Monday, December 8, 2025

ብሩሕ ሕሊናው እየከሳበት የመጣው የአቻምየለህ ታመሩ ነገር እና ፋኖዎች የሰሩት ወንጀል፤አልፏል እርሱት የሚለን ፍርደገምድሉ ዳኛ ሃብታሙ አያሌው ክፍል 1 ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/9/25

 

ብሩሕ ሕሊናው እየከሳበት የመጣው  የአቻምየለህ ታመሩ ነገር እና ፋኖዎች የሰሩት ወንል፤አፏል እሱት የሚለን ፍርደምድሉ ዳኛ ሃብታሙ አያሌው

ክፍል 1

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 12/9/25

የቀድሞ ጓደች የአሁን ጠላቶች

ሃብታሙ አያሌው የማደንቀው ብሩህ የፖለቲካ ተንታኝ እና ለሃገራችን ሊለካ የማይቻል እጅግ ከባድ መስዋዕስት የከፈለ ጀግና ኢትዮጵያዊ መሆኑን ደጋገግሜ የመሰከርኩለትና ያሞገስኩት የቁርጥ ቀን አርበኛ ነው። ያንን ብርቱ በዕሩ እና በሳል ተሟጋች አንደበቱ ማሳነስ ከቶ አይቻልም። እንዲያም ሆኖ አንዳንድ ወቅት በ MYTHYCAL ቅዠት ውስጥ ይዋኛል። በስሑት ከሚዋኛችው አንዱ በDecember 1/2025 ሕዳር 22/2018 <<የአገዛዙን ቅጥረኞች አደገኛ ሴራ የሚያጋልጥ ማስረጃ፥ የነ ማስረሻ ሰጤ መንገድ እና መሬት ላይ ያለው እውነታ ! December 1/2025>> በሚል ባቀርበው ፐሮግራም ላይ ያስተላለፈው ትንተና  በክፍል 2  አቀርባለሁ።

ለዛሬ ግን አቻምየለሀ ታመሩ እስክንድር ነጋን « ወራዳ ሰው» በሚል የገለጸበትን ዘለፋ እንመልከት ።ሁሌም ሳደንቀው የነበረው ብሩሕ  ሕሊናው እየከሳ የመጣበት በጎጃምነቱ ለጎጃም ፋኖዎቹ ለነ ዘመነ እና አስረስ ማረ ብቻ ሳይሆን ለሻዕቢያና ለወያኔ ሥስ ልብ ላለው ለወሎየው ባሕላዊ ጀነራል «ተፈራ ማሞ» ልዩ ክብር በመስጠት ከነዚህ ቡድኖች ጋር ፍቅር የወደቀው አቻምየለህ ታመሩም የእስክንድር ነጋን ስም በማጠልሸት ከሚንጋጉት ጋጋታ ቡድን ውስጥ ገብቶ እራሱን ባማስገመት ወደ ከፉ አወዳደቅ እየትንሸራተተ ነው።

በDecember 4/2025 “የሐተታ ርዕስ” ባላደረገብት ጽሑፉ ላይ  «ከግደያ ለማመለጥ ተገፈቶ ወደ አፓርታይዱ ሥርዓት ወደ አኦሮሙማው አብይ አሕመድ ሮጦ እጁን ሰለ ሰጠው ማስረሻ ሰጤ» በተቸበት ጽሑፉ ላይ  አቻምየለህ እንዲህ ይላል።

«ማስረሻ ሰጤ የሚባለውን ነውረኛ ግለሰብ ብቻ የጦስ ዶሮ በማድረግ እስክንድር ነጋ፣ ፈንታሁን ሙሀቤ፣ እያሱ አባተ፣ ጌታ አስራደ ወዘተ የመሳሰሉ ወስላቶችን ንጹህ ለማድረግ ነው።....» ይልና

እስክንድርን

የኦሮሙማ ሰላይ እንደሆነ ትግሉን ለማፍርሰ ተልኮ መምጣቱ እና በደብቅ ከመንግሥት ጋር እንደተወያየ ዋዜም የተባለውን ሚዲያ ዋቢ በማድረግ እንደ ማስረጃ ያቀረበው ዋዜማም እስክንድርን የኦሮሙማ ሰላይ እንደሆነ ትግሉን ለማፍርሰ ተልኮ መምጣቱ እና በድብቅም “ከመንግሥት” ጋር ስለ ምን ጉዳይ በሚመለከት እንደተወያየ ሲነጋገሩ የሚያስደምጥ አንዲትም ብጣሽ የተቀዳች የድምጽ ማስረጃ ሳያቀርብ  እንደ ዋቢ ተመርኩዞ እስክንድርን ሰላይ እንደሆነ ትግሉን ለማፍርሰ ተልኮ መምጣቱን ይከሰዋል።

እስኪ ለማስታወሻችሁ የምትሆነውን ለታሪክ የተመዘገበች የማንረሳትን የጥቢቡ ሰለሞን አባባል ተጠቅሞ የፋኖ ትግል ለማፍረስ የመጣ ነው ሲሉ ጥላሸት ሰለሚቀቡት ሰዎች እና መልስ ሳይሰጥ ከመድረክ ሰለመጥፋቱ ከኢትዮ 360 ሃብታሙ አያሌው ጠይቆት የሰጠው መልስ ላስታውሳችሁ።

የእስክንድር ምላሽ ፡ -

እንዲህ ይላል፦

« ከመድረክ ጠፋህ፤ ስምህ ሲጠፋ መልስ አትሰጥም፤ ውሸት ሲደጋገም ዕውነት ይሆናል፤ ሲባል አልሰማህም ውይ? ብለህ ጠይቀኸኛል ፤ ዕውነት ነው ይኼ።የጠቢቡ ንጉሥ ሰለሞንን ዝነኛ ታሪክ አነሳላችኋለሁ። ታሪኩና ምሳሌው”ተረት አይደለም” እውነተኛ ታሪክ ነው። ሁለት ጎረቤታማ ሴቶች ነበሩ። አንድዋ መሃን ነች አንድዋ ወላድ ነች።አንድዋ ስትወልድ መሃንዋ ባለመውለድዋ ትቀናልች።ከመቅናትዋ የተነሳ ልጁ የኔ ነው ትልና ወደ ንጉሥ ሰለሞን ክስ ታቀርባለች። ሁለቱም ይቀርቡና ልጁ የኔ ነው ; የኔ ነው በሚል ነጉሡ ፊት ክርክራቸውን ያስደምጣሉ። ታዲያ በዚህ ጊዜ ነው ንጉሡ ብልህ ነበርና እውነተኛዋን እናት ማን እንድሆነች ለመለየት ሲል ‘እንዲህ ከምትከራከሩ፤ ልጁ በጎራዴ ለሁለት ተከፍሎ ፤ግማሽ፤ግማሽ ውሰዱት፤ ሲል ፍርድ ይሰጣል፡ ታዲያ ያቺ ያልወለደቺው ክፉ ሴት አልወለደቺውምና ልጁ ቢሞትም ግድ አልሰጣትም ነበርና በውሳኔው ተስማምታ ዝም ነው ያለች። የልጁ እውነተኛ እናት ግን የልጀዋን መታረድ አላስችል ብሏት እየጮኸች ‘ልጁ ከሚሞት ለከሳሽዋ እንዲሰጥ ትወስናለች። በዚህ ወቅት ንጉሥ ሰለሞን ጠቢብ አዋቂ ነበርና እውነተኛ እናት ማን እንደሆነች ያወቀበት ስልት ስለነበር፤ "መሞት የለበትም ለጄ ከሚሞት ላልወለደቺዋ መሃንዋ  ትውሰደው ብላ በመወሰነዋ የልጁ እናቱ እስዋ መሆነውን ሰላወቀ፤ ለጁ ለናትየው እንዲሰጥ ወሰነ። በዚህ ጠቢቡ ሰለሞን የታወቀበት አንዱ የፈትሕ መንገድ ነበር።.........

አሁንም በጠቢቡ ሰለሞን የሚመሰል ሕዝብ አለን።” “በልጁ” የሚመሰል “ፋኖ” አለፋኖ ቢፈርስም ይፍረስ እያለ በፈጣሪ ሥም ሳይቀር እየማለ እና እየተገዘተ የውሸት ናዳ የሚያወርድ ወገን አለ። ይህ ወገን በመሃንዋ ክፉ ሴት ይመሰላል። ፋኖ ከሚፈርስ እ ልፍረስ ብሎ ዝምታን የመረጠ ደግሞ አለ።ይህ ደግሞ በወላድዋ እናት ይመሰላል።በ ወለደ ብለው በሚጮሁት ልክ በሬ ወለደ ብለው በሚጮሁት ልክ መስየ ፋኖ እና ሕዝቡ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጌ ‘ፋኖ ከሚፈርስ እኔ ልፍረስ ብያለሁ። አሁንም እላለሁ፡ «በዝምታየ በተቀጣጠለ እሳት ላይ ነዳጅ እንዳይርከፈከፍ አደርጋለሁ።እሳት የሚያድረሰውን ጥፋት ሙሉ ለሙሉ ማስቀረት ባልችልም የጥፋቱን አድማስ እንዳይገፋ አድርጌአለሁ። በዚህ ሂደት የከፈልኩት ዋጋ ለመልካም ስሜ መክሰስ ከሆነ እሰየው ነው የምለው።... ለፋኖ ትግል ሲባል እንኳን ስሜ አካሌም ይፍረስ።እስካሁን ድረስ በዚህ መንፈስ ተጎድቻለሁ ለወደፊቱም በዚሁ እቀጥላለሁ

ሃብታሙ አያሌው፦ንግግሩን በምሃል እንዲህ ሲል እስክንድርን የየይቀዋል፦

«በዚሁ እቀጥላለሁ ስትል፤ አሁንም ከዚህ በኋላ ለሚፈጠሩ ነገሮች ዝምታን እመርጣለሁ የሚል ነው- ወይስ የፋኖን ትግል ብዥታን የሚፈጥሩ ነግሮች ሲከሰቱ ዝምታን በመመረጥ እቀጥላለሁ በሚመስል ትርጉም እንዳይወሰድ ፤ እሱም ከሆነም አለመሆን ግልጽ ብታደረው፦

እስክንድር ለዚህ ሲመልስ፡

ትክክለኛ ጥያቄ ነው። ይህንን ስል፤ ከሚዲያ ሙሉ በሙሉ እርቃለሁ ማለት አይደለም። ተጨባጭ በሆኑ ማብራራት በሚያስፈልጉ ነገሮች አለናገርም ማለት አይደለም።በተለይ ካለሁበት ከተሰጠኝ ሃላፊነት «በውዴታ ግታ» ይህንን አሰምርበታለሁ «በውዴታ ግዴታ»  ከተሰጠኝ ሃላፊነት አኳያ እየወጣሁ የማብራራት ግዴታ አለብኝ።ይህንን ሃላፊነት እወጣለሁ። ሆኖም ግን ቅድም እንዳልኩት « ይፋኖን ትግል ለማፍረስ ሆን ብለው የሐሰት ናዳ ለሚያወርዱ ተከታትይ መልስ አልሰጥም። በታላቁ መጽሐፍ ውስጥ «በስማችወ ይታወቃሉ» የሚል ቃል አለ። ለነዚህ ምን በየ ነው መልስ እመሰጠው። እነዚህ የሐሰት ናዳ የሚያወርዱ አካላት ሕዝቡ እራሱ ያውቃቸዋል።ሕዝብ ጠቢብ ነው፤ ሕዝብን በጠቢቡ ሰለሞን የመሰለኩትም ለዚህ ነው። ሕዝቡ የሚለያቸው በሚናገሩት ሳይሆን በሚያፈሩት ፍሬ፤ በምላሳቸው ሳይሆን በተግባራቸው ይለያቸዋልሕዝብ እንክርዳድ እና ፍሬ ይለያል። ዝምታን በመመረጥ እቀጥላለሁ ያልኩት በዚህ መሠረት ነው እንጂ አስፈላጊ በሆኑ ነግሮች ሲኖሩ ላለማብራራት ከሚዲያ እርቃለሁ ማለቴ አይደለም።ሆኖም ባልደራስ አመራር ሆኜ በየወቅቱ ስቀርብ እንደነበር አልገኝም። አሁን ካለው የጦርነት አውድ ትይዩ እኔ እና አንተ አሁን እየተነጋገርን ያለነው በሳተላይት ነው፤ በስልክ መስመር አይደለም። ይህ መስመር ልክ እንደ ስልክ እንደልብ ከሕዝብና ከሚዲያ እንድንገናኝ አይፈቅድም። አስፈላጊ ሲሆን፤ ወደ ሚዲያ እየመጣሁ መብራራት ያለባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ አብራራለሁ። አመሰገናለሁ ፤ ደህና ሁን።»

ሲል እስክንድር ስለ የሐሰትጋጋታ አመንጪዎች እና አላግባብ በበሬ ወለደ ስሙን የሚያጠለሹት “ስለ ሥም ቀቢዎች” የሰጠው አስገራሚ መልስ ነው።

የእስክንድር ነጋ የነፃነት ታጋዩ የደቡብ አፍሪካው የማንድላ አረአያነት እና መስዋዕትነቱን በአንዳንድ ግብዞች ያበረከተውን አስተዋጽኦ “አመድ አፋሽ” ሆኖ እንዲቀር ስሙን ማጠልሸት የዘወትር ክስተት እየሆነ ከመጣ ቆይቷል። ይህ ባሕል እየሆነ በምሁራን ሳይቀር የተከሰተው የሐበሻ ባሕሪ ፤ የስነ-ባሕሪ ተመራማሪዎች ምንጩ ምን እንደሆነ ሊያጠኑት የሚገባ ነው። ከነዚህ የእስክንድር ስም አጠልሺ መሁራን መካከል በቁንጮ ምሁርነት የምናውቀው የታሪክና የምጣኔ ተመራማሪው አቻምየለህ ታምሩ ነው።

ምክንያቱ ባለታወቀ ምክንያት ከጅምሩ ጀምሮ እስክንድር ነጋን ክፉኛ በበዳ ዓይን መመልከቱ በቅቡ ከትቸበት ጽሑፍ ብቻ ሳይሆን የቆየ ነው። ታስታውሱ እንደሆን የሚከተለው ትችት በአቻምየለህ ላይ 4/15/25 «ብሔርተኝነት የሰው ልጅ የኩፍኝ በሽታ ነው፡ የዘመነ ካሴ ታጣቂ በመምህራንና በፋኖ ታጋዮች ላይ የግድያና የሽብር ድርጊት ሲፈጽሙ የጎጃምና የጎንደር ምሁራን ድጋፍ» ( ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/15/25)

በሚል  ርዕስ ለጥፌ ነበር; ትንሽ ላስታውሳችሁ

«......በታሪክና በበቃ የማሕበራዊ ሙግት ተመራማሪነቱን የተዋጣለት ምክንያታዊ ተሟጋችየነበረውጎጃሜው አቻምየለህ ታምሩ በጎጃሜነቱ ትሥስር ተገፋፈቶ ፈጹም ጎጠኛ፤ ፍጹም ትምክሕተኛ ፤ በዙ ሓጢያት የፈጸመ የፋሺስት ብቅል የሆነውን ዘመነ እና አስረስ ማረ የተባሉ “ቦምቦሊኖዎች” የሚመሩት የጎጃም ፋኖ ታጣቂ ቡድን ደጋፊ ነው።

ይህ ድርጅት በአምሐራ ነፃ አውጭነት ስም ተከናንቦ የጎጃም ተወላጆች የሆኑን በሌላ የፋኖ ድርጅት የተሰማሩትን የፋኖ ታጣቂዎች እና መሪዎችን (እነ ኮለኔል መኳንንትን አስታውሱ) ንጹሃን መምሕራን ጋዜጠኞችን ማፈንና የግድያ ወንጀል ሲፈጽሙ የጎጃም ምሁራን ዝም ማለታቸውና ከዝምታቸውም አልፈውየዚሀ ወመኔታጣቂ ቡድን ደጋፊዎች ሆነው ማየት እጅግ ተገረምኩ።

ታስታወሱ እንደሆን በበርካታ ትችቶቼ የፋኖ ትግል መልሕቁ የሳተ ነው። ባጨሩ በተለያዩ ትዋናዮች ትዕይንት ተጠልፏል ስል ብዙ ሰው ልብ ያለው አልነበረምና ይኼው ዛሬ ብዙ የግድያ ወንጀልና ሽብር እየተፈጸመ የትግሉ መነሻ ስቶ ይገኛል። በየ ነበር። ይህ ሁሉ መዘዝ መነሻ የሆነው “ስሜተኛ-ብሔረተኛነት” ነው።በጎጃሜነት ትሥስር የጎጃም ፋኖ ወረበላ ፋሺስቶችን ከሚደግፉ የጎጃም መሁራኖች ውስጥ አንዱ አቻምየለህ ታምሩ ነው።

« አቻም ወገንተኛ ሆኖ ለአውራጃው/ ለጠ/ግዛት ልጆቹ በመወገን ማስረጃ ማቅረብ በማይችልበት ውንጀላው እስክንድር ነጋን ብቻ ለይቶ ከጀምሩ እስካሁን ድረስ እየቀባ ጥላሸት ቀብቶት መኖሩን ይታወሳል፡

ላስታውሳችሁ፤ እንዲህ እያለ፡

“ቀደም ብሎ እስክንድር ነጋ ላይ አንድ ነገር ቢሰራ ኖሮ በአርበኛ አሰግድ መኮንን ላይ የደረሰው መከራ ላይደርስ ይችል ነበር” በማለት ምስኪኑን እስክንድርን ይወነጅለዋል፡፡

“አንድ ነገረ ቢሰራ ኖሮ” የሚለው እስክንድርን “በሞት” ወይስ  ከትግሉ ማስወገድ? አልገባኝም! በማለት ጠይቄ ነበር።

ሆኖም አሁን አሁን ሳስበው “አንድ ነገረ ቢሰራ ኖሮ” ሲል እስክንድር መገደል ነበረበት ማለቱ እንደሆነ አሁን ተረዳሁት። በዚሁ “አንድ ነገረ ቢሰራ ኖሮ” ቁጭቱ ብቻ ሳይወሰን “አንድ ነገረ ቢሰራ ኖሮ” እያለ ያለው አቻምየለሀ ታምሩ እሰክንደርን ከኦሮሙማ ሥርዓት የተላከ ሰላይ ነው ሲል ለራሱ አሳምኖ እኛንም እንድናምነው በጽሑፉ ነግሮናል እና “የእስክንድር ማሰወገጃው መንገደ መግደል ነው” “መረሸን ነው” የሚል ውሳኔ ከያዘ ቆይታል ማለት ነው። “እስክንድርን መረሸን ነው” የሚል አዝማሚያ ስትሰሙ ምን የሰማችኋል። እስክንድረን መግደል? ያስደነግጣል። “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ንአምን በአሃዱ ወሰለስቱ” ያሰኛል።

የአቻምየለህ ታምሩእስክንድር ያለው የመረረ ጥላቻው በዚያ አላበቃም፡

 <<የኋላ ታሪኩና በአማራው የኅልውና ተጋድሎ ውስጥ ሊያራምደው በሚሞክረው ጸረ አማራ እሳቤው>>

በማለትም ይወነጅለዋል፡፡

የእስክንድር ጸረ አማራ የኅልውና  የኋላ ታሪኩ አቻምየለህ ማስረጃ\አላቀረበም አቻምየለህ  የአማራ ተቆርቋሪ እስክንድር ነጋ ግን ጸረ አማራ” የሚሆንበት በታአምርም መባል ያልነበረበት ጮርቃነት ነው።

 አቻምየለህ ከትልቁ ኢትዮጵያዊ ማማ ወርዶ ወደ ጠባብ ጎጃምነት ወርዷል።ለእነ ዘመነ አጉራዘለል ባሕሪ ጣራ መንካት የእነ አቻም ድርሻ አለው።<<ለአማራ አሳቢና እምባ አቅራሪ እሰክንድር ሳይሆን  እኔ ነኝ የአማራ አሳቢና ተከላካይ እኔና ዘመነ ካሴ ነን >> በሚል ውስጠ ገለጻ እስክንድር የአማራ ሕልውናን ለማጥፋት አስቦበት-የመጣ በማለት ይወነጅለዋል፡፡

አቻም ከላይ እንደተመለከታችሁት አማራ ማለት እኛ እንጂ እስክንድር የአማራን ሕልውና በመጻረር የሚታወቅ<<የኋላ-ታሪኩ>> -----ሳይመረመር የተቀላቀለን የሚለው የአቻምየለህ ጽሑፍ የሚያሳየን አቻምየለህ ትምክሕተኛ ወደ-ሆነው ወደ ማፊያዊና ማፈሪያ ወደ ሆነው ካምፕ ተፈጥፍጦ ሊወድቅ እንጥልጥል ላይ እንደሆነ ነው (if not already) የታዘብኩት። ያሳዝናል።

አቻምየለህ አልበቃ ብሎትተፈራ ማሞ የተባለየወያጡት እየጠባ ያደገ ሻዕቢያቱን እና ወያኔነቱን በግልጽ የነገረን ተፈራ ማሞንየአምሐራ መሪ ይሁን ብሎ ለፋኖዎቹ ሹመት ያቀረበላቸው ሰው ነው

ተፈራ ማሞ ማለት አምሐራ እየመጣበት ያለው ጉድ 16ኛው / ከበባና አደጋ ነው ብሎ ካሕናቱም ምሑራቱንም ለክቡር መሰዋእትነት እንዲዘጋጁ ጥሪ ያደረገ የዛሬ ፋኖ ችግኝ የተከለ ጀግናው አሳምነው ጽጌን  የሕሊና በሽተኛ  ብድ ሰው በማለት ጀግና አዋራጅ ለሆነው አፍቃሬ ሻዕቢያው ተፈራ ማሞን የአምሐራን ፖለቲካና ወታደራዊ መሪ እንዲሆን ዘመቻ አስፈጻሚ ሆኖ ያየነው ጎጃም ያበቀለቺው ምሁር ነው።

ተፈራ ማለት የወያኔና የሻዕቢያ ታጣቂ ቡችላ የነበረ ከሻዕቢያና ከወያኔ ታጣቂዎች ጋር ሆኖ መንገድ እየመራ ከወሎ እስከ አዲስ አበባ ድረስ አገራቸውን ሲከላከሉ የነበሩት መሁራንና አምሐራ ገበሬዎች እያደነ እንዲሁም የእምየ ኢትዮጵያ ወታደሮችን ሲገድል የነበረ መጨረሻም እነዚያ ብርቅየ ግፉአን ከነ ቤተሰቦቻቸው በረንዳ አደር ሲሆኑ ለባነዳነቱ የነሱን ቦታ የተሰጠው” “ለባንዳነቱ ያልተጸጸት ባንዳ ነው ተፈራ ማሞ ማለት።

የአቻምየለህ ብርቀየ መሪ ተፈራ ማሞ የፀረ አምሐራው የኢሳያስ አፈወርቂ አድናቂና ከማድነቁ የተነሳ በቅርቡ ከትግራይ እና  ከኤርትራ ሕዝብ በፊት እነሱን ላመከላከል “የአምሐራ ማሕበረሰብ የሞት መስዋዕት መክፈል እንዳለበት ለታጣቂ ተመራቂዎች በግሃድ ሲሰብክ ሰምተናል። ይህ ብቻ ሳይሆን ፤ ተጠይቆም ይህንኑ “ወኪልነቱን” በኩራት የሚያምንበት እንደሆነ ጥረኛነቱን ነግሮናል።

ተፈራ ማለት ወደ ውጭ አገር ለመሸሽ እግሩ ሳይታመም ታመምኩኝ ብሎ የሚወሰልት ሲጨንቀው ወደ ፋኖ የተቀላቀለ፤ሚስቱን መቆጣጠር የማይችል አፍቃሬ ሻቢያነቱ/አፈቃሬ  ኢሳያስነቱን ለመግለጽ አምሐራ ሕልውናውን ለመጠበቅ ከሻቢያ ጋር "ማበር" እንዳለበት በተመስገን ደሳለኝ ፈትሕ” መጽሔትም ላይ በገለጸውም ግልጽ አድርጓል። ይህም አንድም በቅጥረኛነቱ፤ አለያም ከፋኖ ጋር ካለተማማ ወደ ኢሳያስ እጁ ሰጥቶ በዚያው ወደ ውጭ አገር ለመሸሽ የተጠቀመበት ሌላው ስልቱ ነው።

እንግዲህ አቻምየለህ የህንን  ባንዳነቱን በገሃድ ያወጀን  “በታሪከ የተዘገበውን ባንዳው ተፈራ ማሞን ነው የአማራ ሕዝብ የፋኖ ተዋጊ መሪ ሆኖ እንዲሾምለት የጠየቀው ። የአቻምየለሀ  ሁለተኛው የሕሊና ከሳት ከዚህ ይጀምራል።

የጎጃምና የጎንደር ምሁራን ምልከት መሪያችን የሚሉት የሻቢያው ግርፍዘመነ ካሴ ብቻ አይደለም፤ ተፈራ ማሞ የተባለ ማፈርያም ጨምሩላቸው። ተፈራ ማሞን ስታነሱ የተፈራ ተጻባኢ የነበረው ሥርዓቱ የትም እንደማያደርስ ተሎ የነቃው ጀግናው አሳምነውን አስታውሱ።

አብይ አሕመድ የሚያስተላልፋቸውን ጸረ አምሐራ ክንዋኔዎችን ለማስፈጸም አስር ጊዜ  ስብሰባ ሲጠሩትና ሲወተውቱት የነበሩት ከኦሮሙማ ፋሺስቶች ጋር ጠጅ ለማንቃረር ያደሩ ቅጥረኛ ባንዳዊያን ብአዲኖችን ያጋደመ የወንዶች ልክ በአሳምነው  ገናናነትና ምጥቀትነት የሚቀና ቀናተኛና ሐሜተኛ ሰው ተፈራ ማሞን ለማንገሥ እያነፈነፉ ዘመቻ ማቀንቀን የሚገርም መስተንክር-ነው።

«የጎጎ ምሁራን» የጎጃምና የጎንደር ሁራን ለምን እንደዘቀጡ አልገባኝም። አቻምየለህ አስገራሚ መንሸራተት የወያኔ እና የሻዕቢያ ዋና አቃጣሪው ባሕላዊ ጀነራል ስለ ተፈራ ማሞ ምን እንዳለ ያላነበባችሁ ሰለምትኖሩ ቃል በቃል ምን እንዳለ ባለ «አራት ዓይን» እያለ ከዚህ ሁሉ አማራ ልዩ አፈጣጠር የተቸረው ባለ አራት ዓይናማው ተፈራ ማሞን እንዲህ እያለ ያሞካሸዋል፤

«አማራ በዚህ ወቅት የሚያስፈልገው መሪ እንደ ተፈራ ማሞ አይነት በአማራ ላይ የተጋረጠውን የኅልውና አደጋ እንደ እጁ መዳፍ አብጠርጥሮ  የሚያውቅ አራት ዐይና ብቻ ነው

በማለት በሚያስቅና በሚያስደነግጥ አባባል ሐሜተኛውና ስም አጥፊውን ተፈራ ማሞ“እስክንድር ኢትዮጵያዊ እንጂ አማራ አየደለም” በማለት ጸረ ኢትዮጵያነቱን የገለጸ፤ የሻዕቢያ ወያኔ ተቀጣሪ ፤ አማራ እንጂ ኢትዮጰያዊ መሆን ጸረ አማራነት ማለት እንደሆነ «ጸረ ኢትዮጰያ እና የሰው ልጅ ጸር የሆነውን አከራሪ በሔረተኛ ፖለቲካ የሚክተል» ተፈራ ማሞን የአማራ መሪያችን ነው ይምራን ብሎ መሪ አድርጎ ሹሞታል አቻምየለህ ታምሩ ሳይሸማቀቅ። ዝገርም እዩ!! አለ ትግሬ።

እነዚህ ምሁራን ምን አዚም ደዞረባቸው አላውቅም። እንዲህ ያሉ በተረ-ቀላሎች (Small men) እንዲህ  ሊያሞካሹትና መሪያችን ነህ ብለው ሰማየ ሰማያት የተሰቀሉትም ይሁኑ ተሰቃዮች ምን እንደሚገፋፋቸው አልገባህ አለኝ።

ለ እስክንድር ነጋ

በቅርቡ በDecember 4/2025 አቻምየለህ  “በፌስ-ቡኩ” ላይ “ለሐተታው ርዕስ” ባላደረገበት ጽሑፉ ላይ  «ከግደያ ለማለጥ ተገፈቶ ወደ አፓርታይዱ ሥርዓት ወደ ኦሮሙማው አብይ አሕመድ ሮጦ እጁን ሰለ ሰጠው ማስረሻ ሰጤ» በተቸበት ጽሑፉ ላይ  አቻምየለህ እስክንድር ነጋ እና የድርጅቱ መሪዎች እንዲህ ሲል ይከሳቸዋል።

«እስክንድር ነጋ ባለፈው አመት በጥር ወር 'የመንግሥት አካል የለበትም' ያለው ከነ ኃይሉ ጎንፋው የአፍሪካ ኅብረትና ከነ ወርቅነህ ገበየሁ ኢጋድ ጋር የጀመረው "ውይይት" ዛሬ "የሰላም ስምምነት" በማድረግ ተጠናቋል!» ይላል አቻም።

‘የሰላም ድርድር’ ተብየው እስክንድር ነጋ የጀመረው ልክ እንደ ማስረሻ ሰጤ እጅ ሰጥተን ወደ አዲስ አበባ እንግባ የሚል ድርድርም ሆነ ስምምነት እንደተጠናቀቀ አልሰማንም አላየንም። አንድ ሰው ስለ ከዳ”ስምምነት” ሰለተባለው  ድርጅታችንን አያውቀውም አይወክልም ሲል እስክንድር በአንደበቱ ሚዲያ ላይ ቅርቦ ግልጽ አድርጓል። ከፈረሱ አፍ ማለት ነው። ታዲያ የአቻምየለህ መቀደድ ትርጉሙ ስም ማጥፋት ካለሆነ ምን ይፈይዳል። በማንኛውም ባገራችን ውስጥ ካየናቸው የሽምቅ ተዋጊዎች ታሪክ ያየነው አንድ ሁለት ሰው ከአመራሩ ወጥተው ለመንግሥት እጅ ሲሰጡ አይተናል። ያ ግን የድርጀቱ ስምምነትን ወይንም ስለ መፍረስ አይገልጽም።

አቻም በመቀጠል

«እስክንደር ነጋ ያኔ የጀመረው ጉድ ሲጋለጥበት ለማስተባበል በሰጠው መግለጫ ከአፍሪካ ኅብረትና ከኢጋድ ጋር ባደረገው ንግግር “የመንግሥት አካል የለበትም” የሚል ማስተባበያ ሰጥቶ ነበር። ከታች ባጋራሁትና በወቅቱ በለጠፍኹት አስተያየት ላይ እንደሚታየው ግን እስክንድር ነጋ “የመንግሥት አካል የለበትም” ያለው "ውይይት" የተደረገው ከኦሕዴድ ወኦነጎቹ ከወርቅነህ ገበዬሁና ከኃይሉ ጉንፋ ጋር የተደረገውን አፈርሳታ ነበር።» ይላል።

አፈርሳታ የሚለው ቃል በጎጃም አማርኛ ምን ለማለት እንደሆነ ባላውቅም፤ አፈርሳታ የማውቀው  እኛ ትግሬዎች “አውጫጭ” የምንለውን ነው። ይህም፤ አንድ ሰው ባንድ ገጠር ወንጀል ፈጽሞ ሳይታወቅ ሲቀር፤ ሰውየውን ለይቶ ለማግኘት የገጥሩ ማሕብረሰብ ሰብሰቦ ሙሉውን ቀን ሳይበላ ሳይጠጣ ፀሐይ ላይ አስቀምጦ ሲሰለቸው ‘ወንጀለኛውን” ጠቁሞ ለማውጣት እንዲመች የሚደረግ የመንግሥት የምርመራ ሥልት ነው። ታዲያ አቻምየለህ እዚህ ላይ ሰለተጠቀመበት “አፈርሳታ” የሚለው ቃል ምን እነደሆነ አልገባኝም። ድርድር ነው ይልና እንደገና አፈርሳታ ነው የላል ያንን ለአንባቢ ፍርድ ልተወው።  

እንዲህም ይላለ።

«ማስረሻ ሰጤ የሚባለውን ነውረኛ ግለሰብ ብቻ የጦስ ዶሮ በማድረግ እስክንድር ነጋ፣ ፈንታሁን ሙሀቤ፣ እያሱ አባተ፣ ጌታ አስራደ ወዘተ የመሳሰሉ ወስላቶችን ንጹህ ለማረግ ነው።»  ይላል።

እነዚህ ወስላቶች ላቸው  ሰዎች እስካሁን ድረስ እጃቸው ሲሰጡ አልሰማንም፤ አላየንም። እጃቸው እሰካልሰጡ ድረስና አሁንም ትግል ላይ እስካሉ ድረስ የአቻምየለህ ‹አሉባልታ› ፈሬ ከርሲኪ ነው።

አያይዞም እንዲህ ይላል፤-

«እስክንድር ነጋ የተገናኘው የዐቢይ አሕመድ ሹሙ ወርቅነህ ገበዬሁ ከሚመራው ኢጋድና  ሌላኛው የዐቢይ ተሿሚ ኃይሉ ጎንፋ ከሚዘውረው የአፍሪካ ኅብረት የጸጥታ ክፍል ጋር ነው።»ይላል

 ኢጋድ የተባለው የፍሪካ ሕብረት አካል የሚመሩት ከላይ የተጠሱት ሰዎች ቢሆኑም የንግግሩ ጭብጥ ወሳኝነት እንጂ ከተጠቀሱት ሰዎች ጋር በመነጋገራቸው የሚያስጮህ አይደም። ለምሳሌ የአፍሪካ ሕብረት መሪ ተራው  ለኢትዮጵያ ደርሶ “አብይ አሕመድ” ሊቀመንበር ሆኖ ቢሾም፡ አብይ አሕመድ ከሚመራው የአፍሪካ ሕብረት ጋር በምንም መልኩ “አልነጋገርም” ማለት አለበት? ምን እሚት ቂልነት ነው። ጡ መርሆአቸው ለተደራዳሪው አስረከቡ ወይስ በመነሻ መሰምራቸው ነጥብ ላይ “ጸኑ” የሚለው ነው ዋናው መተኮር ያለበት

አቶ አቻምየለህ ቀጥሎም እንዲህ ይላል፦

«ዋዜማ በውይይት ተብዮው የተሳተፉን አካላት አናግሮ  ስለ ውይይት ተብዮው የዘገበውን ይህንን ትር በመጫን ማንበብ ይቻላል።» ሲል ለአንባቢዎቹ የጠቁማል።

ለአቻምየለህ ምን የሆነው ዋዜማ የተባለው ሚዲያ ግን እሱም እንደማንኛውም ሰው ፤ “ምንጭ” እያለ ከሚገልጸው ከሁለተኛ ወገን እንደሰማ እንጂ የተነጋገሩበት የክሩ ድምፅ ቅጂ አላቀረበም

ዋዜማ እዲህ ይላል።

«በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ በኩል የተናጠል ንግግሩ የክልሉን ግጭት ማስቆም ይችል እንደሆነ ገምግሞ ስለ ቀጣይ ድርድር ውሳኔ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ሰምተናል።» ሰምተናል! ሰምተናል! ሰምተናል! እሱም ልክ እንደኛ ነው የሰማው። እሱ የተካፈለበትና የነበረበት ሳይሆን የሰማውን በፈንታው ለኛም ለአቻምየለህንም ያሰማው «በስማ በለው ሰማን” የሚለው ነው።

አቻምየለህ በመጨረሻም የጎጃሙ «ዘመነ ካሴ ድርጅት» ለዘልዓለም ይኑር ያለበትን በሸዋዎቹ በነ መከታው እና በእነ እስክንድር ነጋ የተመሰረተው የሸዋው አፍሕድ ን በጠመንጃ ተጨፍጨፎ (“ተወዶ” ይላል በራሱ ቃል ሲጠቀም)  የጎጃም ወገንተኛነቱን በግልጽ ያሳየበትን እንመልከት፡

እንዲህ ይላል አቻም፦

«አፋሕድ የሚባለው የቁጭ በሉዎች ድርጅት መወገድ ያለበትና ልክ እንደ ብአዴን ሁሉ የአማራ ሕዝብ አካል ሳይሆን ብል[ፅ]ግና የክፉ ቀን ምርኩዝ የሆነ ጭንጋፍ ድርጅት መሆኑ መታወቅ አለበት።» ሲል “አፍሕድ” በጠመንጃ ተጨፈጨፎ መወገድ እንዳለበት ምክንያቱን ሲያስቀምጥ ፤

1ኛ - ውግያ ውስጥ የማይሳተፍ ቁጭ በሎ የሚውል ስለሆነ፤

2ኛ -የአማራ ሕዝብ አካል ሳይሆን የኦሮሞዎች (ኦሮሙማ ብል[ፅ]ግና) የክፉ ቀን ምርኩዝ የሆነ በፋኖ ሽፋን የተደራጀ አማራ ያለሆነ ‘’ጭንጋፍ ድርጅት ስለሆነ “መወገድ” አለበት ሲል እነ እስክንድና መከታው ማሞ ከመላ ሺዎች ታጣቂዎቻቸው ተደምሥሠው በምትካቸው  የፋኖ ድርጅት የአቻምየለሀ አርአያዎች  የሆኑት “የአፋብሃ መሪዎች” እነ ዘመነ እና የሻዕቢያው ተቀጣሪ እነ ተፈራ ማሞ የሚመሩት ድርጅት ብቸኛ የአማራ ሕዝብ ነፃ አውጪዎች እንዲሆኑና እነዚያ ግን በጠመንጃ ሃይል እንዲወገዱ ጥሪ አቅርቧል።

ይህ እየተጓዘበት ያለው የተጠናወተው የወንዝ ልጅነት ተላላፊ በሽታ ተሎ ካልዳነለት የአቻምየለሀ ታምሩ ብሩሕ  ሕሊና መክሳት እያሳሰበኝ መጥቷል። በከፍል 2 ወደ ሃብታሙ አያሌው «ሰንከልከል» (መወላገድ) እመለሳለሁ። ይቀጥላል..

ጌታቸው ረዳ 

Ethiopian Semay