Tuesday, October 28, 2014

በገብሩ አስራት መጽሐፍ ትችት “ክፍል 3”




በገብሩ አስራት መጽሐፍ ትችት “ክፍል 3”
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) getachre@aol.com


ዛሬ የመገንጠል ጥያቄን በሚመለከት አንመለከታለን። በተያያዥ ድርጅቱ ጥላቻ ጠጥተው በሰከሩ ግለሰቦች በመገንባቱ ገብሩ የደርጅቱ ጠባሳ እና ብሔራዊ ወንጀል በዘገበበት በዛው ቀጥልበት በሚያስብል መጽሐፉ ውስጥ ብዙ ነገሮችን አካቷል። “በመሪዎች ሰበብ”  ተከሰተ የሚባልለት “የ 1969 ዓ.ም ቀውስ/ሕንፍሽፍሽ” አውስቷል። ከገብሩ በተቃራኒ የተለየ ሃሳብ ያላቸው እነ ሃይሉ መንገሻ (ከመስራቹ አንደኛው) እና ብስራት አማረ የመሳሰሉት ከገብሩ የሚለይ ሃሳብ እንዴት አንደሚያቀርቡት ጊዜ ሲፈቅድ እንመለከተዋለን)። ገብሩ ይህንን አስመለክቶ በወቅቱ ድርጅቱ የፈጸማቸው የሰብአዊ  ነክ ጉዳዮችን በሚመለከት አንዳንድ ታጋዮቹ “የድርጅቱ ሰለባ ሆኗል”  ወይንም  “በርካታ የዚያ አካባቢ ወጣቶች ሓለዋ ወያነ/06/ በተባለው እስር ቤት ታጉረው እዛው ቀርተዋል።”  ወዘተ..  በማለት  ባጭሩ “ዳበስ፤ዳበስ” ቢያደርገውም፤ ከድርጅቱ መሰረታዊ ጥልቅ የሆነ ወንጀለኛ ባሕሪ ሲነፃፀር ጭራሽኑ አልነካውም ማለት እችላለሁ። 


በተለይ  አማራ በመሆናቸው “በሳዮናይድ መርዝ” ተገደሉ የሚባሉ በገብረመድህን አርአያ የተገለጸው ምስጢር እና (ድርጅቱ  ‘ሳዮናይድ’ መርዝ ለተለያዩ የድርጅቱ ሥራዎች ይጠቀም አንደነበር በእርግጠኛነት መናገር እችላለሁ። በድርጅቱ የሚፈለጉ ሰዎች ለመግደል የተላኩ ፈዳይን/ነብሰገዳይ ክፍሎች  ድንገት ግዳጅ ላይ እያሉ በላት እጅ ቢወድቁ ‘ሳዮናይድ/መርዝ’ ውጠው አንዲሞቱ ገብሩ ለፈዳያኖቹ ያድላቸው አንደነበር እራሱ አይክደውም።( ለምሳሌ እነ ቢኒያም ከብዙ አመታት በፊት ከ “ድወት” በትግርኛ  የተደረገው ቃለ መጠይቅ አስታውሳለሁ።)  በጥይት “ተጨፈጨፉ” የሚባሉ  በሺዎች የሚቆጠሩ (አማራ) ሙርከኞችም ሆኑ፤ድርጅቱ  ወደ ስልጣን ከመጣ በሗላ “የተፈጸመው እና አሁንም እየተፈጸመ ያለው  ‘አማራን የማጽዳት ዘመቻ’  በሚመለከት ይህ ዘግናኝ ትልቅ  የወንጀል ተግባር” ሰፊ እውቀት አንዳለው እርግጠኛ ነኝ። ለምን እንዳልዳሰሰው አንባቢ የየራሱ ግምት ቢኖሮውም፤ መልሱ የሚያውቀው ደራሲው  ብቻ ነው። በዚህ ሌላ ቀን እመለስበታለሁ። ምናልባትም ደራሲው  በዲሞክራሲ እና ሉዓላዊነት ብቻ በማትኰሬ ከመጽሐፉ መነሻ  ውጭ ነው ካለ፤ ለወደፊቱ በተባራሪ ሰነድም ሆነ በመጽሐፍ መልክ ቢዘግብልን የሚያስመሰግነው ነው እላለሁ።


ዛሬ የምንዳስሰው ትችት፤ ገብሩ መጽሐፉ በገጽ ላይ ከ52- 53 እና በሌሎች ገጸች ላይ ስለ የትግራይ ሪፑብሊክ ማቋቋም ስለ መሰረዙ ጉዳይ በዳሰሰው ጉዳይ ነው። ገብሩ አንደሚገልጸው “ማኒፌስቶ ተብሎ በሰነድ ደረጃ የቀረበው የድርጅቱ መርሐ ግብር ትግሉ ከተጀመረ ከአንድ አመት በሗላ በ1968 ዓ.ም. የካቲት ወር ላይ ሲሆን፤ለተራው ተጋይ እና ለሕዝቡ የደረሰው ግን በሚያዚያና በግንቦት ወር ላይ ነበር ይላል። ይህ ፕሮግራም የረቀቀው እና  የጸደቀው በጉባኤ ወይም በአባላቱ ስብሰባ ሳይሆን በነበረው አመራር ብቻ የተነደፈ መርሐ ግበር የያዘው ጽንሰ ሓሳብ ሲያብራራ፤   


 “ የአብዮታዊው ትግል ዓላማ ከባላባታዊ ስርዓትና ከኢምፔሪያሊዝም ነፃ የሆነ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ማቋቋም ይሆናል።(መግለጫ፤ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት/ትህነድ/ የመጀመሪያ ህትምት፤በየካቲት ወር 1968 ዐ.ም ገጽ 18 ገብሩ አስራት፤- ሉዓላዊነት እና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ገጽ 51)


የሚለው  “የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ ማኒፌስቶ ከታጋዩ ባጋጠመው መጠነኛ  ተቃውሞ  ከ6ወር  በሗላ የትግራይ አብዮት ዓላማ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ  ማቋቋም ይሆናል” የሚለው አንቀጽ  አንዲወጣ ተደረገ።” (52)  ስለሆነም  ህወሓት የመገንጠል ዓላማው ያኔ ባጭሩ ተቀጭቷል፡ በማለት ገብሩም ሆነ የተቀሩት የወያኔ አመራሮች እና ታጋዮች ይህንኑ ሲጽፉ እና በአጽንኦት ሲሞግቱ ይደመጣሉ። 


ያነን ከማየታችን በፊት፤  አቶ ገብሩ  አስራት እንደስቀመጠው “መጠነኛ ተቃውሞ” እንጂ “ሆ!” ተብሎ ዓይኑን  ያጉረጠረጠ ተቃውሞ አንዳልገጠመው  ገልጾልናል። እንዲህ ዓይነት አገር እና ዜግነትን የሚያፈርስ ማኒፌስቶ ሲነደፍ ለምን “ዓይን ያጉረጠረጠ” ተቃውሞ ከሰፊው ታጋይ ሊደመጥ  እንዳልቻለ ገበሩ የገለጸው ነገር የለም። ከብርቱ ተቃውሞ ይልቁ መጠነኛ ተቃውሞ ለምን ታዬ ? የሚል ጥያቄ  ጭሮብኛል። መጠነኛ ተቃውሞ በመታየቱ  ያንን ማኒፌስቶ የቀየሱት የድርጅቱ አመራሮች ያንኑን ዓላማ በሕቡም በግልጽም  አንደገና ተመልሶ ለማስረጽ  “መጠነኛ”  ተቃውሞ ተብሎ  በተገለጸው መሿለኪያ ‘ጓዳ ’ በማየታቸው ነደፉት የተባሉት አመራሮችና ተከታዮቻቸው ፡ተሰረዘ፡ የተባለው መርሃ ግብር ቀጣይነት አንዲኖሮው ያደረጉት ቀጣይ እንቅስቃሴስ ይኖር ይሆን? ይህንኑ አብራራለሁ።     


 “የትግራይ አብዮት ዓላማ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ  ማቋቋም ይሆናል” የሚለው አንቀጽ  አንዲወጣ ቢደረግም፤በተግባርና በእምነት ደረጃ ግን ድርጅቱ እስከወዲያኛው ድረስ ሥጋ አንዳልጠለጠለ አንበሳ በጥርሱ ውስጥ ነክሶት ሲጓዝ ታይቷል።


የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ብሎ ራሱን የሚጠራው ይህ የወያኔዎች /የአማጺያን ብሔረተኛ ድርጅት ገና ከማለዳ ‘የትግራይ ሪፑብሊክ” ለመመስረት ዓላማ አንደነበረው ግልጽ ነው። ከመስራቾቹ ጥቂቶች ‘ትግራይ በሸዋ ገዢዎች/በኢትዮጵያ ሥር መውደቅ የለባትም’ ‘ከትግራይ መውጣት የሌለበት መንግሥታዊ ሥልጣን በሚኒልክ በመነጠቃችን መልሰን ስልጣን መያዝ አለብን’፤ በማለት ከጥንት ወላጆች የተላለፈው ብሔረተኛነትና የሸዋ ቅራኔ ያነገበ ድብቅ ስሜት ባይኖራቸውና “ሥልጣን” የሚለው ብሔረተኛ ጥንስስ ከውስጣቸው ባይኖራቸው ኖሮ በድንገት ተጠንስሶ በጥንቃቄ ተመክሮበት በምስጢር ተይዞ ሱዳን ድረስ ተሂዶ ለሕትምት የሚያበቃ የምስጢር ጉዞ ባልተካሄደ ነበር። 


 እነ ገብሩና መሰል ተጋዮች እና ሕዝቡ የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ ተቃውሞ ስለገጠመው ባጭሩ ተቀጭቷል ቢሉንም፤ የብሔረተኛ ዓይነተኛ ባሕሪው “መለየት/መቧደን”  እና በአካባቢው/በክልሉ ያጠነጠነ ርዕዮት በማትኰር ገፋ ሲልም ‘መገንጠልን’ አንደ አማራጭ  የሚያቀነቅን መሆኑን አብዛኛዎቻችን የምንስማማበት ይመስለኛል። እየተኬደበት ያለው “መስመር” የሚሉትም ይኼው መስመር ነው። የብሔረተኛ ቀዳሚ ስራ ከአካባቢውና አጎራባች ማሕበረሰብ የሚከልልበት “አጥር ማበጀት ነው”።፡ያ እስከሆነ ድረስም የድርጅቱ መሰረታዊ “የመገንጠል ባሕሪ” አንደ ገብሩም ሆነ እንደ እነ አረጋዊ የመሳሰሉ የትግራይ ብሔረተኞች ሊሂቃን “ባጭሩ አንዲቀር አድርገነዋል” ይበሉን አንጂ ከድርጅቱ ባሕሪ የተነሳ የመገንጠል እና የጠባብ ስሜት ውስጣዊ እና ውጫዊ  ገጽታው ተለጥጦ እየሰፋ አንጂ እርማት አድርጎ ሲሸማቀቅ አልታየም። ይባስ ብሎ ንድፉን የቀየሱት አመራሮች “ነድፈን የመጣንበት የብሔረተኛነት ንድፍ  ከተቀማን ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም፤ ሁላችንም ወደ እየ መንደራችን እንበታተናለን” በማለት እስከመዛት የደረሱበት ምክንያትም ይኼው “መስመራቸው” አንዳልተውት ሳይደባብቁ እየነገሩን ነው። 


የህ ብሔረተኛ ቡድን እየለፈፈብን ያለው ዛቻና ጥንስስ አንደ ማስፈራሪያ አድርጐ የሚጠቀምበትም አንቀጽ 39 ብሎ የሰየመውን “ሰይፍ” በዓይናችን ላይ በማውረግረግ ነው። በተራዘመ ሂደት ቀስ እያለ ‘ሲችክላቸው’ የነበሩት የብሔረተኛ  ችካሎቹ  ውስጥ  የመጨረሻው የአጥሩ የዳርቻ ሲደርሱ “አንቀጽ 39” የተባለው  ቋሚ አንጨት ለመገንጠል እንዲረዳቸውም ‘በሕገ መንግስቱ መተዳደሪያ ሰነድ’ እነ ገብሩ ሲያጠናክሩት አንጂ “ሲሰርዙት” አልታዩም። ይህ ደግሞ የብሔረተኛ የመጨረሻ ግብ ፤በመገንጠል ስለሚደመደም ነው ። 



ድርጅቱ  ጫካ ውስጥ  እያለ በወቅቱ ከተደራጁት አገር አቀፍ ድርጀቶች አብሮ እንዳይታገል ለግንጠላው ሴራ አንዲያመቸው “ለግንጠላ ዓላማዬ የገፋፋኝ ኢትዮጵያዊ ድርጅት የሆነው ኢሕአፓ ባሳየኝ ኢትዮጵያዊ ትምክሕት ነው” (ትከክልኛው የገብሩ አገላለጽ ለማየት ገጽ 132 ያንብቡ) በማለት  አንደምክንያት ሲያስታክክባቸው (ገምጋም ናይ 10 አመት ጉዕዞ ኮሚኒስት ሓይሊ ህወሓት ማሌሊት -MLLT (የህወሓት ኮሚኒሰት ሃይል የ10 ዓመት ጉዞ ግምገማ ማሌሊት-MLLT በመስራች ጉባ የጸደቀ ሓምሌ 1977 ዓ.ም) ያሰፈረውን በገብሩ እና በአረጋዊ መጽሐፎች ተገልፆ  አንብበናል። እነ ገብሩ የመገንጠል መርሃ ግበሩ  “መጠነኛ ተቃውሞ”  ገጥሞት አንዲሰረዝ ሆኗል ይበሉን አንጂ፤ ፕሮግራሙ ቀረ ከተባለ በሗላም፤ ቢሆን፡ ለምሳሌ ኢሕአፓን የሚጠሯቸው ለረዢም ጊዜ “ዓባይ ኢትዮጵያ” በሚል “ፕሮፋይል” ስያሜ እንደነበር ገብሩ አስረድቶናል። ገብሩ በግልጽ አንደነገረን ፤ አንዲህ ይላል፡


“ ኢሕአፓን  “ዓባይ ኢትዮጵያ”  ወይንም  የትልቋ ኢትዮጵያ አቀንቃኝ በማለት አንጂ በስሙ አንኳን አይጠራውም ነበር። ይህ ስያሜ ከተሓህት ታጋዮች አባላት አልፎ አካባቢው ገበሬዎች ዘንድም ዘልቆ ነበር።”  ይላል። 


ይህ ባሕሪ የሚያሳየን፤- “የመገንጠል” ጠባብ ስሜቱ ትቶት አንዳልነበረ እና “ስም በመስጠት” (ካቶገራይዝ/ ፕሮፋይሊንግ  በማድረግ) ሕዝቡም  ”ኢትዮጵያ” የሚል ስም እንደጠላት እና መጥፎ ስያሜ አንደሆነ አድርጎ እንዲመለከተው “የባዕድነት” ስሜት አንዲሰማው ወደ ገበሬው ዘልቆ አንዲሰርጽ ማድረጉ “የመርሃ ግብሩ ድብቅና ግልጽ” ዘመቻው  አንዱ መገለጫ ባሕሪው ካልሆነ ልላ ምን ምክንያት ሊሆን ይችላል? 


 ገብሩ “የመብት መጋፋት” ብሎ  ቢያጠቃልለውም ፤ ከዚያ በጠለቀ ‘ይህ የረቀቀ  የባዕድነት ፖለቲካዊ  የስነ ሉቦና ዘመቻ ‘ ( በሕዝቡ ላይ የፏከተው የሕሊና አጠባ) ገብሩ እንዴት ይመለከተዋል? ገብሩ ሁለቱም ድርጅቶች ተጠያቂ ማድረጉ (ገጽ 77) ከምን የመነጨ ነው?  ተሓህት ትግራይን ለቆ አንዲወጣ  በተሓህት ሲጠየቅ “ግንኙነቱ አንዲሻክር” አስተዋጽኦ  አድርጓል (77) ወይንም  ቻሌንጅ በሚባለው  የኢሕአፓ መጽሔት እትሙ ላይ  የማይረባ ተሓህት (Bullshit TPLF)   እያሉ እስከመጻፍ ደርሰው ስለነበር ድርጀቱ ምን ያህል ጥላቻ አንደነበረው በዋቢነት መጽሔቱ የጻፈውን  ስድብ ለታጋዮች ይቀርብ ነበር……ለድርጅቱ የነበራቸው ጥላቻ  በርግጥም የሚያንጸባርቁ ነበሩ ፡…በዚህም ቅራኔው አንዲባባስ ሆኗል…ወዘተ  .. . የሚሉ  የገብሩ  ድምዳሜዎች ሃቅነት ቢኖራቸውም  (እሱ አንዳለው ለቅራኔው ማባባሻ ሊሆኑ ቢችሉም) ፤- “ ትግራይን ለቆ አንዲወጣ”  ተሓህት ኢሕአፓን መጠየቁ  ‘ሪፑብሊክ ትግራይን” ለመገንባት ያቀደው መርሃ ግብሩ  በምንም መለኪያ ከውስጣዊው ስነልቦና አንዳልተወውና ‘ኢትዮጵያ’ የምትባል አገር የሸዋ/የምኒሊክ የጠላት አገር ናት ከሚል ድምዳሜ የደረሰበት አመላካች ባሕሪው ነበር’  በሚል ሐረግ ቢተካው ትከክለኛ ስዕሉ  ለማየት ይረዳ  ነበር።  


ሆኖም ያንን ለማካካስ ሲባል ይመስለኛል፤ ገብሩ “…የትግራይን ሪፑብሊክ የማቋቋሙን ጉዳይ ማካተቱ አመራሩ የተጠናውቶት የነበረውን ጠባብነት ጥልቀት የሚያመለክት ነው።” (132) በማለት የደመደመው የጥቂት አመራሮች  “የጠባብነት ጥልቀቱ” ምን ያህል እና ከምንስ መነሻ የመነጨ አንደነበር ሳይተነትነው በደፈና አስቀምጦታል። ድርጅቱ ‘ትግራይ የኢትዮጵያ/የሸዋ አማራዎች ቅኝ ግዛት ነች’ የሚለው ለትግራይ ሪፑብሊክ መመስረት መነሻ ያደረገው ዓላማ ምክንያት በኢሕአፓ ትምክሕት መገፋፋቱ ሽፋን ያድርግ እንጂ፤ ገብሩ በትክክል አንዳስቀመጠው “አንድ ድርጅት ወይም አካል ስሕተት ሲፈጽም ራሱ የፈጸመውን ስሕተት ሌላ ወገን ተጽእኖ ስላሳደረበት ነው ብሎ ማመን አይቻልም።” (ገብሩ 132) ብሎ አንዳስቀመጠው መሪዎቹ ለግንጠላቸው ውጪአዊ አካል እንደ ሽፋን ቢጠቀሙበትም፤ በጥልቅ ሳይፈተሽ “ተድበስብሶ መታለፉ” (132) አማራሮቹ ከውስጥ ያመቁት ቀጣይ ዓላማ ደብቀውት አንዲጓዙ ረድቷቸዋል።


እንዳውም ድርጅቱ ጠባብነቱን በ1968 ዓ.ም አውግዞ አስቀርቶታል፤ ይባል እንጂ “ተሓህት በአስር አመት ጉዞው የጠባብ ብሔረተኝነት ዝንባሌ ተጠናውቶታል (130) የሚል በወርዒ ጉባኤ ላይ ጎልተው ለትችት ቀርበው ከነበሩት መወያያ ርዕሶች አንዱ አንደነበር ገብሩ ገልጿል። ይህም የሚያመለክተው ድርጅቱ ጥበቱ/ግንጠላው በ1968 ዓ.ም አቁሞታል ብለው የነገሩንን በ10 ኣመታት በታየው ጉዞውም እንዳልተወው ጎልተው ከታዩት (ለድረጅቱ በጠባብነት መጓዝ) የመከራከሪያ አጀንዳ ሆኖ መቅረቡ አመላካች ጠቋሚ ነበር። 


አንባቢ መገንዘብ ያለበት  “በጠባብ”  እና “የትልቂቷ ኢትዮጵያ አቀንቃኝ” መሃል  ያሉት የአገላለጾች  ውክልና/ ስሜት/ ቃላቶቹ ምን አያሉን አንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል ። አስገደ ገብረስላሴም በመጽሐፉ (ጋሕዲ) ያሰመረበት የተሓህት ከኢሕአፓ ጋር ያናከሳቸው መነሾ ባሕሪ ‘ጸረ ኢትዮጵያ/ጸረ አማራ’ መሆኑ ገልጾልናል። ገብረመድህን አርአያም ‘እነማን ነበሩ? አሁንስ?..” በሚል በላከልኝ የቆየ ሰነድ የሚከተለው ቁም ነገር የብሔረተኞቹ የሕሊና ቀውስ እና ምንነት በእንዲህ ይግለጸዋል። 


1969 መጀመሪያ ጀምሮወይንበሚለው የድርጅቱ ልሳን መጽሔት ላይ በተደጋጋሚየክርስትና ሃይማኖትና አማራውበሚል ርእስ ተጽፎ የሚወጣው ጽሑፍ፣የክርስትና ሃይማኖት የአማራው ዋና መሳሪያና የግዛቱን ህልውና ማስጠበቂያ ነው፣ በመሆኑም የትግላችን ጠላት አማራውና መሳሪያው የተዋህዶ ክርስትና ስለሆኑ አብረው እንዲጠፉ ማድረግ አለብንእያለ ያትት ነበር። ይህንን መጽሔት በሰፊው ለታጋዩና ለአባላቱ በማሰራጨት ሰፊ ቅስቀሳ አካሂዶበታል። በነሐሴ 1969 “ወይንመጽሔት አማርኛ ቋንቋም አብሮ መጥፋት እንዳለበት ሃተታ ይዞ ወጥቷል።



ወይንየምትለውን መጽሔት የሚያዘጋጁት ከፍተኛ የአመራር አባላት በፕሮፓጋንዳ ቢሮ ሆነው ለዚሁ ተግባር የተዘጋጁ ጽሑፎችን በስፋት የሚያሰራጩት፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና መለስ ዜናዊ ነበሩ። እነዚህ ሶስቱ የህ.... አመራር አባላት እብዶችና በጸረ- ሃይማኖት፣ ጸረ-አማራ ባህሪያቸውና አቋማቸው በሰላማዊው ህብረተሰብና ታግዩም ጭምር በግልጽ የሚታወቁ ናቸው።



የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ የሚመራውም በነዚህ ሶስት እብድ አመራሮች ነበር። ከዚህ በመነሳት መስከረም 1970 በጸረ-ሃይማኖት፣ በተለይም በተዋህዶ ኦርቶዶክስ ላይ ቅስቀሳውን በስፋት ለማካሄድ በማሰብ፣ ሕዝብ ያሳምናሉ ተብለው የሚታመንባቸውን ታጋዮች መርጠው እገላ ወረዳ መሬቶ ተብላ በምትጠራ ቁሽት ውስጥ ተሰብስበው ቦታ ተዘጋጅቶ ከላይ በተጠቀሱት ሶስቱ አመራር ሴሚናር ተዘጋጀ። በሴሚናሩ ላይ የሚከተሉት ታጋዮች ተካፍለው ነበር፤- በማለት 15 የሚሆኑ ታጋዮች ስም በመዘርዘር የአማራ (ኢትዮጵያዊነት) መሸሸጊያ እና መሳሪያ ነው ተብሎ በነዚህ አመራሮች መሪነት  በክርስትና ሃይማኖት ላይ ዘመቻ በማካሄድ፤ “ተስካር፤ሠርግ፤ጠበል፤የህጻናት ጥምቀተ ክርስትና  አንዲቀር፤ ቤተክርስትያናት በበዓል ጊዜ አንዳይቀድሱ በዚህ መሰረት አድዋ አውራጃ እንዳባጻህማ ወረዳ የሚገኘው እንዳሥላሴ ተብሎ የሚታወቀው ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን መሪ አባ ሃይለሥላሴ የሚባሉ ቄስ፣ሃይማኖታችንን አታርክሱት፣ የተቀደሰ ሃይማኖት ነውብለው ስላሉበቦታው የነበረ ጸጋይ በርሄ የሚባል ታጋይ በያዘው አጭር ጓንዴ ተኩሶ ጭንቅላታቸው ላይ በመምታት በሕዝብ ፊት ገደላቸው። ቀሪው ምእመናን ተደናግጦና በርግጎ ተበታተነ። ሃለቃ ጸጋይ በርሄ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የነበረውን ንብረትና ሃብት ጠራርጎ ወሰደው።



በተመሳሳይ፣ ዛና ወረዳ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን መሪ የነበሩት አባ ቄስ አርአያ ከአንድ 90 ዓመት አዛውንት ባህታዊ ጋር ሆነው፣እባካችሁ ሃይማኖታችንን አታርክሱብንበማለታቸው ከቢተው በላይ ጋር ተደራቢ ሆኖ የሄድው አርከበ እቁባይ ሁለቱን ንጹሃን ዜጎች በሕዝቡ ፊት ገደላቸው። በስብሃት ነጋ፤ አባይ ፀሃየና መለስ ዜናዊ የሚመራው ጸረ-ክርስትና ሃይማኖት ከላይ የተጠቀሱትን 15 ታጋዮች የተግባሩ ፋጻሚዎች በማድረግ በርካታ ቤተ ክርስቲያናትን አቃጥለዋል። ከአድዋ፣ አክሱምና ተምቤን አውራጃዎች ብዙ ቀሳውስትና ባህታውያን እንዲሁም ዲያቆናት ሌሊትና ቀን እየታፈኑ ተውስደው የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል።…….ካለ በሗላ



 ገብረመድህን ከገብሩ አስራት የሚለየው የሚከተለው ዘገባ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡



 የካቲት 1971 የህ.... 1ኛው ጉባኤ በተካሄደበት ጊዜ የተመረጠው አመራር ማለትም፤ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ስብሃት ነጋ፣ የፕሮፓጋንዳው ሃላፊዎች መለስ ዜናዊን እና አባይ ፀሃየን መረጠ። እነዚህ ሶስቱ ጸረ-ሕዝብ አመራሮች ሃይላቸውን እና ጉልበታቸውን

በማጠናከር ድርጅቱ ያወጣውን በርካታ አዳዲስ ፖሊሲ ግንባር ቀደም በማድረግ በሥራ ላይ ማዋል ጀመሩ። እነሱም፣የተዋህዶ ክርስትና ሃይማኖት የአማራው መሳሪያና መገልገያ ስለሆነ፣ እግዚአብሄር የሚባል ነገርም ስለሌለ፣ ከአሁን ጀምረን ከነፃ መሬታችን ጠራርገን ማጥፋት አለብን። ለወደፊትም የሃገራችን የትግራይ መንግሥት ሲቋቋም ሕዝባችን ከማንኛውም

አጉል እምነቶች ነፃ የሆነ ሃገር እንመሰርታለን በማለት የህ.... አመራር ወሰነ።…..”



በማለት በ1968 ዓ.ም የትግራይ ሪፑብሊክ እንመሰርታለን ያለውን የድርጅቱ ማኒፌስቶ በወጣ ከስድስት ወር በሗላ በተቃውሞ ተሰረዘ የሚሉን እነ ገብሩ እና አረጋዊ ሲመረመር ገብረመድህን አርአያ “የካቲት 1971 የህ.... 1ኛው ጉባኤ በተካሄደበት ጊዜ….ድርጅቱ ያወጣውን በርካታ አዳዲስ ፖሊሲ ግንባር ቀደም በማድረግ በሥራ ላይ ማዋል ጀመሩ። ይላል። አዳዲስ ፖሊሲ ከተባሉት መካካል ደግሞ ገብረመድህን ሲያብራራልን “የተዋህዶ ክርስትና ሃይማኖት የአማራው መሳሪያና መገልገያ ስለሆነ፣ እግዚአብሄር የሚባል ነገርም ስለሌለ፣ ከአሁን ጀምረን ከነፃ መሬታችን ጠራርገን ማጥፋት አለብን። የሚለው ሲሆን፡  ለምን ሲባል፦ለወደፊቱ በምንመሰርታት “የትግራይ ሪፑብሊክ” የአማራ መሳሪያ የሆነው “ተዋህዶ ክርስትና” (1971) እና “አማርኛ ቋንቋ” (ነሓሴ 1969)  ሕይወት አንዳይኖረው ለማድረግ መሆኑን ወይን በተባለው መጽሔት አንደተገለጸ ነግሮናል።



ይህ የሚያመለክተው ህወሓት እስከ 1971 የካቲት እና ባሻገር የግንጠላው ስራ በይፋም ሆነ ለግንጣለው የሚያመቸው አፍራሽ ስራው በአማራው እና ክርስትና እንዲዘመት ማድረጉ  እነዚህ “ኢትዮጵያዊነትን” በጠንካራ መሰረት ያስቀመጡ ሁለቱ ክፍሎች አንዲፈርሱ ተንቀሳቅሶ ተግባራዊ  ማድረጉን የሚያሳይ  አንደ እነ ገብሩ ወይንም መሳይ የድርጅቱ መሪዎች አንደሚሉት በ1968 ዓ.ም ከማኒፌስቶው ሰርዞታል፤ የሚለው የተሳሳተ ደምዳሜ መሆኑን መረዳት አንችላለን። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ገብሩ አንቀጽ 39 አስፈላጊነት ሲሰብክ እና ድርጅቱ ዓረናም ነድፎ በማኒፌስቶው የተንቀሳቀሰበት አንደነበር ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው። ገብሩ እስካሁን ድረስ ማርክሳዊ” የሆኑት ሐረጎች “ብሔር ብሔረሶብ” የሚሉ ቃላቶች እየተጠቀመባቸው እና ለወደፊቱም ኢትዮጵያ/ሕዝቧ በዛው ትንታኔ መተንተን አንዳለባት በአጽንኦት ይናገራል።  ትንታኔዎቹ ምን ትርጉም እንዳላቸው እስካሁን ድረስ ገብሩም ሆነ አንዳንድ ተቃዋሚዎች እና ወያኔዎች ስለ እነዚህ ቃላቶች ምንነት ዘርዝረው ሲገልጹልን አልሰማሁም። በይፋ የተተረጐመ ትንታኔ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።ሁሉም አንደ “ተናጋሪ ወፎች/ፔሮት፤ ከሚጮኹት ጋር እየጮኹ፤ ሲባል እየሰሙ ከማስተጋባት ሌላ “ምጥጥየዎቹ ተናጋሪ ዎፎቹም” ሆኑ  “አውራዎቻቸው” ይህ ነው የሚባል ትንታኔ እስካሁን ያስረዱን ነገር የለም። በቋንቋ የሰለጠኑ ምሁራኖች የሰማሁት የነዚህ ሁለት ቃላቶች ትርጉም ከነገብሩ አስራት በጣም የተለየና ተቃራኒ  አንደሆነ ነው። ተናገሪ ዎፎች/ፔሮት ጆሯችን ከማደንቆር ይቆጠቡ የምለውም ለዚህ ነው።


ድርጅቱ አማራውን እና ክርስትና ሃይማኖት እንዲዳከም በነዚህ ተቋማት እና ማሕበረሰብ ላይ የተለያዩ ጥቃቶች አንዲከናወኑ ማድረጉ፤ ለግንጠላው እንዲያመቸው አንደሆነ አንቆቁልሽነት የለውም። ይህም የግንጠላው ፍላጎቱ እንዳላቆመ ማስረጃ ነው። በማኒፌስቶው በግልጽ ያስቀመተውም ይህንኑ የሚያስረዳ ነበር።



“…ሕዝቡ በኢትዮጵያዊነቱ አያምንም ፤በግድ በሃይል ተይዞ  ለዘመናት በአንድነት የቆየ ነው። ስለሆነም አሁን ባለው የህብረት መልክ የህብረት ትግል ማካሄድ “ምኞትና የትምክሕተኞች ሀልም” ነው።…  ባለንበት ዘመን የነበረውን የብሔሮች ቅራኔ እየተባባሰ በመሄዱ እነዚህን በሔሮች በአንድነት እንዲታገሉ ለማድረግ በጣም አስቸጋሪና የማይቻል ሆኖ ይገኛል።” (መግለጫ -ት.ህ.ነ.ኣ.ድ- የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት የመጀመሪያ እትም የካቲት 1968 ዓ.ም  ገጽ XI) (የወያኔ ገበና መሕደር፤ ደራሲ ጌታቸው ረዳ)


ቀላል ምሰሌ ለመጠቀም፤- እስካሁን ድረስ በኢሕአፓ ጫንቃ መውረድ ያልፈለገው እና መሪዎቹንም አፍኖ መግደሉን የሚያሳየን አሁንም ድርጅቱ በ1968 ማኒፌስቶ እየተመራ መሆኑ እየነገረን ነው ማለት ነው፡፡ “የትግራይን ሕዝብ ከተቀረው ጋር ቀላቅሎ ጸረ ጭቆና ማታገል አይቻልም፤ አስቸጋሪም ነው” ፤ “በኢሕአፓ ትምክሕተኛ ባሕሪ ተገፋፍተን መገንጠልን መርጠናል” ወዘተ…. ብሎ ያመነበት ማኒፌስቶ  ፍቆ ቢጥለው ኖሮ ዓባይ ኢትዮጵያ ብሎ በሚጠራቸው ከፍተኛ አመራሮችና ታጋዮች የግድያ ወንጀል ባልፈጸመ ነበር።


እነ ገብሩ ታጋዮቻችን “ኢትዮጳያዊ መሆኑን አሌ በማይባልለት የማሌሊት ፓርቲ” (130) እየተመሩ በኢትዮጵያዊነት ታንጸው ደርግን አስወግደዋል፤ ቢሉንም፤ “…ሕዝቡ በኢትዮጵያዊነቱ አያምንም ፤በግድ በሃይል ተይዞ  ለዘመናት በአንድነት የቆየ ነው።” የሚለው የ1968 ማኒፌስታቸው ፤ መንግሥት ከሆኑ በሗላም ይህንኑ እምነታቸው በፓርላማቸው በግልጽ ሲደሰኩሩ እና ኢትዮጵያዊነት እና አማራውን ሰንደቃላማችን እና ታሪካችንን ንቀው ለናቂ አጋልጠውን ሲያበቁ፤ ያንንኑ ዘመቻም ለመሰል ተገንጣዮች እና ጸረ ኢትዮጵያ በር በመክፈት አንዲያስተጋቡላቸው ሰፊ መድረክ ተከፍቶ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ እሴት ላይ አፍራሽ ዘመቻ ተከፍቶብን አንደነበር ገብሩ እራሱ አይክደውም። በአውድዮ -ቪዲዮም የተቀረጸ መረጃ አለ።ሕዝቡ በጆሮው በዓይኑ አይቶ አድምጦ ሰምቶታል። ስለዚህ ገብሩም ሆነ ሌሎቹ “የመገንጠል ጥያቄው” ከማኒፌስቶ በመለስተኛ ተቃውሞ አንዲወገድ ተደርጓል፤ ቢለንም፤ የገብሩ አስራት “ዓረና’ ፓርቲ “ሪፑብሊክን” መመስረት የሚያስችል መብት አንቀጽ 39 በማኒፌስቶአቸው አንኳ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተሸክመው እየተጓዙበት አንደነበር (ምናልባትም አሁን ማኒፌስቶው ማግኘት አልቻልኩም ቢዘረጉት ጥሩ ነበር!) ገሃድ ነው።


አንኳን እና እነ ዓባይ እና ስብሐት እነ ገብሩም በዓረና ድርጅት ማኒፌስቶ አንዲሰፍር አድርገውት አንደነበር የሚታወቅ ነው ማለቴ ነው። አንቀጽ 39 ለማስገንጠል የተዘጋጀ መሳሪያ ካልሆነ ሌላ ግብ ምን አለው? ብለን መጠየቅ አግባበነት አለው።



“ የአብዮታዊው ትግል ዓላማ ከባላባታዊ ስርዓትና ኢምፔሪያሊዝም ነፃ የሆነ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ማቋቋም ይሆናል።  (የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ደርጅት መግለጫ (ተ.ሓ.ህ.ት) ገጽ ገጽ 18 የካቲት ወር 1968 ዓ.ም) የሚለው በ48 የተለያዩ ጉዳዮች እምነቶች/ደምቦች የታተመው ሕገ ደምብ/መተዳደሪያ/እምነት/መመሪያ (የፈላግችሁ ቃል ስጡት)  ከላይ የተጠቀሰቺው የመገንጠል ጥያቄ ከማኒፌስታችን አንዲወጣ ተደርጓል ቢሉንም፤-የሚከተለው ጉዳይ እና መተከል/ስነ ሃሳብ ግን ከማኒፌስቶአቸው/ ከቅስቀሳቸው/ ከመጽሔቶቻቸው እና እትሞቻቸው አልሰረዙትም ፤ስሕተት ነው ብለውም በጉባኤ ያላወገዟቸው ሰነዶች አሉ። 

ለምሳሌ አንዲህ ይላል።



“የአማራ ብሄር በትግራይ ህዝብ ላይ የምታደርገው ተጽዕኖ እንመልከት። በኢትዮጵያ ያሉት ጭቁን ብሄሮች በተለይ ብሄረ ትግራይ በጨቋንዋ የአማራ ብሄር የሚደረስባት ተጽዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመሄዱ በብሄሮች መካከል አለመግባባትና መጠራጠርን አስከትሏል” ((ት.ህ.ነ.ኣ.ድ) የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት (መግለጫ) 1968 ዓ.ም. ተ.ሓ.ህ.ት ገጽ 8-9) …” የትግራይ ህዝብ ለረዢም ዘመን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጐ ሲጠላ እና ሲናቅ እንዲሁም አድልዎ ሲደረግበት ቆይቷል። ይህ በደል ጨቋኝዋ የአማራ ብሔር ሆነ ብላ የመንግሥት መመሪያዋ አድርጋ ስትሰራበት የቆየች ሲሆን… የ ፫ሺ ዓመታት የሚያኮራ ታሪክና ባህላችን መመኪያቸውና መፎከሪያቸው  ሆኖ ይገኛል። ይህ  የታሪክ ስርቆት በአንድ በኩል የአማራው ብሔር መፎከሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ትግራይ ሕዝብ ታሪክ እንደሌለው ህዝብ እንዲያስቆጥረው የተደረገ የመንግሥት መመሪያ ነው። የትግራይ ሕዝብ ክብሩና መብቱ እስኪመለስለት ድረስ ትግሉ አያቋርጥም። ጨቋኝዋ የአማራ ብሔርም ጭቆናዋ እስካላቆመች ድረስ  ሕብረተሰብዓዊ ዕረፍት አታገኝም”” የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት መግለጫ ገጽ የካቲት ወር 1968 ዓ.ም.ገጽ  15-16) (የወያኔ ገበና ማሕደር- ደራሲ ጌታቸው ረዳ) የሚለው በኪነታቸው በሙዚቃ በድራማ፤በስድብ እና በግጥም ሲያሰራጩት የነበረ የቅርብ ጊዜ ሃቅ ነው።



ይህ በቅጥፈት የተተረከ እምነታቸው ከማኒፌቶአቸው እና ከድርጅቱ ጋዜጦች፤ድራማዎች፤እምነቶች እና አሰራሮቻቸው አንዳልተወገደ እየታወቀ እነ ገብሩ “ትንሿን ሐረግ” ተመዝዛ ተቆርጣ እንድትወጣ በመደረጉ “ተሓህት” በታጋዮች እና በሕዝቡ ተቃውሞ የመገንጠልን ዓለማ እንዲተው ተደርጐ ተጋዮች በኢትዮጵያዊ ስሜት ታንጸው ለዲሞክራሲ እና ለመብት እኩልነት ለማስፈን ደርግን አስወግደዋል፡ ብሎ ማለት አባባሉ አንደገና አንዲመለከተው እጠቁመዋለሁ። 


የአማራው ሕብረተሰብ የትግራይን ሕብረተሰብ ታሪክ በመስረቅ የታሪክ ስርቆት በመፈጸሙ፤ አማራው ሕብረተሰብ (ጨቋንዋ ብሔር) የሰረቀውን የትግራይ ታሪክ ለባለቤቱ ለትግራይ ሕዝብ እስካላስመለሰ ድረስ የአማራውን ሕብረተሰብ  “ህብረተሰባዊ ሰላም” እንዳያገኝ እንታገለዋለን” በማለት ከላይ በፕሮግራም የሰፈረው ለትግሉ መነሻና ዓብይ ምክንያት ስናስተያየው፤ “ለእኩልነት ታግለዋል” ተብሎ ሃውልት የቆመላቸው በእነ ገብሩ መጽሀፍ ፡የፍትሕ ተጋዮች፤  እየተባለላቸው ያሉት የህወሓት ተጋዮች (በተሰውት ላይ እያመጻደቁ ሽፋን መስጠት) ፍፁምነታቸው ለኢትዮጵያ አንደሆነ ማቅረቡ በጥርጣሬ ዓይን እመለከተዋለሁ።



ሰማዕታት ተብለው የሚነሱ ‘ሙታን የድርጅቱ ታጋዮች’ በሕይወት ቢኖሩ “አሁን በሕይወት ካሉት” ኢትዮጵያን እያመሷት ካሉት የወያኔ ተጋዮች እና ተከታዮች የተለዩ ነበሩ ብሎ ገብሩ የሚያምንበት ምን መሰረት ይዞ ነው?


እኛ የምናውቀው ገብሩም ሆነ መሳይ አመራሮች ይዘውልን የመጡ የተሓሕት ተጋዮች “ለዲሞክራሲ እና እኩልነት” ሲታገሉ ሳይሆን ለ22 ዓመት እያየናቸው ያለው፤ በትግርኛው ብገልጸው ይሻላል “ብርሰት” ነው ያስከተሉብን! (የዘር ማጥፋት፤ስደት፤ ሰቆቃ፤ሲኦላዊ ሕይወት፤ፍትሕ አልባ፤የሕገ አራዊት) መሳሪያና ታዛዦች እንዲሁም አስፈጻሚዎች ሆነው ነው ይህ አውዳሚ ተልእኮ ዘርግተው አባሪ፤ተባባሪ፤ዘራፊ አስዘራፊ፤ገንጣይ አስገንጣይ ሆነው የእነ መለስ ፤ስብሓት ጸረ አመራ ሕብረተሰብ ራዕይ ባፍራሽ ጎኑ ሲተባበሩ ነው እየታዘብናቸው ያለነው።


የድርጅቱ ከፍተኛ ኮለኔሎች እስከ ታች ተጋዮች ድረስ የምናያቸው የድርጅቱ ታጋዮች “የታገሉለት የራስ መጥቀም መነሻቸው ያደረጉት” ሥልጣን ፤አምባሲ፤ደህንነት፤ አገራዊ ማሕተም፤ ሰነድ፤መታወቂያ፤ አንዳፈለጋቸው ከትግል ጓዶቻቸው ጋር በመነጋጋር ወደ ውጭ አገር መጥተው ልጆቻቸው እና ትዳራቸው መስርተው፤ንግድ አቋቁመው፤ አሁንም “ለወያኔ ድርጅት” ቆመው አስፈላጊው መሰዋእት እና የገንዘብ፤ የሰላማዊ ድጋፍ እና ሞራል ሽፋን ሰጪ ሆነው እኛው ጋር እየኖሩ ያሉት በሕይውት ያሉት ሰሞኑን አንተ (ገብሩ) በክብ ጠረጴዛ ከእነ ኢሳያስ ዓባይ፤ኮለኔል ጉዕሽ ወዘተ… ጋር ሆነህ ቃለ መጠይቅና ውይይት ያደረጉልህ የወያኔ ደጋፊዎችና ታጋዮች ስናጤናቸው፤  “የተሰው የድርጅቱ ታጋዮች ለዲሞክራሲና ለፍትሕ” ሲሉ ነው የተሰውት ከምትላቸው አሁን በሕይወት ቢነሩ ከነዚህ የሚለዩበት ምን ይሆን ነበር?

እርግጥ ጥቂቶች የሉም/አልነበሩም ማለት ሳይሆን “ሟቾቹ” የተሰውት “ለፍትሕ እና ለእኩልነት፤ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት” ብለው የተሰው ናቸው የምትለው አባባል፤ በሞት ለሰናበተ ሰው ከልምድ የተወረሰ ባሕላዊ አባባል ከመሆን የሚያልፍ ትርጉም የለውም።  መስዋእትነታቸውም ሆነ አሁን በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ አሁን ከላይ የጠቀስኳቸው በሺዎቹ የሚቆጠሩ በሕይወት ያሉት ታጋዮችም ሆነ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የወያኔ ደጋፊዎች የሚለያቸው ነገር ቢኖር በጣም፤በጣም ‘እሚነት’ ነው።


ከቶውንም ተሰውተዋል ከተባሉት 50ሺዎቹ ታጋዮች አሁን በሕይወት ቢኖሩ ተጨማሪ ማሰሪያዎች ይሆኑ አንደነበር እንጂ የተለዩ ፡ሚሰሆች፡ ይሆኑ ነበር ብሎ ደፍሮ መናገር ከቶ አይቻልም። መለስ ዜናዊ በሕይወት ኖሮ አፍራሽ ሴራው ባናየው ኖሮ፤ አንደተቀሩት የተሰውት ታጋዮች ሳናየው ጫካ እያለ በመስዋእት እዛው ቀርቶ ቢኖር ኖሮ “እሱም” አንደገብሩ አባባል “ለፍትሕ ፤ለእኩልነት፤ለዲሞክራሲ እና ለኢትዮጵያዊነት” የተሰዋ ተብሎ አንደሌሎቹ አንደሚዘመርላቸው፤ የክብር ሃውልት አንደተሰራላቸው ሁሉ “ከኤንጅል/ከመላእክቶች” አንዱ ሆኖ  ይነገረን አንደነበር እና፤ እኛም አንደ “ተናጋሪ ወፎች” ያንኑ በመድገም ሳናየው “እንዘምርለት” ነበር ማለት ነው።   


ህወሓት በግልጽ ጸረ ኢትዮጵያዊነት ባሕሪውም ሆነ የመገንጠል ባሕሪው አሁንም ከሚያራምዳቸው አፍራሽ ውሳኔዎቹ አልተላቀቀም። ደርግን የአማራ ስርዓት አድርጎ በድርጅቱ የተነገረው ትምህርት እስከ መጨረሻው ድረስ አንዳለ ነበር። ከማኒፌስቶው ተሰርዛለች የተባለቺዋ “የመገንጠል ጥያቄ” ተሰረዘ የሚባለው ቅባት ድብቅ አውነታው አንዳይታወቅ ጋርዶታል።


ይህ በአማራ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት፤ጥላቻ ፤ጥቃት እና የውሸት ዘመቻ አሁንም በሥልጣን ላይ ባሉት ወያኔዎች ኩፉኛ እየተተገበረ መሆኑን እየተገነዘብን “ወያኔ ትግራይን የመመስረት ዓላማው በ1968 በተቃውሞ አስቀርቶታል” የሚለውን የገብሩ አባባል እና “ማሌሊት ኢትዮጵያዊ ድርጅት መሆኑን አሌ ባይባልም” (ገፅ 1310 ) ብሎ አፍ ሞልቶ መደምደም  እርማት ወይንም ጠለቅ ያለ ትንታኔ  የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። ቅድም አንደገለጽኩት የገብሩ አስራት ዓረና እና መሪዎቹ  እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የመገንጠል መብት በማኒፌሶቻቸው ማስቀመጣቸው ግልጽ ነው። እነ ገብሩ ይህ ኢትዮጵያዊነትን የሚያፈርስ አንቀጽ ኮሚኒስታዊና ጣሊያናዊ  ርዕዮት አንደሆነ ያውቃሉ። ከበርካታ አመታት በሗላ አንኳ አንቀጹ አስፈላጊ ነው ተብሎ ዓረና ማኒፌስቶ መቅረጹ ‘ለዋስትና መስጫ” አንቀጽ ነው ብሎ መግለጫ እና መልስ መስጠት ምን ማለት ነው? ለምን አስፈለገ?   


በግሌ አንደማምነው ገብሩ የመገንጠል ጥያቄ የሚያምን እና ኢትዮጵያዊነቱ  የሚክድ ስሜት አለው ብየ አላምንም። ከጎረፈው መጉረፍ ጊዜው በመሆኑ ግን አብሮ ጎርፎ ሊሆን ይችል ይሆናል። በዚህ ላይ ከኔ የምትለዩ ልትኖሩ ትችላላችሁ። ልትጮሁብኝ የምትኖሩ ወዳጆቼ ልትኖሩ ትችላለችሁ። በተለይ አሁን ከተገነጠሉ በሗላ የመገንጠል እምነት አለው ብየም አላምንም። ሆኖም የድርጀቱ ባሕሪ በጥቂት አመራሮች ምክንያት ብቻ የተነሳ የመገንጠል አዝማሚያ አንደነበር ገብሩም ሆነ መሰል አመራሮች ሊሰብኩን መሞከራቸው “ለድርጅቱ’ ጸረ ኢትዮጵያዊነትና ጠባብ አመለካካት በጥቂት ሰዎች አነሳሺነት የተጠነሰሰ ሳይሆን ስሩ እና መነሻው ሥልጣን ከትግራይ ወደ ሸዋ ለምን ተዛወረ በሚል በነ አሉላና መሰል የትግራይ ብሔረተኛ መሳፍንቶች ጊዜ የተነሳው መነሻ አንደሆነ እና ተያይዞ ቀስ እያለ እየፋመ፤እየተቀጣጠለ ተዳፍኖ ውስጥ ለውስጥ ሲራመድ የነበረው “ሥልጣን ከትግሬዎች እጅ መነጠቅ የለበትም” ከሚል መነሻቸው  ባቀረብኩት በአንድ ሕዝባዊ መድረክ ያቀረብኩትን ጥናት መመርመር አስፈላጊ ነው (የደረግ ጭካኔ ለጫካ መኮብለል የተደበቀው ጠባብ የትግራዋይነት ስሜት ሽፋን የመስጡን ሁኔታና አጋጣሚው አንዳለ ሆኖ)። 


የምርምር ወረቀቴን ለማንበብ አንዲመቻችሁ ከወደ መጨረሻ  ሊንኩን እጠቁማችሗለሁ። ገብሩም በዚህ የሚለው ካለ ልስማ።


ወንድሜ ገብረመድህን አርአያ ደግሞ ቀደም ብሎ በላከልኝ ሰነድ የሚለውን ላስቀምጥና ሃሳቤን ልቋጭ።


በህ.... ፕሮግራም በገጽ 16 ተጽፋ የምትገኘው ደርግንም የአማራ መንግሥት በማለት በመፈረጅ ታወግዛለች። ደርግ ግን የአማራ .... ይህን ሁሉ ውሸት የሚደረደረው ዋናው ምክንያት አማራውን ለማጥቃት የተቀነባበረላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማነው። በገጽ 16 መጨረሻ ላይ ጽሑፉ እንዲህ በማለት ያጠቃልላል፣ጨቋኟ አማራም ህብረተሰብአዊ እረፍትና ሰላም አታገኝምይላል።



ወይንየሚባለው የህ.... ልሳን መጽሔት 1969 መጀመሪያ በአማራው ላይ እንዲፈጸሙ በመሬት ላይ ተግባራዊ መሆን አለባቸው ተብለው በአጭርና በረጅም የትግል ጉዞ የተግባር ዝርዝር ሃታታ በስፋት በመዘርዘር አውጥተዋል።



ከተዘረዘሩትም አንዱ የአማራው ሕዝብ እረፍትና ሰላም አያገኝም ለመኖርም አይችልም የምትለው የህ.... አቋምና ፖሊሲ ይዛለች። .... በአማራው ላይ አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል። እርምጃውም አማራው ከመኖር ወደ አለመኖር ይለወጣል። በዚህ መሰረት በወይን መጽሔት የተዘረዘረው በጥር 1969 ወደ ተግባር ተለውጦ አማራው በተገኘበት መግደል ተጀምሮ ከዛም ወደ ወልቃይት ፀገዴ ተሸጋግሮ የዘር ማጥፋት ተካሂዷል።



1. ማንኛውም በህ.... ነፃ መሬት የሚኖር አማራ ከትግራይ ለቆ በአስቸኳይ ይውጣ። በሕዝብ ግንኙነት ከያሉበት እየተለቀሙ በርካታ በጡረታ የተገለሉ ጦር ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ ፊናንስ ፖሊስ፣ በሌላ የመንግሥት ሥራ ሲሰሩ የነበሩ በተለያዩ ቦታ ይኖሩ

የነበሩ፤ ከትግራይ ሚስት አግብተው፤ ልጆች ወልደው ብዙዎቹም ልጆቻቸው ለትዳር የበቁ የልጅ ልጅ ያዩ ናቸው። ይህ ድንገተኛ ዘረኛ የህ.... ፖሊሲ እንደተላለፈ አማራውም ከየቦታው እየተያዘ ሃለዋ ወያነ 06 ገብቶ ይጠፋል፣ ንብረቱም ይወረሳል።



የትግራይ መሬት ለትግራይ ሰዎች ብቻ በማለት ከሃገራችን ልቀቁልን ይላል። በትግራይ 1969 የተጀመረው አሁን አማራው ከተለያየ ቦታ እየተጠረገ ተገፍቶ፣ ተፈናቅሎ በረሃ ላይ ወድቆ ይገኛል። ስለዚህ ከመሬታችን ውጡልን የተጀመረው 1969 በህ.... ሲሆን አሁንም ይህንን ክልል ተብለው የሚጠሩ የረጅም ጊዜ ውጥን .... በተግባር እፈጸመው ይገኛል። ከህ.... ትግል መነሻ ጀምሮ እስከ ዛሬ አማራ ዘሩ እየጠፋ ነው።



2. .... አባይ ኢትዮጵያ ከትግራይ ውጣ ሲባል፣ ትግራይ ኢትዮጵያ እኛም ኢትዮጵያውያን ነን ብለው አንወጣም በማለታቸው ለጥቃት ተዳረጉ።ወይንመጽሔት 1969 ጀምሮ በተከታታይ የሚያወጣው ጽሑፍ በህ.... ፕሮግራም ላይ የተቀመጡ የረጅም ጊዜ እቅድ በመተንተን እና በማብራራት ለታጋዩ ለውይይት በማቅራብ ሲያብራራ፣ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ብሎ የሚናገረውን አማራ ማጥፋት ከሱም ጋር አብሮ የሚቀበረው አማርኛ ቋንቋ ይሆናል ይላል።



በህ.... ፕሮግራምና በወይን መጽሔት እንደተዘገበው፣ አማራው የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንደመሆኑ በግንባር ቀደምትነት ....አማራውን ማጥፋት ግዴታው ነው ይላል። ኢትዮጵያን ለማጥፋትና ከዓለም ካርታ ፍቆ ለማስወጣት አማራው ሲጠፋ ብቻ ነው በማለትወይን’ መጽሔት ይዘረዝራል። ከጎንደር /ግዛት ከወሎ ለምና ሰፊ መሬት የነጠቀው ወያኔ በፕሮግርራሙ መቅድም V ላይ እንደዘረዘረው እውን ሆኖለታል። በሰፊና ለም መሬት የተከበበች ትግራይየትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክነፃ ሃገር ማቋቋም ግብ አማራው ከጠፋ ተቀናቃኝ አይገጥመኝም በማለት የታቀደ የረጅም ጊዜ የስትራተጂ እቅድ ቀስ በቀስ ወደ ተግባር የሚለወጥ ነው።



የህ.... አመራር ኢትዮጵያን እገዛለሁ የሚል ተስፋም ህልምም አልነበረውም። ደርግ ተዳክሞ በራሱ ጉዞ እንደጠፋ .... በለስ ቀንቶት ግንቦት 1983 ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ እንደ ዋናው የፖሊሲ ፕሮጀክትና እቅድ 1984 መጀመሪያ በተግባር ላይ ዋለ። አማራውን ለብዙ ዓመታት ከኖረበት ቦታ ያፈራውን ሃብትና ንብረቱን፤ በትዳር ከኦሮሞው፣ ከሲዳማው፤ ከወላይታው ጋር ከተሳሰረበት ለአማራውነፍጠኛ፣ ተስፋፊየሚል ተለጣፊ ስም በመስጠት የአማራው ዘር እየተፈለገ በሁሉም እድሜ የሚገኙትን እየሰበሰበ በጥይት በመደብደብ፤ በገደል በመወርወር ፈጅቷል። ይህንን ተግባሩን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመቀጠል በቤንች ማጂና ጉራ ፈርዳ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽሟል። ሊገድላቸው ያልቻለውን ደግሞ የማንገላታት ተባሩን ቀጥሎ የአማራውን ብሄረሰብ እየነጠለ ከጉራ ፈርዳ፤ ከቤኒሻንጉል እንዲባረሩ በማድረግ ለክፉ ሰቆቃ ተዳርገዋል። .... ይህንን ሁሉ የሚያደርገው ከመመስረቱ ጀምሮ የወጠነውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ነው።



ይህንን ለመተግበር ወያኔ አስቀድሞ ያዘጋጀው እቅድ የአማራውን ቦታ ማጥበብ ነው። ትግራይ ከበጌምድርና ከወሎ ሰፊና ለም መሬትወስዳለች። ከወሎ ሰፊ መረት ወደ አፋር ተከልሏል፤ የጎጃም መሬት ለአፋርና ለሌሎች ተሰጥቷል፤ ሸዋ እንዳለ የኦሮሞ ሆኗል።  

በዚህ አይነት የአማራው መሬት ተከፋፍሎ የቀረችው መሬት የበሬ ግንባርም አታክልም። አንድ ነገር ካልተደረገ በስተቀር ነገ ደግሞ ከዚችው ከቀረችው መሬት ውጣ ሊባል ይችላል። .... ይህንን አማራውን የማጥፋት “Systematic elimination and genocide” ዋናው ፖሊሲ አድርጎ የተነሳው ገና ትግራይ በረሃ እንዳለ ነው። አማራውን መግደል፤ ካልተቻለም በዘዴ ማጥፋት ብሎ ያቀደውን አሁን በግልጽ እያስፈጸመው ነው።
 
 በማለት የትግል ቀኝ እጄ እና ወንድሜ የሆነው ገብረመደህን አርአያ የሚያረጋግጠው ሰነድ ድርጅቱ የመገንጠሉን ጥያቄ በፍጹም አንዳልተወው፤ ከላይ ባቀረብኩት ተጨባጭ የሰነድ ማስረጃና ድርጊቱ ማነጻጸር እንችላለን።አቶ ገብሩ እና መሰል አመራሮች ድርጅቱ የመገንጠሉን  ያያቄ ፍቆ ጥሎታል የሚለው ትንታኔ አምነው የሚጓዙ ተንታኞች ፤ ትንትኔአቸው “የመገንጠሉን ሐረግ ከማኒፌስተው አንዲወጣ ቢደረግም” በተግባር እየተተገበረ ያለው ግን ……ይኽ፤ይኸ፤….ነው“ በሚለው ቢተነትኑልን እና  አንደገና ትንተናቸው ለሁለተኛ ጊዜ በክለሳ ማበጠሪያ አንዲበጠር  ቢያደርጉ ገብሩም ሆነ ሌሎቹ የሚጽፏቸው ሰነዶች ሙሉዕነት ሊላበሱ ይችላሉ።


 ክፍል 4 ይቀጥላል። ለወያኔ መመሰረት ከባዶ (ወይንም በደርግ ጭካኔ ምክንያት የተጫረ ሳይሆን) መነሻ ሳይሆን ከጥንት ስር የሰደደ፤ እያመረቀዘ የተጓዘ መነሻ አለው። የትግራይ የመሳፍንት እና የጉልተኞች ስርዓት አቀንቃኝ የትግራይ ብሔረተኞች እነ መምህር ገብረኪዳን /ዶ/ርሰለሞን ዕንቋ/ዶ/ክንፈ አብርሃም የማሳሉ የሚጽፉት ወያኔ በጽሑፎቹ ያሰፈረውም የሚነግሩን መነሻው ከገብሩ ትንታኔ በመሰረታዊ ልዩነቶችና ትንታኔዎች የተለዩ ናቸው።


ደርግ ለትግላቸው ሽፋን ሰጪ ቢሆንም ዋናው መነሻቸው እና ተያያዥ ባሕሪው ለማወቅ ከፈለጋችሁ በመሰራት ላይ ካለው አዲስ መጽሐፌ የተገኘ የኔን የምርምር ወረቀት ለማንበብ ወይንም ለማድመጥ ሊንኩ ይኼው የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?” (ጥናታዊ ጽሑፍ) Getachew Reda Research Paper/audio Ye Tegre BihereteNoch Be Amara Lay Yalachew Tilacha Kemin YemeneChe New? Audio 7/13/2014

የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?” (ጥናታዊ ጽሑፍ) paper http://www.ethiopatriots.com/pdf/GetachewRedaTinatawiTigrieyochAmaratilache140706.pdf ስላነበባችሁኝ አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) getachre@aol.com(Ethiopian Semay)

No comments: