Tuesday, August 1, 2023

ትግሬዎችና የመካድ ባሕሪያቸው ተከታታይነት ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 2/31/23


ትግሬዎችና  የመካድ ባሕሪያቸው ተከታታይነት

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay) 2/31/23

የኔን ትችቶች እንደ ጨው የሚያቃጥላችሁ እንደላችሁ ይገባኛል። ሃቅ ብዙ ዕንቅፋት ይገጥማታል መጨሻ ግን ጎልታ ትታያለችና ለታሪክ እንተወው።

እንደመግቢያ ይህንን ልበል፡

ማህበረሰባችን በውሸት ተውጧል፣ ይህ ሕብረተሰብ ቶሎ ነቅቶ ራሱን ለማጽዳት ለእውነት ፍለጋ ወደ እግዚአብሔር መንገድ ቢመለስ የተሻለ ይሆናል የሚል ምክር አለኝ።

እያየሁ ያለሁት ትዝብት ማሕበረሰቡ በውጭ አገርም በትግራይ ውስጥም ወንዱም ሴቱም በሞትና በርሃብ ወቅት በክሕደት ወቅት ጭፈራ ውስጥ  ገብቶ ዳንኪራ እየመታ ሲደሰት አያለሁ። ለሞቱት ወገናቸውም ምንም ክብር የላቸውም።

ውሸት (ክሕደት) መዘዝ አለው። ውሸት እራስህን ማሳመን ይቻላል፤ ሆኖም              ከጎረቤቶቻችን ጋር “ያለ እምነት” መሥራት አንችልም።

ትግራይ ውስጥ በጣም የቆየ በተለይ ወያኔ ከተመሰረተ ወዲህ  ክሕደትና ውሸት በማሕበረሱ ቅቡል ሆኖ በመስፋፋቱ የበለጠ ወደ መከራ እየተጓዝን ነው። እውነት፤ እውነት እላችኋለሁ  እኛ ትግሬዎች የተከናነብነው ጨለማ ማየት ተስኖናል እያልኩ ምክር በመለገስ ወደ ርዕሴ ልግባ።

ርዕሱ ጥቂት ትግሬዎችን አይመለከትም። አብዛኛውን ይመለከታል። ባለፈው ጊዜ “አየ ትግሬ፤ ትግሬነቴን አስጠላኝ” በሚል ርዕስ ሰፊ ሓተታ ጽፌአለሁ። ትግሬዎች ዘረኞች ናቸው/አካባቢያዊነት ያጠቃቸዋል፤የሃይል ሚዛን ያዩና ከሃይለኛው ጋር ተሎ የመጠጋት ባሕሪያቸው መለያቸው ነው፤ በማለት “በሴራና በተንኮል ስለሚንቀሳቀሱ እምነት የሚጣልባቸው አይደሉም” ብየ ዓረቦች እኛን ትግሬዎች (Habesh) እንዴት በምሳሌ እንደሚጠቅሱን ባለፈው ጽሑፌ ገልጫለሁ።

 ትግሬዎችን ማመን አስቸጋሪ ነው ስል  ብዙ ሰዎች “ቃር ቃር” ይላቸዋል። በኔ ላይም የዘለፋ ውርጅብኝ አስተናግጃለሁ።

ይህ  የድንቁርና ዘለፋ አዲስ አይደለም።አማራው ተበድሏል እና ተነስ ብየ ስከራከር አማራዎች እኔን ሲሰድቡኝ ነበር። “ከአማራ በላይ አማራ ለመሆን ለምን ትሞክራለህ፤ ልታጣላን ነው” እያሉ በትግሬዎችም በአማራዎችም የተለያዩ የስድብ ማዕበሎች አስተናግጃለሁ። ለዘለፋቸው ይቅርታ ባይጠይቁኝም፤ አሁን ግን አማራው እኔ ምን ስል እንደነበር ገብቶአቸው ሲታገሉ እያየሁዋቸው ነው። አንዳንዶችም ጠንከር ብለው ወደ ብረት ትግል ገብቷል። የህልውና ትግል ነውና እንዲሳካላቸው እመኛለሁ።

 “ትግሬ ውሽማ እንጂ ባል ኣይሆንም ብየ! >…”- የሚለው የአዝማሪ ዘፈን” እንዲሁ ከጥላቻ የመጣ ሳይሆን ከሃገራዊ አምነት ጋር የተያያዘ ነው። ትግሬዎች ምንም ብትል፤ ብታባብል ከትግሬነታቸው ባሕሪ ፈቀቅ አይሉም። በማለት ባለፈው ጽሑፌ “ትግሬዎች በሴራና በተንኮል ስለሚንቀሳቀሱ እምነት የሚጣልባቸው አይደሉም” ብየ ዓረቦች እኛን ትግሬዎች እንዴት እንደሚያዩን በምሳሌነት ያቀረብኩትን ጽሑፍ” ተንተርሶ አንድ ምሁር ነኝ የሚል የትግራይ ተወላጅ ከትናንት በስትያ ደውሎ ያቀረብኩትን ነጥብ ማሸነፍ ሲያቅተው የስድብ ናዳ በማውረድ ራሱን አቃጥሎ ተሰናበተኝ።

ትግሬዎች አይታመኑም ስል በማስረጃ ነው። አገርን በመክዳት ከፍተኛ ዕርከን የያዙ ካገራችን ብሔረሰቦች መካካል  ውስጥ “ትግሬዎች” ከፍተኛውን ደረጃ ይዘዋል። ከዘመነ አክሱም ጀምሮ ያልተዘጋብንን ዛሬ አገሪቷ ብዙ ዕዳ እያስከፈላት ያለውን የኢትዮጵያውያን ነገሥታት ያስከበሩዋቸው  የባሕር ወደቦቻችንን ለጠላት ከማስረከብ ጀምሮ ሃይማኖትን ከማፍረስ እና ብዙ የጣሊያን ፖሊሲ ከመተግበር እና በርካታ ብሔራዊ ወንጀሎችን በመፈጸም “መታመን የማይችሉ” ታሪክን የመድፈር ባሕሪ የተጠናወተው፤ በጣም አደገኛ የክሕደት እርከን ውስጥ ያለ ማሕበረሰብ ነው።

ትግሬዎች ሲክዱ ያለ ምንም ይሉኝታና ሓፍረት “ፈጣጣ ክሕደት” በአደባባይ ላይ ወጥተው ሲናገሩ ምንም አይሳቀቁም። ሌላ ቀርቶ “የርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ ቴድሮስ ፀጋየ” ስለ ኢትዮጵያና አዲስ አባባ ሽንጡን ገትሮ በሚያሰደንቀው የሙግት ችሎታው ከነ "ጃዋር ኦነጎች" ጋር ሲከራከር “እሰይ” ብለን ዘምረንለት እንዳላደነቅነው ሁሉ ድንገት ግልብጥ ብሎ <<< የትግሬ ታጋይ ሆይ   እያሳደድክ በለው ያንን መኝ አማራ>>(ተጋዳላይ ትግራይ አርኪብካ በሎ ነቲ  ዓሻ ኣምሓራይ) እየለ እየጨፈረ በመዝፈን ፡“ በዓፋርና በአማራ ሕዝብ ላይ ብዙ ወንጀል የፈጸመውን “ቲ ዲ ኤፍ” የተባለው “የትግሬ ጦር” እንደ መለስ ዜናዊ ዘመን ዛሬም ኢትዮጵያ  ተቆጣጥጥሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጦር መሆን አለበት እያለ ሲከራከር ብዙ ሰዎች የደነገጡ ነበሩ። ከደነገጡትና ይህንን መስመሩን መጀመሪያ የተቃወምኩት እኔ ነበርኩ (ትችትም ጽፌአለሁ)

ሆኖም ቴድሮስ ፀጋየ አዲስ ባሕሪ የተላበሰው ሳይሆን ያው የዚያ ችግር ገመድ ጎታች መሆኑ ነው። ከላይ የጠቀስኩት የትግራይ ምሁር ነኝ ባይ እኔ ጋር ስልክ ደውሎ ካነሳቸው አንደኛው ነጥብ የቴድሮስን ጀግንነትና ሃቀኛነትን ለማሳመን የጣረበት ክርክሩ አንዱ ነው።

ትግሬ የመታመን ችግር አለበት ስል ከምንም በመነሳት አይደለም። ለምሳሌ በዚህ ቪዲዮ የምናየው የትግሬዎች ክሕደት የተለመደው “የዓድዋ ድል የትግሬዎች እንጂ የኢትዮጵያዊያን ድል አይደለም” የሚለው የተለመደ “ፈጣጣ ክሕደታቸው” አንደገና በባድመ እንደገና ፈጣጣ ቀጣይነት በዚህ ቪዲዮ ታደምጣላችሁ። የትግሬ ሊሂቅ ሲዋሽ አብሮ ሕዝቡም እንደንብ በመትመም አብሮ ይዋሻል።

የባድመ ድልና የባድመ መሬት የትግራይ እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም የሚል በዚህ ቪዲዮ ታደምጣለችሁ። ይህ “ፈጣጣ ክሕደታቸው” ምንጭ  ወደኋላ ብዙ ዘመናት ታሪክ የነበረ (እዚህ መዘርዘር ስለሚረዝም) የክሕደት ባሕሪው ቀጣይነት ማሳያ ነው።

በዚህ ቪዲዮ የምታዩት ዳዊት ገብረእግዚአብሔር ይባላል። በዘመነ ወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ መስፋፋት አድርጎ ከወያኔው ጻድቃን ወ/ተንሳይ የናጠጠ የተመቸው ሃብታም ነው። ዳዊት የወያኔዋ ቁንጮ “የሞንጀሪኖ” የሰብለወርቅ ገብረግዚአብሔር” ወንድም ነው። አድዋዊ ነው።

አማራ ከምድረገጽ መጥፋት አለበት እያለ በድፍረት በየሚዲያው ሲናገር የነበረው ዘረኛው መምህር ገብረኪዳን ደስታ አጼ ምኒሊክና አማራን የሚሰድብ፤ የገብረኪዳን መጽሐፍ ብዙ ሺ ብር ሰጥቶ ያሳተመለት ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር ነው።

ዳዊት መቀሌ ላይ በመመላለስ፤ በየስብሰባው በመገኘት የወያኔ የግንጠላ ሴራ ከሚገፉት ግምባር ቀደም አንዱ ነው።

 በሳውዲ አረቢያ የሚኖረው የትግራይ ተወላጅ ሚሊየነር ዳዊት ገብረእግዚአብሔር “ባድመ የትግራይ መሬት እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም” ሲል ስሙት።

አያይዞም ኢትዮጵያ/ኢትዮጵያውያን ስለ ባዲመ የመናገር መብት የላቸውም ይለናል።

የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት የውቦች ውብ (ሞዴል) ሆና የተመረጠቺው  እና “ዳላስ” በተባለው የአሜሪካ ፊልም ተዋናይ የነበረቺው “የሐረር ወርቅ ጋሻው” (ኢትዮጵያ ወርቅ ጋሻው) በባድሜ ጦርነት ወቀት በኤርትራ ተማርከው የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወታደራዊ ሙርከኞች ከነበሩበት ስቃይ ለማስለቀቅ ወደ ኤርትራ በመጓዝ ያደረገቺው ጥረት ዳዊት ከሚናገረው ቪዲዮ ውስጥ ተካትታ ታያለችሁ።

ሆኖም ባንዳው ዳዊት ገብረእግዚአብሔር ሻዕቢያን ከባድመ ጠርጎ ያስወጡትን የነዚህ ወታደሮች ውድ ህይወትና መስዋእትነት በፈጣጣ ክሕደቱ ከድቶአቸዋል።

 እንደ አለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያውያን ደማቸውን አፍስሰው የኤርትራን ወራሪ ጦር አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ በማሸነፍ ባድመን ነፃ ካወጣ በኋላ ዛሬ  ኢትዮጵያ ሳትሆን የትግራይ መሬት ነው እያለ ያለን ዓድዋዊው አክራሪ ዳዊት ባድመ ትግራይ እንጂ የኢትዮጵያ መሬት አይደለም የሚለው ክሕደት፤ ተመሳሳይነቱና መነሻው የዓድዋ ድል የትግሬዎች እንጂ የኢትዮጵያውያን አይደለም የሚሉት ባሕላዊ የክሕደት ባሕሪ ተያያዥ ገመድ ነው።

ኢትዮጵያውያኖች  ዓድዋ ድረስ ዘምተው ጣሊያንን በማሸነፍ  ከጣሊያን የቅኝ ግዛትነትና እናቶቻችን የጣልያን የጭን ገረድ ሆነው “እኛ ልጆቻቸውም ክልሶች” ሆነን ከመወለድ ያዳኑን ጀግኖች ኢትዮጵያውያንን እንደከድዋቸው ሁሉ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ዘምተው ወደ ባድመ በመሄድ ባድመን ከሻዕቢያ ብትር ነጻ ካወጡላቸው በኋላ  ባድመ የትግራይ ድልና የትግራይ መሬት እንጂ የኢትዮጵያው አይደለም ሲሉ  የትግራይ ተወላጆች  የመታመን ችግር አለባቸው ብየ ስል ከትላላቅ ፈጣጣ ክሕደታቸው መክንያት በመነሳት ነው።Watch the Video below

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ