ዴምህት እና ገብሩ፤ ስብሓት እና ገብሩ (ክፍል 1)
ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ብሎግ አዘጋጅ)
Tuesday, November 11, 2014
ከላይ የሚታየው ፎቶግራፍ በትግራይ ስም የሚጠራው ትህዴን/ዴምህት የተባለው
በኢሳያስ ቁጥጥርና ልዩ እንክብካቤ የሚደረግልት በኢሳያስ ትዕዛዝና የሚንቀሳቀሰው ኤርትራ ውስጥ የመሸገው የሽምቅ ተዋጊ ነው። ተባራሪ
ወሬዎች አንደሚሉት ከሆነ ድርጅቱ በስብሓት እና በኢሳያስ ምስጢር የተሸረበው በሰንደቃላመው መሃል የአክሱም ሃውልት የለጠፈው *ትግራይ
ትግርኚ* ጦር እንደሆነም አዳዲስ ወሬዎች ሰሞኑን መናፈስ ጀምሯል።* ከትግራይ በረሃማ መንደሮች ወጣቶች በገፍ እየታፈሱ በመኪና
እየተጫኑ ወደ ኤርትራ በግልጽ ሲወሰዱ ደምብር ላይ ተቀምጦ ያለው የትግሬ ጦር አይቶ አንዳላየ እየሆነ አንደሆነ እና ይህም በነስብሓት
የተገመደ ሴራ ነው የሚሉ ተባራሪ ወሬዎችን እየሰማን ነው።
በመጀመሪያ የኔን ጽሑፍ ብልክላችሁም ባልልክላችሁም ፈልጋችሁ በድረገጸቻችሁ በማውጣት እና በደምጽ እያነበባችሁ በየራዲዮኖቻችሁ የምታስተላልፉልኝ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼን አመሰግናለሁ። በስልክም በደብዳቤም በየወቅቱ እየደወላችሁ የምታበረታቱኝ በርካታ ወገኖቼም እንዲሁ አመሰግናለሁ።
ይህ ጽሑፍ ስለ ገብሩ መጽሐፍ ተከታታይ
ትችቴ ሳይሆን ገብሩ በጻፈው ላይ ያኰረፉ ሁለት የኤርትራ ቅጥረኞች በሰጡት አስተያየት የሚተነትን ነው። በወያኔ እስር ቤት እየተሰቃየ
የሚገኝ አንድ ታዋቂ ወጣት ጋዜጠኛ ስለ ዴምህት የሰጠው አስተያየት በትችቴ ውስጥ ተካትቷል። ስለ ገብሩ አስራት መጽሐፍ መተቸቴ አላቆምኩም። ግን አንዳንድ ነገሮች ድንገት
ከማሃል ከች እያሉ ስላስቸገሩኝ ታገሱኝ። ዴምህት/ትህዴን/ቲፒዲኤም ብሎ ራሱን የሚጠራ ኤርትራ ውስጥ የመሸጉ በረቀቀ ትምህርት ያልበሰሉ
፤ ድሮ የወያኔ ተዋጊ ሃይሎች የነበሩ ታጋዮች የሚመሩት የሽምቅ ተዋጊ ቡድን፤ ገብሩ አስራት ስለ የኤርትራ ጉዳይ ፤ቀይ ባሕርና
እና ኢትዮጵያ፤ አንዲሁም ባጠቃላይ ሉዓላዊነትን አስመሰልክቶ፤ ወያነ ትግራይ በክህደት ስለወሰነው ኢትዮጵያዊ ጥቅም ያላገናዘበ የኤርትራንና ኢትዮጵያ ጉዳይ፤ በግልጽ ሴራ የተበደለው የኢትዮጵያን ጥቅም ሕጋዊነት ባለው መንገድ ላመስከበር በሚመለከት
አንደገና መታየት አንዳለበት ስለ ጻፈው መጽሐፍ እና በ ቪ ኦ ኤ ቃለ መጠይቀም ያረጋጋጠውን ይህንኑ መስመር ያልጣማቸው ቅጥረኞቹ
ስብሓት ነጋ እና ዴምሕት በጋራ ያስነጠሱት ልሃጫቸውን/droplet አንመለከታለን። በተለይ ዴምህት ያሰራጨው ጸያፍ (ludicrous) እና በባንዳዊ ባሕሪ
(mercenary behavior) ታጅቦ ስለ ኤርትራ ወግኖ ገብሩን የዘለፈበትን ድርጅታዊ መግለጫውን እንመለከታለን። ስለ ገብሩ
ጥብቀቅና መቆሜ ሳይሆን፤ ገብሩ ያሰመረበትን ኢትዮጵያዊ ክርክር ተቃውሞው ለኤርትራ ወግነው ከኤርትራ በላይ ኤርትራዊ የሆኑትን መቃወሜ
ለዘመናት የታገልኩበት እልክ አስጨራሽ መስምር በመሆኑ ዛሬም የካሃዲዎች እና ተባባሪ የቅጥረኞቻቸው ፕሮፓጋንዳ ማጋለጥ ኢትዮጵያዊያን
መከተል ያለብን የትግላችን አንዱ ክፍል ነው። የዴምህት መግለጫ
ትችቴን አንዳለስረዝምባችሁ በክፍል ሁለት(2) ከኤርትራዊው ስብሓት ነጋ በጋራ አያይዤ የምተቸው ትንተና በሚቀጥለው ሳምንት ይለጠፋል።
ከዚያ በፊት ግን እንደመግቢያ የሚሆነን፤
ተመስገን ዳሰለኝ የተባለው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛም በዴምህት ምን ያህል
አደናቆት አንደተቸረው እና ተመስገንም ለዴምህት ምን ያህል አክብሮት አንዳለው የጀነጀነው ሃሰተኛ ምሰክርነቱን ዛሬ እንመለከታለን።
ፕሮፌሰር መሳይ ከበደም በዴምህት ላይ ተመሳሳይ የተንሸዋረረ የዴምህት ሙገሳ እና እምንት አንዳላቸው ተመስገን የገለጸው ጽሑፉን
እንመረምረዋለን። ፕሮፌሰሩም ያንን ጽፈው ከሆነ እያደር ከመገረም አልፌ ምን ልብል?
ትህዴን/ዴምህት ስለተባለው ድርጅት
ካሁን በፊት አንደገለጽኩት፤ ድርጅቱ የኔን ጹሑፎች በድረገ ጻቸው ያወጡት አንደነበር እና ባንተ ኮርተናል፤አይዞህ እያሉ በኢመይል
በገለጹልኝ ወቅት ደጋግሜ የጠየቁኩዋቸው ጥያቄ ፤ ድርጅታቸው ስለ ዓሰብም ሆነ ስለ ኤርትራ ነጻነት ጉዳይ አንዲገልጹልኝ ነበር።
የሰጡኝ መልስ ፤ ወያኔዎች የሚነግሩንን መሰመር ነበር። ድርጅቱ ቅጥረኛ መሆኑን ከዚያ በ ላ መገንዘብ ችያለሁ። ካሁን በፊት በማስረጃ
አስደግፌ የዘገብኩት እና ፤ በቅርቡ አስመራ ድረስ “ዓርቢ ሓርነት ”፤ ከተባሉት አስመራ ውስጥ የመሸጉ የኢሳያስ ስርዓት ተቃዋሚ
የሆኑትን በድብቅ የሚንቀሳቀሱ የውስጥ አርበኞችን በረቀቀ መንገድ ደውለው ያነጋገሯቸው የውጭ አገር ጋዜጠኞችም ዴምህት በኢሳያስ
የሚታዘዝ መሆኑን የዘገቡትን ማረጋጋጫ አንመለከታለን። ዲምህት የተባለው
ብዙ የገበሬ ተዋጊ ያሰባሰበ ድርጅት፤ የኢሳያስ ልዩ የጸጥታ ጠባቂ ጦር በትግራይ ተዋጊዎች ሽፋን ስም ለኢሳያስ ልዩ አገልግሎት
ሰጪ ሆኖ የተመሰረተ አንደሆነ ብዙ ወገኖች መረጃ የላቸውም። ቢኖራቸውም ሊያምኑ አይፈልጉም ፡ በተለይ ግንቦት 7 የተባሉት ጀሌዎች።
ባለፈው ወርም በኢሳያስ ትዕዛዝ በበርካታ የጦር የጭነት መኪኖች ተሳፍረው ወደ አስመራ ከተማ በማቅናት ከተማዋን ከብበው ወጣቶችን
የማፈስ አሰሳ ሲከናወን የጥበቃ ከለላ ሲያከናውኑ አንደነበር ተዋጊዎቹ የሚለብሱት ልብስም ሆነ ወዛቸው ጫካ እና ጦርነት ያላጎሳቆላቸው
ቅልቦች መሆናቸው ከኗሪዎችና ከሚያሰራጩት አውዲዮ ቪዲዬ ተረጋግጧል።
የተዋጊዎቹ ውበት እና አካላዊ ቁመና
በረሃ እና ጦርነት ያጎሳቆላቸው የሽምቅ ተዋጊዎች ሳይሆን የሚመስሉት እረፍት ያደረጉ፤ወዛቸው የወዛ፤ ልብሳቸው ያማረ እና ያልተቦጫጨቀ
እና ያልተጨማደደ አንደሆነ በቀላሉ ከዚህበ በታች ያለውን ፎቶግራፍ በማየት ማረጋገጥ ትችላላችሁ። ለምሳሌ ይህ ከዚህ የምታዩት ፎቶግራፍ
የድምህት ታጋይ ጎይታኦም ነጋሽ የተባለ ታጋይ ነው።
ደምብ ልብሱን ስትመለከቱቱት አንኳን የበረሃ፤ ከተማ ውስጥ ያሉት የኢሳያስ
መኰንንችንም የሚያስንቅ ደምብ ልብስ እና ምቾትን ያንጸባርቃል። ይህንን ስንመለከት ለሊቢያ ሉዓላዊነት ቆሞ የነበረው የሰሜናዊ ቻድ
የጉንት ቅጥረኛ የሊቢያ ተዋጊዎችን ያስታውሰናል። የህ ፎቶግራፍ ግምባር ሓርነት አደቦ ኤርትራ (Father
Land Front for the Liberation of Eritrea) ከተባለው የተገኘ። ነው። ከላይ የሚነበበው ፤ የዴምህት ’ዴሞክራስያዊ ምንቅስቓስ ህዝቢ ትግራይ’ ፤ ካድሬዎችና ተዋጊዎች ባባቶቻችን በኤርትራ መሬት ላይ ሆነው ወደ ኤርትራዊ ደረት ያነጣጠሩትን ከባድ መትረየስ አፉን ከፍቶ ሲታይ ይላል።
ከላይ የምታዩት የዴምህት መሪ የሚባልልት
ሞላ አስገዶም በኤርትራ ወታደራዊ ደምብ ልብስ አጊጦ ሲታይ ነው።
ከታች የምተቸው የተመስገን ደሳለኝ ጽሑፍ ምንኛ የተሳሳተ መሆኑን ለማገናዘብ
አንዲረዳን መጀመሪያ ከላይ ከጠቀስኩት የኤርትራ ተቃዋሚ ድርጅት ልሳን የዘረጋው ለኤርትራ ወታደራዊ መኮንንኖች ምኒስትሮች ፤ታጋዮች
እና ሕዝብ ዴምህትን አንዲመክት ያስተላለፈው ጥሪ ባጭሩ አንመለከታለን።
ግምባሩ ያስተላላፈው የዴምህት ማንነት
የተነተነውን ለመደርደሪያ እንመልከት። መግለጫው ትግርኛ ነው።
አንዲህ ይላል፤_
“ዴምህት ተብለው የሚጠሩ እነኚህ ለኢሳያስ አፈወርቂ የቆሙና
የተመሰረቱ፤ ኤርትራ ውስጥ አንዳሻቸው ለማድረግ አረንጓዴ መብራት አንዲበራላቸው የተፈቀደላቸው ብረት የታጠቁ ሰራዊቶች መቶ በመቶ
ትግሬዎች ናቸው። ዓላማቸው ደግሞ ‘ትግራይ
ትግርኚ’ ከሚለው ሜዳ ውስጥ እያለ ያልመው የነበረው የኢሳያስ የመጨረሻ የጭንቀቱ መዳረሻ እርከን
ያቀደውን እቅድ ከመተርጎም ሌላ ዓላማ የላቸውም። የድርጅታቸው ስም እና ዓላማ ለትግሬ ይላል። ተግባራቸው ግን ኢሳያሳዊ ነው። በእንዴት
መሳይ ጥበብ ወደ ኤርትራ ገቡ? ከመቸውስ ቁጥራቸው ባጭር ጊዜ 45 ሺሕ ደረሱ? ለመሆኑ ኤርትራ ውስጥ ገጠሮች እና ከተሞች ውስጥ
ገብተው የሙዚቃ፤ የፖለቲካ ፤የወታደራዊና ማሕበራዊ ስራዎች ለመስራት
ያለ ገደብ እንዴት ሊለቀቁ እና ሊጨፍሩ ቻሉ? የሚሉ ጥያቄዎች ለማንሳት ተገድደናል።” ይላል መግለጫው።
በመቀጠልም፦
“ኢሳያስ
በኤርትራዊያን የነበረው እምነት ስለተሟጠጠ፤ ከትግሬዎቹ ወላጆቹ እና አጎቶቹ ከአፈወርቂ አብርሃም ካሳ የሚወለዱ የደም ዘመዶቹ የሆኑ
ትግሬዎች ሰብስቦ ከስሩ አደራጅቶ ተጠባባቂ ቦዲ ጋረድስ አድርጓቸዋል።“
“በኢሳያስ
ስር የምትገኙ ከፍተኛ ወታደራዊ ክፍሎች እነ ታጋዮች፤ሕዝባችሁ በዴምህት እየተዋረደ፤እየታሰረ እና እየተጎተተ አይታችሁ አንዳላያችሁ
ስትሆኑ ሞት ይሻላችሗል። በታጋዮቻችን ደም የተቀቡ ጠመንጃዎቻችን
ኢሳያስ ለደምህት አስታጥቆ ጠመንጃዎቻችን እኛኑን መግደያ እና ማስፈራሪያ እየሆኑ ነው።”
አስገራሚው የትግርኛ ገለጻው አንዲህ ይላል፤-
“ (ብሓለንጊ
ዴምህት ትግረፍ ዘለኻ
ኤርትራዊ ዜጋ…) በዴምህት አለንጋ
እየተገረፍክ ያለኸው ኤርትራዊ ዜጋ፤በተለይ በ335 እስርቤቶች ውስጥ 60ሺህ የሚሆኑ ኤርትራዊያን እስረኞች አንደ አዳርሰር በተባሉ
ከመሬት በታች ተቆፍረው የተገነቡ የሲኦል እና የጭለማ እስርቤቶች
ታጉረው የሚገረፉ እስረኞችን እየመረመሩ የሚገርፉ ገራፊዎችና ረሻኞች ለዚህ ስራ የተመለመሉ ከዴምህት የተመረጡ የዴምህት አባላት
ናቸው። ከዴምህት እየተረጨ ያለው ቤንዚን ሁላችንም ተባብረን ክርቢት ለኩሰን መሪያቸው የሆነውን ኢሳያስን አስወግደን እነዚህንም ከመሬታችን እናስወግድ። የሕዝባችንን ስቃይም በዛው
ለማሳጠር መፍትሔው በጋራ መነሳት ነው። እንደ ጁቢተር ኮኮብ ከፊት ለፊታችን ደምቆና ገዝፎ እየታየን ያለው የኢሳያስ የመጨረሻ “ቀብር” አፈር ለማልበስ ከተኛንበት ነቅተን አንነሳ።” ይላል።
እንግዲህ ዴምህት በዚህ ግምባር
ግምገማ 45ሺህ ወታደር ሲለው ከታች የምተቸው ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ግምት ደግሞ መቶ ሺህ አድርሶታል። የቁጥሩ
መጠን የሚያሳየን በጣም ከፍተኛ መሆኑ ሆኖ ዴምህት ያን ያህል ረዢም (13 ኣመት) ጊዜ እና ሰራዊት ይዞ አንዲት ትንሽ የገጠር
መንደርም እስካሁን ድረስ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ነጻ አድርጐ አለመያዙ የሚያሳየን ነገር ምክንያቱ ለናንተ ግልጽ አንደሚሆን እገምታለሁ።
አሁን ወደ ተመስገን። የተመስገን ደሳለኝ ጽሑፍ ያየሁት ድንገት ድምህት ድረገጽ ለመጎብኘት ስሄድ ነው በድርጅቱ መጽሔት በትግርኛ ተተርጉሞ ያየሁት። በተመስገን የተጻፈ እውነታን ያላገናዘበ ስሜታዊ ጽሑፍ ስመለከት አስገረመኝ እና ሳላስበው ከድምህት እና ከነገብሩ ጋር አያይዤ ለመተቸት ወሰንኩ። ጋዜጠኛው ብዙ ተከታይ አንዳለው ስለማውቅ እሱ በሚጽፋቸውም ያን ያህል ሕዝብ ማጃጃል ስለሚችል ያንን እውነታ ማጣጣም እና ግልጽ ማድረግ የግድ ነው።
ጋዜጠኛ ተመስገን እና ዴምህት።
ያለ ሕግ ዛሬ በባንዳዎቹ የወያኔ
እስር ቤት እየተሰቃዬ ያለው ተመስገን ደሳለኝ የተባለው ጋዜጠኛ ስለዚህ ቅጥረኛ እና ጠባብ ብሔረተኛ ቡድን፤ “ስለ የትግራይ መስቀል ስለመሸከም ” በሚለው ጹሑፉ ውስጥ የትግራይ ሕዝብ በወያኔ ጭቆና ስለመሰቃየቱ እና ከሌሎች
አካባቢዎች በድህነት ስለመቆራመዱ ከሕዝቡ አገኘሁት ያለው ዘገባ ፤ እንዲሁም
ስለ ድምህት እና ስለ የመጀመሪያው ወያኔ መስራች ብላታ ሃይለማርያም ረዳ ትከክልኛ ኢትዮጵያዊነት የዘገበውን ጽሑፉን
በትህዴን/ዴምህት መጽሔት በታላቅ አድናቆት እና አክብሮት ወደ ትግርኛ ተርጉሞው “መጽሔት ብስራት” በሚባል የትግርኛ መጽሔታቸው የዘረጉትን ትርጉም ድንገት አይቸው አስገርሞኛል።
ተመስገን ደሳለኝ ጻፈው ብለው የተረጎሙት
አንዲህ ይላል። (ትግርኛውን ትቼ ማለት ነው) ፡ የሚተለው ከዘሓበሻ የቀዳሁት ነው። Tuesday,
June 17th, 2014 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31331
ሳልሳዊ ወያኔ
*በብላታ ኃይለማርያም ረዳ ፊት-አውራሪነት በ1935
ዓ/ም ትግራይን በአፄው ላይ እንድታምፅ ያነቃቃው የወያኔነት እንቅስቃሴ፤ በያኔዋ የአፄው የክፉ ቀን ወዳጅ ታላቁ ብሪታኒያ ማበር ጭምር ሲቀለበስ፤ በክሽፈቱ ፅንስ ውስጥ ሌላ ትውልድ እንደሚገነግን ግልፅ ነበር፡፡ እናም የእነ ኃይለማርያምን ኢትዮጵያዊነት ጨፍልቀው የተነሱት እነ ስብሐት ነጋ፣ ያን ብርቱ የማህበረሰብ ክፍል ሰቆቃ ጠምዝዘው ከማህበረ-ባህሉ የተጣረሰ መንገድ መርጠው ሸገር ሲደርሱ፤ እነርሱኑ ካፈራ መሬት፣ የተቀለበሰውን ዳግማይ ወያኔ ረግጦ የሚነሳ ትውልድ እንደሚመጣ ዘንግተው ሰንብተዋል፡፡*
ይላል ተመስገን።
እውነት ነው ተመስገን አንደነገረን
የብላታ ሃይለማርያም አንቅስቃሴ ኢትዮጵያዊነት ነበር? ወይስ ጉልተኞች የትግራይ ብሔረተኞች ዮሐንስ ከተሰው በሗላ የቆዬ ውስጣዊ
ጸረ ሸዋ/አማራ ንግሥና በመቃወም አንደገና የተነጠቀው የትግራይ ንግሥናዊ ሥልጣን ለማስመለስ የሚል አጋጣሚ ሲጠብቅ የነበረ የባላባቶቹ
አብዮት *ሰበብ*? ወይስ ሌሎች ጉዳዮች የተላበሰ ነበር?
ባጭሩ እንመልከተው። የብላታ ሃይለማርያም
የመጀመሪያው ወያኔ እንዴት ተፈጠረ? በሚል ርዕስ ሰፋ ያለ ሀተታ የዘገቡት የአጼ ሃይለስላሴ ታሪክ መጽሐፍ ደራሲ አቶ በሪሁን ከበደ
የነገሩን ከተመስገን ጋር የሚጻረር ነው። ተመስገን ኢትዮጵያዊነትን ለማጎልበት የወያኔ እንቅስቃሴ ተመሰረተ ሲለን አቶ በሪሁን ከበደ
ደግሞ ብላታ ሃይለማርያም፤ጉግሳ መንገሻ ፤ልጅ በኹረጽዮን ፤ልዑል
ራስ መንገሻ፤ ደጃች ማሩ …..ወዘተ ወዘተ…..በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ የተካፈሉበት የገበሬውን አመጽ ነጥቀው ለየራሳቸው ምክንያት
ማነሳሻ ያደረጉት አመጽ አንጂ ከቶ ኢትዮጵያዊነት ከማጠናከር ጋር
የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል።
በተለይ ሁለቱም ብላታ ሃይለማርያም
ረዳ እና ባሻ ጉግሳ መንገሻ የሸፈቱት ምክንያት ሲያስረዱ፤ ሁለቱ እነዚህ የጎበዝ አለቆች ከመሸፈታቸው በፊት አንግሊዞች ትግራይን
ገንጥለው ከኤርትራ ጋር አዋህደው ቤተ መንግሥቱን አክሱም ላይ አድርገው ለ25አመት በእንግሊዞች እጅ ቆይተው በመጨረሻው ሕዝቡ የፈለገውን
አስተዳዳር አንዲመርጥ እንለቅለታለን በማለት ብዙ ጥረት እና ስብከት የሚያደርጉበት ወቅት ነበር።
ከዚህ ሌላ ንጉሠ ነገሥታችሁ የሉም፤
በወሬ ነው የምትገዙት፤ ኩሓ ከነበረው ካቶሊክ ቤተክርስትያን የናንተ ታቦት አንዲገባ የተደረገው ንጉሠ ነገሥቱ ባይኖሩ ነው አንጂ
ንጉሡ ካሉም የካቶሊክ እምነት ተከታይ ሆነው በመምጣታቸው ነው አንጂ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የጸኑ ቢሆኑ ኖሮ የካቶሊኮች ቤተክርስትያን
ከነበረበት ላይ የናንተ ታቦት አንዲገባ ሲደረግ ዝም ብለው አይመለከቱም ነበር። እያሉ ካንዳንድ የውስጥ የእንግሊዝ ተቀጣሪ መሰሪዎች
እየታገዙ ውስጥ ለውስጥ ሕዝቡን በማነሳሳት ሲሰብኩበት የነበረ ጊዜ ነበር።
ይህ የወሬ ዘመቻ እየተካሄደ እንዳለ
ብላታ ሃይለማርያም ለብዙ ጊዜ ይዘውት የነበረው የጭቃ ሹምነት ለሌላ ባለተራ ሰው አንዲተላለፍ የበታች ሹሟምነቶች ስለወሰኑባቸው
በይግባኝ ከልዑል ራስ ስዩም ቀርበው ጸንቶባቸዋል።
ወቅቱም ልዑል ራስ ስዩም ይህን
ውሳኔ ያጸደቁባቸው ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት ሲሆን ወዲያውኑ አልሸፈቱም። ምቹ ጊዜ ሲጠብቁ ቆይተው ነገሩ ያልገባቸው
በየዋህነት ታቦታችን ለምን ከካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አንድትገባ ተደረገች ብሎ ሕዝቡ የተቆጣበት ሰዓት ጠብቀው ሸፈቱ።
ወዲያው የርሳቸው መሸፈት የሰማው
አማረ መለስ የተባለው የአፈመምህርን ልጅ ገድሎ ከብላታ ተዘነቀ። አብረው ጥቂት ከቆዩ በሗላ ባልታወቀ ምክንያት ተጣሉና እርስ በርስ
ተታኩሰው ብላታ የሽፍታነት ጓደኛቸውን አበራ መለስን ገደሉት።
እሱ እንደሞተ ባሻ ጉግሳ ፤ የዕብዩ
ወልዳይ የተባለውን አስከትለው ሸፈቱና ከብላታ ጋር ተቀላቀሉ። እንግዲህ እነዚህ ሁለቱም ወንበዴዎች የሸፈቱት ምክንያት ይህ ነው።
እንግሊዞች የሰበኩት መርዝ እውነት አስመስለው ሕዝቡን ሰብከው፤ ተከታይ አግኝተው ኩሓ የነበረውን ጦር ሠራዊት ደምስሰው ቀረጥ በዛብህ
በሽፍታ ተገፋህ፤ፍትሕ አጣህ… ወዘተ እያሉ ራሳቸው ሲፈጽሙት የነበረውን የፍትሕ ጉድለት ስራና የጭቃ ሹም ጉልበተኛነት ደብቀው የአማራ
ባለስልጣኖች በደሉህ፤ ሃይለስላሴ ከዱህ፤ረገጡህ… እያሉ ሕዝቡን አነሳስተው አምባላጌ ተራራ ላይ ወስደው ለጦርነት ማገዱት።
ብላታ ሃይለማርያም ኢትዮጵያ በጣሊያን
ስትወረር ነጻነቷን ስታጣ ክብሯ ሲደፈር ያልሸፈተው ነጻነት ሲመለስ በገዛ መንግሥታቸው ለምን ሸፈቱ? ለምን ነጻ ወጣሁ በማለት ነውን?
ለብዙ ጊዜ ከእጃቸው መዳፍ የነበረው የጭቃ ሹምነት ለባለተራ አንዲያስረክቡ በመደረጉ ለምን ስልጣኔ ተነጠቅኩ ብለው አንደሆነ እውን
ነው።ይህንን ድብቅ ቅሬታቸው ደብቀው ነው የዋሁን የኩሃ እና የመሳሰሉ አካባቢውን ሕዝብ መርተው ለጦርነት ያስነሱት።
ንጉሡ ሕዝቡን በደሉት ብለው የሚሉት
ንግግር ሕዝቡን ለመበደልም ሆነ ለመጥቀም መቸ ጊዜ አገኙና ነው? ንጉሡ አገሪቷን አንደገና ለማጋጋም ላይ ታች በሚሉበት፤ሥልጣናቸው
ገና በመላ ኢትዮጵያ ስር ባልሰደደበት ጊዘ ነው። ሃይለስላሴ ሙሉ ሥልጣን ለማግኘት የበቁት በ1934 ዓ.ም ጥር 23 ነው። ስለዚህ
ወያኔ የተነሳው በንጉሱ ስለተበደለ ነው ማለት አይቻልም። ራያም ዓፋሮችን እየዘረፉ ስላስቸገሯቸው ዓፋሮች ለባለስልጣናት አርዳታ
አንዲያገኙ አቤት ስላሉ፤ ባለሰልጣኖች ይህንን ዘረፋቸውን አንዲያቆሙ በማድረጋቸው ራያዎች የተቆጡበት ወቅት አንደነበርም መሰመርት
አለበት።
በወቅቱ እንግሊዞች ኢትዮጵያን ለማዳከም
ውስጥ ውስጡን ሲሰሩ በነበሩበት ሰዓት አንደነበረ አንኳን በወያኔ ሥር የተሰለፈው በወቅቱ መንግስት ስላልተረጋጋ ጣሊያን ሲለቅ ሽፍታ
በየቦታው አንደ አሸን ስለፈላ እየተዘረፈ ተቸግሮ ስለነበር መርሮት
ነበር። በተጨማሪም የነበረው የወቅቱን የእንግሊዞች የረቀቀው ፖለቲካውንም
አብሮ ያልገባው የዋህ ገበሬ ቀርቶ የጎበዝ አለቆቹ እነ ብላታ ሃይለማርያምም ቢሆን የእንግሊዞቹ የረቀቀ ፖለቲካ በቅጡ አልገባቸውም
ነበር።
እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ትግራይ
ትግርኚን ለመመስረት (ደጋማውን ኤርትራ እና ትግራይ) አስመራና ኬኒያ ናይሮቢ መሰረት ያደረጉ ወታደራዊ አስተዳዳሪዎች በ1933
በሎርድ ሞይን እና በከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ሎንግ ሪንግ ወዘተ….ወዘተ… የሚመራ አስገንጣይ ኮሚቴ ግንቦት ላይ መቋቋሙን ልብ
በሉ። ንጉሡ ገና ባልተደላደሉበት ወቅት ነው። ንጉሡ ከነዚህ ጋር ከመነታረክ ብለው ወደ አንግሊዝ መንግስት ቅሬታቸውን ጽፈዋል።
ወታደሮቹ ከስፍራቸው አንዲወገዱ እና ትግራይን ለማስገንጠል ሕዝቡን ለማነሳሳት የሚደረግ ሴራ ጣልቃ ገብነቱን አንዲያቆሙ ጽፈዋል።
ባንዳው ራስ ሃይለስላሴ ጉግሳ በአምባለጌ
የሰፈረው ኢትዮጵያ ሰራዊትን እወጋዋለሁ ብለው ፈርተው ዞር ብለው ስለነበር ለጣሊያን የገቡትን ቃል አፍርሰዋል ብለው ጣሊያኖች ሲሲሊ
ድረስ ወደ ጣሊያን ወስደው አሰሯቸው። እዛው ሆነው የትግራይ ሕዘብ በሃይለስላሴ መንግሥት ላይ አንዲነሳ ከነ ፊታውራሪ ይኩኖ አምላክ
ተስፈይ፤ከነ ደጃች ፋሲል ተፈሪ፤ከየራያው ደጃች አርአያ ድግላ ጋር መጻጻፍ ጀመሩ። አንግሊዞች መጀመሪያ በልዑል ራስ ስዩም በሗላ
በራስ ሃይለስላሴ ጉግሳ ትክሻ ትግሬን ከኢትዮጵያ ለማስገንጠልና ከኤርትራ ጋር ለማዋሃድ ያደረጉትን ጥረት በንጉሱ ጥበብ መክሸፉን
በተረዱ ጊዜ አሁንም የመንገዱን ፕላን ለውጠው ሌላ አዲስ መንገድ ቀይሰው በብላታ ሃይለማርያም ረዳና በባሻ ጉግሳ መንገሻ አማካይነት
ወያኔ የሚባል ድርጅት አንዲፈጠር አደረጉ።*
በማለት ከዚህ በሰፋ መልኩ ከበስተጀርባው
ያለውን ሽፋን አቶ በሪሁን ከበደ በሰፊው ተንትነውታል። እዚህ ላይ መጠየቅ ያለብን ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ *በብላታ ኃይለማርያም ረዳ ፊት-አውራሪነት በ1935 ዓ/ም
ትግራይን በአፄው ላይ እንድታምፅ ያነቃቃው የወያኔነት እንቅስቃሴ፤ በያኔዋ የአፄው የክፉ ቀን ወዳጅ ታላቁ ብሪታኒያ ማበር ጭምር ሲቀለበስ……. እናም የእነ ኃይለማርያምን ኢትዮጵያዊነት ጨፍልቀው የተነሱት እነ ስብሐት ነጋ፣ ያን ብርቱ የማህበረሰብ ክፍል ሰቆቃ ጠምዝዘው ከማህበረ-ባህሉ የተጣረሰ መንገድ መርጠው ሸገር ሲደርሱ፤ እነርሱኑ ካፈራ መሬት፣ የተቀለበሰውን ዳግማይ ወያኔ ረግጦ የሚነሳ ትውልድ እንደሚመጣ ዘንግተው ሰንብተዋል፡፡* እየነገረን ያለው እነ መለስ ዜናዊ
የመሩትና የቀለበሱት ዳግማይ ወያኔ “ኢትዮጵያዊ ነበር”!!! ዳግማይ ወያኔ ብቻ ሳይሆን ብላታ የመሩት ቀዳማይ ወያኔም አንደዚሁ
ኢትዮጵያዊ አብዮት ነበር። ነው የሚለው። በየካቲት 11, 1967 ዓ.ም የተመሰረተው ዳግማይ ወያኔ የተባለው መለስ ዜናዊ እና ስብሓት
ነጋ ቀለበሱት እየተባለለት ያለው “ኢትዮጵያዊው የወያነ ትግራይ አብዮት” ብቻ ሳይሆን
በንጉሱ እና በእንግሊዞች የከሸፈው ብላታ የመሩት ቀደማይ ወያኔም
ኢትዮጵያዊ ነበር ብሎናልቨተመስገን። ተጨባጭ ሰነዶች የሚነግሩን ግን የተመስገንን ተጻራሪ ነው። እራሰቸው ብላታ ሃይለማርያም
በካሃዲው በመለስ ዜናዊና በሰብሓት ነጋ የተመራው ለዳግማይ ወያኔ ያላቸው እና ያሳዩት ልዩ ፍቅር እና አክብሮት የተናገሩት የጋዜጠኛ
ተመስገን የተቃራኒው ነው።
ኤርትራን ያስገነጠለው በመለስ ዜናዊ
(ወያኔ ትግራይ መሪ) የተመራው ለዳግማይ ወያነ አክብሮታቸውን ለመግለጽ በማክበር የራሳቸው (የብላታ ሃይለማርያም) የጦር ሜዳ መነጽር
በክብር ማስረከባቸው ትርጉሙ ምንድ ነው? ለእንዲህ ያለው ኢትዮጵያን ያዋረደ፤ ሰንደቃላማዋን ጨርቅ እያለ የዘለፈ፤ የባሕር በሯን
ያስነጠቀ፤በስጦታ ለጠላት ያስረከበ፤ አማራ የትግራይ ጠላት ነው ብሎ በመመሪያው ያጸደቀ፤ አማራ ያስገደለ፤ከስራ ያፈናቀለ ባንዳዎች
የተጠራቀሙበት እና የመሩት ቡድን እውነት ብላታ ሃይለማርያም ድሮ ለኢትዮጵያዊ ዐላማ ታግለው ከነበረ እና መነሻቸውም ያ ከነበረ
አንዴት ትብሎ ነው *የጀመርነውን ፈጸማችሁት* በማለት በ1984 የካቲት 11 ቀን በመቀሌ ከተማ የወያኔ በዓል ሲከበር በአድናቆት
እና በክብር የጦር ሜዳ የግል መነጽራቸውን ለመለስ ዜናዊ በሕዝብ ፊት ሊያስረክቡ የበቁት?
እስኪ ብላታ ሃይለማርያም ስለ ዳግማዊ
ወያኔ በባዓሉ በክብር እንግዳነት ተገኝተው የተናገሩትን ንግግር ቃል በቃሉ ወደ አማርኛ ተርጉሜ ላስነብባችሁ። እንዲህ ብለው ነበር፦
“እንደ እኔ የታደለ የለም። እነዚያ የመጀመሪያ ወያኔ መስራች እና ታጋይ
ጓዶቼ ይህንን ድል እና ይህችን የተከበረች ቀን ከኔ ጋር ኖሮው በዓይናቸው ቢያዩት ኖሮው አንዴት ዕደለኞች በሆኑ ነበር። እኛ የጀመርነው
የቀዳማዊ/የመጀመሪያው ወያኔ ትግል፤ በዳግማይ ወያኔ ተጠናቅቆ ድል ማግኘቱ ደግሞ የጓዶቼ መስዋዕትነት በከንቱ ፈስሶ አልቀረም።”
በማለት ብላታ ሃይለማርያም የወያኔዎችን
ጸረ ኢትዮጵያ ድል አንደ ድል ቆጥረው በባንዳዎቹ በወያኔ መሪዎች በእነ መለስ፣ስብሐት እና ስዩም መስፍን የተነደፈው ጸረ ኢትዮጵያ
ፖሊሲ/ንድፍ አንደ ድል ቆጥረው መርካታቸውን ጋዜጠኛ ተመስገን ያውቅ ይሆን? ተመስገን ደሳለኝ ሊነግረን ይችል ይሆን? (አሁን እስር መሆኑን አውቃለሁ።
ዕዱሉ ቢገጥመው መልሱን እጠብቃለሁ?
*የትግሬን መስቀል የመሸከም* ምናምን
ብሎ ሲጽፍ ትግራይ ሄዶ በነበረበት ወቅት ስለ ጉልተኞች እና ራሶች፤ መሳፍንቶች ደጃዝማቾች ፤ባሻዎች የመሩት አብዮት * ስለ ኢትዮጵያዊነት
የተመረኰዘ አብዮት አንጂ *መስፍናዊ አልገዛም ትግራዋይነት* ያነገበ አምቢተኛነት ከውስጥ አልነበራቸውም ብለው የነገሩት እነማን
ይሆኑ?
አሁንም በጽሑፉ ውስጥ ተመስገን
ስለ ዴምህት/ትህዴን የጻፈውን አንመልከት። ወልቃይት ውስጥ በትህዴን ምን አንደተደረገ ባለውቅም አንዲህ ይላል።
* ወልቃየት……ራሳቸውን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ ብለው በሚጠሩ ነፍጥ-አንጋች ፋኖዎች የተፈፀመ የመሆኑ እውነታ የህወሓትን የተሳሳተ ግምት ያስረግጣል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ የሳልሳዊ ወያኔ ወኪል እንደሆነ እየታመነ የመጣ የሚመስለው ስብስብ ሁመራ፣ ወልቃይትና ሽሬን በመሳሰሉ ከባቢዎች እንዳሻው የመንቀሳቀስ አቅም መገንባቱ ይነገራል፡፡ ድርጅቱ ከአስራ ሶስት አመት በፊት ወደ ኤርትራ በተሰደደው የህወሓት ሰው ፍሰሀ ኃይለማርያም ተድላ አስተባባሪነት መመስረቱ ይታወሳል፡፡ እንደ ትህዴን እምነት መሪው ፍስሀ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ መንግስት ደህንነቶች ነው የተገደለው፤ ከዚያን ጊዜም ወዲህ ሌላኛው የህወሓት አባል የነበረው ፀጋዬ ሞላ አስገዶም ከግማሽ መቶ ሺ አያንስም የሚባለውን ታጣቂ እንቅስቃሴ እየመራ እንደሆነ ንቅናቄውን በተመለከተ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ድርጅቱ ለፕሮፓጋንዳ ሥራው የራሱ ቴሌቪዥንና ራዲዮ፤ እንዲሁም ‹‹መጽሔተ ብስራት›› የተሰኘች በአማርኛና ትግርኛ የምትዘጋጅ የህትመት ውጤት እንዳለው ይታወቃል፡፡
ትህዴን የመረጠው የትግል ስልት ትክክል ነው አይደለም የሚለውን ሙግት ወደጎን ትተን፣ ኢትዮጵያን የሚመለከትበት መንገድ አስደማሚ ነው፡፡ በ1993 ዓ.ም
አጋማሽ በለቀቀው የፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ እንደገለጸው፣ ዓላማው ‹‹አንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነው››፤ የንቅናቄው ጠንከር ያለ የክልሉን የድጋፍ መሰረት ስናስተውል፣ የአንዲት ኢትዮጵያ መንፈስ የትግራዋይ ዋነኛው መለዮ መሆኑን ያስረግጥልናል፡፡ ‹ትግራይ የኢትዮጵያ መፈጠሪያ መሬት ናት› የሚለው የስብስቡ ድምፅ፣ ‹‹ትላንት የተፈጠረች›› ከሚለን ህወሓት ጋር ያለውን ተፃርሮሽ ፍንትው አድርጎ ያሳየናል፡፡ ፕ/ር
መሳይ ከበደም፣ ከሳምንት በፊት በበተኗት መጣጥፍ ለድርጅቱ ቡራኬያቸውን እንዲሰጡት ያስገደዳቸው፣ ይኸው የአንዲት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊነት ምስረታ ናፍቆት ይመስለኛል፡፡ *
Tuesday,
June 17th, 2014 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31331
እውነት
ተመስገንም ሆነ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ *ግምባር ሓርነት አደቦ ኤርትራ (Father Land Front for
the Liberation of Eritrea) ብሎ ራሱን የሚጠራ ኤርትራ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት እና የውጭ ጋዜጠኞች ወደ አስመራ
ከተማ በመደወል ትህዴን ስለ ተባለው የኢሳያስ የጸጥታ ልዩ ተወርዋሪ ቅጥረኛ ሰራዊት መሆኑን ለማረጋገጥ ከኗሪዎቹ ያገኙት የቃለ
ምልልስ ምንነቱን በማስረጃ የተደገፈውን ሰነድ ሲነጻጸር እነዚህ ሰዎች የሚናገሩትን ያወቃሉ? ያሰኛል። እስኪ ይህንን መረጃ ተመልከቱት።
ዴምህትን በተመለከተ በቅርቡ ከታወቁት
የአውሮፓ ጋዜጠኞች የተዘገበው አንዲህ ይላል፡
Two members of the Eritrean resistance, speaking via a secure connection, described conditions inside the country. said tension in the capital, Asmara, is high, with reports of trucks filled with Ethiopian “mercenaries” – from the Tigray People’s Democratic Movement (TPDM), known locally as Demhit, which Eritrea supports – ringing the city.*
October 25, Paris — This Saturday morning, two Eritrean journalists in exile and two European journalists, the British Martin Plaut and I had a telephone conversation for over an hour with movement activists Arbi Harnet Asmara. The appointment had been madeand coordinated by activists in Europe from the network of internal resistance and the interview took place via a secure connection with a thousand precautions; and of course a preliminary agreement on the guarantee of anonymity our stakeholders and the interference of their voice if we chose to broadcast the recording of our discussion. Their names were also changed. We were able to ask the questions we wanted.
These are the voices of men determined, thoughtful and well
articulated in Tigrinya. They pass the phone to each other, depending
on the question. Sami
gives a first response followed by Temesgen. The conversation starts with an update on
the tense situation in the capital. Last 48 hours, several reports indicate
deployment in the suburbs of Asmara sixty trucks and several hundred
infantry men of the Ethiopian Tigray rebellion called “ Demhit ”( Tigray People’s Democratic Movement,
TPDM ), which regularly plays role of auxiliary
militia of the Eritrean ruling junta. Having no confidence in his own army, Afeworki regularly
uses this force of tens of thousands of men, according to the UN
, to maintain order or do the dirty work. Sami and Temesghen confirm.*
በማለት ወደ ወታደራዊ ሰልጠና አንሄድም
ብለው በየቤታቸው የተደበቁ የኤርትራ ወጣቶችን ለመመንጠር * ግፋ * (ምንጠራ) እየተባለ በሚጠራ በተካሄደ የምንጠራ ዘመቻ፤ ድምህት
የተባለው ቅጥረኛ ከ60 በላይ የሚሆኑ የወታደራዊ የጭነት መኪኖች ተጭነው ወደ አስመራ በመዝለቅ ከተማዋን ከብበዋት አንደሰነበቱ
ነው ከላይ የናበባችሁት የገልለተኞች ጋዜጣዊ ዘገባ።
እነኚህ ናቸው በእነ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና በእነ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ኢትዮጵያዊ ሳልሳዊ ወያኔ፤ ምናምን፤ ምናምን እያሉ ቅጥረኞችን እያሞካሹብን ያሉት። ይህ ደግምግሞሽ አመል፤ ካሁን በፊት የነመለስ ወያኔን “ኢትዮጵያዊ” ነው እያሉ የወሎ፤የጎንደር፤የጎጃም የሸዋ የወለጋ ገበሬዎችን እያሞኙ መነግድ እየተጠረገላቸው እየመሩ አንዳመጡብን፤ አሁንም ከዚያ ያልተማሩ ጋዜጠኞች እና ምሁራን ወገኖች ያንኑ ሞኝነት እየደገሙ ማየት ያስገርማል። የጨነቀኝ ነገር፤ ያልተማረውስ ግድ የለም፤ የተማሩትስ አንዴት እናስተምራቸው?
በሚቀጥለው ክፍል ብርሃኑ ነጋ *The Eritrean regime doesn't interfere
in our affairs* በማለት ዴምህትም ከግንቦት 7 ጋር የጠበቀ ግንባር ፈጥሬአለሁ ብሎ ያሰራጨው ጽሑፍን እንመለከታለን። ብርሃኑም
ይህንን ውህደት (አንድነት?) የብርሃኑ ፕሮፓጋንዳ ለአመታት እያቆነጃጀ ሲያስጋባለት ከነበረው ወዳጁ ከአብርሃ በላይ ጋር
ያደረገውን ቃለ መጠይቅ እውነት መሆኑን ከእግርጌ በሚታዬው ርዕስ አረጋግጧል።
ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ( በቀኝ) ከኢትዮሚዲያ አዘጋጅ አብርሃ
በላይ (በግራ) በቅርቡ በጉደኛዋ የሲያትል ከተማ ሽር ጉድ
ጉባኤ! Berhanu Nega says Eritrea crucial to
building capacity
Ethiomedia October 22, 2014 |
ዴምህትና
ገብሩ፤ ሰብሓትና ገብሩ በኤርትራም ሆነ ስለ ዓሰብ ያላቸው የፖሊካ እና የታሪክ አመለካካት ልዩነት፤ ለማሳየት፤ የኢሳያስ ልዩ የጸጥታ ጥበቃ ተወርዋሪ ሃይል የሆነው ቅልብ ጦር እና ቅጥረኛው
ዴምህት እና ከእንግሊዞችና ከኤርትራኖች ደም ተደቅሎ የተወለደው ኤርትራዊው ስብሓት ነጋ የገብሩን አዲስ መስመር በመዝለፍ ፤ ዛሬም
ስለ ኤርትራ ጥብቅና ቆሞ ከጥንት ጀምሮ ወላጆቻችን ገምባሌ ታጥቀው አካኪ ዘራፍ እያሉ ድምበራችን እስከ ባሕር ዳርቻ ነው እያሉ
*አጉል ፈካሪዎች እና ገምባሌ ታጣቂ ወላጆቻችን “ሕመቕ” አንደግመውም (በትግርኛ የተጠቀመው ሕመቕ በእንግሊዝኛው ትርጉሙ
idiocity,
dumb,stupidity/ moronism) አንደግመውም ያለውን እና በኤርትራዊያን ፊት ስትጠጋ በፍርሃት የምትንቀጠቀጠው
ጉልበት የሌላት ኢትዮጵያ……በማለት ባልተገራ ባንዳዊ ምላሱ አገራችንን የዘለፈበትን በሚቀጥለው ሰሞን እንመለከታለን።
እነኚህ ከገብሩ አስራት ጋር በእውቀት
የማይገናኙ ደናቁርት፤ ገብሩ አስራት ስለ ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ጉዳይ ተብከንክኖ መጽሐፍ በመጻፉ እና ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ የእነ
መለስ፤ ሰብሐት ፤ ስዩም መስፍን፤ ኢሳያስ አፈወርቂ ግልጽ እና የረቀቀ ደባ በማጋላጡ *ለኤርትራ* ቆመው አንዴት አንደጠመዱት የሰሞኑን
መግለጫቸው እና ቃለ መጠይቃቸውን እስክንመለከት ድረስ ደህና ሰንብቱ። የቁርጥ ቀን ወገኖቼ፤ በነዚህ ቆሻሾች ልባችሁ አይዘን። ጊዜ
ያልፋል። ሁሉም በሰራው አሳፋሪ ተግባር አንገቱን አቀርቅሮ ያፍራል። ኢትዮጵያ የታምር አገር ነችና በታምራትነቷ አንደ እነ መለስ
ዜናዊ እነ ስብሓት ነጋም ከምድር ዓለም ተሰውረው ከመሬት በታች ተቀብረው የምስጥ መጫወቻ የሚሆኑበት ጊዜ በጣም በቅርብ ነው።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን
ሰማይ አዘጋጅ) getachre@aol.com (Ethiopian
Semay)
No comments:
Post a Comment