ተደባዳቢ ወጣቶች እና አደባዳቢ አዝማሪዎችን በማዘጋጀት ሞገደኛነትን Violence ለኢትዮጰያ ሕዝብ በማሳየት ገንዝብ የሚሰራው Abbay TV
ከጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
3/25/26
አባይ ሚዲያ ብሎ ራሱን የሚጠራ
የዜና ማሰራጫ ጣቢያ ማን ነው? ይህ ጣቢያ ውጭ አገር በነበረበት ወቅት የብርሃኑ ነጋ ኢሳትና ግንቦት 7 እንዲሁም የኦንጎችን
ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት አንደነትን የሚያፍረሱ የስብሰባ ፐሮፓጋንዳዎችንና
ዜናዎችን እየለቃቀመ በየምደርኩ ካሚራውን እይተከለ ውጭ ለሚኖሮው ኢትዮጰያዊያ ማሕበርሰብ ሲያደናግር የነበረ ፥ሚዲያው ለብቻው ለማድረግ
ሁሉም ቦታ ካሚራውን የሚቀስር ስግብግበኛ እና አደገኛ ጣቢያ እንደነበር አንዳንዶቻችን የምናስታውሰው ነው።
ሁለት ከስተቶችን እንመለክታለን;
1ኛ አባይ ሚዲያ ከ 6 አመት በፊት አብይ አህመድ ሲጠራው አዲስ አበባ እንደገባ የሻዕቢያ ቱልቱላ ሆኖ ምን ያሰራጭ እንደነበር፥
2ኛ በቅርቡ በዚህ በተለጠፈው ቪዲዮ ጉዳይም እንመለከታለን
ወደ ርዕሳችን ከመግባታችን በፊት Ethiopian Semay ድረገጽ እሰካሁን ደረሰ በ25
ቀን ውስጥ 226,682 (ሁለት
መቶ ሃያስደት ሺ ስድስት መቶ ሰማንያ ሁለት) አንባቢዎች እንደተጎበኘ ተዘግቧል።
አሁን ወደ ርዕሳችን;
በቪድዮው ላይ እንደምታዩት ይህ ሚዲያ ጠብን የሚቀሰቅሱ የአዝማሪዎችን በመቅጠር (?) ግራ እና ቀኝ የመቀመጫ ጠረጴዛዎችን በማዘጋጀት በሴቶች ፍቅር የተለከፉ ሁለት ጠበኛ “የሴት እና ወንድ
ቡድኖችን” በማስተናገድ ‘’የምዕራባዊያን /ሥርዓተ-አልባ\ ወጣቶችን’’ ባሕል በመቅዳት፤ ተደባዳቢ ወጣቶችና የአደባዳቢ አዝማሪዎችን የጠብና ድብድብን
ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳየት፣ ሃገር ተረካቢው ወጣት ጸብን በመመገብ ለገንዘብ ሲባል አደገኛ ባህል እያስተማረ ነው።
እንደሚታወቀው መጥፎ መንግሥት ባለባቸው ሃገሮች አምባገነንነትን ብቻ ሳይሆን ፥ ብክለትን ፥
ንቅዘትን፥ ስደትን ፥የወደፊቱ የሃገሪቱ ዕድል የሚወስን ተረካቢው ወጣት ሕሊናው፤ በዕጽ ፥ በግብረ ሰዶምነት ፥ በመጠጥ እና በቁማር እንዲበላሽና የምዕራቡን ዓለም ‘ጋጠወጥ’ ወጣት የሚሰራውን ብልግና እና ባሕሪ
በመቅዳት ኢትዮጵያ ወስጥም ወጣቱ በቡድን እየተቧደነ እርስበርስ በመደባደብ ብሩህ ተስፋ ያለው ወጣት እንዳይገኝ መንግሥትና ሚዲያዎች በሃገሪቱ ተረካቢ ትውልድ
ላይ አፍራሽ ሚና እየተጫወቱ ነው።
ለብዙ አመታት በተለይ ደግሞ
በዚህ 6 አመታት አዲሰ አበባ ውስጥ እያየነው ያለው ትውልድ፤ ለገንዝብ ምንጭ ሲባል ወላጆቻቸውን በመግደል፤ በነጠላ
እና በገፍ እየተደራጁ “ሰውን በማገት” ሕጻናትን ከበረንዳ እያፈሱ ከወረበላዎቹ ጋር በምስጢር የሚሰሩ ለወረበላ የሐኪሞች ቡድን በመሸጥ ሕጻናቱ
ከነ ሕይወታቸው እንደ ፍየል እየታረዱ ልባቸው
እና ኩላሊቶቻቸው ለታመሙ
ሃብታሞች በገንዘብ በመሸጥ
የደራ ገበያ ሆኖ እሰካሁን
ድረስ ሃገር ወዳድ አርበኛ ዩቲበሮች
ራሳቸውን ለአደጋ በማጋለጥ
ወረበላ ወጣቶችን ወደ ሕግ በማቅረብ የሃገራችን ወጣቶች ምንኛ ጨካኞችና ወንጀል ውስጥ እንደተዘፈቁ ብልሹ ባሕሪያችው እያሳዩን ነው (ለነዚህ የዩቲበር አርበኞች
ምስጋናየ የላቀ ነው)።
ኢትዮጵያ ውስጥ ክፉ ራዕይ ይዘው የተነሱ ሁለት የፋሺት ሥርዓቶችን አይተናል። ክፉ ራዕይ የዘው የማይለቅ የፖለቲካ
በሽታ ያሰረጩብን መሪዎች መለስ ዜናዊ እና የመለስ ራዕይ እየጠባ ያደገው
አብይ አህመድ ሥልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ ወጣቱ በክፉ ባሕል ተለክፎ መውጫ በር አጥቶ
የሃገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ተቆልፎበት ቤተሰቦቹ እና ማሕበርሰቡን በማሸበር ላይ ነው።
ቪዲዮው ላይ እንደምታዩት Abbay TV - ዓባይ ቲቪ የሚባለው ወጣቶችን የሚያደባድቡ አዝማሪዎችን በመቅጠር ፣ ጎረምሶች በሴቶች ፍቅር እይተለከፉ
(ያውም ባለትዳሮች!!) እርስበርስ እንዲደባደቡ በስዕለ ድምጽ (ቴለ-ቪዥን) እየቀዳ ለሕዝብ በማሳየት የወጦችና የባለትዳሮች ድብድብ እንደ ሥልጡን ባሕል ተቀባይነት እንዲያገኝ
ሕበረተሱብን ጭንቅላት
እያሳሳቀ በመበከልላይ ነው።
ኢትዮጵያን ለማዳከም ከተሰሩት
ብከላዎች ወስጥ ይህ የሳብቨርዢኑ (የብከላው) አንዱ አካል ነው። አኢትዮጰያ ውስጥ የተሰሩብንን የበከላ መንግዶችና አይነቶች (ሰልም ሳብቨርዢን) ምንነት ለተከታታዮቼ ካሁን
በፊት በመጽሐፍ መልከም ይሁን በድረገጾቼ ሰፊ ጽሑፍ ባቀረበኩት ላይ አስታውሱ።
ሰፊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቴሌቪዥንን፣ ፊልሞችን፣ የቪዲዮ ጨዋታዎችን እና ማሕበራዊ ሚዲያዎችን
ጨምሮ አመጽን ለሕበረተሰቡ በመመገብ በልጆችና በጎልማሶች ላይ የጥቃት አስተሳሰቦችን፣ ስሜቶችን በማጋጋል ትውልዱ ሞገደኛ የባሕሪ
ለውጥ የማድረግ አቅም አለው።
ወቶቹ ሞገደኛነትን የጥቃት ባሕሪያትን የመኮረጅ እድላቸው ከፍ ያለ ሲሆን ፤ ይህም ብዙውን
ጊዜ በባሕሪው ላይ ረጅም ጊዜ የሚቆይ እና ወደ ጎልማሳነት የሚቆይ ተጽእኖን ይፈጥራል። ኢትዮጰያ ውስጥ በዜጎች ላይ በየመንገዱ
እና መጠጥ ቤቶች አስጊ ደረጃ የደረሰ የአካል ጥቃት በብዛት እያየን ነው።
በግሌ የማየው ዓለም በተፈጥሮዋ ለሰው ልጆች የማትመች ጠበኛ ነች፡በዚያ ላይ ጠበኛ ትውልድ ሲጨመር
የሰው ልጆች የመኖር ተስፋቸው በጭንቀት
የተሞላ አድርጎታል።
Abbay TV – (ዓባይ ቲቪ)
ሰለ ተባለው ሚዲያ ካሁን በፊት የተቸሁበትን ርዕስ ላስታውሳችሁ ፤
«የአባይ ሚዲያ ዜና በሻዕቢያና በወያኔዎቹ ቅኝት! ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Feb 9, 2020» በሚል
ከ6 አመት በፊት የጻፍኩትን ትችት አስታውሱ።
ይህም ትችት ፣ ከዘመነ አክሱም ጀምሮ የጀግኖችን አጥንትና ደም የተከሰከሰበትን የኢትዮጵያ የባሕር
ወሰኖቻችንን በተለይ ደግሞ “የምጽዋ ወደባችንን” በአሜሪካን የስለላ ሳተላይት አና በወያኔ ተዋጊ ባንዳዎች እየታገዘ ሻዕቢያ ምፅዋን የያዘበትን “ፈንቅል” ብሎ የሚጠራው በየአመቱ የሚያከብረው የኢሳያስ አፈወርቂ የጉራ መተንፈሻ በዓል፡ ይህ አባይ ሚዲያ ተብየው የሻዕቢያ ቱልቱላ የሻዕቢያን
ውሸት በቃለ አጋ’ኖ እየቀባባ በኢትዮጵያ የቀድሞ ሠራዊቶች ላይ ከሻዕቢያ ምላስ የባሰ ስድብ ቀባብቶ በዜና መልክ አቅርቦት የነበረውን ያቀረብኩትን ታስታውሱ ይሆናል
ብየ እገምታለሁ።
ትንሽ ይተቸሁበትን ጽሑፍ ቀንጭቤ ላስታውሳችሁ፡
«ከአዲስ አበባ የሚተላለፈው የዚህ የዜና አውታር አንባቢ እንዲህ ትላለች፡-
“ኤርትራ 30 አመትዋን በድምቀት አከበረች”
በማለት 150 ያክል ተሰብሳቢ የተገኘበትን ስብስብ “ሚሊዮን
ሕዝብና የውጭ እንግዶች የተሰበሰብበት ድምቀት” እንዳለው አስመስላ አንብቢ ተብየዋ እንዲህ ብላለች፡
“ኤርትራ 30 አመትዋን በድምቀት አከበረች። “ፈንቅል ለልማት” በሚል መሪ ቃል 30ኛው አመትዋን ስታከብር የአገሪቱን ክቡር ፕረዚዳንት እና ሌሎች የስቪልና የወታደራዊ መሪዎች መገኘታቸውን ያገሪቱ የዜና አውታሮች ገልጸዋል። ሻዕቢያ ምፅዋ የነበረው ትልቅና ከባድ የደርግ ሠራዊትን እያራወጠች “የደመሰሰችበትን” 30ኛ አመት መሆኑን ተዘግቧል።
በባዓሉ ላይ የተገኙት ክቡር ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል። የሰሜናዊ ባሕር የባሕር ሃይል ዋና አዛዥ የሆኑ ብ/ጀሜራል “ተኽለ ልብሱ” ሃገራዊ በዓሎቻችንን ‘ትግላችንን” ለማስታወስና ምዕራፎቻችንን የምንገመግምበት ነው’ ሲሉ ብ/ጄኔራል ተኽለ ልብሱ በዓሉን በማስመልከት ተናግረዋል” ።
ይላል የሻዕቢያው ቱልቱላ “አባይ ሚዲያ” ።
ይህ የሻዕቢያ ቱልትላ ሚዲያ ድብቅ ማንነቱ ግልጽ በማድረግ በድሮ የኢትዮጵያ ሠራዊት ክብር ላይ የስድብ ውርጅብኝ በዜናው አስራጭቷል።
እንግዲህ ወገኖቼ ይታያችሁ። “የተደመሰሰበት በዓል” ብሎ ባልተገረዘ አንደበቱ የሚገልጽ ጠላት እንጂ ኢትዮጵያዊ ሚዲያ ነኝ የሚል የአገሬውን ሠራዊት “የተደመሰሰበት ዕለት” እያለ እንደጠላት አሳፋሪ ቃላት ሲጠቀም የብከላው እርከን ጣራ መድረሱን ያሳያል።
አባይ ሚዲያ የተባለው ይህ የሻዕቢያ ቱልቱላ በዚህ አላበቃም፤
ከዘመነ አክሱም ጀምሮ ከዚያም አምደጽዮን (በእኛ ዘመን ከ1306-1336 ዓ.ም የነገሠ) ከሸዋ ገስግሶ ምፅዋን ከቱርኮች ያስለቀቀ፤ቀጥሎም በገናናው ኃይለስላሴ ተከብሮ ቆይቶ በከሃዲውና ቅጥረኛው የትግሬ ባንዳዎቹ አጋዥነትና ፈቃጅ ሰጪነት የተነጠቅነውን ምፅዋን እያጋነነ ከሻዕያ የዜና አውታሮች በባሰ መልኩ እያንዳንድዋን ቃል ከጠላቶች የተበደረውን የስድብ ቃል እየተዋሰ ለጠላቶቻችን በዓል ከማዳመቁ ባለፈ ጅግናውን “የኢትዮጵያን ወታደር” “የደርግ ሠራዊት” እያለ ባንዳዎቹ ወያኔና ሻዕቢያ የሚጠቀሙትን “አዋራጅ ቃል” በመጠቀም አባይ ሜዲያ የተባለው አዲሱ የሻዕቢያ ቱልቱላ መላው የድሮ የኢትዮጵያ ወታሮችን ከብር በመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት በመዝለፍ የባንዳዎች አፈቀላጤነቱን አረጋግጧል።
ያ ሁሉ በሺዎች የሚቆጠረው ምጽዋ ላይ የተሰዋው ጀግና “የኢትዮጵያ ሠራዊት” እንጂ አባይ ሚዲያና ሻዕቢያ እንደሚሉት-“የደርግ ሠራዊት” አልነበረም። ዘንግቶት የአፍና የብዕር ወለምታ እንኳ ቢሆን ግድ አልነበረም፤ ሆኖም እንዲህ ያለ የተጠናቀረ ዜና አስነዋሪ ቃላቶች (ወያኔና ሻዕቢያ የሚጠቀሙበትን የደርግ ሠራዊት፤ የተደመሰሰበትን እያለ) ያውም ‘’ሻዕቢያ ምፅዋ የነበረው ከባድ የደርግ ሠራዊትን እያራወጠች “የደመሰሰችበትን” 30ኛ አመት........’’
እያለ «እያራወጠች» የሚለውን ቃል በመጠቀም ይቅር የማይባልበትን ወራዳ ዜና ሰርቶ ሠራዊቱን ማዋረዱ ለዚህ ጣቢያ የቅሬታ ደብዳቤ እንዲጽፍና የሚዲያው ባለቤት “ይፋዊ ይቅርታ” እንዲጠይቅ መላው የድሮ ኢትዮጵያ ሠራዊት ማሕበርና ግለሰቦች ማሕበር ካላችሁ “በደብዳቤና በኢመይል እንዲወገዝ” እጠይቃለሁ።» ብየ ነበር (ከ 6 አመት በፊት-)።
ይህንን በሚመልከት አንድ ነገር ልበልና ላጠቃልል።
ባንድ ወቅት
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም እንዳሉት- ላለፉት 30 አመታት የኤርትራ ታሪክ በሻዕቢያና በወያኔ ግምባር መሪነት አዲስና የማናውቀው
መልክ እየያዘ መጥቶ አሁን ካለበት አሳዛኝ ደረጃ ደርሰናል። ትክክል ብለዋል። በ1970ዎች ውስጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እኛ በማናውቀው
በተወላገደና በሚያስፈራ ሁኔታ፤በተቀናጀ ስልት ታሪካችንን የሚያበላሹ በርካታ መጻሕፍት ተዘጋጅተው በዓለም ሙሉ ተሰራጭተዋል። ፕሮፌሰሩ
ይህንን ሁኔታ አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡
“በዚያ ጊዜ የኢትዮጵያዊነት ስሜት “እንደ አድሃሪነት” መቆጠር የተጀመረበት
ጊዜ ስለነበር ከኢትዮጵያ በኩል መልስ ለመስጠት የሞከረ አልነበረም” በማለት አሁን ላለንበት ውርደት እኛ በተውነው ክፍት ቀዳዳ
በመግባት ጠላቶች ዓላማቸውን እንዴት እንዳሳኩ ነግረውናል ።
እውነት ነው። መቼም ቢሆን
ጠላት የሚወጣው ከውስጥ ነውና ጠላት ብቻውን “ያለ የውስጥ ተባባሪና ፕሮፓጋንዳ አሰራጭ” መልዕከቱን፤የሚጠቀምባቸው ቃላቶችን፤ እንዲሁም
ተክለሰውነቱን መቅረጽ ከቶ አይቻለውም። ላለፉት 30 አመታት በሠራዊታችን እና በሕዝባችን ሉዓላዊ ክብር የደረሰበትን የሻዕቢያና
የወያኔ ትግሬዎች ስድብና ውርደት በውስጥ ሚዲያዎችና ተባባሪ ግለሰቦች እየታገዘ የሕዝቡንና የወጣቱን ንቃተ- ሕሊና “4ቱን የክለሳ/ በሳብቨርዥን እርከኖች”
ተጠቅሞ ሕሊናን እያጠበ “ኢትዮጵያን እንደ ወራሪ” እሰደቡ ‘ጸረ ኢትዮጵያ’
እንዲጓዝ መደረጉ የምታውቁት ነው።
ዛሬ ደግሞ
ያንን የሕሊና አጠባ እንዳይበቃ እንደ እነሱን ተከቶ እንደ አዲስ ቱልቱላ የገባው “አባይ
ሚዲያ” የተባለ የዜና አውታር “የሻዕቢያና የወያኔ” ቃላቶችና ፕሮፓጋንዳዎችን እየተዋሰ ለእናት አገራቸው የተዋደቁት የምጽዋ
አርበኞችን ሻዕቢያ
ያራወጣቸው እያለ
“በሻዕቢያ ተዋጊ የተደመሰሰው የደርግ ሰራዊት” እያለ የአርበኞቻችን
እናቶች ፤ አባቶች፤ ቤተሰቦችና መላው አገር ወዳድ ዜጋ አንጀት ያሳረረው እንዳይበቃ፡ ዛሬ ደግሞ አደባብዳቢ አዝማሪዎችን በመቅጠር ወጣቱን በማደባደብ ሥራ ላይ ተጠምዷል።
ሰላም እንሰንብት
ከጌታቸው
ረዳ Ethiopian Semay
በጸብ ምክንያት ቀረጻ
ቆመ ! | በቤቲ
ምክንያት የተነሳው የዳኦድ እና የኦሊ አስደንጋጭ ፍጥጫ | መሰንቆ | Abbay TV - ዓባይ
ቲቪ - Ethiopia
https://youtu.be/cwBfHaxpxPY?si=isVhXATkRp2KdUtU