Thursday, December 26, 2024

አፋቸው እንደ ባሕር ኦይሰተር የሚከፍቱ በጨረቃ ላይ የሚጮሁ ተኩላዎች ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 12/25/24

 አፋቸው እንደ ባሕር ኦይሰተር የሚከፍቱ በጨረቃ ላይ የሚጮሁ ተኩላዎች

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay) 12/25/24

 

““Oysters የተባለ እንሰሳት በጠፌ ጨረቃ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ይከፈታል ይባላል።Crab የተባለው እንሰሳ (አብዛኛው ዓለም ይበላዋል) ኦይስተሩን ሲያይ ትንሽ ድንጋይ ወይም የባሕር አረም (አራሙቻ) ይወረውርበታል። ኦይሰተሩ እንደገና ራሱን መዝጋት ያቅተዋል። የክራቡ ምግብም ይሆናል። አፉን በጣም በመክፈት ራሱ ላይ ከፍተኛ ችግር ሚያደርስ ሰውም ዕጣ ይኸው ነው።>> {ጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ- ጦቢያ መጽሄት-ቅጽ8-ቁጥ-12/1993 -ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያውያን ጋር የተፈራረሙት ውል (ኮንትራት) የላቸውም”}

የባሕር ዓሳዎች ብቻ ሳይሆኑ አፋቸው ከመጠን በላይ የሚከፍቱ የሰው ኦይሰተሮችም አሉ። አንዱ ዘመድኩን በቀለ የተባለ ሲፍረዘኒክ ነው። ሲፍረዘኒኮች ለነሱ በማይታወቃቸው ክስተት ከውስጣቸው ይደናገጣሉ፤ የሚረብሻቸውን ውስጣዊ ፍርሃት ለማስታገስ  “ይጮሃሉይወራጫሉ” በተከታታይ ሰው ይዘልፋሉ ወይንም ጭራሽኑ ራሳቸውን አጥረው
ጥሞና ውስጥ ይገባሉ
። ባሕሪው ብዙ ነው። 

መጥፎ ደረጃ ሲደርሱም “ያለ ምክንያት ያለቅሳሉ”፤ ሲያለቅሱም በላይቭ ቪደዮ ራሳቸውን እየቀዱ በሕዝብ ፊት ሲያለቅሱ ይታያሉ።ሁለት ሰዎች በላይቭ ቪዲዮ እራሳቸው ቀድተው እዬዬ ሲያለቅሱ ያያናቸው አሉ። አንዱ ዮኒ ማኛ የተባለው እና ዘመድኩን በቀለ ናቸው። ለልቅሶአቸውም ምክንያት ፍለጋ ራሳቸው ይጠይቁና “ምን እንደነካኝ አለውቅም” ሲሉ ለልቅሶአቸው ምክንያት ሳይውቁት ከሕሊናቸው ጋር በልቅሶ ሲታገሉት አይተናቸዋል።

እንዲህ ዓይነት ስሜት እንዲገቡ ገፊው (ካልፕሪት) የሆነው ሃይል ከነሱ ውጭ ቁጥጥር የሆነ “የመረበሽ” (ዲስተርብድ) ስሜት ሲከማች በሁለተኛ ዕርከን የሚከሰት “ጭንቀት” ውስጥ ይገባሉ። ሁለቱም መረበሽ እና ጭንቀት ተደምረው “ያለ ምክንያት ከማልቀስ” አልፈው ከዚያ አጥር ለመውጣት የአደባባይ ውግያ (ኮምባታንት- ሆነው ይታያሉ) ለከት የለሽ ንትርክ በመክፈት “ከሚቃረኑት ሰው ብቻ ሳይሆን የሚቃረኑዋቸው ቤተሰቦቻቸውንም ጭምር በመጥቀስ ስድብና ተከታታይ ስም የማጠልሸት ዘመቻ” የመሳሰሉት ባሕሪዎች በመግባት ከግለሰብም ከቡድንም ጋር ዕብደት የሚመስል የባሕሪይ ቋንቋ ሊቃውንት Loquacious” የሚሉት አይነት ንትርክ ውስጥ በመዘፈቅ የጭንቀትና የመረበሽ ግፊታቸውን ለማስታገሻ ይጠቀሙበታል።

ሁለቱ ሰዎች ሲያለቅሱ የዘረጉት ፤ “ላይቭ ቪዲዮ” የሚያሳየንም ይህ እውነታ ነው። አሳዛኙ ደግሞ በነዚህ ሰዎች ጭቅጭቅና መሰዳደብ የሚረኩ በርካታ ተከታዮች አፍርተዋል። የተከታዩ ብዛት  ክስተት የሚያመላክተን “የባሮ-ሜተር መለኪያው” ውጤት ተከታዮቹ በተመሳሳይ “ታነል - Tunnel” የሚሰቃዩ የነሱ ቅጂ (copy) ወይንም የዘመኑ የአዲስ አበባ ወጣቶች እንደሚሉት “የነሱ ጀለሶች” ናቸው።

ለምሳሌ በዚህ “የሲፍረዘኒክ ባሕሪ“ የሚጓዙ ሰዎች  ጭንቀታቸው እና የውስጥ ርበሻ (ዲስተርባንስ) ወስደው የሚደፉበት ጫንቃ የግድ በየሚዲያው እየገቡ እንደ ውሻ እያፈናፈኑ መጮህያ ክፍል ይፈልጋሉ። ለምሳሌ ዘመድኩን በቀለ እንደምሳሌ ብንመለከተው- ሰውየው ወዳጅና ጠላት የሚባል መስመር የለውም። ጭንቀቱና ረብሻው የሚደፋበት ቦታ ምርጫ የለውም። አምና ዘመነ ከሴን ሲዘልፍ እስክንድርን ሲያወድስ ፤ ዛሬ ደግሞ እስክንድርን ሲዘልፍ ዘመነ ካሴን ሶያሞካሽ የምናየው ባሕሪ cumulative emotions የሚባሉ የተጠራቀሙ የውስጥ ጭንቀቶችና ርበሻዎች መጠናቸው አልፈው ሲገነፍሉ “መንገድ” ላይ “ባደንቋሪ ጩኸት እየጮኸ” ባገኘው ሰው ላይ ድንጋይ እንደሚወረውር ዕብድ ሁሉ ጤነኞች የሚመስሉ ግን አስፋልት ላይ ያልወጡ እንደ ዘመድኩን ያሉ ማንም ከማንም ሳይመርጡ ሁሉንም በየተራ ይጨረግፋሉ። ሲጨረግፉ  ደግሞ>> እኔ ማንንም አልፈራም>> የሚል እኩያዎቻቸውም ጭምር ሳይቀር በንግግራቸው ጣልቃ እያስገቡ የሚጠቀሙበት “ኮመን” ሐረግ ይጠቀማሉ።

ሲጨረግፉ ደግሞ ለነገ አይሉም። ለነገ ብቻ ሳይሆን “ይሉኝታ” የላቸውም። ለምሳሌ ዘመድኩን በቀለ እስክንድርን ሲዘለፍ፤ ከነ ባለቤቱና ልጁም ጭምር አብሮ ቀላልቅሎ ይጨረግፋቸዋ።ሚሰቱን “ትግሬ” በማለት ትግሬ መሆን ነውር እንደሆነ ለማስመሰል በሚመስል መልኩ ነገድዋን ለማስተዋወቅ “ትግሬ” ሚሰቱ ይላታል፡ ሚሰቱና  ልጁም በሕዝብ ገንዘብ እያኖራቸው ነው ሲል እስክንድርን ይወነጅላል።

እንዲህ ሲል፡

<<ሚሊዮን ዶላር ከአማራና ለአማራ ትግል የሰበሰበ ነው።በሰበሰበው ገንዘብ ልጆቹን ዘጭ አድርጎ እያኖረ ነው፤ ሚሰቱን ዘጭ አድርጎ እያኖራት ነው>> ይላል።

እንደምናውቀው እስክንድር ያለው አንድ ልጅ እንጂ ብዙ ልጆች እንደሌሉት ነው በበኩሌ የማውቀው። ዘመድኩን ግን እስክንድር ካንድ ልጅ አልፎ ልጆች እንዳሉትና እስክንድር በሕዝብ ገንዘብ በምቾት እያኖራቸው እንደሆነ ይናገራል።

እስክንድር ሚሊዮን ዶላር ከሕዝብ ሰብስቦ ለባለቤቱና “ለልጆቹ” (?) አንደላቅቆ እያኖራቸው እንደሆነ አንዲትም የሰነድ ማስረጃ የሰው ምስክርነት ፤ የፍርድቤት ማስረጃ ሳያሳይ እስክንድርና ባለቤቱ እንዲሁም ልጁ (ልጆቹ ?) በተዘረፈ የሕዝብ ገንዘብ አሜሪካ ውስጥ እየኖሩ እንደሆነ የእስክንድርን ስምና የልጁን፤ የባለቤቱንም ስም በውሸት ሲያጠፋ ትንሽ አይሰቀጥጠውም። ይህ ደግሞ ከላይ ካየነው ባሕሪ የመነጨ ነው። ሰዎች <<በፕሪሚቲቭ/ኢንስቲንክት ኮንዳክት>> ሲመሩ ርሕራሄና ይሉኝታ የማይሰማቸው እጅግ አረሜኔ ጨካኞች ይሆናሉ። በዘመድኩን ያያነው ይህ “ፓተርን/ትሬንድ” ነው።

በዚህ አላበቃም፤ ዘመድኩን እንዲህ ይላል።

<<እስክንድር ማለት ለኔ አዲስ አበባን የሸጠ ፤ ያዲስ አበባን ወኔውን የሰረቀ፤ የአዲስ አበባን ሕዝብ ልምሻ ያደረገ ፤ሰንታየሁን ይዞ በየታክሲው በየ ምናምኑ እየሄደ ቪዲዮ እየቀረጸ “ዋይ!ዋይ! ሲል የነበረ’ እስክንድር ለኢትዮጵያዊያን የጠቀመ እንጀራቸው የነበረ አማራን ግን ቅርቃር የቀበረ ፤ጉድጓድ ውስጥ የከተተ ፤ ጠንቋይ ቀላቢ ነው…>> ይላል።

እንግዲህ ይህ በሬ ወለደ የስም ማጠልሸት ባሕሪ እውነትነት እንደሌለው አንድ ባንድ እንሂድበት፡

“ያዲስ አበባን ወኔው የሰረቀ” የሚለው በሚከተሉት የቪዲዮ ማስረጃዎች ያዲስ አባባን ወኔ ያነቃቃ እጅግ አስገራሚ ኢትዮጵያ እንደሆነ ከታች በምሰጣችሁ ቪዲዮ እንመለከታለን።

፤ሰንታየሁን ይዞ በየታክሲው በየ ምናምኑ እየሄደ ቪዲዮ እየቀረጸ “ዋይ!ዋይ! ሲል የነበረ>> የሚለውም ከታች የማቀርባቸው የቪዲዮ ሊንኮች የሚያሳየው “እስክንድርና ስንታየሁ” የሰሩት ታምራዊ ጀግንነት በግፍ ከየመኖርያ ቤቶቻቸው እየተገፈተሩ ከረምት በዝናብ ውስጥ የበሰበሱትን አዛውንቶችና የህጻናት እናቶች ዕምባ ሄዶ አነጋግሮ ያጽናናቸው ፤ ምግብ የሰጣቸው፤ ዕምባቸው ያበሰላቸው፤ ስቃያቸው በሚዲያ በቪዲዮ ቀርጾ እንዲሰማ ያደረገ (ሁለቱም ጀግኖች) ኢትዮጵያዊያን በደልና ጩኸት ድምጽና ዋይ ዋይታን ነው ሲያስተጋባና ለሕዝብና ለዘጋቢዎች ሲያስተላልፍ የነበረ እንጂ “”በየምናምኑ በየታክሱ እየሄደ ለታይታ “ዋይ ዋይ” የሚል ሰው አልነበረም”። ዘመድኩን <<የናቶችና የህፃናት እምባ ይውጋህ>> እንዳልልህ ልጆችና ውድ በለቤትህ ስላሉህ ላንተ ይህንን አልመኝም>>። ግን ንግግርህ በጤንነትህ ከሆንክ ነውር ነው። የሕዝብን ድምጽ የሆነን ሰው ማቃለል፤ በሰማይም በምድርም ያስኮንናል።

በመቀጠል፡

 <<እስክንድር ለኢትዮጵያዊያን የጠቀመ እንጀራቸው የነበረ አመራን ግን ቅርቃር የቀበረ ፤ጉድጓድ ውስጥ የከተተ፤>> ስለሚለው ውንጀላው ደግሞ

ዘመድኩን በቀለ ኢትዮጵያና አምሐራ ሕዝብ ለየብቻ አድርጎ በመመለክት ልክ እንደ ወያኔዎች “ኢትዮጵያ” ለትግሬው ምኑ ናት እንደሚሉት ሁሉ ዘመድኩንም ኢትዮጵያ ለአምሐራው ምኑ ናት ሲል በግልጽ ኢትዮጵያ አገሩ አንዳልሆነች ይዘባርቃል። ኢትዮጵያ አምሐራ ሲጠቃ አልጮኸም ሲል በደንቆሮ ክርክሩና ውግዘት ኢትዮጵያዊያንን (ኢትዮፒያኒስቶች) ሲያወግዝ እሰማዋለሁ። ለመሆኑ አምሐራውን የበደለው ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይስ አምሐራው ራሱ ካብራኩ የወጡ ልጆቹ?

አምሐራ ተበድሏ/ተበድላለች እና ጩሁላቸው ሰንላቸው እነኚህ ዛሬ “አምሐራ ነን” የሚሉ ተመጻዳቂ አምሐራዎቹ ምን ነበር ሲሉ የነበረው? ከማንስ ጋር ነበር በማበር አፍንጫቸውና ኣፋቸው ከድነው ቆመው የነበሩት? ጎጃም፤ ጎንደር፤ ወሎ ማን ጋር ነበር ቆመው እስክስታ ሲመቱ የባዕዴን ባንዴራ እያውለበለቡ፤ የባዕዴን መታወቂያ አንግታቸው ላይ እያንጠለጠሉ ከማን ጋር ነበር የወገኑት? ከወያኔና ከኦሮሙማው አብይ አልነሩም (እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ? የአምሐራ ወጣት የት አባቱ ነበር ተሸሽጎ ወይንም ወግኖ ሲታገል የነበረው ? ወጣቱና ምሁሩ “የማን አባቱ ጎፈሬ ሲያበጥር” ነበር ሌላው (ኢትዮጵያዊው) አምሓራ ሲገደል ቆሞ ያይ ነበር የምትለው?

እስክንድር ለኢትዮጵያ የጠቀመ ለአምሐራ ጉድጓድ የከተተ የሚል አንዲህ ያለ በጣም የጨመለቀ ስድብና ውንጀላ ዕብድ ሰው የሚለው ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል? ለኢትዮጵያዊያንም ለአምሐራውም እንዴት እንደታገለላቸው ከታች በሊንኩ የቀረቡት ቪዲዮዎች ማስረጃውን ተመልከት!!!

 በዚህ በረዢም የትግል ዘመኔ አፋቸው እንደ ኦይሰተር ሲቀዱና ሲዘጉ አይቻለሁ። አፋቸው የሚቀዱ ኦይሰተሮች ብዙ ያየሁ ብሆንም እንደ ዘመድኩን አይነት በጣም የሚከፈት ግን አላየሁም። ደግሞ ወደ ውጭ አገር የመጣው ባጭር ጊዜ ሆኖ መአት ኦይሰተሮች ነው ያፈራው።

እንዲህም ይላል፡

 <<እስክንድር ጠንቋይ ቀላቢ ነው፤ ማሰረጃ ቪዲዮም አለኝ>> ሲል  ይናገራል። እንዲህ ያለ  ቀዳዳ  ስም የማጠልሸት ባሕሪ አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ይህ ስም ማጠልሸት ሃሜት ያገኘው ሌላ ጊዜ ማንነቱን ለማሳየት ከምመለስበት የሻዕቢያ ባንዴራ እየሳመ በሚለፈልፍበት አዳራሽ ውስጥ እያውለበለበ ታዳጊ ህጻን የሚመስል በጣም የደነቆረ "Strange" የሚሉት ዓይነት “በላይ መንገሻ” የተባለ አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር በአፓርታይድ ግርድናነቱ የሚዋብ የአብይ አሕመድና <<የሻዕቢያ የፖለቲካ ማዓረስነት>> /Stooge/Puppet/ ግርማ የሚመስለው ምናልባትም ዘመድኩን የስም ማጠልሸት መረጃው ያገኘው ከዚህ ወፍ ዘራሽ ኦይሰተር ሳይሆን አይቀርም።

 ይህ ሲነሳ አንድ ነገር ትዝ አለኝ።

የትግሬ ምሁራን ልክ እንደ እነዚህ ያሉ ስም አጥፊዎች የሸዋ ሕዝብ ከቤተክርስትያን መልስ ወደ ጠንቋይ የሚሄድ ሕዝብ ነው እያሉ በሸዋ ሰዎች ስም ሲያጠፉ ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ (መምህር ገብረኪዳን ደስታ እና ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ ለምሳሌ…) አሁን እየሰማነው ያለው ደግሞ ተመሳሳይ ዘመቻ ነው።

በመጨረሻም “ኢትዮጵያውያን ሆይ” የዚህ ሰው “ክፋትና መርዛማ ሰም ማጠልሸት” ምን ያህል “ፕሪሚቲቭ” ሰው እንደሆነ ወደ እዚህ “ውጭ አገር” በቅርቡ የተቀላቀለን አደገኛ ስም አጥፊ መሆኑን እና “ኢትዮጵያኒስት” የሚል ቃል ለዘመድኩን በቀለ፤ ምን ያህል ጥላቻ እንዳለው ለማየትና እስክንድር ማን መሆኑን እንድታዩት “ዘመድኩን ከዋሻቸው ውሸቶች እውነቱን ለማበጠር እንዲያስችላችሁ” ይህንን  ከታች የማቀርባቸው ለማስረጃ ከማሳያችሁ ከመቶዎቹ የቪዲዮ ሊንክ ማስረጃዎች ጥቂቶቹን ሊንኮች ላሳያችሁ። ቪዲዮዎቹ የሚያሳዩት ዘመድኩን እንደሚለው “ወደ አሜሪካ የመጣው ባለቤቱና ልጁን ለመቀለብ ከሕዘብ ገንዘብ ለመዝረፍ ሳይሆን የእስክንድር ቃል ልዋስና <<ከቀበሮ ጉድጓድ>> ወጥቶ << አምሐራ ከፍተኛ ጀነሳይድ እየተፈጸመበት እንደሆነ ለማስቆም እነ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌን እና የመሳሰሉ አገር ወዳድ ምሁራን ይዞ ወደ ተባበሩት መንግሥታት ስሞታ ለማስሰማት እንጂ ገንዘብ ለመስረቅ እንዳልሆነ ብዙ የሰነድ ማስረጃዎች አሉ።

ዘመድኩን እንደሚለው አዲስ አበባን የሸጠ ፤ ያዲስ አባባን ሕዝብ ያላሸቀ ሳይሆን፤ የሕዝብ ልቅሶ፤ የቤቶች መፍረስ፤ የአምሐራ መፈናቀል፤ አርበኞች እና አርበኝነት ምን እንደሆነ ጧፍ አብርቶ ወጣቱን ሃውልት ፊት ለፊት ቆሞ ያስተማረ፤ ስለ ዲሞክራሲ (ሕዝባዊ ደምጽ)፤ ስለ ጥቃትና መብት “ምሁራን ጋብዞ” በራሱ ሚዲያ ሕዝብን እንዲነቃ ያደረገ ፤ ኢትዮጵያዊ አርበኛ እስክንድር ለታሪክ የተቀረጹ ቪዲዮዎቹ ለዘላለም የሚኖሩ ምሰክሮቹ ናቸው።  ቪዲዮው እስክንድር በዋና ኢዲተርነት ሲያካሂደው ከነበረው “ኢትዮጲስ” የካሜራ ቀረጻ እና ከመሳሰሉ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ጋር በመተባባር የተካሄደ የሚዲያ ማስረጃ እነሆ፤ <<ፍርዱ ለናነተው ልተው!!>>

80 ዓመቷ አዛውንት ከሚኖሩበት ቤት ከነእቃቸው በአንሶላ ተጠቅልለው ውጭ ተጣሉ!! | ተሻገር ጣሰው!

https://youtu.be/DxckMgCkThY?si=-106ekJjXEueZzT2

#Ethiopis #Home less People #Home deconstruction #Citizens forceful displacement #Addis Ababa

https://youtu.be/MPSIs8PGFeI?si=cidBePqDHKZ4o2q8

#ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እርዳታ እንዳይቀበሉ የተከለከሉ የአዲስ አበባ ተፈናቃዮች #ኢትዮጲስ

 

https://youtu.be/hKwQKR_-PQU?si=NJ_v41SqULY37SW_

 

#ኢትዮጲስ #ቆሻሻ መጣያ የሆነው የለገሀሩ አንበሳ #የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች በለገሀር #እስክንድር ነጋ #ገለታው ዘለቀ #ስንታየሁ ቸኮል #Ethiopis

 

https://youtu.be/380N498wq0w?si=Ge9taPA7HTJZesSF

#Ethiopis #በአዲስ አበባ፤ ኮልፌ ቀራኒዮ፤ ካባ መኖሪያ ቤት የፈረሰባቸው ዜጎች #Force full displacement in Addis

 

https://youtu.be/NLkDHcowdLY?si=3tW3VELTU7gF729Q

 

#ኢትዮጲስ #ቆሻሻ መጣያ የሆነው የለገሀሩ አንበሳ #የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች በለገሀር #እስክንድር ነጋ #ገለታው ዘለቀ #ስንታየሁ ቸኮል #Ethiopis

 

https://youtu.be/380N498wq0w?si=bVYlarwjehPRWt3O

 

የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን

 

https://youtu.be/dQvn3jh5ksg?si=urzp5G8TdSszcwIl

 

#ኢትዮጲስ #በአዲስ አበባ፤ አውቶብስ ተራ መንግሥት ያፈናቀላቸው

https://youtu.be/-tWhsuIohy4?si=jm9Xj3x1ikblL7Go

 

#የአማራን ሕዝብ ለማፈን እየተደረገ ያለ መንግሥታዊ የትጥቅ ዘመቻ #ፋኖ #Ethiopis #Bahire Hasab

 

https://youtu.be/g7tlCL10Ki8?si=lOgBDvmeW-kpQox4

 

Ethiopian journalist Eskinder Nega on World Press Freedom

 

https://youtu.be/7EUDiLYLpz8?si=QF0FPf4ARdGvOWrT


አፋቸው እንደ ባሕር ኦይሰተር የሚከፍቱ በጨረቃ ላይ የሚጮሁ የሰተኩላዎች የአፋቸው “ክፋት” እና “ክፍተት” አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ለነሱ ጤና ጎጂ የማሕበረሰባችንም “ቀውስ” ምን ያህል ጥልቀት ውስጥ እንዳለ አመላካች ቀስት ነው። ለማንኛውም በተጠና መንገድ ማይሙም ፊደል የቆጠረውም፤ ምሁሩም እንደ ከብት መንጋ የተነገረውን ሳያላምጥ እየዋጠ እስክንድርን መዝለፍ እጅግ ነውረኛነትና የተጠበቀው የብርሃን ተስፋም ጭምር እንዲደበዝዝ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው። 

ሰላሙን ለናንተ ይሁን!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay

           

 

Monday, December 23, 2024

የኦሮሞ ሁቱዎች በወለጋ መልካም የፈረንጅ ገና በዓል! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/25/24

 

የኦሮሞ ሁቱዎች በወለጋ

መልካም የፈረንጅ ገና በዓል!

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/25/24

ማሳሰቢያ

 ባለፉት 36 አመታት ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ የጅምላ ግድያ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተደጋጋሚ ችላ ተብሏል? የዜና ዕጥረት ሳይሆን 90% ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችና ምሁራን በ36 አመት ውስጥ የጅምላ ግድያ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተደጋጋሚ እየተፈጸም እንደሆነ ቢነገራቸውም ፤ 90% (አብዛኛው ማሕበረሰብ) ደንታ ቢስ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

በሕዝብ ችላ የተባሉት የዚህ ዓይነት አረመኔያዊ ድርጊቶች ሲደጋገሙ ከፍተኛ ተቃውሞ አለማሳየትና ዳተኛነት ከገዳዮቹ ይልቅ  ቸልተኞቹ ለወንጀሉ መደጋገም በር ከፋቾች ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።

ይህ ቸልተኛነት የታሪክና የስነ ልቦና ምሁራን ሊያጠኑት የሚገባ  ርዕስ ቢሆንም ፤ እኔም ሆንኩኝ ጥቂቶች ሳንሰለች ለብዙ አመታት የዘርና የሃይማኖት ጭፍጨፋዎች ለሕዝቡና ለዓለም ደጋግምን ለማሳወቅ የምንጽፋቸው ሰነዶች በህይወታችንና እና በሥራችን ከፍተኛ ጫና ያሳደረ እንደሆነ ብናውቅም እኛ ጥቂቶች መስዋዕት በመክፍል ወጣቱ እንደተፈለገው ባይሆንም አሁን ባለበት የመጋፈጥ ደረጃ ሲደርስ በአቦ ሰጥ የመጣ ክስተት ሳይሆን ባበረከትናቸው የጊዜ፤ የሰነድ የገንዘብና የጉልበት መስዋዕቶች አድርሰነዋል የሚል እምነት አለን። ያለፉት የ36 አመት ትግሎች እዚህ እንዲደርስ ስንት መስዋዕት እንደከፈልን በብዙዎቹ ወጣቶችና ምሁራን ትግሉ ውስጥ ስላልነበሩ አይታወቅም።

ዕንቅልፍ አጥተን የንጽፋቸው ሰነዶችና የሚሰራጩት የሕዝብ ዕንባዎች ል ብላችሁ ማየት እንደሌለባችሁ ለማሳሰብ ነው።

አብሮ ለማሳወቅ የምፈገው ነገር ደግሞ ‘ብዙ ሰዎች’ ስም ሳይጠቅሱ ሰለ አንድ ጉዳይ ሲጽፉ አያለሁ። ያ ደግሞ ተባባዎችና አስተባባዮች ምንነታቸው እንዲደበቅ የሚረዳ ስለሆነ ፤ እኔ እንደምታውቁኝ የሰዎች ስም በመጥቀስ ሳልደብቃቸው የምጋፈጥ ባሕሪ ስላለኝ እዚህ ላይም ስም ተጠቅሰው ስታዩ፤ ለዋዛ ሳይሆን ለቁም ነገር መሆኑን ተቀበሉኝ።

አሁን ወደ ዋናው ጉዳይ እንግባ።

ከዚህ ጽሁፍ ግርጌ አብሮ የተያያዘው ቪዲዮ በአምሐራ ሕዝብ ጀነሳይድ አልተፈጸመም ለሚሉ ለአስተባባዮቹ ለነ ዶ/ር ዮናስ ብሩ እና እንዲሁም <<እኔ ሰው ለመታረዱ አላውቅም! እኔ አራጆች ብየ አልጠራቸውም፡ ያውም ማን እያረደ እንደሆነ በማናውቅበት ሁኔታ አራጆች የሚለው የአማርኛ ቋንቋ ባንጠቀም ጥሩ ነው>> ለሚለው ‘የገበታ’ ሚዲያ አዘጋጅ የሕግ ምሁር ለሞገስ ዘውዱ ተሾመ እና ለመሳሰሉ አስተባባዮች እንዲመለከቱት እጋብዛለሁ:: በዚህ ቪዲዮ የምታደምጡዋቸው ተጠቂዎች “ሲዋጉ የተጨፈጨፉ” ሳይሆኑ ዕለታዊ ኑሮአቸው በሚኖሩ ምስኪን ነገዶች ላይ በየመኖርያ ቤቶቻቸው ውስጥ እንዳሉ ልክ እንደ ረዋንዳው እና እንደ ጀርመን ሃይማኖትና ዘር ያተኮረ ጭፍጨፋ የተፈጸመባቸው እንጂ አስተባባዮቹ እንደሚሉት የጦር ወንጀል የተጸመባቸው ወይንም በማቆነጃጀት አሳንሰው “ዘርን ማፈናቀል” ብቻ ሳይሆን “የጀነሳይድ የዘር ጭፍጨፋ ወንጀል እንደሆነ ከተጠቂዎቹ አንደበት እናደምጣለን።

ወለጋ ውስጥ “የኦሮሞ ሁቱዎች” በአምሐራ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል ልክ ሩዋንዳ ውስጥ ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ የፈጸሙት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በመጻሕፍት ዘግበው ለዓለም ያሳወቁ እንደ እነ

1)      Machete Season –The Killers In Rwanda Speak (Jean Hatfield)

2)      When Victims Become Killers (Mahmood Mamdani)

3)      We wish to inform you that tomorrow we will be killed with our families (Philip Gourevitch)

4)      Conspiracy to Murder – The Rwanda Genocide (Linda Melvern)

5)      The Butchers in Rwanda

የመሳሰሉ እዚህ ለመዘርዘር ቦታ የማይበቃቸው የሩዋንዳ ዕልቂት ደራሲያን እና ሪፖረተሮች/ጋዜጠኞች/ የጻፉዋቸው መጽሐፍቶችና የጥናት ሰነዶች ስታነቡ ከዓለም ዓይን ተደብቆ ያለው የ35 አመት ዕልቂት በኢትዮጵያ ተመሳሳይ ነቱ የሚገርም ነው።

በተጨማሪም “ኦሮሚያ” ተብሎ በተሰየመው “አፓርታይዳዊ ክልል” በከርስትያኖችና በእስላም አምሐራ ሕዝብ እና በጋሞ ነገዶች እንዲሁም የመሳሰሉ ሌሎች ማሕበረሰብ አባላት ላይ የተፈጸመው “ጀነሳይድ” በመካድ አልተፈጸመም እያሉ በየሚዲያው የሚፈላሰፉ ምሁራን ይህንን ዕንባና ሰቆቃ ደጋግመው እንዲያዩትና የሩዋንዳው ዕልቂትና ይህ እልቂት ልዩነት እንደሌለው እሳቤአቸው እንዲያስተካክሉ ደግሜ ይህ ቪደዮ እንዲያጤኑት እጋብዛለሁ።

በዚህ ልደምድም፡

አንዳድ ሰዎች ይህ የአምሐራ ጭፍጨፋ ሁሉንም አምሓራ እንደ የሩዋንዳ ቱትሲ ዕልቂት ሁሉንም ቱትሲ በያሉበት ያዳረሰ ዕልቂት ስላይደለ ጀነሳይድ ሊባል አይቻልም፤ ሲሉ እሰማለሁ። ለዚህም መልስ በጋዜጠኛ ተስፋየ ተሰማ አባባል ልደምድም <<ወለጋም፤ አርሲም፤ ደብረዘይትም፤ ባሌም፤ ሐረርም……ወዘተ እየለ ይቀጥልና “አራጆቹ አቅም ካገኙ” አምሐራ አለበት በሚባልበት ምድር ሁሉ በመሄድ ያጠፉታል። “ሂትለር” እቅም ባከማቸ ወቅት እስከ አውስትርያ፤ ሆላንድ ፤ መላው ኣውሮጳ ወዘተ… ተሻግሮ “ይሁዲዎችን” ጭፍጭፏል። አምም አራጆቹ አቅም ሲያገኙ ከምድረገጽ ከማጥፋት አይመለሱም። ስለዚህ የሕልውና አደጋው ከፍተኛ ነው።>> 

ይህ ቪዲዮ ያቀረብኩበት ተያያዢነቱ በገና በዓል ተጠቂዎቹ ከሰዎች ለምነው ያገኙት ቆሎ ሲበሉ የተቀረው ሸሞንሟናው አዲስ አበባው የኪነት ባለሙያዎች እና ባለጊዜ ከተሜዎቹ ግን ቁርጥና ዊስኪ የተራጨበት ቀን እንደነበር ተጠቂዎቹ ከዚህ በታች በተለጠፈው ቪዲዮ ካንደበታቸው ትሰሙታላችሁ።  

መልካም የፈረንጅ ገና በዓል!

ሰላም ለናንተ ይሁን

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

Welega genocide አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም የአማራው ፈተና #Amhara Genocide Ethiopia

https://youtu.be/Z5kjsjz-_LU?si=s8y0dwOgVcf0-rjN



Saturday, December 21, 2024

የፋኖዎቹ ትግል “በፕሮቪንስያሊስቶች” ተጠልፎ ወድቋል! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/22/24

 

የፋኖዎቹ ትግል “በፕሮቪንስያሊስቶች” ተጠልፎ ወድቋል!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 12/22/24

እስክንድር ላይ የግድያና የሥም ማጥፋት ዘመቻው ተጧጥፏል። ትግሉ የመጠለፉን (ሃይጃክድ የመደረጉ) ምልክት ነው። ትግሉ “ፕሮቪንሺያሊስቶች” እየተመራ ነው። በተለምዶ አውራጃዊነት ወይንም በእንግሊዝኛው ቃል “ፕሮቪንሺያሊዝም” (Provincialism) አሁን ወሎ ጎጃምና ጎንደር ክ/ሃገር ውስጥ በአምሐራነት መሪነት ሳይሆን <<በአውራጃ ልጆች መሪነት>> የሚቀኝ (በጫካም በውጭ አገርም) እየታየ ያለው የትግል መርህ ነው።

ቃሉ ለሀገራዊ ወይም ለሀገራዊ አንድነት ኪሳራ የቆመ ለራስ አካባቢ መሪዎች ወይም “ክልል” የመቆርቆር አባዜ የተጠናወተው ማለት ነው። በተለይ ይህ በወሎ ጎንደርና በጎጃም ፋኖ ውስጥ እየታየ ያለው “የአውራጃ ልጆችነት በሽታ” የሚታየው በፋሺስት ቡድኖች የሚታይ ባሕሪ ነው። ይህ ባሕሪ ለትግሉም ለሀገርም ከፍተኛ አደጋ አለው። ያው ያየነው የ27+5 አመት የዜሮ ድምር ክስተት አዙሪት ነው።

በዚህ ትንታኔ ወሎ ጎጃምና ጎንደር አውራጃዎች ሲጠቀሱ፤ መልካምና ቅን እሳቤ ያላቸው ከጠባብ “አውራጃ ልጅነት” ነጻ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን የወሎ ፤ የጎጃምና የጎንደር ፋኖ (አንዳንድ) መሪዎችና ደጋፊዎቻቸውን አይመለከትም።

 የዚህ ብዕር ባውዛ የሚያበራው በዘመነ ካሴና በወሎ “ምሬ ወዳጆ” በተባለ (ማይሙ) እንዲሁም ጎንደር ውስጥ ባሉት አንዳንድ የፋኖ መሪዎች እና እንዲሁም ትግራይ ጠልና እስላም ጠል የፋኖ መሪዎችን እና ደጋፊዎቻቸውን ላይ ነው።

የዚህ ቡድን አደገኛነት ነገሩ የቆየ ነው። ዜጎችን ፤ ሽማግሌንና እናቶችን አፍኖ እምብርክ እስከ ማስኬድ ከማሰር፤ ከማሸበርና ከመሰወር እስከ  መገድል ጀምሮ የቆየ ትግሉን የጀመረበት ባሕሪ ነው። ዛሬ እስክንድር ነጋ ላይ የመግደል ዛቻ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ዛቻው የቆየ ቢሆንም።

 “የአውራጃ ልጆች አንድነት“ (በሩዋንዳዊያን Kinyarwanda ተብሎ በሚጠራው ሀገራዊ ቋንቋ  “ኢንተርሃሙዌ” የሚባለው ፤ለአንድ የጥፋት ግብና አብሮነት በጋራ ተቀናጅቶ የሠራ መዋቅር አሁን በወሎ፤ በጎጃም እና በጎንደር ፋኖ  በእስክንድር ላይ የግድያና የሥም ማጠልሸት ዘመቻ እየተካሄደ ያለው አጀማማር ሩዋንዳ ውስጥ “ኢንተርሃሙዌ” የተባለው ቅንጅት ሲጀምር ያሳየው አጀማማር ይመስላል።

እስክንድርን እስከ መግደል የዛተው የዛቻው ጀማሪው የጎጃም አውራጃ ልጆች ነፃ አውጪ ዘመነ ካሴ የተባለ ካፍንጫው ርቆ ማሰብ የማይችል መንደርተኛ የጎበዝ አለቃ ነው። ከዚያ ተከትሎ የራሱ አሽከሮችና የጎጃምና የጎንደር እንዲሁም የወሎ አውራጃ ልጆች ቃሉን በመከተል ይኼው እስክንድር ላይ የማያባራ የግድያና የሥም ማጠልሸት ዛቻ እያካሄዱበት ነው። ለዚህ ክፉ ሥራ የተመደቡም አሉ። አንዳንድ ሰዎች እነዚህን <<የአውራጃ ልጆች>> “የብአዴን ልጆች” ይልዋቸዋል።

የሚገርመው ደግሞ የፋኖ ትግል አስቀድሞ ሁሉም እንደገመተው አምሐራን ነፃ ያወጣሉ የተባለው ግምት ተኮላሽቶ አምሐራን ነፃ ለማውጣት ሳይሆን የገዛ ወገናቸ  አምሐራ የሆነው ኢትዮጵያዊው እስክንድርና ብዙ አምሐራዎችን በመግደልና ለመግደል በመዛበት አሁን እያየነው ያለው የጫካው ትግል “በፕሮቪንስያሊስቶች” ተጠልፎ የመውደቁ ክስተት ስናይ ከመገረም ያለፈ ተግርመናል።

አሁን በሦስቱ ፕሮቪንስያሊስቶች (የአውራጃ ልጆች) በኢትዮጵያዊው እስክነድር ነጋ ላይ የዛቱትና እየደረጉት ያሉት ሴራ ስንመለከት ካሁን በፊት ከገጠሙት ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት በከፋ መልኩ በግድያ ቀለበት ገብቶ እንዲጠፋ በየሚዲያው ሲያውጁ መስማት የትጥቅ ትግል በሚያካሂዱት ፕሮቪንስያሊስቶች ላይ ከፍተኛ የምርምር ጥናት ማካሔድ ያስፈልጋል። ባሮ ቱምሳ የተባለው የኦነግ መሪ በኦነጎቹ (ባጃራ) የመገደሉ ዕጣ ፈንታ ስናይ እስክንድር ላይ ይህንን እንዳይከሰት ያሰጋል

ብዙዎቹ የወሎ የጎንደርና የጎጃም ፋኖ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው እስክንድር ላይ እስከ ግድያና የሥም ማጥፋት ዘመቻ የሄዱበት ምክንያት በደምብ መፈተሽ የሚኖርበት ነው። በተለይም በጎንደርና በጎጃም ፋኖ ኢንተርሃሙዌው መዋቅር።

ስለሆነም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ይህ “የአውራጃ ልጆች” አደገኛ በሕሪ በቸልተኝነት ከተተወ ለእስክንድር ብቻ ሳይሆን አደጋው ለሀገራችን ኢትዮጵያም (ለአምሐራው በዋናነት) ጭምር ነውና መመከት አለብን።

 ትግራይ ውስጥ ወያኔ የጀመረው የእርስበርስ “የአውራጃ ልጆች ዘመቻና ጥፋት” ታስታውሳላችሁ፤ አሁን ያ ግርሻ ከስንት አመት በሗላ ትግራይ ውስጥ በሰብዓ እንደርታ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ። ይህ በአውራጃ ልጆች መቀናጀት ሰበብ በሚፈለጉት ላይ ‘ገዳይና ሥም አጥፊ’ “የኢንትርሀሙዌ ቡድን በማዋቀር” ብዙ ቀና ሰዎች ተገድለው ጠፍተዋል። እዚህ ፋኖ ላይም ችግኙ አቆጥቁጦ ያለው ያንኑ ነው።

በየሚዲያው የምታዘባቸው ብዙዎቹ ምሁራን ከጎንደር፤ ከወሎና ከጎጃም የተገኙ “የአውራጃ ልጆች” በሚያስፈራ ፍጥነት ጠባብ ጎሰኞች ሆነው አይቻቸዋለሁ። አንዳንዶቹ እስከ 7 ትውልድ ያልተደባለቀ የአምሐራ ትውልድ ያለው “የጠራ ደም” ያላቸው መሪዎች ፋኖን መምራት እንዳለባቸው የሚሰብኩ “የናዚ አቀንቃኞች” አሉዋቸው።

 እነዚህ በኢትዮጵያዊያን በተለይ ቀና በሚባሉ አምሐራ ምሁራን እነዚህን የናዚ አቀንቃኞች ከኦነግም ከወያነ ትግራይም ተለይተው አይታዩምና ዘመቻቸው እንደዋዛ መታየት የለበትም። ጀርመን የጀመረው የደም ጥራትና ያስከተለው ጥፋት ይህ መፈክር ነው።

ይህንን እስክንድር ላይ እየሰማን ያለነው የግድያም፤ እስክንድር አምሐራ አይደለም እና <<ትግሬዋ ባለቱ እስክንድር ነጋ ከሕዝብ የሰበሰበው ገንዘብ እየኖረችበት ነው>> የሚል <<የሲፍረዘኒኩ ዘመድኩን በቀለ>> የሥም ማጥፋት ዘመቻ (ወንጀል) ይህ ወንጀል በመረጃ ቲቪ ተላልፎ ከሆነ ጣቢያው ስም በማጥፋት መከሰስ ነበረበት) እና የነ ዘመነ ካሴ ደጋፊዎች እነ “አቶ ተክሌ የሻው” የመሰሉ <<የደም ጥራት አደገኛ ሰባኪዎች>> ለአውራጃ ልጆች ኢንተርሃሙውዌው ቡድን ጭንቅላት ቀራጺዎች ናቸውና መልዕክታቸው መጠናት አለበት

ትናንት አንድ ወዳጄ ሥልክ ደውሎ “ትንግርቱ” የተባለው እስክንድርን ሲቃወም ሰምቼው ገረመኝ እንዴት ታየዋለሁ ብሎ ጠየቀኝ።

እኔም እንዲህ አልኩት ፤ ምን እንዳለ ባልሰማውም “ረ/ፕሮፌሰር ተበየው” ትንግርቱ ገ/ጻድቅ እንኳን ባንድ ግለሰብ እስክንድር ነጋ ቀርቶ <<የትግራይ ሕዝብ ጠፍቶ እንደገና መሠራት>> እንዳለበት የሰበከ  ወጣት ፋሺሰት ስለሆነ ልጁ በግለሰብ ላይ መዝመቱ አያስገርምም አልኩት።

ረዳት ፕሮፌሰር ትንግርቱ ገ/ጻዲቅ ለአምሐራ ሕዝብ የሰበከው ሰበካ፦

<<ሺሕ አመት አስበህ ይህንን ትውልድ (የትግራይ ሕዝብ) ኒውትረላይዝድ (ካላጠፋህ/ካላሟሟኸው) ካለደረግኸው ፤ ትግራይ የሚለው መጠርያ እራሱ “ወንጀል” ማለት ስለሆነ ቃሉ በሕግ ታግዶ መጥፋት አለበት። ትግራይ የሚለው ቃል ይህንን ስም ይዘን እያሽሞነሞንን የምንቀጥልበት ሁኔታ መኖር የለበትም። ትግራይ የሚባለው ክልል ወደ አራት አምስት ክልል ከፋፍሎ ይህንን ትግራይ የሚባል የወንጀል ስምና አካባቢ መከፋፈልና በቋሚነት ከነስያሜው “ሪ-ቪዚት” (መከለስ) አለበት እላለሁ።>>

የሚል የናዚና የፋሺስቶች መርሃ ትምሕርት ያሰከረው የዘመነ ካሴ ደጋፊ <<የኢንተርሃሙዌው ቡድን አባል ነው>>። ሰለዚህም ረ/ፕሮፌሰር ትንግርቱ ገ/ፃድቅ በእስክንድር ነጋ ላይ መዝመቱ አትገረም፤ አልኩት። ወዳጄም፤ ይህንን ስነግረው አልሰማሁትም ነበር አለኝ። ቪዲዮውም ላኩለት። አየውና ደውሎ “ደነገጥኩኝ” አለኝ።

የፋኖ ትግል በኢንተርሃሙዌው<<የአውራጃ ልጆች>>  ከተጠለፈ ቆይቷል የምልበትም ከላይ በስም የተጠቀሱት ታዋቂ ሰዎች እና እንደ ትንግርቱ ያሉ በጣም ዘረኞች የሆኑ ሰዎች የተካተቱበት የዘመነ ካሴ ደጋፊዎች በሚያራግቡት አደፍራሽ “መናፍህ” ምክንያት  ነው።  

ፋኖን በሚመለከት የኔን ጽሑፍ ስትከታተሉ የነበራችሁ ተከታታዮቼ እንደምታስታውሱት የፋኖ ትግል ከተጠለፈ ቆይቷል ነበር ያልኩት (ገና ሲጀመር ዘመነ ካሴ ጠልፎ አኮላሽቶታል)።

እንደምታውቁት አውራጃዊነት ትግራይ ውስጥ ስር የሰደደ አደገኛ መልሕቅ ነበር። አሁን ፋኖ ውስጥ  ጎንደር፤ ጎጃምና ወሎ ላይ ተንሰራፍቷል  ይህ ፕሮቪንስሊዝም ርዕዮት እየተከተለ ያለው ቡድን እጅግ በጣም በታጠረ እይታ ውስጥ እየዳከረ የራሴ የሚለውክልል” “አውራጃ” “ክፍለ-ሃገርና ከዚያ አውራጃ የተወለዱ መሪዎችንባጠቃላይ ተወልጄበታለሁ በሚለው የማሕበረሰብ ማንነትን ከጫፍ ከፍታ ላይ በመስቀል የኔ የማይላቸውን ቁልቁል የሚመለከት የራሱን ማሕበረሰብ በደረቱ ላይ ለጥፎ  ፍቅሩን እና ፍቺውን ለራሱና ላካባቢው የሚያጎላ፣ ብዙ ጊዜ ወደ አግላይ ድርጊቶች በማትኮር፣ ግጭት በመጥመቅ  ላይ ነው። በእውነቱ ይህንን ወቀሳ ሳቀርብ ጠላት እንዳይመቸውም እየቀፈፈኝ ነው። ሆኖም መገለጽ ያለበት ጉዳይ ነው።

ይህ በአውራጃ ተወላጆች መሪዎች እምነት ጥሎ እስከ ወዲያኛው የመመራት ፍላጎትና መሪዎቹን የማጉላት ክስተት ከፍተኛ ችግር አለበት።  ችግሩም “እኛ እና እሱ በሚል አግላይ መርሆ እስክንድር ላይ ግልጽ የግድያና የሥም ማጥፋት ዘመቻ በመካሄድ ትግሉ እንዲቃጠል አድርገውታል። ባጭሩ ትግሉ ጥናት የሚያስፈልገው ባልታወቀ ብክለት ተበክሏል። አውራጃዊ መሪ ለአምሐራ ችግር መፍቻ አድርጎ የሚጓዝ የሽምቅ ነፃ አውጪፖለቲካ ምጥቀት ያጠረው የብቃት ቁርቆዛ ነው

 አውነት ነው፡ “ፕሮቪንስቶቹ” ስካር ውስጥ ናቸው። የጎሪላ የሽምቅ ተዋጊ ሕግና ጥንቃቄ አይከተሉም። በዘፈቀደ እየተጓዘ ወታደር ሲማርኩ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው ባንዴ ይሰክራሉ። ይህ ደግሞ አደጋ አለው። ከውስጥ አንድነትን የሚሸረሽር የግድያና የስም ማጥፋት ዘመቻ እያጧጧፉ በወታደራዊ ድል መስከር ረዢሙን ጉዞ ባጭር ማስቀረት ነው። በሽምቅ ተዋጊዎች ሕግ በጊዜዊ ድል የሚሰክር ቡድን ሕጻን እና የኳስ ጨዋታ ደጋፊ ብቻ ነው። ድል ሲያገኝ ይቦርቃል ሳይታሰብ ግብ ሲገባበት የሚይዘው የሚጨብጠው አጥቶ ይጨልምበታል። በኒዚህ የአውራጃ ልጆች እያየን ያለው ይህንኑ ችኮላ ነው።  እስክንድርን መተናኮል ጊዜ የሚፈጅ ቢሆንም በሗላ ትግሉን እጅግ ዋጋ ያስከፍለዋል። እመኑኝ ፖለቲካው ውስጥ ቆይቻለሁ።

 እስክንድር ላይ እየወረደበት ያለው የግድያ ዛቻ፤ ጥላቻና የሥም የማጠልሸት ዘመቻ በትግል ዕድሜየ ውስጥ ያላየሁት እጅግ አሳፋሪ ዕብደት እያየሁ ነው። ታላቁ እስክንድር በኦሮሙማው መንግሥት እና ወገኖቼ ብሎ ባመናቸው የመንገሥ ሕልሜ “በ ዲ ኤን ኤ” የተላለፈልኝ የነጋሽና የአንጋሽ ዘር ልጅ ነኝ’’ የሚሉ እንደ  ዘመነ ካሴ” ዓይነቱ <<የፋሺሰት ክሊክ>> ግሰለቦችና ደጋፊዎቹ በኩል የግድያ ዛቻ የተሰነዘረበት አጅግ አሳዛኝ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ማየቴ እስክንድርን ሳይ በምስጋና ቢስ ሕዝቦች የተገለሉ ያጎረሳቸውና የታገለላቸው እጅ በሚነክሱ ሰዎች የተገለሉና የተገደሉ የብዙ  የዓለምና የአፍሪካ ነፃ አውጪ መሪዎች ታሪክ ያስታውሰኛል።

እስክንደር 10 ጊዜ ሲታሰር ሲደበደብና ሲፈታ “ለዝናውና ለስለላ አለመሆኑን መፈተሽ አለበት” እያለ የሚለፍልፍ የጀርመኑ ሲፍሮዘኒክ (ዘመድኩን በቀለ) ሰምቼው የፋኖ ችግር በነዚህ ዓይነቱ ሰዎች መዳፍ ውስጥ መውደቁ” ያሰዝናል።

እስክንድርን መተናኮል ትግሉን እጅግ ዋጋ ያስከፍለዋል የምልበት ምክንያት አንዱ ትግሉ “በፕሮቪንስያሊስቶች” <<ሃይጃክድ>> ሆኖ መጠለፉ ነው። በዚያው ላይ የማይሙ ብዛትና አጃቢ የት የሌለ ነው።

ሰላሙን ለናንተ

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay