Sunday, November 10, 2024

የዳዊት ከበደ ባህታ አውራምባ ታይምስ አዘጋጅ የሸዋ ጥላቻው ዛሬም አልለቀቀውም ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/10/24

 የዳዊት ከበደ ባህታ አውራምባ ታይምስ አዘጋጅ  የሸዋ ጥላቻው ዛሬም አልለቀቀውም

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 11/10/24

ዓድዋዊው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ባህታ የአውራምባ ታይምስ ድረገጽ ዋና አዘጋጅ ነው። አብዛኛው የትግራይ ተወላጅ ይሁን እራሱ ዳዊት የ “ትሕነግ” (የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግምባር TPLF (Tigray People Liberation Front) ተቃዋሚ ነኝ እያለ ሲናገር ሰምተነዋል፤ በዛውም ቅዋኔ በማሳየቱ መታሰሩን እናውቃለን። ሆኖም ብዙ ጊዜ እንደምናገረው 95% በግምት (አብዛኛው የትግሬ ሕዝብ) ምንም የወያኔ ተቃዋሚ ቢሆንም ትንሽ ስትፍቃቸው ወያኔ የሚያሰራጫቸው የጥላቻ ንግግሮች ተቀባይና  አንጸባራቂ ሆነው ታገኛቸዋላችሁ።

ለዚህም  ማስረጃ ዳዊት (አውራምባ ታይምስ) ማሳያ ሆኖ ታገኙታላችሁ። ዳዊት ከበደ የሸዋ ጥላቻው ካሁን በፊት በአውድዮ በድምጹ በትግርኛ የተናገረውን  አስደግፌ “ስለ ሸዋ” (ስለ አምሐራ “ ሸዋ” ጥላቻው) ማቅረቤን  ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ ከርዕዮት ዋና አዘጋጅ ቴድሮስ ፀጋዬ አና በአማራ ሕዝብና ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥላቻ ሰከረው አሉላ ሰለሞን ጋር ከሁለት ሳምንት በፊት ማለት ነው፤ <<ብድሑር ፖለቲካዊ ባህሊ ዝግናሕ ዘሎ ሕንፍሽፍሽ ናበይ ይወስደና|AWRAMBA TIMES>>  በሚል ርዕስ ከላይ ተለጥፎ የምታዩት “እስክሪን ሻት” (ምስል) የውይታቸው ርዕስ የዩቱብ ሽፋን ላይ <<ብሞቑሕ ፕሪቶሪያ ኣብ ትሕቲ ሸዋ>> (ሸዋዊው የፕሪቶሪያው እግረሙቅ(በሸዋ እግር ሥር የጣለን የፕሪቶሪያው እግረሙቅ)

በማለት የውይታቸው አድማቂ ርዕስ በመጻፍ ዛሬም አምሐራ በፕሪቶሪያም ይሁን በሥልጣን ላይ የሌለውን ሕዝብ ለአምሐራ ያለው ጥላቻ ልክ አልፎበት በመገንፈሉ ዛሬም ለምንኛውም ነገር ተጠያቂና አሳሪ አድርጎ የሚከሰው መከረኛው (ፓንቺንግ ባግ) ለጥላቻ ማብረጃቸው ትግሬዎች ትናንትም ዛሬም ምንላብት ነገም ከአምሐራ ራስ አይወርዱም ስል ስናገር የነበረውም ለዚህ ነው።

ደግሜ ደጋግሜ ለብዙ አታት ስናገረው የነበርኩት ዛሬም ማስረጃ፡ይኼው። የትግሬዎች ፖለቲካ ለማንኛውም ትልቁ እስከ ትንሽዋ የትግሬዎች ችግር ተጠያቂ የሚያደርጉት “አምሐራን” ነው። ናዚዎች ለሁሉም ችግር ተጠያቂ ያደረጉት “አይሁዶችን” ነበር። ይህ የትግሬዎች ለአምሐራ ያላቸው ጥላቻና “ክስ” የጀመረው እሱ እንደሚሉት ንኳ ብንወስድ ከ14ኘው ክ/ዘመን ከዚያም በፊት ይወስዱታል። በደምብ የገነነው ግን አፄ ዮሐንስ ሲሞቱ አጼ ምኒልክ ሲተኩ ፤ ለምን ሥልጣን ዝተ አለሙ ትግሬዎች ላይ በበላይነት አይቆይም በሚል የተነሳ ብዙ የውሸት ትርክቶች እያባዙ ሕዝቡን መርዘውታል።

ለምሳሌ ያህል፤- የጣሊያን ሰላይ የፕሮተስታንት ሃይማኖት ተከታይ ነበሩ ብለው አንዳንድ የዛሬ ዘመን የትግራይ ወጣት ትውልዶች የሚታሙት ደብተራ ፍስሐ አብየዝጊ

የተባሉ የትግራይ ሰው በ1899/ፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር (በኛው ዘመን 1891) “ታሪኽ ኢትዮጵያ” (የኢትዮጵያ ታሪክ) የሚል ጣሊያን ናፖሊ ከተማ የተፃፈ የትግርኛ የእጅ ጽሑፍ ስንመለከት አምሐራን ለትግራይ ድህነት አምርረው በብዙ ገፆች ይጠቅሳሉ። ሰለሆነም ብዙ የትግራይ ምሁራን ይህንን መጽሐፍ አስደግፈው ለአምሐራ ያላቸው ጥላቻ መነሻ አድርገው ተጠቅመውበታል።

ስለ መጽሐፉ አስመልክቼ << የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? የሚል መጽሐፍ ጽፌ በ2010 ዓ.ም ለገበያ አቅርቤ ነበር።

እንዲህ ሲሉ የዘገቡትን ልጥቀስ

ደብተራ ፍስሃ ለወያኔዎች መነሳት ቦይ የቀደዱ፤ ቀኝ ዘማሚ ‘ወግ አጥባቂ’ ትግራዊ ብሔረተኛ ቢሆኑም እሳቸው የጻፍዋቸው አንዳንድ ታሪኮችን እያጣመሙ የትግራይ ምሁራንና ጀሌዎቻቸው ጥላቻቸው እንደሚመች አድርገው ሲናገሩ ሰምቻለሁ።

ለምሳሌ ደብተራ ፍስሐ አብየዝጊ “ታሪኽ ኢትዮጵያ” በሚል የእጅ ጽሑፋቸው አጼ ምኒሊክ አዲሱን ንግሥናቸውን ለማረጋገጥ ወደ ትግራይ ሲመጡ ይዘዋቸው የመጡት ሠራዊቶች (የጎንደር የሸዋ ወዘተ….) ትግራይ ውስጥ ስለ የወንዶችን ብልት በብዛት በሠራዊቱ መሰለብ አስመልከተው እንዲህ ይላሉ፡

  ትግርኛው፤-

<<<<መቸም እቶም ጋ*ላ ውፋት እዮም እሞ ንዝረኸቡዎ ተባዕታይ ይሰልቡዎ ነበሩ>>

አምርኛ ትርጉም፦

<<መቼም ቢሆን የአፄው ጋ*ላ*ዎ*ች ብልት በመስለብ ሱሰኞች ነበሩና ያገኙትን ወንድ ሲስልቡ ነበር>> ቢሉም የዛሬ የትግራይ አክራሪ ብሔረተኞች ግን “በዛሬው ቋንቋ” የጦር ወንጀል ተደርጎ ከሆነም እኩል የዘመቱት አማራና ኦሮሞዎች (ምናልባትም ሌሎች ነገዶች) ላይ ሳይሆን አምርረው ትግሬዎች የሚጠሉት ፤ የሚወቅሱት ፤ የሚተርኩበት፤  እንደ ጠላት የሚያዩትና ተጠያቂ የሚያደርጉት ግን አሳዛኙ አምሐራውን ብቻ ነው። ለምን?

ያንን የአምሐራ ጥላቻ ከወላጆቻቸው እየሰሙ ያደጉ እንደሆኑ የመጀመሪያው “ወያኔ” መሪ እንደ እነ ብላታ ሃይለማርያም ረዳ (ከቃለ መጠይቃቸው ያደመጥኩት) የመሳሰሉ አክራሪ ባላባቶች ያቀጣጠሉት “ጸረ ሸዋ” (ፀረ-አምሐራ) ጥላቻ በ1975 ዓ.ም  በትግራይ አክራሪ ፋሺሰት ተማሪዎች  የተመሰረተው “የትጥቅ ትግል” ያሰራጨው ማኒፌስቶ አንደምታስታውሱት እንዲህ ይላል፡

<<የትግራይ ህዝብ ለረዢም ዘመን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጐ ሲጠላ እና ሲናቅ እንዲሁም አድልዎ ሲደረግበት ቆይቷል። ይህ በደል ጨቋኝዋ የአማራ ብሔር ሆነ ብላ የመንግሥት መመሪያዋ አድርጋ ስትሰራበት የቆየች ሲሆን… የ ፫ሺ ዓመታት የሚያኮራ ታሪክና ባህላችን መመኪያቸውና መፎከሪያቸው ሆኖ ይገኛል። ይህ የታሪክ ስርቆት በአንድ በኩል የአማራው ብሔር መፎከሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ትግራይ ህዝብ ‘ታሪክ እንደሌለው’ ህዝብ እንዲያስቆጥረው የተደረገ የመንግሥት መመሪያ ነው። የትግራይ ሕዝብ ክብሩና መብቱ እስኪመለስለት ድረስ ትግሉ አያቋርጥም። ጨቋኝዋ የአማራ ብሔርም ጭቆናዋ እስካላቆመች ድረስ ሕብረተሰብዓዊ ዕረፍት አታገኝም!”>> ይላል።

የትግራይ ምሁራንም ይህንን ማኒፌስቶ በመቀበል ባለፉት ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁንዋ ድረስ በትግራይ ክልል የበቀለው አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችን የዚህ አዲስ የአክራሪ ብሔረተኛ ወረርሺኝ ሰለባ አድርጓል።

ስለሆነም ለምሳሌ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ የተባለው  የትግራይ ምሁር ስትመለከቱት (እንዲያውም ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ የሰው ስነ ፍጥረት ግኝት በማግኘቱ  በመላው ዓለም ውስጥ ስመ ጥር የሆነ አርኪኦሎጂሰት ፕሮፌሰር ተብሎ የተሸለመው ወጣት) ያለ ምንም ማንታት በጭፍን ከላይ ያነበብነው የትሕነግ ማኒፌሰቶ በመቀበል በበኩሉም እንዲህ ይላል፡

 <<ከኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው 1500 ዓመታቱ የትግራይ ህዝብና በተወሰነ ደረጃ የኤርትራ ድርሻ ነው>> ይላል

ለጭብጡ እንደማስረጃ የሚሰጠው ደግሞ (I am archeologist; I know what I am talking about.) “አርክዮለጂሰት ስለሆንኩ የምናገረውን አውቃለሁና እመኑኝ” የሚል ነው።

አርኪኦሎጂስት ስለሆንኩኝ እኔ የምለውን አምናችሁ ተቀበሉኝ ከማለት ውጭ ከኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው 1500 ዓመታቱ የትግራይ ህዝብና በተወሰነ ደረጃ የኤርትራ ድርሻ እንዴት ብቸኛ ባለቤትና ብ ሰሪ ሆኖ ሌላውን የቅርብ ተጓዳኝ አካባቢ ሕዝብና የሩቅ ሕዝቦች እንዳላካተተና ያቺ አካባቢ ብቻዋን ታጥራ እንዴት የዚያ ዘመን አስተዳዳርና ጥበብ በብቸኛ ባለቤትነት “ጌታ” ሆኖ አንደኖረ በረዢም የእንግሊዝኛ ንግግሩ “አንዲትም ማስረጃ” ሊያቀርብ አይችልም ወይንም እስካሁን ድረስ አላቀረበም።

በዚህ መሰረት በዚህ ዘመን ሰው መሆን ወይም ሰው ሆኖ ለመገኘት መሞከር በብዙ ሰዎች ከባድ ሆኖ ቢታይም እንደ እነ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ባህታ የመሳሰሉ ጋዜጠኞች ለአምሐራ (ሸዋ) ያላቸው ጥላቻ ሊያበርዱት ባለመቻላቸው ዛሬ “ሸዋ” የሚባል አካባቢና አጠራር በወያኔዎች ሕ መንግሥት የተሻረና ሸዋ (አምሐራ) የሚባል ሥልጣን ላይ ሆኖ ፕሪቶሪያን እንደ የትግሬ ማሰሪያ አድርጎ የሚጠቀም የሸዋ ሥልጣን (የሸዋ ሥርወ መንግሥት) የሚባል በሌለበት አገር እነሆ እነ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደም ሆኑ መሰል የትግራይ አክራሪ ሃይሎች ምንም ሳይመስላቸው (ሸዋዊው የፕሪቶሪያው እግረሙቅ ሰንሰለት(በሸዋ እግር ሥር የጣለን የፕሪቶሪያው እግረሙቅ)

እያሉ ዛሬም ለሚከሰቱ ማንኛቸውም የትግራይ ችግሮች ተጠያቂ የሚያደርጉት 50 አመት ሙሉ በመጨፍጨፍና በመታረድ ያለው ያልታደለው ምስኪኑ አምሐራ ሸዋሸዋ ፤ ሸዋ የሚያስብላቸው የፈጠራ የጥላቻ ቅዠት ስያቃዣቸው ዛሬም እየሰማናቸው ነው። ምሕረቱን ያውርድ!

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay