የዘመነ ካሴ የራስ መካብ ባሕሪ እየጎላ መምጣቱ አደገኛነት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል!
ጌታቸው
ረዳ
(Ethiopian Semay)
10/26/24
ስለ አምባገነኑ ወጣት ዘመነ ካሴ የሚተነተኑ አደገኛና ራስን
የመካብ ትምክሕታዊ ባሕሪዎቹ ስንገልጽ ተከታዮቹ አይቀበሉን ይሆናል። ያ ግን ለብዙ አመታት የመንጋዎች ባሕሪ ምንነት ስለምናውቅ
ልክ እንደ ብርሃኑ ነጋ አምላኪዎች <<ስንምክራቸው>> አልሰማ ብለውን እንደነበረና ቀኑ ሲደርስ የብርሃኑ ነጋ
ምንነት እውነታው ሲገለጥ እንዳፈሩት ሁሉ የዘመነ ካሴ ተከታዮች <<አውራጃዊነትና ስሜታዊነት>> በብዙዎቹ ተከታይ
መንጋዎቹ ያየነው ስለሆነ የጊዜ ጉዳይ ሳይባል ይኼው አሁን አሁን የልጁ የመንደር ጎረምሳዊ ባሕሪው እየጎላ ምንነቱን ይሉኛል የማይል
“ኢጎው” እየፈካ መጥቷል።
ፈረንጆች ራስን በራስ መካብ “ኢጎኢዝም” ብለው ይጠሩታል። <<“ኢጎ” የመልካም አመራር ጠላት ነው>> ይላሉ የዚህ ባሕሪ ምንነት ያጠኑ ባለሙያዎች ሲተነትኑት። ኢጎ ከፋሺስት ባሕሪ ጋር የተጣመረ መሆኑን ብዙ መጻሕፍቶች ጠቅሰውት ተመልክቻለሁ። የተጋነነ ኢጎ ባህሪያችንንም ያበላሻል። ልክ እንደ ዘመነ ካሴ ንግግሮች የስኬታችን መሐንዲሶች መሆናችንን ስናምን፣ <<ጨካኝ>> ፣ <<የበለጠ ራስ ወዳድ>> <<ጉራን ከመጠን ማብዛት>> እና ሌሎችን ንግግሮችና ነጥቦችን <<የማቋረጥና ያለማድመጥ>> እድላችንን ይጨምራል።
በሁሉም ንግግሮቹ
ላይ ዘመነ ራሱን የሚጠራው “አርበኛ” እያለ ራሱን የሚጠራ እና የሚያሞካሽ
“ዘመነ ካሴ” እራሱ ጨካኝ መሆኑን እና ተያይዞ በትውልዱ የነገሥታት ልጅና ትልቁ ዝሆን እንደሆነ አመራር እና ጀግንነት ሲወለድ
ከእትብቱ ጋር እንደወረሰው ግምባሩ ላይ የተጻፈበት “ዕድል” መቀበልና ማክበር እንዳለብን ሰሞኑን ሞቷል ሲባል አልሞትኩም ለማለት
ለማስተባበል በመጣበት ንግግሩ ላይ ተናግሯል።
በተፈጥሮ አመራርና
ጀግንነት የተሰጠው ዝሆን የሆነ ይህ በፉከራና በራስ መካብ የሚንጎባለል ወጣት አሳሳቢ ባሕሪ እንዳለው እያን መጥተናል (እኔ እንኳ
እንደምታውቁት ካወቅኩት ቆይቷል)።
የሚናገራቸው ትዕቢታዊ የዘወትር ባሕሪው ለዚህም ምሕረት የለሽ መሆኑን ያሳየን
ሰው መሆኑን በተግባር ጎጃም ውስጥ ካለ እሱ በቀር ሌላ የፋኖ አመራርና የፋኖ ሃይል እንደማይኖር ፤ ከኖረም በማንቁርታቸው እየታነቁ
ለሱ እንደሚገዙ በመሃላ እንደሚያስምላቸው፤ ከመሃላው የወጣ እንደሚረሸን እና እምቢ ያሉትንም ሰዎች አፍኖ ከማሰር እስከ መግደልና
ማስጨነቅ፤ሽማግሌዎችና እናቶች እምብርክክ ማስኬድን የመሳሰሉ፡ጭካኔዎች አሳይቶናል።
ይህ “ኢጎ”
የተጠናወተው የመንደር ጎረምሳዊ ባሕሪው በጥለቅ ለማየት የፖለቲካ ተንታኙ የርዕዮት ሚዲያ አባል <<ቴዎድሮስ አስፋው>>
በሚደነቅ ግሩም ትንተና ስለ ዘመነ ካሴ አስፈሪ ባሕሪው ምን እንደሆነ ለማድመጥ እነሆ ይህንን ቪዲዮ ሊንክ ተጫኑ።
ከብልፅግና ግድያ ያመለጠው በራሱ አንደበት ግን እየሞተ ያለው ... @EthioSelam_ኢትዮሰላም #tewodros
https://youtu.be/uGVWkXpkLOA?si=KMWB-BI-QiwxRDvA
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)