Saturday, July 26, 2014

አንዳርጋቸው/ግንቦት 7/ ባንዳ ነው አይደለም? አንዳርጋቸው/ግንቦት 7/ ባንዳ ነው አይደለም?



አንዳርጋቸው/ግንቦት 7/ ባንዳ ነው አይደለም?


አንዳርጋቸው/ግንቦት 7/ ባንዳ ነው አይደለም?


ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

አቶ ተድላ ትናንት ማታ Where is Ethiopian Character, Andargatchew Tsige is not Banda !!!” በሚል ርዐስ በስሞታ ተቃውሞውን ለEthiopatriots.com አዘጋጅ ወቀሳውን ሲገልጽ፤ ለኔም ሁኔታው ባይገባኝም በግልባጭ “ፎርወርድ” ያደረገልኝን ተመለክቼዋለሁ። እንዲህ ይላል፦

(“For sometimes I did challenge the editor of "ethiopatriot" to remove "Bekumu Yemote" photo of  Dr.Birhanu carrying a donkey on his shoulder. Ethiopatriots as the name attests  should be a "patriot" website not "anti Ethiopian".

Ethiopians are known all over the world by their fairness towards humanity. We have Ethiopian value. We even go to the burial of our mortal enemy. When someone is in trouble we are not going to add more trouble. We have a saying, "LeWedeke Zaf Misar Yebezabetale"………. I am really troubled by www.ethiopatriots.com Andargatchew and Birhanu "Banda T Shirt" still posted to welcome readers. Where is the Ethiopian character ???........ You do not need to support the G7 Movement but you need to hear the voice of Ethiopians all over the word. Andargatchew Tsige for whatever flaws he might have is not Banda. ) ይላል።

የግንቦት 7 አመራሮች እና የፓልቶክ/ድረገጽ ጀሌዎቻቸው፤ አንዲሁም ኢሳት የተባለው የግንቦት 7 የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫው ክፍል “ኤርትራን እና ስርዓቷ፤ መሪዋን እና ስብእናውን እያሞገሱ፤” ኢትዮጵያን በሚያንኳስስ መልኩ ለኤርትራኖች በመወከል፤ ፀረ ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋቡ በዩቱብ ተቀርፆ የተዘገበ ማሕደር ነው። ስለዚህም “ሳይልኳቸው ወዴት፤ሳይጠሯቸው አቤት” የሆኑ ስለ ጠላቶቻችን የሚሳሱ “ቡት ሊኪንግ” ስብስቦች ናቸው።


ኤርትራ ለኛ (ለኔ ልበል) እጅግ አደገኛ ጠላት አንጂ “ወዳጅ” የሚል ቃል የሚጠቀሙት የግንቦት 7 መሪዎች እና የኦነጐች ማጃጃያ ቃል በኔ ዘንድ ቦታ አንደሌለው ግልጽ ልሆንላችሁ እፈልጋለሁ። ለወደፊቱም ቢሆን ኤርትራኖች እኛ ያቀረብነውን “ዴማንድ/የይገባኛል/ ሉአላዊ ጥያቄዎቻችን ካላከበሩ “ኢትዮ -ኤርትራ” በሚል የየዋሃን “ወንድማማች” ስብስብ ማሕበሮች ወይንም  የግንቦት 7 መሪዎች እና “ጸረ ትግሬ” የፓልቶክ ጀሌ ወጣቶቻቸው ወይንም “የፖለቲካ ተቃዋሚ ነን በሚሉ ዛሬ የምናያቸው አዲስ አበባ ያሉትን “ዲፕሎማት ተቃዋሚዎች” ሳይሆን ፤ “በጉዞ ሂደት” በሚወለዱ በቆራጥ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች መሪነት በሚቋቋም “ኢትዮጵያዊ መንግሥት” “አዲስ ጦሪነት”  በመክፈት ኤርትራን “በማንበርከክ” አስገድዶ’ “የይገበኛል ሉአላዊ ጥያቄአችንን” እንደሚያስከብሩ ባንዳዎች አንዲያውቁት፤ ይህ ትንቢት በልቦናቸው እንደይዙት “ከሻዕቢያ እና መሰል ኤርትራኖቹ” ጋር ሆነው የሚያፌዙብን ባንዳዎች ሁሉ ተዋጊው ብዕራችን አንደማይተኛላቸው፤ በዚህ አጋጣሚ ይወቁት። ስለ ኤርትራ የሚሳሳ አንጀት ላላቸው ኢትዮጵያዊያን ጀሌዎቻቸው መምከር የምፈልገው ነገር፤ ከእኛ በላይ ስለማታውቋቸው፤ በማታውቁት ሥራ ገብታችሁ እያዳመጥናችሁ ካለው “ሳይጠሯችሁ አቤት፤ ሳይልኩዋችሁ ወዴት” ባሕሪያችሁ ተቆጠቡ። ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ አትሁኑ። ተረጋጉ!

ለኤርትራ ባንዳዎች የሚራሩ ቃላቶች ከሻዕቢያ እና ከወያኔ እየተቀበሉ “ወዳጆች ነን፤ጎረቤታሞች ነን” የሚሉ “ኤርትራኖች እና  ወያኔዎች ሲያሾሩብን” የፈጠሯቸው ስልታዊ ቃላቶች ኢትዮጵያዊያን ነን የምትሉ ወገኖች አነኚህ ቃላቶች ከጠቀም አንዲቆጠቡ ኣሳስባለሁ። ኤርትራኖች እና ወያኔዎች አነኚህ ቃላቶች ለምን አንደሚጠቀሙባቸው እና ‘ኢትዮጵያዊያንም አነዚህ ቃለቶች አንዲለማመዱዋቸው” በማድረግ ላይ የሚያደርጉት ይህ የረቀቀ ተንኮል፡ “ከአርበኞች እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች” ለወደፊቱ ወደ ኤርትራ ለመነጣጠር አድብቶ እየጠበቃቸው ያለው “ቀስት” አደገኛ መሆኑን ስለሚያውቁ (ኢሳያስ ይህንን ቀስት ይፈራዋል፤ለዚህ ነው ወጣቱ ሳዋ እየወሰደ እያሰለቻቸው የሚገኘው) እነኚህ የ “ማጃጃያ” የጠላት ስልታዊ ቃላቶች “ኢትዮጵያዊያን” ከመጠቀም አንዲርቁ አሳስባለሁ። ብዙ ያልተወራረደ ሂሳብ ስላለን ፤ ሂሳባችን እስክናወራርድ፤ድረስ የኤርትራ ጨው እንደለመደች ወደል ላም ምላሳችሁ ከመዘልዘል ተቆጠቡ።

ከላይ “ሊያልፍ ኰት ለብሶ ቆሞ የሚታየው ወጣት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኮሚኒስት ቻይና ለስልጣና በሄደበት ወቅት ነው”ድሮም አሁንም በጠላትነት ቆሟል።።

አሁን ወደ አቶ ተድላ አስፋው አስተያየት።

ወንድም አቶ ተድላ አስፋው ለኢትዮፓትርዮትስ. ካም አዘጋጆች  በሚመለከት፤ አዘጋጆቹ ስለ አንዳርጋቸው እና ስለ ብርሃኑ ነጋ አህያ በጀርባቸው ተሸክመው ‘ባንዳ’/በቁሙ የሞተ…. የለጠፉላቸው “ፓለቲካል ካርቱን” ቅሬታውን ለመግለጽ ዋናውን አቤቱታ ለነሱ ሲልክ ለምን በግልባጭ ለኔ አንደላከልኝ ባይገባኝም፤ ብርሃኑ አህያ በጀርባው ተሸክሞ መታየቱ የፖለቲካ ካርቱኒስቶቹ ለምን በዚያ ሁኔታ ሊያሳዩት አንደፈለጉ የፖለቲካ ካረቱኒሰቶች መነሻ ስለሚኖራቸው ተድላ አስፋው ትርጉሙ ካልገባው ማብራሪያ ይሰጡት ይሆናል። ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ ባንዳነት እና ስለ ኢትዮጵያ ጨዋነት አንስቶ ስለሚያሰማው አቤቱታ ሃሳብ አንዳለኝ ለማወቅ ከሆነ፤ ትንሽ ልበል።በዚህ አረፍተ ነገር ልጅምር።

Ethiopians are known all over the world by their fairness towards humanity. We have Ethiopian value. We even go to the burial of our mortal enemy. Where is Ethiopian Character?” አቶ ተድላ ለመለስ ዜናዊ የሙት መታሰቢያ ፀሎት ለማድረግ ወዳጆቹ አሜሪካኖች፤እና የመሳሰሉ ትልልቅ የውጭ አምባሳደሮች በተገኙበት በአቢሲኒያ ዋሺንግተን ቤ/ክርስትያን ቅጥር ግቢ ሲታሰብ፤ አቶ ተድላ ደጅ ሆነው ፀሎቱ ተገቢ እንዳልሆነ መቃወማቸው አቶ ተድላ አይስቱትም። እኔ ለምን ተቃወሙ አልልም፤ መቃወም አይደለም መለስ በመሞቱ ምን እንደዘገብኩ ሁሉም የሚያውቀው ስለሆነ ለመስ አዛኝ እንዳልሆንኩ የዘገብኩትን መለስ ብሎ ፋይሉን ማንበብ ነው። ሆኖም፤ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት አስመልክተው ኢትዮፓትርዮትን “Ethiopians are known all over the world by their fairness towards humanity. We have Ethiopian value. We even go to the burial of our mortal enemy.” ብለው “ኢትዮጵያን ቫሊዩ” የሚሉትን ኢትዮጵያዊ ወደ ጠላቱ የቀብርም የፀሎትም ቦታ ሄዶ ሀዘኑን የሚገልጽ ሕብረተሰብ መሆኑን ካወቁ አቶ ተድላ አስፋው እንደ “ጠላት እና ባንዳ” የሚመለከቱትን የመለስ ዜናዊ የሙት ጸሎት ስነስርዓት በተከበረበት ኢቢሲኒያ ቤተክርስትያን ድረስ ሄደው “ለዚህ እርኩስ “የማማለጃ- ፀሎት” አያስፈልገውም” ብለው ለምን ተቃዉሞ እና ጩሆትዎን አሰሙ? We even go to the burial of our mortal enemy.” ብለው ኢትዮጵያዊ “ቫሊዩ” የሚሉትን እርስዎ ሲያከብሩት አላየንም። ታዲያ በኢትዮፓትርዮትስ ጀርባ ላይ ሚዛን ያጣ አለንጋዎን ለማስጮህ ለምን ከጀሉ?  

 እስኪ ከእርስዎ ወደ አንዳርጋቸው ልመልሰዎት። ይሄ ጥያቄ አስቀድሞ መጠየቅ የነበረበት በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና ሰብአዊነት ልብ ለተሞላው “ኢትዮጵያዊ ቫሊዩ” ያውቅ ነበር ብለው ለሚከራከሩለት (ኢትዮጵያዊ ስነምግባር/ቫልዩ ከሚያከብሩት ኢትዮጵያዊ ነበር ብለው ከሆነ መላት ነው) ለአንዳርጋቸው ጽጌ መቅረብ የነበረበት ጥያቄ ነበር። ወደ እራሱ አንደበት ልውሰደዎት፦ አንዳርጋቸው ጽጌ ተድላ አስፋው የሚያደንቀውን የአንዳርጋቸው ኢትጵያዊ ጨዋነት እና ሰብአዊነት አንዳርጋቸው በራሱ አንደበት በድሮ ወዳጁ የሗላ ጠላቱ በመለስ ዜናዊ ላይ ምን ሲል ነበር? ፦

“መለስ ሚባል ሰው፤ከተቀበረበት ሥላሴ ቤተክርስትያን ወጥቶ፤መንገድ ላይ አንዲወረወር ነው ያደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ” ይላል አንዳርጋቸው ጽጌ ለሕዝብ ያስሰማው የቀድሞ በዩቱብ የተለጠፈው ንግግሩ። አቶ ተድላ አስፋው በኢትዮፓትርዮትስ ድረገጽ ስለ አንዳርጋቸው የተለጠፈውን ካርቱን አለመደሰቱን ሲገልጽ፤ አንዳርጋቸው “የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጨዋነቱ ወጥቶ ሬሳን ከሥላሴ ቤተክረስትያን መቃብር ቆፍሮ አውጥቶ መንገድ ላይ እስከመጣል የደረሰ ሕዝብ ነው”  እያለ የኢትዮጵያን ሕዝብ  “የሕዝብ ሞራላዊ ስነ ምግባር” በዓለም ፊት ሬሳ ከመቃብር ቆፍሮ መንገድ ላይ የሚጥል አረመኔ ሕዝብ ነው እያለ በሃሰት ሲያጎድፍ እና ሲዳፈር አቶ ተድላ ምን አሉ? አቶ ተድላ! ምነዋ ለዚያ ሕዝባዊ ኤቲከስ የሚያጎድፍ ጽያፍ ንግግር ሲሰነዝር ያኔ ምነዋ ዝም አሉት? የኢትዮጵያን ሕዝባዊ ቫሊዩ በአረመኔነት የሚከስ ሰው እና ቡድን የሰማሁ በኢሳያስ አፈወርቂ እና በጽንፈኛ ኤርትራኖች ምላስ ካልሆነ እንዲህ ያለ ድፍርት ሰምቼ አላውቅም።ምናልባትም እንዲያ ያለ አንደበት እዛው ኤርትራኖች ጋር እያለ የቀሰመው ተላላፊ የምላስ ባሕሪ ሊሆን ይችላል። ሕዝቡ ለመለስም አልቅሷል፤ ውጭ ያለው ተቃዋሚም ለአንዳርጋቸው አልቅሷል። ድንጉጥ ባሕል/ቫለዩ ይሁን ወይንም ለሁለቱም ወግኖ ይሁን ፤ ብቻ ሕዝቡ አዝኗል፤ “ለሁለቱም አልቅሷል፤አዝኗል!” ጉደኛ አንጀት! “ለአራጁም ለአሳሪውም ለሚዋሸውም፤ ለሚየስገነጥለውም፤ ለሚዶልትለትም፤ ለሚያጃጅለውም- ለሁሉም የማንጨበጭብ ልምድ እና አዛኝ እጅ! ለሁሉም የሚያለቅስ አንጀት ያለው ወርቅ ሕዝብ የት ይገኛል?! ነገ ኢሳያስ ወይንም አቦይ ስብሓት፤ ወይ በረከት ስሞን ቢሞቱ ያለቅስ ይሆን? ማን ያውቃል፡ ለመስ ካለቀሰ ለምን ለኢሳያስ አያለቅስም። ሁሉም ጠላቶቹ ናቸው። ለትርጉም የማያበጅ “ብሽቅ አንጀት!”

አቶ ተድላ አስፋው “We have Ethiopian value. We even go to the burial of our mortal enemy. Where is Ethiopian Character?” ብለው መጠየቅ የነበረበዎት ግየንቦት 7 አመራሩን ነው። ይህነን ለማድመጥ The Two Faces of Andargachew Tsige http://youtu.be/0VrFHs4GPvg ያድምጡ። እስኪ የተናገረው “ቫሊዩ” ወደ አንግሊዝኛ ይተርጉመት፡ ለፈረንጅ አድማጩ ምን ስሜት አንደሚሰጥ ንገሩን። እንዴት ነው ሞኞች እያረጋችሁን ለመቀጠል የምትፈልጉት? ፖለቲካውን ያለ እናንተ እኛ አንከታተልም እየመሰላችሁ ነው? አንደ ቂሉ ማሞ ብርሃኑ ትከሻ ላይ የተሰቀለው ወደል አህያ አይተው አንዲህ ያንጣጣዎ ምንድ ነው? ከሰይጣንም ፤ ከአልሸባብም ቢሆን ዕርዳታ ከሰጠን አንቀበላለን የሚሉት ግንቦት 7 መሪዎች “አህያ በትከሻቸው ላይ መጫኑ” ምን ያስከፋቸዋል?


አቶ ተድላ አስፋው፤ በመቀጠል፦ “Andargatchew Tsige for whatever flaws he might have is not Banda.” ይላል። ጽቡቕ! እስኪ ገፋ አድርገን ወደ ሗላ የገዛ እራስዎን ጽሑፍ አንዴ ጎራ ብለን አንቃኘው? Ginbot 7 has been on news recently after Dr.Birhanu’s leaked “embarrassing” audio and the interview Ato Andargatchew gave on ESAT this month. (Dr. Birhanu should apologize for the public (Tedla Asfaw) September 19, 2013 ) ብለው በጻፉት እንጀምር። “ኤምባረሲንግ” ብለው የሰየሙት የብርሃኑ ምስጢራዊ አውድዮ የስልክ ንግግር ተጠልፎ ለሕዝብ ይፋ የሆነውን ምስጢራዊው ሰነድን ነው። ለምንድነው ኢምባረሲነግ ብለው አቶ ተድላ የሰየሙት? መቸም ፖለቲካ ውስጥ የሚያሳፍር ነገር የባንዳ ስራ ነው እና የባንዳ ሥራ ነው ማለታቸው አንደሆነ እገምታለሁ ! አቶ ተድላ ይህንን አሳፋሪ ገበና ያሉትን እንዲህ ሲሉ አብራርተውት ነበር፤-

Dr. Birhanu has a budget of 500,000 dollar from bankrupt Eritrea. The budget is used for Ginbot 7 and also for ESAT. Most of us believed that ESAT has nothing to do with Ginbot 7, that is now history, Ginbot 7 owns ESAT.” እስኪ ይህነን ዘርዘር እናድርገው.
አንዳርጋቸው ችግር ውስጥ እያለ ለምን ይህንን ታሪኩን ትናገራላችሁ ካልተባልን በቀር ፤ መሪ ነበር እና ታሪኩን መነገር ያስፈልጋል። በጐ ጎኑን እናንተ ንገሩን (ደሞ ከሚገባ በላይ እየተተረከ ነው)፤ ሸካራ ጐኑ ደግሞ እኛ እንናገርለት። ሸካራ ጐን ከቤተሰብ እና ከወዳጅ አይጠበቅም። ከታዛቢ እንጂ። አንዳርጋቸው በመያዙ ግን ስለ ተደሰትን ሆኖ መተርጎመ የለበትም። እያወራን ያለነው “ፖለቲካ/ትግል ነው”። አፋችሁ ክደኑ “ሃሽ ሃሽ” ከሆነማ ፖቲካ ሳይሆን እየታገልን ያለነው የእግር ኳስ ጨዋታ ነው ማለት ነው። አንዳርጋቸው ድሮ የወያኔ  ሗላ ደግሞ የሻዕቢያ “ሳይለኩት ወዴት፤ ሳይጠሩት ምን ልናገር  አቤት!”  ነው የምንልበት ብዙ ምክንያቶች አሉ። አብዛኛዎቹ ለማወቅ በብዙ ጸሐፍት ስለተዘረዘሩ አልደግመውም። የቅርቡ እንኳ ብንመለከት፤ አንዳርጋቸው ከሚያደንቀው እና ከሚያሞግሰው
ከሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ እና ተስፋዬ ገብራብ ጋር አስመራ በነበረበት ወቅት (ለግንቦት 7 እና ኢሳቶች ኢሳያስ ወዳጃችን ነው የሚሉን። አንደ ዜና ማዕከልም በኢሳያስ የሚዶጐም ስለሆነ፤ ስለ ኢሳያስ መጥፎ ሥርዓት አንዲት ቃል ማውራት የተከለከለ ነው! ይኼ ደግሞ አንደ ሚዲያ ሃላፊነቱን ዘነግቶ ለግለሰብ/ላንድ ንጉሥ አሽከርነት ከማደር የተለየ አያደርገውም።)  በአፍሪቃ ውስጥ ያልታዬ ድንቅ መሪ ሲል ፤ በኢሳያስ ዱጐማ የሚተዳዳረው የግንቦት 7 በኢሳት ቲቪ ቀርቦ ምን እንዳለ ማስታወሱ ጠቃሚ ነው። የጥቁሮች መሪ ነበረው  “ማልካም ኤከስ”  እንደሚለው “በሃውስ ኔገር“ አንደበት በወረደ መልኩ አንዲህ ይላል፡

“የፕረዚዳንቱ ልጆች ዩኒቨርሲቲ ፈተና መግባት አቅቷቸው በቂ ውጤት ስላላገኙ፤አንደ ማንኛውም ኤርትራዊ $10.00 (አስር ዶላር) በወር እያገኙ ነው አገልግሎት የሚሰጡት።” ሲሳይ አገና እንዲህ ሲል አንዳርጋቸውን መልሶ ይጠይቃል፦
“ልጆቹ ውጭ አገር ሄደው ተምረው አያውቁም”? አንድም ልጅ አንኳን ፈረንጅ አገር ሄዶ ለመማር ቀርቶ ሱዳንንም አያውቅም”።”ሦስቱም ሳዋ በረሃ ሳዋ ነው የተማሩት….”
አንዳርጋቸው ስለ ኤርትራ ቅንጣት ነገር አያውቅም። አብርሃም የተባለው ትልቁ ልጁ “የኤርትራን አየር ሃይሉ ክፍል ባይነ ጥላ መስርያቤት ተሰጥቶት ባቱን ወክሎ የሚከታተለው እሱ ነው። በአባቱ ላይ ክጀላ እየተደረገ ስለመጣ፤ እሱን እዛው መድቦታል።” አንዳርጋቸው አንዳለው ልጁ $10.00 ዶላር ወይንም 30 ዶላር ወይንም 500.00 ናቕፋ የሚያገኝ ሳይሆን ልጁ ጥጋበኛ እና የፋብሪካዎች ሃላፊ ሆኖ በየቦታው በመዞር የአባቱን ሥርዓት እንዴት አንደሚረከብ በልምምድ ላይ ነው (አስተዳደሩምንም ሳይቀር በመቆጣጠር ሥርዓቱን እየተለማመደው ነው።። ታሪኩ ባጭሩ ላቅርብ፡ 
ልጁ አንኳን አውሮጳ ሱዳንም አያውቀውም ሲል አንዳርጋቸው በእርግጠኛነት እንደ አሳዳጊው ተከራክሯል። አንኳን የኢሳያስ ልጅ፤ የሥርዓቱ አገልጋይ ባለሥልጣኖች ልጆች ዓለምን ዞረዋል። አንዳንዱ ውጭ ይማራሉ። ቀልድ ነው።፡ የየማነ ማንኪ ባለቤት እና ልጆች ሁሉ የሚኖሩት ካናዳ ውስጥ ነው። (ያውም እኾ የኤርትራ ባለሥልጣኖች መቀመጫው ከተቀዳደደ ባረጀ የድሮ ፊያት ነው የሚጓዙት ብሎ ሲል እማ ያስቃል። ረንጅ ሮቨር፤ቢኤም እና መርሰዲስ አንደሚነዱ ከነፎቶግራፋቸው አንድ ቀን እለጥፍላችሗለሁ። ዝገርም እዩ! )።

በእግረመንገዳችን ስለ አብርሃም ኢሳያስ ስለ ልጁ ከተነሳ ይህንን እንፈትሽ።

ኤርትራ ውስጥ፤  ቀጽሪ ኤክስፖ” እየተባለ በሚጠራ የስርዓቱ አሽከሮች ማጃጃያ፤ እስክስታ ማውረጃ፤ የገንዘብ ማመንጫ የሆነ፤ ውጭ አገር የሚኖሩ ደጋፊዎች በየአመቱ የሚፈነጥዙበት ፈስቲቫል አለ። ታዲያ በሐምሌ 2013 (በፈረንጆቹ በኤርትራኖች የዘመን አቆጣጠር)  ማዝናኛዎች እና የከተማ መጠጥ ቤቶች ለፀጥታ እንዲያመች በጊዜ አንዲዘጉ በተደረገበት እና ከተማዋ ጭር ባለችበት ሌሊት ኢሳያስ እና ልጁ አንዲሁም የስርዓቱ አሽከሮች ልጆች እና አንጨብጫቢ ሃብታሞች ብቻ በኤክስፖው እና በመሳሰሉ ትልልቅ ሆቴሎች እየጨፈሩ እየበሉ እየጠጡ በነበረበት በኤክስፖው ቅጥር ግቢ ውስጥ ድንገት  የቶከስ ድምፅ ተሰማ። የፀጥታ ክፍሎቹ ተደናግጡ፡፡ ባካባቢው የነበሩ የሚዝናኑት ወጣቶች በመሰብሰብ ጥያቄ አጥብቀው ማን አንደተኰሰ ካልተናገሩ ችግር አንደሚገጥማቸው ተነገራቸው፡፡ አንድ ከነዛው ወጣቶች በድፍርት “ይህ እማ ካላችሁ  ኣብርሃም ኢሳያስ (የኢሳያስ አፈወርቂ ልጅ) ሽጉጥ አውጥቶ  ወደ ሰማይ ከተኰሰ በሗላ መኪና አስነስቶ ከግቢው ወጥቷል።  ሲል ነገራቸው፡፡ በማግስቱ ወሬው ወደ ከተማው ተዳረሰ። ሕዝቡም ስለ ዜናው በመገረም፤ የመሪዎቻችን ጥጋብ ወደ ልጆቻቸው መተላለፉ ማሳያ አሳዛኝ አጋጣሚ ማየታችን በጣም ይገርማል፡ አንሱን ማን ያስራል?  ኤርትራ አንዲህ የጠገቡ የመሪዎች ልጆች ታፈራለች የሚል ግምት አልነበረንም፤ በማለት በከተማው ውስጥ በሃሜት ውስጥ ለውስጥ መታማት ጀምሮ ነበር። 

 አብርሃም ኢሳያስ የተባለው ይህ በህር ልጁ ባለ ትዳር ነው (የ31 ኣመት ዕድሜ ጎልማሳ ነው)። ማይ ነፍሒ በተባለው ኮለጅ ትምህርቱን በማቋረጥ  አባቱ ወደ በየኩባንያ ህንጻ ሄዶ አስተዳደራዊ ልምድ እንዲቀስም በማድረግ ፤ ለምሳሌ  ሆርን ኮንስትራክሽን (Horn Construction Company) አንዲሰራ ተደርጓል፡፡ ኩባኒያው የሻዕቢያ ሲሆን  በጀነራል ዳሪክቶር ብርጋዴር ጀነራል ጣዓመ ጎይቶም ክንፉመቐለበተባለው ልክስክስ/ኮራፕት የኢሳያስ ቀኝ እጅ የሚመራ ነው። እንዲሁም  የመሳሪያ ተተኳሽ የጥገና ሥራ ሁሉ ልምድ እንዲወስድ ተደርጛል። “አባቱ ድንገት በሞት ወይንም በሕመም /በአደጋ ክፍተት ከታየ፤ የአባቱን ቦታ አንደሚተካ ቦታው እተመቻቸለት እንደሆነ እየተነገረ ነው።

ስለዚህ አቶ አንዳረጋቸው የኢያስ ልጆች ሳዋ ሄደው በ30 ናቕፋ እና በ500.00 ናቕፋ ደሞዝ እያገኙ አንደማንኛውም ድሃ ኤርትራዊ ይኖራሉ ብሎ ማለት “አሳፋሪ ውክልናዊ ንግግር ነው”። ይኼ “ሳይጠሩት አቤት ሳይልኩት ወዴት” የምንለው ወይንም በጣሊያኖቹ አነጋገር “ባንዳነት/ውክልና” ነው። ለመሆኑ አንዳርጋቸው ስለ ኢሳያስ ልጆች፤ ስለ ባለስልጣኖቹ መኪና ረዢም ጊዜ ወስዶ ማውራት ምን ይጠቅማል? እስኪ ስለሚያወራው የሳዋ የትምህርት ተቋም ምን ይመስላል? ቋንቋውን ለማይገባችሁ ለማትከታተሉ የሩቅ ሰዎች፤ “ሳዋ” የሚያፈራቸው ልጆች (YPFDJ የሚላቸው የሥርዓቱ ደጋፊ ወጣቶች) እነኚህን ይመስላሉ። ሁለቱም ግበረሰዶማዊ ሴቶች ናቸው።
YPFDJ Patriotism in Action
 እነህ ግበረሰዶማዊ ሴቶች ነው “ወጣቶች፤ወጣቶች፤ እያለ በመመጻደቅ ሊያቀርብልን የሞከረው”።

 ሌላው ስለ አቶ አንዳርጋቸው “ሳይጠሩት አቤት፤ ሳይልኩት ወዴት” ገላጭነት፦ ስለ ኢሳያስ ተክለ ሰውነት ደግሞ አንዲህ ይላል፡ “በማንኛውም አፍሪካ ውስጥ (በሞተር ሳይክል) ያለአጃቢ የማይሄድ፤ ያለጠባቂ የሚሄድ ፕረዚዳንት የማይታይበት አገር እኔ የማውቀው ኤርትራ ውስጥ ነው።” መንገድ ለመዞር “ፍሬቻ” እያሳየ እንደማንኛውም መንገደኛ ትራፊክ መብራቱን ጠብቆ ነው የሚጓዘው።” ይለናል።
ሲሳይ አገና፤ “ፕረዚዳንቱ መኪና ይዘው እየነዱ መንገድ ላይ ይሄዳሉ?
አንዳርጋቸው፤- “አዎ መኪና ይዘው እየነዱ ይሄዳሉ ።ዛሬ ፤አሁን። በመቶ ሰው የሚቆጠር አቅፎ ያለምንም መሣሪያ ያለ ምንም ጠባቂ ሽማግሌዎቹ ጋራ ተቃቅፎ… መንገድ ላይ ይሄዳል። መሳርያ የያዘ ፖሊስ ወይንም ሰው የማይታይበት ከተማ (አፍሪቃ ውስጥ) አስመራ ብቻ ናት። ” ብሏል እውነታውን በጨው ዓይኑን አጥቦ ልክ አንደ ሻዓብያ ካድሬ በሚመስል መልኩ ሲያስተባባል።
እውነታው ግን እንዲህ ይነበባል
Last year, a plethora of defections of high-ranking military and government officials hit the headlines. The most high-profile defection was that of Ali Abdu in November 2012. Ali held a key post as Minister of Information and had very intimate personal and political ties with Issayas, whom he never challenged. Another notable defection was that of two trustworthy Air Force pilots, Captain Yonas Woldeab and Captain Mekonnen Debesai. In early October 2012, they flew in Eritrea’s only presidential plane to Saudi Arabia and asked for political asylum.” ዓሊ ዓብዶ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ፤ ይህ ነው፤
ዓሊ ዓብዶ (እጁ እኪሱ ላይ ከትቶ ያለው ነው። ሁለቱ ኤሊያስ ክፍሌ እና ስለሺ ጥላሁን ናቸው። ከዚያ ከሕሊናችን ከማይፋቅ፤በጣም ዘግናኝ ከሆነው የኢሳያስ የዘር ማጽዳት ወንጀሉ ወዲያ ኢትየጵያዊያን ወደ እዚህ ጭራቅ አጅ ይነሳሉ ሚል ግምት አልነበረኝም። አጅ መንሳት ብቻ ሳይሆን - የአመቱ ምስጉን ሰብአዊ ሰው ተብሎ በኛ ሰዎች ይሞገሳል የሚል ሕልም አድሮባችሁ ያውቃል? ባንዳ የሚባል ቃል ምን አንደምትተረጉሙት ባላውቅም “ባንዳ” ማለት ይህ ክፉ ባሕሪ ካልገለጸው ምን አንደሚገልጽ አላውቅም። ዓሊ ዓብዶ የኢሳያስ የማስታወቂያ/የዜና ሚኒስትሪ/ሓላፊ እና የሥርዓቱ አፈ ቀላጤ  የነበረ ዛሬ ከድቶተት  “አውስትራሊያ” ጥገኝነት እየጠየቀ ነው። የግንቦት 7 ምስጢር እና የሌሎቹ ጉዶች  በደምብ ስለሚያውቅ- እሱን አግኝቼ ለማነጋገር  እሞክራለሁ (አሁን ባለበት ሁኔታ መረጋጋት ስላላበት እና ፖለቲካውም አስጠልቶኛል ብሎ ለአውስትራሊያ መንግሥት ስላመለከተ በቅርቡ ማግኘት ዕደሉ ቢጠብም  ለወደፊቱ የማግኘት ዕደል ይኖራል የሚል ግምት አለኝ።) በዚህ መልክ፤ ኢሳያስ እና ሕዝቡ ፤ኢሳያስ እና የሥርዓቱ ባለሟሎች አንዳርጋቸው ሊያቆነጃቸው ከሞከረው ስዕል ሰማይ እና ምድር ናቸው። 

ሲሳይ አገና ነገሩ እጅግ ስለሰቀጠጠው እና አውነታው እየተጋጨበት አንደሆነ ስለሚያውቅ፤ አንዲህ ሲል አንዳርጋቸውን ለማረም ይጠይቀዋል፦

“ግን አቶ አንዳርጋቸው፤ ከ…(እውነታው) አንዳይጋጭ። ባለፈው ጊዜ መሳሪያ የያዙ ማስታወቂያ ሚኒስትሩን (ሥርዓቱን ለመቃወም) ይዘውት ነበር። እሱ የተወሰነ የኩርፊያ ምልክት ነው። ያ ……(እንዲህ ባለ) ወታደር ባለበት ከተማ ወስጥ …..

አንዳርጋቸው ሲሳይን በማቋረጥ በጣም አሳፋሪ በሆነ የሥርዓቱን አፈቃላጤነት በሚያስብል  እንዲህ ይላል፡

“ዌል ሁኔታውን እናንተ ይህንን በተመለከተ የደረሳችሁበት ጥናት ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም፤ ግን እዛ ላይ የመጡ ወታደሮች ፤የመጡበትን ምክንያት ተነግሯቸዋል።መንግሥት ወድቋል ተብለው ያመጧቸው ወታደሮች ናቸው።….”

ሲሳይ አገና አንዳርጋቸውን በማቋረጥ፤

“መንግሥትን ለመጠበቅ?!”

አንዳርጋቸው “ አዎ! አንደዚያ ብሎ ነው ሐላፊያቸው ያመጣቸው። (ወደ አስመራ ሲጓዙም) ሲያልፉም፤ ባለፉበት ቦታ ሌላ ታንከኛ ብርጌድ እያያቸው ነው ያለፉት፤ “ለሥራ ተፈልገው ይሆናል” እየተባለ ነው ያለፉት። ማስታወቂያ ሚኒስቴር ሲደርሱ የተጠየቀው እና የተነገራቸው ነገር ምን አንደሆነ በተነገራቸው ሰዓት ላይ ምንም ለማድረግ ፈቃደኛ ያለመሆናቸው…ወደ መጡበት ቦታ በሰላም ተመልሰው ሄደዋል።”  ሲል  ዋሽቷል።  (በነገራችን ላይ ኢሳያስ የሰጠው ቃለ መጠይቅ ደግሞ “ወዴት እያቀኑ እንደሆነ አስቀድመን ነቅተንባቸው ነበር። አንዲያቆሟቸው ያላደረግንበት ምክንያት “ሁኔታው አስቀድምን ተነግሮን ስለነበረ ‘ይበልጥ አንዲበላሹ” ነበር ዝም ብልን አንዲያሳሉፏቸው ስንከታተላቸው የነበረው። አኔ ሰብሰባ ላይ አለሁ፡ አውቀነዋል። ስብሰባችን እስክንፈጽም እነሱ ተከታታዮች አድርገንላቸው ነበር።” ሲል ገልጿል። አንዳርጋቸው የተናገረው ግን የሻዕቢያ ራዲዮን ያሰራጨው የውሸት ፕሮፓጋንዳ ነው። ሆኖም ኢሳያስ እንደጠበቀው በቀላሉ (መልዕክታቸው ለሕዘብ በቲቪ ከማስተላለፍ ሊቀጨው አልተቻለውም) አልሆነለትም፤ ሰዎቹ “መልዕክታቸው በቲቪ አንዲተላለፍ አድርገዋል።” በሗላ ግን የውስጥ ሰላዮች አንደከዷቸው ስላላወቁ፤ በሽምግልና ድርድር በመግባታቸው ምክንያት ተኰላሸባቸው።

ለውጥ ፈላጊው ቡድን፤- የሥርዓት ለውጥ ለማድረግ ሕዝባዊ ምርጫ እንዲደረግ፤ እስረኞች እንዲፈቱ እና ኢሳያስ ሥልጣኑ ለሕዝብ እንዲያሰረክብ፤ ማድረግ ያለበት ቅድመ ሁኔታ የተጻፈ “አዋጅ” በአክሱማዊው የሻዕቢያ ቡችላ በሆነው የዜናው ክፍል ሃላፊ ገረዝጊሔር (ቅድመ ሁኔታውን በጠመንጃ አንዲያነብ ተገድዶ) አንዳነበበው የታወቀ ሆኖ ሳለ፤ያውም  መፈንቅለ ሙከራው በትላልቅ የኢሳያስ ጀነራሎች የገቡበት ፕላን ሆኖ- ነገር ግን በሗላ ቆይተው፤ ፈርተው ሃሳባቸውን በመለወጥ ፕላኑ እንዲኰላሽ ያደረጉት አብረው የመከሩ ጀነራሎች አንደሆነ የተዘገበ ነው (ልክ መንግሥቱ ሃይለማርያም መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አንዴት አንደከሸፈ ተመሳሳይነት)። “የሳይጠሩት ወዴት፤ሳይልኩት አቤት አለሁ ወዴት” የአንዳርጋቸው አፈ ቀላጤነት ግን የሻዕቢያ ዜና ማሰራጫ የተናገረውን በመድገም ውጥረቱን ሊያጣጥለው ሞክሯል።

በሕዝብ የተተፋው ጭራቁ ኢሳያስ በወጣቱ እና በሽማግሌው የታቀፈ ተወዳጅ መሪ ነው ይለናል። “ድጋፍ ስላደረገልን ብዬ አይደለም። በዓይን የሚታይ ነው” ሲል  የሻዕቢያን ዜና ደግሞልናል። የኢሳያስ ቀኝ እጅ አንደ እነ ዓብደላ ጃቢር የመሳሰሉ ሰዎች ‘በሚዩትኒው’ ሰበብ ተይዘው ደብዛቸው ጠፍቷል። የኤርትራ ሥርዓት ለአፍሪካ አርአያነት እና ለኢትዮጵያ የሚመኝላት “ኢሳያሳዊ አስተዳዳር” ነው የሚለን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፤  በዓይን የሚታየው፤ የኢሳያስ አፈወርቂ አውነታ ግን “ኢሳያስ” አያቶቹ የሚያክሉ ሽማግሌዎችን ቀይ ጃዊ እያስለበሰ የሚያስር ናዚያዊ ሥርዓትን ነው አንዳርጋቸው እያደነቀው ያለው። - ይህንን ይመስላል”


አንዳርጋቸው የሚመኝልን መጻኢት ኢትዮጵያ በኤርትራ ቅጅ ይህንን ኢምፖርት ላመድረግ ነው ( ወፌ ላላም እዛው በአንዳርጋቸው ታጋዮች ላይ የተፈጸመ አሁንም እየተፈጸመ አንዳለ ሰለባዎቹ በቃላቸው ነግረውናል)። አንዳርጋቸው እንደገና ይቀጥል እና “እዛ ላይ የታየው ትልቁ ችግር፤ ኤርትራ ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድክመት ነው። ነገ ጥዋት እኛ ሥራ መሥራት ብያቅተን ችግሩ እዛ ቦታ የተሰበሰብነው እኛ መሆናችን ነው የማውቀው። ድክመቱ የኤርትራ መንግሥት አይደለም።የኤርትራ መንግሥት መስዋዕትነት እየከፈለም፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃም፤”ጋንግ አፕ” እየተደረገበት፤የተለያዩ መዋቅሮች እየተደረጉበት፤በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች በእግራቸው ቆመው፤አገራቸው ውስጥ ያለውን አስከፊ ሥርዓት አንዲያስወግዱ የቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው ያለው። ነገር ግን ይህነን ድጋፍ በሚገባ መጠቀም የሚችል የሰው ሃይል መመደብ የሚችል ቀርቶ የነሱን ድጋፍ ፤የነሱን ድካም ከንቱ ያደረገው “የኢትዮጵያ ተቃዋሚ እራሱ ነው”።በነሱ (ኤርታራኖች ድጋፍ )በኩል በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት ነው።

ሲሳይ አገና -

 “በተቃዋሚዎች በኩል ያለው ችግርስ ተቀርፏል አሁን?”

 ቅድም የተናገርኩት እሱ ነው። የነበረው ትጥቅ ትግል በመፍታት የሚሰጠው ድጋፍ፤በሚገባ በመጠቀም በአገር ውስጥ ስፋት ያለው እንቅስቃሴ ማድረግ ወደ እሚችልበት ሁኔታ ማሸጋጋር የኛ ነው። በነሱ በኩል ከሚገባው በላይ ነው የሚደግፉት ያለው። ታይቶ በማይታወቅ! ካሁን በፊትም እኰ ትግል አይቼ አውቃለሁ። በኤርትራ በኩል የሚደረገው ድጋፍ ስመለከት ባሁኑ ሰዓት ላይ 4 ኮከብ እና 5 ኮከብ ሆቴሎች ውስጥ ሆኖ የሚደረግ ዓይነት ትግል አድርጌ ነው የማየው። የምትበላውም የምትጠጣውም ለሰራዊቱ በሚገባ የሚለብሰውን፤ ምን የሚለውን…….፤ ሌላ ቦታ እኮ ሻዕቢያ እራሱ (ትግል ሲያደርግ) ከምን አንደተነሳ እናውቃለን፦ ኢቭን ወያኔ።በዛ ደረጃ ኢሕአፓ (በሻዕቢያ) ሲደረግለት የነበረው ድጋፍ- በዛ ዘመን ስታወዳድረው፤ ከሚገባ በላይ የበዛ ነው ጭራሹ።

ሲሳይ አገና፡

 “ ኤርትራን በተለያዩ ሁኔታዎች ስንመለከት ከዓለም የተነጠለች አገር ነች፡እንኳን ከራሷ አልፋ ተቃዋሚን የምትደግፍበት ሁኔታ ….”

አንዳርጋቸው፦

“እርሾ እኮ ነው የሚያስፈልገው ለድጋፍ።(ድሮ) ስድት እና ሰባት ሰዎች እኰ መረረ እና የቆረጠ ነገር……፤ የተወሰ ሥልጠና እና የበሰበሰ ካርባይን እና ጓንዴ ይዘው እኰ ነው ሜዳ የተገባው። አሁን ኤርትራ ያሉት ተቃዋሚዎች ትጥቅ (የት የሌለ ነው)። ኤርትራ እኮ አንተን በቋሚነት መሳርያ አንድትሰጥህ ፤ምግብ አንድትሰጥህ ግዴታ የለባትም፤ መሆንም የለበትም።”

ሲሳይ አገና፤-

ኤርትራ ምን ልታገኝ ነው እናንተን የምትደግፈው? በናንተ በኩል ምን ልትሰጡ ነው?

አንዳርጋቸው ጽጌ፤-

ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያደረግሁት ንገግር ሲገልጽልኝ “ እዚህ  የምትመጡት በኤርትራ መንግሥት ጭንቅላት አመለካካት እና በኤርትራ ሕዝብ ጭንቅላት እምነት እና አመለካካት ኤርትራ ኢትዮጵያን ፤ ኢትዮጵያ ኤርትራን በጣላትነት አንዱ ኣንዱን ፈርጆ ወያኔን ለማዳከም እዚህ ቦታ ላይ የምትመጡ ከሆነ፤ ወይንም ደግሞ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎችን የሚፈልጋቸው፤ ወያኔን አንዲያደክሙለት ነው የሚል እምነት ከሆነ እዚህ የምትመጡት፤ሁላችሁም ተሰብስባችሁ ወደ እምትፈልጉበት ቦታ መሄድ ትችላላችሁ።” (አንባቢ ሆይ! ኢሳያስ ምን ማለቱ አንደሆነ ተረዱለት።)

 “ኤርትራኖች አናንተን ሲረዱ ከናንተ ምን ያገኛሉ? ብልህ ለጠየቅከው.. (ሻዕቢያ) የአገር እና የሕዝብ ክብር የማንነት ክብር አለው (ከሻዕቢያ ጋር፡) ” ይላል አንዳርጋቸው ያልተባለውን ለማስተዋወቅ የምናውቀውን አሳፋሪ የሻዕቢያ ማንነትና ኩራት ምን መሆኑንን አንደማናውቅ”።

አውንታው ግን የተቃዋሚዎች ኤርትራ መደራጀት የሚፈልገው “ለኛ ብለው ሳይሆን ለነሱ ጥቅም ብለው እንደሆነ በምስጢር የተጠለፈው የብርሃኑ ነጋ ንግግር አድምጠነዋል። እሱ ከሚለው በጣም በራቀ መልኩ እውነታው እስኪ እንመልከት። ቲፒዲ ኤም/ዲምሕት የተባለው በኢትዮጵያ ሰንደቃላማ መሃል ላይ በጉልበቱ “የአክሱም ሃውልት” የለጠፈው የትግሬ ተዋጊ ለምሳሌ እንፈትሽ። አንዳርጋቸው ተቃዋሚውን ደካማ የሚላቸው ምን እንዲሰሩ በኢሳያስ እየታዘዙ እንደሆነ እንመልከት፤-
ማሕደራቸው አንዲህ ይቃኛል፦The Tigray People’s Democratic Movement (TPDM, known by its Tigrinya accornym De.M.H.T.) is one of half a dozen Ethiopian opposition groups stationed in Eritrea whose mission statement appears to have changed from bringing change to Ethiopia to fighting change in Eritrea by being President Isaias Afwerki’s last enforcement unit.
Over the weekend, TPDM was dispatched to Asmara to conduct routine roundup of Eritrean youth who have to be mobilized for military enlistment.  In previous dispatches, only TPDM members with passable Eritrean Tigrinya accents were recruited to conduct the roundup.  In this patricular mission, there appears to have been a breakdown and TPDM members with noticeable Tigrayan accents were roaming the Merkato neighborhood of Asmara and asking for “metawekia” and “mewasawesi“–Ethiopian words for “moving permit”– whose Eritrean version is “tessera” and “menkesakesi” respectively.In the ensuing altercation among Asmara residents and TPDM, shots were fired near Hamasien Restaurant.A TPDM soldier who was wounded by stone-throwing Eritreans was treated in Orota Hospital. When asked for his identification, he disclosed that he is an Ethiopian national and gave his address as Alla (near Dekemhare) and gave the name of his Eritrean handler.
Since the incident, the Isaias Afwerki regime has gone on full information-management campaign:

“መሬት ላይ ወርደህ ስትመለከተው የሚገርም ነገር ነው። ከኤርትራ በላይ ለኢትዮጵያ ወዳጅ መሆን የሚችል ማን ነው? አንደ ኤርትራ ለኢትዮጵያ የሚመሳሰል አካባቢ የለም። ኢትዮጵያ ከኬኒያ ጋር አትመሳሰለም፤ ከሱዳን፤ከጅቡቲ ጋር አትመሳሰልም። እነዚህ ወዳጅ አድርጐ ኤርትራን ጠላት አድርጎ የሚያይ የፖለቲካ ሃይል፤ ከድንቁርና የተላቀቀ አይደለም ብዬ አስባለሁ።በኤርትራም በኩል ካለ አንዲሁ።” (ሲል አንዳርጋቸው /የግንቦት 7 ፖሊሲ “ኤርትራን” አንደ ወዳጅ እንጂ አንደ ኢትዮጵያ አካል እንደነበረች እና እንደ አንድ ሕዝብ አድርጐ አንደማይመለከት ልሳኑ ከላይ ያረጋግጣል።)። ኤፍሩም ማዴቦ የተባለው የግንቦት 7 የሕዝብ ግንኙነት (ሦስተኛው ባለስልጣን) ሃላፊ የሆነው ሌላው የሻዕቢያ ባንዳም “ነግሮናል” ያውም ለነሱ ወክሎ “ነፍጠኞች እያለ እተሳደበን” (Do you know NEftENga? Yes, we have NefTeNgOch from the old system here inside us with in the opposition who wants your Assab…..!እያለ። ኦክላንድ ከተማ አሜሪካ ውስጥ በሻዕቢያ ሰብሰባ አዳራሽ ተገኝቶ! ወገኖቹን የሚዘልፍ ማን ነው? አዎ! ግንቦት 7ን የሚመሩት ባንዳዎች ናቸው! በመረጃ ከምላሳቸው የተገኘውን መረጃ እኮ ነው እያሳየናችሁ ያለነው! ፓልቶክ ላይ የስሜትና የጎሰኛ ዉሃ የሚጐነጭ ተሎ የሚጨፈለቀው “ፈዛዛ ቲማቲም” ሂዳችሁ ስለ ግንቦት አርበኞች እና ስለ ኤርትራ አገርነት እና ወዳጅ መሆን አውሩለት፡ ያደምጣችሗል። ብሽቅ ተቃወሚ!

አንዳርጋቸው ስለ ዓረቦች ፤ኤርትራና ኢትዮጵያ ሲተነትን ይገርማል። ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያዊ ሆኖ አማርኛ አጣርቶ የሚናገር ሰው መሆኑን እያወቅን “አማርኛን” የጠላት ቋንቋ ነው ብሎ በዓረብኛ እና በእንግሊዝኛ ሲናገር ምን ማለት አንደሆነ እያወቅን በዓረቦች የሚጣላ “የኢትዮጵያ ወዳጅ” ነው ይለናል። ዓረቦች በጠላትነት ያዩታል” ይለናል፤ ሲዋሸን። ኢሳያስ “አንጀራ መብላት አንኳ ከፓስታ ስልጣኔ” ጋር ያወዳደረ ደንቆሮ ናዚ_( ይህንን ለማንበብ በኔው ብሎግ ከሁለት ዓመት በፊት ተለጥፏል ፈልጋችሁ አርካኢቭ ላይ አንብቡት) “ዓረባዊ ስሜት የለውም፡ ኢትዮጵያዊ ወዳጅነት ይፈልጋል” ይለናል አንዳርጋቸው ስራው እየሰራለት በነበረበት ወቅት። ታሪኩን የምታውቁት ሁሉ እና የኤርትራ ታሪክ ያነባችሁ ከአንዳርጋቸው ጋር እንደማትስማሙ የታወቀ ነው። ብቻ ዘርዝሩ አልገባም።

አቶ ተድላ አስፋው  ወንድሜ ስለ ግንቦት 7 መሪዎች ለምሳሌ እነ ንአምን ዘለቀ እነ ኤፍሬም ማዴቦ (ከሻዕቢያ ጋር ቃል ኪዳን ሲገባ ያለው ፎቶ) አና የፓልቶክ ክፍሎቻቸው
ስለ ኤርትራ እየተወከሉ በባንዳነት ሥራ አፈቀላጤ እየሆኑ እኛ ጠላት ስንለው እነሱ “ጠላታችን አይደለም፤ ያውም የአመቱ ሰው መባል ሲያንሰው ነው” ፡ እያሉ እኛን “ነፍጠኞች/የድሮ ርዝራዦች/ትምክሕተኞች” እያሉ ከጠላቶቻችን ከሻዕቢያ ጀሌዎች እና መሪ ጋር እየተሻሹ የሚያደርጉት ስነ ምግባር ከማየታችን በፊት፤ እስኪ ያንን አንድበት አንደገና የግንቦት 7 ሚዲያው ኢሳት ባንተው ሸጋ አገላለጽ አንመልከት፦

“We all remember when Tamagne Beyne of ESAT fundraiser/Activist answered this question long time ago by saying if ESAT is a Ginbot 7 media let it be, “Behonese”. Dr. Birhanu backed Tamagne positively thanks to the leaked audio that ESAT is financed by Ginbot 7. It is no more “Behonese”, ESAT is a media wing of Ginbot 7.” ግርም!

ይኸ ከሆነ ግንቦት 7 ደግሞ በሻዕቢያ የሚደገፍ ነው። ሻዕቢያ ላንዳንዶቻችሁ ወዳጅ ከሆነ አላውቅም ለኔ ግን ከወያኔ እኩል የማየው የኢትዮጵያን ሕልውና ለማጥፋት ዕድሜውን ሙሉ የሰራ ጠላት ነው። ከ9 ሚሊዮን ብር/$500፣000 (ያውም በስድት ወር ውስጥ ብቻ) በሻዕቢያ ለግንቦት 7 ሲሰጥ እሩብ የሚሆን ገንዘብ ለግንቦት 7 የፕሮፓጋንዳ ክንፉ ለኢሳት ራዲዮ እና ተቪ የተሰጠ ነው።ይህ ባንዳነት ነው። ኢሳት ለኢትዮጵያ ሕዝብ እያስተላለፈ ያለው የወያኔ ገበና የሚደነቅ ነው የሚሉ ሰዎች- መልስ አለኝ።  ከኢሳት ይልቅ ሻዕቢያ ከአስመራ በራሱ ጣቢያዎች የወያኔ ገበና ያጋልጣል። ታዲያ ያንን ስለሰራ ሻዕቢያም የኢትዮጵያ ሕዝብ  ዓይን እና ጀሮ ነው” ማለት ይቻላል? ኢሳት ስለ ወያኔ መጥፎነት ሲያሰራጭ አንደም ቀን ስለ ሻዕቢያ መጥፎ እና ወንጀል መዘገብ አይፈቀድለትም። ከዘገበ ግን ድጐማው ይቋረጣል ደሞዝተኞቹ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ። ታዲያ “ባንዳ” ማለት ጠላት ስለ እምንለው የሻዕቢያ ወንጀል ማውራት ካልቻለ፤ ስለ ጠላት ደግነት  ካሰራጨ ከዚህ ወዲያ ለጠላት ማደር ምን አለ? ለዚህ ነው ስለ ሻዕቢያ መጥፎነት በኢሳት መነገር የማይፈቀድ።ስለ ድግነቱ እና ዲሞክራትነቱ፤ሰብአዊነቱ/አፍሪካዊ አርአያነቱ…… ግን በወኪላቸው በአንዳርጋቸው በኩል አንዲነገር ተፈቅዷል። አንዲህ ያለ ለጠላት የወገነ ሚዲያ “ባንዳ” ካልተባለ ሌላ ስም ምን ይስማማዋል?

ስለሆነም ነው ካንተው ከወንድም አቶ ተድላ አስፋው ጋር እንዲህ ስላልክበት ጉዳይ የምስማማው “Dr. Birhanu should be asked this coming Sunday why does he need to “Deceive” the public for almost three years. He should apologize for the public. ……One thing ESAT can not do is to criticize its financiers, Isaias Afeworki and Ginbot 7. As long as it does that it will be on air. The Diaspora fundraising has to go on because Isaias Afeworki is not a reliable partner.”

Ato Andargatchew is working hard to make sure Isaias finance is coming. That was the reason he came strongly to sell Isaias as “a man of the year of 2006″. Lionizing a dictator as a model for Africa “self rule and reliance”. If Ginbot 7 has such leadership in mind for future Ethiopia after Woyane it will not win any free and fair election.” ይህ ነው እኔም ባንዳዎች የኢሳያስ አስተዳዳራዊ ሞዴል ተመስጠው ለአፍሪአካ እና ለመጪዋ ኢትዮጵያ ምን እያለሙላት አንደሆነ ለመንገር ከሁሉም ጋር እየተጋጨሁ እውነቱን ለመንግር እየጣርኩ ያለሁ። ሰሚ ጀሮ ካለ! ከዚህ ወዲያ ባንዳናት አለ? ኤፍሬም ማዴቦም ልክ አንዳርጋቸው እንደሚለው ነው እየሰበከ ያለው። ለዚህ ነው ግንቦት 7 አመራሮች በተማሩ አደገኛ ባንዳዎች የተሞላ ነው የምለው። ስለ ኤፍሬም ማዴቦ እና ስለ የግንቦት አመራር አባል እና የኢሳቱ መሪ ንአምን ዘለቀ የኢሳያስን ስርዓት በማሞገስ እና ፖለቲካቸው ለማካሄድ ሲሉ በመላ የዓለም መንግሥታት ማሕበር የተወሰነው “ኢሳያስን የሚያወግዝ” ውሳኔ ያስተላለፈው መቀጮ (ውሳኔው ዋጋ ቢስ ቢሆንም) ከኤርትራኖች ጋር ሆነው በየአደባባዩ የተናገሩትን ከዚህ በታች ያለውን ማሕደር አድምጡ/እዩ።

Ephrem Madebo of Ginbot 7 Ethiopian opposition movement at Eritrean Festival in Oakland http://youtu.be/pW1mopFgf2k

Ephrem Madebo of Ginbot 7 and Aklilu Wondaferew of Shengo with Addis Dimts radio Host Abebe Belew http://youtu.be/M72Khe9NrdU

ከዚህ በታች ያለው በጥሞና የቪኦ እና የግንቦት 7 ጋዜጠኛው ፋሲል የኔአለም የተባለው የግንቦት 7 እና የ ኢሳት ጋዜጠኛ (የብርሃኑ ነጋ አምላኪ)  የሻዕቢያው ወዳጅ ለሆነው የኢሳቱ አቶ ንአምን ዘለቀ የሰጠው ቃል አድመጡት። በጣም ታፍራላችሁ፤ ያባሳጫቹሗልም። ግንቦት 7 ባንዳ ነው የምንለው ከዚህ ወዲያ ሌላ ባንዳነት የባሰ ጥብቅና ካለ ንገሩን። ንአምን አንዲህ ይላል ተጠይቆ ሲመልስ፤-

“ኢትዮጵያዊያኖች በሰልፍ መገኘት ብቻ ሳይሆን ‘ ሰልፉ ድጋፍ አንዲያገኝ፤ በሰሜን አሜሪካ  እና አውሮጳ በሚገኙ ሬዲዮኖች፤ ድሕረገጸች ሰልፉ ድጋፍ እንዲኖረው፤ ብዙ የማስተባባር ብዙ ጥረት ተደርጛል። ስለዚህም ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች ሰንደቃላማዎች አሸብርቀው፤ይዘው ብዙ ተገኝቷል።…ወጣት ኢትዮጵያዊያን በተለይ!” ይላል ንአምን።

ይህ ባንዳነት የዲያስፖራ ራዲዮኖቻቸው፤ ቲቪ፤ ድረገፆች በዚህ የባንዳነት ሥራ መሰማራታቸው ያለ ምንም ሐፍረት አንደ ጀብዱ  የኢሳት ጣቢያ ዋና ደይሬክተር ነግሮናል። ቃለ መጠይቁ ተከታተሉት፡(አሳፋሪ ፎቶዎችም ታያለችሁ)። Ethiopians Participation on Eritreans Demonstration http://youtu.be/caF_F0aSsXA
Shameless Ethiopians Participating at Shaabiya YPJDF Demonstration
Niamin Zeleke coordinator of the Shaabia Ethiopian Demonstration

 ለዚህም ነው አቶ ተድላ አስፋው ካሁን በፊት ““Ethiopians should ask how could Ginbot 7 leadership defend working closely with Isaias Afewroki?” ብልህ ስትጠይቅ፤ ከዚያ ጠላት ጋር አገራችን ከሚያጥላላ እርኩስ ጋር መስራት ብቻ ሳይሆን ስለ እሱ ተክለ ሰውንት ጥብቅና ቆመው “የ2006 ኣ.ም የአመቱ ሰው’ ብለው እነ አንዳርጋቸው እና እነ ….የመሳሰሉ ሰዎች ሲሟገቱ መስማት “የባንዳነት ስራ” ከዚህ ሌላ ካለ አስረዱን ብለን የምንሟገተው። ያውም አቶ ንአምን ዘለቀ በቃለ መጠይቁ ምን እንዳለ አድምጣችሁ ፍረዱ። (በዚህ ሁኔታ እኔ እና እሱ በኢመይል ተመላልስናል። የኤርትራን ሕዝብ ያለ ማዕቀብ እያጠፋ ያለው ኢሳያስ አፈወርቂን ሳይቃወም፤ በኢሳያስ እና አለቆቹ ተደረገ የተባለው የውሸት/የይስሙላ ማዕቀብ “የኤርትራን ሕዝብ ይጐዳል” ብለው ለባንዳዎች ውክልና መጮህ  አሳስቦአቸው ከነ ኦ ኤል አፍ እና ኦብነግ ባንዴራ ሰንደቃላማችንን አጎራብተው ጎን ለጎን እስያቆሸሹብን የባንዳ ስራ ሲሰሩ እና ስለ የማይረባ “የዩ ኤን  ማዕቀብ” መጮህ ከዚህ ወዲያ “ለጠላት ውክልና የለም። እነ ንአምን ሁሉ የግንቦት 7 መሪዎች እና አባሎች ናቸው። እነዚህ ሁሉ!

ወንድሞቼ ይህ ሁሉ የኤሊት ጋንግ ብልጣብልጥ ስብስብ ሕዝባችን አንዴት ለጠላት መንበርከክ አንዳለበት የሚሰሩት “የሳብ ቨርሲቭ” አንቅስቃሴ በሚዛናችሁ ፍረዱ! ይህ ብሽቅ፤ ቅጥረኛ ተቃዋሚ ሥራው ሁሉ ስታዘበው “ያበግናል፤ ያበሽቃል!”

ወንድሜ አቶ ተድላ አስፋው- አንተ ልበልህ እና   “Ethiopians should ask how could Ginbot 7 leadership defend working closely with Isaias Afewroki?” ብለህ ስትጠይቅ አንደገረምህ፤ እኛም ገርሞን የጠየቅከውን ነው ደግምን ድሮም፤ አሁንም ደግመን ስለ ኤርትራ መሪም ሆነ ፖሊሲያቸውን አንዲፈትሹ የምናሳስባቸው። ስሜት አደገኛ ፈረስ ነው እና “አልቦት አልቦት” “ጋልቦ፤ጋልቦ” እራሱ እስኪቆም ድረስ አንጠብቃለን።  በሚቀጥለው ጽሑፌ “Isayas  lapdog in Ze-Habesha website- training “rubbish Eritrean and Ethiopian nationalism” to the Ginbot7 Pets! በሚል ዶ/ር ፀጋዘአብ የተባለው የለንደን ኗሪ የሆነው የታወቀ ሻዕቢያ ቱልቱላ እና ጸረ ኢትዮጵያ ስለ ወሻከተው ጉድፍ እተነትናለሁ። ጠብቁኝ።  አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) Ethiopian Semay  ኢመይል ለማድረግ (getachre@aol.com) ይፃፉ።



No comments: