዝዋን ደግሞ ይበልጥኑ ሐዘኑ የበረታ ያደርገው አንደነበረ ደራሲው ያብራራል።
ከሚስቱም አልፎ፤ “አቶ ሰውየው”
ውስጣዊ ግብግቡ ያሰቃየው ደግሞ አብረውት የሚሰሩት የሥራ ባልደረቦቹ ‘ጉቦ እና ስጦታ” ተቀብሎ ቤተሰቦቹን እንደ እነሱ የደበለ
ደስተኛ ኑሮ ለምን እንደማይኖር ነጋ ጠባ የሚወተውቱት የሞራል ፍጥጫ መጋፈጡና “በዚህ የወረራ ዘመን አሁን ካልበለጸግክና ቤተሰብህ
ካላንደላቀቅክ መቸ ሊደላህ ነው?” ሲሉት የሕሊና ውጥረቱ አንዴት ይፈታተነው አንደነበረም ይገልጻል። በዚህ የተነሳ የዘራፊዎች ማሕበር
ላለመሆን ሲታገል ሁሉም ስላገለለው፤ “ብቸኛነት” እጅግ ያጠቃው አንደነበርም ይዘረዝራል። አንደሌሎቹ ቤተሰቦቹን በጉቦ ይበረከትለት የነበረውን ገንዘብ አጠራቅሞ የተመቸ
ኑሮ ካለመኖር ያደረገው የሞራል ብርታት እራሱን እና ቤተሰቡን አንደተቀሩት የጋና ድሃዎች ጐስቋላው ፈታኝ ኑሮ አንዴት እንደኖረው
መጽሐፉ በሰፊው ይተርካል።
በመጽሐፉ የተረካቸው ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ ወጣን ብለው በቦረቁት በጋና ማሕበረሰብ ላይ የታየው የሞራል ንቅዘት፤
የመጠጥ፤ የዝሙት፤የጉቦ፤ የባሕል ብልሽት፤ እየዘረፉ ቤት ንብረት ማካባት፤ ከደረግ ንቅዘት ነፃ አወጣናችሁ ብሎ የፎከረው ሃሰተኛ
የወያኔ ዘመን እራሱ በባሰ ንቅዘት እና ዝርፍያ አንዴት አንደተነከረ ተመሳሳይነት አለው።
Ethiopian young poet who shocked Fascists puppets on poetic stage
የፋሺስት ግልገል
ዳኞችን ሕሊና ያራወጠው ስሙ ያልታገለጸ ወጣት ገጣሚ
|
ታለንት ሸው
ከዚህ ቀጥሎ በጽሑፌ መደምደሚያ
የሚቀርብ የተቀረፀ ስዕለ ድምፅ (አውድዮ ቪድዮ) እንድታዩት የምጋብዛችሁ የአንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ ገጣሚ (መቸም ኢትዮጵያ በፋሽስቱ
ወያኔ ዘምን አማርኛን በማጥፋት የቅኝ ግዛት አንግሊዝኛ ቋንቋን በመተካት “ኬንያ እና ናይጀሪያን” እየተወዳደረቻቸው ነች። ኢትዮጵያዊነት
ክብርና ቋንቋችንን ያራከሰ የቅኝ ዘመን- ዘመነ ወያኔ !!!!) “ታለንት ሸው” በመባል የሚታወቀው የፋሺስቶች መድረክ ላይ ቀርቦ
ያደረገው የግጥም ውድድር ላይ ያስሰማው “ኢትዮጵያዬ!!!” የሚል ግጥም በዳኝነት የተቀመጡት ሦስት የወያኔ ጀሌ የፋሽስቶቹ ውሾችን
ያቁነጠነጠ፤ያቃጠለ፤ያስበረገገ፤ሐፍረትን ያከናነበው ግጥሙን አንድታደምጡ እጋብዛችሗለሁ።
የወጣቱ ግጥም በእኔ ዳኝነት እስካሁን
ድረስ የኢትዮጵያ ወጣት ገጣሚዎችን ባስገራሚው ግጥሙ ያሸነፈ የአመቱ ኢትዮጵያዊ ገጣሚ ብዬ ሰይሜዋለሁ። ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ማሕደር በኩራት የገለጸ፤ ስለ ወያኔዎች እና ተገንጣዮች
ማንነትና አሁን ያለቺው ኢትዮጵያ ገጽታ ያብራራ ፤ ስለ ታሪክ ድንቁርናቸው፤ እና ግብዝ እውቀታቸው፤ እንዲሁም ውሻነታቸውንና እና
ጸረ ኢትዮጵያዊ ባንዳነታቸውን ያጋለጠ “ገጣሚው እና ግጥሙ” ለመጀመሪያ ጊዜ ለ22 አመት እንዲህ ያለ ወጣት በድፍረት ባንዳዎችን
በሕዝባዊ መድረክ የተጋፈጠ ወጣት ገጣሚ አይቼ አላውቅም። አርበኞች ኢትዮጵያዊያን በዚህ ወጣት መኩራት ይገባናል።
የታወቁ የአገራችን ታላላቅ ገጣሚዎች
እነ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን(ቀዊሳው)፤ ሃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው)
ጸጋዬ ገብረመድህን (ደብተራው)፤ እያሱ አለማዮህ (ሃማ ቱማ) … ወዘተ ያፈራችሗቸው ገጣሚ ወጣቶችን ይሄው ጊዜአቸውን ጠብቀው በጽንስ መወለድ ሂደት ላይ መሆናቸው ደስ ይበላችሁ።
ታላቁ ባለ ቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መደህን (ቀዊሳው)
በቅርቡ በሞት የተለየን ገጣሚ ሃይሉ
ገብረዮሐንስ (ገሞራው)
በፋሺስት ወያኔዎች የተረሸነው ጸጋዬ (ደብተራው) |
ከድሮ የኢትዮጵያ አውቅ ወጣት ተማሪ ፖለቲከኞች ስማቸው
ገንኖ ከሚነሱት የእንቅስቃሴ መሪዎች መሃል በሕይት ያለው ብቸኛ የፖለቲካ መሪ ገጣሚ
እያሱ ዓለማዮሁ (ሃማ ቱማ)
|
የፋሽስቶች ሕሊናን ያራወጠ የ2006 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ወጣት ኢትዮጵያዊው ገጣሚ
(ስሙ ያልታወቀ)
እነኚህ ሁለቱ የምታዩዋቸው የመድረኩ የፋሺስት ቡችሎች በዳኝነት ተቀምጠው ወጣቱ ገጣሚ ግጥሙን ሲያነብ ተደናግጠው ያሳዩት “የእናስቁመው” ቁጣ እና ድንጋጤ ነው። |
የትግራይ ፋሺስት ባንዳዎች እና
ትንንሾቹ ቡችላዎቻቸው ኢትዮጵያዊ አንዳይናገር፤ አንዳይጽፍ፤ አንዳይመራመር፤ የወጣት ሕሊና እንዲዝግ የተቻላቸውን አድርገው ለ22
አመት ወጣቱ አበላሽተውት፤ እራቁታቸው እስክስታ የሚረግጡ ወጣት ልጃገረዶች በሽርሙጥና እንዲሰማሩ አድርጎ ሕሊናቸውን አንቅዟል።
እነኚህ በዝግ ቤቶች እርቃናቸው የሚጨፍሩ ወጣት ልጃገረዶች የፋሺስት ባለስልጣኖች የዝሙት ማርኪያቸው ሆነዋል። ግበረሰዶም በወጣቱ
እንዲስፋፋ፤ በታሪካችን ተሰምቶ የማያውቅ የእጽ፤የኰከይን እና ሄረወን መድሃኒቶችን ወደ አገር አንዲገባ በነቀዘው ሥርዓቱና ተባባሪዎቹ
የኢትዮጵያ ወጣት ተለክፎ፤ ወደ ዕብደት ሲያመራ፤ ባለስልጣኖችም በጉቦ፤ በስስት፤ በንብርት ዝርፍያ ገብተው ኢትዮጵያዊነት ባሕሪን
ሲያቆሽሹ ፤ ባለትዳሮችም በጫት እና በኰከይን ሱስ ተጠምደው ትዳራቸውን እየፈቱ፤ ኑሯቸው በትነው ልጆቻቸው ለመከራ ተዳርገዋል።
ከዚህ በላይ የምታዩዋቸው እነኚህ የፋሺስት ቡችሎች ወጣቱ ገጣሚ ግጥሙን ሲያነብ ተደናግጠው ያሳዩት “የእናስቁመው” ቁጣ እና
ድንጋጤ ነው። በግራ በኩል ያለው “ፋሺስት ግልገል’ ከንፈሩን በመንከስ ገጣሚውን ለማስቆም በንዴት ሲያምትር ነው።
|
ሕብረተሰቡ ነቅዞ ባለበት ዘመን፤
ሁሉም ሞቷል፤ደንዝዟል፤ “እስካሁን ድረስ የአርበኞች ውልደት አልተከሰተም” The Beautiful Ones Are Not Yet
Born” ባልንበት ዘመን፤ እንዲህ ያለ አስገራሚ ወጣት ገጣሚ መድረክ ላይ ብቅ ብሎ የፋሺስቶቹ ቡችላ ተላላኪዎችን ሲያስደነግጥ
ማየት፤ ለ22 አመት የደነዘዘው ወጣት ከእንቅልፉ ነቅቶ “የአርበኞች ውልደት በሂደ
ት ላይ አንደሆነ” አበሳሪ ዜና ነው።
በዚህ ፎቶ የምትመለከቱት በወጣት ገጣሚው የብዕር ቦምብ
ቆስሎ፤ ሕሊናው ከድቶት ለሞት የተቃረበው ከፋሽት ግልገሎቹ ዳኞች አንዱ ነው።
|
የጋናዊው የአይኩዌይ አርማሕ (Ayi Kweyi Armah) “የአቶ ሰውየው”
ስነ ባሕሪና የዚህ ወጣት ኢትዮጵያዊ ገጣሚ ባሕሪያቸው መገጣጠሙ አስገራሚ የአልበገሬ ግጥምጥሞሽ ባሕሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።ሁሉም በሸሸበት
ዘመን፤ ሁለም በደነዘዘበት ዘመን፤ ሁሉም በነቀዘበት ዘመን፤ ሌቦች እና ሃሰተኞች ቂሞኞች እና ወንጀለኞች በበዙበት ጸረ ኢትዮጵያ
ሃይላት በተከበበበት ማዕበል ገፍትሮ በመዋኘት ኢትዮጵያዊ ኩራትን በደም አደባባይ ቆሞ ፋሺስቶችን በብዕር ቦምቡ ያቆሰለ ፤ ሕሊናቸው
ውስጥ ቦርቡሮ ቁም ስቅላቸውን ያሳየ ወጣት ገጣሚ ማየት በታሪካችን ያላየናቸው “ውብ ማራኪ ቆነጃጅቶች፤ ቆንጀዎችና አርበኞች” በመወለድ
ሂደት ላይ የጀመረ መሆኑን ስንመለከት፤ የእናቶች እና የእህቶችን የሃዘን ሸማ የሚያበቃበት ዘመን እየተወለደ መሆኑን ይነግረናል።
የምታዩት ፎቶ ከሦስቱ የፋሺስቶቹ ቡችላ ዳኞች አንዱ ነው። በወጣቱ ግጥም ተበሳጭቶ ወጣቱን ለማስቆም
በንዴት ሲያምትር።
|
የፋሽስት ግልገሎችን ሕሊና ያስደነገጠ
ይህ ኢትዮጵያዊ ገጣሚ “ታለንት ሸው” በተባለው የወያኔዎች መድረክ ላይ ቀርቦ በነበረበት ጊዜ “ግጥሙ አንዲቋረጥ” መደረጉን እና
“ዳኞች” የተባሉት ባንዳዎችም የታየባቸው ድንጋጤ እና የሕሊና መሸማቀቅ እና ፍጥጫ፤ የነበረው ሂደት ለመከታታል ይህንን አስፈንጣሪ
በር/ ሊንክ/ ይጫኑ። Ethiopia: Amharic Poem http://youtu.be/age46605Ntw
አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን
ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) (Ethiopian Semay) getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment