Wednesday, September 4, 2024

የነቀዘው አዲስ አበቤና 49 አመት ከፋሺሰቶቹ ጋር ፍቅር የወደቀው የትግራይ ሕዝብ የሚነቃው መች ይሆን? ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 9/4/2004

 

የነቀዘው አዲስ አበቤና 49 አመት ከፋሺሰቶቹ ጋር ፍቅር የወደቀው የትግራይ ሕዝብ  የሚነቃው መች ይሆን?

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 9/4/2004

ሰላም ለሁላቸሁ ይሁን።

ከፎቶይ የሚታዩት አካልዋን ያጣች የወያኔ ወጣት ታጋይና ከታች ደግሞ የበሰበሱት የአዲስ አበባና የክ/ሃገሮች  የአብይ ወጣት ደጋፊዎች ፎቶ ነው፡

እህልና ሰው አንድ ነው። እንስሳ ብቻ ነው በባሕሪ ስለሚለይ የማይነቅዝና የማይበላሽ። እህል ሲበላሽ በሰበሰ ወይንም ነቀዘ እንለዋለን። እህልን የሚያነቅዘው ነቀዝ (በትግርኛው ነቐዝ) የተባለ ከእህሉ ጋር ተደባልቆ የሚኖር ተባይ ሊሆን ይችላል ፤ እህልን የሚያነቅዝ ሌላው ምክንያት አየር ሳያገኝ ታፍኖ የቆየ እህል ወይንም የአየር ጠባይ ነው። ሕብረተሰብም ልክ እንደ እህል ይበሰብሳል የነቅዛል! አዎ።

ሕብረተሰብንስ የሚያነቅዘው ምንድነው? መጥፎ መሪ እና መጥፎ ሥርዓት። እነዚህም የሕብረተሰብ ተውሳኮች/ተባዮች ናቸው።

ዛሬ ያላንዳች መሸፋፈን ልክ ካሁን 28 ዓመት በፊት ይህ ሕብረተሰብ የተነበረከከ ፤ሽንፈት የተቀበለ ሕበረተሰብ ነው፡ ብዬ ስልሕብረተሰብ እየዘለፍክ ነውተብዬ እንደተጨሆብኝ ሁሉ ዛሬም በድጋሚ እንድትጮሁብኝ ለመጋበዝ ሳይሆን ላመስታወስ ነው።

ትዝ ይላችሁ እንደሆነ በግልጽ አማርኛ  በውጭ ያለውም ሆነ በውስጥ  ያለው ሕብረተሰባችን ከመበስበስ ባሻገር እርከኑን ተሻግሮ እንግሊዞቹ እንደሚሉትሯትን/ሮትን” (Rotten) እንደሚሉት በስብሶ/ ነቅዞ/ ረጥቦ/ የጠላት ባንዴራ እየተሸከመ በየአደባባዩ ይንከላወት እንደነበር  ታስታውሳላችሁ (የቅርብ ትዝታ ነውናብዙዎቻችሁ የተካፈላችሁበት ክስተት ነበርና)። ይህ ባሕሪ እኛ ትግሬዎችእጋል” “የገማ/ የጠነባ እንቁላል ወይንም የሚገማ ውሃእንደምንለው ዓይነት ነበር ወቅቱ።

 ረዢም ጊዜ ሳይንቀሳቀስ እንስራ ውስጥ የኖረ ውሃም ሆኖ ነፋስ እየመታውም የሚሸት የኩሬ ውሃ አጋጥሟችሁ ያውቃል? የአገሪቷ ርዕሰ ከተማ ኗሪ ወጣት ተነስ ተብሎ ፤ ለማነሳሳት እየታሰ ተደብድበው ተሰቃይተው በግብር ያሳዩትን እነ ታላቁ እስክንድር ነጋን  ከድቶ የፈረንጅ “ዩ ትዩብ - ፕራንክ” ቀልድ እየተጫወተ በራሱ ላይ ሲያሾፍ የሚውል ከንቱ ትውልድ ሆኗል።

  ያዲስ አበባ ሕብረተሰብ ወጣትና ምሁር በስብሷል። ሕብረተሰብ ሲበሰብስ አፍንጫን አይደለም የሚሰነፍጠው የታዛቢን ዓይንና ሕሊናን ጭምር ያሸማቅቃል። በቅርቡ እያየነው ያለው ዘገባ የመንግሥት ተብየውም ሆነ ሃብታሞች ያቋቋሙዋቸው በመዲናዋ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) ለሚቀጥርዋቸው ሠራተኞችም ሆኑ አስተማሪዎች ደሞዝ በመከልከል ቤተሰቦቻቸው እንዲሰቃዩ በማድረግ በረንዳ አዳሪ በማድረግ የነቀዙ ቱጃሮች የድሃው ሠራተኛ ወዝ የሚበዘብዙ አረመኔ ባለሃብቶች የሚንደላቁባት ከተማ ሆናለች።

አዲስ አበቤው በአመዛኙ ከትንሽ እስከ ትልቅ በተለያዩ መገለጫዎች በስብሷል። አዲስ አባቤው ብቻ ሳይሆን በብዙዎቹ ክፍለሃገሮች ያለው ሕብረተሰቡ ከነባሩ ጨዋ ማሕበረሰብ ባሕል ወጥቶ  ሂደቱና ባሕሪው በመለወጥ ራሱን ወደ ሞት ሂደት ሲያሸጋግር ይታያል።ራሱን የበሰበሰ “ግኡዝ ሕብረተሰብ” ለማነቃቃት ብዙ መስዋእት ቢደረግም አልሆነም።

የበሰበሱ መሪዎች የበሰበሰውን ሕብረተሰብ ለመስለብ እንዲያመቻቸው ሕብረተሰቡን ለ36 አመት በማበስበስ ኢላማቸውን አሳክተዋል። መሪዎች ያንን ካላደረጉየሚጫኝ አህያ አይሆንላቸውም። ልክ ግምበኞች / የሕንጻ መሃንዲሶች አልፈርስም ብሎነክሶጠንክሮ  የየዘ መሰረት (ቤዝ)  እምቢ ሲላቸው “ውሃእያፈሰሱ፤ እንዲረጥብ እያለሳለሱ እንደሚያፈርሱት ጠንካራ መሰረት ሁሉ ጠንካራ ሕብረተሰብንም ለማበስበስ” የተለያዩ ዘዴዎች በማስተዋወቅ እንደ ዋለሃ (ዋልካ) ተፍረክርኮሊጥ ሆኖ  እስከሚታጠፍላቸው ድረስሃይለኛ ስራ ይሰራሉ። የሚታጠፍ ነገርጥንካሬ ስለሌለው  ሃይልያጣል።የሚታጠፍ ሰው ስብእናውና ሞራሉ ደካማ ስለሆነ የበታችነት ስሜት ተሰምቶት ልጠፍህ ለሚለው ክፍል ሁሉ በቀላሉ ይታጠፍለታል።ተስፋ የሚባል ትርጉም የገባው ከሆነም፤ ምህረቱና ተስፋው በዛው ክፍል ይጥላል።ያችን የተነጠቀውን ተስፋውና ሰብእናው ለማግኘት በራሱ መቆም ስላልቻለ ሰላቢዎች ወደ ጠመዘዙት ለመጠምዘዝ ምቹ ሆኖ ይገኛል። ያንን ግብ ለማሳካት ሥልጣኑን የያዙት ቡድኖች ኢትዮጵያን በነገድ (በቋንቋ) ለይተው እንዲከለል ስላደረጉት፤ ባንድነት መቆም ስለማይችል እርስበርስ እየተባላ መሪዎቹ ምቹ ስለሆነባቸው ማሕበረሰቡን ወደ ፈለጉት ማዞር ችለዋል። አሁን የቀሩን የተበላሹ የትግራይና የአዲስ አባባ ወገኖቻችን አብይንና ወያኔዎችን እያሞገሱና እየተከተሉዋቸው ያለው ባሕሪ በተጠቀሰው ዘዴ ምክንያት ነው (እስተክሆልም ሲንድሮም)።

ታስታውሱ እንደሆነ የአምሓራን ሕብረተሰብ ተነስ እያልኩ ስቀሰቅስ የነበረው ብዙ ትዕግስትና መተጣጠፍ ሲያሳይ ስለነበር ነው።

  አዲስ አበቤው በእስክንደርና በጥቂት መሰል አርበኞች መሪነት ጥይት ከያዘ ኦነጋዊ ፖሊስ ጋር ሲታገል የነበረው አመርቂ የምኒልክ ጀግንነቱን ሲያሳየን የነበረው ወጣት ዛሬ አማራ በተነሳበት ወቅት ውሃ ውስጥ የገባ አይጥ መሰሉ በከባድ የምጣኔ ሃብትና የፍትሕ እጦት እየተሰቃየ እያለ ፀጥታን መምረጡ ይገርማል። ብዙ የአማራ ምሁር አማራ በመሆናቸው ብቻ በኦነጋዊው ፖሊስና በኦነጋዊው ፍትሕ እያተፈሱ ሲታጎሩ ሲራቡና ሲደበደቡ አይቶ እንዳላየ “ዳንኪራ እየመታ ነው” (ልክ እንደ ቀይ ሽብሩ ዘመን)።በዘመናችን ግፍ ሲፈጸም በግሃድ ወያኔምም ሆነ ደርግ ተፋልመናል።

አዲስ አበቤው ብቻ ሳይሆን እኔ ከተወለድኩበት የትግራይ ማሕበረሰብም ቢሆንነከሱት የፋሺሰት ጅቦች ጋር አብሮ መኖር ለምዶታል።ከመልመዱ የተነሳ የመውደድ አባዜው ዛሬም ብሶበት  ሲጨፍርና ባንዴራቸውን ለብሶ ፎቶ ሲነሳ እያየን ነው። ኩፉኛ 49 አመት ድፍንፈጣጣ ፍቅር !! ዛሬም አልለቀቀውም (ኢትዮጵያ የምታቀርብለትን ፍጆታ እየተጠቀመም ቢሆንየሃገረ ትግራይ ምስረታው ቅዠት አልለቀቀውም)።ስለጠነቡትየትግራይ ምሁራኖች ማውሳት ቆሽት ማሳረር ስለሚሆን አልነካካውም።

የትግራይ ነገር ሳነሳሐረርውስጥ ማታ ማታ ሲመሽ ጅቦች የሚቀልቡ ፡አድቨንቸሪስቶች” (ጀብደኞች) አሉ። ይህ ጉደኛ ትዕይንት የትግራይ ሕዝብ ባሕሪ እና የወያኔ ግንኙነት ታሪክ ጋር ይመሳሰልብኛል። ዛሬ ዛሬ ከመቸውም በበለጠ ሐረር” ውስጥ ማታ ማታ ሲመሽ ጅቦች የሚቀልቡ ፡አድቨንቸሪስቶች” (ጀብደኞችየጐብኚዎች መስህብ እየሆነ በካሜራ እየተቀረጸ መጥቷል። ቀላቢውም ሆነ ተመልካቹ  የሳቱት ነገር ቢኖር ጅቦቹ የቀላቢውም ሆነ የተመልካቹ ህይወትቀሳፊዎችእና ተቀናቃኞች መሆናቸው የመገንዘብ ሕሊናቸውበጊዜያዊ የመጠጋጋት የጀብደኝነት እርካታውስጥ ገብቶ ስለተማረከ፡ ከመጋቢያቸው እያሽካኩ በጓደኝነት ባሕሪ  ሥጋ እየተሰጣቸው የሚመገቡትጅቦችቀላቢ ሲያጡየገዛ ቀላቢያቸውን እንደሚበሉት ቀላቢዎቹ የተረዱት አይመስሉም።

ጅቦቹ ከቀላቢያቸው የሚፈልጉት ነገር ቢኖርመመገብነው። ቀላቢዎቹ ከጅቦቹ የሚፈልጉት ነገር ደግሞ ጀብደኛነትን ለዓለም ለማሳየትና እግረመንገድም መናከሳችሁንአቁሙ ነው። የመጠጋጋቱ የጨዋታው ትርጉም ሲመረመር ከዚህ  ያለፈ አይሆንም። መጋቢዎቹ የዘነጉት ጉዳይ ሰንጋ ቢታረድላቸውም ልጆቻችንና ከብቶቻችንን መናከስና መብላታችሁን አቁሙ ስለተባሉጅቦቹመናከሳቸውን ያቆማሉ ወይ?” ነው ጥያቄው።

የሁለቱ ፍጡራን ትካት (ኢንስቲንክት) የጭምትነት ባሕሪ የጎደላቸው ስለሆኑነካሹም” “ተነካሹምየተፈጥሮ ባሕሪያቸው እንደማይገጥም እያወቁ ሁለቱም እየተጠጋጉ እናፈራ ተባእያሉ በማያዛልቅ ጨዋታ ገብተውየበይ እና የተበይየመገዳደል ጨዋታቸው እያሳመሩ ጅቦቹ ከጀብደኛ ቀላቢያቸው አፍ ጥርስ ተነክሶ የተንጠለጠለላቸው ስጋጠጋብለው በመንጠቅ ይጎርሳሉ። ይህ አስገራሚ የገዳይና የተገዳይ ጀብደኛ ጨዋታ በካሜራ ተቀርጾ ለዓለም ሕዝብ እየታየ ነው።የትግራይ ሕብረተሰብም ባሁኑ ሰዓት  ከ1.2 ሚሊዮን የትግራይ ወጣት ተዋጊ በጦርነቱ ሲሰዋ የተቀረውም “ቱራማታይዝድ” የሆነ በስቃይ የሚኖር ማሕበረሰብ ሆኖ ለዚህ ሲኦላዊ ሕይወት ከዳረጉት መሪዎቹ ጋር በመጓዝ  ከሚበሉትና ከሚያስበሉት የሰው ገላ ከለበሱ  አራዊቶች ጋር” ተጠጋግቶ በበይና በተበይ የጨዋታ ሕግጋት አስገብተው እየበሉት እንደሆነም እያወቀ 49 አመት ካለ ሞት በቀር ምንም ካልረቡት  አራዊቶች ጋር ፍቅር ይዞት ሲያሞግስና ሲጨፍር ማየት በሽታው በቃላት ለማስረዳት ይቸግራል

አጼ ዮሐንስ ሲያውለበልቡዋት የነበሩት  ዓለም ያወቃት ባለ ሦስት ቀለማት ሰንደቃላማች ማውለብለብ ትግራይ ውስጥ “ሕገ ወጥተደርጎ ስለታወጀ፤ በምትኳ የአራዊቶቹን ባንዴራ ለብሶ እያውለበለበ በመታየት በትግራይ ነገሥታት ሰንደቅአላማ ላይ ተሳልቋል። የትግራይ ሕዝብ መበስበስ የሕገ ወጥ  ቡድን ተባባሪ መሆን ዋጋው እያስከፈለው ቢሆንም አሁንም ወደ እማያውቀው ወደ “ፋንታሲ” ዓለም መጓዙን ቀጥሎበታል። የትግራይ ሕብረተሰብ በመበስበሱ ሕገ ወጥ ተግባሮችን ሞትን እርዛትን ግንጠላን አገር ማንኳሰስን ሕጋዊ አድርጎ  ተቀብሏል ማሰብ ያቆመው የትግራይ ሕዝብ ወንጀለኞቹ በዘረጉለት ሃዲድ መጓዙን ስለመረጠሞራል ፕርንሲፕልበመጣስላገር ታማኝነት” መሆኑን አቁሟል። ምልክት በሌለው ባጭበርባሪ ጎዳና የሚጓዝ ተጓዥ ለአደጋ እንደሚጋለጥ ሁሉ፤ይህ ሕብረተሰብ ለከፋ የሞራል መበስበስ መጋለጡ ዛሬም አላቆመም።

እነ ኢዛና ፤ አምደጽዮን ፤ ቴዎድሮስ ፤ ዮሐንስ፤ ምንሊክ እና  ተፈሪ እየኖሩበት ያለውን ሰፊ አገር ሲመሰርቱ ያችን ሰንደቃላማ ይዘው ነበር ታሪክ የሰሩ። ሆኖም ዛሬ በነዚህ ኩታራዎች ብልግና ሰንደቅአለማቸው ወደ አፈር ሲጣል እና ሲረገጥ ቢያዩ ምንኛ ባለቀሱ!?

ዛሬ አዲስ አበቤውና ትግሬው በተመሳሳይ የበሰበሰ ጎዳና እና ትርዕት እየተጓዘ መሆኑን ስንታዘብ ያሳዝናል።

ካነበብኩት አንድ መጽሐፍ ውስጥ 1500 አመት በፊት የሮም መሪዎች በመበስበሳቸው ለታላቋ የሮም መንግሥት መበታተን ምክንያት እንደሆነ አንብቤአለሁ። የበሰበሱ መሪዎች አገር ሲመሩ የበሰበሰ ሕበረተሰብ ያፈራሉ። አገር ባይፈርስም በውስጧ የታቀፈው ሕብረተሰብ አቅፈውት ሲጓዙ የነበሩት ተቋማት (ሰትራክቸሮቹ) ስለሚፈርሱ የሕሊና መፍረስ ስለሚገጥመው ባስተሳሰቡ መካን እና የበሰበሰ ማሕበረሰብ ይሆናል ማለት ነው።

ዛሬም የበሰበሰና የነቃ መሕበረሰብ ሚናው እየለየ መጥጧል።   ፍትሕለሚጠይቁ ፋኖዎች ሲያናንቁት የነበረው እነሆ ዛሬ አጥራቸው ውስጥ ብቅ ሲል ባንዳዎች ሌሊቱንም ሆነ ቀትር መተኛት አልቻሉም። ወንበራቸው በፋኖ ተነጥቆ ፋኖዎች ተቀምጠውበታል (እሰየው!!) አሳምነው ጽጌ ምነው ብቅ ባልክና ፍሬሕን ባየህ!?

ትግሉ አብይ እስኪወገድ መቀጠል አለበት።እንቅስቃሴውእንዳይጠለፍ ሕዝብ ነቅቶ መከታተል የዜጎች ግዴታ ነው እያልኩ ለአመታት የምጮኩበትን የትጥቅ ትግል አማራው ተግባራዊ ማድረጉ ቅቤ አጠጥታችሁኛል። በሃገረ ትግራይ ሥካር ተመርዞ ሃገረ ትግራይ ወደ እሚላት ሃገረ ጽልመት እየተጓዘ ያለው 49 አመት ከፋሺሰቶቹ ጋር በፍቅር የወደቀው የትግራይ ሕዝብና አዲስ አበቤውስ መች ይሆን የሚነሱት

ጌታቸው ረዳ