የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ምሬቶችና እውነታዎች
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay) 10/23/24
ወደ ትችቴ ከመግባቴ በፊት ይህንን ልበል፡
ባለፈው ሰሞን ፕሮፌሰር ሃብታሙ <<አለም አቀፍ የፋኖ አስተባባሪ ኮሚቴ>> በተባለው የነዘመነ ካሴ
ደጋፊ ሚዲያ ቀርቦ በልደቱ ቤተሰብና ንብረት ላይ የተናገረበት ነጥብ በማውገዝ መተቸቴን ይተወሳል። አንዳንድ ሰዎች በግል የውስጥ
መልዕክት ሲልኩልኝ የባለፈው ሳምንት በፕሮፌሰሩ ላይ መተቸቴ ፕሮፌሰሩ እኔ አብዝቼ የምነቅፈውን የጎጃም አማራ ፋኖ መሪ የዘመነ ካሴ
ደጋፊና በውጭ አገር አስተባባሪ አባል ስለሆነ ያንን ለመቀጥቀጥ እንደተጠቀምኩበት ጽፈውልኛል።ይህ ግን እውነትነት የለውም።
ከፕሮፌሰሩ ይልቅ ልደቱ አያሌውን በተደጋጋሚ ለብዙ አመታት ተቺቼዋለሁና በመግቢያው ላይ ታስታውሱ እንደሆነ፤ ያልኩት ነጥብ “ፕሮፌሰሩን
የተቃወምኩት በፕሪንስፕል” አንደሆነ ገልጫለሁ። ስለዚህ በዚህ እንዲያዝልኝ።
ዛሬ ደግሞ የማቀርበው ለፕሮፌሰሩ ድጋፍና ያሰማን ብሶት መደመጥ እንዳለበትና እውነተኛ ምሬት መሆኑን በድጋፍ ስመጣ የዘመነ ካሴ ደጋፊ መሆኑን እያወቅኩም ቢሆን ፕሮፌሰሩ ስለ አምሐራ ሕዝብ ስቃይ፤ግፍ
ብሶት፤ ታሪክና ስለ ኦሮሞዎች ወረራ አስመልክቶ የጠቀሰው እውነትነት ስላለው በዚህ ዛሬ እተቻለሁ።
ፕሮፌሰሩ ብዙ አውነታዎች አሉት። ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ከሺዎቹ አምሐራ ምሁራን አንዱ ሲሆን፤ እንደ አምሐራነቱ በወላጆቹና
ቤተሰቦቹ ላይ እንዲሁም ምንም ፖለቲካ በማያውቅ አምሐራ ገበሬና ሰራተኛ ሕዝብ በአክራሪና ተገንጣይ ኦሮሞ ፖለቲከኞችና በአክራሪ
ውሃቢ ኦሮሞና በአክራሪ ፕሮተስታንት ቡድንና ድርጅቶች ለብዙ አመታት አንዳንዱም ወደ 400 አመታት የሚወስድ ጥቃት በኢትዮጵያና
በአምሐራ እንዲሁም በኦርቶዶክስ አማኝ ሕዝብ የደረሰና እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋና ግፍ በምሬት ለማስረዳት ሞክሯል።
ይህንን ለማስረዳት በሚሞክርበት ጊዜ ሰዎች ሰሚ ሲያጡ ምሬታቸው ከልክ ሲያልፍ ፤ በቃኝ የሚሉበት ወቅትና ስሜታቸው ሲገነፍል
አላስፈላጊ ንግግር ላለመናገር ቁጣቸውን መቆጣጠር ከምሁራን የሚጠበቅ ነው። ለዚህ ነው ስለ ልደቱ ያነሳው ነጥብ የተቃወምኩት።
ስለሆነም ፕሮፌሰሩ ልክ እንደ ኦነጎቹ እሱም ሳይሸሽግ ለሚያደርጉት የዘር ማጥፋት ወንጀል መልሱ ነግሯቸዋል። ለኦሮሞዎች ኢትዮጵያ ባዕድ ናት፤ ኢትዮጵያ በኦሮሞዎች መልክ እንሰራታለን፤
3000 አመት እንገዛችኋለን፤ ኢትዮጵያ አቢሲኒያዎች (በተለይ ነፍጠኞች፤ ምኒልኮች) የሰርዋት አገር ናትና አገራችን አይደለችም
ብላችሁ ሕዝባችንን ከመጨፍጨፍ አቁማችሁ ባዕድ ነን የሚለው ስሜታችሁን ይዛችሁ ወደ መረጣችሁበት ጥንታዊ አገራችሁ አቅኑ፡ ሲል እቅጩን
ተናግሯል።
ለምን እንደዚያ አለ የሚል ጠያቂ ተቃዋሚም ደጋፊም ሊኖር ነው። ግን እርሱ ያለው እነሱ በሚሄዱበት መንገድ በመመልከት
የሰጠው መልስ ነው። ብዙ ታገስናቸው፤ ካሁን አሁን ይሻላቸው ይሆን፤ እየተባለ በብዙ አምሐራ ሕዝብና ኢትዮጵያዊያን ብዙ ተዘመረላቸው፤ ተቀደሰላቸው፤ ዕልልታ ተቸራቸው ድጋፍ ተሰጣቸው፤ መልሳቸው
ግን አምሐራን ቤተ ክርስትያነትን፤ ቅርሶችን
ማውደም ሆነ፡
የሚያወድሙት ሁሉ የኛ ነው ስለማይሉት ፤ ባዕዳዊ ስሜት ስለሚሰማቸው ሥልጣን ይዘውም ይሁን ሥልጣን አይያዙ መፈክራቸው “አገራችን
አይደለም” ወይንም “በመስፋፋትና በጭፍለቃ ስሜት ‘’ሁሉም ኬኛ” የሚል ስሜት ስላላቸው ልክ 400 አመት በፊት ያደረጉት ነባሩን ሕዝብ በመዋጥ ዛሬም
ያንን እየደገሙት እያየን ነው፡ ይህ እኛ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም ስሜታቸው እነሱን ለማቀፍና ለማብረድም የሕዝቡን ዕልልታ፤ድጋፍ
(ደማችሁ ደማችን ነው ተዋህደናል) የሚል ግጥምና ዝማሬ ቢደረግላቸውም ከምንም አይቆርጡትምና እውነቱን መነገር አለበት። ነው የፕሮፌሰሩ
ክርክር።
በአጽንኦት የሚናገረው ፤ አሁን ምሬታችን የናንተ ያህል
ግልጽና ጣራ ስለደረሰ ፤ ኢትዮጵያ አገራችን አይደለችም ካለችሁ፤ አምሐራ ጠላታችን ነው እያለችሁ ከተከለለው አፓርታይዳዊ ኦሮሚያ
ከሚባለው የ27 አመት አዲስ ስምና ክልል አምሐራ
ውጣልኝ እያላችሁ ሕዝባችንን ከመጨፍጨፍ ስላልቦዘናችሁ፤ ካሁን በኋላ ይለይለት ግልጽ ግልጹን መናገር ከተባለ እናንተም
ወደ ጥንታዊ ቦታችሁ ተመልሳችሁ በመሄድ አገራችን ወደ እምትሉት አቅኑ። ሲል ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ምሬቱን እንደ እነሱ በግልጽ ሳይደብቅ ተናግሯል።
ነፃነታችንን አክብሩልን፤ ሁሉም በየስሜቱ ለመድረክና ለውይይት ይቅረብ ካላችሁ የኔ መስመር ይህ ነው፤ ነው የፕሮፌሰሩ
ሙግት። ውደዱት አትውደዱት ግልጽ ነው። ዝምታ ብዙ አመታት ውጦን ነበር አሁን ግን መልስ መስጠት ጊዜው ነው። እንለያይ ካላችሁም በዚህ ነው የምንለያው የሚል ነው የዶክተር ሃብታሙ መስመር።
አሁን ያሉት ኦሮሞዎች የባዕድ ሰሜት አሳድረዋል፡ ስለሆነም አገራችን ነች ብለው ስለማይቀበልዋት አምሐራውና ኦርቶዶክስ እንደሁም ያለፉት የነገሥታት ዘውድና አስተዋጽኦ በክፉ አይን የሚያዩ ስለሆኑ ሕዝባችንም በየሰዓቱ ሌትም ቀንም ያለ ዕረፍት እየጨፈጨፉት ስለሆነ አብሮነት ችግር ላይ ወድቋል ፤ በግልጽ እንነጋገር ነው የፕሮፌሰሩ ሙግት። ትክክል ነው። በግልጽ እንወያይ። መደባበቅ ዛሬውኑ መብቃት አለበት። የደረሰው እና እየደረሰ ያለው ውድመትና ጭፍጨፋ ዓይን ገላጭ ነው።
አሁን ያሉት ኦሮሞዎች ሃገራዊ ባሕልና ሃገራዊ እሴት የሚጻረሩ ናቸው። በአክራሪ ውሃቢ እስላም ፤ በአክራሪ ፕሮቴስታንት
በግምባር ቀደም ጸረ ኢትዮጵያዊ ነባር ባሕል፤ ጸረ አምሐራና ጸረ ኦርቶዶክስ በሆነው ኦነግ የተሰበኩ አዲስ ትወልድ ኦሮሞዎች ብዛት ያለቸው ስለሆኑ፤ በተሰበኩበት ተልዕኮ መሰረት አምሐራና ኦርቶዶክስ አንዲሁም አምሐራ የሆነ እስላም ላይ ሳይቀር በተጠቀሱት
ክፍሎች ለዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ጥቃት እንዲጋለጡ ተደርጓል፡
እውነታውን እንነጋገር። አብዛኛው ኦሮሞ እየተከተለውና እየተቀበለው ያለው አክራሪ ውሃቢያና አክራሪ ፕሮተስታንትና ኦነጋዊው የፖለቲካ እሴት፤ የሐሰት ትርክቱ ተቀብሎታል። ኦነጋዊያን ከአክሱም አልፈው መላው የሱዳንና የግብፅ ሥልጣኔ የኛ ነው ብለዋል። ኦነግም ሆኑ ወያኔዎች መገንጠል የኢትዮጵያ ማፍረሻ ከአምሐራ ጭቆና ነፃ ማስገኛ መንገድ ነው ብለው ሃገር ለማፍረስ የመገንጠል ሕገመንግሥት ቀርጾው አሁንም አፓርታይዱ ሕገ መንግሥት ህያው ሆኖ አለ። ፕሮፌሰሩ የሚለው፤ እንግዲህ መገንጠል ከፈለጋችሁና አትኑሩ ካላችሁን አሁን ያለው ከሕግ ውጭ በአመጽና በሴራ የያዛችሁት ሰፊ ክልል የናንተ ስላለሆነ ከ16ኛው ክ/ዘመን በፊት ወደ ነበረው ወደ ጥንት ቦታችሁ ወደ ኋላ አፈግፍጉ፤ ነው እያላቸው ያለው። እውነት ነው።
አሁን ያለው ቦታ ከሕግ ውጭ ከወያኔ ጋር ተመሳጥረው ያካለሉት አፓርታይዳዊ የስልቀጣ እርምጃ ነው። ሌለው ዜጋ መብት
የለውም። ባለቤቶቹ እነሱ ናቸው። ለዚህ ነው “ውጣልኝ” እያሉ ዘፈን ቀርጸው ወጣቱን እያስጨፈሩት ያሉት። ከዚህ አልፎ ሰሞኑን ደግሞ
ከ8 ሚሊዮን በላይ ኦሮሞዎች እየተደመጠ ያለ Warra Boole (ዋራ ቦሌ አራት ኪሎ) የሚል “ሶና ታከለ” የተባለ አክራራ ኦሮሞ ዘፋኝ “አምሓራ የተባለቺው” ፍቺ በሌለው ሕልም 4 ኪሎ ተመኝታ ኦሮሞ ባለቤቱ ባለባት አዲስ አባባ ባለቤት ለመሆን ትፈልጋለች”
እንደሚል ኦሮምኛ አዋቂዎች ተርጉመውታል።
ከዚህ አልፎ “ኦሮሚያ ክልል” የተባለው አፓርታይዳዊው ክልል ያለምንም ማስረጃ
የሃሰት ትርክቱን ለወጣት ኦሮሞዎች ሲቀሰቅስ የጻፈውን ልጥቀስ ፤ እንዲህ ይላል፡-
<< ጥቂት የነበሩ አዲስ መጤዎች (ያሁኖቹ አምሐራዎችና ትግሬዎች) ከአገሬው ተወላጅ ጋር ተቀላቀሉ.... የኦሮሞ
ክልል በ4ኛ ክ/ዘመን በአክሱማዊው ኢዛና ተገፍተው መሬታቸው በሴም ቋንቋ ተናጋሪዎች ተነጠቀ....>>
ይላል፡ የአብይ አሕመድ ኦሮሚያ ክልል (የኦሮሞ ታሪክ
ከ16ኘው መ/ክ/ዘ ከሚል የሃሰት ትርክታቸው ገፅ 24-25) :- ምንጭ ባንተአምላክ አያሌው።
ይህንን እንጠይቅ፦ የአክሱም ሥልጣኔ የኦሮሞዎች ከነበረና ኦሮሞዎች አክሱም ውስጥ ከነበሩ፤ እንዴት ነው ንጉሠ ነገሥት
ኢዛና “ኦሮሚያ ክልል” የሚባል ክልል ሳይኖር ወደ ክልላቸው መጥቶ አባረረን የሚሉት?
ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ የሚለው አውነትነት አለው። ኦሮሞዎች ከብት አርቢዎች እንደነበሩና ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ እንጂ
ከተማ ቆርቁረው ቤተጸሎት ገንብተው ህንጻዎች አንጸው፤ ፊደል ቀርጸው አያውቁም። የኛ ግንብ ፤ የኛ ከተማ፤ የኛ ፊደል የሚሉት አንዲትም
ነገር የላቸውም። ይላል። ልክ ነው።
ዐምሐራ ፡ ማህበራዊ ምንነቱና ተግዳሮቱ
የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌውም ፤እንዲህ ይላል፡
<< ኦሮሞ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ቋሚ ከተማ እንኳ አልነበረውም፡ ኦነጋውያን እንዳዉም ከተሞችን የቆረቆሩ
አጼ ምኒልክን ከተማን በሃገራችን ሠሩብን እያሉ ሲከሱ መስማት ያሳዝናል። የኦሮሞ ሕዝብ በሰሜን ኢትዮጵያ አክሱም ፤ በሱዳንና በግብፅ
ለተገነቡ ታላላቅ ከተሞችና ሥልጣኔዎች ባለቤት ከሆነ ቢያንስ ሃይልንና
የበላይነትን ባገኙባቸው በ16ኘው መቶ ክፍለ ዘመን ለምን ራሱን የሚገልጥ አንድ የሥልጣኔ አሻራ አላሳረፈም?>>
ይላል ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው። (ሰረዝ የተጨመረ)
በዚህ መልክ ተገቢው ጥያቄ በፕሮፌሰር ሃብታሙም ሆነ በባንተአምላክ የተጠቀሰው ሃቅ ነው:: ታዲያ ከግራኝ አሕመድ ወረራ በኋላ ወደ መሃል ሃገር የተስፋፋው ኦሮሞ ተገንብቶ ያገኛቸውን ሥልጣኔዎችና ቅርሶች እንዲሁም ከተሞችን ከማድነቅና ከማክበር ይልቅ ማውደም እና የባዕድነት ስሜት ለምን ተሰማቸው ብሎ መጠየቅ አግባብ ነው።
ውሃቢ እስላም ኦሮሞዎችም ሆኑ ኦነጎችን እንደ ሶማሌዎች እንደ ናይጄሪያዎችና ኬኒያዎች ለመላው ኦሮሞ ያስታጠቁት ዐረብኛ ልሳንና የላቲን ፊደል የማንነት መለያቸው የማድረግ ጉድ ስትመለከቱ ሃገራዊ ፊደል የሆነውን ግዕዝም ሆነ አምሐርኛን ከመጥላትና የባዕድነት ስሜት ያመነጨው ነው።
ግዕዝ ልንሰማው የማይገባ ልሳን ነው ብለው በላቲን ፊደል በተጻፈ በኦሮምኛ ይቀድሳሉ ፤ ይዘምራሉ። የሚያሳዝነው ይላል ደራሲ ባንተአምላክ:-
<<አማርኛ የቅኝ ግዛት ቋንቋ ነው፤ግዕዝ ልንሰማው የማይገባ ልሳን ነው የሚለው ከሳሽ እርሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጭ ብሎ በቅኝ ገዢዎች የላቲን ቋንቋ እየጻፈ፤ በዓረብኛ ቁርአን እየቀራ ፤ መድረሳ እየተማረ ፤ መስጊድ ውስጥ በአረብኛ እያመለከ ነው።>> ይላል።
እውነት ነው። በአረብኛ ማምለክና መማር ወይንም በላቲን መጻፍ አንድ ሰው ካመነበት ነውር አይደለም። ከባሕር ማዶ በመጣ በአረብኛ እየተገለገለ፤ከላቲን በተደቀሉ የቅኝ ገዢዎች “ሆሄ” እየጻፈ ሃገር በቀል የታሪክ የማንነት የሥራ ቋንቋዎች የሆኑትን አምሐርኛና ግዕዝ ይውደሙ በምኖርበት አካባቢ አይሰሙ ማለት ግን ነውር ነው። ይላል ደራሲ ባንተአምላክ። ለዚህ ነው ፕሮፌሰር ሃብታሙም እንዲህ ያለውን እሳቤ ያለውን ሰው እንዴት ብለን ኢትዮጵያዊ አድርገን እንቀበለው? የሚለው በዚህ ወረርሺኝ ተቀብሎ የኔ ብሎ እየተጠቀመ ላለው ለመላው ኦሮሞ ሕዝብ ነው ምሬቱ። የፕሮፌሰሩ ክስ እና ምሬት እውነትነት አለው።
ባንተአምላክ አያሌው ይህንን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡
<<የሚቀርበውን ክስስ በየትኛው የፍርድ ሚዛን እውነት ብለን አንመዝነው? በአረብኛ ሲማሩ በራሳችን ቋንቋ
አልተማርንም ፤ በላቲን ወይንም በአረብኛ ሲጽፉ በራሳችን ቋንቋ አልጻፍንም ሳይሉ በአማርኛ ሲማሩ፤ በግዕዝ ሲዘምሩ ግን
የባይተዋርነት ስሜት የሚይሰማቸው ከሆነ
ችግሩ የማን ነው?>> እውነት ነው፤ እውነትም ችግሩ የማን ነው? (ድምቀትና ሰረዝ የተጨመረ)
ርዕሱ እና ጉዳዩ አወያይ ስለሆነ በክፍል ሁለት ስለምመለስበት እስከዛው ግን የሚገርመኝና እናንተንም ይገርማችሁ ይሆናል
ብየ የምገምተው ሃሰተኛ ስብከታቸው እነዚህ አክራሪ ኦሮሞ ምሁራን የሚሉት ስያጡ ፤ እንዲህ ይላሉ፡
<<ኦሮሞዎች
ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡበት ምክንያት አምሐራዎች ቅኝ ስለገዙን ቁጣችንን
ለማብረድ ሚሰቶቻችንን በብዛት አዘውትረን እንደበድባለን>> እስከማለት ደርሰዋል።
ከባንተአምላክ ያገኘውን የጥቅሱ ምንጭ ከራሳቸው ኦሮሞ ጆርናል እና ፈረንጆቹ ኦሮሞዎቹ ነገሩን ብለው የጻፉት ልጥቀስ፤-
<< ሚሰት መደብደብ በኦሮሞዎች ዘንድ እጅግ የተስፋፋ ነው። ሰሊዚህ የወንዶች ፈጣን ቁጣና ጭካኔ ዋናው ምክንያት ከሌሎች ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ተደጋጋሚ አደጋዎች ጭንቀት ከምዕተ ዐመት ቅኝ ተገዥነት የተነሣ የሚፈጠር አቅመአልባነት ነው።>> Journal of Oromo Studies VOLUM E 4, NUMBERS 1 & 2, July 1997 p. 135 Kelly (1992:327-340), ትርጉም ባንተአምላክ አያሌው ገጽ 218-219)
<<Also Observers that wife-beating is wide-spread among the Oroma
Oromo. He hints that this escalating male aggression may be attributed, among, other
factors, to the constant crisis , stress and disempowerment associated with a
century of colonialism >> (Journal of Oromo Studies VOLUM E 4, NUMBERS 1
& 2, July 1997 p. 135 Kelly (1992:327-340),
እንግዲህ << ኦሮሞዎች ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡበት ምክንያት አምሐራዎች ቅኝ ስለገዙን ቁጣችንን ለማብረድ ሚሰቶቻችንን
በብዛት አዘውትረን እንደበድባለን>> እስከማለት የሚደርስ በሽተኛ ኦሮሞ ምሁር ዋነኛው ተልዕኮው (የራሱን ሚሰት መደብደብ
አረመኔነቱን ማሳያ መሸሸጊያ ለማድረግ የተጠቀመበት ቢሆንም፤ ዋናው መልዕክቱ ግን ጎሰኛነት ዕውር ነውና ተጨቁነሃል እናቶቻችሁን
ልንደበድብ ምክንያተችን አምሐራ ስለጮቆነን መወጣጫ አደረግናቸው እያሉ የሚያስተምሩት በላቲን ፊደል ያደነቆሩት አምሐርኛ ማንበብና
መስማት የማይችል ኦሮሞ ወጣት ቂምና በቀል እንዲያረግዝና ለዚህ ጭፍጨፋ ተወናይ እንዲሆን አድርገውታል።
ስለዚህም ነው ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝም ሆኑ ሌሎች አምሐራ ነገድ ምሁራን አብዛኛው ኦሮሞ ልሂቅና ፖለቲከኛ በበታችነት ስሜት እየተሰቃዩ ሚስቶቻቸው ሲደበድቡ ሳይቀር አምሐራ ነው እንዲህ ያደረገን እያሉ በሚያስቅና በሚገርም ሁኔታ በየጆርናሉ ሲጽፍ የሚውለውም በዚህ የጨቋኝና ተጨቋኝ ሐሰተኛ ትርክት ምክንያት ነው።
ይቀጥላል.........
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment