Sunday, May 30, 2021

ከፍል 2 የትግራይ ተዋጊ ሃይሎች የእርስ በርስ የመታኮስ አይቀሬ እጣ ፈንታ ትንበያ ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ (Ethio Semay) 5/30/2021

 

ከፍል 2

የትግራይ ተዋጊ ሃይሎች የእርስ በርስ የመታኮስ አይቀሬ እጣ ፈንታ ትንበያ

ጌታቸው ረዳ

ኢትዮ ሰማይ (Ethio Semay)

5/30/2021



ይህ ሓተታ ባለፈው ጽሑፌ ማለትም በ5/29/21 ከጻፍኩት ክፍል 1 የቀጠለ ክፍል 2 ነው። እንደሚታወቀው የዛሬው “ህ.ወ.ሓ.ት” ተዋጊ ድርጅት ድሮ በየካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም ደደቢት ተብሎ በሚታወቀው በምዕራባዊ ትግራይ ውስጥ የሚገኘው በረሃማ ሥፍራ “ተ.ሓ.ህ.ት.” (ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ) በሚል ሥያሜ ተሰይሞ ወደ በረሃ መውጣቱን በታሪክ የተዘገበ ነው። ለማታውቁ ወጣቶች መስራቾቹን ለማሳወቅ ያክል ባጭሩ ልጥቀስ። በየካቲት 11 ቀን ወደ ጫካ የወጡት ሰዎች ስም ዝርዝር፤

በቅንፍ የተዘገበው ስም የበረሃ መጠሪያ ስማቸው ነው።

(1)-ኣረጋዊ በርሀ (በሪሁ በርሀ)

(2-ገሰሰው አየለ ድሮ በቀዳማዊ ሃይረለስላሴ ዘመን የፓርላማ አባል የነበሩ- የበረሃ ስም (ስሑል ኣየለ)

(3) ሙሉጌታ ሓጎስ (ኣስፈሃ ሓጎስ)

(4) አረፋይነ ካሕሳይ (ፀሓየ ካሕሳይ)

 (5)-ፋንታሁን ዘርኣፅዮን (ግደይ ዘርኣፅዮን)

 (6)-ንጉስ ታየ (ቀለበት ታየ)

 (7)-ኣምባየ መስፍን (ስዩም መስፍን)

(8)-ዘርኡ ገሰሰ (ኣጋአዚ ገሰሰ)

 ከነዚህ ሌሎች ተማሪዎች ያልሆኑ መንገድና ስንቅ ለማገዝ ይረዳሉ ተብለው የታሰቡ አብረው የተሰለፉት የሚከተሉት አንድ ትግሬ እና ሁለት አማራ ገበሬዎች/ነጋዴዎች አብረው ወደ ጫካው በመሄድ የመሰረቱ ። እነሱም

(9)-ወ/ሚካል ገ/ስላሴ (አስገደ ገብረስላሴ ትግሬ ትውልድ ቦታ ሽሬ- ሥራ እስራል የሰለጠ ወታደራዊ ኮማንዶ ጦርሰራዊት)

(10)-ኣምባየ ወ/ጊዮርጊስ (ዘውግ “አማራ”

(11)- ኣብተው ታከለ (ዘውግ -ዛሬማ በሚባል አካባቢ የተወለደ “አማራ”)

 

እነዚህ 11 ሰዎች ናቸው።

 

እነዚህ 11 ሰዎች ወደ ጫካ ደደቢት ሲሄዱ ታጥቀዋቸው የሄዱት መሳሪያዎችና ባለቤቶቹ፡

የግደይ ዘርኣጽዮን ወላጅ አባት ጠመንጃ የነበረ “ጓንዴ” ጠመንጃ። የገሰሰው አየለ “ካርባይን; ቶምሰን እና ፍሎቨር ሽጉጥ”። የአስገደ ገብረስላሴ “አልቤን ጠመንጃ እና “ብጻይ (ጓድ) “ደሳለኝ” ተብሎ በወያኔዎች የተሰየመ ወደል “ስናር አህያ”። እነኚህ መሳሪያዎች ታጥቀው ትግሉን ጀምረው በትግራዋይነት አክራሪ ብሔረተኛነት ስሜት ወጠቱንና ገበሬዎን በማነሳሳት በሺዎቹ ታጋዮችን በማስሰለፍ መድፎች፤ዘመናዊ መሳሪያዎች፤አየር መቃወሚያ “ዙ” በመታጠቅ የመንግሥት ሥልጣንነትን መቆጣጠር ችለው ነበር።

 

ለ27 አመት ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘር አንድ ያልሆነ፤ እርስ በርስ የማይተዋወቅ የነበረውን ሕዝብ እንዲተዋወቅ አደረግነው” በማለት የውሸት ትርክት በማናፈስ፤አገራችንን በቋንቋ በሃይማኖትና በወገንተኝነት ሸርሽረው “ትግሬዎች ሥልጣኑን በበላይነት እንዲመሩት አዋቅረው” የትግሬ የበላይነት በማንገሥ፤ የትግሬዎች መንግሥት መስርተው ነበር።

 

የወያኔ ባለሥልጣናት በነደፉት “ዘረኛ - ፖሊሲ” ዕልቂትና ጥላቻን አስፍነው ኢትዮጵያ ውስጥ “በደም የተነከረ አስተዳዳር” ከመሰረቱ በሗላ፤ ቀናቸው ደርሶ ከሥልጣን ተባርረው ዛሬ ከ29 አመት በሗላ እንደገና “ወደ ነበሩበት” የትግራይ ጫካ በመሸሽ ደቡባዊ እና መካካለኛ ትግራይ አካባቢ ብቻ ተደብቀው ከመንግሥት ጦር ጋር በመዋጋት ላይ ናቸው።

 

ተዋጊ ሰራዊታቸው በነዚህ አካባቢ ሊንቀሳቀስ የወሰኑበት ምክንያት ፡ ሽሬ እና አክሱም ገጠር አካባቢዎች ለኤርትራ ድምበር ቅርብ ስለሆነ በሁለቱም በኩል (በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተዋጊ ወታደሮች) እንዳይከበቡ ስጋት ስላለባቸው እዛው ራያ እና እንደርታ አካባቢ ተደብቀው መንቀሳቀሱን መርጠዋል (ለጊዜው)። በተልይ የእንደርታ እና ራያ ሕዝብና ወጣት ከትጥቁ ዘመን ጀምሮ በተለይም መንግሥት ከሆኑ ወዲህ በነዚህ ሁለት አውራጃዎች (በከፊል ተምቤን) ውስጥ ከፍተኛ የብሔረተኛ ትምህርት እንዲሰርጽ በማድረግ፤ መንግሥታዊ መቀመጫውም “መቀሌ” በማድረግ በስልት  ፤ በዘፈን እና በትምህርት ቤት እና በገበሬ ማሕበራት፤ በህጻናት ሕሊና ውስጥ ሳይቀር “የትግሬ ሃያልነት” እና “የትግራይ ጥንታዊ አገርነት የውሸት ትርክት” በመቀስቀስ የኢትዮጵያዊነት ጥላቻ በሰፊው እንዲካሄድ በማድረጋቸው እነኚህ አካባቢዎች የሚናገሩዋቸው የትግርኛ ልሳኖች ሳይቀር ወደ “ኤርትርኛ እና ዓድዋ አክሱምኛ ልሳን” በመናገር በሚገርም ሁኔታ ከሌሎቹ አውራጃዎች የበለጠ ብሔተረተኛ እና ጠባብ እንዲሆን ስላደረጉት ለዚህ አዲስ ትግላቸው መከታ እንደሚሆናቸው ስላወቁ ወታደራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊም ሆነ የስለላ እንቅስቃሴአቸው በነዚህ አካባቢ አውራጃዎች በማድረግ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ።

 

ወደ ትንታኔአችን ከመግባታችን በፊት ግን ለጊዜው እያደረጉት ያለው አንቅስቃሴ እንመልከት። (“ክርቢት”) (ፈዳያን) ሲባሉ የነበሩ እንደ ዱሮው ዓይነት “በቅርቡ የኮማንዶ ሥልጠና የወሰዱ አልሞ ተኳሽ ወጣት ወታደሮችን” ተወርዋሪ ነብሰገዳይ እና አፋኝ ቡድን እንዲሆን በማዘጋጀት ፤ ከአጋሜ (ዓዲግራት) በጥንት ዘመን አጠራር “ትግራይ” ሲባል ወደ ነበረው “አክሱም ዓድዋ እና ሽሬ” የሚያገናኘው አውራ መንገድ ላይ በሚጓዙ መኪኖች ላይ አደጋ በመጣል የትራንስፖርት/የመጓጓዣ/ ችግር እንዲኖር እና ህዝቡ በመንግሥት እንዲያምጽ ሙከራ እያደረጉ ነው። የኔ ዘመዶች ለስራ ወደ መቀሌ ተጉዘው፤ተመልሰው ወደ አክሱም ሊሄዱ ፈልገው መንገዱ ከተዘጋባቸው እጅግ ቆይቷል።  

 

የትግራይ ተዋጊ ሃይል ተብሎ በማቆላመጥ የሚጠራው የወያኔ “ሽብርተኛው” እና “አገር አፍራሽ ቡድን” ዋና ዓላማ የትግራይ ህይት “ክሪፕል” አድርጎ  የውጭ አገር ጣልቃ ገቦች እንዲገቡ ለማድረግ ነው። በሚገርም ሁኔታ፤ ምግብና መድሃኒት  ስለሌላቸው ፤ የገጠሬው ሕዝብ ኑሮ በችግር ላይ ስላለ፤ ለችግረኞች የሚጓጓዝ  የዕርዳታ እህል “በመዝረፍ” ለተዋጊ አባሎቻቸው” ቀለብ” እንዲያገኙ በማድረግ ላይም ናቸው።  

አብሮ ከዚህ ጋር እያካሄዱት ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ፤ በተጨማሪ አዳዲሶቹ የከተማ ከንቲባዎች እና ወረዳ አስተዳዳሪዎች፤ እንዲሁም ወያኔን የሚቃወሙ ግለሰቦች በከተማ ውስጥ በድብቅ ከሚገናኙዋቸው የሰለጠኑ “ገዳዮች” እና ከበረሃ በሚላኩ “ፈዳያን” (ነብሰገዳዮች) ወደ ከተማ እና ገጠር አስገብተው ተፈላጊዎቻቸውን በመግደል ህዝቡ ሳይወድ በፈርሃት አዲሱን አስተዳዳር እንዳይደግፍ በማድረግ ድሮ ወያኔ ሲጠቀምበት የነበረው የግድያ ባሕሪው በስፋት በማካሄድ ላይ ይገኛል። በዚህም ብዙ ሰዎች ከሥልጣናቸው በፍርሃት እየተውት ይገኛሉ።

 

ወያኔዎች ለምን እንደገና ወደ ጫካ ወጡ?

 

መልሱ ከስብሓት ነጋ እናገኘዋለን። “ሥልጣናችንን ከተቀማን፤ የኢትዮጵያ አንድነት የሚባል አይኖርም፤ ሁላችንም ወደ እየመንደራችን እንበታተናለን ወይንም ወደ ሁለተኛ ዙር ጦርነት እንገባለን” (ስብሓት ነጋ ፡ - አባ መላ ከተባለ ውጭ አገር የሚኖር ድሮ የወያኔ አለቅላቂ የነበረ “ኢትዮ-ሲቪሊቲ ሩም” (ፓልቶክ ሩም) ያደረገለት ቃለመጠይቅ የተናገረውን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። በዚህ መርህ ነበር ወያኔዎች ወደ ጫካ ሊወጡ የቻሉት እና ስብሓት ነጋም ቃሉን ባለማጠፍ ወደ ጫካ በመውረድ ተማርኮ ዛሬ ቃሊቲ ውስጥ ይገኛል።

 

የወያኔ ተዋጊዎች አሁን የሚገኙበት ቁመና

የወያኔ መሪዎች ወደ ጫካ ሊመለሱ የወሰኑበት ምክንያት ከላይ የተገለጸው ምክንያት ግልጽ ከሆነ፤ ወደ ሥልጣን ሲወጡ፤ ኢትዮጵያን እንደ አገራቸው ሳይሆን የተመለከትዋት “የምትታለብ ጥገት ላም” በማድረግ ትግራይን በልማት አሳድገው ድንገት ሥልጣናቸው ቢነጠቁ “የትግራይ አገርነት” ለመመስረት አቅደው እንደገቡም ልብ ማለት አስፈላጊ ነው። ይህንን እውን ለማድረግ የ27 አመት ሥልጣናቸውን ሽፋን አድርገው ትግራይ “ራስዋን የቻለች አገር በማስመሰል” ከውጭ  አገሮች፤ አምባሳደሮችና የሳይንስ፤ የጥበብ፤ እርሻ፤ የንግድ ኩባኒያ ባለቤቶችና ጠበብቶች ጋር በመገናኘት ልዩ ጠቀሜታዎችን በማስገኘት ትግራይ “የአፍሪካ የኢንዳስትሪያል ቀጠና” በማድረግ “አንድ አገር” ያገር የሚያሰኘውን “”ልዕለ ቅርጽ እና ታህታይ ቅርጽ” (ሱፕራ እና ኢንፍራ ስትራክቸር) በመገንባት ዝግጅት አድርገው ነበር።

 

ይህንን እውን ለማድረግ በተጨማሪ ትግራይ ስትገነጠል በተማረ እና በገንዘብ ሃይል ትግራይን ለመግንባት እንዲያመች በሺዎች ምናልባትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትግሬዎች ወደ መላው  ዓለም በሚገኙ የበለጸጉ አገሮች “በማሸጋጋር” በስደተኛ  ስም “ቪዛ” ተጠቅመው በቁጥጥራቸው ሥር በነበሩት ኤምባሲዎቻቸው በኩል እንዲወጡ በማድረግ የዲሎማሲ እና በገንዘብ ገልበት ትግራይንም ሆነ አሁን ያሉት ተዋጊዎችን እንዲያግዙ አቅደው ስለነበር፤ በዕቅዳቸው መሰረት ‘ይኼው ዛሬ’ ትግሬዎቹ ‘ውጭ አገር ሆነው’ ለግንጠላው እና ለተዋጊው ሃይል በዲፕለማሲ፤በአማራ ሕዝብ እና ንግድ ቤቶች እንዲሁም በኢትየጵያ ባህል እና ታሪክ ላይ ጥላሸት እና ጥላቻ ከማሰራጨት፤ አልፈው በገንዘብ፤ በልብስ፤በቀለብ፤በመድሃኒትና ለሴት ተዋጊዎቻቸው የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመላክ በታቀደው ዓላማ ተሰማርተው “ለመጻኢት ትግራይ” በማገዝ ላይ ይገኛሉ።

የተዋጊው ዓይነት

አሁን የሚገኙበት ቁመና ከመጀመሪ የፊት ለፊት ውግያ ኩፉኛ ስለተጠቁ፤ ከዚያ ፍጥጫ አፈግፍገው ወደ ሽምጥ ተዋጊ ስልት ገብተው እራሳቸውን ለማዳንም ሆነ አልፎ አልፎም በመንግሥት የተሾሙትን ግለሰቦች በመግደል ተሰማርተው ይገኛሉ። በአካልም ሆነ በሕሊና ያልጎለመሱ አዳዲስ “ተዋጊ ህጻናት” (ልብ በሉ ህጻናት ነው እያልክ ያለሁት) በስሜትም ይሁን አስገድደው ወደ ጫካ እንዲገቡ በማድረግ ክረምቱን ለክፉ ህይወት እየዳረግዋቸው ይገኛል።

 

በሚሰራጩ ቪዲዮዎች የሚታዩት ብዙዎቹ ተዋጊዎች የድሮ ተዋጊዎች፤ የኪነት ሰዎች፤ መምህራን፤ ተማሪዎች፤ የመንግሥት ሰራተኞች እና የወያኔ መንግሥት ወታደሮች/ፖሊሶች/ልዩ ሃይሎች ሲሆኑ፤ እንደ ድሮ የገበሬ ተዋጊ ሃይል እስካሁን ድረስ አልተቀላቀልዋቸውም።  ከከተማ ተጫምተዋቸው የሄዱበትን “ሰንደል” ነጠላ ጫማ፤ አፈር ያልነካቸው “ጂንስ ሱሪዎች” እና የጸዱ የከተማ ጃኬቶች ለብሰው “በስሜት ማነሳሻ” ሙዚቃ እየተቀሰቀሱ ባንዳንድ ክፍት በሆኑ በረሃዎችና ገጠሮች ውስጥ “ዳንኪራ” ሲጨፍሩ ይታያሉ። የታጠቁም ያልታጠቁ ሰዎችም ሲጓዙም ሲጨፍሩም አብረው ይታያሉ።

 

 ቀለባቸው ምን ይሆን? ለምትሉ ጠያቂዎች እነሆ “ነፃ ትግራይ” ከሚባለው ፓርቲ መሪ የሆነው “መሓሪ ዮሓንስ” ከተባለው እኔ “መሓሪ ዱቼ” በሚል ቅጽል ስም የምጠራው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረ፤ ዛሬ በተዋጊው ስምሪት ውስጥ “ክፍሊ ህዝቢ” (ፓብሊክ ሪሌሽን- የሕዝብ ግንኙነት) በመባል የሚጠራው ክፍል ተመድቦ በመንቀሳቀስ ላይ ያለ ይህ ወጣት ባለፈው ሰሞን “አክሱማዊት ሚዲያ” ከተባለ የዩቱብ ሚዲያ ባደረገው ቃለ መጠይቅ “ተዋጊዎቹ ምን  ዓይነት ምግብ እና ማን እንደ ሚቀርብላቸው ተጠይቆ ሲመልስ፡ እንዲህ ይላል።

“አንዳንድ ልብሶች በግል ከቤተሰቦቻችን ይላኩልናል። ይህ ወደ ድርጅቱ ቢላክ ጥሩ ነበር፡ እኔ በግሌ አልደግፈውም። ሆኖም በቤተሰብ በኩል የሚላኩልን ምግቦችም ሆነ ልብሶች፤ጫማዎች አለፍ አለፍ ብለው ይኖራል። የምንመገበው ከተገኘች ያው ገበሬው ቁራሽ እንጀራ ከራሱ ቆርሶ ይሰጠናል፤ እርስዋን መመገብ ነው።ያቺን ካልተገኘች ደግሞ “ቆሎ” ቆልተን መብላት ነው። ከሚሰጠን የየግል የዴቄት ራሽን ተጠቅምን ብዙ ጊዜ “ቂጣ” በመጋገር እንመገባለን። እንደ ተዋጊነታችን መሰረት በየተራ ምግብ በማብሰል “ተረኛ መጋቢ” ሆነን ተራ ሲደርሰን በተመደብንበት ተዋጊ ጋንት/ ሃይል/ ያንን ሓላፊነት ወስደን ሰራዊቱን እንመግባለን።

 

ጠያቂው እንዲህ ሲል መሓሪን ኩፍኛ በማሾፍ “ያስሳቀው” ጥያቄ ይጠይቀዋል፡ እንዲህ ሲል

 “የሚጠጣ ውሃ ስትጠጡ ውሃውን አፍልታችሁ ነው? ወይስ እንዴት ነው የምትጠጡት?’

መሓሪ በጥያቄው ተገርሞ ጥልቅ የማሾፍ ሳቅ ይስቅበትና እንዲህ ሲል ይመልሳል፦

 

 “አፍልተን አንጠጣም ያገኘነውን ውሃ ነን የምንጠጣው። መጀመሪያ ወደ ጫካ ስወጣ በውሃ አለመስማማት የተነሳ እጅግ ከፍተኛ የጤና መታወክ ገጥሞች ከሞት ነው የተረፍኩት። አሁን ግን “ጃርዲያው፤አሜባው፤ የሆድ ህዋሳት ትሎች ሁሉም ለምደናቸዋል፤ እነሱም ለምደውናል። አይጎዱንም። ለምጀዋለሁ።

 

 “የምትትኙትስ የት ነው?”

አሁንም መሓሪ በጥያቄው ተገርሞ ይስቃል፡

“አይሮፕላን ስለምንፈራ ብዙውን ጊዜ ሌሊት ነው የምንቀሳቀሰው፤ ቀን በጣም ውሱን እንቅስቃሴ ነው። ረዢም ጉዞ የምንጓዘው ሌት ነው። በጋ ሲሆን በጣም ከምንወደው ሞቃታ በሆነው በገበሬዎች ጓሮ ውስጥ ባለው “ገለባ -ሳር” ነው የምንተኛው። ዛሬ ግን ክርምት ስለሆነ ዝናብ ሲዘንብ ደጅ መተኛት ስለማይቻል በየገበሬው ጎጆ ተጠልለን ነው የምንተኛው።

 

 “ሓራ መሬት *ነፃ መሬት አላችሁ)?

 

“ እስካሁን ድረስ ናጻ መሬት አልያዝንም። ተንቀሳቃሽ ሃይሎች ነን። አንዳንድ ጊዜ እናንተ የምታስተላልፍዋቸው ዜናዎች ጥንቃቄ (አከሮሲ) የጎደላቸው ሆነው ስለምታዛባቸው፤ እውነታው ጋር በሚሄድ ማስተላለፍ ይኖርባችሗል ብየ ወንድማዊ ትችት ለማስተላለፍ እፈልጋለሁ (ቅር ካላላችሁ) ። በማለት በውጭ አገር ባሉት የወያኔ ሚዲያዎች በሚነዙት መረን የለቀቀ ፕሮፓጋንዳ/ዜና/ ያልተደሰተበት እንደሆነ ስለ ሁኔታው ወጋ በማድረግ አሳስቦአቸዋል።   

 

አራቱ የፖለቲካ ድርጅቶች በረሃ ውስጥ ባንድነት የመታጨቁ የሗላ ሰበብ

 

የትግራይ ሕዝብ በተዋጊዎች ላይ ያለው ስሜት፤

የትግራይ እጣ ፈንታ፤

የታጋዮቹ ዕጣ ፈንታ፤    (አሁን በረሃ ላይ የወጡት 4ቱ ፓርቲዎች “ኦለድ ጋርድስ” ከሚባሉት  “ትግራይ ትግንጠል ብለው የሚያቀነቅኑት የውጭ ተላላኪ ባንዳዎች ናቸው” (ስብሓት ነጋ ከአንድ አመት በፊት ‘ከአውራ አምባ’ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ) ከሚሉት ጋር የወደፊት ግጭት መነሻ እንደሚሆን በዝርዝር እንመከታለን።

የኤርትራ ዕጣ ፍንታ’    በዝርዝር እንመለከታለን።

 

 ባጭሩ ስለ ኤርትራ በሰፊው የምንመለከተው ቢሆንም ለጊዜው ይህን የመነጋገሪያ ጥቅስ የውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነትም ሆነ የወያኔ ተዋጊዎች የትግራይ ትግርኚ ዓለማ ከ ኢሳያስ መወገድ/ሞት/ በሗላ ተዋጊዎቹ ‘ከኤርትራ’ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት እንድትወያዩበት ይህንን መነጋገሪያ ሰብሓት ነጋ ከ6 አመት በፊት የተናገረውን ንግግሩን ልስጣችሁና በሚቀጥለው ክፍል 3 እንገናኝ።

“ስብሃት ነጋ እንዲህ ብሎ ነበር፦

 

 “የኤርትራ ሕዝብ ጤናማ ከሆነ ምስራቅ አፍሪካን ይለውጣል፤ይህ ሕዝብ ወደ ቀውስ ከገባ ግን እንደ ሶማሌ እና ደቡብ ሱዳን አካባቢ ሕዝብ አይደለም፡ አካባቢውን ያናውጣል። ድንገት ኢሳያስ ከሄደ በቀጥታ ኤርትራ ወደ ቀውስ ትገባለች። የኤርትራ መንግሥት ይወድቃል፡ በአገሪቱ ቀውስ ይፈጠራል። በርካታ የውጭ ሃይሎች እጃቸውን የሚያስገቡበት አደገኛ ቀውስ ስለሚኖር፤ ኢትዮጵያ ይህንን በጥናት በማረጋገጥ በኢሳያስ ወቅት እና ድሕረ ኢሳያስ ወቅት አደገኛ ችግር እንዳይፈጠር………” (ስብሓት ነጋ ሰኔ 3/2007 ለፓረቲው ካደረገው ንግግር ካገኘሁት ሰነድ)   

ክፍል 3 ይቀጥላል። (ተቀባበሉት- ሼር አድርጉት ፤ ሌላውን አስተምሩበት) አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ - ኢትዮ ሰማይ (Ethio Semay)

 

Saturday, May 29, 2021

የደደቡ ፕረዚዳንት ማዕቀብ፤ ተቃዋሚዎች እና እንዲሁም የትግራይ ተዋጊ ሃይሎች የእርስ በርስ የመታኮስ አይቀሬ እጣ ፈንታ ትንበያ ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ (Ethio Semay) 5/29/2021

 

የደደቡ ፕረዚዳንት ማዕቀብ፤ ተቃዋሚዎች እና እንዲሁም የትግራይ ተዋጊ ሃይሎች የእርስ በርስ የመታኮስ አይቀሬ እጣ ፈንታ ትንበያ

ጌታቸው ረዳ

ኢትዮ ሰማይ (Ethio Semay)

5/29/2021



የሚታው ፎቶግራፍ የወያኔ ኮማንዶ አሰልጣኝ ሲሆን ከጀርባው የሚነበበው ጽሑፍ

 “በሰማይ ማርያም ጽዮን፡

በክልል ደብረጽዮን” ይላል።

 

ተከታታዮቼ እንደምን ሰነበታችሁ? ለትንሽ ወቅት ጠፍቼ ነበር፤ ሰላም እንደቆያችሁኝ ተስፋ አለኝ። በፌስቡክ መሰንጀር በኩል ሰላም ለማለት የጻፋችሁልኝ ወገኖች መልስ ባለመስጠቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

ለዛሬ የምትወያዩባቸው ሦስት ርዕሶችን ይዤ መጥቻለሁ።

1ኛ) የደደቡ ፕረዚዳንት ማዕቀብ

2ኛ) የትግራይ ወያኔ መንግሥት ለመጣል ሲታገሉ የነበሩ ተቃዋሚዎች

3ኛ) ወያኔ ከተወገደ በሗላ ኦሮሙማውን ሥርዓት ለመጣል እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች

4ኛ) በረሃ የወጣው የትግራይ መከላከያ ሃይል ተብሎ የሚጠራው የግንጣላ ዘመቻ ተዋጊው ሃይል እርስ በርስ የመታኮስና የመለያየት ትንቢታዊ እውነታ እንመለከታለን።

 

በመጀመሪያው በደደቡ ፕረዚዳንት ማዕቀብ፤ ልጀምር።

 

ድረገጾችን ስጎበኝ ዜናው ሁሉ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ስለመጣል ጉዳይ በሰፊው ተዘግቧል። የአሜሪካ ማዕቀብ የመጣል ፍላጎት ስለ ሰው ህይወትና ሰላም አሳስቧት ሳይሆን አምጣ የወለደቻቸው ልጆቿ ወያኔዎች ጥጋብ አላስችል በሏቸው ባመጡት ባሕሪ ከሥልጣን በመወገዳቸው ኩፍኛ አዝና ተቆጥታለች። ስለሆነም ልጆችዋን ወደ ነበሩበት ለማስቀመጥና ከሌላኛው ቅጥረኛ ልጃቸው ለማስታረቅ በየትኛውም አገሮች የምትጠቀምበትን ማዕቀብ የተባለው ብዙ ሕይወት በረሃብና በምጣኔ ሃብት የምታሳልቅበት ስልትዋን ለመጠቀም ወስናለች።

 

አሜሪካ በታሪኳ ልክ እንደ ጀርመን ናዚ “ኣዲሱ የዓለም ስርዓት” ተብሎ የሚታወቀው አገሮችን የመዋጥና የመቆጣጠር በልዕለ ሃያልነት አባዜዋ የምትታወቅ የብዙ ሺዎች የዓርብ እና የቬትናም ሕዝቦች በመርዝና እሳት የሚተፉ አውሮፕላኖችን አሰማርታ በመጨፍጨፍ የታወቀች ወንጀለኛ አገር ነች። ለዚህ ወንጀልዋ የሚቀጣትም ሆነ ማዕቀብ የሚጥልባት አገርም ሆነ ፍርድቤት እስከዛሬ አልተገኝም። በታሪኳ አንድ ጊዜ የሳወዲ አረቢያ መንግሥት በፍልስጢየም ጉዳይ የነዳጅ ማዕቀብ አድርጋባት ምጣኔ ሃብትዋ ተቃውሶ የምትይዘው የምትጨብጠው አጥታ ነበር። በዚህ ጉዳይም ዓለም በሙሉ በነዳጅ እጦት ተናግቶ እንደነበር ይታወሳል። ከዚያ ወዲህ ጨክኖ ይህችን ወንጀለኛ አገር ማዕቀብ የጣለባት አገር ከቶ የለም።

 

አሜሪካን በማዕብ መቅጣትና ማንበርከክ የሚቻል ዕድል የሚኖሮው አፍሪቃኖች ባንድ ድምጽ አሜሪካን ላይ ማዕቀብ ቢጥሉ ትቀዝን ነበር (ለቃላቴ ይቀርታ) ። ሆኖም እርሷን የሚያገለግሉ ጀሌዎች ስላልዋት አይሞከርም። ሙሉን ተውት እና የምስራቅ ቀንድ አፍሪካ አገሮች ብቻ ማዕቀብ ቢጥሉ ሱሪዋን ትፈታ ነበር። ሆኖም በተለይ ጁቡቲ የመሰለች “የመላ አፍሪካን አገሮች የምታስደፍር” ክብረ-ቢስ ወራዳ አገር ይዞ አሜሪካ ላይ ማዕቀብ ማድረግ አይቻልም።

 

የ27 (21?) የሶቭየት ሪፑብሊክ እስቴቶች ከፈረሱ ወዲህ አሜሪካ ከአውሮጳዎች ጋር በመናበብ የልብ ልብ አግኝታ እነ ሀርመን ኮሀንን የመሰሉ አደገኛ አይሁድ አሜሪካኖችን በመክ ‘በወያኔ ቅጥረኞችዋ’ ተባባሪነት “በእጅ አዙር” ስልት በመጠቀም ኢትዮጵያ የአሜሪካና የእንግሊዝ የቅኝ አዙር ግዛት ሆና ቆይታለች። ይህ ቁጥጥር ዛሬም በፋሺስቱ ኦሮሙማ መሪው አብይ አሕመድም ጊዜ በትግራይ ውስጥ ጦርነት እስከተከተጀመረበት በፊት የተለወጠ ነገር አልነበረም። ዛሬ ምን ተገኘና ነው ማዕቀብ ለመጣል የወሰነቺው ለሚለው መልሱ ከላይ የጠቀስኩት ነው።

 

የአሜሪካ ባለሥልጣኖች መቸውንም ቢሆን ኢትዮጵያን በበጎ መልክ ተመልከተዋት አያውቁም። ብዙ ሰዎች የ100 አመት ወዳጅነት አለን ወዘተ እያሉ ሲያወሩ እመለከታለሁ። ሃቁ ግን ያ አይደለም።የአሜሪካ ቱባ ቱባ ባለሥልጣኖች ኢትዮጵያን እንዴት ይመለከትዋት እንደነበር ከነ ኒክሰን እና ከነ ሄንሪ ክሲንጀር ብንጀምር ስዕሉ ግልጽ ነው።

 

 ዛሬ በዘውግ የተከፋፈለችው ኢትዮጵያ በጣሊያን ፋሺሰቶች የተጀመረው ፖሊሲ አሜሪካ እንዴት እውን እንዳደረገቺው በቀርብ ገዝቼ ባነበብኩት ኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት የፕሮፌሰር “ትዮዶር ቬስታል” “The Lion of Judah in the New World” (Author Theodore M Vestal) በጻፉት መጽሐፋቸው እንዲህ ይላሉ።

“The decline in the fortune of the Horn nations might have been foreseen by Henry Kissinger, who in 1972 as head of the National Security Council, known under his direction as the “committee in charge of running the world.” Wrote a confidential report on the future of Ethiopia. He purportedly recommended that U.S. policy should be to keep that nation in perennial internal conflict, using such vulnerabilities as ethnic, religious, and other divisions to destabilize the country. Kissinger’s recommendation appears to have been followed success fully, for not only Ethiopia but the Horn of Africa have been in turmoil ever since.” (The Lion of Judah in the New World - Author Theodore M Vestal page 188)

በተቀራራቢነት ስተረጉመው እንዲህ ይላል፡

“የምስራቅ አፍሪቃ ቀንድ አገሮች ሀብት ‘የማሽቆልቆል ምክንያት’ ሄንሪ ኪሲንጀር በ 1972 በአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ም/ቤት ሓላፊ ሆነው በመሪነቱ ስር “ዓለምን በበላይነት የሚያስተዳድር ኮሚሽነር” በመባል የሚታወቀው ሓለፊነት ሲመራ በነበረበት ወቅት እንደሆነ ሲገመት ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ ሚስጥራዊ ዘገባ በጻፈው ሰነድ ውስጥ እንዲህ ይላል፡፡

“አገሪቱን ለማተራመስ እንደ ጎሳ ፣ ሃይማኖታዊ እና ሌሎች ክፍፍሎች ያሉ ተጋላጭነቶችን በመጠቀም ሕዝብዋ በየዓመታቱ ውስጣዊ ግጭት ውስጥ እንድትቆይ ማድረግ የአሜሪካ ፖሊሲ መሆን አለበት፡፡” በማለት ኪሲንጀር የሰነዘረው ምክር ተሳክቶለት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በመሆኑ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከዚያ ዘመን ጀምሮ የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች የብጥብጥ ቀጣና ሆኗል። (የይሁዳ አንበሳ በአዲሱ ዓለም - ደራሲ ቴዎዶር ኤም ቬስቴል ገጽ 188) ሲሉ ሰነዱን ይፋ አድረገውታል።

 

ስለሆነም ዛሬ “ደደቡና ሕሊና ቢሱ ፕረዚዳንት ባይደን” የግብጹ ሑስኒ ሙባረክ ከሥልጣን ለማውረድ ታሕሪር እስኩየር በሕዝብ ድምጽ ሲቀወጥ ባይደን “ሙባረክ አምባ ገነን አይደለም” ሲል በጆሮየ ሰምቼው ከዘያ ቀን ጀምሮ የባይደን ጭንቅላት ያወቅኩበት አጋጣሚ አንዱ ነበር።  ደደቡ ፕረዚዳንት ስለ ትግራይም ሆነ ጠቅላላ ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊና ፖለቲካዊ እውቀት የለውም። ደደቡ ፕረዚዳንት የመለስ ዜናዊ ወዳጅ በነበረቺው በ“ሱዛን ራይስ” እና በመሳሰሉ ጸረ አፍሪካ ግለሰቦች የሚዘወር እንደሆነ ግልጽ ነው”።

 

ደደቡ ፕረዚዳንት ኢትዮጵያን አስመልክቶ በማያገባው ገብቶ ከዘላበዳቸው “ከሦስቱ ነጥቦቹ ” ውስጥ አንዱ “የአማራ ሃይል ከትግራይ ይውጣ” የሚለው ነው።፡ይህ አባባል ምን ማለት እንደሆነ ከጣሊያን ጀምሮ ጥርስ ውስጥ የገባው ከዚያም በሻዕቢያ ከዚያም በወያኔ ከዚያም በኦሮሙማ ከዚያም ዛሬ በአሜሪካ ዒላማ ውስጥ የመግባቱ ምስጢር ከላይ የጠቀስኩትን የኪሲንጀር ፖሊሲ ህያው ቀጣይነቱን አማላካች ነው።

 

ደደቡ ፕረዚዳንት እና አማካሪዎቹ የጂኦ ፖለቲካ ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት ምን ያህል ስኬታማ ናቸው የሚለው ለወደፊቱ የሚታይ ሲሆን፤ “ህጻንነቱን ያልጨረሰው” አብይ አሕመድ “በአገር ፍቅር የተቃጠለው የዙምባቤው ሮበርት ሙጋቤ” ስላልሆነ ሥልጣኑን ለመቆጣጠር ሲል ውሎ አድሮ ሸብረክ ማለቱ የማይቀር ነው።

 

 ማዕቀቡ ከፍተኛ የሰብአዊ ሰበቦች ቢያመጣም ለድሃው ማዕቀቡ ተደረገ አልተረደረገ አንዴ የፈራረሰ አገር (ፈይልድ ስቴት) ስለሆነ ውጤቱ ከድጡ ወደ ማጡ እንጂ ከምቾት ወደ ርሃብ አይሆንም።

 

የጊዜ ጉዳይ ቢሆንም ማዕቀቡ በአሜሪካ የባይደን ፖሊሲ አውጭዎችና አስፈጻሚዎች ላይ ከፍተኛ ዕዳንም ጭምር ያስከትልባቸዋል። ይህ ማለት በርካታው ኢትዮጵያዊ ባይደንን እና ኮንግረሶችን በመቃወም በምርጫ ወቅት የሚያስከፍላቸው ዕዳ ይኖራል። መዘንጋት የሌለበት ግን ደደቡ ፕረዚዳንት ሱዳኖችና ግብፆች ኢትዮጵያን እንዲወሩ ከገፋፋ “ጥቁር አሜሪካኖች” በባይደን አስተዳዳር ኩፍኛ ተቃውሞ ማስነሳታቸው አይቀርም። ያም ሆነ ይህ ማዕቀቡ ይሰራል አይሰራም ቆይተን የምናየው ይሆናል።

 

2ኛ) የትግራይ ወያኔ መንግሥት ለመጣል ሲታገሉ የነበሩ ተቃዋሚዎች!!

 

ፅሑፌን ስትከታሉ የነበራችሁ ወገኖቼ እንደምታስታውሱት በወቅቱ ወያኔን ለመጣል ስንታገል ብዙዎቹ ተቃዋሚዎች የትግል ስልታቸውም ሆነ የሚታገሉለት ራዕይ ፈጽሞ የተበላሸ ስለነበር፤ በሕብ ዘንድ አቃፊነት አግኝተው የነበሩ የሚዲያ ባለቤቶችም ሆኑ የፖለቲካ መሪዎች እያደሩ ከአክራሪ እስላም ፖለቲካ አራማጅ ፖለቲከኞች ፤ ከገንጣይ ቡድኖች እና ከፀረ አማራ ሃይሎች ጋር እየተገናኙ “በእፍ እፍ ፍቅር” አብደው “ስለ ኢትዮጵያ የቆሙ ሃይሎች ናቸው፤ እንግዲህ ግንጠላ ትተዋል” ወዘተ … እያሉ፤ “ተው” አይሆንም ስንላቸው ለነበርን ሰዎች ክፉኛ እየሰደቡና እያንኳሰሱን የትግሉን ዓላማ እንዲኮላሽ በማድረግ ሕዝቡን በሁለት ጎራ ከፍለው በማበጣበጥና በማደባደብ (አሁንም ሰበቡ አለ) ገንጣዮችና አክራሪ ሃይሎች ጉዞው ክፍት ሆኖላቸው “በመጨረሻ ወያኔ ከተወገደ በሗላ” ደብቀውት የነበረውን ቆዳቸው በግሃድ ወጥቶ ዛሬ ኢትዮጵያ ምን እያደረጓት እንደሆነ የምታውቁት ጉዳይ ነው።

 

በወቅቱ ይህንን እውነታ ስለታየኝ ወያኔ ከተወገደ በሗላ ጸባችን ያኔ ተቃወሚ ነን ከሚሉት ጋር ነው ብየ እንደነበረው ሁሉ ዛሬ እውን ሆኖ እነ ብርሃኑ ነጋ ፤ “አቃጣሪው” አንዳለም አራጌ እና እልፍ ተቃዋሚ ነን ባዮች አማራን በመዝለፍና ምን ታመጡ ብሎ አማራውን “መጤ” በማለት የኢንተርሃሙዌውን ቡድን ፕሮፐጋንዲሰት ሆኖው “የዱርውን መንግሥት” መሳሪያ ሆነው፤ እነሆ ዛሬ ልክ እንደተነበይኩት በተቃራኒ ቆመው ከኢትዮጵያዊው ሃይል እና ከአማራ ታጋይ ሃይሎች በሚዲያ ይጠዛጠዛሉ።

 

3) ወያኔ ከተወገደ በሗላ ኦሮሙማውን ሥርዓት ለመጣል እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች!!

 

ዛሬ የምር የሚናገሩ ጥቂቶች የሆኑም ሆኑ መስመራቸው ግልጽ ያላደረጉ አገር ውስጥም ሆኑ ውጭ አገር ብዙዎቹ ተቃወሚዎች በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚናገሩት ንግግር ስታደምጡ “ወያኔንም ጭምር ወደ ምርጫ አስገብቶ ወደ ፖለቲካው ዓለም በማስገባት ሰላም ማምጣት የሚሉ አሉ”። ይህም በዕርቅና በምናምን የሚል ስልታቸው ነው። ይህ መስመር ደግሞ የወያኔና የኦነግ ፖለቲካዊ ባሕሪ (ተፈጥሮ) ካለመረዳት የመነጨ እንዝህላልነት ነው።

ኦነጉን ወደ ጎን እንተውና አሜሪካ እየጨሁለት ያለውን ሱዳኖችና ግብፆች እያንቋለጡለት የሚኘውን በሽሽት ላይ ያለው የወያኔ ተዋጊ ሃይል እና መሪዎች ዓላማ ምን ነው? የሚለውን መመለስ አለብን። ዓላማቸው ዛሬ ሳይሆን ገና ጫካ እያሉ ግልጽ አድረገውልናል። እኛ ትግሬዎች ኢትዮጵያን ዝነተ ዓለም ካልገዛናት “አፍርሰናት” ትግራይ ሪፑብሊክ አንመሰርታን ብለው በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ በራድዮ በቴ/ቪዥን በጽሑፍ ግልጽ አድረገዋል። ተቃዋሚው ግን ከወያኔ ጋር ፍቅር ይዞት ሙጭጭ ብሎ “በዕርቅ” ይመለሰል እያሉ አንጀቴ እስኪያመኝ ድረስ ያስቁኛል።

ወያኔ ሁለት አማራጮች ነግሮናል። (1) ወያኔ ያዋቀረው በዘር የተለያየን ነን በማለት በቋንቋና በዘር ያዋቀረው “አፓርታይዳዊው” አስተዳዳር ቀጥሎ ትግራይ በወያኔዎች እንድትዳዳር እና አማራ ከርስቱ ከመሬቱ ተነቅሎ ወጥቶ በወራሪው ወያኔ  በኩል መሬቱን ለትግሬዎች እንዲያስረክብ ። ይህ ካልሆነ “መገንጠል”! (2) ያ ክልሆነ ግን ኤርትራ “ሃገረ ኤርትራ እንደተባለቺው’ ትግራይም “ሃገረ ትግራይ” ተብላ ጠላታችን ከሆነቺው ኢትዮጵያ መለየት”! የሚል ነው።

ይህ የማታገያ መስመራቸው ተቃዋሚዎች “የወያኔ ፋሺስታዊ ባሕሪ” ማወቅ አቅቷቸው “በሰላም በድርድር ዕርቅ” ምናምን የሚሰራ እየመሰላቸው በሕልመ አለም ሲቃዡ በየሚዲያው አደምጣለሁ። ይህ የወያኔ አቋማቸው የማይለወጥ ነው። ወያኔ ፋሺስት ነው።ፋሺስቶች በድርድር አያምኑም። በድርድር የሚያምን ቢሆን ኖሮ አብይ አሕመድ ወያኔዎች የዘረፉትን ንብረት በያዛችሁት ይጽደቅላችሁ ብሎ እነ ስዩምን በውጭ ጉዳይ ምኒሰትርንት እነ ..እነ በረከትን ወዘተ….. ሲለምናቸው “አፍንጫህን” ብለውት ነው ይህ ሁሉ ጦርነትና እልቂት ያመጡት። ከሪያ ኢብራሂምን አታዩም?! ከምን ወደ ምን ተለውጣ ከምቾት ወደ ቃሊቲ ትገባ አንዴት እንደመረጠች። ደቡብ ሱዳን የነበሩት የተባበሩት የሰላም አስከባሪ ሃሎች የነበሩት ትግሬዎች ወዴት አንደተቀላቀሉ እናስታውሳለን አደል?

የነገድ ፖለቲካ እጅግ አደኛ የፋሺስቶች ልዩ ባሕሪ የሆነ ድርድርን እንደ ሽንፈት ስለሚያየው ውይት ዕርቅ እይቀበልም። ስዚህ እነዚህ የዛሬ ቃዋሚዎችም ነገ ፋሺሰቱ አብይ ሲወገድ ወያኔን ወደ ዕር አምጥው ኦነግንም ወደ ዕርቅ አምጥተው የቤንሻንጉል የሰው በሊታው ታጣቂም ወደ ዕርቅ አምጥተው “ወንጀላቸውን በይቅርታ ተወስኖ፤ “የቋንቋና የነገድ ፖለቲካ አስተዳደር በከፊልም ቢሆን መቀበላቸው አይቀሬ ነው። በተለይ አብይ አሀመድ በዚህ ላይ ልዩ ተጫዋች ስለሚሆ ወንጀለኞች ዓለማቸውን ያያሉ። በዚህ አገሪቱ አዙሪቷ ይቀጥላል””


 4ኛ) በረሃ የወጣው የትግራይ መከላከያ ሃይል ተብሎ የሚጠራው የግንጣላ ዘመቻ ተዋጊው ሃይል የእርስ በርስ የመታኮስና የመለያየት ትንቢታዊ እውነታ በሚቀጥለው ክፍል በሰፊው እንመለከታለን።……..ተቀባበሉት (ሼር አድርጉት) ……………..ይቀጥላል

 

Thursday, May 20, 2021

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ(ም) አነጋጋሪ ሆነ አሉ አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) Ethiopian Semay 5/20/2021

 

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ(ም) አነጋጋሪ ሆነ አሉ

አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

Ethiopian Semay

5/20/2021

Mercenaries shaking hands vowing to destroy Ethiopia

የዚህች ሀገር ፖለቲካ ከማርጀት አልፎ እየጃጀ መምጣቱን የምንረዳው በየቀኑ ሊባል በሚችል ሁኔታ በጣም አስቂኝና አነጋጋሪ የሆኑ ክስተቶችን በመታዘባችን ነው፡፡ ፖለቲካን ከከተማ እስከጫካ ከልጅነት እስከሽምግልና ሲያራውጠው የነበረው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በዕረፍት ከሚገኝበት ሥፍራ ሆኖ ሰሞኑን በአሜሪካ ላይ በወሰደው አደገኛ ስጉምቲ ማለትም እርምጃ አሜሪካ እየተንቀጠቀጠችና ዲያስፖራውም ሰውዬውን በማግባባት አደገኛ እርምጃውን ቀለል እንዲያደርግ በማባበል ላይ እንደሚገኝ በኢትዮ360 አንድ ዝግጅት ዛሬ ምሽት ሰማሁ፡፡ ጀግና ማለት እንዲህ ነው! አሜሪካን በዓለም ላይ እንደልቧ የምትፈነጨው እንደ አቶ አንዳርግ ያለ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢንተርናሲዮናል ወደር የለሽ ጀግና በመጥፋቱ ነው፡፡ ይህን አንግሎ-ኢትዮጵያዊ ወይም ኢትዮ-እንግሊዛዊ ቼኩቬራና ሆቺሚን በዚህ ወቅት ማግኘት ለግንቦት ሰባትም፣ለኢዜማም፣ለብልጥግናም ….እ … ለአርበኞች ግንቦት ሰባትም፣ ለኦነግም፣ ለኦህዲድ ሸኔም፣ ለብአዴንም ትልቅ የምሥራች ነው - ምሥር ያብላንና፡፡ ግን ግን እውነቱን ለመናገር ካበዱ አይቀር እንዲህ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ገና ከዚህ የባሰ ለጥገና የሚያስቸግር የአእምሮ ብልሽትም ያሳየናል፡፡ “ካላበዱ ወይ ካልነገዱ (የልብ አይገኝም)” መባሉም እኮ ለዚህ ነው፡፡

 

አሞራና ጭልፊት መጥተው ጫጩቶቹን ሲልፏቸው በአጥር ሥር ተወትፎ ካሳለፈ በኋላ በሚስቱ በእመት እናት ዶሮ ፊት አንድ አውራ ዶሮ እንዲህ ብሎ ፎከረ አሉ - እንደመፎገ(ከ)ር የሚቀል የለምና፡፡

 

አምጪማ አምጪማ ጦሬን፤ ወንዙን ሳይሻገር እንድዠልጠው ወገቡን! ዘራፍ! ዘራፍ አካኪ ዘራፍ!

እመት እናት ዶሮም መለሰች፡-

አንቱም አንቱም አይዋሹ፤ አሁን ተመልሶ ቢመጣ አጥር ላጥር ሊሸሹ፡፡

 

የዛሬ ስንት ዓመት ገደማ ደግሞ (በ1978ዓ.ም ይመስለኛል) አሜሪካ ሊቢያን አጥቅታ ጋዳፊ ለጥቂት ከሞት ተረፈ፤ አንዲት ሴት ልጁ ግን በአየር ጥቃቱ ሞተችበት፡፡ ያኔ ታዲያ ኢትዮጵያም ፀረ አሜሪካ ስለነበረች (ወግ አይቀርምና ሲዳሩ ማልቀስ) ሚዲያዎቿ ሁሉ በአሜሪካ ላይ ተቃውሞ አዘነቡ፡፡

 

በዚያን ወቅት ከሰማሁት ዜና መቼም የማይረሳኝ የሚከተለው ነው፡-

 

“የአጋርፋ ገበሬዎች ማኅበር የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምን አስጠነቀቀ!”

 

የሚገርም ማስጠንቀቂያ ነበር፡፡ እርግጠኛ ነኝ - የአሜሪካ ጦር ያኔ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠንቀቅ ተሰልፎ የአጋርፋ ገበሬዎችን ወረራ ይጠባበቅ ነበር፡፡ ግና እግዜር ሰወራቸውና አሜሪካኖች ተረፉ፡፡ቀልድ ጥሩ ነው፡፡ ያለ ቀልድ ሕይወት ጎምዛዛ ናት፡፡

 

አቶ አንዳርጋቸው ግሥላ ሆኖ አሁን “አንድነቷ ተጠብቆ” ስለሚገኘው ሀገሩ ምን ነበር ያለው? “እኔ ክንዴን ሳልንተራስ አሜሪካ ኢትዮጵያን አታፈርስም፡፡ ባንዲራቸውን ዐይናቸው እያዬ አቃጥላለሁ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘሁትም ከዚያ በላይ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፡፡ ” ፐ! ፐ! ፐ! አይ ወኔ!! ወላድ በድባብ ትሂድ፡፡ እንኳን የኔው ሆነ አንዱካ! የኛ ባይሆን እንዴት በቆጨኝ፡፡

በል አንተ ደግሞ “ስልብ አሽከር በጌታው እንትን ይፎክራል” በልና ሳንወድ በግድ አስቀን፡፡

 

ጥቂት ጥያቄዎች አሉኝ፡፡

 

 አንደኛ ;-

 ነገር ባንዲራው ምን አጠፋ?

 

ሁለተኛ :-

 ነገር ባንዲራን ማቃጠል የሥልጡን ፖለቲካ አካል ነው ወይ?

 

 ሦስተኛ :-

 ነገር ዋናው አገር አፍራሽ መሀል:

 

 አራት :-

 ኪሎ ተቀምጦ የማይመስል ነገር ውስጥ መግባት የጣዱን ትቶ የዕንቅቡን እንደማማሰል አይቆጠርምን?

 

አምስተኛ :-

 የሰው ሀገር ባንዲራ ማቃጠል አማራን በነፃነት ትግል ስም ወደ ኤርትራ በረሃ ወስዶ በአውሬና በአማራ-ጠል ፖለቲከኞች ሤራ እንደማስጨረስ ቀላል ነው ወይ? አምስተኛ በሀገራቸው መኖር ያልቻሉ የዘር ፖለቲካ ሰለባዎችንና የኢኮኖሚ ስደተኞችን በክፉ ቀን ያጠጋችን ሀገር በዚህ መልክ ወሮታውን መክፈል ነውር ከመሆኑም ባሻገር በህጉ መሠረትና ከህግ ውጪም ለሚደርስ ቅጣትና የበቀል በትር ተጠያቂው ማን ሊሆን ነው?

 

የምን አትርሱኝ ነው? በቃ፤ ዒላማ ተስቶ ዓላማ ሲጨናገፍ አርፎ መቀመጥም እኮ ያባት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን ሁሉም ነገር ገብቶታል - በጎንደርኛና በኃይሌ ገ/ሥላሤኛ ልንገር፡፡ የዓዞ ዕንባን ከእውነተኛ ዕንባ የመለየት ችሎታውም በእጅጉ አድጓልኝ፡፡ ይህን ጥሬ ሃቅ አንዴክስ አልሰምቶ ከሆነ ችግሩ ከሌላ ሳይሆን ከራሱ ነው፡፡ ስለዚህ በኢትዮጵያ ስም ለትዝብት ከሚዳርግ ንግግርና የማስመሰል ሞቅታ መቆጠብ ይገባል፡፡ እንዳማሩ መሞት በዚህ ዘመን ሲያምር የሚቀር ቢሆንም አንዳንዴ አካባቢያዊና ሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ማጤን በቀላሉ ሊያስወግዱት ከሚቻል ሕዝባዊ ትዝብት ይታደጋልና ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥን መቀነስ ደግ ነው እላለሁ፡፡ እውነታን ማሽሞንሞን ለማንም አይጠቅምም፡፡ አንዳርጋቸውና በብዙ ውጣ ውረዶች አልፎ ኢዜማ ላይ የደረሰው የፖለቲካ ስብስብ ፈተናውን ዘጭ ብሎ ወድቋል፡፡ “ማንነትህን እንድነግርህ ጓደኛህን ንገረኝ” የሚባለው ምሣሌያዊ አባባል ትልቅ መልእክት አለው፡፡

 

 ሽንት ቤት ውስጥ የተቀመጠ ሰው የፈረንሣይ ሽቱ ቢቀባ ወይም የናርዶስ ሽቱ ሰውነቱ ላይ ቢያርከፈክፍ እውነተኛ መዓዛውን ለመለወጥ ይቸገራል፡፡ ከአሁን በኋላ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በማስመሰልና በጠላትህ ጠላቴ ነው የሲብስቴ ፈሊጥ የሚመራ አይሆንም፡፡ ይህን ሁሉ ስል ግን የአንዱን የቀደመ አስተዋፅዖ የማላወድስና የሰሞኑን ተቃውሞ መነሻ ምክንያት የማልቀበል ሆኜ አይደለም፡፡ ሰውዬው ለሀገሩ ብዙ ለፍቷል - በተሳሳተ አቅጣጫ ቢሆንምና ትግሉ በአሰለጦች ቢጠለፍም፡፡

 

“ኢትዮጵያን አትንኩ” ብሎ መጮህም ያስመሰግናል እንጂ አያስወቅስም - የአጯጯሁን መንገድ አለመለየት ለትዝብት ከመዳረጉ በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወዝና ጣም ከሌለው ትያትራዊ የብልጽግናዎች ቀልድ ወይም ኮሜዲ እንታቀብ - The moral of the story. አሃ፣ ያን ያል ትልቅ ስብዕና ያው ሰው እንደዚህና እስከዚህ መውረድ የለበትማ! “ሳይበላስ ቢቀር” አለ ቴዲ አፍሮ፡፡ “እኔ ቆሜ ዐቢይ ማነው አሜሪካ ኢትዮጵያን አታፈርስም!” ይባላል? ዋናው አፍራሽ ማን ሆነና? ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ፡፡ በልጅነቴ እንግሊዝኛን እያጣመምኩና የአማርኛ ፈሊጦችን በቀጥታ ወደ እንግሊዝኛ እየመለስኩ ጓደኞቼን አዝናና ነበር - አንደኛዋ ፈሊጥ አሁን ትዝ አለችኝ - “tell me sayer!” - ከገባችህ ወንድ ነህ! ሆድህን አሞህ ውሎ አሞህ ይደር እንጂ አልነግርህ፡፡ “ንገሩኝ ባይ”፡፡

Wednesday, May 19, 2021

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን የትብብር መድረክ Ethiopian Semay ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓም (19-05-2021)

 

 

                                 



ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለዬቅል

ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓም (19-05-2021)

Ethiopian Semay

በሥልጣን ላይ ያለው ጎሰኛ ቡድን ከያቅጣጫው ያይንህ ላፈር ዘመቻ ተከፍቶበት ጭንቅና ምጥ ውስጥ ይገኛል።መሪውን አብይ አህመድን የሰላም አባት ብለው ሾመው ሸልመው፣ ለሥልጣን ያበቁት ሳይቀሩ የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።ከዚያም ባለፈ አገራችንን ለመበታተን ካሴሩት የውስጥና የውጭ ሃይሎች ጎን በመሰለፍ የዓለም አቀፉን ሕግ ጥሰው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት የክተት ዘመቻ አውጀዋል።ይህ የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ኢትዮጵያ አገራችን ላይ ለሚሰነዘር ወታደራዊ ጥቃት መንደርደሪያ ቅድመ ጦርነት አድማ መሆኑንን ድርጅታችን ያምናል።

 

 ይህ የተቀናጀ የውጭ ሃይሎች አሰላለፍና የክተት አዋጅ ለሃያሰባትና ላለፉት ሦስት ዓመታት በጠቅላላው ለሰላሳ ዓመታት በሕዝቡ ጫንቃ ላይ ሰፍረው ሕዝቡን ቁም ስቃዩን ሲያሳዩት የነበሩትን ጸረ ሕዝብና ጸረ አንድነት የሆኑና በሥልጣን ሽኩቻ የተራራቁትን የአንድ ድርጅት የኢሕአዴግ ቤተሰቦች፣ ህውሃትንና ኦህዴድ/ኦነግን አቀራርቦና አስታርቆ የግፍ፣የዘረፋና የስቃይ ኑሮ እንዲቀጥል ከመሻት የመነጨ ተቃውሞ ነው። ይህ በአሜሪካ ግንባር ቀደምትነት፣በአውሮፓ አጃቢነትና በግብጽና በሱዳን ተላላኪነት የሚፈጸመው ኢትዮጵያን የማጥቃት ዘመቻ፣ለአገር አንድነት፣ለዴሞክራሲና ለስርነቀል ለውጥ የሚካሄደውን የኢትዮጵያውያን አገር ወዳዶች ትግል አብሮ ለመጨፍለቅ የታሰበ ተንኮል መሆኑን እናምናለን።በዋናነት ዒላማ ያደረጉትም በኢትዮጵያዊነቱ  የማይደራደረውን በተለይም የአማራውን ማህበረሰብ ነው።ከራሱ መኖሪያ መሬቱ ይልቀቅ የሚለው ጫጫታም የዚያ አካል ነው።የአገሩን አንድነትና ሰላም ለማስከበር የተሰማራውንም ጦር ሃይል ወንጀል የፈጸመ የውጭ ሃይል አድርገው ስለውታል።

 

እኛም በሥልጣን ላይ ያለውን ፣ለዚህ ችግር የዳረገንን ጎሰኛ ቡድንና ስርዓት አጥብቀን እንቃወማለን፤ከሚመራበት አገር አፍራሽ፣ሕዝብ አጫራሽ ከሆነው ሕገ ጥፋት” (ህገመንግሥት ልንለው አንችልም) ጋር ተወግዶ አገራችን በአንድነትና በሰላም የምትቀጥልበትን የፖለቲካ ጎዳና እንድትከተል እንሻለን።የአሜሪካና ጭፍሮቹ፣የህወሃት፣የግብጽና የሱዳን ምኞትና ሰልፍ የእኛ ሰልፍና ምኞት እንዲሁም ፍላጎት አይደለም።ለዚያም ነው የጽሁፋችንን ርዕስ “ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለዬቅል” ያልነው።

 

እኛ ለኢትዮጵያ አንድነትና ለሕዝቡ መብት ስንል እነሱ በተቃራኒው የቆሙ ናቸው።የሚፈልጉትን በተረኛው መንግሥት ካገኙ ለሕዝቡ ደንታ የላቸውም፤እንደቀድሞው እጅና ጓንት ሆነው ይቀጥላሉ።መንግሥት ተብዬውም አሁን ዳር ዳር ቢልም በቀጣዩ መንበርከኩና ታማኝነቱን በተግባር መግለጹ አይቀርም።

 

በሥልጣን ላይ ያለው ቡድን ግን ከግራም ሆነ ከቀኝ፣ከላይም ሆነ ከታች፣ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚሰነዘርበትን ተቃውሞ በአንድ ቅርጫት ላይ ጠቅጥቆ በእኩል ያወግዛል፣ይፈርጃል።ለዴሞክራሲ መብት፣ለአገር አንድነት የቆሙትን ሁሉ ጥላሸት እዬቀባ በቅርቡ ያሉትን እያሳደደ በእስር ቤቱ ያጉራል፣በሚስጥርም ይገላል።በውጭ አገር ያሉትንም በተላላኪዎቹ በኩል ለማስፈራራት ይሞክራል።ለእሱ አገር ማለት ቤተመንግሥቱ ነው።

 

እነዚህ የዴሞክራሲ ቁንጮና የሰብአዊ መብት አስከባሪ ነን ባዮች ምዕራባውያንያዛኝ ቅቤ አንጓችእንደሚባለው ለትግራይ ተወላጅ ያሰቡና የተጨነቁ በመምሰል የአዞ እምባ እዬረጩ ነው። ኢትዮጵያና ሕዝቧ ያለባትን ችግር ክደው ለጥቅማቸው ሲሉ በተባባሪነት ያገለገላቸው ህወሃት በሥልጣኑ ላይ ካልተመለሰ በማለት ያዙን ልቀቁን ይላሉ።ለነሱ ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት ማለት በፈለጉበት አገር ያሻቸውን ሲያደርጉ፣ሲዘርፉ አብሮ የሚዘርፍና የሚተባበራቸው ቡድን በሥልጣን ላይ እስከተቀመጠ ድረስ ነው።ከዚያ ሌላ አገር ወዳድ ያገሩ ባለቤት ከሚሆን፣ሕዝብ መብቱ ተከብሮ የባለጸጋ አገር ዜጋ ከሚሆን አገር ብትፈራርስ ይመርጣሉ።የነሱ ብልጽግና በሌላው አገር ክስረትና ድህነት ላይ የተመሰረተ ነው።ይህ በሌሎች አገሮች ያዬነው ሃቅ ነው።ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢሕአዴግ/ብልጽግና አረመኔዎች እጅ ሲገደል፣ደሙ ሲፈስ፣ሲፈናቀል ድምጻቸውን አላሰሙም፣የሕዝቡንም ጩኸትና አቤቱታ አላዳመጡም።አሁንም ቢሆን ከእውነት የራቀ የፈጠራ ትርክት እያራገቡ ይገኛሉ።ምን ጊዜም ቢሆን ሰልፋቸው ከአምባገነኖችና ከወራሪዎች ጋር እንጂ ከሕዝብ ጋር አይደለም፤ሆኖም አያውቅም።ኢትዮጵያን በቀውጢ ቀን መካድ ልማዳቸው ነው።እኛ ኢትዮጵያውያን የነዚህን ጣምራ ጠላቶቻችንን ትርክት ማክሸፍና አገራችንን ለዚህ የተባበረ ጠላት ዘመቻ የዳረጋትን የጎሰኞች ስርዓት ለማሶገድ መታገል ግድ ይለናል።

 

ከባዕድ የጎረሱት በሶ ይወጣል ደም ጎርሶእንደሚባለው እነሱ ለሚወረውሩት ፍርፋሪ፣እርዳታና ድጋፍ እራሳችንንና አገራችንን መሸጥና አሳልፈን መስጠት አይኖርብንም።ውጤቱን እያዬነው ነው።የነሱ እርዳታ አገራችንን ፈቀቅ አላደረጋትም፤የነሱ ብድር በዕዳ ውቅያኖስ እንድንዘፈቅ አደረገን እንጂ ሕዝቡን ከድህነት አሮንቃ አላወጣውም።የተጠቀሙት አቀባባይ ባለሥልጣኖችና አበዳሪዎቹ ብቻ ናቸው።ተዋርዶ ከመኖር በድህነት ተከብሮ መኖር ይሻላል።ሊኖረን የሚገባው ግንኙነት የዓለም አቀፍ ሕግና ደንብ በሚያስቀምጠው ግንኙነት ደረጃ እንጂ በጌታና በባሪያ መካከል የሚኖር ግንኙነትን አይደለም፤ እስከወዲያኛው እምቢ ልንለው ይገባል።ይህ የጎሰኞች ቡድን በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የአገራችን አንድነቷ ፣ክብርና ደረጃዋም ሊጠበቅ አይችልም፣የሕዝቡም መብት አይረጋገጥም።በአሜሪካ ፊትአውራሪነት የተሰለፉት ሃይሎች በተሳሳተ አመለካከት የአማራው  ማህበረሰብ በህወሃት/ኢህአዴግ ተነጥቆ የነበረውን ታሪካዊ መኖሪያ መሬቱን አስመልሶ ለመቋቋም ጥረት ሲያደርግ እንደ ወራሪ ቆጥረው ለድጋሚ መፈናቀል ነጋሪት እዬጎሸሙበት ነው።ከዚያም በዘለለ ትግራይ ክፍለሃገርን እንደ ነጻ አገር በሚያሳይ መልኩ የኢትዮጵያን አንድነት እዬተፈታተኑት ነው።

 

ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም ነውና አገራችንን በጎሳ ተዋረድ ሸንሽኖ ለዚህ ውርደት የዳረጋትን በሥልጣኑ ላይ ያለ ቡድን አሶግደን የአገር አንድነትን፣የሕዝቡን ትስስር፣ታሪኳንና ዳርድንበሯን  የሚያስከብር አገር ወዳድ መንግሥት ለማምጣት በአንድነት መቆምና መታገል ይኖርብናል።ትግላችን ጣምራ ትግል ነው።አንደኛው በውጭ ሃይሎች የመጣ ጠላትን ለመቋቋም፣ ሌላው በአገር ውስጥ ያለ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አንድነት የጎሰኞች ስብስብ ለማሶገድ።ትግሉም ቀላል አይሆንም።ግን ህብረት ካለ የማይቻል የለም።እኛ የተረከብናትን ኢትዮጵያን ለልጅ ልጆቻችን ማውረስ የትውልዳችን ግዴታና አደራ ነው።ትልቅነት የመሣሪያ ጋጋታና የገንዘብ ብዛት ብቻ አይደለም ፤የሞራልና የጀግንነት ከዛም በላይ የእውነት ባለቤት መሆን ለድሉ ዋስትናና ጉልበት ነው።ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ሊወሯት የመጡትን ጠላቶቿን አሳፍራ የመለሰችው እውነትን ባነገቡ፣ በቆራጥና አገር ወዳድ ልጆቿ ትግል ነው።የቬትናም ሕዝብ የናፓል ቦምብ ውርጅብኝን ተቋቁሞ ነው እየተፈራረቁ የመጡበትን የምዕራብ ቅኝ ገዢዎች በዃላም ግዙፏን  አሜሪካንን ድባቅ መትቶ የነጻነቱና የአገሩ ባለቤት የሆነው።እርግጥ ነው ወቅቱ የተለዬ ነው።ከወቅቱ ጋር የተገናዘበ የትግል አቅጣጫ መከተል ተገቢ ነው።ዱሮም ሆነ አሁን ጊዜ የማይሽረው ትልቁ መሣሪያ ግን አገር ወዳድነቱ ነው።ለፍትሃዊ ዓላማ መቆሙ ነው።ያንን ካነገብን ውጣ ውረዱ ፣ችግሩ ቢበዛም የማታ ማታ ድሉ የእኛ ይሆናል።

 

በሥልጣን ላይ ላለው ቡድን የመጨረሻ ዕድል ለመስጠት ሲባል፣ አሁንም ሁሉንም በኢትዮጵያዊነቱና በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምን፣የጎሳ ፖለቲካን የሚቃወመውን ያካተተ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ፈቃደኛ እንዲሆንና እንዲተባበር እንጠይቃለን።ከዚህ የተለዬ አማራጭ መፍትሔ የለም።ሰላምና መረጋጋት ሳይኖር ምርጫ ማካሄድ እብደት ነው። በሕዝብ ጭፍጨፋ ወንጀል ያልተሳተፉ፣ያልቀሰቀሱና ያልተጠረጠሩ በእስር ላይ የሚገኙት በነጻ እንዲለቀቁ የዓለም አቀፍ ኢትዮጵያውያን የትብብር መድረክ ጥያቄ ያቀርባል

አገር ወዳዶችን ማሰርና ማሳደድ ይቁም! የዘር ማጥፋት ዘመቻው ይቁም!!ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!!

 የተባበረን ጠላት በተባበረ ክንድ እንመልስ!!

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን የትብብር መድረክ