Sunday, March 31, 2019

የለማ መገርሳ አትጠራጠሩኝ ዥዋዡዌ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)


የለማ መገርሳ አትጠራጠሩኝ ዥዋዡዌ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
Lema-Megersa-Pendulum (Cartoon source Welkait.com)
ውይ!! ያች አገር ምን ብትደርግ ይሻላት ይሆን? ‘ትናንትም ፤ ዛሬም ነገም “ውሸትን”  በውብ ቃላት እያስዋቡ የተናገሩትን ውሸት ሲነቃባቸው ቆርጦ ቀጥል ነው እያሉ “አሉ” ይላሉ:፡የኦሮሞ አፓርታይድ (የኦሮሞ ክልል) አስተዳዳሪው ለማ የአላልኩኝም የትናንቱ “የአሉ/ታ” ንግግር አድምጨዋለሁ። ይሄ የክህደት፤የማስተባበል አመል በኢትዮጵያውያን ልሂቃን እጅግ የበታ ፈውስ ያልተገኘለት ‘በሽታ’ ነው። ይህ ‘ይቅርታ’ አለመጠየቅ፤ ‘ስህተትን ያለማረም’ አመል፤ ድርቅ የማለታቸው መጥፎ ልምድ አገሪቱ ወደ ማጥ ከሚያስገባት ዋነኛው ምክንያት ይህ አመል ነው። የአለምነው መኮንን “ቆርጦ ቀጥል ነው” መከራከሪያ ዛሬ በለማ መገርሳ ተደገመ!
እንደዚያም ሆኖ- በለማ የተዋቡ ቃላቶች ሰክረው “ተጠራጥረንህም አናውቅም” እያሉ የሚጽፉ ጸሃፍት የድረገጹ ሲንጋጉ አስተውያለሁ። የሕዝባችን የለመጠራጠርና በየ አዳራሹ በእጅ እና በፉጨት የማንጨብጨብ በሽታም ይሄም መድሃኒት ያልተገኘለት ሌላው ችግር ነው።
በቅርቡ የታዘብነው ‘የአላልኩም እና ይቅርታን መጠየቅ” ያልለመዱ ‘ከስህተታቸው መታረም ያልፈለጉት’ ምሁራን እና ፖለቲከኞች መካከል አብይ እና ለማ የቅርቡ ዋነኛ ምሳሌዎች ናቸው። ስለ አብይ “ወደ ለየለት ጦርነት እንገባለን፤ እና እኔ እውነት ከደሜ ውስጥ ነው፤ ኢንሳ ውስጥ ስሰራ ኢትዮጵያን ወይንም ዜጋን የሚጎዳ ስራ አልሰራሁም….”  ንግግሩ በሰፊው ስለተነጋገርንብት ወደዚያው ሳልገባ ዛሬ ደግሞ፤ይግረም ብሎ ‘ለማ መገርሳ’ አብዛኛዎቹ ከሶማሌ፤(አንባቢዎች ብዙዎቹ ኦሮሞዎች መሆናቸውን አትዘንጉ) “ወደ አዲስ አበባ እንዲሰፍሩ ያደረግኩዋቸው ‘ተፈናቃዮች” “ፖለቲካዊ ይዘት የለውም፤ ምንም ፖለቲካ ፋይዳ አይደለም” የአዲስ አበባውን ናሪ የዲሞግራፊ (የሕዝብ ስብጥር ‘ተዋጽኦ’) ለመለወጥ አይደለም…” ሲል በጣም ቁጣ አዘል የተሞላበት ንግግር ሲናገር አድመጫለሁ። ሰፋሪዎቹ ለምን ወደ አዲስ አበባ እና ዙርያዋ ለማስፈር እንደፈለገ ከራሱ አንደበት ያለፈው ወር ንግግሩ የምንረዳው ነገር፡ የትናንቱን የአሉታ እና አውንታን “የመሸፋፈን ንግግሩ” እውነታውን ለማወቅ ከዚህ በታች ያለውን /ር አብርሃም ዓለሙ ከኦሮምኛ ወደ አማርኛ ‘የለማ መገርሳ ንግግር” (ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ  ፋይዳ እንዳለው የተናገረውን) ረስታችሁት ከሆነ ለምን ለማን መጠራጠር እንደሚገባን ይህንን ይፋዊ ንግግሩን ላስነብባችሁ።
 በነገራችን ላይ ተርጓሚው (ካልተሳሳትኩ) ለማ መገርሳ “የአመቱ ሰው ሽልማት መሸለም አለበት” ብሎ ስለ ለማ መገርሳ መሸለም ሃሳብ ሲሰጥ የነበረ ምሁር ነው። ስለዚህ በለማ ላይ ምንም ጥላቻ የሌለው ሰው መሆኑን እንድታውቁት ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። ማወቅ ያለባችሁ ተርጓሚው ዶ/ር አብርሃም የቋንቋ ምሁር ነው። ለማ መገርሳ አላልኩም የሚል ከሆነም ፊት ለፊት እኔ ከተረጎምኩት ትርጉም ሁለታችን ቀርበን ሚዲያ ላይ እውነታውን ልንከራከርበት እንችላልን ብሏል ደ/ር አብርሃም።ለማ ግብዣው ተልኮለታል፤ ግን እስካሁን ሊጋፈጠው አልፈለግም።
በነገራችን ላይ ተፈናቃዮቹ ወደው ሳይሆኑ በገዳ ሽማግሌዎች እባካችሁ ተብለው እንደምንም ተብሎ “በግፊት ነው እንዲሰፍሩ የተደረገው” (ይህንን የእባካችሁ እዚህ ስፈሩ ወደ ሰፈራችሁ አስፍሩን አትበሉን የሽማግሌዎች እነ ኦሮሞ ፖለቲከኞች ግፊት “ለፖለቲካዊ ሴራ” እንደሆነ አስቡት) ሴራው ደግሞ ለማ እንዳለው፦
“የከተማ ፖለቲካን (አርበን ፖለቲክስ) ማጤን አለባችሁ፤ ችላ ልትሉት አይገባም፤’ ያላችሁት፣ ትክክል ነው፡” የከተማ ፖለቲካ (አርበን ፖለቲክስ) ሊጤን ይገባዋል፣ ምክንያቱም የዚህ ሀገር ፖለቲካ ማእከል (ሴንተር ኦፍ ፖለቲክስ) ከተሞች ስለሆኑ ነው፡፡ የዚህን ሀገር ፖለቲካ የሚወስነውም ከተማ ነው፤ ከተሞች ናቸው፡፡ የከተማ ውስጥ ፖለቲካ ማለት አንድ ቁጥር ዲሞግራፊ (የህዝብ ስርጭት) ነው።ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ለኦሮሞ አንድነት። ይሄ በፖለቲካ ላይ ያለው ፋይዳ፣ ሄዶ ሄዶም በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ፋይዳም ከፍተኛ በመሆኑ” ይላል ለማ መገርሳ (ምንጭ ኢትዮ ሰማይ) አሁን ወደ እራሱ አንደበት እናምራ። ይህንን የለማ መገርሳ የቀድሞ ንግግሩን ለማወቅ በቴድሮስ ጸጋየ (ርዕዮት ሚዲያ) የተለቀቀው የትርጉም ጽሁፍ እነሆ።
የአዲስ አበባንና ዙርያዋን የህዝብ ተዋጽኦ demography ለመለወጥ ከግማሽ ሚልዮን የሚበልጡ ኦሮሞዎች አዲስ አበባ ማስገባታቸውን አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ!!! (Reyot – ርዕዮት)
ጥያቄዎች፣
1. “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ብሎ ያለ ርዕሰ መስተዳድር፤ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን” የሚል ጠቅላይ ሚኒስትር በጋራ በቋንቋ ተከልለው ከስር ከስር “ኢትዮጵያ” በማለታቸው ያከበራቸውንና እምነት የጣለባቸውን ሌላውን ኢትዮጵያዊ የሚገፋና ከአገር ባለቤትነት የሚፍቅ ሸፍጥ መስራት ምን ያህል ያስጉዛቸው ይሆን?
2. ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም ጉዳይ “በቦታው የነበርኩ ቢሆንም ሲነገር አልሰማሁም፣ አላውቅም” ሊሉን ይደፍሩ ይሆን? የለማ ቡድን አባላት የሚከተለው መልእክታችን ይድረሳቸው፡፡
ይሄ ጨዋታ ለአሳዳጊያችሁ ለህወሀትም አልበጀ፡፡ ኢትዮጵያ እንደሆነች ሊጥሏት ያሰቡትን ሁሉ ጥላ የምትነሳ ሀገር ናት፡፡ “እፍ ይሏታል እንጂ አያጠፏትም” እንዲል ገጣሚው፡፡
Reyot – ርዕዮት
የ3 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ Video ትርጉም በጽሁፍም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተደረገ የጨፌ ኦሮሚያ የእርቅ ህዝባዊ ሸንጎ (አቶ ለማ መገርሳ ከጉባኤው ተሳታፊዎች አዲስአበባንና ኦሮሚያን አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጧቸው መልሶች)፦
አብርሃም አለሙ (ዶክተር) እንደተረጎመው
( ” ‘የከተማ ፖለቲካን (አርበን ፖለቲክስ) ማጤን አለባችሁ፤ ችላ ልትሉት አይገባም፤’ ያላችሁት፣ ትክክል ነው፡፡ የከተማ ፖለቲካ (አርበን ፖለቲክስ) ሊጤን ይገባዋል፣ ምክንያቱም የዚህ ሀገር ፖለቲካ ማእከል (ሴንተር ኦፍ ፖለቲክስ) ከተሞች ስለሆኑ ነው፡፡ የዚህን ሀገር ፖለቲካ የሚወስነውም ከተማ ነው፤ ከተሞች ናቸው፡፡ የከተማ ውስጥ ፖለቲካ ማለት አንድ ቁጥር ዲሞግራፊ (የህዝብ ስርጭት) ነው፡፡ እዚያ ላይ አንዱን ወደዚያ መግፋት፣ አንዱን ወደዚህ መጎተት፣ አንዱን ጠቅሞ ሌላውን ለመጉዳት ሳይሆን፣ እንደ ኦሮሚያ ብዙ ነገሮች እየሰራን እንዳለን መገንዘብም ያስፈልጋል፤ በቂ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ የጀመርነው በጣም አበረታች ነው፡፡ ከሶማሌ የተፈናቀሉትን ከ 500፣000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ የሆኑ ሰዎች፣ እንደምንሆነው ሆነን፣ ገፍተንም፣ ምንም ብለን፣ ከዚህም ከዚያም ብለን፣ የገዳ አባቶችንም፣ ሽማግሌዎቻችንንም ይዘን፣ እንደለመድነው እርቅ ፈጥረን፣ አቅፈን፣ ስመን ወደ ነበሩበት ቦታ ልንመልሳቸው እንችል ነበር፡፡
ቢያንስ ቢያንስ መመለስ ይቻል ነበር፤ እኛ ግን ልንመልሳቸው አልፈለግንም፡፡ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ለኦሮሞ አንድነት፣ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ዛሬም ችግር ላይ ያሉ ቢሆንም፣ ገጠር አላሰፈርናቸውም፤ ከተማ ነው ያሰፈርናቸው፣ እነዚህን ሰዎች፣ እወቁ፡፡ በአንድ ጊዜ ከ 500፣ 000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ሰዎችን፣ እንዲያውም አዲስ አበባ ዙሪያና አዲስ አበባ ውስጥ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 6000 (ስድስት ሺህ) አስገብተናል፤ አዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ አይደለም፡፡ እኒህን ከዚያ የተፈናቀሉትን ሰዎች፣ የዚህን አካባቢ ባህል የማያውቁ ሰዎች፣ በብዙ ነገሮች ከአካባቢው ጋር የማይመሳሰሉ፣ ይቸገራል መችም፣ ይቸገር፤ ዛሬ ችግር የማያጣው ቢሆንም፣ ከተቸገረም እዚሁ ከተማ ውስጥ ይቸገር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በእግሩ የሚቆምበት መሬት ይኑረው፤ እሱ ቢቸገርም ለልጆቹ የሚሆን ስለሆነ፣ ብለን ህዝባችንንም አስቸግረን ካለን ነገር ላይ አዲስ አበባ ዙሪያ ነው ያሰፈርናቸው፡፡ አብዛኛው የሀረርጌ ሰዎች ናቸው፣ እወቁ፡፡ ቦርደዴ ማስፈር ይቻል ነበር፤ ምስራቅ ሀረርጌ ልናሰፍራቸው እንችል ነበር፡፡ ማስፈር ትክክል ከሆነ እንዲያውም እዚያው አካባቢ ነበር ማስፈር የሚገባው፤ ያን ባህል ነው የሚያውቀው፣ ያን አየር ነው የሚያውቀው፡፡ ወደማያውቀው ባህል እዚህ አምጥተን አዲስ አበባ ውስጥ አሰፈርነው፡፡ ቢቸገር ቢቸገር ሁለት ዓመት ነው ሊቸገር የሚችለው፤ ከዚያ በኋላ ሰው ሆኖ ይወጣዋል፡፡ ይሄ በፖለቲካ ላይ ያለው ፋይዳ፣ ሄዶ ሄዶም በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ፋይዳም ከፍተኛ በመሆኑ፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን በብዙ መንገድ ስለሚፈይድ፡፡
ወጣቱንም ስራ እናስይዛለን ብለን በንግድ ስም፣ በሌላም ነገር ስም ብዙ ነገር ስናደርግ ነበር፤ እናም አብዛኛውን ከተማ ውስጥ አስገባነው፡፡ ወደ ከተማ ስናስገባው የሚኖርበት ቦታ ኖሮት ነው፡፡ ከ500፣ 000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያን ክልል ሰራተኞች ዘንድሮ መሬት የሰጠናቸው ገጠር ውስጥ አይደለም፤ ይብዛም ይነስም ከተማ ውስጥ ነው የሰጠናቸው፡፡ ግማሽ ሚሊዮን ለሚሆኑ ነው የሰጠናቸው፡፡ ብዙ ልንቆጥር እንችላለን፡፡ ይሄ በቂ ነው ብዬ አይደለም፤ ሊሰራበት ይገባል፡፡ ሆኖም ችላ ያልነው ነገር አይደለም፤ እየተሰራበት ያለ ነገር ነው፡፡ ስንሰራም በከፍተኛ ጥንቃቄ መስራት የሚያስፈልግ በመሆኑ፣ ይህም በዚሁ ረገድ ቢታይ መልካም ይሆናል ብዬ ነው የማየው፡፡”)
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

Saturday, March 30, 2019

አበበ ገላው እንደ የ ቪ ኦ ኤው ሄኖክ ሰማእግዚአብሔር! ቆቤን አንስቼ ለኢሳቶቹ ለምናላቸው፤ ለኤርምያስ እና ለሃብታሙ እጅ እነሳለሁ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)



አበበ ገላው እንደ የ ቪ ኦ ኤው ሄኖክ ሰማእግዚአብሔር!
ቆቤን አንስቼ ለኢሳቶቹ ለምናላቸው፤ ለኤርምያስ እና ለሃብታሙ እጅ እነሳለሁ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
የኢትዮ-ሰማይ ተከታታዮች እንደምታስታውሱት ‘ኢሳትን’ ስቃወም እንደነበር የምታውቁት ነው። የተቃወምኩባቸውንም ምክንያቶች በርከት ያሉ በብዙ ምክንያቶች አስደግፌ ነው። ዛሬ፤ ዛሬ በቅርቡ ኤርምያስ ለገሰ ሃብታሙ አያሌው፤ ምናላቸው ስማቸው ተወልደ በየነ (ተቦርነ) እና እየሩሳሌም ተ/ክለጻድቅ እና የአውሮጳው ካሳሁን የልቤን እየተናገሩልኝ ቀልቤን በመስለባቸው ያለወትሮየ ኢሳትን ለማመስገን በቅቻለሁ።

ሲሳይ አገና በዘር ጽዳት እና በብዙ ሰብኣዊ ወንጀል እጃቸው የጨቀየ የዛሬ ወጣቶችን በዘረኝነት እንዲታነጹ ያደረጉ፤ የአገራችን ቋንቋ በላቲን ፊደል እንዲተካ ያደረጉ አፍሪቃዊ ስሜት የራቃቸው “ማፈሪያዎች” ‘ኦነግ እና የመሳሰሉ ብዙ ሰዎችን በግድያ እና በዘር ማጥፋት የተካፈሉ የድርጅት መሪ ወንጀለኞች ሁሉ ለመንግሥት ተብየው (የኦሮሞዎቹ አብይ አሕመድና የትግሬዎቹ የወያኔ አፓርታይድ ጥምር መንግሥት) በማሳሰቢያ መልክ “ልዩ ክብር እና የሚጦሩበት ድጎማ/ጡረታ” ይሰጣቸው ሲል የተከራከረውም ሆነ “እኔም ግንቦት 7 ነኝ ሲለን የነበረው ዛሬ ደግሞ እኔም አብይ ነኝ!” ለማለት እየቃጣው ያለው እውቁ ጋዜጠኛ አበበ ገላው (ሁለቱም የኢሳት ጋዜጠኖች) ከላይ የተጠቀሱ ምርጥ ጋዜጠኞችን ባይቀላቀሉዋቸው እና ሁለቱ ከላ ተቀምጠው ዜናን የማንበብ ስራ ቢሰጣቸው ለጣቢያው ጥራት ይሰጣል የሚል ምክር አለኝ።

ኤርምያስ እና ሃብታሙ የራስ ቆቤን አውርጄ በአክብሮት ሰላምታ ከማመስገን በላይ በምን ቃላት ላመሰግናችሁ እንደምችል ጨንቆኛል።አብይ የተባለ እጅግ የተካነ “ካን አርቲስትን” (የሕሊና ሰላቢን) በማጋለጥ የታወቀው የኔ ጀግና ብየ የሰየምኩት ‘ቴድሮስ ጸጋየ” (የርዕዮት አዘጋጅ) ልቤን ቅቤ እያስጠጣ ሲያርስልኝ ከርሞ፤ በቅርቡ ደግሞ እስክንድር ነጋ ወደ ፊት በመምጣት የኦነግን “ትግል ወራሽ” የሆነው አብይ አሕመድ(በአብይ ተከታይ ኦሮሞው ዶ/ር ብርሃነመስቀል አባባል) እንዲሁም ዋናው ‘ኦነጉ’ ለማ መገርሳ የተከናነቡበትን አሳሳች “ጭምብላቸውን” አስወልቆ “ወደ ለየለት ጦርነት እንገባለን“ እስኪሉ ድረስ “የደበቁትን ባሕሪያቸው” አዳራሽ ውስጥ በቁጣ ፈንድቶ ለትዝብት እንዲዳረጉ ያደረጋቸው ቆራጡና ምክንያታዊው እስክንድር ነጋ ያረካኝን እያጣጣምኩ ሳልጨርስ፦- ተጨማሪ እርካታ በመጨመር “የፋሺሰቶቹ የወያኔዎቹ የስለላው መዋቅር (ኢንሳ) ዋና ቀያሽና አስተማሪ የነበረው ኮለኔል አብይ አሕመድ/ዛሬ ጠ/ሚኒስቴር/” ማስረጃ በማያልቃቸው በእነዚህ የቁርጥ ሰዓት ልጆች እነ ኤርምያስ ለገሰ፤ ሃብታሙ አያሌው፤ ምናላቸው ስማቸው ፤ተወልደ በየነ (ተቦርነ) ካሳሁን እና እየሩሳሌም ተ/ክለጻድቅ የብዙ ተፈናቃይ እና የብዙ እናቶች እምባ እያስደመጣችሁ ለነዚህ ዜጎች ቆማችሁ የአብይን ከንቱ ውዳሴ እና “ፕሮፓጋንዳ” በማጋለጥ ክንብንቡን በማስወለቅ “ንጉሡ እርቃኑን” እንዲታይ በማድረግ እርሱና ተባባሪዎቹ ውስጠ ገበናቸውን በማጋለጣችሁ ያለኝን አክብሮት በድረገጾች ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ።ሲመሰገን የሚቀብጥና የሚቦጠረቅ ሲነቀፍ ደግሞ “የሚቆጣ” አስገራሚ ንጉሥ እንደ አብይ አላየሁም። እናንተ ግን ምንነቱን መጋለጥ ሲኖርበት እንዲጋለጥ መመስገን ባለበት እንዲመሰገን መጣራችሁ ጨዋነታችሁ አሳይታችሁታል። እርሱ ግን አልገባውም።   

ወደ ኢሳት ጋዜጠኞች ከመግባቴ በፊት አንድ ነገር ብየ ልለፍ።

 ሐሙስ ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ አብይ አሕመድን ጠይቁ ተብለው የተጋበዙ ጋዜጠኞች ተብየዎቹ  ብዙዎቹ  ‘ትርኪ ሚርኪ’ ገለባ ጥያቄዎች ሲጠይቁ ግምባር ቀደም ጥያቄ ሆኖው መቅረብ ከሚገባቸው ጥያቄዎች አንዱ በለገጣፎ በስሉልታ…..ወዘተ ወዘተ…የእናቶች የአዛውንቶች የወጣቶች የህጻናት እንባ ያስለቀሱ እንዲደበደቡ ያስደረጉ ሌሊት ማታ ሳይቀር ቤቶቻቸው በቡልዶዘር እንዲፈርስ አድርገው ሜዳ ላይ እንዲጣሉ ያደረጉ “ጸረ ድሃ የሆኑት  እስላማዊ  የኦሮሞ አንስት “ጉዲት ከንቲባዎች” በሕዝብ ሕይወት ሲያላግጡ ዝም ብላ የተመለከተቻቸው ‘የሴቶች ፍናፍንት (ለዝቢያን) ግብረሰዶማውያን” መብት አክባሪ ነኝ የም “መአዛ” የተባለቺው የጠ/ሚኒሰትር አዲሲትዋ የአገሪቱ ጠ/ፍርድ-ቤት ዋና ሹም  “ለምን እነዚህ ጻረ ሰላም የሆኑት “እስላማዊ ጉዲት ከንቲባዎችን” ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲከሰሱ ትዕዛዝ እንዳልሰጠችና” አብይም ለምን በዚህ ጉዳይ እራሱን ላለማስገባት እንዳልፈለገ መጠየቅ ሲገባቸው “ኢሕዴግ እርስበርሱ ተጣልተዋል ወይ?” እያለ በማይረባ አዙሪት ጥያቄ ሲጠይቁ ማምሸታቸው የሚገርም ነው።

እነዚህ ጸረ ሕዝብ የሆኑ ስርዓቱ የመለመላቸው “እስላማዊ-ጉዲቶች” በኢትዮጵያውያኖች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው  የመጀመሪያ አይደለም። ታስታውሱ እንደሆን ከሁለት አመት በፊት በገለጣፎ ዮሃንስ ቤተክረስትያን ተብሎ በሚጠራ ቤተክርስትያን ላይ ጥቃትና ድፍረት በመፈጸም ቤተክርስትያኑ በቡልደዘር እንዲፈርስ ትዕዛዝ የሰጠቺው እና ታቦቱም በፖሊስ ጣቢያ ሽንት ቤት ተጥሎ እንደሰነበተ ክርሰትያኖች የደም እምባ አልቅሰው “የሚሰማቸው አጥተው” ጽላቱ እና የቤተ/ክርስትያኑ ቅዱስ ዕቃዎች አፈር ላይ በአልባሌ ተጥሎ ቆይቶ “ኦሮማራ” በሚባለው ‘ቃለ አጋኖ’ (በቀለ ገርባን ባሞገሰ አሳፋሪ ትዕይንት) የውዥምብርና የስካር ወቅት “ከንቲባዋ ይቅርታ ጠይቃ (የተባለው እውነት ይቅርታ ጠይቃ ከሆነ) ወደ ግንባታው እንዲመለስ መደረጉ” ታስታውሳለችሁ። ያቺ ከንቲባ አሁን ካሉት ከንቲባዎች የተለየች መሆንዋን አለመሆንዋን ባለውቅም ‘ይህች ከንቲባ ወ/ሮ “ጫልቱ ሳኒ” ትባላለች።ዛሬ ደግሞ እርስዋን የተኩ እንደ እንቁላል ተፈልፍለው ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበቸው ቤቶች በቡልደዘር እንዲፈርስ ሲያደርጉ ደብድበው ሜዳ ላይ ስለተወረወሩ ዜጎቻችንን ሁኔታ ጋዜጠኞቹ አብይን ለመጠይቅ ድፍረት ያጡበት ትዝብት ነው።የሚገርም ነው!

እግዚሃር ይሰጠውና አንዱ ጋዜጠኛ ስለ የወያኔ የስለላ ድርጅት የነበረው “ኢንሳ/ INSA/ Information Network Security Agency” የተባለው መ/ቤት አሁን በጠ/ሚኒስተርነት የተቀመጠው አብይ አሕመድ በተቅዋሙ ውስጥ ስለነበረው አስተዋጽኦ ተጠይቆ የሰጠው መልስ እንደ ወትሮው በቃላት እያስዋበ እራሱን ያመጻደቀበትን “አራዳዊ” ማምለጫ ዘዴውን የሰሙት የኢሳቶቹ ኤርምያስ ለገሰ እና ሃብታሙ አያሌው አብይ ሊደብቀው የሞከረውን ሽንፍላውን ለሁለት ገምሰው ጠጠርና አራሙቻ የተሳተፈበትን ስነምግባር በማጋለጣቸው ብዙ ዜጎች እንደኔው ተደስተዋል የሚል ግምት አለኝ። “በሞቴ እባካችላሁ!!!ይህንን አንጀት አርስ” አድምጡልኝ እና ወደ አበበ ገላው ልግባ። ESAT Eletawi Fri 29 Mar 2019

https://youtu.be/TQiLYCndQVo

 

ይህ የስለላ ተቅዋም ንደምታስታውሱት የመጨረሻው የተቁዋሙ አድራጊ ፈጠሪ የነበረው ዛሬ ወደ መቀሌ ሸሽቶ “አጋአዚያን” የተባለ “በትግራይ ትግርኚ ምስረታ ፕሮጀክት” ያስተባበረ የሚገኘው የወያኔው ሜ/ጀኔራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ ነበር። ተቅዋሙም መረጃ ሰብስቦ ለወያኔዎች፤ ለሜ/ጀ መስፍን አማረ እና ለጌታቸው አሰፋ ሲያስረክቡ ብዙ ሰዎች የዚህ ተቅዋም ሰለባ ሆነዋል። ይህ ተቁዋም ምንነቱ እኔ ከመግለጽ የኤርምያስ እና የሃብታሙ ጭብጥ እዚህ በጽሑፍ ጽፌ ከመዘርዘር ይልቅ ከላይ የሰጠሁዋችሁን ቪዲዮ ክርክር ከማር የተገመሰ ንግግራቸው እየገመጣችሁ አድምጡት እና አበበ ገላውም ሆነ እራሱ መመከት የማይቻለውን ለመመከት የሞከረ የኢንሳ መሪ ተዋናይ የነበረው አብይ አሕመድ “ኢንሳን” ሲያዋቅር የተጫወተው ጸረ አገር እና ጸረ ሰብኣዊ  መብት “ቀፋፊ” ሚና አድማጮች ፍረዱ።

በተያያዥ አበበ ገላው ተመስጋኝ ማሕደሩ እንዳለ ሆኖ፦ ዛሬ ምን እንደነካው ባላውቅም አብይ አሕመድ ለመከላከል ሲቃጣው የተደመጠበትን የጋዜጠኛ አበበ ገላው የተናገረውን (በእርሱ ፈንታ እኔ የተሸማቀቅኩበትን) ንግገሩን ስታምጡ እናንተም ገርሞአችሁ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ። የአበበ ገላው አስተሳሰብ እንደዛሬ “የደከመብኝ” ጊዜ የለም። አብይ አሕመድ ሲሰራበት በነበረው የስለላ ተቋም ውስጥ በዜጎች እንዲሁም በጋዜጠኞች ላይ ሲሸረብ የነበረውን የወንጀለኞች ስራ ያጋለጠ እዛው “ኢንሳ” ሲሰራ የነበረ የተባረረ “አንድ የድርጅቱ የውስጥ አዋቂ” አበበ ገላው ከ7 አመት በፊት ያደረገለትን ቃለ መጠይቅ በተገኘው መረጃ ላይ ነው ዛሬ ‘በዕለተ-አርብ’ ኢሳት እለታዊ ክፍለ ጊዜ ውይይት ውስጥ እነ ኤርሚያስ/ሃብታሙ የመነጋገሪያ መረጃውን እየጠቀሱ ሲነጋገሩበት የነበረው። ታዲያ፡ አበበ ገላው ድሮ “እኔም ግንቦት 7ነኝ” ያለበትን አንደበቱ ዛሬ ደግሞ “እኔም አብይ አሕመድ ነኝ!” ወደ እሚል የሚመስል “ድምፀት”(ቶን) “አብይን ለመከላከል” ሞክሯል።
 አበበ እንዲህ ሲል የነ ኤርምያስን ነጥብ ለማንኳሰስ እና መረጃው ያረጀ ያፈጀ 7 አመት ስለሆነ ዋጋ ቢስ ነው እንዳውም በድርጅቱ ላይ ብቻ እናትኩር በማለት ድርጅቱ ያለ ሰው እና ያለ አብይ በእግሩ የሄደ ይመስል አብይን ለመከላከል ያልሞከረው ድንጋይ አልነበረም። እንዲህ ይላል፦

አበበ ገላው፦

… ከ7 አመት በፊት ነው ይኼ ሰውየ “ከኢንሳ” ተባርሮ ነው ይህንን መረጃ የሰጠን። እኔ ነኝ ኢንተርቪው የደረጉት በወቅቱ።ከ7 አመት ይኼ ሰውየ መረጃው ሲሰጠኝ ስለ አብይ አሕመድ የማውቀው ነገር አልበረም። እንደውም አሁን ነው ኤርሚያስ ካነሳው በላ ነው፤ ወደ ላ ዞሬ ስሰማው (ሳዳምጠው) አብይ አሕመድ የሚለውን  መኖሩን ሪያላይዝ ያደረግኩት። ግን ዞሮ ዞሮ ይህ መረጃ ባጠቃላይ ስለ አብይ አሕመድ አይደለም።ኢንሳ ውስጥ ስላለው እንቅስቃሴ ነው። አብይ ሁለት ሦስት ቦታ ነው እሚጠቀሰው። እሚጠቀሰውም፤ “አሉታዊም አዎንታዊም ነው”። አሉታዊው”ጃሚንግ”” በማድረግ ሲሆን አዎንታዊው ደግሞ “አብይ ጥሩ ማኔጄር  እንደሆነ፤ ፈጣን እንደሆነ እያለ ይገልጸዋል።” አበበ የአብይ የዜጎችን ሰብአዊ መብት ጥሰት ስራው “ለሰላይ ተባባሪ ሰራቶኞቹ ፈጣን እና ጥሩ ማናጀር እንደነበረ” ሰውየው የተናገረውን በማካካሻ መልክ ሊያካክሰው መጣሩ የሚገርም ፤የሚገርም ነው!

 እንዲያም ካለ በኋላ አበበ፦ ክርክሩን በመቀጠል እንዲህ ይላል፦

ይህ አስቀድሜ እንዳልኩት አብይ አሕመድን በተመለተ አይደለም “ኢንሳን” በተመለከተ ነው። ሁለተኛ መታወቅ ያለበት እራሱ አብይ ከተባረሩት እንጂኔሮች ውስጥ አንዱ ነው። ይኼ ደግሞ የታወቀ ሃቅ ነው። የተባረረበት ምክንያት ደግሞ “ዲጅታል ሰርቨይላንስ” ኣናድርግም በማለቱ ከተለያዩት ሰዎች አረጋግጫለሁ። ይህ መረጃ “አብዴትን ስላልሆነ” ያን ያህል ትልቅ መረጃ ሆኖ እስከዚህ “ሬለቫንት (ቁምነገር) እንዳለው አድርጌ በበኩሌ አላየውም።” ይላል አበበ ገላው በመጀመሪያ ዙር አብይን የተከላከለበት አስተያየቱ።

ይቀጥሉና ሃብታሙ እና አርሚያስ አከታትለው አበበን መልስ እስኪያጥረው ድረስ ደጋግሞ ከ7 አመት በፊት የሆነ ቁም ነገር የሌለው ገለባ ነገር ነው የሚለውን “መከራከሪያው” እስኪደጋግም መልስ እስኪያጣ ድረስ እነ ኤርምያስ እነ ሃብታሙ በዝርዝር የአብይን የዲጂታል ሰርቨይላንስ የተጫወተበት ሚና ምን እንደነበረ (ያውም እየተቆጠቡ) ጉዱን ዘከዘኩት። ያውም አብይ “ዲጂታል ሰርቨይላንስ” በቦሌ እና በመሳሰሉ አካባቢዎች “የስለላ ካሜራዎችን”…ልትከል ስል የሰማኝ የለም! እንዳልተክል “ተከለከልኩ” እያሉ ጠ/ሚኒሰትሩ የስለላ አውታሮችን መዘርጋት “አኩሪ” ስራ አድርገው በመቁጠር እራሳቸውን ሲኩራሩበት መስማት የሚገርም አሰፋሪ ክስተት ነው። እያሉ እነ ሃብታሙ እና ኤርምያስ አበባን በማስረጃ ለማስጨበጥ ሞክረዋል።

ኤርምያስ እንዲህ ይላል፦

፤ እኔ በቅርብ ስለማውቀው ወደ ውስጥ መግባቱ ዝርዝሩ አሁን በዚህ አስፈላጊ ሆኖ ባላገኘውም ባጭሩ ጠ/ሚኒሰትሩ የያኔ ኮሎኔል እና የስለላው መረጃ ስራ ከፍተኛ ሹም በነበሩበት ወቅት ፤ የተቃዋሚ የዜና ማእከሎችን “ጃሚንግ/በማድረግ(ጃሚንግ ማለት የሳተላይት መልእክቶችን /የራዲዮ/የቲቪ ደምጾችን በአድማጭ ጀሮ በደምብ እንዳይደመጥ “በሃይለኛ ረባሺ የድምጽ ሞገድ በማኮላሸት/በመበጥበጥ” የአፋኝ ስርዓቶች ዋና መገለጫ ስራ ነው) ጃሚንግ በማድረግ መሳተፉቸውን መረጃው ገሃድ ነው። እያሉ ሲያስረዱት፤ ቃለ መጠይቅ የሰጠው ሰውየም አብይ አሕመድ መሳተፋቸው በግልጽ መስክሯል።”  እያሉ አበበን ለማስረዳት ረዢም ርቀት በጓዙም አበበ እያቅማማ ‘7 አመት የሆነን ነገር…….’ .እያለ ማቅማማቱን ቀጠለበት።

ያውም እኛ እኮ 7 አመት ‘20’ አመት./..ወዘተ የተደረገን እንርሳው እና ወደፊት እንራመድ ነው እያልን ያለነው ይላሉ ሁለቱም ኤርምያስ እና ሃብታሙ። “ነገር ግን ጠ/ሚኒሰትሩ እራሳቸው ወደ ላ ሄደው “ኢንሳ INSA” ውስጥ ያደረጉትን አስተዋጽኦ እራሰቸውን በማመጻደቅ እንዲያ ያለ ወንጀለኛ ተቋምን ማቋቋማቸው ሲመጻደቁ መስማት ተገቢ አይደለም ብለናቸዋል። እሳቸው ግን ወደ ላ እየተመለሱ ያልሆነ ታሪክ በመጎንጎን እራሳቸው እና ተቋሙን ማሞገስ ስለሞከሩ የግድ የ7 አመትም ሆነ የልዮሽ ተመልሰን የተደፈደፈውን ጥቀርሻ ተመልሰን እንድንፈትሽው እራሳቸው ጠ/ሚኒስትሩ አስገድደውናል። ዞሮ ዞሮ ስለ “ኢንሳ” እንወያይ ስለ አብይ እንተው (ኢረለቫንት ነው/ፍሬ-ከርስኪ ነው) የምትለውንም ቢሆን “ኢንሳ” ሲመራ የነበረው በዋናነት ጌታቸው አሰፋ ቢሆንም ዋናው ቀያሹ እና “የተቁዋሙ ዋናው አንጎል/Brain/” አብይ ነው! ብለው ሲሉት፦

የማሃል ዋና አወያዩ ጋዜጠኛ ምናለቸው ስማቸው  አበበ ገላውን እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል።
ወደ ማጠቃለያው እንሂድ እና “መረጃው ጠቃሚ ነው ጠቃሚ አይደለም፡ የሚለውን አድመጭ ይፍረድ እና ወደ ፍረጃ ሳንሄድ እንዲሁ አንተ በመረጃው ላይ ያለህ ማጠቃለያ ሃሳብህ ምንድ ነው?
በመጨረሻ ሲጨንቀው አበበ ገላው እንዲህ ይላል-

ቅድም እንዳልኩህ ነው። ይህ መረጃ ከ7 አመት በፊት የሆነ መረጃ ነው።

ምናላቸው ስማቸው ፡ጣልቃ ገብቶ “እርሱ ቀደም ብሎ አስተያጥ ተሰጥቶበታል።

አበበ ገላው፡

የተሰጠበት ቢሆንም “ኢምፖርታንት” ነገር ስለሆነ ነው። ይህ መረጃ ከተከሰተ በላ ብዙ ክስተቶች ተከስተዋል።ከዚያ በላም የለውጡ ሃይል የሆኑትን እነ አበይ አሕመድ ከውስጥ ሆነው ሲታገሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው! (……?)  ማድረግ አያስፈልግም ስለዚህ ይህ ነገር “አፕዴት” መደረግ ያለበት ነገር ነው ይላል አበበ በማጠቃለል።

ትንታጉ ሃብታሙ አያሌው በአበበ ገላው እንደ “ቪኦኤው ሄኖክ ሰማ እግዚአብሔርነት” መከላከል የማይቻለውን ስርዓት ለመከላከል በቅጽበት መገልበጡ (መለወጡ) በአበበ አዲስ ባህሪ ተገርሞ ጎርነን ባለ ደምጽ ፈገግ በማለት (ኤርሚያስ እማ እጅግ ተገርሞ አንባቢ ፊቱ እንዳያነበው ጎንበስ ብሎ አፉን ከድኖ ለብቻው በረጂም የመገረም ፈገግታ መደመጡ ያስታውቃል)- ሃብታሙ እንዲህ ሲል ቀጠለ- 

“ይኼ መረጃ 7 አመት  አልፎታል የሚለው “አዲስ አበባ” በ1997 የዛሬ 14/15 አመት በፊት በእነ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ትዕዛዝ የፈሰሰው ደም ለኔ እንደ አዲስ ነው የሚከረፋኝ! ወንጀል “7 አመት” ሊሆን ይችላል “17 አመት” ሊሆን ይችላል፡ ወንጀል ወንጀል ነው! እንለፈው ብለን በስምምነት ካላለፍነው በቀር “ከ7 አመት በፊት የነበረውን ወንጀል ከ7 አመት በላ’ “ጽድቅ” አድርገው ሲያመጡት ነው “ሕመም የፈጠረው”! እኛ ትተነዋል፡ ይቅር! እሳቸው ግን ጸድቅ አድርገው አያምጡት! (ነው እያልን ያለነው)። በማለት ሃብታሙ ንግርሩን አጠቃለለ።  

ማጠቃለያ፦
ባጠቃላይ አበበ ገላው ስገመግመው የጋቢና ውይይት ክ/ጊዜ አዘጋጅ የነበረው ለወያኔ/ኢሕአዴግ ስርዓት ጥብቅና የቆመው የቪኦኤው “የሄኖክ ሰማ እግዚአብሔር” እና ለአብይ አሕመድ መከላከል የቆመው ‘አበበ ገላው” አንድ ሆነው ታዩኝ። ወዳጄ ሊቀሊቃውንቱ አቻምየለህ ታምሩ (ቪ ኦ ኤ ላይ ተጋብዞ) “ወያኔ/ኢሕአዴግ አፓርታይ ነው” ብሎ ስለተናገረ “የቪ ኦ ኤው የጋቢና ክ/ጊዜ አዘጋጅ ‘ጋዜጠኛ ሄኖክ ሰማ እግዚአብሔር’ “አቻምየለህ እባክህ! ኢሕዴግ ‘አፓርታይድ አይደለም! አፓርታይድ አትበለው!” ብሎ በቁጣ መገንፈሉ እና ዛሬ በተመሳሳይ ግጥምጥሞሽ አበበ ገላው ደግሞ አብይን ለመከላከል ሲል ፡”ኢንሳ” ስለታባለ ያለ ሰው እና ያለ አብይ አሕመድ የሚንቀሰቀስ “ሮቦት/መንኮራኩር” ይመስል ኢንሳን እንጂ የአብይን አታንሱ! የአብይ ጉዳይ ከ7 አመት በፊት የተፈጸመ “ያረጀ ያፈጀ - ፍሬ ቢስ-” ጉዳይ ስለሆነ ዛሬ አናንሳው፡ ይህ መረጃ ከተከሰተ በላ ብዙ ክስተቶች ተከስተዋል።ከዚያ በላም የለውጡ ሃይል የሆኑትን እነ አበይ አሕመድ ከውስጥ ሆነው ሲታገሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው! (……?)  ማድረግ አያስፈልግም” ፤ በማለት አበበ አብይን ሲከላከልለት በሚገርም ሁኔታ ግን “አብይ አሕመድ እራሱ” የሰራሁት መጥፎ ነገር ካለ ከወጣትነቴ ጀምሮ አምጡ! ቆፍሩ! ያውም የራሴን “ባዮግራፊ መጽሐፍ” እየጻፍኩ ነኝ፡ “የምኮራበት እንጂ ቅር የሚለኝ ነገር የለኝም።” እያለ እራሱ አብይ “የምታውቁልኝ ገበና ካለ አምጡ!!” እንዳለ እየታወቀ “አበበ ገላው” “ባለፈ ጉዳይ አብይን ለመክሰስ ብትሞክሩ በዚህ ጉዳይ ላይ “ኢሬለቫንት” (ፍሬ-ከርሰኪ) ነው ይላቸዋል።

 ‘እግሩ ሳያሳርፍ ከኢትዮጵያ መመለሱ እንኳን ደህና ወደ አሜሪካ ተመለስክ” ሳንለው አበበ ገላው እንደ ሄኖክ ሰማ እግዚአብሔር ፈለግ እንዲከተል የአብይ ቤተመንግሥት ምን እሚሉት “የጤና አዳም ቅጠል” አበበን አሽትቶ እንደላከው ግራ የሚገባ ክስተት ነው። 

ኤርምያስ፤ሃብታሙ ምናላቸው ስማቸው ፤ተውልደ (ተቦርኖ) ካሳሁን እና ውቢትዋ እየሩሳሌም (እየሩስ) ምስጋና ይድረሳችሁ። በርቱ! ቀጥሉ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

     
  

Sunday, March 24, 2019

…“ብልት ላይ ሃይላንድ አንጠልጥሎ ቶርች ማድረግ አልቀረም”…Ethiopia: (Ethiopis) posted at Ethio Semay



“ዛሬም ብልት ላይ ሃይላንድ አንጠልጥሎ ቶርች ማድረግ አልቀረም “የቪዲዮ ማስረጃ” ይኼው ተመልከቱ!!
                                          

(Ethio Semay)

ቶርች፤ድብደባ ወከባ ቀርቷል እያላችሁ ስታደነቁርን የነበራችሁ የኦሮሞ ፋሺስቶቹ ስርዓት የእነ አብይ አሕመድ እና የለማ መገርሳ አለቅላቂ ዲያስፖራዎች “እንዳይጋለጥ ተደብቆ የነበረው የመሪዎቻችሁን ጉድ” ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነው በእስረኞች እና በህጻናት እንዲሁም በእናቶች ላይ “እንሰሳዊ ወንጀል” ሲፈጽም  ጆሮኣቸው ““በጥፊ እና በጥይት አፈሙዝ ተደብድበው መግል እየፈሰሰባቸው የደነቆሩ ፤ እንዲሁም በብልት ላይ ሃይላንድ ተንጠልጥሎባቸው የተሰቃዩ ” የአማራ እና የጋሞ ኢትዮጵያውያን ነገዶች እየተለቀሙ ቅሊንጦ ታስረው የተሰቃዩበት “የቪዲዮ ማስረጃ” ይኼው ተመልከቱ!! (ምንጭ ኢትዮጲስ) (Ethio Semay)

…“ብልት ላይ ሃይላንድ አንጠልጥሎ ቶርች ማድረግ አልቀረም”…Ethiopia: Ethiopis