Friday, September 22, 2023

ታጣፊ አልጋቸውን ይዘው መሥርያቤታቸው ውስጥ የሚተኙ ታታሪ ወያኔዎች የልደቱ ምስክርነት ሲፈተሽ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/21/2023

 

ታጣፊ አልጋቸውን ይዘው መሥርያቤታቸው ውስጥ የሚተኙ ታታሪ ወያኔዎች የልደቱ ምስክርነት ሲፈተሽ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/21/2023

አንብበው ከጨረሱ በላ ቪዲዮውን ከታች ይመልከቱ

የልደቱ “ወለም ዘለም” ባህሪ ብዙ ጊዜ ስለጻፍኩ በዚህ ሰውየ አልጽፍም ብየ ነበር፡ ሆኖም ወያኔዎች የልደቱን ንግግሮች ስለወደዱለት ደጋግመው ስለሚጠቀሙበት እርሱም ደግሞ ደጋግሞ ወያኔዎችን ግማሹ መላእክት ፤ግማሹ ሰይጣን እያደረገ በመሳል ሥርዓቱን እንደ ሥርዓት ከመመዘን ይልቅ የወያኔ ናዚ አባል ግለሰቦችን << ታጣፊ አልጋቸውን ይዘው መሥርያቤታቸው ውስጥ የሚተኙ አገር ወዳድ ታታሪ ‘ወያኔዎች’ >> እያለ የበጎ ተምሳሌት እንደሆኑ በመሳል የሥርዓቱን ትክክለኛ ስዕል እንዳይታይ ዛሬ የተወለዱና ለወደፊቱም ለሚወለዱ ወጣቶችን ለማሳሳት “ዘር አጥፊና አገር አጥፊውን ‘ኔቲቭ ኮሎናይዘሩን’ ወያኔን”  “የተዛባ ሥርዓት” ብሎ በመጥራት የሚለፋ ከንቱ ሰው ነው።

 የወያኔ ግለሰቦችን (ልክ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም የወያኔን የደህንነቱ ሹም የነበረ ክንፈ ገብረመድህንን ልክ እንደ ልደቱ ሲያቆለጳጵሱት እንደነበሩት) ሁሉ ልደቱም ግለሰቦችን በምሳሌ እያጣቀሰ (ያውም ስም ሳይጠቅስና እንዳፈተሹም፤ ለአቃቂር እንዳናቀርባቸው) ታሪክን ማዛባት (ዲስቶርሺን) በእውነትና በማስተዋል ላይ የሚደረግ የማዛበት ጥቃት ነው። ከሙሉ ኩንታል እንክርዳድ አንዳንድ ጥሩ ስንዴ አገኘሁ እያለ የሚያወራ አውቆ እያወቀ ታሪክ እያጣመመ “ልዩ ፖለቲከኛ ሆኖ ለመታየት” ታሪክ የሚያዛባ ከንቱ ፖለቲከኛ ነው።

ልደቱ እያደረገ ያለው ገዢዎቻችን እና አራጆቻችንን እንደ ሥርዓት ከማየት ይልቅ ሥርዓቱን በግለሰቦች እየመዘኑ እራሳችንን፣ ማህበረሰባችንን እና የወደፊት ግቦቻችንን እንዴት እንደምንረዳ ያለፈውን መረዳት እና ማስታወስ እንዳይኖረን “አምታች” ግለሰብ ነው።

ዛሬ ዛሬ የመጣ አዲስ ፖለቲካ ደግሞ በልደቱ ብቻ ሳይወሰን “ሞገስ ተሾመ ዘውዱ” የተባለ የገበታ ሚዲያ አዘጋጅ “አማራዎች ሲታረዱ አላውቅም ፤ ማን እንደሚያርዳቸውም አላውቅም”፤ አራጆችን “አራጆች” ብለን ባንጠራቸው ጥሩ ነው፤ የሚል ፤ “ምክንያቱሳ?” ተብሎ ሲየጠየቅ “ነገሩን 'ሲጅ' ማድረግ ነው ፤ ሁኔታውን ያባብሳል..” የሚል (ሁለት ሰዎች ተኝተው አንድ ጅብ መጥቶ አንድ እግሩን በልቶት ሁለተኛውን እግሩን እንዳይደግመው “ዝም እንበል” እንደሚለው ሰውየ፡ ዛሬ የበቀሉ ፖለቲከኞች ደግሞ “አራጆችን አራጆች ብንላቸው እንደገና እንዳያርዱና ተከታይ ትውልድም ያንን እንዳይደግም” የሚል የክሕደትና “የፍጅትን ክብደት የሚያሳንስ አዲስ የ2015/2016 ፖለቲካ ቅስቀሳ ብቅ ማለት ጀምሯል (አዲስ ባይሆንም ያንን በእነ ደመቀ መኮንን እና ተከታዮቹ ሲባል የነበረ ቢሆንም)።

 “ወያኔ” <<ሁሉም አማራ በየቀኑ አልገደለም፤ሁሉም አማራ ቢገድል ኖሮ አሁን አማራ የሚባል ባልኖረ ነበር>> የሚለው ልደቱ ወያኔ አማራ ሕዝብ ላይ በማኒፌስቶውና በተግባር “አማርኛ ቋንቋን ፤ ሰንደቃላማችንን፤ ኦርቶዶክስን፤ አማራን እና ኢትዮጵያን” አከርካሪያቸውን ለመስበር፤ ትግራይ ጫካ 17 አመት እና 27 አመት በመንግሥትት በተጠቀሱት ላይ ምን እንደፈጸመ ልደቱ ቢክድም ታሪክ ዘግቦታል።

ልደቱ እያደረገ ያለው “ወያኔ በባሕሪው ዋና የአማራ የዘር ጨፍጫፊነቱን ለመሸፈን የማይቻል ሆኖ ስላገኘው ያንን ግን “በዘዴ የወንጀሉን ክብደት ለመቀነስ” “የሚጠቀምበት” ሙግት ነው።  ልደቱ እንዲህ ያለ ሙግት ሲያቀርብ ወያኔዎች ንግግሩን ስለ ወደዱለት በወያኔው ዘፋኝ በጸረ አማራው “እያሱ በርሄ” የተዘፈነ “ክላሲክ ለስላሳ ሙዚቃ” እየታጀ እዚህ የተለጠፈው ቪዲዮ የለጠፉት ወያኔዎች ናቸው። ወያኔዎች ልደቱን እንደ ማስረጃ በመጠቀም ሃቁ ይሄው ነው እያሉን ነው።ልደቱ ዋናው ምስክራቸው ነው።

የልደቱ ክርክር፤ ወያኔ በአማራ ነገድ ላይ ያነጣጠረው የዘር ፍጅት ወንጀል ለማጣጣልና ለመካድ ነው። ለዚህም ሥርዓቱን በዘር አጥፊና “በነቲቭ ኮሎናይዘርነት” ሳይሆን ልደቱ የወያኔን ሥርዓት የሚጠራው “ዲሞክራቲክ የሆነ፤ የሰደቡትንም ጭምር የማያስር” የመጻፍ ፤የመናገር፤ ትችትን የፈቀደ፡ ነገር ግን <<የተዛባ ሥርዓት>> በሚል ነው የሚገልጸው።

አንባቢዎቼ ልብ ልትሉ የሚገባ “የየ አገሮች የፋሺስት እና የናዚ ባሕርያቶችን አካሄዶች እንደየ አገሩና ዘመኑ ይለያያሉ”። ልደቱ ይህንን ላለመጠቀም የግድ ባንድ ዘመን የተፈጸመው በሌላ አገር እና በሌላ ዘመን ተመሳሳይ እርምጃ መወሰድ ነበረበት የሚል “ፋውል ፍልስፍና” ይጠቀማል።

ልደቱ ከንቱ  ሰው ነው የምልትም “በተዛባ ሥርዓት” ውስጥ “አስተዳደራዊ ብልሽት” እንጂ “የዘር ጭፍጫፋ” አይካሄድም። የዘር ፍጅት የሚካሄድበት ሥርዓት “በዘር፤ በቋንቋ የሚያስተዳድር፤ በሃይማኖት፤ በቆዳ፤ በርዕዮተ ዓለም፤ በአገር ወረራ…” ልዕልና የሚያምን ቡድን ሲፈጠር ነው። የዘር ፍጅት የሚካሄድ “በተዛባ ሥርዓት” ውስጥ ሳይሆን “ሆን ተብሎ በውይይት ታቅዶበት ተመክሮበት፤ተዘጋጅቶበት አመቺ ሁኔታዎችን በመጠቀም አንድን ዘር/ነገድ/ብሔረሰብ የመኖር ሕልውናውን እያስጨነቀ የጥላን ትርክት እየተጎተተ ቀስ ብሎ እያደገ ከጥንት በቅሎ የሚመጣ ነው።

 ይህንን እውን ለማድረግ እንደ ጀርመን ናዚ ገጣሚዎችና የኪነት ሰዎች ወያኔዎችም አማራን ቀለብ ለማስገባት  በመጀመሪያው ማኒፌስቶውና በዘፈኖቹ እና በሚገጥማቸው ግጥሞቹ ሁሉ “አማራን ቀለበት ውስጥ” በማስገባት የዘር ፍጅት አካዷል። ፍጅት ለማካሄድ የታጠቀ የቡድን ልዕልናን ወይንም መንግሥትነትን ሲቆጣጠር ነው።  በጀርመን ውስጥም ናዚ ባስተዳዳራቸው አገሮች ሁሉ ሁሉም አይሁድ አልጨፈጨፈም። ባነዚ ባለሥልጣናት ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ ይሁዶች በቀጣሪዎቻቸው ደግንትና (ባልተገለጸ ምክንያታቸው) ከሞት እንዲድኑ ያደረጉ ናዚዎች ነበሩ (ልደቱ ታጣፊ አላጋቸውን ይዘው ሥራ ውስጥ የሚያድሩ በጎ ወያኔዎች ነበሩ የሚላቸው አየነት፤ ‘’ምን ሲያደርግ እንዳያቸው’ ባይታወቅም)።

በስልት እና በድፍረት ፍርሓትን በመጋፈጥ “ኖርዲክ ጀርመን” መስለው አለፍ ብሎም አንዳንድ ጊዜ አይሁዶች ከአሰቃቂ እጣ ፈንታ ለመራቅ ሲሉ ሌሎች አይሁዳውያንን ያወግዙበት የነበረውን የውግዘት ባህል አንብበናል። “አለምነህ መኮንን” የመሰለ “አማራን ያወገዘና የተሳደበ” ወራዳ ግን በስልት ህይወቱን ለማዳን ሳይሆን ለማገልገል ቢሆንም ፡ ልደቱ ድሮ “አማራ አይደለሁም” ባለው አንደበቱ  ወያኔዎች ልደቱን በአማራነት ሳይሆን ያሰሩት (ታስሬ ነበር የሚለውን ንግግሩን) በሚያምታታው ፖለቲካው ነው።

 በሚገርም ሁኔታ ልደቱ  በተጫወተው የጮሌ ፖለቲካ ወያኔዎች “ሽጉጥ” አስታጥቀውታል፤ (ያንን አርሱም ሲክድ አልሰማንም) ፤ከዚያ እልፎ በወያኔ ናዚ ፓርላማ በመግባት በሚሰራው የጮሌ ፖለቲካ “መኖር ብቻ ሳይሆን ደሞዝ እንዲግጥ” ሲፈቀድለት ስለ አማራ ጭፍጨፋ የተቃወሙት አንጋፋ የሰብኣዊ ተሟጋቾች እንደ እነ ሐኪም አስራት ወልደየስ እና ብዙ ሰዎች  ግን ተገድለዋል።

ልደቱ የወያኔም ሆኑ የናዚዎችና የፋሺሰቶች ባሕሪ የኖሩበት ዘመንና የጭካኔ አዋሳሰድ ስልቶችና ልዩነቶችን ሳይለይ ወያኔ እና ናዚዎችን ባንድ መደብ በመመደብ የግድ ሁለቱም ዘር አጥፊዎች ከሆኑ አንድ አይነት አፈጻጻምና ጭካኔ መታየት ነበረበት የሚል የልደቱ የክርክር አዝማሚያ “ወያኔ ናዚ አይደለም፤ ወይንም ዘር አጥፊ አይደለም” ስለሆነም መላው አማራ ስላላጠፋ ወያኔ ናዚ ሊሆን አይችልም ነው ክርክሩ።

ልደቱ በለመደው ምላሱ አንዴ አማራ አይደለሁም ይልና ቆየት ብሎም “እኔ አማራ ነኝ” ከሚለው እና እዚህ በዚህ ቪዲዮ የምናደምጠው አማራ በየቀኑ አልተገለደም ከማለት አልፎ ፤ ሁሉም አማራ ቢገደል ኖሮ እዚህ ድረስ አሁን አማራ የሚባለው ዘር አይኖርም ነበር” ከማለት ተሻግሮ “አዎ አማራ የዘር ጥቃት ተፈጽሞበታል ስለዚህ አሁን ፋኖ እያደረገው ያለው ትግል የሕልውና ትግል ነው” የሚለው ተለዋዋጭ ንግግሩ የሚያሳይን ከጊዜው ጋር የሚገለባበጥ እራሱን ለማመጻደቅ ‘አቋሜ አንድ ነው’ ይበል እንጂ “ተለዋዋጭና አቋመ ቢስ” ነው”።

መካድ የዘር ማጥፋት ዋና አካል ሲሆን ፣ በተለይም ክሕደት የዘር ማጥፋት ዘመቻው እየተካሄደ ባለበት ወቅት/ዘመንፕሮፓጋንዳ” እናየጅምላ ግድያ ማስረጃዎችን ከመደበቅ” ጀምሮ እስከ የልደቱ አይነት “ሁሉም አማራ በጅምላ አልተገደለም” የማስተባበያ ንግግርን ክሕደት ውስጥ ይጠቃለላል

ልደቱ ይጥላው አይቀበለው deliberate mass murder (ሆን ተብሎ የጅምላ ጭፍጫፋ በወያኔ ዘመን አማራው ላይ ተካሂዷል። “ሁሉም አማራ በየቀኑ አልተገደለም” የልደቱ የወያኔ ጥብቅና ወያኔን ከጅምላ ገዳይነቱ ነፃ አያወጣውም።የወያኔም ሆነ የናዚ ጀርመን የጅምላ እልቂት ስልታዊና  በመንግስት የተደገፈ “state-sponsored” ፍጅት  ነበር። ልደቱ በየቀኑ አማራ አልተገደለም ክርክሩን ትምሕርት ቢሆነው የወዳጄ ሐኪም ዶክተር አሰፋ ነጋሽ  << PERPETRATING GENOCIDE OR PROMOTING FAMILY PLANNING? THE UNETHICAL USE OF BIRTH CONTROL PROGRAM AS INSTRUMENT OF AMARA ETHNOCIDE by Assefa Negash, M.D.Amstelveen, Holland – the 17th of July 2017) >> የሚለው ጽሑፍ እንዲመለከት እጋብዘዋለሁ። ይህ የናዚና የወየኔ የፍጅት ስልት አንደነትን ያሳል።

ይህ ብቻ ሳይሆን << Why Have the Amaras Once Again Become Victims of Ethnic Cleansing by TPLF? By Assefa Negash, M.D. 18th of April 2012 >> የሚለውም ጉጉል በማድረግ ልደቱ እንዲመለከተውና እራሱ ልደቱም << እኔ እየነበርኩበት ባለው አዲስ አባባ  ኢትዮጵያ ውስጥ ነው አማራ ሁሉ እየተፈጀ ነው፤ ትግሬ ሁሉ እየተጠቀመ ነው፤ የሚለው የውሸት ትርክት እተነገረ ያለው?>> ስለሚለው የልደቱ ውዥምብራም ክርክሩ የዶ/ር አሰፋ ጽሑፍ ይረዳዋልና ይመልከተው።

 ጀርመን ውስጥ የይሁዲ “ጥላቻ” የጀመረው “ሆሎካስት/ጀነሳይድ/ የሚባለው ፍጅት” ከመከሰቱ በፊት አውሮጳ ውስጥ ለዘመናት የተከሰተ ነበር፤ ትግራይ ውስጥም ወያኔ ወደ መንግሥትነት ከመምጣቱ በፊትና ፍጅቱን ከማካሄዱ በፊት ትግራይ ውስጥ ለዘመናት በዮሐንስና በምንሊክ ዘመን (ሸዌና ትግሬ የሚል የትግራይ ጠባብ ብሔረተኞች “ንጉሥነታችንን ተነጠቅን” ከሚለው ትርክት) ጀምሮ ብቻ ሳይሆን አንዳንዶቹ ወደ 13ኛው እና 14ኛው ክፍለ ዘምን በአምደጽዮን እና በዘመነ ዘርአ  ያቆብ ዘመን በመውሰድ “በትግሬና አማራ” ጥላቻ እንደተጀምረ የወያኔ ናዚዎች በመጽሕፍታቸው ጠቅሰውታል። ስለዚህ ዕቅዱ ሲጋተት በሂደት እየጎለበተ የመጣ “ወያኔ የተረከበው ጥላቻ” መንግሥት ሲሆን ጥላቻውን ወደ የዘር ፍጅት አሳድጎ “ተግብሮታል”።

ስለዚህ አማራ በማኒፌሰቶው አማራን በጥቃት ኢላማ “ሲያስቀምጥ አላነበብኩም” የሚለን ልደቱ አያሌው እና ዛሬ አማራ ለምን በወያኔ ቀለበት ለጥቃት ተጋለጠ ብላችሁ ግራ ለምትጋቡ መልሱ ከላይ የጠቀስኩት ነው (የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?” በሚለው መጽሐፌ  ውስጥ በሰፊው አሳይቻለሁ። ወያኔ አማራን ለመጨፍጨፍ ማኒፌሰቶ አላስፈለገውም ነበር። በማኒፌሰቶ ተነደገፍም አልተነደፈም ጀርመኖት በይሁዶች ከጭፍጨፋው በፊት አውሮጳ ውስጥ ጥላቻቸው ተንሰራፍቶ እንደነበር ሁሉ “ትግሬዎችም” በአማራ ላይ ሥር የሰደደ የንግሥና ቁርቁሳቸው አማራን በጥላቻ ቀለበት ማስገባት የጀመሩት በ1967 የጀመረ ሳይሆን በ13ኛው እና 14ኛው ክ/ዘመን እንደነበር ሳይደብቁ ጽፈውታል።

 ልደቱም እግረመንገዱን ይህንን ቢመረምር ጥሩ ነው። ነገዶች “የግድ” እደግመዋለሁ “የግድ” እንደ እነ ዚያኛዎቹ የ16ኘው ክፍለ ዘመን የታየው በከብት አርቢዎቹ ወራሪዎች ቢላዋ ከምድረገጽ የጠፉት 26 ብሔረሰብ ጎሳዎች ለምን አማራ ዛሬም እንደነሱ ሊጠፋ አልቻለም የሚለው የልደቱ ከንቱ ሙግት ዘመኑና የክፍለዘመኑ የግድያ ስልት፤ ብስለት፤ ዓለም አቀፍ ሕግና “ስልታዊ ጥንቃቄ” ልዩነት መኖሩን ያላገናዘበ ሙግት ነው።

ስለሆነም ሁሉም አማራ በየቀኑ አልተጨፈጨፈም፤ሁሉም አማራ አልተገደለም፤ የሚለው የልደቱ ከንቱ የወያኔ ውዳሴ፤ ለምን በጸጉር ስንጠቃ መራቀቀቅ ውስጥ መግባት እንዳስፈለገው ባይገባኝም፤ ወያኔ መላው አማራ “ዛሬም ድረስ እየተካሄደበት ያለው የጅምላ ጭፍጨፋና” በአማራ ማሕበረሰብ ህይወት ላይ ያሳደረው የ48 አመት << ቱራማ ፤ ፍጅትና ስደት>>  ወያኔ ከዘር ማጥፋት ወንጀለኛነቱን ነጻ አያደርገውም።አንብበው ከጨረሱ በላ ቪዲዮውን ከታች ይመልከቱ

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

 


 

 

Thursday, September 14, 2023

 

የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ህወሓት የኤርትራን ነፃነት ሲገፋበት ኢሳያስ ግን የኢትዮጵያዊነት ፍሎጎት አሳድሮ ነበር

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

9/14/23

ይህ ቪዲዮ አማርኛ እና ትግርኛ የያዘ ሰነድ ነው።ወያኔ የሚባል ድርጅት ከጅምሩና ከጥንስሱ መነሻው ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች ቀርበውበታል። ኢትዮጵያን በአፓርታይዳዊ ፌዴራሊዝም ከማዋቀር ጀምሮ ሕዝባችን እስከ እርስ በርስ ጥላቻና ጦርነት በዕቅድ ማስነሳትና መቆስቆስ ጀምሮ የኤርትራን ነፃነት እውን ለማድረግ በአካል ሻዕቢያን በመደገፍ በጦርነት እስከ መካፈልና ብሎም ወደ ተባባሩት በአካል ሄዶ ደብዳቤ በማስገባት የኤርትራን መገንጠል ተቃውሞ እንደሌለውና ሁለቱም የባሕር ወደቦችን ለኤርትራ እንዲሰጡ ያለ ምንም ተቃውሞ ፈርሞ አሳልፎ ለሻዕቢያ በመስጠት ሃገራዊ ክሕደት መፈጸሙ የተለያዩ ሰነዶችን ካሁን በፊት አቅርበናል። ዛሬ በዚህ ስዕለ ድምፅ የምታደምጡት ከኢሳያስ ጀምሮ እስከ ኦነግ እና የመሳሰሉ የሻዕቢያ መሪዎች ሳይቀሩ በዚህ ጉዳይ አስምልክቶ ግልጽና “ፈራ ተባ” ያሉ የሚያሳዩ ኢሳያስ “ኢትዮጵያዊነት ስሜት” እንደነበረው የሚያረጋግጡ ፍንጮች መሆናቸውና ወያኔ ምን ያህል የከፋ የመጨረሻ ባንዳ መሆኑን በዚህ ሰነድ እናደምጣለን። ሌንጮ ለታን በደምብ አድምጡት። የሻዕቢያ አመራር አባል የነበረው መስፍን ሓጎስም ከጥቂት አማራር አባላት ስብሰባ ላይ ግልጾላቸው እንደነበር በዚህ የትግረኛ ቃለ መጠይቅ ከአውስትራሊያ ራዲዮ ጣቢያ ባደረገው ቃለ መጠየቅ አረጋግጧል።

ጌታቸው ረዳ

Click the video image to play



 

Tuesday, September 5, 2023

ለትውስታ!! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 9/5/83

 

ለትውስታ!!

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

9/5/83

ፎቶ፤ አክሱም በወጣትነት ዘመን ነው። ዛሬ ለምነህ በማታገኘው “ውብ” “ድንቅ” የአብሮነት በመልካሙ ዘመን!

ይህ ፎቶ ከስንት አመታት በላ አክሱም ያለቺው  እህቴ ዛሬ ልካልኝ ደስታውን መቋቋም አልቻልኩም። ይኼው እንዲህ ያማረብን ነበር፤ ተወበዳጁ በንጉሡ ዘመን። ከታች ያለው ፎቶ “እስላም ክርስትያን ሳንባባል” ስንዋደድ የነበርነው የልጅነት ጓደኛዬ “ማዕሩፍ ኑርዬ” ነው። ማዕሩፍ ዛሬም ከተወለደባት ከአክሱም ከተማ አልተንቀሳቀሰም። ዛሬም እዛው ይኖራል። ከስንት ዘመን መለያየት በላ ሰሞኑን በስልክ ስንገናኝ “ተላቀስን” ! መልካሙ አስለቃሽ የደጋጎች ሰዎች ዘመን።

የዛሬዎቹ የተማሩ የተመራመሩ ተብየዎች ባልነበሩበት ዘመን “የጭካኔ ዘመን” ይበሉት እንጂ ዘመኑ የደጋጎች የገራገር ሰዎች ዘመን ነበር (ሰሞኑን መጎስ ተሾመ በተባለው ተበጥራቂ በራሱ ሚዲያ ላይ “ተራቃቂ” እንግዶችን በመጋበዝ “ሃይማኖቶቻችን በጨካኞች ሲመራ የነበረ” ሥርዓታችንና ባሕላችን የአረመኔ የጨካኞች ዘመን፤ የሚሉ እንግዶችን ባሕላችንን ሲደበድቡት ሰንብተዋል። የራሳቸው ዘመን በቅጡ ሳይመረምሩ ዘመናችንን የጉረኞች፤የልዩ ነን ባዮች ፤የርሃብተኞች የጨካኞች ዘመን እያሉ “የዲግሪ መረቂያቸው” እያደረጉት ያለው የደማቆቹ ኮዋክብት አገር “ሙሶሎኒና ሮማን ፕሮቻስካ” የዘለፍንን እንዳይበቃ በራሳችን በዛሬው ወጠጤዎች ያ ደጉ ዘመን “ሲዘለፍ” ቸል ማለት አልቻልኩምና መልስ መስጠት አስፈላጊ ስለሆነ በዚህ ርዕስ እመለሳለሁ። ለማንኛውም ሰላም እንሁን!

ጌታቸው ረዳ

Sunday, September 3, 2023

አራጆች የሚል ቃል ባንጠቀም ጥሩ ነው” “እኔ ሰው ስለመታረዱ አላውቅም” የሕግ ምሁር መጎስ ተሾመ! “አራጆችን አራጆች ካላልናቸው ምን እንበላቸው? “ሃኪሞች እንበላቸው?” ጋዜጠኛ ተስፋየ ተሰማ ትችት አቅራቢ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 8/3/23

 

አራጆች የሚል ቃል ባንጠቀም ጥሩ ነው” “እኔ ሰው ስለመታረዱ አላውቅም” የሕግ ምሁር መጎስ ተሾመ!


     “አራጆችን አራጆች ካላልናቸው ምን እንበላቸው? “ሃኪሞች እንበላቸው?” ጋዜጠኛ ተስፋየ ተሰማ

 

ትችት አቅራቢ

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay) 8/3/23

ይህ ውይይት የተካሄደው በቴድሮስ ፀጋዬ አወያይነት በርዕዮት ሚዱያ ሲሆን ቴድሮስ ፀጋዬን ለሚዛናዊ አወያይነቱ ሳላመሰግነው አላልፍም።

የሆነው እንዲህ ነው፤፡

 “የሃሳብ ገበታ” የሚል የመወያያ መድረክ አዘጋጅ የሆነው የሕግ ምሁርና ተማሪ ሞገስ ተሾመ እና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ በትናት ዕለት፤ በርዕዮት ሚዲያ (ቴድሮስ ጸጋዬ) ቀርበው “አማራ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበታል” በሚል ርዕስ ስለ አማራ ጉዳይ ውይይት አድርገዋል።

ረዢም ውይይት ካደረጉ በላ በውይይቱ መሃል “ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ” እምባ እየተናነቀው ወለጋና የተለያዩ ቦታዎች ውስጥ አማራ በመሆናቸው ሳይሞቱ በህይወት እያሉ “እንዲሰቃዩ” በሚል “እግር እና እጆቻቸው እየተቆረጡ” ተሰቅለው ከተሰቃዩ በሗላ ከዚያም ሲገደሉ ያዩ “ከግድያው ያመለጡ አማራዎችን”  አገር ቤት ሄዶ ቃለመጠይቅ አድርጎላቸው ከተመለሱ ሁለት ሳምንት እንደሆነው እየገለጸ “ሆድ ብሶት” እምባ እየተናነቀው ስለ ሁኔታው ሲናገር ለነበረው “ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማን” ተወያዩ አቶ መጎስ ተሾመ የሚከተለው አስደንጋጭ ንግግር ተናገረው፡-

<<ይህ “Appeal to pity” እያደረግክ ነው ያለኸው>> አለው።

“Appeal to pity” ማለት፡ ተከራካሪው ክርክሩን በሎጂክ(በተጨባጭ አመክንዮ) አስደግፎ ከመሞገት ይልቅ በተመልካቾች ስሜት ውስጥ ሓዘን እንዲሰማቸው በማድረግ እንዲያዝኑልህ ድጋፍ በመፈለግ ስሜታቸውን በመስለብ ሞጓቹን ለማሸነፍ መሞከር ማለት ነው።>>

በማስከተልም ሞገስ ተስፋየን እኔን በተመለካች ዘንድ “ለእርድ” አቅርበኸኛል፤ ማለትም “ጸረ እንዲህ ጸረ እንዲህ ነው እንዲሉኝ….” በማለት የተስፋየን እንባ አድማጭን በቀላሉ ስለሚስበው እኔን “ጥፋተኛ እና ለአማራ ስሜት እንደሌለኝ ለማድረግ መሞከር ነው” ሲል አወገዘው።

የሞገሰ አባባል ቢገባኝም “የመጎስ ተቃውሞ ፍጹም መባል ያልነበረበት፤ በሌላ መንገድ መግለጽ እንደነበረበት ብመኝም ፤ ጋዜጠኛው የሰነበተበትን እና ያደመጠውን የአማራዎችን አሰቃቂ እሮሮ (ሕሊናውን ትራማታይዝ እያደረገው) ድቅን እያለ ሲረብሸው ያለመረዳቱና ነጥብ ለማስቆጠር እንደሆነ መተርጎሙ ይገርማል።

እንደውም እንደታዘብኩት ከሆነ ተስፋዬ ተጎሳቁሏል። የሳይኪያትሪስት ሐኪም በማያት “ከቱራማው” ለመራቅ እንዲረዳው ሕክምና ማድርግ አለበት የሚል ሃሳብ አለኝ። ሞገስ ይህንን እረዳዋለሁ ብሎ ቢልም  “ልቅሶህ የአድማጭ ሐዘኔታ ፍለጋ ነው” በሚል “ቀፋፊ” ቃል መጠቀሙ አግባብ አይደለ።

ክርክራቸው እየተጋጋለ ሲሄድ ጋዜጠኛ ተስፋየ “አራጆቹ እያለ ሲናገር” ሞገስ << እኔ ሰው ለመታረዱ አላውቅም! እኔ አራጆች ብየ አልጠራቸውም፡ ያውም ማን እያረደ እንደሆነ በማናውቅበት ሁኔታ አራጆች የሚለው የአማርኛ ቋንቋ ባንጠቀም ጥሩ ነው>>  (ሞገስ ተሾመ)

ጋዜጠኛ ተስፋየ ደግሞ “አራጆች ካላልናቸው ምን ብለን እንጥራቸው? ስም ስጣቸውና እንሰማው፡ ብሎ ሲጠይቀው ከመጎስ መልስ ሲያጣ <<አራጆችን “ሐኪሞች” እንበላቸው?>> ሲል ተስፋየ በድጋሚ መጎስን ቅርቃር ውስጥ አስገባው። 

ውይይቱ “አማራ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበታል” በሚለው ላይ ደግሞ “ጋዜጠኛ ተስፈየ ተሰማ እና የሕግ ባለሞያው ሞገስ ተሾመ” የሕልውና አደጋ መኖሩን ሁለቱም ቢስማሙም የሕልውና አደጋው ላይ ዝርዝር ሲገቡ ሞገስ ልዩነት አሳየ፤ እንዲህ ይላል በጥቅሉ

“ አዎ አማራ አደጋ ላይ ነው። ግን የሕልውና አደጋ አለው ስንል አጥቂዎቹ አማራን በሙሉ በያለበት እየሄዱ ያጠፉታል ማለት አይደለም። ያ ከሆነ አማራው ብቻው ሳይሆን የሚጠፋው “ምቹዋል መጠፋፋት” የጋራ መጠፋፋት ነው የሚሆነው፤ አንድ የተወሰነ ቦታ ብቻ ሊያጠቁት /ሊያጠፉት/ ይችሉ ይሆናል እንጂ ከምድረገጽ ሊጠፋ አይችልም..” ሲል

ጋዜጠኛ ተስፋዬ ደግሞ ወለጋም፤ አርሲም፤ ደብረዘይትም፤ ባሌም፤ ሐረርም……ወዘተ እየለ ይቀጥልና “አራጆቹ አቅም ካገኙ” አማራ አለበት በሚባልበት ምድር ሁሉ በመሄድ ያጠፉታል። “ሂትለር” እቅም ባከማቸ ወቅት እስከ አውስትርያ፤ ሆላንድ ፤ መላው ኣውሮጳ ወዘተ… ተሻግሮ “ይሁዲዎችን” ጭፍጭፏል። አማርም አራጆቹ አቅም ሲያገኙ ከምድረገጽ ከማጥፋት አይመለሱም። ስለዚህ የሕልውና አደጋው ከፍተኛ ነው።>> ስል መልስ ሰጠ።

መጎስ ደግሞ አማራውን ሲጨፈጨፍት መነሸውን ካላወቅን እና ካልነገሩን መላውን አማራ ያጠፋታል ማለት አንችልም። ይላል መጎስ። ተስፋዬ ደግሞ ምክንያታቸውን ለማወቅ ከነገሩኝ ምክንያት ሌላ ቁፋሮ ውስጥ አልገባም ፤ ምክንያታቸው “አማራ ነህ” ብለው ስለገደሉኝ “አማራ በመሆኔ ብቻ ስለገደሉኝ” ምክንያታቸው “ኣማራ በመሆኔ ነው”። ከዚህ ሌላ ምን ምክንያት እጠብቃለሁ።ይላል ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ።

በማከታል፤ አሁን ያለው መከላከያ የአገር መከላከያ ነው ወይስ የአንድ ነገድ መገልገያ ነው? የሚል ክርክር ገቡ። ሞገስ ደግሞ እንዲህ ይላል አጣቃላይ ማጠንጠኛው ንግግሩ << ፖለቲካው መካለከያውን ስላበላሸው እንጂ የኢትዮጵያ መከላከያ ነው።>> ሲል ጋዜጠኛ ተስፋዬ ደግሞ’ በቅሉ ሲገለጽ <<በኦሮሞ ጀኔራሎች እና አገር መሪዎች የሚታዘዝ ኦሮሙማ ለተባለው ሃይል አገልጋይ ነው እንጂ አገራዊ አይደለም። በተለይ ኦሮሞ ልዩ ሃይሉ አገር መከላከያው አገራዊ ቢሆን ኖሮ አማራን ባገኘው ዕደል ሁሉ በድሮን እና አይሮፕላን እየጨፈጨፈ፤ አራጆችን ብረት እያቀበለ እየተባበረ አይቶ አንዳላየ ከጸረ አማራዎች ጋር የቆመ እና በቀርቡም “የወንድ ብልት የቆረጠ”፤ ትግሬን የጨፈጨፈ አማራዎችን እየጨፈጨፈ ያለ የኦሮሙማ እንጂ ኢትዮጵያ መከላከያ ነው ማለት አልችልም። ሲል ተስፋዬ መጎስን ሞግቶታል።

ከዚህ በማያያዝ የ16 አመት ወጣት የሆነ ጎጃም ውስጥ መከላከያው ብልቱን ስለ ቆረጠው ወጣት ወላጅ እናቱ እንደተናገሩ አድመጠናል (ፋይሉን ሴቭ ባላደርገውም በጀሮየ ሲናገሩ ሰምቻለሁ)። ይህንን ተስፋየ በመናገሩ መጎስ ማስከተል <<፡“መከላከያ ብልት መቁረጡን ማስረጃ የለም”>> ሲል ሞገስ መልስ ሰጥቷል።

በሚገርም ሁኔታ ሞገስ <<“ማስረጃ የለም” ማለቱ ሳይበቃ “መከላከያ ብልት ይቆርጣል” ማለት አንድን ሕብረተሰብ ብልት ቆራጭ ነው ብሎ የማለት ያክል ነው። መጠንቀቅ  አለብን።>> ሲል ሲመጻደቅ ሰማን። ብልት መቁረጥ ባሕል እንደነበረና እስካሁን ድረስም ብልታቸው እየተቆረጡ እንዳሉና ከዚያም አልፎ አማራዎች አየታረዱ ደማቸው እየተጠጣ ስጋቸው እየተላ ዜናዎች እንደተዘገቡ አልሰማም ማለት ነው? ኦሮሞ ክልል ፕረዚዳንቱ “ሺመለስ አብዲሳ” እንኳ መስክራል፤”ሸኔ ዮሞተን የወንድ ሬሳ የሚፍር ግብረ ሰዶማዊ ነው፤ የሰው ስጋ ይበላል” ሲል ተረናግሯል። ይህ ተደጋጋሞ እየተከሰተ ያለ ከስተት ካሁን በፊትም በኦሮሞ ማሕበረሰብ ባሕል ውስጥ ‘ብልት ቆረጣ’ የሚያኮራና ተቀባይነት “እንደነበረው” ሞገስ ተሾመ ዘው ማሕበረሰብ እንደማይታወቅ ለምን ሊክደን ፈለገ?  

ጉምዝ ውስጥ “ሙርሌ” የተባሉት ነገዶች “ቀይ” ብለው የሚጠርዋቸው (አማራዎችን) እያረዱ እንደሚበሉና ባሕላቸው እንደሆነ እናውቃለን፡ አደለም እንዴ?

ያ እንዳይበቃው ሞገስ ተሾመ የሚከተሉት ነጥቦች ይዞ ሲከራከር ነበር፡

1)    አምሓራን እየጨፈጨፈ ያለው ተጠያቂ ቡድን ማን መሆኑን እስካሁን ድረስ አይታወቅም” ሲል ሰምቼው ገረመኝ።

አምሐራን በፕሮግራም ነድፎ ስም አውጥቶውለት ጭፍጨፋ ሲያካሂዱ የነበሩት የፖለቲካ ቡድደኖች አንተ ባታውቃቸውም “አዎ!” እኛ እናውቃቸዋለን።

አራጅ አለ፤ ታራጅ አለ። ከሳሽ አለ፤ተከሳሽ አለ። “ከሳሽ” የአምሐራ ሕዝብ ሲሆን ተከሳሽ ደግሞ የሚከተሉት ናቸው።

1)“በነ ሌንጮ እና ዳውድ እንዲሁም ጃል ማሮ እና አብይ አሕመድ እያገዙት የሚመሩት የረዢም ዕድሜ ያስቆጠረ የኦነግ ቡድን” ፤

(2) “የህወሓት መሪዎች”

(3) አርቲፊሻል ወያኔዎች “የኦፒዲኦ መሪዎች”

(4) ዛሬ ሥልጣን ላይ ያለው “ስሙን የቀየረው የአኖሌው የጥላቻ ሃውልት መሰረተ ድንጋይ አኗሪ “አብይ አሕመድ” የሚመራው የድሮው ኦፒዲኦ የዛሬው “ብልጽግና መንግሥት”

(5) ደቡብ ክልል ሲመራው የነበረው “የሺፈራው ሽጉጤ” ቡድንና ፖሊሶቹ።

(6)”ኽዋረጅ” የተባለ የጅማ ኦርቶዶክስ ቀሳወስትና ምዕመናን ሲያርድ የበረው እስላማዊ አክራሪ ሃይል፤

ከአንድ እስከ ስድስት ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ቡድኖችና ፓርቲዎች እንዲሁም ግለሰቦች ለአማራ ዘር ማጥፋት፤መፈናቀል፤ድህነት፤ ለበረንዳ አዳሪነት እና አማራዎች ለመታረዳቸው  “ቀንደኛ ተጠያቂዎች” እነዚህ ናቸው።

በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በስም የታወቁ (ሰለባዎች የሚጠቅሳቸው) የመንግሥት ወታደሮች (ፖሊሶችና ልዩ ሃይሎች)፤ ከንቲባዎች፤ ሚኒሰትሮች የፓርላማ አባሎች፤ የክልል መሪዎች እና ግለሰቦች ሲካተቱ፤ አብረውም በውጭ አገሮች የሚኖሩ ከአምሐራ እና ከክርስትያን ኦርቶዶከክስ ቤተ ጸሎት እንዲሁም የአምሓራዎች እስላም መስጊዶች እንዳትጋቡና እንዳትጸልዩ፤ እንዳትገበያዩ በማለት ከዘር አጽጂው ቡድን ጋር የተቀናጁ፤በስም የሚታወቁ የዜና ማዕከሎች ግለሰቦችና የፖለቲካ ተዋናዮች የተጠያቂዎች ናቸው። እያልን ሞገስን በእርግጠኛነት እሞግተዋለሁ።

እነዚህ በራሳቸው ፕሮግራምም ሆነ በሕዝባዊ ይፋ ቅስቀሳ አምሐራን ለማጥፋት ፕሮግራም ነድፈው አምሓራን ልዩ የመለያ ኮድ ስም ሰጥተው እየጨፈጨፉ (ሞገስ “ሸሽጉት” እያለን ያለው የጭፍጨፋ ቃል ልጠቀምና <<እያረዱ>>) ያሉ ቡድኖችና ግለሰቦች አይታወቁም ማለት “ፌዝ” ነው።

ለመሆኑ በአምሐራ ላይ የዘር ማጽዳት የመጀመሪያ ተሞክሮ የት እና  መቸ ነበር?

 ብዙ ሰዎች ሐረርጌ ውስጥ ነው ሲሉ እሰማለሁ። አይደለም። አምሓራን በጅምላ መጨፍጨፍ የተጀመረው “አሶሳ”(በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ የምትገኝ ከተማ) ውስጥ ነው።በፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር በጃኒዋሪ 1990 (1982 በራሳችን ዘመን) መኮነን በተባለ የኤርትራ ሕዝባዊ ግምባር (ሻዕቢያ) የኮማንዶ መሪ በሚመራቸው ተዋጊዎችና ጥቂት የሱዳን መኮንኖች እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት (ኦነግ) ግምባር በመቀናጀት ከሱዳን ዘልቀው ወደ አሶሳ በመግባት። የአማርኛ ተናጋሪዎችን ከከተማዋ ለማጽዳት በሚል ዝግጅት አምሐራዎችን ጨፈጨፉዋቸው።

ጭፍጨፋው የተካሄደው ሁለት ቦታ ላይ ነው። ታሪኩ እንደዚህ ነው። ጎጃም ሰፈር እየተባለ ሲጠራ የነበሩት ኗሪዎች ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ ተብለው በተጋበዙበት አዳራሽ እንደገቡ መዝጊያው የሊት እንዲቆለፍባቸው ተደርጎ “ነዳጅ ተርክፍክፎ” ስፍር ቁጥር የሌላቸው አምሓራዎች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተደርጓል። ሻዕቢያም ስለ ጥምር ዘመቻው በራዲዮኑ ተናገሮታል። የትግርኛ ዜናውም አለኝ።

ኪዚህ ባሻገር ኮለኔል መንግሥቱ ይለማርያም ስለ አሶሳው ጭፍጨፋ በወቅቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በቴ/ቪ የሚከተለውን ንግግር አድርገው ነበር፡ (የድምጽ ቅጁ እኔ ጋር ይገኛል)

ልጥቀስ፦

<<የተከፈተብንን ጦርነት እንዳለ ሆኖ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያን አንድነት ጸር የሆኑት ቡድኖች ከጎረቤት አገር አስታክክው በመግባት ከፍተኛ የውግያ ድጋፍ ተሰጥቶአቸው፤ በምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል በተለይ አሶሳ ላይ አያሌ ንጹሃን ዜጎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል።የሕዝብ የልማት አውታሮች የሆኑ የሐገር ንብረቶች ተዘርፈው ወደ ጎረቤት ሃገር ተወስደዋል።የተቀሩትም እንዲወድሙ፤ እንዲፈርሱና እንዲቃጠሉ ተደርገዋል። ከሁሉም፤ ከሁሉም የሚያሳዝነው ደግሞ ብዛታቸው ወደ 200 የሚሆኑ ሕሙማን ሳይቀሩ “የእገሌ ማሕበረሰብ አባላት ናቸው” በሚል ብቻ ተለይተው “ቤት ተዘግቶባቸው” በጥይት ተቆልተዋል ፤ በእሳት ጋይተዋል። በወቅቱም ተጨማሪ ጥቃት ላለመድረስ ሲባል ተገቢውን እርምጃ ተወስዷል። ይህንና በሌሎች ግምባሮች የከፈቱብንን ጦርነቶች በመቋቋም ላይ እያለን ‘ሻዕቢያ” ነኝ ባዩ ፤ ያለው የሌለው ሃይሉን በማሰባሰብ ፤ የሰሜኑን አገራችን ጎሮሮ የሆነው በምፅዋ በኩል በማስሰለፍ ሌላ የጥቃት በር ከፈብናል፡….>> (መንግሥቱ ይለማርያም)

ስለዚህም አማራን በማረድ ዝንተ ዕለት ሥራቸው ያደረጉ “አራጆች” በመጎስ ካላወቃቸው ማንነታቸውን መለየት አንችላልን፡ እናውቀዋቸዋለን።

እንዲህ ዓይነቱ እልቂት 1983 ወያኔ መንግሥትነቱን ከተቆጣጠረ በኋላም የጅምላ ጭፍፋው የተለመደ ሆነ። ወዲያውኑ የኢትዮጵያን ካርታ ቀይሮ ወደ 14 ብሔሮች፤ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በሚል 14 የውስጥ ድምበር ያላቸው “ጥቃቅን አገሮችን” መሠረተ። በቋንቋ "የተከለሉ በነዚህ ድንበሮች" ውስጥ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ  አማራዎች ላይ በተጠቀሱት ቡድኖች መዋከብ ተጀመረ። ከዚያም በሺዎች የሚቆጠሩ አማርኛ ተናጋሪ እና ክርስቲያኖች ጅምላዊ መበራርና ጭፍጨፋ የዘወትር ትዕይንት ሆነ።

 አድራጊዎችም በወያኔ አይዞህ ባይነት ያው ከአሶሳ ዕልቂት ጀምሮ ሲሳተፉ የነበሩት በእነ “ሌንጮ ለታ እና ዶ/ር ዲማ ነገዎ” የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር መሪዎችና አባሎችና ደጋፊዎቻቸው ናቸው። ሰዎቹ ያኔ በዘመነ ወያኔ ጭፍጨፋ ሲፈጽሙ “ተቀምጠውበት በነበሩበት ፓርላማ” ዛሬም በሚገርም ክስተት ተመልሰው በዘመነ “አብይ አሕመድ ፓርላማ” አዳራሹን ተቆጣጥረውት የጭፍጨፋ ወንጀላቸውን እያካሄዱ ናቸው። እነ ገዱ አንዳርጋቸው፤ እነ ክርስትያን ታደለ እነ ዶ/ር ጫኔ እነ ቧ ያለው ወዘተ ንግግር ሲያደርጉ እየታፈኑና ሲያሾፉባቸው የምናያቸውና የምናደምጣቸው ያው የአራጁ ቡድን ተቧዳኝ አባልት ስለሆኑ እንኳን እኛ የፓርላማው አባል “ኦነጉ” ዶ/ር አንጋሳ ኢብራሂም” እንኳ ሳይሸማቀቅ <<እኔ ነገ ብሞት ይህችን ምስጢር ይዤ እንዳልሞት’ ሳልናገር ብሞት ስለሚቆጨን አራጁ ቡድን ምንግሥት እንደሆነና ሽመልስ አብዲሳም ግምባር ቀደም አሳራጅ እንደሆነ  ነግሮናል። (ሻሸመኔ ከተማ አማራ እየተለየ ንብረቱ ሲቃጠል የከተማው ከንቲባ ለሺመልስ አብዲሳ ሥልክ ደውሎ ዕርዳታ ሲጠይቅ <<አያገባህም አርፈህ ተኛ>> እንዳለው መጎስ ተሾመ አልሰማሁም ሊል ነው?   አራጆችና ተባባሪዎቻቸው እነማን መሆናቸው ብግልጽ ይታወቃሉ።

አብይ አሕመድም እኮ ልክ እንደ ሞገስ ተሾመ “ሽብርተኞቹ እነማን መሆናቸውን በእርግጣኛነት እገሌ ነው ብሎ ለመለየት ያስቸግራል” ብሏል። አብይ እንዲያ ሲል “እራሱ አብይ አሕመድ በምስጢር አሸባሪዎችን በልዩ ሃይሎቹ በኩል መሣርያ እያቀበለ በገንዘብም እንዲንበሻበሹበት 25 ባንኮችን በዓለም ታሪክ ተደርጎ የማያውቅ ፤ በአንድ ወር ውስጥ እንዲዘረፉ በማድረግ፤ በግብረ ሽበራው ሥራ እየተካፈለ መሆኑን  ስለሚያውቅ እኔ መሆኔን አለወቃችሁኝም”>> ለማለት ነው፡ ‘አራጆቹ አይታወቁም’ ሲል የነገረን እንጂ ፤ ሰለባዎቹ ግን አራጆቻቻው እነማን መሆናቸው በየቃለ መጠይቃቸው ብግልጽ ነግረውናል። ሰለባዎቹ የሚሉት እኛን ያረደንና ያፈናቀለን ንብረታችንን የዘረፈን “መከላከያው፤ ልዩ ሃይሉ፤ኦነግ ሸኔው እና አገሬው” ነው ሲሉ በቃለ መጠይቅ ነግረውናል።

ከባሌ ከአባገዳዎች፤የሃይማኖት መሪዎች፤ከቄሮዎችና ከአገር ሽማግሌዎች የተላለፈው የሞት አዋጅ ታስታውሳላችሁ?

የአቋም መግለጫ የተባለ በገበያ የተነበበ “ነፍጠኛ እና ዶርዜ” ብለው በሚጠርዋቸው ዜጎች ላይ የታወጀው የጭፍጨፋና ንብረትን የመዝረፍ፤ወፍጮ እንዳያስፈጩ የሚያግድ የግድያ አዋጅ በቪዲዮ የተደገፈ፤ ምስላቸው የሚታይ ገበያ ላይ ወጥተው ሕዝብ ሰብስበው አዋጁን ሲያነብቡት እነማን እንዳወጁት “የሕግ አዋቂው” ሞገስ ባያውቀውም እኛ እናውቃቸዋለን። ይህ የባሌ የጭፍጨፋ አዋጅ የታወጀበትም ምክንያት ለዘነጋችሁ ሰዎች ላስታውሳችሁ

ጥቂት ልጥቀስ

እንዲህ ይላል፡

<<ዛሬ ይህን ሰልፍና አዋጅ ያወጣነው ጅግናችን የቄሮ አባት የሆነው አቶ ጃዋር መሐመድ ላይ በጠላት የመገደል ሙከራ ስለተደረገበት ደምፅ ሆነን ነው። ጃዋርን የሚቃወም መቸም ቢሆን የባሌ ሕዝብ ጠላት ነው።>>

የሚል ነበር የሞት አዋጁ የመነሻው ምክንያተቸው። ጃዋር በእርሱ ምክንያት ለታረደ ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቅና ሓዘን ይሰማው እንደሆነ ሲጠየቅ” “እልጠይቅም” ነው ያለው። ስለዚህ እነ ማን መሆናቸውና በምን ምክንያት አማራውን እንደሚያርዱት መጎስ ባያውቅም “ነፍጠኛ” እያሉ የሚጠርዋቸው አማራዎችና “ዶርዜ” ብለው የሚጠርዋቸው ጋሞዎችም አራጆቻቸውና ለመታረዳቸውም ምክንያት “አማራ እና ጋሞዎች በመሆናቸው ብቻ” እንደታረዱ ያውቃሉ። ሌላ የሕግ ፍልስፍና መራቀቅ ውስጥ መግባት አያስፈልግም።

ኦሮሚያ ተብሎ ያልነበረ ካርታ ተቀይሶ አማራዎች ሲዋከቡ ወያኔ ከላይ ሆኖ አምስቱ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች OLF, Islamic Oromiya Liberation Front (ILFO), Oromo People's Unity Organization (OPUO), Oromo Abo Liberation00 Movement.

የዘር ማጽዳት እና ጥቃት በመፈጸም የቀን ተቀን ሥራቸው እንደነበርና ዛሬም እየቀጠለ መሆኑን አራጆች በመሪዎቻቸው ስምና  በድርጅታቸው መለያ ስም እነማን እንደሆኑ እናውቃቸዋለን።

ከላይ የተጠቀሱት ድርጅቶችና መሪዎች በፕሮግራማቸው ኢትዮጵያ “የአምሐራና የኦርቶዶክስ ስሪት” ነች ብለው ስለሚያምኑ፤ “አምሓራን ማጥፋት” የሚል ንድፍ ነድፈው አምሐራን ቅኝ ገዚኛና “ነፍጠኛ” የሚል “ኮድ” መለያ በመስጠት በሐሰት ተንቀሰቅሰዋል። ስለዚህ ሓላፊነት የሚወስዱ በስምና በድርጅታቸው የሚታወቁ ስለሆኑ ወንጀለኞችን እንደመደበቅ ተደርጎ እንዳይታይ ታሪክን ግራ ላለማጋባት ጥንቃቄ እናድርግ።

ጌታቸው ረዳ