Red Terror Campaign |
Zeriu Kehishen of EPRP (the photo to the left) and Walleling Mekonnen (the photo to the Right) |
the two anti Ethiopia elements Lencho Leta of OLF (Left) and Meles Zenawi of TPLF (Right) |
አገር እንዲኖረን የማታጋያው ርዕየት ምን ይሁን?
ሽርባ
ሽሞፈና
“ወያኔ”ን ሲሻኝ “ትግሬ” ወይም
“ተሓህት” እያልኩ እንደተኪና ተወራራሽ ተጠቅሜበታለሁ - ድርና ማግ ስለሆነ፡፡ ተሓህት ድርጅታዊ መረብ ውሰጥ ያሉትን ትግሬዎች
ያጠቀልላል፡፡ ወያኔ የተሃሕት መነሻ ቅኝት ነው፡፡ ከተሓህት ውጭ ያሉት አብዘኛዎቹ ትግሬዎች በወያኔነት ያምናሉ፡፡ የግራ ተራማጆች
ካመለካከት፣ ዞገኞች ደሞ ከብልጠት - “ውግዝ ከመአርዮስ” ሊያስረግጡብኝ ይችላሉ - ይሁን፡፡ ለመግባባት ግን “ትግሬ”ን እየዘለላችሁ
“ወያኔ” ማለት ወይም ከዚህ ወዲያ ጽሑፌን አለማንበብ አማራጮች ናቸው፡፡ እንዲህ እያለ ብረገም አይቆጠርም፡፡ ተሓህት የትግሬነት
ጣጣ ብሎም ጥቅም ነው፡፡ “አይደለም” የሚሉ ካሉ ከሥልጣን ግብር የተገፉ ናቸው፡፡ አለያ ስዬ አብርሃና አረጋዊ በርሄ ከለገሠ ዜናዊ
ወይም ከስብሃት ነጋ የሚለዩበት ሂሳብ ምን ሊሆን? የዘር ብክነት የሌለበት ሰው ግን አይጣላኝም፡፡
የገጠመን የፖለቲካ ሁከት ትውልድ አስቆጠረ
፡- ሠላሳ ዓመት ዘለለው፡፡ ይህም ጠንቀኛ የፖለቲካ ሸበብ ያገራችንን አካላዊ ግዝፈት ሸርፎ መንፈሳችንን ከወግ በላይ እንዳልከሰከሰው
ነው፡፡ ባብዛኛው የትግሮቹ አካሄድ እንከን ይበዛበታል፡፡ የሌሎችን መብት በልጠውና ኢትዮጵያዊነትን አፍርሰው ምን ለመሆን? በሌላ
በኩል አካሄዳቸው ዝንፈት የማያሳይና በቆራጥነት የተያዘ ነው፡፡ በትግሬነት ብልጠት መሄዱን በግብርም በመንፈስም ነቅነቅ አላሉበትም፡፡
የተንጫጫ ቢንጫጫ አልገደዳቸውም፡፡
ተቀናቃኞች መንገዳቸው ላይ እንዳይቆሙ
የማያደርጉት ድፍረት የለም፡፡ የፖለቲካ እሥረኞችን ቁጥር አስቡልኝ፡፡የተቃዋሚዎችን አፈናና አገዳደል - ግፈኛ ተብለው ከሚጠቀሱት
አስተዳደሮች አንዱ ነው፡ የአየንዴዋን ችሌ ወይም የፖልፖትዋን ካምቦዲያ ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ያለፍርድ የተሰወሩ፡ ቤተሰቦቻቸው
በተወለድ ግፍ የሚፈጸምባቸው “ወዮ” ያሰኛል፡፡ ቴሌቪዥን ቀርቶብን፣ አንድም አማራጭ ጋዜጣ፡ ወይ ሬዲዮ የሌለበት አገር ነው፡፡
እነዚህ ሁኔታዎች ዝርክርክነታቸውን (የማታ ማታ)፤ ቆራጥነታቸውንም (ላሁኑ ጥቅማቸው) የሚገልጹ ናቸው፡፡ አማራውንና ኦሮሞውን አዳክመን
የተጠናከረ የትግሬ ግዛት እንደሻችን መመሥረት እንችላለን ብለው ነው ያሰቡት፡፡ እስከዚህ ቀን ድረስ ለትግሬ የተባለ ብዙ ሥራ አገባደዋል፡፡
የተቃውሞ የፖለቲካ አደባባዩ በትግሮቹ
የፖለቲካ ወግ ማጣት ላይ ያተኮረ ፍጅት ነው፡፡ አንድም ተቃዋሚ ድርጅት ወያኔዎችን በግብር መታገል አልቻለም፤ የጎንዮሽ ንትርክ
ብቻ ነው፡፡ የግራው ርዕዬት በሁሉም ላይ ያራጠጠውን ተሃሕት እያየ “ኢሕአዴግ” የሚል ተለዋጭ ያቀርባል፤ መነጣጠር ያለበትን ትግል
ያፈዘዋል፡፡ “የትግሮች አካሄድ ልክ አይደለም” ሲባል “ዘረኝነት ነው፡ ጥላቻ ነው፡ ለምን ትግሬ ትላላችሁ ሕዝቡን አታክሉ” ብሎ
ይሟገታል፡፡ ግና፡- መዋቅራዊና የግዳጅ ሥራዎችን የሚሠሩት በሙሉ ትግሮች ናቸው፡፡ ሌላ የሚታመን ዘር የለም፡፡ “እነዚህ ሰዎች
አጀንዳቸው ትግሬ ነክ
ብቻ ነው፡ ይህ ህልውናችን እየጎዳ ነው፡ ብሎም በእራሳቸው ምንነት ላይ ብቻ ነው ያተኮሩት፡፡ መደረግ
ያለበትን ትግል እየቆረቆራችሁ ነው፤ ተሃሕት የነፃነት ጥያቄውን ከሀያ ዓመት በኋላም አልተወም” ስንል መልሱ ይዘለላል፡፡ ቴሌቪዢኑን
ተመልከቱት፡ ጋዜጣውን አንብቡት፡ ሬዲዮኑን መርምሩት ….. ሁሉም የሚካሄደው በትግሮች ነው፡፡ ከትግሬ ሌላ ስንት የወታደራዊ አብራሪዎች
አሉን? የስለላ መዋቅሩ በሙሉ ትግሬ ነው፡፡ ስምንቱን የዞግ ክልሎች የሚቆጣጠሯቸው ትግሮች ናቸው፡፡
የግራው ንቅናቄ ትግሉን ሲያስተባብር
ይመጣል (ገና) ብሎ ባሰበው ስልተ ምርት ላይ ላባደሩ ይበራከታል ብሎ ነበር፡፡ (ያኔ የኢትዮጵያ ገበሬ ዘጠና በመቶ ነበር)፡፡
የብዙኃንን መንግሥት የመመኘት ሕልም ነበር፡፡ አገራችን ገና ላልወለደቺው ላብ አደር/ወዛደር የበላይነት አስቀድሞ አብዮት ይካሄድ
ተባለ፡ - የምኞት ሽቅለት፡፡ የግምት አብዮት ነበረ የሚያሰኘውም ለዚህ ነው፡፡ አሁን በምዕራቡ ያስተዳደር ፍልሰፍና ላይ ነው የምንራኮተው፡፡
አገር የለም እየተባለ ዴሞክራሲ ለይ መፈጣፈጥ፡፡ ስለአሜሪካ ዴሞክራሲ የሚያወሩ “አሜሪካ” የሚባል አገር ያላቸው ናቸው፡፡ ጀርመንም፣
እንግሊዝም እንዲሁ፡፡ ዴሞክራሲ የብዙኃን የበላይ አስተዳደር ነው፡፡ ተግባራዊነቱ ቢረጋገጥ፤ ዞገኞቹ እንደሚጠይቁት በ“አብዮታዊ
ዴሞክራሲ” ሄደን ማህበረሰባትን፣ ጎሣዎችንና ሃይማኖቶችን እኩል ማድረግ አይቻልም፤ ኦሮሞዎች፣ አማሮች ብሎም ሱማሌዎች ብቻ ናቸው
ሊጠቀሙ የሚችሉት (ከነሱም አጥቂ መኖር አለበት)፡፡ በቡኩሌ ቡድን የሥልጣን መወሰኛ መብት መሆን የለበትም፡፡ የግለሰብ መብት የሁሉም
መብቶች ጅማት ነው፡፡
አገሪቱ ከሁሉም አቅጣጫ ከባህር ወደቦቿ
(በተሃሕት ዕድሜ ልከ) ታጠረች፡፡ በሕዝቧ ላይ ይፋዊ ግፍ ተፈመጸበት፡፡ ተጠያቂዎቹ ትግሬዎች ብቻ አይደሉም፤ በመተባበር ድምፃቸውን
የሰጡት የተባበሩት መንግሥታት አባላት ቢያንስ የታሪክ ተወንጃዮች ናቸው - በተለይ የጸጥታ ምክር አባል አገሮች፡፡ በአራት ሚለዮን
ነፃነት የሰማንያ ሚሊዮን ሕዝብ መሠረታዊ መብት ተገፈፈ፡፡ ዓለምን እናሰተዳድራለን የሚሉትንም ኃያላን መንግሥታት ያሰተዳደር ጥልቀት
ታዘብነው፡፡ ጅቡቲ የአሜሪካኖች ጠንካራ የጦር ሠፈር ሆና እኛ ለባህሩ ባዕድ ሆን፡፡ አሰብም ለኤርትራ ታክሎ መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ
ሕዝብ ከቀይ ባህር ንብረቱ ታገተ፡፡ የቀይ ባሕር ፍፁማዊ ባዕድነት በታሪካችን የመጀመሪያ ነው፡፡ በምዕራባውያን አጫዋችነትና በትግሮች
አስፈጻሚነት (አስገዳጅነት) የሆነ ነው፡፡ ሁሉንም የወደብ መብት ያጣነው እንደሰው ልጅ ታሪክ ተጠቅተን አይደለም - የትግሬዎች
ምርጫ ስለሆነ ብቻ እንጅ፡፡ አሁን አገር የለንም፡፡ የሚወራረድ ካለ ይሞክረኝ (ጅሎች አይታጡም ስላለኝ አንድ ሰው፡፡) ትግላችን
አገራችንን የማስመለስ ብቻ ነው፡፡
የስድሣ ስድስቱ ንቀናቄ አባቶቻችን
ያገኙትን ድል (አድዋ) ሳንጠግበው ሁከት ውስጥ ማገደን፡፡ ድኸን ሳንቆም የእንብርክክ፡፡ እንደዛሬው ሳይሆን ኩራት ነበረን፤ ምንነት
ነበረን፤ አገር ነበረን፤ መሬት ነበረን፡ ዛሬ ግን ከትግሮቹ በቀር ሌላው ከመሬት ይዞታው ተነቅሏል፡፡ በታሪካችን አንድ ሰው ከመሬት
የሚነቀለው ከወግ የወጣ ያገር በደል ሲያደርስ ብቻ ነበረ፡፡ ለጨዋታ ግን የትግሮቹም ጊዜያዊ ሲሳይ ቋሚነት አይኖረውም፡፡ መቅሠፍት
እንዳይሆን እፈራለሁ፤ ሌላው ድህነትን
የለመደው ቀሰ በቀሰ ነው፡፡ ባዳር የተገኘ ጥጋብ ግን ባዳር ይጠፋል፡፡ በነጋው በሌላ እህል የማይደገም
የዱበዕዳ ቁንጣን፡፡ ትግሬዎችች በኋላ “ለዚህ ነበረ ወይ?” እንዳትሉ፡፡
እዚህ ያነሳሁትን ሁሉ በተንጠባጠበ
ሁኔታና ባገኘሁት አጋጣሚ ደጋግሜ አንስቼዋለሁ፡፡ ድጋፍም አይቻለሁ፤ ውግዘቱ ያይላል፡፡ ግን የማነሳውን ጥያቄ መንዝረው የሚከራከሩ
አላየሁም፡፡ “ያብዮቱን ሰነድ ለምን ትደፍራለህ?”፡ ነው ፍጥጫቸው፡፡ እኔ ደሞ ኅለውናችንን በሚነካ መንገድ የሚሄዱትን የፖለቲካ
አባወራዎች ስነቅፍ “ለምን ትነካለህ፡ መሪወቻችን የእኛ ፈቃድ ናቸው” ነው ክሳቸው፡፡ እና - ብዕሬንም ሳነሳ ፈገግ ያልኩበት ጉዳይ
ነው፡፡ ከማይስማሙት የሚመጣውን ውግዘት ተለማምጄው የቆየ ሰለሆነ በስሜቴ ላይ የሚያመጣው ነውጥ አይኖርም፡፡
እምለው ግን! - ስንዛግጥ የኖርነው
በግራ የፖለቲካ ልጋግ ውስጥ ነው፡፡ አብዮቱ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፖለቲካዊ ባህል ላይ የተመሠረተ አልነበረም፡፡ በሙሉ ስህተት ነበር፡፡
ቀደም መደባደቢያ አድርገን ያነሳናቸው ንደፈ ሀሳቦች ኢትዮጵያን እንደሕዝብ የሚያስቀጥሉ አልነበሩም - መቸውኑም አይሆኑም፡፡ ወያኔን
ብቻ እንታገል የሚለው አቀራረብ ብቻውን የትም የሚያደርሰን አይደለም፡፡ የምንታገልበት ርዕየት ይቀድማል፡፡ ዞገኛና ዘረኛ ሁሉ የትግላችን
አባሪ አይሆንም፡፡ ይህ ትግል ሉዐላዊያን ባንድ ገጥ፤ የቀሩት በሌላ ሆነው የሚይለይለት ነው፡፡ ተሃሕትንም ሆነ መሰሎቹን የምንታገልበት
መተክል አንድ ነው፡፡ አንዱን ዘረኛ ለመታገል ሌሎች ዘረኞችን መወዳጀት ከሌላ የጣጣ አዙሪት ነው የሚያስገባን፡፡ የትግሬዎች መብት፣
የአማሮች መብት፣ የጉራጎች መብት፣ የኦጋዴኖችና …..ወዘተርፈ ተብሎ ወያኔ አይወድቅም፡፡ በዘር መብት ላይ ተመሥርተን ብንቀጥል
እያንዳንዱ ሰው ከክልሉ ውጭ ሁለተኛ ዜጋ ነው፡፡ እንዲያ ሲሆን ኢትዮጵያዊነት ጠፍቶ ነው፡፡
ከውጭም ከውስጥም ያሉት ንቅናቄዎች
የዚሁ የተሳሳተ ፖለቲካ ካህናት ናቸው፡፡ ወያኔ “ሕዘቦች” ይላል፡ ተቃዋሚዎችም “ሕዝቦች” ይላሉ፡ እስካሁን ያለው መድረክ የጎሣና
የዞግ ፖለቲካ ግርፍ ነው፡፡ ሕዝቡ በጎሣና ዘር ሸምቅ ሳይፈራራ የምናስተባብርበት ንድፈ ሀሣብ መገኘት አለበት፡፡ ኢትዮጵያን እንዳገር
ለማስቀጠል እሰካሁን የሄድንበት ፖለቲካ ቅጥ አልነበረውም፡፡ ከታች አክልበታለሁ፡፡
የግራው ንቅናቄ የመደብ ጭቆናን የርዕዮተ
ዓለም መንደርደሪያ አድርጎ የብሄርና የሃይማኖት ጭቆና ገሃዳዊ ያገሪቱ ማጥቂያዎች ነበሩ፡፡ ሃይማኖቶቹ የረድፍ ገድል ውስጥ ነው
ያሉት፡፡ ሁለቱ ሃይማኖቶች በተፎካካሪነት እንዲተያዩ ስለተደረገ ቁሰሉን አሽሮ ለጋራ አገራቸው ባንድ እንዳይቆሙ ተደርጓል፡፡ የጠቡን
ዓውደ ሀሣብ የፈለፈለው የነብረሃነመስቀል ወረቀት ነው፡፡ የብሔር ንቅናቄ እንደአሸን እንዲግተለተል ተደርጎ በዚሀ መሀል የትግሬ
ብሔርተኛነት አውራ ባለጉልበት ሆኖ ዘለቀ፡፡ ሁላችን ከዘጠና ሚሊዮን በልጠናል ይባላል፡፡ የሙላውን ሕዝብ መንበር ትገሬነት በአፈጠጠ
ሁኔታ ወሰደው፡፡ አንዱ አሥመራ፡ ሌላው አዲስ አበባ፡፡ ቤተከርሰቲያንም አብራ ትግሬ ሆነች፡፡ የፖለቲካ አደባበዩ በዘር ሥንከሳር
ታወደ፡፡ የጋራ
ህልውናችን ልጥልጥ ዳጥ ላይ ወደቀ፡፡ አማራነትና ቤተክህነት ያለወግ ተጠቁ፡፡ ግምት ወይ ባዶ ክስ አይደለም፡፡
በተጨባጭ የሚመሳከር ነው፡፡
እስልምና እስካሁን የ”አብዮታዊ ዴሞክራሲ”ው
ተጠቃሚ ነበር፡፡ ሲበስል ወደፊት ለብቻው እመለስበታለሁ፡፡ ለመቆያ ግን ትንሽ ላክል፡፡
ወያኔዎች/ትግሬዎች እስልምናን በፖለቲካ
ፍቅር ሀያ ዓመት ተዳርተውታል፡፡ በዚያው ልክ የተዋኅዶ እምነትን ከብዙ አንፃር አጥቅተውታል፡፡ ትግራይ ውስጥ በነበሩ የታሪክ መዛግብት
የሆነውን ጉድ ሁሉ ቀን ያውጣው፡፡ በሌሎች ክፍለሀገራት የነበሩ ቅርሶች ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ተመዝብረዋል፡፡ ለምዕራቡ የቅርሳቅርስ
ገበያ እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡ እንቁ የሚባሉ ታሪካዊ ቅርሶች መነሻቸው ሳይጨመር ካገር እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ አንዳንዶቹ በሙዚየሞች
ብቅ ማለት ጀምረዋል፡፡ ከሁሉም በላይ የተሠወሩት ገና “እዝጎ” የሚያሰኙ ናቸው፡፡ የላሊበላዉ መስቀልም በእግዜር ፈቃድ ነው የተመለሰ፡፡
ሲኖዶሱ የተሰደደው ወያኔ ሥልጣን ከያዘበት ዘመን ጀምሮ ነው፡፡ አሁን ደሞ የገዳማቱ ሥነደንብ በድፍረት እየተጣሰ ነው፡፡
ፋሉል ይጋልብ የነበረው የግራ ንቅናቄ
የአማሮችንም፣ የኦሮሞችንም ምሁራን እያከለ የእስልምናን በደል ከብሄር ጭቆና ጋር በአቻነት ሰብኮለታል፡፡ ኢትዮጵያውያን የእስልምናም
የተዋህዶም አማንያን ይሀን የፖለቲካ ብስናት ሲያስታግሱት ቆይተዋል፡፡ ጽንፈኛ እሰልምና ግን እየተንከባለለ ብዙ ጉዳት አድርሷል፡፡
አሁን ውስብስብ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡
ወያኔዎች/ትግሬዎች ባሰሉት ደባ በዋለልኝ
ስም የቀረበው ወረቀት የሠራላቸው የሣት ስብቀት ይኸ ነበር፡- የዘርና የሃይማኖት ውድድር መፍጠር፡፡ ደቡብ ውስጥ ያለቁት ሰዎቻችን
ጉዳት የሃይማኖታዊ አዕምሮ ግሽበት የፈጠረው ነበር፡፡ በጣም የሚያሰኘው ከሀያ ዓመት በኋላ ለምን መጅሊሱም ትግሬ እንዲሆን መወሰኑ
ነው፡፡ ከጀርባው ያለው ኮተት በጣም ያነጋግራል፡፡
አባቶቻችንን የቸገራቸው ተስቦ ተስቦ
አሁን ያፈጠጠው ትዕይንት ነው፡፡ የትግሬዎቹን የመብት ግፊት ከተፈናጣሪው እስልምና ለመለየት ያለው ግብግብ፡፡ ሁሉም ሊነካው በፍርሪት
ላይ ነው፡፡ የዘር ፖለቲካ ሰውነት ሲባረክ፤ ተቃዋሚው እየተገነዘ ሲፈታ የኖረው በዚሁ የግራ የፖለቲካ ክህሎት ነው፡፡ የሃይማኖቱም
ጉዳይ እንደከረምነው በዚሁ የግራ ዐውደ ሀሳብ እንዳይጋይ ምሁራንን አጢኑበት እላለሁ፡፡ ከድጥ ወደማጥ እንዲባል ዴሞክራሲያዊ መብት
አገር ማልሚያ እንጂ መጎፈሪያ ጃርት አይሁን፡፡
በመሠረቱ የብሄርን ጥያቄ ሰውነት ሰጠው
ተብሎ የሚዘከረው ዋለልኝ መኮንን ነው፡፡ የሰውየው ተውኔት በበታችነት ስሜት የተናጠና በቅብጢ ጀብዱ የዋዤ ነበር፡፡ ድርሰቱ ግን
አውሮፕላን መጥልፈው አልጀርስ ውስጥ የተጠጉ
የኋላ የኢሕአፓዎች አመራሮች “ጥፎሽ” ነው፡፡
እስካሁን “እከሌ” ወይ “እነከሌ” የተባለ ባለቤት ያጣ የዋለልኝን አፅም አላሰተኛ ያለ የገመና ንብረት
ነው፡፡
“የዋለልኝ ነው” አለመባሉ ይመቸኛል፡፡
ሲጀመርም ሆነ ባሁኑ ሰዓት የነፃ አውጭ ንቅናቄዎች ቅዱስ ዶሴ ነው፡፡ ያ ሰው ግን የመዘዘኛዋ ዶሴ ባለንብረት ለመሆን ከፊትም ከኋላዋ
ማጀቢያ ሐሣብ አልነበረውም፡፡ የብሔር ጭቆናውን አልተነተነውም፡፡ ከሱ ያገኘናቸው ፅሁፎች አላሰዩንም፡፡ በስድሣ ሚሊዮን (ያኔ)
ሕዝብ ላይ የዱብ ዕዳ መርግ (ተወረዋሪ የአለት ደንጋይ) ፈንቅሎ ለመወርወር የሚያስችል ዕውቀት አልነበረውም፡፡ ቅብጠቱ ግን ስሙንና
ጀብዱውን (ግብሩን) ከልክ በላይ ለጎሣ ፖለቲካ ማዋሱ ነው፡፡ “On the question of nationalities” “the
struggle” በተባለው የዩኒቨርሲቲዉ መጽሔት በራሱ
ስም ወጥቷል፡፡ በስንኞቹም መሀል እኔነትን ጨምሯል፡፡ ይህን የኢትዮጵያ ሕዝብ የገጠመ ጣጣና የሁከት ሰነድ ይዘን የዋለለኝን የገድል
ሽቅለት ሳስበው ያነጋግራል፡፡ ራሱን የመክዳት ብስጭት ነበረበት ማለት ፍርደ ገምድል ብሎም ድፍረት አይሆንብኝም፡፡ ወሎየዎች የሚዛኑበትን
አማረኛ አንገቱን ደፋበት፡፡ የክበባዊ የአማረኛ ዜማውን ከተራቢ አዲሰ አበቤዎች ለመሸሽ እንግሊዝኛን መምረጡ አብዮቱን ሳይራመድ
ፈጀው፡፡ የሰሜኑ የጎሣ ፖለቲከኞች ለእርድ ያቀረቡት ሰው እንደነበረም ጅልነቱ ይመሰክራል፡፡ ዋለለኝ በፍጹም ራሱን አልነበረም፡፡
የርችት ተኩስ መሆኑ እንጂ ሰነዱ ዝርዝር
ቁም ነገር አልነበረውም፡፡ «ኢትዮጵያ የብሄሮች አገር ናት» የሚለው ሀሣብ የጥንስስ ገንቦ የነብርሃነመሰቀል ራስ አልነበረም፡፡ የውጭ
ሰዎች በፈራ ተባ ቀድመው ሲያነሱት ሲጥሉት የነበረ ነው፡፡ ለሁሉም የአበሣችን መነሻ ሀሳብ ይኸው ነው፡፡ በዚህ ሰነድ ማን ባለቤት፤
ማን ጨቋኝ እንደሆነ አልተብራራም፡፡ የእንክርት ፖለቲካ ነበር፡፡ ያማራውን አበላል፣ አለባበስ፣ አነጋገር፣…..ወዘተ እየወረፈ የቀሩትን
ማህበረሰባት በሙሉ ያማራው ባህል ግብር ተሠሪዎች ያደርጋቸዋል፡፡ አማራ ምሁራን ይህን ልብ አላሉም፡፡ ከፖለቲካ ዘፈኑ አብረው ገቡ፡፡
በዚህ ረገድ የማህበረሰባት ታሪካዊ ስሞች ያማራ ስያሜዎች ተብለው ተቀየሩ፡፡ እናም በአብዮት ስም የበታችነት ስሜት እንዲነግሥ ተደረገ፡፡
የብሔር ጥያቄ ቋንቋ፣ የኑሮ ዘይቤ መንሸራሸር በደል ሆነ፡፡ በደም የተቃየጠው (የተቀላቀለው) በቋንቋ ዞግ ለየ፡፡ ያገሪቱ መሬት
- መሬቶች ሆነ፡፡ ሕዝቧ -ሕዝቦች ተባለ፡፡ ክልል ትግሮች እንደሻቱት ተከተረ፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ እንዳገር (በመንፈስም በአካልም)
የት ላይ እንዳለች አይታወቅም፡፡ የሁለቱ ትግሬ ክልሎች (ኤርትራ እንዳገር) አስተዳደራዊ መዋቅራቸው እጅግ ተሰናድቷል፡፡ በሀያ
ዓመት ያየነው ይኸን ነው፡- አንድ ቀን ያላነቀፈው የትግሬ መብት - የሌሎች ሰቆቃ፡፡
ሌላ ነገር ተደርጓል ከተባለ የጨዋታ
ብቻ ነው፡፡ ከትግሮቹ ክንውን እንደምናየው ከተሳከረ ሁኔታ ላይ ነን፡፡ ባሁን አያያዛቸው ኢትዮጵያን እየገዙ ነው፡፡ አማሮችንም
ኦሮሞዎችንም ለማዳከም ያላደረጉት ጥረት የለም፡፡
በዋለልኝ ስም የሚታወቀው የነውጥ ወረቀት
ይዘት በወርዱም በቁመቱም ከቀዳሚዎቹ የዴሞክራሲያ ዕትሞች ያንዱን አያክልም፡፡ በእንግሊዝኛውም ቢሆን የታረመ (as a
doctrine) አልነበረም፡፡ እንተርጉም ቢባል ስህተት
ሞልቶበታል፡፡ የወደፊቱ ትውልድ መጎብኘቱ አይቀሬ ነውና፡፡ ብሄርተኞች ግን የደባቸው ዋቢ አድርገው ያለንበትን
የፖለቲካ ተውኔት ፈጥረውበታል፡፡ ባገሪቱ የተነሱ ድርጅቶች ሁሉ ይህን የሁከት ሀሣብ በፕሮግራሞቻቸው ላይ የቀድሞዎቹ (እንደኢሕአፓ፡
መኢሶን) በመተክልና በማታጋያ ደረጃ፤ የኋለኞቹ እንደሕዝብ ማሰባሰቢያ (ለምሳሌ መኢአድ፡ ኢዴፓ…ወዘተ) አሥፍረዋል፡፡ ይህ ያልተካተተበት
የድርጅት መርሀ ግብር ገና የለም፡፡ በግልም ሆነ በቡድን የብሔር ጥያቄን ያልዋጠ (internalize)
አለያም ያላላመደ አልገጠመኝም፡፡ ዕውቅ የተባሉ ምሁራን
በጥቃት ደለል ላይ ሲደንሱ አይተናል፡፡ የኤርትራን አገርነት ተቀብለው በዚያው በኩል ትግል የሚያልሙ ገጥሞናል፡፡ የሚያሣፈር ስለሆነ
እንዳትጨቀጭቁኝ፡፡
በዚህ ውካታ አስተዳደርን በዘር ድርጅት
እንመሠርታለን የሚል ዕብደት የብዙዎች መሆኑ ነው፡፡ ግራዎቹ መገንጠልንም መብት አድርገው ሰብከዋል፡፡ ቢሻ አብሮ - ቢጠላ መሄድ፡፡
የጨዋታው አዙሪት ይህ ነው፡፡ የኤርትራው ጥያቄ በቅኝ ግዛት ተፈረጀ (ራሱን የቻለ ጥንጠና አለው፡፡) ለሌሎችም ክፍት መንገድ ተተወ፡፡
ወያኔዎቹ የሚሠሩት በዚሁ መተክል ላይ ቆዝመው ነው፡፡ ሙሉ ሥልጣኑን ይዘው “ተሃሕት” የሚለውን የነፃነት ድርጅት አልተውም፡፡ መሀሉን
እያናከሱ ትግራይን በሁሉም መስክ ገንብተዋል፡፡ አመፅ ካስገደዳቸው አገር ሆነዋል፡፡ ይሀን “አሊ” ማለት ዕውቅ ንዘንዝ ነው::
ሄደው አገር መሆን ይችላሉ ወይ? ብዙ
ክበባዊና ሉላዊ ሁኔታዎች ግን ይህን አይፈቅዱም፡፡ መታሰቡም ይገርማል፡፡ በመጀመሪያ ኤርትራ አገር ስትሆን በመጀመሩት (እንደኤርትራ)
ጎዳና ለምን ትግራይ አገር አልሆነም? የአሜሪካኖች ሰሎ ነው? የእነኢሳይያሰ? ወይሰ የራሳቸው የአድዋዎች ግንዛቤ? የታወቁ ያገሪቱ
መዋቅሮች ወደትግራይ (የጠቅላላ ሠራዊታችን ተቋሞች በሙሉ) ሲዘዋወሩ የተቃውሞ መሪዎች የሻቢያ/ወያኔውን መንግስት “የወያኔ/ኢሕአዴግ”
መንግስት ማለቱ ምን ዋጋ ነበረው? ሥልጣን በያዙበት ሰሞንም የነበረው ተሃሕት/ተሃሕኤ ነበር፡፡
የአማራው ሕዝብ ከተለያየ አቅጣጫ ሲዋከብ
ነበረ፡፡ አሁን ግን ወከባውን በቸልታ ሊመለከት ከሚችልበት ደረጃ ስላለፈ ቀን ያልፋል ብሎ ሊጠብቅ አልተቻለውም፡፡ ግን ትግሉን
እንዴት ነው ሊመራው የሚችለው? አማራው ኢትዮጵያ ነው፡- በእርግጥ፡፡ የሌሎቹን በጎሳ ፖለቲካ ይዋኙ የነበሩትን እንዴት ነው ሊመራ
የሚችለው? ብቻውን ትግሬዎቹን ሊቋቋም ይችላል? በዚሀ ጎዳና ከሄደ የሚፈጠረው ተውኔት ምን ይሆናል? ሌላው ባገር ደረጃ የተደራጁ
ስብስቦች የሚያነሱት የወቀሳ ናዳ ነው፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ትግሮቹ የመጨረሻ የሚሞክሩት ስነልቦናዊም ሆነ አካላዊ ጉዳት ነው፡፡ ያም
ሆነ ይህ አማሮች መነሳታቸውና ይህን ሁላችን የሚያጠፋ የፖለቲካ አዙሪት መቀየር የግድ ነው፡፡
ደርግ ውስጥ የነበሩ አብዮተኞችም ሆነ
እነሱን በቂ አይደሉም ብለው ይታገሉ የነበሩ ድርጅቶች የአማራውን መነሳሳት ቀደምም በዐይነ ቁራኛ ሲጠብቁት የነበረ አሁን ደሞ ልነሳ
ነው (ሞረሽ) ሲል ውዥቀት ውስጥ የገቡበት ሁኔታ ነው፡፡ አሁንም የጀመርነው ትግል አልተደመደመም ነው የሚሉት፡፡ ትግሮች አገሪቱን
በዘር ከልለው ሁሉንም በበላይነት የተቆጣጠሩበት ሁኔታ ያላለቀው ትግል ምንድን ነው?
የመደብ ጥያቄ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ለማሰተባበር (አብዮት ለመቀስቀስ) የሚችል አልነበረም፡፡ “መሬት
ላራሹ ለማን? ለኤርትራውያን? ለትግሮች? ለወሎየዎች? ለጎንደሮች? ለሀረሮች? ለአርሲዎች? ለማ? ይልቅ በመደብ ትግል ስም ዛሬ
ለምንሰፈሰፈለት አገር ገድላቸውን ያሳዩ አርበኞች ያለፍርድ ገደልናቸው፡ ከዚያም የኢትዮጵያዊነት ትርጉም ደብዛው ጠፋ፡፡ ሞታቸውም፣
ምንነታችንም በቅጽበት ባዶ ሆነ፡፡ ከዚያም ክርሰቲያኖችም አበዱ፡ እስላሞቹም፣ ማርከሲስቶቹም አበዱ፡፡ ውሾቻችን እንቀብር እንዳልነበር
የሰው ልጅ አስከሬን ለመቀጣጫ ፀሐይ ላይ ሲሰጣ አየን፡፡ አስከሬንም እንደሸቀጥ ዕቃ ተሸጠ፡፡ የሰው ልጅ ሁለት ጊዜ የሞተባት አገር
የዚህ ትውልድ ኢትዮጵያ ብቻ ነች፡፡ በርዕዮተ ዓለም ተቃውሞ የተነሱት (ጎጃም፡ ሸዋ፡ በጌምድር፡ ወሎ) ተቀጠቀጡ፡፡ “ተሰፋ ለዘውድ”
እና “አድኃሪያን” እየተባሉ በግርግር ፖለቲካ አለቁ፡፡ በተቃዋሚዎችና በደርግ መሀል በዚሀ ሰቆቃ ላይ ልዩነት አልነበረም፡፡ የእነዋቆ
ጉቱ አሟሟት ግን ታሪካዊ ሸፍጥ ተደርጎበታል፡፡ ሞታቸው በኦሮሞ ስም ለተነሳው የብሔር እንቅስቃሴ እርሾ እንደሆነ ተሰበከ፡፡ የጠባብ
ብሄርተኛ ድርጅቶችም ሆኑ የግራ ድርጅቶች የኦሮሞን ጭቁንነት ለማረጋገጫ ተጠቅመውበታል፡፡
በዚህ ጽሑፍ ጨምቄ ያነሳኋቸው ነጥቦች
ሁሉ ከባዶ አዕምሮ የተገመቱ አይደሉም፡፡ ባልኩት ሁሉ ላይ በቂ ታሪካዊ መዝገቦች አሉ፡፡ “ለቀባሪ አረዱ” እንዲባል ……..በቅደም
ተከተል እመለስበታለሁ!
ለዚህ መንደርደሪያ ማከያ ክፍል ሁለትን
ይዤ እመጣለሁ……….ካልደበረኝ፡፡
ቸር ያቆየን!!
በኢትዮጵያን ሰማይ
አንባቢዎች ስም ሽርባ ሽሞፈናን ከልብ አመሰግናለሁ። ሽርባ ሽሞፈና ካልደበረው በቅርቡ በጉጉት የምንጠብቀውን ሁለተኛውን ክፍል እንደሚያስነብበን
ተስፋ አለኝ። ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment