Thursday, February 29, 2024

በሻለቃ ዳዊትና በእስክንድር ላይ የሚዘምቱ የፖለቲካ ባለጌዎች ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 2/29/24

 

በሻለቃ ዳዊትና በእስክንድር ላይ የሚዘምቱ የፖለቲካ ባለጌዎች

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

2/29/24

ሻለቃ ዳዊትን በተለያዩ ምክንያቶችና ወቅቶች እንደ እኔ የተቻቸው ፈልጋችሁ አታገኙም። ያ ወቅት ሌላ ፤ ዛሬ ሌላ  ያ ዘመን ከ2010 ዓ.ም በፊት ነው። ሰው የነበረውን መስመር አስተካሎ ባዲስ አካሄድ ወቅቱ በሚጠይቀው ጎዳና ከተራመደ ሌላ ምን ይፈለጋል? ዛሬ ግን ሻለቃው “ኢምፖስተር” በማለት የሚጠሩት ህቡእና ግልጽ ነብሰገዳይ ቡድን አሰማርቶ ነብስን የሚቀጭና የሚሰውር <<የወያኔ የነገድ አስተዳዳር አስቀጣዩ የኦሮሙማው የጋጠወጥ ማፍያዎች መሪ>> አብይ አሕመድ ከነገሠ ወዲህ ግን “ሻለቃው” አብይ አሕመድን እንቅልፍ ካሳጡት አርበኞች አንዱ ሆነው ብቅ ብለዋል።

ያንን በማድረጋቸው  “ጥበብ ሳሙኤል” የተባለ የአብይ አሕመድ አለቅላቂና ፀረ አማራና የሕግ ሙያ ትምሕርተ አለበት ተብሎ የሚነገርለት (?) ጋዜጠኛ :- አብይ አሕመድን በመደገፍ በሻለቃው ላይ ያለ ዕረፍት ረዢም ጊዜ ሲዘልፋቸው ያስገረመኝ ያህል፤ ሰሞኑን ደግሞ በሻለቃ ዳዊት ወ/ልደጊዮርጊስ ላይ አዳዲስ ዘላፊዎች ብቅ ብለዋል።

“ሻለቃ ሆይ! በትግሉ ውስጥ ዛሬ ይኑሩ አይኑሩ አማራውን ለመታደግ ከፍታዎትን አሳይተዋል ፤የበኩልዎን አድርገዋል ለዚህም <<በአክብሮት ባርኔጣየን አነሳለዎታለሁ፤ አንኳን ደስ አለዎት !!!!>>

አርበኛ ብቅ ባለ ቁጥር ሱሪውን የሚጎትቱ ብዙ የፖለቲካ ተውሳኮች አሉ። ሻለቃው በዛው ዕደሜአቸው የሚቻላቸውን በማድረጋቸውና ከፍታቸውን በማሳየታቸው ፤ይህን በማድረጋቸው ዓይናቸው ከቀላ ውስጥ አንዱ ወደ “ጥንት ትፋቱ” የተመለሰው፤ በቅርቡ ከወየኔም ከኦነጎችም  እየተወዳደሰ መተፋፋግ የጀመረው  የወያኔው አሽከር “ኤርሚያስ ለገሰ” እና ዶ/ር አምሳሉ የተባለ “ከጎንደሬዎች እጅህን አንሳ” እያለ ሲከራከረኝ የነበረው እስከ ቅርብ ጊዜ ወዲህ የአብይ አሕመድ አወዳሽ የነበረው “ከጠ/ቅላይ ሚኒስትሩ በታች ያሉት እንጂ እሳቸው ተገቢው ሥራቸው እየሰሩ ነው…>> እያለ አየሩን ሲየቆሽሽ የነበረው (በቅርቡ ደግሞ ከኔ አልፎ  ዘመድኩን በቀለ (ነጭ ነጭዋን) ጋር የተጣመደው “ጎንደር ለጎንደሬዎች” ባዩ ዶ/ር አምሳሉ የተባለው በሻቃው ላይ አፉን የሚከፍተውና እና ሌለው ደግሞ እንዲሁ በወያኔ ዘመን “የኦነግ ባንዴራም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማም እኩል አሸብርቁ” እያለ ሲያውከን የነበረው ዛሬ የአብይ አሕመድ ካድሬ ሆኖ “የሃቅና ሳቅ” ዩቱብ አዘጋጅ “አበበ ቶላ” (ቶኩቻው) የተባለው እንግሊዝ አገር የሚኖሮው  <<የፖለቲካ ባለጌ>> ፤ ባልተገራ ምላሱ በውትድርና እና በትምህርት እንዲሁም አገራቸውን ያገለገሉበት የውትድርና ማዕርጋቸውን በማንኳሰስ “ሹሉቃ” እያለ የመንደር ስድብ ሲዘልፋቸው መስማት እጅግ ከገረመኝ የሰሞኑ ክስተት አንዱ ነው።  ሌሎችም አሉ።

ሻለቃ ዳዊትን ብቻ ሳይሆን የተጠመዱት <<ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋንም>> ሳይቀር “እስክንድር ያለ ቦታው ነው የገባው፤ እዛ በረሃ ጠመንጃ ይዞ ከመታገል ይልቅ እዚህ መጥቶ ለተጋዮቹ የንዋይ (የገንዘብ) ድጋፍ ሰጪ ቢሆን የረባ አስተዋጽኦ ያደርግ ነበር>> ሲል ያደመጥኩት እጅግ የማከብረው ተመራማሪው ወጣት ምሁሩ የጥንቱ ወዳጄ <<አቻምየለህ ታምሩ>> እንዴት ወደ እዚህ ዓይነት የወረደ ግምገማ እንደገባ አስደግጦኛል። ምሁሩ ፕሮፌሰር ሃብታሙም በበኩሉ “የእስክንድር ዓላማ ምንድነው?” ሲሉ አቻምየለህ ታምሩ ጋር አብረው ጠይቋል።  እስክንድር ለምን ተገፍቶ ፤ ተገፍቶ ፤ ተገፍቶ ፤ እኛ እና ጠያቂዎቹ ያልተቀበልነው መከራ የተቀበለ አስገራሚ የዘመናችን አርበኛ እስክንድር “ኣላማው ምንድነው?” ትበሎ ሲጠየቅ እውነት እስክንድር ለምን ተገፍቶ እዛ ጫካ እንደገባ ዓላማው ለምን እና ለማን ተብሎ ፍዳውን እያየ እንዳለ “ሰሚ አጥቶ ለነበረው ለአማራው ተስፋ ፤መመኪያ ፤ የሞራልና የጉልበት አለኝታ እየሆነ እንደሆነ እውን ይጠፋቸዋል? ዓለማው ምንድነው!? ደጋግሞ እስክንድር ያዳመጠ ሰው እንዴት ዓላማው እስካሁን አልበራለትም? ከጥፋት ራስን መከላከል እንዴት የዓላማ ጥያቄ ያስነሳል? ወይ ከዚህ ከዲያስፖራ ምቾት ለቅቀን እዛው ጫካ እራሳችንን እናግኝ ካልሆነ “መከራቸውን እያዩ ላሉ ራሳቸውን ከመጥቃት ለማዳን የሚታገሉ ዜጎችን ጥያቄ ውስጥ ማስገባት ነውር ነው። በዙርያቸው ለግንጠላ እየሄዱ ባሉ ታጣቂዎች የተከበው የአማራ ሕዝብና ሕዝባቸው በጥቃት ቀለበት የገባባቸው ታጋዮች፤ ዓላማቸው ምንም ይሁን ምን ለጥያቄ የሚቀርቡ አይደሉም።

እኛ በተደንደላቀቀ አልጋ ተኝተን ግማሹ እስር ቤት በካቲና ታስሮ ግማሹ በየጫካው በጥይት እየተቆላ እኛ ዩ ቱብ ላይ በጋለ ብረት በሚጠበሱ በታሰሩትና በጥይት በሚቆሉት ላይ ዓላማን ማስነሳት ዕብደት ወይስ ውቀት? እነ መስከረም አበራ እና በሺዎቹ እመጫቶች ልጆቻቸውን ጥለው በጭለማ ታስረዋል፤ እነዚህን ለማስለቀቅ በሚጥሩ አርበኞች ላይ መሳለቅና ዓላማቸውን መጠየቅ የተመቻቸው ሰዎች ጥያቄ ነው። እግዚአብሔርን እንፍራ እንጂ። እኔ ትግሬ ነኝ፤ ትግራይ ምድር ውስጥ በየአዳራሹ የሚነገረው ስለግንጠላ ነው፤ ብታደምጧቸው ትደነግጡና ዕብደት ወይስ ድንቁርና ትላላችሁ። ጉዟቸው ስለ ግንጠላና ዛቻ እንጂ ስለ አንድነት አይደለም። ኦሮሞዎቹም እንደዚያ፤ በነዚህ መሃል እንደ “ሳንድዊች” የታጠፈው ሕዝብ እንደሚዳቓ ያለ ተከላካይ ቆሞ በሁለም እጣጫ ይለቅ? የነዚህ ታጋዮች ዓላማ መጠየቅ ፈጣሪን የደፈርነው መስሎ አልታያችሁም?

መስክሩላቸው ብንባል <<አፋቸው ማይክሮፎን ላይ መትከል እንጂ “ተግዳሮትን” (ቻለንጅን) መቋቋም የማይችሉትን እንደ እነ ኤርምያስ ለገሰ እና የፖለቲካ ባለጌው “አበበ ተላ” (ቶኪቻው) በሻለቃውና በእስክንድር ትግል ላይ “ከስራ መልስ የድብርታቸው ማስወገጃ በማድረግ” በየዩቱቡ ተድጠው  የነዚህ ሰዎች ትግልና ማዕረጋቸውን ማብጠልጠል ስናደምጥ ‘ዩ ቱብ’ የሚባለው እጅግ ሲበዛ የፖለቲካ ባለጌወችን የልብ ልብ ሰጥቷቸው በታጋዮች ላይ ሲቀልዱ ማድመጥ እውነትም <<ኢትዮጵያ አገሬ  መኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ>> የሚባለው እውነት ነው።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

Saturday, February 24, 2024

ደቂቀ እስጢፋ (የሰይጣን ተከታዮች/የሰይጣን ልጆች) አዲስ መጽሐፋ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ 2/24/2024

 

ደቂቀ እስጢፋ (የሰይጣን ተከታዮች/የሰይጣን ልጆች) አዲስ መጽሐፋ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ

2/24/2024

የትግሬ ሊሂቃን ውሸትና የአባ ኢስጢፋኖስና ተከታዮቻቸው ገበና የሚያብራራ አዲስ መጽሐፍ “ደቂቀ እስጢፋ” አፄ ዘርአ ያዕቆብ አባ እስጢፋኖስን ‘ሰይጣን” ብሎ ስለሚጠራቸው ደራሲዋም የአባ እስጢፋኖስ ተከታዮችን “ደቂቀ እስጢፋ” በማለት የመጽሐፉ ርዕስ ሰይማዋለች) በዶ/ር መስከረም ለቺሳ በማስረጃ መርምራ የጻፈቺው አስገራሚ መጽሐፍ በገባያ ውሏልና እያነበብኩት ስለሆነ አንብቤ ስጨርስ ግምገማ እስክሰጥ ድረስ ታገሱኝና “ሲቦተለክ የነበረው የትግሬ ልሂቃን መሰሪ ውሸትና በጭፍን ሲጋልቡ የነበሩ ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ የጻፉ አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ሊቃውንት እንዴት ሲያጃጅሉን እንደነበር ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስና መሪያቸው አባ እስጢፋኖስ ጉድ” ለማንበብ ፍላጎት ላላችሁ መጽሐፉን ለማግኘት አዲስ አበባ ድረስ በማስላክ ይህ አዲስ የታሪክ ግኝት እንዳያመልጣችሁ እመክራለሁ።ገልጠን ብናየው የሚያስብል ዓይነት የትግሬዎቹ የደቂቀ እስጢፋኖስ ገመና አነብባለሁ ብየ አልሜም አለውቅም ነበር።

ደራሲዋን ለማግኘት      meski_lechi@yahoo.com

Tel: 251 978 21 22 23 በመደወል መጽሐፉን ማግኘት ትችላላችሁ።

ይህ መጽሐፍ ለዘመናት የቆየ ብዙ ምሁራን አጼ ዘርአያ ያዕቆብን በመውቀስ ሲያሳስቱን የነበሩትን የደቂቀ እስጢፋኖስ ታሪክ ምንነቱን እርቃኑን ገላልጦ ያሳየን መጽሐፍ ስለሆነ ሊነበብ የመገባ አዲስ ግኝት ነውና  ውሸትን በእውነት መክቱ።

ለአንዳንድ ማንበብ ፍላጎት ለሌላቸው ደደብ ኢትዮጵያውያኖች መልዕክት፡

ለምን ሰደብክን ለምትሉ ደደብ ከሆናችሁ እናንተን ይመለከታል፤ ካልሆነ እናንተን አይመለክትምና መልዕክቱን መቀበል ነው። ብዙ ደደቦቹ ኢትዮጵያውያን አንዲህ ላለ አዲስ ግኝት ሲገኝ መጽሐፉን ገዝቶ ሕሊናን አዳብሮ ደራሲውንም ማበረታታት ስላልለመዳችሁበት፤ ያንን ዳተኝታችሁን በማስወገድ እንደ ዶ/ር መስከረም ለቺሳ ያለ ትንታግ ወጣት ምሁራንና ደራሲዎችን አበረታቱ።

ከደራሲዋ የተጠቀሰ

ደቂቀ እስጢፋን አስመልክቶ ምእመኑ (በተለይ የገጠሩ ማኅበረሰብ) ዘንድ ያለው እውቀት፡ በመገናኛ ብዙኃን የምናደምጣቸው ምሑራንና ሰባክያን ከሚሉት ጋር ሲነጻጸር፡ ፈጽሞ የተለየ ነው።.....

ተቀጥላ (appendix) በሚለው የመጽሐፉ የመጨረሻ ማሳረግያ ገጾች ላይ ከደራሲዋ እንዲህ የሚል ይነበባል፡-

<<…..የሚከተሉት ማስረጃዎች፤ ስለደቂቀ እስጢፋኖስ ከምእመናን እንዲሁም ከጥቂት መነኮሳትና ካህናት ያገኘቸው ናቸው። አንዳንዶቹ የደረሱኝ በጽሑፍ ሲሆን ሌሎቹን ደግሞ ያገኘሁት በቃል ነው።… ከተለያዩ ግለሰቦች የተገኙ እንደመሆናቸው በመረጃው መካከል ዩሃሳብ መጣረስ የሚመስሉ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ያን ማጣራት፤የአንባቢዎች ፈንታ ነው። እኔ ግን የደረሱኝ መረጃዎች ፤እንዳለ አቅርቤአለሁ።

በማለት ደራሲዋ ከተጠቀሱ ስለ ዘመናችን የደቂቀ እስጢፋኖስ ተከታዮች ምንነትን ባህሪ የደረሳትን ስታስነብብ ፤ ከተጠቀሱት መረጃዎች አንዳንዶቹን ለናንተ ልጥቀስ፡

“ልጄ፤ስለነዚህ ሰዎች መረጃ ስትጠይቅ ጠንቀቅ በል፡ በጣም አደገኞች ናቸው።”

“ደቂቀ እስጢፋኖስ ማለት እኮ፤ቅባቶች ናቸው። ወደ ጎጃም አንዳንድ ቦታዎች ብትኼጂ ‘እኛ ደቂቀ እስጢፋኖስ ነን’ ይላሉ።’ቅባቶች ነን’ ማለታቸው ነው። በተዋህዶ አያምኑም።”

“ ደቂቀ እስጢፋኖስ ማለት በጣም ሃብታሞች ናቸው። አብያተ ክርሰትያናት ኮሚቴዎች ውስጥ በመግባት አጫቃጫቂ የኾኑ ነገሮችን ሥዕሎችና ቅርጾች እንዲቀመጡ በማድረግ፤ሥርዓት እንዲፋለስ ያደርጋሉ። እነርሱ ቤተክርስትያን ውስጥ በሚሠሩት ሥራ ምክንያት ቤተክርስትያን ትቃጠላለች።”

“ደቂቀ እስጢፋኖስ ማለት፤ ዋልድባ ቤተ ጣዕማ ያሉ ሰዎች የሚከተሉትን እምነት የያዙ ማለት ናቸው፡ ዘጠኝ መለኮት ብለው ነው የሚያምኑት። እምነታቸው ወደ ካቶሊኩ ያደላል።”

 “ደቂቀ እስጢፋኖሶች በእኛ (ኦርቶዶክሶች) ቤተክህነት ውስጥ አሉ። እንዲያውም የሚጠመጥሙት፤እንደመሪጌቶቻችን ነው። መሪጌታ ነው የሚመስሉት። ግን አይደሉም። ቅኔውን፤ዶግማውን ይመራሉ። ግዕዙን ምኑን ይማራሉ። ሲጀመር፤ከመጀመሪያው ዓላማቸው ከኦርቶዶክሱ መሃል ኾኖ፤ኦርቶዶክሱን መስሎ ግን ኦርቶዶክሳዊ ያልኾነ ሥራ መሥራት ነው። ልክ ‘የአብርሃም ልጆች ነን ትላላችሁ፤ ነገር ግን የአብርሃም ሥራ አትሠሩም’ እንደተባሉት ማለት ነው። መንፈሳዊ እይታ ያለው በደምብ ለይቶ መዝዞ ሊያወጣቸው ይችላል። ነገር ግን፤ጊዜው እስኪደርስ ድረስ ፤እውነት እስክታሸንፍ፤እስከዚያው ይቆያሉ።”

የደቂቀ እስጢፋኖስ ዓላማ፤ምንኩስናን በሕዝቡ ዘንድ ማስጠላት ነው። የሚያያቸው ሰው ‘እነሱ እንዲህ ከኾኑ ፤መንኩሰውም ግብረሰዶማዊ ከኾኑ፤ታድያ ሃይማኖት ምን ጥቅም አለው?’ እንዲሉ ይፈልጋሉ።’ጾም ጸሎት፤ምግባር ታዲያ፤ ምን ጥቅም አለው?’ እንዲሉ ያደርጋሉ።”……

"ደቂቀ እስጢፋኖስ የሚባሉት፡ አሉ፤ በጎጃም፣ በወሎ፣ አዲስ አበባ ደግሞ፡ መገናኛ ላይ ብዙ ናቸው። እኔ ንግሥ ለማክበር በየቦታው ስለምኼድ፡ አዋራቸዋለሁ። ሳያቸው በደንብ ለይቼ አውቃቸዋለሁ። የቡዳ ዘሮች የሚባሉት ናቸው። ግንባራቸው ይከብዳል። ከነርሱ ጋር አውርቼ፡ ማታ እንቅልፍ አይወስደኝም። እቃዣለሁ።በምንድነው የምታምኑት?’ ስላቸው፡ቅባትይላሉ። ተዋሕዶን አይወዷትም።ደቂቀ እስጢፋኖሶች ነንብለው በግልጽ ይናገራሉ። እና፡ተዋሕዶየሚለውን ቃል አይወድዱትም። ቀን ሰው አይተው፡ ማታ ይመጣሉ።ወደንሃልብለውኝ ወንዶቹ አንድ ቀን ማታ መጡብኝ። ግብረ ሰዶም ለመፈጸም። እንዲህ ናቸው። እነሱን ሳያቸው በጣም ነው የምረበሸው። የተዋረሰ ክፉ መንፈስ አለባቸው። በጸበል ራሱ በቀላሉ አይለቅም። በገቡ ቁጥር ዝም ብሎ መጮህ ነው። ከነርሱ የተወለደች አንዲት ልጅ አውቃለሁ። ኹል ጊዜ ትጠመቃለች። ግን መንፈሱ ሊወጣላት አልቻለም። ስቃይ ነው።

(ደቂቀ እስጢፋ፥ ገጽ 302—307

እያሉ ሰዎች ለደራሲዋ የሰጡት አስተያየት ስለ የዛሬዎቹ ደቂቀ እስጢፋኖስ ባሕሪ ከላይ አንደተጠቀሰው ይነበባል።

ስለ ዋናዎቹ ደቂቀ እስጢፋኖስ ለማወቅ ግን በጣም ሰፊ ሃይማኖታዊና የመሳሰሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች በዘመኑ የተጻፉ የግዕዝ መጻሕፍተና የንጉሡ ክርክርና መጻሕፍቶችን እንዲሁም የደቂቀ እስጢፋኖስ ሰነዶች ሁሉ በማካተት የዳሰሰ አዲስ ክስተት የያዘ የምርምር መጽሐፍ ነው። 

* * *

መጽሓፉን ለማግኘት፦

አራት ኪሎ ገለን ሕንጻ (ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ግቢ ቀጥሎ)፥ ሦስተኛ ፎቅ፥ ቢሮ/ሱቅ ቁጥር 303

0978 21 22 23

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ