To change zoom level Press Ctrl and + symbol keys the same time (together) (small size font or minimize page Press Ctrl and - (Minus) symbol.
New Book by Getachew Reda
አዲስ መጽሃፍ
የወያኔ ገበና ማህደር
Getachew Reda
P.O.Box 2219
San Jose, CA
95109
(ዋጋ $30.00) Tel-(408) 561 4836
GetachewReda
P O Box 2210
San Jose, CA 95109
አይጥ ለሞትዋ የድመት አፍንጫ ታሸታለች!!!
ገብረመድኅን አርአያ
ፐርዝ አውስትራሊያ
ተ.ሓ.ህ..ት.ብሎ ራሱን የሰየመው የዛሬው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፋሺስቱ ፓርቲ፣ በየካቲት ወር 1967 ዓ.ም. ትግሉ ከጀመረበት ቀን አንስቶ በትግራይ ሕዝብ የፈጸመውን አሰቃቂ የወንጀል ግፍ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ያውቁታል።
ውድ ኢትዮጵያውያን ሆይ!
የትግራይ ሕዝብ ያ የ17 ዓመት የወያኔ ትግል “ዘመነ እልቂት” ይሉት ነበር። ዘመነ እልቂቱ ከደደቢት ትግራይ አልፎ አሁን በኢትዮጵያ ሀገራችን ሙሉ በሙሉ ሸፍኖ ወደ ‘ዘመነ ጨለማ” ተሸጋግሯል።
አሁን-ለማንሳት የፈለግኩት፤በውጭ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ስለ ወያኔ ማንነትና ማወቅ ያለባችሁ ጉዳዮች ብዙ ነገሮች አሉ። እዛው በየአገሩ በምትኖሩባቸው ከተሞች-ውስጥ የወያኔ ድርጅታዊ ተልዕኮ ለማሳካት ከትግራይ የመጡ የፋሺስቱ ወያኔ ደቀ መዛሙርት፤በጥቅም የተገዙ አድርባዮች እና ካድሬዎች እንዲሁም ሰላዮች በመሆን በምትንቀሳቀሱባቸው ማሕበራዊ እና ፖለቲካዊ ወይንም ሃይማኖታዊ ሕይወታችሁ ውስጥ ተመሳስለው በመግባት አንድነታችሁን ለመበጥበጥ የተሰማሩ እንዳሉ በተለያዩ ሰዎች እንደተገለጸ ይታወሳል።ከተጠቀሱት የወያኔ ካድሬዎች ውስጥ በትግራይ ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ላይ በማን አለብኝነት ተነሳስተው ለብዙ ኣመታት ሰብአዊ እና-አገራዊ ወንጀሎችን የፈጸሙ እና ያስፈጸሙ የወያኔ የወያኔ እስር ቤት እና የስለላው መዋቅር በሃላፊነት የሰራ ብስራት አማረ ማን ነበር? የሚለውን ዛሬ ግልጽ ላደርግላችሁ እሻለሁ።
ብስራት አማረ ማን ነው?
ብስራት አማረ ትውልዱ አክሱም እስከ 9ኛ ክፍል አክሱም አውራጃ የተማረ ሆኖ ወደ ህወሓት ትግል የተቀላቀለው በ1968 ዓ.ም. አጋማሽ አካባቢ ነበር። ብስራት አሁንም የፋሺስቱ ወያኔ ምርጥ ታማኝ እና ሙሉ አባልነቱ እንዳለ ሆኖ በውጭ አገር እየኖረ አሁንም የፋሺስቱ የወያኔ-ፖለቲካ እና ፖሊሲ አራማጅ እና ጠበቃ በመሆን በየራዲዮኑ እና ፓል ቶክ ስለ ወያኔ ብፁእነት ሲሰብክ እያደመጥነው ነው። ያ አልበቃ ብሎት አለቆቹን በመወከል ተቃዋሚዎችን በመዝለፍ አልፎም አገር ውስጥ በመሄድ በጌቶቹ ፍረድ ቤት የክስ ማሕደር በመግፈት ተቃዋሚዎችን ለማንገላታት እየሞከረ ነው።ይህ ደግሞ አዲስ ስልት እና አሳፋሪ ተግባር ስራየ ብሎ ተያይዞታል። ህ.ወ.ሓ.ት. የተባለው ድርጅት የፋሺስትነት ባሕሪይ እንዲኖሮውና እና በታጋዮችና በኗሪዎች ላይ ፋሺስታዊ ድርጊቶች እንዲፈጸም አስተዋጽኦ ካደረጉት የወያኔ ካድሬዎች አንዱ ብስራት አማረ እንደነበር ብዙ ታጋዮች ያውቁታል። ብስራት አማረ ዛሬ ውጭ አገር እየኖረ ወያኔን በመደገፍ ቢለፈልፍ ሰው እየገረፈ እና እየገደለ ስለገነባው ድርጅት ጥብቅና ቢቆም ባሕሪያዊ ነውና መገረም የለብንም።
ብስራት አማረ ማን ነው?
ታሪኩን ትንሽ ወደ ኋላ በመመለስ እስኪ እንዳስስ።የተ.ሓ.ሕ.ት (ህ.ወ.ሓ.ት) መሪዎች ከመነሻው ይዘውት የመጡ የድርጅቱ የትግል መርሆ ተግባራዊ ሲያደርጉት የነበረውን ፀረ ኢትዮጵያ፤ፀረ አማራ፤ እና ፀረ ሕዝብ እንዲሁም በዋነኛነት ኤርትራን ለማስገንጠልና አልፎም የትግራይ-ሪፑብሊክ መንግሥት ለማቋቋም አመራሩ ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲውና አካሄዱ አብዛኛው ታጋይ አገርና ሕዝብን የሚጎዳ ጥፋት መሆኑን ከተገነዘበ በኋላ፤ አመራሩ እየተከተላቸው የነበረውን ጸረ ሕዝብ እና ፀረ ኢትዮጵያ እምነቶቹ ባጭሩ መገታት አለበት ብሎ በመወሰን ዲሞክራሲያዊ የሆኑ ጥያቄዎች በማስነሳት መንቀሳቀስ ጀመረ።
በታጋዩ ውስጥ የተንጸባረቀውና የተነሳው ቅሬታና እንቅስቃሴ በትግራይ ሕብረተሰብ ውስጥም-በየቦታው ተመሳሳይ ሆነ። ሕዝቡም የጥንት ቅድመ አያቶቻችን እና ወላጆቻችን ደማቸውን እና አጥንታቸውን ከስክሰው የጠበቋትን እና-ያስረከቡንን ኢትዮጵያን ዛሬ የህወሓት መሪዎች ከሻዕቢያ ጋር ተባብረው አገራችንን ሊበትኗት ነው የሚል ስጋት ከገጠር እስከ ትግራይ ከተሞች ተንፀባረቀ።
በ1968 ዓ.ም.መጨረሻ የወያኔ መሪዎች ይህ የታጋዩ እና የሕዝቡ እንቅስቃሴና ቅሬታ ስላስደነገጣቸው በድርጀታችን ውስጥከመቀሌ፤ከተምቤን፣ከአዲግራት፣ከራያና ከሁለት አውላዕሎ አውራጃዎች ተሰባስበው “ሕንፍሽፍሽ” (ብጥብጥ) ፈጠሩ በማለት የተነሳውን የዲሞክራሲ እንቅስቃሴ ለማዳፈን ተነሱ። ሃቁ ግን ታጋይ ሁሉ የተነሱት ቅሬታዎች በሰላማዊ እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ ማንጸባረቃቸው እንጂ፡ህንፍሽፍሹን የፈጠሩት እራሳቸው አመራሮቹ ነበሩ።
በዚህ-ጊዜ አመራሩ እንቅስቃሴውን ለመግታት ለኤርትራ የቆመበትን ፖሊሲውን ለማራመድ እና እንዲሁም ፀረ-ሕዝብነቱ እና ፀረ-ኢትዮጵያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያመቸው ዘንድ አመራሩ የሚከተሉትን እርምጃዎች በመውሰድ አፈና ማካሄድ ጀመረ።
አመራሩ የወሰዳቸው እርምጃዎች
በዚያው ወቅት የነበሩ ድርጀቱ የታወቁ አመራሮች ስም ዝርዝር 1ኛ ስብሓት ነጋ 2ኛ መለስ ዜናዊ 3ኛ አረጋዊ በርሄ 4ኛ አባይ ጸሃየ 5ኛ ስዩም መሰፍን 6ኛ ግደይ ዘርአጽዮን 7ኛ አውኣሎም ወልዱ 8ኛ ስየ አብርሃ 9ኛ አጽብሃ ዳኘው (በመለስ ዜናዊ የተገደለ) ተሰብስበው በ1968 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ 06 (ሓለዋ ወያኔ/እስር ቤት) እንዲስፋፋ በመወሰን በሁለት ደረጃ አስቀመጡት።ቀዋሚ እና ተንቀሳቃሽ እስር ቤት።
1ኛው - ቀዋሚ 06 ወይንም ሓለዋ ወያነ የሚባለው፦በስፋት ሲከፈቱ 1- ቡምበት 2- ባኽላ 3- ዓይጋ 4- ወርዒ 5- ፃኢ 6- ዓዲ በቅሎ 7- ዓዲ ጨጓር 8 ሱር 9- በላሳ- ማይ ሓማቶ 10- ቆሎ ምሸላ..ወዘተ..ወዘተ.. ሲከፈቱ እነኚህን ለማንቀሳቀስ የተመረጡ ሰዎች ለአመራሩ ታማኝ የሆኑ ብቻ ነበሩ።
2ኛው ተንቀሳቃሽ 06 ወይንም ሃለዋ ወያነ/Mobile የሚባለው ነው። ስራ ተግባሩ የሚከተሉትን የጭካኔ እርምጃዎች፤ ዓለም አቀፋዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ወይንም ባሕላዊ ሕጎችን ሳይከተል በማን አህለኝነት በጠመንጃ ጉልበት ተንተርሶ፤መፈጸም ነው።
1-ሰለመዊም ሆነ ተጋይ ወንድ፣ ሴት፣ ሽማግሌ፣ ቄስ፣ ድያቆን፣ ቃዲ፣ ሓጂ፣ ሸኽ ሳይል የፈለጋቸውን ጥፋት ይኑረው አይኑረው በስማ በለው እናበአሉባልታ ሰውን አፍኖ መጥለፍ (kidnapping)
2-በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ውስጥ ድርጅቱ ነብሰ ገዳይ ተኳሾችን አሰርጎ በማስግባት የሚፈልጋቸውና አብረዋቸው ድንገት የቆሙትን ሲዝናኑ የነበሩትንም ያልተፈለጉ ንፁሃን ጭምር በጀምላ በተገኙበት ቦታ ሰልሎ በመግባት መግደል፡
3- በፈላ ውሃ እና በጋለ ብረት እስረኛን በአሰቃቂ ምርመራ ማቃጠል (Torture)
አመራሩ ከላይ የተጠቀሱት ክንዋኔዎች እንዲመራ ለብስራት አማረ ሃላፊነቱን ሰጠው።
ወደ ዝርዝር ከመግባታችን በፊት የሰውየው ገጸ ባሕሪያት እኔ እንደማውቀው፦
ውሸት-የሚያበዛ፤ምቀኛ፤አስመሳይ፤አድርባይ፤ለሰው ክብር የማይሰጥ ተሳዳቢ፤ ሰውን የሚንቅ፤በትግሉ ወቅት የሚያጎበድድላቸውን አለቆቹን በመመካት እና ከአለቆቹ የተሰጠውን ኃላፊነት ምርኩዝ አድርጎ በመመካት ዝሙት በመፈጸም ሴትን አስፈራርቶ የደፈረ ነው።
ከላይ-የተጠቀሱት በሁለት ክፈሎች የተመደቡት የ06-ዘርፍ ስራዎችን ሽብር ለማካሄድ በሃላፊነት የተመድቡ ሌሎች ሰዎች አሉ። እነሱም፤-
1ኛው ብስራት አማረ ዋናው መሪ 2 አሰፋ ጉሬዛ 3 ተስፋይ ጡሩራ 4 ታደሰ (06) 5 ትእግስት አሰፋ 6 ሉኡል በርሄ 7 ታደለ 8 ያለምብርሃን 9 ነፃነት ሰንደቅ (ከትንሽ ጊዜያት በኋላ የተገደለ፤ እና አልፎ አልፎ-አሰፋ ማሞ እና ሌሎች የመሳሰሉ የዚህ የሽብር ቡድን አባሎች ይገኙበታል።
ዋና ተልእኳቸው
በሕንፍሽፍሽ የተበከሉ ታጋዮች (ሀ) ከሠራዊቱ ከየክፍሉ አፍኖ መጥለፍና ሓለዋ ወያኔ አስገብቶ በሰቆቃ ደብድቦ ማስቃየት እና ከዚያ በኋላ ስለ ሁኔታው በውሸትም በትክክልም እንዳፈለጋቸው ለመደባቸው አመራር ማቅረብ ነው። አመራሮቻቸውም ለስልጣናቸው ማጎልበቻ እስከ ጠቀመ ድረስ በሰው ሕይወት የሚደርሰው ጉዳት ጉዳያቸው አልነበረምና ስለ ሆነም ማጋጣዎቹ ካድሬዎቻቸው እንደ የናዚዎቹ የጎስታፖ ቡድኖች የፈለጉትን ሽብር በማንኛውም ሰዓት ወቅት ቀን ይሁን በውድቅት ሌሊት የማፈን የመግደልና የማስፈራራት ተግባር በፈለጉት ሰው ላይ የመፈጸም ሙሉ መብት ነበራቸው።ጥፋት አደረጋችሁ ተብለውም የሚጠይቃቸው ዓለም አቀፋዊም ይሁን ሃይማኖታዊ ወይንም ባህላዊ አካል በስልጣናቸው ዙርያ የለም። ሁሉም በጁ ሁሉም በደጁ በጫካም ይሁን ዛሬም ስልጣናቸው የማይገሰስ ባለሙሉ ስልጣን ነገሥታቶች ናቸውና የተጎዳው ሰው ቤቱ ይቁጠረው። በሰላማዊ ዜጋ ላይ ከባድ ጉዳት አድረሰዋል። የኢ.ድ.ሕ አባል፤የደረግ እና የኢሕአፓ አባል እና ሰላይ ፀረ ኤርትራ ነፃነት ነህ ወይንም ነሽ እየተባሉ ከላይ በተጠቀሱት የሽብር ቡድን አንቃሳቃሾች ትእዛዝ እና ተሳታፊነት ከየከተማውና ገጠሩ እየታፈኑ ለነ ብስራት አማረ እየተላለፉ በመስጠት ብዙ ሰብአዊ ጉዳቶች ተፈጽመዋል። እነህኚ የሽብር ቡድኖችና መዋቅሮች ተልእኳቸው ሽብር በማካሄድ ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አፍኖ ሕዝቡ ለድርጅቱ ሙሉ ተገዥ ሆኖ በፍርሃት እንዲንበረከክ ማድረግ ነው።
እንግዲህ-የሽብሩ መልክ እና ስፋት ሰፊና የተለያየ መልክ ቢኖሮውም አመራሩ በድርጅቱ ውስጥ ሕንፍሽፍሽ ተፈጥሯል ብሎ ራሱ አመራሩ የፈጠረው ሽብር በታጋዩ ውስጥ በጣም በርካታ ታጋዮች ከ1969- 1975 መጨረሻ የቀጠፈው ያጠፋው ህይወት ዘርዝሮ ለመጻፍ በዚች አጭር ፅሑፍ አስቸጋሪ ነው። ቢሆንም ብስራት አማረ ከነ ቡዱኑ አመራሩ በሰጠው ሃላፊነት የፈፀመው ግፍ ግድያ የሰቆቃ ድብደባ ባጭሩ ከነመረጃው አቀርባለሁ።
ብስራት አማረ ከ1969 ዓ.ም. ጀምሮ በሕንፍሽፍሽ ተለክፈዋል እየተባሉ ያጠፋቸው ጥቂቶች ከማውቃቸው ሰዎች መካከል፤
1. አበራ ማንካ (በብስራት አማረ የተገደለ ነገር ግን እራሱ ገደለ ተብሎ በአመራሩ ለሽፋን የተነገረለት)
2. ተስፋይ (ተስፋይ ህንፍሽፍሽ ተብሎ በአመራሩ የቅጽል ስም የተሰጠው) ብስራት አማረ በሰቆቃ (በቶርቸር አሰቃይቶ) የገደለው፡
3. ወዲ ሓኔታ እንደ ተስፋይ በሰቆቃ የተገደለ
4. ኪዳነማርያም በላይ የፈላ ውሃ ጭንቅላቱ ላይ ተደፍቶበት የሞተ፤
5. ኃ/ሥላሴ ገ/ሚካኤል በድብደባ እና በጋለ ብረት የተገደለ፤
6. አባዲ ተምቤን (ጎልያድ) በብስራት አማረ የተገደ (ወያኔ የሚለው ራሱ የገደለ)
7. ጐይቶኦም አብረሃ
8. ዳዊት ግምባር (ሕንፍሽፍሽ)
9. ግርማይ ዘርኦም
10. ብስራት አለማየሁ
11. ሐጐስ ኃይለስላሴ
12. ሐድሽ ዮሐንስ
13. ንግሥቲ
14. ግደይ
15. ዘርኡ በዛብህ
16. ሙሉጌታ አብርሃ
17. አዛናው ገ/ጻድቕ(ይህ ታጋይ ከመለስ ዜናዊ እና ከስብሐት ነጋ ጋር በነበረው ቅራኔ ብስራት አማረ ዛና ወረዳ አካባቢ አፍኖ አጠፋው
18. ባሻይ ሐንጣል
19. ተኽላይ
20. ክንፈ ራያ ወዘተ…ወዘተ..
የመሳሰሉት-እነዚህ ለምሳሌ የተጠቀሱት ባሕርን በማንኪያ እንደመጨለፍ የቀረበ እንጂ ረጋ ብሎ በጥናት ይቅረብ ከተባለ በጣም በርካታ ሕይወት-ብስራት አማረ በሚመራው የሰቆቃ እና የስለላ ዘርፍ የተገደሉ እና ከየክፈላቸው እየተለቀሙ ታፍነው ደብዛቸው የጠፉ እጅግ በጣም፤በጣም ብዙ ናቸው።በሰቆቃ ማለት በፈላ ውሃ በድብደባ በጋለ ብረት በእሳት እየተሰቃዩ የጠፉ በርካታ የሰዎች ህይወት ተጠያቂዎቹ አመራሮቹ.እነ ስብሓት ነጋ እና እነመለስ ዜናዊ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ ክፉ ሰቆቃ ሲፈጽሙ ከነበሩት መካከል ሰው እያፈነ የሕዝብን ሰላም-በፍርሃት ሲያስሸብረው የነበረው “የወያኔ ጀስታፖው” ቡድን መሪ ብስራት አማረ እና መሰሎቹ ለተፈጸሙት ኢሰብአዊ እርምጃዎች በሃላፊነት ተጠያቂዎች ናቸው።
የብስራት አማረ የሽብር ቡድን እና ተግባር እስከ 1975 ዓ.ም በተቀናጀ የአፈና እና የግድያ እንቅስቃሴ ያለምንም ተጠያቂነት አሁንም ወደ-ሰላመዊ ነዋሪ ሕዝብ ተሸጋገረ።ለምሳሌ ከሕዝቡ መሃል እየታፈኑ የውሃ ሽታ ሆነው እዚህ ቀሩ ሳይባሉ እየታፈኑ የተገደሉት ጥቂቶቹን ልጥቀስ።
በ1971 ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ ብስራት አማረና በስራ ከሚገናኘው በመቀሌ አካባቢ የከተማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አለማዮህ በቀለ ከሚባለው ሃገረ ሰላም ኗሪ የሆኑ በጠላ ንግድ የሚተዳደሩ ሁለት ወጣት ሴቶች በተደጋጋሚ አስገድደው ከደፈሯቸው በኋላ ድርጊታቸው በታጋዩ እና በሕዝቡ እንዳይጋለጥባቸው የደርግ ሰላዮች ናቸው በማለት በብስራት አማረ ሪፖርት ተዘጋጅቶ በሌሊት ከመኖሪያ ቤታቸው አፍኖ በመውሰድ ያጠናቀረውን ሪፖርት ለስብሓት ነጋ አቅርቦ በሁለተኛው ቀን በሓለዋ ወያነ አባሎች በጥይት ተደብድበው እንዲረሸኑ ተደርጓል።
በ1972ዓ.ም.ብስራት አማረ እና አፋኙ ጉጅሌው ከማይጨው ወደ መቀሌ በሚወስደው ዋና መንግድ ላይ አድፍጦ በመጠበቅ አንዲት መኪና ሰዎች-ጭና ወደ መቀሌ አቅጣጫ ስትጓዝ ቤት ማራ በሚባለው ቦታ አስቁሞ 6 አስተማሪዎች 2 ከደሴ የመጡ የመንግሥት ሠራተኞች ከመኪናው እንዲወርዱ በማድረግ አስገድዶ በመጥለፍ ፃኢ ወደ ሚባል አካባቢ ወሰዳቸው። ብስራት አማረ እነኚህ ሰዎች ከጠለፈ በኋላ ብዙ የመቀሌ ኗሪ የሚያውቀው በቅጽል ስም “ጥንቸል” እየተባለ የሚጠራው እና አራት አስተማሪዎች እንዲሁም ሁለት የደሴ ሰዎች በጠቅላላ 6ቱ ሲገደሉ የዓድዋ ተወላጆች የሆኑት የተቀሩት-ሁለት አስተማሪዎች ግን በነፃ ለቀቃቸው። ሲገደሉም ብስራት አማረ ለአባይ ፀሃየ ስለተጠለፉት ሰዎች ጉዳይ እንዲገደሉ ብሎ ሪፖርት አቅርቦለት ይገደሉ አለ፡ብስራትም እንዲገደሉ አደረገ።
ሌላው-አሳዛኝ ድርጊት በ፶አለቃ በላይ የሚባል ተመርተው በሰላም እጃቸው የሰጡ የኢትዮጵያ የደርግ ወታደሮች በብስራት አማረ የተዘጋጀ ሪፖርት ለመስ ዜናዊ እና ስብሐት ነጋ ከተሰጠ በኋላ በሙሉ አማራዎች ስለነበሩ ግደሏቸው ተብሎ 1 ብስራት አማረ 2 ክንፈ 3. ገ/መድኅን 4. አለምሰገድ እይንቺ 5. ሐሰን ሽፋ ሆነው ከ06/ ባዶ ሽድሽተ/ከሓለዋ ወያነ አባላት ጋር በመተጋገዝ በሚጠጡት ውሃ ላይ መርዝ ተጨምሮበት ውሃው እንዲጠጡት ተደርጎ አብዛኞዎቹ ወዲያው ሲሞቱ በሞት አፋፍ ሲግሩ የነበሩት ቀሪዎቹ ደግሞ በጋለ ብረት ሆድ እቃቸው እያስገቡ ጨረሿቸው። ጊዜው በ1972 ዓ.ም. ወርዒ ውስጥ ነው።
በሰላማዊ-ትግራይ ዜጎች ላይ ተፈጸመ አፈና እና ግድያ አሁንም ብስራት አማረ ከአሸባሪው የወያኔው ጀስታፖ ቡድን በመንቀሳቀስ በቀንም በሌሊትም እያፈነ የወሰዳቸው ኗሪዎች፤
1. ፊታውራሪ ብፁእ ወ/ጊዮርጊስ እንደርታ
2. ቀኛ/ኪሮስ ዓድዋ
3. ቀኛ/ኃይለስላሴ ዓድዋ
4. ግራ/ታደለ ማሩ ተምቤን
5. አቶ ወርቀ ልዑል ተምቤን
6. ፊታውራሪ ዘገየ ክለተ አውላዕሎ
7. ግራ/በላይ ገብሩ ተምቤን
8. አቶ ኪዳነ ሐጐስ
9. ወ/ሮ አባዲት
10. አሰፋው ወልደ አረጋይ ዓድዋ ይሓ
11. ቄስ አርአያ ዛና
12. ቀኛ/እምብዛ ዛና
ወዘተ…የመሳሰሉ ሰዎች በብስራት አማረ መሪነት እየታፈኑ መድረሻቸው የጠፋ የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል።
በእነ-ብስራት የሚመራው አሸባሪው ቡድን በፈለገው ቦታ እየተንቃሰቀሰ ሕዝብን ሲያፍን በሽሬ አካባቢ ደግሞ ሌላው በህወሓት አሸባሪው የስለላ እና የምርመራ እንዲሁም የእስር ቤት ሰቆቃ ፈጻሚ ቡድን ሽሬ ውስጥ በእነ አበበ ተክለኃይማኖት (ጆቢ/ዑስማን) እነ አውዓሎም ወልዱ፤ታደለ እና የመሳሰሉ በብዙ ሰዎች ላይ ሰቆቃ ሲፈጽሙ ነበር። ለምሳሌ-
1 ሃለቃ ገ/ሚካኤል 2. አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦ 3. አቶ ገዛኢ ረዳ 4.አቶ ተወልደ ገ/ሥላሴ 5 አበበ ገ/ማርያም 6. አቶ ሙሉጌታ ደስታ 7. አቶ በላይ ባህታ 7 ቄስ ጽጌ 8. አቶ ወልደ ንጉሥ 9.አቶ ገብረጻድቅ ጸጋይ 10 ሃለቃ ጥላሁን እና በ እድሜ እጅግ ወጣቶች የሆኑትን ሳይቀር በሰቆቃ እየተሰቃዩ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች የሸሬ አውራጃ ተወላጆች ናቸው።
ብስራት-አማረም በበኩሉ ሌላው የሽብር ቡድን በመምራት ከ1970-1972 ዓ.ም. በየከተማው የፈጸሙትን ሽብርና ግድያ እንደገና እንመለክት።
ዓድዋ፦ በ1971 ዓ.ም. አካባቢ ዓድዋ ከተማ ከቀኑ 11 ወ/ሮ ጉንቦወርቅ የሚባሉ ጠጅ ነጋዴ ቤት በመግባት እጅ ወደላይ ብሎ ያስገደላቸው ሰዎች 1. መምህር ይሕደጐ 2.አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም 3. ፍስሃ የሚባል ወጣት ነጋዴ 4.አቶ ቢተው ብርሃነ ጠጅ ቤቱ ውስጥ እያሉ ሲገደሉ
ከመጠጥ ቤቱ ውጭ ደጃፍ ላይ ተገደሉ ደግሞ 1.አቶ አብርሃ አበራ 2. አቶ ገብረዝጊ ዓለማየሁ ይባላሉ። የመጠጥ ቤቱ ባለቤት ወ/ሮ ጉንቦወረቅ በታፋቸው ተመቱ፣ ግን አልሞቱም ። አቶ ተፈሪ ተክለሃይማኖትም-እግራቸው ተመትተው ቆሰሉ። በዚህ መልክ የብስራት አማረ የሽብር ኦፐረሽን ቡድን 6 ሰዎች ገድሎ 2 ሰዎች አቁስሎ ወጣ።
አክሱም፦ በመግድያ ፈጻሚ ክፍል (ፈዳይን) የተሰማሩ አክሱም ተወልደው አክሱም ያደጉ የከተማው መውጫ እና መግቢያ የሚያውቁት የአክሱም ልጆች እና ብስራት አማረ ከሚያስተባብረው የሽብር ግድያ የአፈና የእስራት እና የስለላ ቡድን ጉጅሌውን መርቶ አክሱም ከተማ በመግባት መምህር መልአኩ መንገሻ እና ሁለት አስተማሪዎች አስገድሎ አንድ ተማሪ አቁስሎ ወጣ።
መቀሌ፦ብስራት አማረ ከነቡዱኑ መቀሌ ከተማ ተሽሎክሉኮ በመገባት አለነ ቢሆን የሚባለው ታጋይ ከበረሃ ሸሽተው እጃቸውን ለደርግ የሰጡ እና የግ.ሓ.ት (ግምባር ሓርነት ትግራይ)አባሎች የነበሩ ከወያኔ እስር ቤት ከሞት አፋፍ ያመለጡትን እነ ተፈራ እነ ሃይለኪሮስ የመሳሰሉት ለመግደል መድኅን መልጐም ወደ ተባለ ቡና ቤት አለነ ቢሆን የተባለ የበረሃ-ታጋይ ገብቶ ሁሉም መጠጥ እየጠጡ እዛው ባሉበት እንዲረሽናቸው በመግባት ሁለት ሰዎች ገድሎ ከቡና ቤቱ ለማምለጥ ሲሞክር ከቡና ቤቱ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አልፎ የነብሰ ገዳዮቹ ቡደኑ እና የስለላው አቀነባባሪ እና መሪው ብስራት አማረ ግድያውን አስፈጽሞ ወደ በረሃው ተመለሰ።
ሽሬ-ከተማ ውስጥም ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈጸም ብስራትና ጉጅሌው ሽሬ ከተማ ገብተው ተከስተ አሰፋ የሚባል የፊታ/ አሰፋ ልጅ ከሦስት ጓደኞቹ ጠላ ቤት ገብተው እየጠጡ ሲዝናኑ ብስራት እና ጉጅሌው ተከታትሎ በመግባት ተከስተ አሰፋ እና ሦስቱ ጓደኞቹ ገድሎ አንድ አዛውንት የፖሊስ ጡሮተኛ አቁስሎ ወጣ። ብስራት አማረ በሁለት አውላዕሎ እና አዲግራት እና በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ሰላዮች እና ነብሰ ገዳዮች (ፈዳይን) በማሰማራት ተመሳሳይ ሽብር በሰው ህይወት ላይ መውሰዱ ይታወቃል። ብስራት አማረ በነበረው የደህንነት፤የስለላ እና የእስር ቤቶች (ሓለዋ ወያነ) ሃላፊነት ሲፈጽመው የነበረው የህ.ወ.ሓ.ት. ሽብር ስራ አሁንም እስከ 1978 በጥልቀት ሲያስፈጽም የነበረው የአፈና፤የመግደል ሰቆቃ ተግባር በተደራጀ መልኩ ቅርንጫፎቹ እንደተስፋፉ መዋቅሩ እንደሚከተለው ተዘርግቶ ነበር፡
ፖሊት ቢሮ የበላይ ሃላፊዎች
መለስ ዜናዊ፥ ስብሓት ነጋ፥ አባይ ጸሃየ
ደኅንነት ዋና ሃላፊ
ክንፈ ገ/መድኅን
የሓለዋ ወያነ የበላይ ተጠሪዎች
ሓሰን ሽፋ ቢተው በላይ
ብስራት አማረ፣ ዘርአይ ይሕደጎ (ዘርአይ ማንጁስ)
የስለላ እንዲሁም የሲቪል እና ሙርኰኞች እስር ቤት
የሴት ሲቪል እስር ቤት(063)
የወንድ ሲቪል እስር ቤት (062)
የሙርኰኞች እስር ቤት (061)
ወዲ ሻምበል አበበ ዘሚካኤል ታደሰ መሰረት የታጋዮች እስር ቤት
የሴት ታጋይ እስር ቤት (065)
ወንድ ታጋይ እስር ቤት (064)
እነኚህ አምስት ዋና ዋና ክፍሎች ሰቆቃ የርሸና/ግድያ የአፈና-ስራዎች የሚካሄድባቸው ፈጻሚ እና አስፈጻሚ ክፍሎች ናቸው።
ከዘሚካኤል ለገሰ (ወዲ ሻምበል) ስር
064 የሚቆጣጠረው ታደሰ 065 ደግሞ ብርሃነ ሲሆኑ
ከብስራት አማረ ስር
061 ካሕሳይ ቆራጽ
062 ግደይ ወዲ ፊውዳል
063 ወዲ ኮበል የመሳሰሉት አሉበት።
እነኚህ እስር ቤቶች የሚገኙት “ግህነም” ከሚበላው ቦታ ፀገዴ ውስጥ ነው። እስረኞች የሚታሰሩበት ክፍሎች ብዛት እስከ 150 ክፍሎች ሚደርሱ ሲሆኑ፤ ከመሬት በታች ሁለት ሜትር ጥልቀት ተቆፍሮ ከመሬቱ ተመሳስሎ የተሰራ በ4,500 የወታደር ሙርከኛ እስረኞች ጉልበት ነበር የተገነባው። ተገደው ይህ እስር ቤት የሰሩት ሙርኰኞችም እዛው ገብተው እንዲታሰሩ ተደረገ።
ይህ ቦታም አሰቃቂ እና ሰቆቃ የሚካሄድበት አስፈሪ እስር ቤት የሚጠብቁት ዘበኞች ብዛት 500 ታጋዮች ሲሆኑ ሁሉም ጉልበተኞች እና ደንዳና ቁመና ያላቸው ምልምል ታጋዮች ናቸው። መጀመሪያ የተረሸኑት እንኚህ 4,500 የሞሆኑ እስር ቤቱን የቆፈሩት ሲሆኑ ከመላይቲ ኢትዮጵያ ጎሳዎች የተውጣጡ ወታደራዊ ምርኰኞች ይሁኑ እንጂ አብዛኛዎቹ አማርኛ ተናጋሪ አማራዎች ነበሩ።
ምርኮኛ እየተባላ በሰላም እጁን የሰጠ ደርግ ካድሬዎች፤የደርግ አባል፤የደርግ አገልጋይ ወ.ዘ.ተ. እየተባለ ሴቶችም ሳይቀሩ ከጐንደር፤ወሎ ጐጃም በገፍ ወደ እዚሁ የምድር ገሃነም እየተወሰዱ በብዙ ሺሕ ሚቆጠሩ ሕይወት በመለስ ዜናዊ፣በሰብሓት ነጋ እና አባይ ፀሓየ አርከበ ዑቕባይ የመሳሰሉት የዛው ግደለው ደብድበው አፍነው የሚል ትእዛዝ በመስጠት ትእዛዛቸውን ለሚፈጽመውና ለሚአስፈጽመው ለብስራት አማረ በሚተላለፍለት መመሪያ ተረሻኞቹ የሚቀበሩበትን ጉድጓድተቆፍሮ በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች መቃብር በዓይኑ ያየ ሰው ዘግናኝ እና አስፈሪ በመሆኑ ጤነኛ እንቅልፍ መተኛት ያስቸግራል። በጣም የሚገርመው 10 ሺህ ሰው ገድያለሁ ሲል የተደመጠው ብስራት በሰው ልጆች ላይ የፈጸመውን ግፍ ይቅርታ ጠይቆ ከመጸጸት ይልቅ ብስራት አማረ አሁንም አሜሪካ አገር እየኖረ ለአለቆቹ ጥብቅና ቆሞ ማየት እጅግ ያሳዝናል።
በብስራት አማረ እጅ በጥይት ተደብድቦ የተረሸነው ዜጋ እሱ-ከሚያምነው በላይ እጅግ በርካታ ህይወት ጠፍቷል። ብስራት አማረ በነበረው የስለላ፤የምርመራና የእስር ቤቶች ተቋም እና የፈዳያን/የገዳይ ቡድን አቀናባሪነት ስልጣን ተጠቅሞ በፈጸመው ግፍ በሕግ ቋንቋ ጀነሳይድ ነው። ለፈጸመው ወንጀል በዓለም የሰብአዊ መብት ተመጓች ፍረድ ቤት መቅረብ አለበት። ይሄ ካልሆነ የሰው ህይወት ከድመት ህይወት ጋር የሚያወዳድሩት እነ ብስራት አማረ የመሳሰሉ የህ.ወ.ሓ.ት ቁልፍ ሰዎች በሰው ልጆች ደም እያላገጡ መኖራቸውን ሊቀጥሉ ነው ማለት ነው። ይህ ሁሉ ደም አፍስሰው ለሰው ልጆች መብት እና ዲሞክራሲ ተቆርቋሪ ንጹሃን ነን ሲሉ ላደመጠ ውስጣቸው ለሚያውቅ ሰው እጅግ ይዘገንናል። ስለዚህ ባንድነት ሆነን አቤት ማለት አለብን። ይባስ ብሎ አፋቸው መዝጋት ሲገባቸው እና የሰሩት ግፍ ሳይቆጫቸውና ይቅርታ ከመጠየቅ ፈንታ የበደሉትን ዜጋ እንደገና ሳያፍሩ ሲዘልፉት እና ከተሰደደበት አገር ሰላም ሲነሱት ይታያሉ።
ፋሽስቱ፤ነብሰገዳይ፤ ሽብርተኛ እና ቅጠረኛው ህ.ወ.ሓ.ት በግንቦት ወር 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ እንደተቆጣጠረ 1-ብስራት አማረ 2-ታደሰ መሰረት 3-ዘርአይ ይሕደጐ/ዘርኣይ ማንጁስ በቀጥታ,ማእከላዊ ምርመራ በሰቆቃው ማእከል ውስጥ ተመደቡ።ከ1983ዓ.ም ጀምሮ ‘መላ አማራ ሕዝብ ድርጅት’ በሚባለው ሰላማዊ ድርጅት በአባሎች እና አመራሮች ላይ ብዙ የሰቆቃ መርመራ በማካሄድ ባልዋሉት ወንጀል ፈጽመሃል እየተባሉ አዲስ አበባ ማእከላዊ ምርመራ ድረስ ከየክፍለሃገሩ እየተለቀሙ ሰቆቃ እንዲፈጸምባቸው ቁልፍ የደህንነት ሰልጣን በመያዝ ተዋናዮች ከነበሩት በርካታ የህ.ወ.ሓ.ት. ባለስልጣኖች አንዱ ብስራት እና ከላይ የተጠቀሱ እና የመሳሰሉ አረመኔዎች ናቸው። እነ ፕሮፌሰር አስራት ስቃይ የዚህ ነብሰገዳይ እና ሕብረተሰብ አሸባሪ ቡድን ውጤት ነው። እነ አሰፋ ማሩ የተገደሉት በዘርአይ ይሕደጐ እና ግበረ አበሮቹ በመሳሰሉት ነብሰገዳዮች ነበር የተገደለው። አንደነት ቦኖረን እና በዚህ ዓለም ሕግ የሚከበር ቢሆን ኖሮ እነ ብስራት አማረ በሰው ልጆች ህይወት ቀልደው ሲያበቁ ዛሬም እየተንደላቀቁ ስለ ዲሞክራሲ እና የሰው ልጆች መብት መከበር በወያኔ ጀሌዎች የሚካሄዱ የዜና ማሰራጫ ማእከሎች እየተጋበዙ ሕሊናቸውን ሳይወቅሱ እንደ ፒላጦስ ከደሙ ንጹህ ነን እያሉ አፋቸው ባልዘላበዱ ነበር። ጠመንጃ አነግበው በዜጎች ላይ የሰሩት ግፍ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው የፈጸሙት። እነዚህ ሰዎች አንድ ቀን እንኳ ስህተት ፈጽመናል አላሉም።
እነ ብስራት አማረ “ሽብርተኛው እና ነብሰ ገዳዩ ወያኔ”ኤርትራ እንዳስገነጠለ፡የኢትዮጵያ ጥቅም እና ሉአላዊነት አልተከበረም ብለው ያዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ፤እንደ ዱር አራዊት በፖሊሶች እየታደኑ እና እየተዋከቡ ማእከላዊ እና የመሳሰሉት አሰቃቂ እስር ቤቶች እየተወረወሩ የተገረፉ እና ልዩ ልዩ ሰቆቃ የተፈጸመባቸው ስናስታውስ የእነ ዘርአይ ይሕደጐ እና ብስራት አማረ የገነቡት የስለላ እና የሽብር ቡድን ያከናወነው-ዘግናኝ ገፍ ብዙ ተማሪ የሚያስታውሰው ወቅት ነው።
በ1984 ዓ.ም. በአርባ ጉጉ እና በሌሎች ቦታዎች ብስራት አማረና አጋሮቹ የሲቪል ልብስ ለብሰው በወቅቱ የነበረው ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ፤መለስ ዜናዊ፤በረከት ስምኦን እና የመሳሰሉ ባለስልጣኖች ትእዛዝ እና እውቅና ያለ ቦታው የሚኖር ተስፋፊ ነፍጠኛ እያሉ ከተገንጠይ ቡድኖች ጋር አባሪ አስተባባሪ ሆነው በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የተፈጸመው ግፍ ተጠያቂዎች ናቸው። በመጨረሻ ላይ በጠመንጃ ሃይል ተደግፈው በዜጎች ላይ ቁጥር የሌለው ግፍ
ከፈጸሙ በኋላ ባዲስ አበባ ኗሪ እና በሌሎቹ ዓይን ውስጥ ስለገቡ ስብሓት ነጋ እና መሰል አለቆቻቸው አውቅና ተደግፈው ዘርአይ ይሕደጐ/ዘርአይ ማንጁስ ወደ እንግሊዝ አገር ለትምህርት ብለው ላኩት። ብስራት አማረ.ደግሞ ወደ አሜሪላ ላኩት። የሁለቱ ድብቅ ተልእኮ ግን ዘርኣይ ማንጁስ አውሮጳ ውስጥ ካሉት የትግራይ ተወላጆች አስተባብሮ ስደተኛው እና ተቃዋሚ ሃይሎችን እንዲሰልል (በነገራችን ላይ ዘርኣይ በማዕርጉ የወያኔ ሻምበል ነው) በዚህ እንቅስቃሴ ተሰማርቶ የዓድዋ የሽሬ የአክሱም ተወላጅ ተባባሪዎች ሲያገኝ ስለላ ትምህርቱን እየተማረ;በተሰማራው ተልእኮም እየፈጸመ ይገኛል። በዚህም ወያኔ ከፍተኛ የገንዘብ ጠቀሜታ እና እንክብካቤ ይደረግለታል። ዘርአይ ማንጁስ ትውልዱ አክሱም ነው።
ብስራት አማረም ያው ትውልዱ አብረው አክሱም ናቸው። ብስራት ‘ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ’ እንደሚባለው የፈጸመው ግፍ እና ሰብአዊ ወንጀል አይታወቅብኝም በሚል ራሱን በማታተለል ጨዋታ ተጠምዶ አሜሪካ ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያውን የወያኔ ተቃዋሚዎችን ሲዘልፍና;ለሻዕቢያ ጥብቅና ቆሞ የሻዕቢያን ፖሊሲ የሚቃወሙ የትግራይ ህወሓት ታጋዮችና ኗሪዎችን ሲያሸብሩ ከነበሩት ከነ ኰሎኔል ይትባረክ.የመሳሰሉ ከጥቂት እሱን መሳይ የወያኔ ካድሬዎች ጋር ሆኖ ሕብረተሱን በመከፋፈል በየቤተክርስትያኑ እና ትግራይ ተወላጆች ማሕበራት እጁን እያስገባ አንድነት እንዳይኖር የመለስ እና የስብሓት ነጋ ተልእኮ ለብዙ ዓመታት ያለ ስጋት በመፈጸም ላይ ይገኛል። ያ አልበቃ ብሎ አሉላ አባ ነጋ በተባለ የመለስ ዜናዊ ካድሬዎች ፕሮፓጋንዳ መጨፈሪያ ፓል ቶክ ውስጥ እሱ እና ኮሎኔል ይትባረክ በመሆን እኔ ባቀረብኩት የ1977ቱ የዝርፍያ ሰነድ ከመተቸት ይልቅ አንዴ “ሊሆን ይችላል”ሲል አንዴ ደግሞ “ገብረመድኅን አርአያ ተደረገ የተባለው ዝርፍያ የሚያውቅበት ስልጣን ወይንም ግንኙነት አልነበረውም”,እያለ የአለቆቹን ንቅዘት/ሙስና እና አምባገነንነት ለመከላከል-ከመዘላበድ አልፎ እኔኑን ወደ ተራ ዝልፊያ በመግባት ከንቱ ሙከራ ማድረጉ ስታዘበው፤ ይሉኝታ የማያውቅ አንድ ፍጡር ባደባባይ እርቃኑን,ጥሎ ቢራመድም ደንታ እንደሌለው ያሳያል። ለድርቅ የተሰጠ ዕርዳታ ሁኔታ ማወቅ ከነበረበት እንደ እነ ተኽለወይኒ አሰፋ የመሳሰሉት እንጂ ገ/መድኅን አርአያ የሚያውቀው ነገር የለም ሲል ፓል ቶክ ውስጥ ተናግሯል ሲሉ ሰዎች ነግረውኛል። ስልጣን ካልነበረኝ ተክለወይን አሳፋ እና እኔ አርዳታ ከሰጡት ፈረንጆች ጋር ቁጭ ብየ ገንዘብ እየቆጠርኩ የሚያሳየው ዓለም የተመለከተውን የቢቢሲውን ፎቶግራፍ “ ገ/መድኅን አርአያ ከሁኔታው ጋር የተያያዘ ስልጣን ካልነበረኝ የብስራት አማረን ምሳ እና እራት ቂጣ ስጋግር የተነሳሁት ፎቶ ነው ሊል ነው?”የመለስ ዜናዊ ካድሬዎች እና ብስራት አማረ ለማያውቃቸው ሰው ውሸታቸውን ሲዘላብዱ ለሚሰማ እውነት ይመስላቸው ይሆናል። ለዚህም ነው ሰውየው ውሸታም ነው የምላችሁ።አውነታው ለምናውቀው ግን ከሚዘላብዱት ቅጥፈት የተለየ ጉድ የተሸከሙ ጉደኞች ናቸው። የትግራይ ተወላጆች ከነዚህ ውሸታሞች ራሱን ማግለል አለበት። ያ ሁሉ ግድያና ግፍ ፈጽመው ምንም የማይሰማቸው አረመኔዎች ናቸው። ሳይነካ ኑ ንኩኝ እያለ የሚወተውት ለችግር ራሱን የሚጋብዝ ፍጡር እንደ ብስራት አላየሁም።
ብስራት ለወያኔ መቆሙ የራሱ መብት ነው።ነግር ግን ከሰራው ገበና ሳይጸጸት እንደ ገና በላያችን ላይ ሊወጣብን ሲሞክር አስገራሚ ነው። ወያኔ በግፍ የተጨማለቀ ድርጅት ነው። አንድ ቀን በግህንም የተፈጸመው የግፍ ግድያ በ1980 ዓ.ም. በግንቦት ወር ደጀና ውስጥ ለውይይት ተሰብስበን አባይ ጸሃየ በድንገት “ብፆት ግህንም ውስጥ የታሰሩ ስቪል እስረኞች አና ወታደሮች የሰው ዘር በግፍ እየገደልን ነው …” ካለ በኋላ ሳያስበው ድንገት ከሕሊናው ገፍትሮ የወጣው ንግግሩ አስደነገጠው፡ ፊቱ ሁሉ ተለዋወጠ እና ከስብሰባው ተነስቶ ሄደ። ህ፣ወ.ሓ.ት. የመላእክት ድርጅት ነው፤በሰው ልጆች ላይ ግፍ አልፈጸምንም እያለን ያለው ብስራት አማረ እየተከላከለለት ያለው የፋሺስቶች ድርጅት በኔ ላይ የተደረገው የመግደል ሙከራ እና የአካል ማጉደል ወንጀል ብስራት እንደ ዲሞክራሲ ይመለከተዋል። የህ.ወ.ሓ.ት አረመኔ ስራ በተመለከተ ለወደፊቱ በዝርዝር የማቀርበው አሰቃቂ የወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. አመራር የፈጸመው ደርግ በቀይ ሽብር ያስደነገጣቸው ልብ ያልሰሩ ታዳጊ ወጣቶች ወደ ትግሉ ከተቀላቀሉ በኋላ በነዚህ ላይ አመራሩ ያሳለፈው (ከ1970 ዓ.ም-1972 ዓ.ም) የርሸና ውሳኔ አቀርባለሁ። እነኚህ የሞት ቅጣት የተወሰነባቸው እና እርምጃ የተወሰደባቸው ታጋዮች ዕድሜአቸው ለአቅመ አዳም ያልደረሱ የ13 እና 14 ዕድሜ ወጣቶች ናቸው። ሁሉም የበረሃው ኑሮ መቋቋም አቅቷቸው፤ወላጆቻቸው የናፈቁ ህጻናት ነበሩ። ወላጆቻችን ናፍቀውናል እና ወደ እየ ትውልድ ቀያችን መመለስ እንፈልጋለን የምትሉ አስታሰውቁን ይፈቀድላችኋል ብሎ አመራሩ ካታለላቸው በኋላ፡ እንሄዳለን ብለው እራሳቸውን ያጋለጡ ልጅ እግር ታጋዮች ከየቦታው ከሠራዊት ማሰልጠኛ እና ከታጋይ ጋር የተቀላቀሉትን ሁሉ እየተለቀሙ ተረሽነዋል። አረመኔው ወያኔ እነኚህ በጥይት ደብድቦ የገደላቸው ህጻናት “ናብ እነይ” (ወደ እናቴ) በሚል ቅጽል ይጠራቸዋል።
የእነኚህ ወጣቶች ብዛት በጣም በርካታ ስለነበር፤
1ኛ ፃኢ ሓለዋ ወያኔ ወዲ ሻምበል፤ዘርኣይ ይሕደጐ እና ሙሉጌታ ዓለምሰገድ
2ኛ ዓዲ በቕሊ 06 ዓለምሰገድ እይንቺ እና ተስፋይ ጡሩራ
3ኛ ዓዲ ጨጓር 06 - ድልዊ- ብስራት አማረ- እና አሰፋ ጉሬዛ
4ኛ ሱር 06 ጆቤ አበበ ተ/ሃይማኖት እና ኣወተ ተስፋይ
6ኛ ባኽላ 06 አበበ ዘሚካኤል፤ሙሉጌታ ወዛም (ማኢ ዶ አለክን)
በእነዚህ ስድስቱ-ሓለዋ ወያኔ በወያኔ አመራር ትዕዛዝ እየተመሩ ተከፋፍለው የተረሻኞቹ ስም ዝርዝራቸውን በመስጠት ለረሻኝ ክፍል በመስጠት ህጻናቶቹ እንዲረሸኑ ተደርጓል። ይህ ጉድ የሚያወቁ አንዳንዶቹ ጆሯቸውን ደፍነው አውቀው እንዳላወቁ ሆነው ውጭ አገር የሚኖሩ አሉ።
ሁኔታው በጣም,አስቀያሚ እርምጃ ስለነበር፤ በታጋዩ እና ህዝቡ ቅርታ ስለፈጠረ አመራሮቹ ከዚህ ተነስተው አባይ ጸሃየ ፤ስብሓት ነጋ እና መለስ ዜናዊ በየቦታው ያሉት ታጋዮችን በማነጋገር ለድርጅቱ ህልውና ስንል እርምጃ ወስደንባቸዋል እያሉ የታጋዩ ቅሬታ ለማቀዝቀዝ ሞከሩ። ለሕዝቡም በክፍሊ ሕዝቢ አማካይነት/ሕዝብ ግንኙነት በኩል ተመሳሳይ-ዘመቻ በማካሄድ ለመሸፋፈን ሞከሩ። የአሁኑ ጥያቄው የነዚህ ህጻናት ህይወት በዋናነት ተጠያቂው ማን ነው?አቅመ አዳም ያልደረሱ ህጻናት ለምን እንዲረሸኑ ትዕዛዝ ተሰጠ?ተጠያቂው አሁን በስልጣን ላይ የተቀመጠው ህ.ወ.ሓ.ት ነው። ይህ ወንጀለኛ እና ፋሺስታዊ ባሕሪይ ያለው ድርጅት በማን አለብኝ የሚፎልሉ ካድሬዎቹ ለነዚህ እና ለብዙ ሺህ ህይወት መቀጠፍ ተጠያቂዎች ናቸው። ጊዜው ይርዘም ይጠር በሕግ መጠየቅ ይኖርባቸዋል።
ኢትዮጵያ በነፃነቷ ለዘላለም ትኑር!
ገብረመድኅን አርአያ -ፐርዝ አውስትራሊያ
No comments:
Post a Comment