በልደቱ አያሌው ቤተሰቦች
ላይ የተሰነዘረው ውግዘት
የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ በጽኑ ይኮንናል! ምክንያቴን ላስረዳ
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
10/22/24
ፕሮፌሰር
ሃብታሙ ተገኘ በልደቱ አያሌው ቤተሰብ ትውልዶች የውግዘት አመለካካቱን ብቃወመውም በዛው ውይይት ላይ ስለ አምሐራው ጥቃትና ስለ
ጸረ አምሐራ ቡድኖችና ግለሰቦች ያቀረበው ነጥብ ግን የማይጣል መሆኑን ላስምርበት እፈልጋለሁ በዚህም ሌላ ቀን እመለስበታለሁ። ፕሮፌሰር
ሃብታሙ ተገኝ ሳከብረው የነበረ ምሁር ነበር። በፕሮፌሰሩ ላይ ትችት ሳቀርብ ቅር እያለኝ ሳልወድ በግድ ፕሪንስፕል መከተል ስላለብኝ በፕሮፌሰሩ ላይ ትችቴ እነሆ!
በረራ ቀዳሚት አዲስ አበባ በሚል አስደናቂ የታሪክ መጽሐፍ ጽፎ ያስነበበን ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ በብዙዎቻችን አድናቆት ተችሮት የነበረ ምሁር ነው። አለመታደል ሆኖ ፕሮፌሰሩ ሲያቀብጠው ይሁን ሆን ብሎ አለም አቀፍ የፋኖ አስተባባሪ ኮሚቴ ተብሎ በሚጠራ “ሃሰተኞች ሚዲያ” ላይ ሁሌም በመገኘት መድረክ ላይ በሚተላለፈው ከታች በምለጥፈው ዩቱብ ቪዲዮ የልደቱ አያሌው ንብረት ላይና የቅርብ ቤተሰብና የልደቱ አያሌው 7 ትውልድ እርግማን እንዲደርስባቸው በመማጸን ለአማራ ማሕበረሰብ ማስተላለፉን ጥሪ ከዚህ ጽሑፍ ጋር አብሮ የተለጠፈው ቪዲዮ ያስረዳል። ፕሪፌሰሩ ምን እንደነካው ባላውቅም
በቀላሉ የሚታለፍ ውግዘት አይደለም።
ይህ ሰው ጤናማ ሕሊና ወጥቶ ወደ እዚህ ዓኢነት ንዴት እንዴት እንደተሸጋገረ ባላወቅም ውግዘቱ የሰብአዊና የዜግነት
እንዲሁም የነገድ ማንንትን የሚነጥቅ ጥሪ ነው። ልደቱ አያሌው በሚከተላቸው አንዳንድ የፖለቲካ ስሑትነቱን ካንዴም ሦስቴም መተቸቴን ተከታታዮቼ የምታውቁት ነው። ሆኖም በፖለቲካ ስላልተጣጣምን የልደቱ ሃብትና ንብረት ፤የልደቱ ቤተሰብና 7 ትውልድ እርግማን እንዲደርስበት ቅስቀሳ ማድረግ በጣሊያን ፋሺሰቶች ፤ በሶቭየት ሶሺያሊስቶች ፤ ደርግ በኢትዮጵያ ፤ ናዚዎች በጀርመን ፤ ሁቱዎች በሩዋንዳ፤ ወያኔዎች በትግራይ፤ በቅርቡ ደግሞ በዘመነ ካሴ የሚመራው “ጫካኝ” እና “ዝሆን” ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራ የአማራ ፋኖ በጎጃም ተቃዋሚዎቻቸውን በመሰወር ፤ በማፈን ፤ በማሰር፤ በመግደል፤ ሽማግሌዎችን የእምብርክ
ማስኬድ ንብረታቸውን በመንጠቅና በመውረስ፤ ቤተሰቦቻቸውን ከማሕበራዊ ትስስርና ግብይት እንዲገለሉ ጥሪ በማድረግ የታወቁና ብዙዎቹም በዓይናችን ያየናቸው ድርጊቶች ናቸው።
ዛሬ ደግሞ በፖለቲከኛው ልደቱ አያሌው ላይም ምንም እንኳ የተለየ አቋም ቢኖሮውም ለኢትዮጵያ ፍቅር የለውም ፤ አይቆረቆርም ብሎ ማለት ትክክል አይደለም። ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ የልደቱ አያሌውን 7 ትውልድ ድረስ የሚደርስ ብቀላ (ቬንጀንስ) ማሳወጅ የሩዋንዳ ሁቱዎች ሞደሬት ተብለው በሚጠሩ ሁቱዎች ላይ ካስተላለፉት እንዲሁም በአምሐራ ጥላቻ የሰከረው አረመኔው የወያኔው አሉላ ሰለሞን በአማራ ሕዝብ እና ከአማራ ጋር በተጋቡ ትግሬዎች ላይ ያስተላለፈው እና የተላያዩ የጎሳ የፋሺሰቶች ያስተላለፏቸው የብቀላና የጥይላቻ ጥሪዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው ይመስላል።
ፕሮፌሰር ሃብታሙ ያስተላለፈው ጥሪ መወገዝ አለበት።
ጌታቸው በየነ የተባለው ሰው የሚመራው የአለም አቀፍ ፋኖ አስተባባሪ ኮሚቴ International Fano coordinating Committee የተመሰረተው በሚከተሉት ነሓሴ 15/2016 ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፋኖ ተዋጊ መሪዎች ፈቃድና መግለጫ በደብዳቤና አስልክ ድምጽ ቅጅ እውቅና እንደሆነ በተላለፈው የቪዲዮ መግለጫ እንደሆነ እናውቃለን።
ፈቃጆቹም የሚከተሉት ናቸው፦ እነዚህም በስልክ ስማቸው እየጠሩ ከየትኛው ፋኖ እንደተወከሉ ይናገራሉ፡
በጎጃሙ አስራስ
ማሬ ይጀምራል፤ እንዲህ እያሉ፤
አስረስ ማሬ ዳምጤ ( የአማራ ህዝባዊ ልሳን አመራር ነኝ)
ሻለቃ ሰፈር መለሰ )አማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ተወካይ
ደሳለኝ …..አማራ አንደነት ምክር ቤት አሰባሰቢና የኮማንዶ አባልና ብርጌድ አዛዥ
ዋርካ ምሬ ወዳጆ (የምሥራቅ ፋኖ ዋና አዛዥና የመላው አማራ ፋኖ ምክትል አዛዥ)
አበበ ሙላቱ (ከሸዋ ፋኖ አንድነት ምክርቤት የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ )
ይህ ሚዲያ (በዚህ ድርጅት ሚዲያ የምናደምጣቸው ሰዎች ካሁን በፊት የተቸሁበትን ጽሑፍ ታስታውሳላችሁ) ለመመስረት የተፈለገበት ምክንያት መግለጫቸው አንደሚለው “በአለም ዙርያ አድቮከሲና ዲፕሎማሲ፤የሎጅሰቲክ፤ የገንዘብ ዕርዳታ” ስራዎች ለማከናወን እንደሆነ ይገልጻል። በደብዳቤው መጨረሻ መግለጫና በስልክ የሚደመጠው መፈክር “ክናዳችን መዳኚያችን” ይላል። ይህ ከሆነ አድቮካሲውና ዲፕሎማሲው በተቃዋሚዎቻቸው ላይ የ7 ትውልድ ዘሮቻቸው ብቀላን ለማወጅ ከሆነና በአካባቢያቸው ለነሱ የመይገብር ሁሉ አንዲታፈንና ንብረቱ እንዲወረስ ካደረጉ እውነትም ካሁን በፊት <<አማራ ውስጥ ገንግኖ እያቆጠቆጠ ያለው ፋሺዝም ካሁኑ ካልተወገዘ ለአገርም ለአማራ ሕዝብም አደጋ አለው! ጌታቸው ረዳ 8/14/24
https://ethiopiansemay.blogspot.com/2024_08_14_archive.html
ኢትዮጵያዊ አማራ እና ንጹህ አማራ እኛና እነሱ የዘመነ ካሴ የፋሺስት ፍረጃ
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/20/2024
https://ethiopiansemay.blogspot.com/2024/07/ethiopian-semay-7202024.html
በሂደት ላይ ያለው የዘመነ ካሴ ረዢሙ የቢላዋ ምሽት Zemene
Kassie’s night of the Long Knives in the making ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ 8/1/24
https://ethiopiansemay.blogspot.com/2024/08/zemene-kassies-night-of-long-knives-in.html
በጎጃም
አማራ ፋኖ ውስጥ ገንግኖ እያቆጠቆጠ ያለው ፋሺዝም ካሁኑ ካልተወገዘ ለአገርም ለአማራ ሕዝብም አደጋ አለው! ጌታቸው ረዳ
8/14/24
https://ethiopiansemay.blogspot.com/2024_08_14_archive.html
የሚሉ ትችቶቼን ጊዜ ወስዳችሁ አንብቡዋቸው።
ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ብቻ አይደለም በሚቃወሙዋቸው ላይ
ይህ የንብረት መወረስም ሆነ የሃይል እርምጃም መወሰድ አለበት ብሎ የሚሰብክ፤ በዚህ አጋጣሚ አንድ ያልጠበቁኩዋቸው ትልቅና ምሁር ሰው ብየ ስገምታቸው የነበሩት አቶ ተክሌ የሻው (የጨካኙ የዘመነ ካሴ ድጋፊ ናቸው) <<ከቴድሮሰ እስከ መንግሥቱ ኃይለማርያም>> ድረስ የተድርጉ ጭፍጨፋዎችና ጭካኔዎቸ ሁሉ ፋኖም ለሥልጣን ሲባል ማድረግ አለባቸው ሲሉ በሚያስተላልፉት ዩቱባቸው አደምጬአቸው በጣም ነበር የደነገጥኩት፡ (ሰውየው አማራን በማደራጀት እዚህ አሜሪካ ቀዳሚ ሚና የነበራቸው በበጎ ሳያቸው የነበሩ ሰው ናቸው)። ብሔረተኛ መሆን አደገኛና ድንገት ደራሽ ጎርፍ ነው የምለውም ለዚህ ነው።
አሁን ደግሞ ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ በልደቱ ላይ የንብረት መውረስና የ7ትውልዱ እና በመላ ቤተሰቡ ላይ የውግዘት ጥሪ ለአማራ ወጣትና ተዋጊ ማስተላለፍ አዝጋሚው ፋሺዝም እየተንፏቀቀ አማራው ማሕበረሰብ ላይም እያቆጠቆጠ ነው።
ይህ የሚያሳየን ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ስለ ፋሺስት ሕሊና ደጋግሞ እንዳስገነዘበን፡
<<በዚህ አይነት በጎሳ ብሄርተኝነት አይምሮአቸው የተመረዙ ሰዎች የግል ማንነታቸው መገለጫ የሆነውን እንደ ሰው የማሰብ ችሎታቸውን ለጎሳ መሪዎቻቸው አሳልፈው ስለሚሰጡ የአንድ በጎሳ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በሙሉ የጎሳ መሪዎቻቸው የሚነግሯቸውን እየሰሙና እየተከተሉ እንደ አንድ ሰው ወይም እንደ ጎሳ መሪያቸው ማሰብ ይጀምራሉ። ይህ ፈረንጆች “group
thinking” የሚሉትና የአንድ አክራሪ የጎሳ ድርጅት ተከታዮች አንድ ወጥ የሆነ አስተሳሰብ (homogenization of thought) ተሸካሚዎች የሚሆኑበት ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት በአክራሪ የጎሳ አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በጎሳ መሪዎቻቸው ትዕዛዝ(ውሳኔ) ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል። የጎሳ መሪዎቹ የወደዱትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ። የጎሳ መሪዎቹ የመረጡለትን ነገር ሁሉ ለመቀበል ይገደዳል። ምን እንደሚያስብ፤ ከማን ጋር ቡና መጣጣት እንዳለበት፤ ከማን ጋር መወያየት፤ ማንን ማፍቀር ማንን መጥላት፤ በየትኛው የፖለቲካ ስብሰባ ላይ መሳተፍ ወይም አለመሳተፍ እንደሚገባው ወዘተ የጎሳ መሪዎቹ ይነግሩታል። በዚህ አይነት የግል ማንነቱን ያጣ ሰው ይሆናል።>> (ሰረዝ የተጨመረ)
ከላይ እንዳነበባችሁት አማራው ውስጥ ብቅ እያለ ያለው የፋሺዝም ቡቃያ << እኛና እነሱ፤ እኔ ንጹህ አማራ እገሌ ግን አማራ መስሎ ጭምብል በመልበስ የአማራዎችን የኛን የንጹሃን አማራዎችን ትግል ለመጥለፍ የተቀላቀለን አማራ ያልሆነ ወዘተ…… (ዘመነ ካሴና አሰግድ እስክንድር ነጋ ላይ የገለጹበት አገላለጽ ነው) በሚል የፋሺስቶች ፍረጃ ውስጥ ገብቷል፡፡ ዛሬም በፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ልደቱ አያሌወ ላይ የዘሰነዘረው “ልደቱ አማራ እይደለም ፤ንብረቱ የተገነባው በአማራ ሕዝብ መሬትና ርስት ነው! የሚለው የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ፋሺስታዊ የጽንፈኛነት ልክ አንደ የፋሺስዝም ብሔረተኛነት አቀንቃኙ ዘመነ ካሴ እስክንድር ላይ <<እስክንድር አማራ ሳይሆን አማራ መስሎ የአማራነት ጭምብል የለበሰ.. “የኢትዮጵያ አማራ” (ትግሬዎች እኛን ሽዋውያን ተጋሩ እንደሚሉን) ማለቱ ነው ( የኛ ያልሆነ ፤ ጭምብል የለበሰ “ጸጉረ ለወጥ”) የሚለው የነ ዘመነ ካሴ ዕብደት ከፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ፋሺሰታዊ ዕብደት ጋር ተመሳሳይ ነው። ፋሺዝም እያቆጠቆጠ ነው የምለውም ለዚህ ነው።
ለማጠቃለል፡
ስለዚህም ፋሺስቶች አስተሳሰብን ሳይሆን “ወንድነትን” ( በጡንቻ/masculinity) በማሳመን ጠላታቸውን ከማስደንገጥ አልፈው አንደ እነ ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ ያሉ ሰዎች እየሰሩበት ያለው በጠባብ ጎሰኛነት በጠባብ አማራነት የተመረዙ ወጣቶችን በሚጠልዋቸው ሰዎችና ተቃዋሚዎቻቸው ላይ 7 ትውልድ የሚሻገር ጥላቻ (በቀል) እንዲይዙ የማይበርድ እርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር የማድረግ ሙከራ ስለሆነ ምንም እንኳ በልደቱ አያሌው ላይ ያለኝ የፖለቲካ ልዩነት ሰፊ ቢሆንም ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ በፖለቲከኛው ልደቱ አያሌው ንብረትም ሆነ በራሱና በቤተሰቡ እንዲሁም በሚቀጥለው 7 ትውልዱ ላይ ብቀላ እንዲረገዝ ያስተላለፈው ጥሪ በጥበቅ “እቃወማለሁ!!” እያልኩ ይህ ፋሺስታዊ አዋጅ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው የአማራ ወጣትና ምሁር የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ አደገኛ የብቀላና የጥላቻ አዋጅ አንድትኮንኑት ጥሪ አቀርባለሁ። ሥልጣን ላይ ያሉ በሽተኞች ሕመም ማከም አቅቶን ስንሰቃይ ጤነኞች ናቸው የምንላቸው የብዙዎቹ ምሁራኖቻችን በሽታ ሲታከልበት ጭንቀታችን ከምንችለው በላይ ሆኖብናል።
ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay አዘጋጅ)
No comments:
Post a Comment