Friday, August 27, 2010

ሶማሊያ ኢትዮጵያን ስትወረር የወያኔ መሪዎች “ዜግነታቸው” ሶማሌ አስብለው ነበር

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) እና ሓይካማ (ትግርኛ) መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 begin_of_the_skype_highlighting (408) 561 4836 end_of_the_skype_highlighting Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109 ሶማሊያ ኢትዮጵያን ስትወረር የወያኔ መሪዎች “ዜግነታቸው” ሶማሌ አስብለው ነበር ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com (ከየወያኔ ገበና ማሕደር ዓምድ)

ይህ ዝግጅት ሁሌም በኢትዮጵያን ሰማይ የህዋ ሰሌዳ እየተዘጋጀ የሚቀርብ የወያነ ትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት የፈፀማቸው ግፎች እና ብሔራዊ ወንጀሎች የሚቀርብበት ዓምድ ነው።በዛሬው ዓምድ የማቀርብላችሁ ካነበብኳቸው የትግርኛ መጽሐፍቶች አንዱ በቅርቡ ለአንባቢ የተሰራጨ ጋህዲ ቁጥር 3 የትግርኛው ዕትም ካገኘሁት እጅግ አስገራሚ የሆነ የተለያዩ የወያነ ትግራይ ገበናዎች የሚዘረዝር ወያኔን ከመሠረቱት 11 ሰዎች አንዱ በሆነው አቶ አስገደ ገብረስላሴ ወ/ሚካኤል ያጋለጠው አዲስ የወያኔ ማሕደር ይሆናል።

አስገደ ገ/ስላሴ በጋህዲ ቁጥር 3 መጽሐፉ ላይ በገጽ 144 ምዕራፍ 12 « የሶማሊ መንግሥት ለወያኔ ሠራዊት ዕድገትና ጥንካሬ ያደረገው ዕርዳታዊ አስተዋጽኦ » በሚል ርዕስ የሚከተለውን ሰነድ ባጭሩ ጨምቄ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ተርጉሜ ለአማርኛ አንባቢዎች አቅርቤዋለሁ። የዘመን አቆጣጠሮቹ እንደምታውቁት በቋንቋችን ስጽፍ ማሳሰቢያው በፈረንጅ አቆጣጠር ካላልኩበት በቀር በኢትዮጵያ አቆጣጠር መሆኑን ሁሌም ተገንዘብልኝ። በዙህ ሰነድ ውስጥ በትርጉም ስሕተቶች ለሚመጡ ጉዳዮች ሃላፊነቱ የኔው እንጂ የደራሲው አይደሉም።

« ከሶማሌ መንግሥት ጋር ግንኙነት የተጀመረው ወያኔ ሱዳን ውስጥ ጽ/ቤቷን ከከፈተችበት ከ1969 መጨረሻ ጀምሮ ነው። የግንኝነቱ አመሰራረት የተጀመረው ሱዳን ውስጥ ከነበረው የሶማሊያ ኤምባሲ ሲሆን፤ጥቂት ሳይቆይ ከሶማሊ መንግሥት ጋር በቀጥታ ግንኙነቱን መሠረተ። ግንኙነቱ እንደተመሠረተ ማንኛውም የውጭ አገር ግንኙነትና እንቅስቃሴ፤የወያኔ አባሎች ወደ ውጭ አገር ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ በሶማሌ ዜግነትና የሶማሌዎች ስም የያዘ ቪዛ እና ፓስፖርት በመያዝ ነበር የሚንቀሳቀሱት።

የሶማሌ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር በሃይለኛ ጦርነት ተወጥሮ እያለ፤መሳርያ እንደሚያስፈልገውና በዛ ሃይለኛ ውግያ የመሳርያ ቁጠባ ማድረግ እንዳለበትና በችግር እንደተወጠረ እያወቀም ቢሆን ለህወሓት ያደረገው ዕርዳታ ወደር ለውም። በጥቂቱ የሚተለው ነው።

1- ሁሉም የወያኔ መሪዎችም ሆኑ የሕዝብ ግንኙነት ጉዳይ ለማስፋትና ለማጠናከር የሚላኩ ከፍተኛ የወያኔ ካድሬዎች ወደ አውሮጳ፤አሜሪካና ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ሲንቀሳቀሱ ሰላማዊ የዜግነት ዓለም ዓቀፍ ሕጋዊ የመንቀሳቀሻ ሰነድ መያዝ ስለሚኖርባቸው፤ ወደ 50% የሚጠጉ የወያኔ የማዐከላዊ ኮሚቴ አባሎች እና ካድሬዎች የሶማሌ ባለሥልጣኖች / ቪ አይ ቪ/ ቪዛ ተሰጥቶአቸው ስማቸውን ቀይረው በመላው ዓለም እንዲንቀሳቀሱበት የሚያስችላቸው በመፍቀድ በውጭው ዓለም ያለ ምንም ችግር ትልእኮአቸው እንዲያከናውኑ ከፍተኛ አስዋጽኦ አድርጓል።

2- ከ15 በላይ የሚሆኑ የወያኔ ታጋዮች ምግባቸው፤መኝታቸው፤ወጪአቸውና አስፈላጊው በጀት ሁሉ የሶማሌ መንግሥት በመሸፈን አለ የተባለ የከባድ ብረት ማሣሪያዎች፤መድፎች፤ታንኮች፤ሞርታሮች፤ዓየር መቃወሚያ -ሚሳይሎች ታንከኛ፤እና ሁሉም ዓይነት ያካተተ ፀረ ታንክ ፤ፀረ ተሽከርካሪ፤ፀረ ሰው ፈንጂ ለረዢም ጊዜ አሰልጥለውልናል(ገጽ 144) ለምሳሌ እነ ጀላኒ ወዲ ፈረጅ፤ እነ ገብረ ሓፂን፤ብርሃነ አርብጂ የመሳሰሉት ታጋዮች ለአንድ ዓመት ሙሉ 12 ሰዎች ሶማሌ ሄደው ማንኛውንም ዓይነት ከባድ መሳርያ ሰልጥነው ለድርጅቱ ከባድ መሳርያ ስልጠና ወሳኝ ሚና የተጫወተው ይኸኛው ክፍል ነበር(ገጽ18)።

3- እነኚህ ሶማሌ ውስጥ የሰለጠኑ ታጋዮች ወደ ትግራይ ሜዳ በመመለስ የወያኔ ታጋዮችን በሰለጠኑበት የዘመናዊ ከባድ መሳርያዎች ስልጠና አሰልጥነው በርከት ያሉ የከባድ ብረት መሳሪያ ተኳሽ በታሊዮን ቡድን ማነፅ ተጀመረ።

4- የሶማሌ መንግሥት ህወሓት ከውጭ አገር አምባሳደሮች ጋር እንደ አንድ ራሱን የቻለ አገር ተደርጎ እውቅና እንዲያገኝ በማለት ሶማሊያ ዋና ከተማ መቃዲሾ ከተማ ውስጥ እንደማንኛቸውም አገሮች ወያነ ትግራይም ኤምባሲ ጽ/ቤት ተከፍቶለት ከተቀሩት የመላ ዓለም አገሮች አምባሳደሮች ጋር ጎን ለጎን በማስቀመጥ እንዲታወቅ አጽተዋጽኦ አድርጓል።

5- ህወሓት የሶማሌ መንግሥት የሰጠውን ሰፊ የመንቀሳቀስ ዕድል ተጠቅሞ አስፋሃ ሓጎስ የሚባል የወያኔ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ከመላው ዓለም ጋር ለመገናኘት የሚያስችለው የራዲዩ ግንኙነት መስመር በመዘርጋት ከነረዳቶቹ ጋር ሶማሌ ውስጥ አስፈላጊው ግንኙነት ማድረግ ቻለ።

6- ያ ሶማሊያ ውስጥ አምባሲ ተከፍቶለት የነበረው የወያነ ትግራይ አምባሳደር ጽ/ቤቱን እንደ የዘመቻ መምሪያ (ቤዝ/መዋፈሪ) በመጠቀም የደርግን የዕለት ተለት ሁኔታ ዘገባ በማግኘት ብዙ ሥራዎችን እንዲከናወኑ ትልቅ ዕርዳታ አድርገውልናል።

7- ህወሓት ከቻይና መሣርያዎችን በመግዛትም ሆነ የግዢውን ገንዘብ ማስተላለፍ በኩል ሶማሌዎች ዕርዳታ አድርገዋል። መሣሪያዎቹ ከቻይና ተጭነው ወደ ሶማሌ ካቀኑ በሗላ ጭነቱን ተመልሰው የሶማሊ መኮንኖችና ሠራዊቶች እስከ ፖርትሱዳን በመሸኘት ያስረክቡን ነበር። ያ በጥቁር ገበያ /ኮንትሮባንድ ግዢ የተገኘው መሣርያ ግን በጋህዲ ቁጥር 1 እንደገለጽኩት ሻዕቢያዎች ሆን ብለው በሌብነት ዘርፈውታል። “ሆኖም ተጀምሮ ደርግ እስከ ተደመሰሰበት ድረስ በሕግም በኮንትሮባንድም በሶማሌ ስም ከውጭ ዓለም መሳርያ እየተገዛ በኤርትራ በኩል ይተላለፍልን ነበር። ሶማሌ ያደረገልን ዕርዳታ መተኪያ የሌለው ነበር።(ገጽ 16)

8- ለምሳሌ በሶማሌ ቪዛ ዜግነታቸው “ሶማሊያዊ” ተብለው በሶማሊ ቪዛ ሲጠቀሙ ከነበሩት

1- ግደይ ዘርአፅዮን

2- ስብሓት ነጋ

3- አስፋሃ ሓጎስ

4- አደም

5- ካሕሳይ በርሀ/ዶክተር ምስግና

6- ገብረመድህን መሐመድ ያሲን

7- ሥዩም መስፍን

8- መለስ ዜናዊ

9- ወረደ ገሠሠ

10- ጃማይካ ኪዳነ

11- ፀጋይ ጦማለው እና ብዙ በርከት ያሉ ታጋዮችና መሪዎች ነበሩ።

ባጭሩ የሶማሌ መንግሥት የሕዝብ አደረጃጀት ሥራዎች እንዲሁም በመላው ዓለም ውስጥ ያለ ምንም ችግር እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱ አስፈላጊውን የይለፍ እና የቪዛ የፓስፖርት እና የዜግነት መታወቂያዎች በመፍቀድ፤ከመላው ዓለም መሳሪያዎች እርዳታ እንዲያገኙ እና በግዢ ሚመጡትንም በማሃል አስፈጻሚ በመሆን ለድርጅታችን የሰራዊት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረገልን የሶማሌ መንግሥት ምስጋና ይገባዋል።

አንዳንድ ሰዎች ኢትዮጵያ በሶማሌ የስያድ ባሬ መንግሥት ስትወረር ህወሓት ወረራው ሕጋዊ ነው በማለት ይደግፍ ነበር። ስለሆነም ህወሓት የኢትዩጵያ ሉኣላዊነት ቅድሚያ አላስቀመጠም (ጉዳዩ አልነበረም) የሚሉ አሉ። ይህ እንዲህ ሆኖ እያለ፤ የወያኔ መሪዎች በተለያዩ መድረኮች “ሶማሌ በ1969/70 ዓ.ም ኢትዩጵያን ስትወር ደርግ ፀረ ሶማሊ ወረራ ሲመክት የደርግን አቋም እንደግፍ ነበር፤ የሶማሊ ወረራ በመኮነን ፀረ ሶማሌ እንንቀሳቀስ ነበር”፡በማለት አቶ መለስ ዜናዊ፤አቶ ሥዩም መስፍን፤ አቶ አባይ ፀሐየ እና አቶ ስብሓት ነጋ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አድምጬአቸዋለሁ፤ በተለያዩ መድረኮችም ተመሳሳይ መግለጫ ሲሰጡ ነበር። እዚህ ላይ በዚህ ጉዳይ እኔ ምስክርነቴን ለማስቀመጥ ከሆነ ህወሓት በትግሉ ወቅት- ትግሉ ተጀምሮ እስኪያልቅ የሶማሌ መንግሥት ያካሄደው ፀረ ኢትዮጵያ የወረራ ጦርነት ኢትዮጵያን የሚደግፍ የተቃውሞ ድጋፍ በጽሑፍም ሆነ በቃል የተጻፉ ወይንም ሲነገሩ በስብሰባም ሆነ በኮንፈረንስም፤በጉባኤዎቻችንና ስብሰባዎቻችን አንድም ቀን ሰምቼ ፤አይቼ ወይንም አንብቤ አላውቅም።ቢሆንም ጉዳዩ ለታሪክ ተመራማሪዎች እንዲተቹበት እየተወኩኝ ታሪኩ ግን እኔ እየመሰከርኩ ያለሁት ይህ ከላይ የገለጽኩት ሃቅ ነው ትክክለኛው ታሪክ።

ለመሆኑ በማን አገር እየኖረ ነው ሶማሌን የኮነነው? የስያድ ባሬ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ሲፈጽም ህወሓት መቃዲሾ ውስጥ ጽ/ቤት ከፍቶ ሲሰራ ነበር። የት ሆኖ ነው? እንዴት አድርጎ ነው ወረራውን ሲቃወም የነበረው? እንባቢዎች ትዝብቱን ለናንተው ልተው።”

በማለት አስገደ ገ/ስላሴ በጋህዲ ቁጥር 3 (ትግርኛ) መጽሐፉ ላይ በገጽ 144 ምዕራፍ 12 « የሶማሊ መንግሥት ለወያኔ ሠራዊት ዕድገትና ጥንካሬ ያደረገው አስተዋጽኦ » በሚል ርዕስ እነ መለስ ዜናዊ እነ ሥዩም መስፍን፤ስብሓት ነጋ… ኢትዮጵያዊነታቸውን ጥለው ሶማሊዎች ነን በማለት የሶማሊ ዜግነት በመያዝ ከፀረ ኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ሲተሻሹ እና ወረራውን ‘ግፋ በለው እያሉ ያገራቸውን ወታደራዊ የስለላ ምስጢር እየጠለፉ ለጠላት ሲያቀብሉና ሲለዋወጡ የነበሩበትን ሰነድ አጋልጧል። « ጀሮ እያደረ የማይሰማው የለም » የሚባለው ለካ ልክ ነው። መለስ ዜናዊ በእኛ በኢትዮጵያዊያኖች የሚታወቀው « አበበ » ነው፤ ሶማሌ ከሆነ በሗላ « የእስልምና » ስሙ ማን ይበል ይሆን ? ንስሃ አባቱ አባ ጳውሎስ ከስልምና ሲመለስ « ማተብ » አስረውለት ይሆን ? ቱፍ ቱፍ ! ከመዓቱ ይሰውረን ! ሁሉም ቻይ የኢትዮጵያ ሰማይ ማረኝ ጌታየ ! ደጋፊዎቹ እባካችሁ የለመዳችሁት ኩርፍያችሁ በኔ ላይ አትከምሩ « ትልቁን መስቀል ሲሳለም አይቼው ነው ሕገ ክርስትያኑን በመጣሱ ነው ሱባኤ ገብቶ ማተብ አስረውለት ይሆን ብየ የምጠይቃችሁ። ሁሉም ቻይ አምላክ ስንቱን ጉድ ችለህ ይችን ዓለም ታስተዳድራለህ ? ፍርድህ ምነው ዘገየ ?

አሁንም በድጋሜ እንዳትረሱ፦

አዲሱን መጽሐፌን ሓይካማ (ትግርኛ) እና « ይድረስ ለጎጠኛው መምህር » (አማርኛ) ለማንበብ ዕድሉን ያልገጠማችሁ በ408 -561-4836 መልክታችሁን ብትተው የትና እንዴት እንደምታገኙት ማወቅ ትችላላችሁ። getachre@aol.com

8 comments:

Anonymous said...

ena bitekemu min chiger alew ?enantem zare yalewen mengest btkawemuna yegorebet ager passport lemenkesakesha bttekemu hatyat aydelem yelek lela sehtetochachewen endyaremu btnegruachew melkam new

Anonymous said...

ከጌታቸው ረዳ
ውድ አንባቢ ሆይ!
እርስዎ የማን አህል እየፈጩ ነው ስህተታቸውን የማይነግሯቸው? ለምን ለኛ ብቻ ሃላፊነቱን ተውት? አገር በጠላት ሲወረር ከተላት ጋር ሆነው በምስራም በሰሜንም ሠራዊቱን ይገድሉና ያስገድሉ ነበር፡ አገር ከድተዋል ነው፡ ዋናው ቁም ነገሩ፡ ታዲያ እርስዎ ምን ሊያቦኩ ነው ስህተታቸውን በኛ ብቻ እንዲነገር የፈለጉት? ለነገሩ እርስዎ ስህተት የሚሉት ቃላት እኛ ወንጀል ብለነዋል እና ወንጀል እንጂ ስህተት አይደለም። ወይ አገሬ!

Anonymous said...

አይ አቶ ጌታቸው ይህን የ እብሪተኛውና ቕዠታሙን የ ዛእድባሬን ሱማሌ ወታደር መሆኑንን አላወቁትም ጀግናው የ ኢትዮጰያ ጦር ስራዊት .ሚልሻው ባንድነት ዳግም እንዳይነሳ ዘመናዊን መሳርያ ማርኮ ከምድራችን ተባሮ ዛሬ ካውሬ ራትነት ተርፎ ምከሮቸው የሚለው ድሮም ከወያኔ ጋር በመሆን ኢትዮጽያን እንዳልነበረች ለማድረግ የነበረው እቅዳቸው እውን ሳይሆን ስለቀረ በመቆጨት ነው. ወንጀለኛን ገልብጦ መቅበር እንጅ ምክር አያስፈልገውም.

Anonymous said...

Ato Getachew ,enbelna erso zare chaka bigebuna mesarya bianesu yalewen mengest lemetal, mesarya yezo yemimetawen yemengest wetader aynekutem?ena ya wenjel lihonbwo new?yan sel wendem wendemun yegdel malete aydelem yeamelekaket liyunet gen ...selezi endalkut bedebub wey bemrab kehone erso yeminesut geta yerdawo

Anonymous said...

enante zarem yemttekemut kalatoch siastelu megelbet mekber ...wonjel minamen keaymroachehum keandebetachhum melkam neger yefelek...weya mado honachu atakraru wondmoch...

Anonymous said...

wedya mado hono makrarat leneentnam albejem

Anonymous said...

ከጌታቸው ረዳ
ጤናይስጥልኝ ሰላም ለርስዎ ይሁን። አሁንም ደግሜ በድጋሚ ሁለት ነግረ ልበል። አንዱ ምክር ሲሆን ሁለተኛው ለጥያቄዎ መልስ ነው። የመጀመርአው ምክሬ፦ እኔ እየተጠቀምኩት ያለውን የአገራችን ግዕዝ ፊደል መጻፊያ እና ማንበቢያ መሳርያ ተጠቅሜ ከርስዎ እና ከተቀሩት ወገኖች እየተገናኘሁ ነው። እርስዎም እንደተቀረው በኢትዮጵያዊአን ባገራችን ፊደል ቢጠቀሙ ደስ ባለኝ ነበር። ይኸ ላቲን እየተጠቀሙ ያሉት ቋንቋችን አይደልም፤ ኢትዮጵያዊአን አይደለንም ብለው ማንነታቸው የካዱ እና የቋንቋ ጥላቻ ያደረባቸው የሕሊና ድውያን ብቻ ናቸው በላቲን እየተጠቀሙ አማርኛውን የሚጽፉበት። ስለዚህ ችግር ካልገጠመዎት በተቀር እንደተቀረነው ባገርዎ ቋንቋ ቢጽፉ ደስ ይለኛል።

አሁን ወደ ጥያቅዎ ልግባ፡- መሣርያ ታጥቆ መንግሥት መገልበጥና/ መለወጥ የነበረና እና የሚኖር ነው። መንግሥት ሲገለብጡ/ሲለውጡ ግን አገር ለመውረር ከመጣ የጠላት ሠራዊት ጋር ሆነው አገርንና አገርን ከጠላት ወረራ ለመከላከል እየተዋደቀ ያለው የአገር መከላከያ ሠራዊትን መግደል፤ለጠላት ማጋለጥ፤ምስጢር ማሳለፍ፤ጭራሽኑ ጠላት እሩብ/ግማሹን የምሥራቁን አገራችን መሬት (ከተማ/ገጠር/ድምበር…) እያቃጠለ፤ሴቶችን እየደፈረ፤ህፃናት ሽማግሌ እየገደለ፤ቤተክርስትያን፤ገዳማትን፤ቅዱሳት መጻሕፍትን መስጊድን በቦምብ እያጋየ ባለበት ቀውጢ የጠላት ወረራ ዘምን በጠላት ዋና ከተማ ውስጥ ተንደላቅቆ ከጠላት ጋር መመካከር አገርን ማዳከም እንዴት ተቀባይነት አለው ብለው እንዴት ደፈረው ይናገራሉ? ምንስ አገናኘዋል? ጠላት ኦጋዴንን ከተቆጣጠረ ትግራይ አይያዝልኝ እንጂ ጉዳየ አይደለም ብሎ የጠላት ወረራን ያላወገዘ፤ የሐረር ክፍል ሕዝብ ሥቃይ የሐረር ሕዝብ እንጂ ለትግራይ ሕዝብ ምኑም አይደልም ብሎ የወራሪን ወረራ ያላወገዘ የትግራይ ነፃ አውጪ በምኑ መለኪያ ነው ኢትዮጵያዊ ሊሆን የሚችለው? መንግሥት መገልበጥ ከሚሉት ቋንቋ እና አገር ከመሸጥ፤ባሕር እና ወደብ ለጠላት ማስረከብ በጣም የተለያዩ ናቸው። እንዴት የዋህ ነዎት? ወያኔዎች እንኳ ወንጀል መሆኑን ስላወቁ እኮ ነው “የሶማሌን ወረራ አውግዘናል” ብለው እዋሹ ራሳቸውን ከወንጀሉ እየተከላከሉ አሉት!!! ያለማውገዙ ወንጀል መሆኑ እነሱ አውቀውት ራሳቸውን ሲከላከሉ እርስዎ እንዴት እንደዚህ ያለ ገርነት ውስጥ ገቡ? አቶ አብርሃም ያየህ ከኤርትራኖች ጋር ቆመው በኤርትራ ራዲዮን እጃችሁን ለሻዕቢያ ሠራዊት አስረክቡ በማለታቸው ወያኔም ሆነ ትግራይ ህዝብ እና የተቀረው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ምን አይነት ቁጣ እና ምላሽ እንደሠጣቸው ያስታውሱታል? ጎንደር በድርቡሽ ሲወረር አፄ ዮሐንስ ወይንም የጎጃሙ ተክለሃይማኖት የጎንደር ሕዝብ ለማዳን ስነት ፍዳ ከፈሉ? የጎጃሙ ንጉሥ የንጉሥ ተ/ሃይማኖት ልጅ ድርቡሽ ማርኮ “በላት”! የትገራዩ ንጉሠ ነገሥት ዮሐንስ ሕይወታቸውን አጡ! ያ ሲሆን ግን አንዳንድ በሃይማኖት ያኮረፉ እስላሞች ከድርቡሽ ጋር ከወራሪው ጋር ሆነው ንጉሣቸውን አስገደሉ ሕዝባቸውን አስጨረሱ፤ ገዳማት እና ህፃናት፤

Getachew Reda said...

ክፍል 2-ንበረት እና ቤቶች ተቓጠሉ፤አገር ተደፈረ፤ ሴቱ ተደፈረ፤ ሃይማኖቱ እንዲለውጥ ተገድዶ እየተነዳ ወደ ሱዳን ታስሮ ተማርኮ ተገዘ! ታዲያ ይህ የመንግሥት ግልበታ ነው? አፄ ሚሊልክ የተናገሩትን ምክር ልሰንዝር እና ልሰናበተዎት “ የኢትዮጵያ ጠላት ባንዱ ወገን ትቶ ባንድ ወገን ቢሄድና ቢገፋ በኔ ወገን ከልመጣ ምን ቸገረኝ ብላችሁ ዝም አትበሉ። ያ ጠላት በመጣበት በኩል ሁላችሁም ሂዳችሁ በአንድነት ታግላችሁ ጠላታችሁን መልሱ። እስከቤታችሁ እስኪመጣ ዝም ብላችሁ አትቆዩ።......” ነበር ያሉት። ጠላት አገር ሲወር ከጠላት ጋር ማበር ወይንም ከጠላት ከተማ መገኘት፤ማበር፤መሰለል፤መንደላቀቅ፤ማበረታታት፤አገር ማዳከም፤ፕሮፖጋንዳ መንዛት…. የመሳሰሉት ወንጀል መሆኑን ወያኔዎች ስለተረዱ በባድሜ ጦርነት ወቅት ከሻዕቢያ ጋር የተዳበለ ሁሉ እንደጠላት ለምን ኮነኑት? ሊመልሱልኝ ይችላሉ? አስመራ ውስጥ ጠመንጃ ታጥቀው ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ የሽምቅ ተዋጊዎች መንግሥት ለመገልበጥ ነው አላማቸውና በባድሜ ጦርነት ወቅት ኢሳያስን ማውገዝ አይጠበቅባቸውም ብሎ አገር የሚደፍር ሴት የሚደፍር ቤተክርስትያናትን ቅርሳቅርስን አልባሳትን አቃጥሎ ዘርፎ በየትምህርት ቤቱ ህንፃ የሻዕቢያ ሠራዊት ሽንቱን ሸንቶበት ሲሄድ ካላወገዘ የማን አገር ነፃ አውጪና ተቆርቋሪ ነው? መልሱን ልጠብቅ። ለመሆኑ ወያኔ ኢትዮጵአዊ ድርጅት ነው? እንከራከር ማስረጃው በኩንታል ከራሱ ማህደር ማቅረብ ይቻላል። ወያኔ ወነጀል መሆኑን እያወቀው ራሱን ከላከል እንዴት አርስዎ በየዋህነት ተጠቁ?