Sunday, October 13, 2024

አምሐራዎች ያላወቁት ወገናቸው እየመሰላቸው በበጎ ሲያዩት የነበረው የሻዕቢያው ፕሮፓጋንዲሰቱን ወጣት ላስተዋውቃችሁ! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 10/13/24


አምሐራዎች ያላወቁት ወገናቸው እየመሰላቸው በበጎ ሲያዩት የነበረው የሻዕቢያው ፕሮፓጋንዲሰቱን ወጣት ላስተዋውቃችሁ!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

10/13/24

ዛሬ የምንወያየው ከታች በዝርዝር  የምናየው ከላይ ፎቶው ስለ እምታዩት ልጅ ነው።  

 ይህ ወጣት ባንዳንድ ኢትዮጵያዊያን በጎ ኢትዮጵያዊ አመለካከት ያለው እየመሰላቸው በበጎ ሲያዩት እንደነበር መገመት ይቻላል። እኔ ራሴ *አፍቃሬ ወያኔነቱን ባልጠራጠርም* ልጁ እስከዚህ ድረስ ጉልህ የሆነ ፀረ አማራ (ፀረ ኢትዮጵያ) መኖሩን አልመስለኝም ነበርና ትናንት ጸረ አማራነቱን በግሃድ አሳወቀ።

 ናትናኤል አስመላሽ ይባላል፡ ወያኔ የነበረ፤ የወያኔ ትግል አሞጋሽ Tigray Media Network (TMN) የሚባል የዩቱብ መድረክ አዘጋጅ ነው። ልጁ ከጸረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ከሆነው ከሻዕቢያ ቡድንና መሪ ጋር የጠበቀ ግንኙነትና ጥብቅና የቆመ ተልዕኮ ያለው <<ኢትዮጵያን የባሕር በር አልባ ያደረጉዋትን ነፃነታቸውን ያወጁባቸው በዓላቶቻቸው በማክበር ወደ ኤርትራም ሆነ በዓላቸው በተዘጋጁባቸው ቦታዎች ሁሉ በመገኘት ሲቦተለክና አብሯቸው ሲቦርቅ የሚታይና የሚደመጥ አክራሪ የሻዕቢያ አወዳሽ “ጸረ ኢትዮጵያ” ነው>>። ካንደበቱ እንደሰማሁት ከሆነ ትውልዱ “ትግራይ ዓድዋ (ዓዲ አቡን)  አስመራ ያደገ’’ እንደማንኛቸውም ኤርትራ ውስጥ ያደጉ ትግሬዎች የሸዋ ጥላቻው ክፉኛ የተጠናወተው ነው።

በቅርቡ እሱ በሚያዘጋጀው <<Tigray Media Network  ሓሶትን ልኽብጥናን ሳሞራ ዮኑስ//ብዛዕባ ሻዕብያ Oct 11, 2024 >> በሚል ርዕስ (አማርኛ ትርጉም ‘የሳሞራ የኑስ ውሽትና መገለባበጥ’ ማለት ነው) በሚል ርዕስ የባድመን ጦርነት ከመሩት የበላይ አዋጊዎች አንዱ የነበረው በጸረ ሻዕቢነቱ የታወቀው የወያኔ ተጋዮች ከፍተኛ አዋጊና በሗላም የወያኔ መንግሥት የሚመራው በትግሬዎች የበላይነት የሚመራው መከላከያ ጦር ዋና አዛዥ የነበረው ጀኔራል ሳሞራ የኑስ በቅርቡ <<ብራኸ ሾው>> (ትግርኛው “ብራኸ” ማለት አማርኛው “ከፍታ” ማለት ነው) ከሚባል የትግርኛ ዩ ቱብ መድረክ ከምታዘጋጀው “ሃገረ ትግራይ ምስረታ አቀንቃኝ በሆነቺው በአክራሪ  ጸረ ኢትዮጵያነትዋ የምናውቃት “መድህን ገ/ስላሴ” ከምትባል የዚህ መርሃ ግብር አዘጋጅ ጋር ሳሞራ የኑስ ባደረገው ቃለ መጠይቅ  አስመልክቶ ከላይ የጠቀስኩት ናትናል አስመላሽ  በሚያዘወትርበት ባልታረመ እጅግ ጸያፍ አንደበቱ የሳሞራን ፖለቲካ ሳይሆን የሳሞራን አካላዊ ይዘት  እጅግ በሚዘገንን ቃላቶች ሲዘልፈው መስማት የዘመኑ ትውልዶች  ከወላጆቻቸው የሕሊና *የሞራል* ማዕቀፍ ምን ያህል እንደራቁ ሳስበው ለመግለጽ ይጨንቃል።

የፋሺዝምና የናዚዎች ክልሰ ሃሳብና ሕሊና ላነበበ ሰው ልጁ (ናትናል) የወያኔ መሪዎችን “መሪዎቻችን” በሚል ቃል መሪዎቹ መሆናቸውን በቃሉ  ቢያሰምርበትም በሙሉ ሳይሆን በአንዳንድ የወያኔ መሪዎች ላይና አሁን ደግሞ በሳሞራ የኑስ ላይ ተቃዉሞና ጥላቻ ቢኖሮውም “ሳሞራ የታገለለትና በህወሓት መአከላዊ አባልነቱ የመራው የፖለቲካ እሳቤ” ግን ተከታይ መሆኑን ለማወቅ  ከሚሰነዝራቸው አንደበቱና በብዙ መንገዶቹ ያሳብቁበታል።

 ሳሞራን አስመለክቶ የተቸበት የሳሞራን አመለካከት ሳይሆን አካላዊ ሰብእናውን በማይገባ ነበር የተቸው። ስለ ስብእናው አትኩሮት ቆየት ብየ ልመለስና ዋናው የዚህ ትችት መነሻየ ወደ ሆነው የናትናኤል አስመላሽ ጸረ አምሐራነት በይፋ በአንደበቱ መናገሩን ነው። ሸዋን ሲጠቅሱ አክራሪ ትግሬዎችና ኦሮሞዎች እንዲሁም ጣሊያኖች “አምሐራ” ማለት እንደሆነ በብዙ መጻሕፍቶች የተጠቀሰ ነው”

እንዲህ ይላል ሳሞራን ሲተች፤

<<ይህ ሰው አፍቃሬ ሸዋ ነው።የሸዋን ሕዝብ መውደዱ የሚያሳዝ ነገሩ  ነው>> ካለ በላ ሳሞራ ለምን የሸዋ (አማራ) ሕዝብ አፍቃሪ እንደሆነ ሳይገልጽ <<ይህ ሰው አፍቃሬ ሸዋ ነው።  የሸዋን ሕዝብ መውደዱ የሚያሳዝ ነው>> ከማለት በቀር ምንም የሰጠው ማብራሪያ የለም።

የትግራይ ልጆች (ብዙዎቹ) ሸዋን የመጀመሪያ ጠላታቸውና ትርክታቸው አድርገው መሳል የጀመሩት በነሱ ሰነድ በጣም ወደ ኋላ 14ኛው ክ/ዘመን የሚሳብ ጥላቻ ወደ 18ኛው ክ/ዘመን ከዚያም ወደ 1967 ተሸጋግሮ ፤ አስገደ ገብረስላሴ እንዳለው (መጀመሪያ ወደ ትጥቅ ትግል ደደቢት በረሃ ከወረዱት አንዱ የነበረ) <<ጸረ አምሐራ ጥላቻ እንደ ወረርሺኝ መላውን ትግራይ አዳረሰው>> አንዳለው ሁሉ ፤ ይህ የሸዋ (አምሓራ) ጥላቻቸው  የትግራይ ወያኔ በተመሰረተ አንድ አመት <<የካቲት 1968 ዓ.ም የሞት ጦማር>> (ማኒፌሰቶ የካቲት) ይፋ ወጣ።

በዚህ መንገድ የተጓዘው ጥላቻ አምሐራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንደሆነ በአማራ ሕዝብ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሞት ጦማር የታወጀበት የትግርኛ እጅ ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦

 << ብሄራዊ ተጋድሎ ህዝቢ ትግራይ ጸረ አምሓራ ብሔራዊ ወጽዓ እዩ።>> ወደ አማርኛው የተመለሰው ማኒፌስቶ የካቲት 1968 እንዲህ ይላል << የትግራይ ሕዝብ ብሔራዊ ትግል ፀረ የአምሓራ ብሔራዊ ጭቆና ነው>> ይላል። የማኒፌሰቶው የእጅ ጽሑፍ ስዩም መስፍን (ይህንን ያረጋገጥኩት የድርጅቱ ዋና መሪ ከነበረው አንድ የወያኔ አመራር አባል ባነጋገርኩበትና በጽሑፍም የሰጠኝ መረጃ ነው) ።

በዚህ መሰረት አብዛኛው ሽማግሌም ወጣትም የሃይማኖት መሪዎችም ሁሉም “በሸዋ” (አምሐራ) ላይ ጥላቻቸው እየጠነከረ መጥቶ ልክ ኤርትራኖች የትግራይን ሕዝብ ለመጥላት በሚገልፁበት አጋሜ የሚል ቃል ከምላሳቸው የማይለይ የተዘወተረ ጠላት አድርገው የሚናገሩበት አንደበት ሆኖ እንደተሰበኩት ሁሉ ትግሬዎችም “ሸዋ” የሚለው ቃልም አምሐራን እንደ ጠላት እንዲታይ ምሁሩም ያልተማረውም ፍየል ጠባቂ እረኛም በዘፈንም በንግግርም   ተቀባይ እንዲያገኝ እያሰራጩ _:_ እንዲሁም የወያኔን ፋሺሰታዊ  ርዕዮት የምንቃወም ጥቂት ትግሬዎችንም   “ሽዋውያን ተጋሩ” (የሸዋ ትግሬዎች) ፈታዊ ሽዋ (አፍቃሬ ሽዋ) ወዘተ… በማለት የተለመደ ፋሺስታዊ የፖለቲካ መመሪያቸው አደረጉት።

ናትል አስመላሽም ሳሞራ የኑስን ለመተቸት የተጠቀመበት ቃል ወያኔዎችና ኤርትራኖች ያስተማሩትና ትግራይ ውስጥም በልጅነቱ የወያኔ አባል ሆኖ በነበረበትም ሲሰማው ያደገበት “ፈታዊ ሽዋ (የሸዋ ወዳጅ፤ አፍቃሬ ሽዋ) የሚለውን ካስተሳሰቡ  ጋር ያልሰመረ ትግራዋይ ይሉኛል በሌለው ግልብ ሕሊና ተመርቶ ሳሞራን “የሸዋ አፍቃሪ” ሲል አውጉዞታል።

ለምን ሳሞራን (ፈታዊ ሽዋ) “የሸዋ ወዳጅ” እንዳለው ግልጽ ነው። ሳሞራ ብዙዎቹ የቃለ መጠይቁ ንግግሮቹ ከወያኔነቱ ስንዝር እንኳ ያልወጡ ቢሆንም “ኢትዮጵያ” የሚለው ግን በማድመቅ እኛ ትግሬዎች ጥንትም አሁንም አገራችን ኢትዮጵያ ናት በማለቱ ነው። ሌላው “አፍቃሬ ሽዋ” ያስባለበት ምክንያትም ፤ ሳሞራ በቃለ መጠይቁ ለምንድነው ብዙው የወያኔ ታጋይ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በማባረር ወደ ዳንሻ አራሾች እንዲሆኑ እና ወደ መሳሰሉት እንዲቀነሱ የሆኑበት ምክንያት ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ -- “ከ80 ሺሕ በላይ የወያኔ ታጋይ መከላከያ ውስጥ ነበር፡ ስለዚህ እንደ ኢትዮጵያ ለመቀጠል ሌሎች ኢትዖጵያዊያኖችን ማስገባትና የተወሰኑ ቁጥሮችን ማሰናበት የግድ ነበር፤ ስለዚህ ስለ ኢትዮጵያ ሲባል መላው ኢትዮጵያን ያካተተ ስብጥር መደረገት ነበረበት ከሞላ ጎደል ያደረግነው እንደዚያ ነው።>> በማለቱ ናትናል አስመላሽም እንዲህ ይላል፤ <<ይህ አፍቃሬ ሽዋ ይህ ሁሉ ትግል የታገሉ የትግራይ ታጋዮችን አባርሮ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለኢትዮጵያ ሲባል ኢትዮጵያን ለመጥቀም ሲባል አንድ አምሐራ፤ አንድ ከምባታ፤ አንድ አሮሞ ፤አንድ ሐድያ አምጥተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከሁሉም የተውጣጣ ማድረጉ እንደ ጀግንነት ቆጥሮት፤ ዛሬ ግን የትግራይ ተወላጅ የማይገኝበት መከላከያ  ሆኗል……...” እያለ ሳሞራን በናትናል አስመላሽ ፍረጃ አፍቃሬ ሽዋ አስብሎታል።

 ሳሞራ እኩል የብሔር ተዋጽኦ መስረቶ ነበር ወይ የሚለው ጥያቄ መልሱ “አልነበረም ነው” ። ብዙ ታጋዮች ቢቀነሱም ወያኔ ወደ መቀሌ እስከተባረረበት ወቅት የትግሬ ሰራዊት  እና የትግራይ ታጋዮች ታሪክና ገድል ፤ ወታደራዊ ኮሌጆችና ማሰልጠኛዎች በትግራይ ታጋዮች ስና ገድል እንዲንጸባረቅ የበላይነት ንጣልሎበት የነበ ነው። አልነበርም የሚል ካለ መከራከር ይቻላል።

ልጁ ብዙዎቹን ፕሮግራሞቹን ስታደምጡ ተጀምሮ እስኪያልቁ ሰዎችን በፖለቲካቸው ሳይሆን እጅግ ስድ በሆኑ ስድቦችና የሰዎችን  ስብዕናን እጅግ የሚጋፋ ያልሰለጠነ ያደፈ አንደበት የሚጫነው ልጅ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ኢሳያስ አፈወርቅን ለማድነቅ ቃላት አጥሮት ሲጨነቅ ይውላል። ልክ ሰሎሞን ተካልኝ መለስ ዜናዊን “ቅንድቡ” ብሎ ዘፈን እንደዘፈነለት ልክ ናትናኤል አስመላሽም የሻዕቢያው ጸረ ኢትዮጵያው ኢሳያስ አፈወርቂን ለማወደስ ከ7 ወር በፊት “ፈንቅል” የሚባለው የወንጀለኞች የዘመቻ ድል አብሮ ከሻዕቢያኖች ጋር ለማክበር ምጽዋ ድረስ ሄዶ የኢትዮጵያ አርበኞች ደም የቀለመበት ባሕር  ውስጥ ሲዋኝ የተዝናናበትን ፎቶ ላድማጮቹ እያሳየ የሚኩራራ አስገራሚ ልጅ ነው።

ለሻዕቢያ ያለው ፍቅሩ ገደብ የለሽ ከሞሆን አልፎ በትውልድ ሐረጋቸው ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ተወላጆች የሆኑትን  የሻዕቢያ መሪዎች ያልሸመገሉና ጠንካሮች እንደሆኑ ፤ በመሪነት የሚመራት ኢሳያስ ምርኮኛ የሆነቺው ኤርትራም በመልካም አስተዳዳር እንደሚመራት ከፍትሕ እስከ ምጣኔ ሃብትና ሰላማዊ ድምቀት ጀምሮ እስከ የኢሳያስ ቁመና ግዙፍነቱና ርዝማኔው በመገረም ቃላት አጥቶ እየፈለገ ላድማጮቹ ልክ እንደ “ሰለሞን ተካልኝ” (ቅንድቡ) ናትናል አስመላሽም የኢሳያስ ቁመና ለማየት ምን ያህል ወደ ሽቅብ መንጠራራት እንደሚያስፈልግ በሚገርም “የግፊት ሞገድ” ለአድማጮቹ እያቆነጃጀ ሲያሞጋግሰው መስማት ትውልዱ ስለ ኢትዮጵያ ያለው ግንዛቤና ምን ያህል እንደበሰበሰ ማሳያ ነው።

ይህ ልጅ ሳሞራ የኑስን “አፍቃሬ ሽዋ” (ፈታዊ ሽዋ) ቢለውም አማራ የሚፈቀር እንጂ የሚጠላ ሕዝብ አይደለም። አምሐራነት በደራሲ ባንተአምላክ አያሌው አገላለጽ፤-

<< ዐምሐራነት የሃይማኖት ርትዕነት የሚሰበክበት፤ የፍትሕና የሕግ ምንጭ የሚፈስባቸው ፤ ለምልም እና ጽዱል የሆነ ውብ ሕዝብዊ እሴቶች የሚገኙበት፤ የሀገር ፍቅር እሳት የሚንቦገቦግበት፤አልሸነፍ አልገዛም ባይ ፤ ነፃ አርበኞች በአጽማቸው መከስከስ በደማቸው መፍሰስ በሥጋቸው መቆረስ ኢትዮጵያንንና ኢትዮጵያዊነትን ያጸኑበትና ዛሬም ድረስ ደማቅ ታሪክ የሚጽፉበት ፤ መገፋትን የሚጠሉ ጭቆናን የሚታገሉ ጀብደኞች በየዘመናቱ ለምስክርነት ቆመው የሚታዩበት አኩሪ ማንነት ነው።

አምሐራነት በታሪክ ያሸበረቀ በሃይማኖት የደመቀ ፤ በስነጽሑፍ የተራቀቀ ፤ ዓለም የሚያደንቃትና የሚያውቃት ታላቋን ኢትዮጵያ ተጠፍጥፋ የተሠራችበትና ተቦክታ የተጋገረቺበት የሕልውናዋንም ቀንዲል  የሆነ... ሁሉን አቃፊ ፤ ደርዘ ሰፊ ፤ ዘውገ ብዙ የሕዝባዊነት ማሕተም ነው”

ይህ ኩሩ ሰፊ ዘውገ ብዙ ሕዝብን ነው ከላይ እንደተጠቀሰው ዓይነት ወጣት ትግሬዎችና አፍቃሬ ሻዕቢያዎች የመሳሰሉ የጠላት ችግኞች “ሸዋን” (አምሐራን) በመዝለፍ እርኩስ የጠላት መሳሪያዎች እየሆኑ የኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም እየተናጋ ይገኛል። ብዙዎቹ የወያኔ ትግሬዎችና የኦነግ ኦሮሞዎች ቢሸፋፈኑም ትንሽ ስትፍቃቸው ወያኔና ኦነግ ሆነው ይገኛሉ የሚባለውም ለዚህ ነው።  

ሰላም እንሰንብት

ጌታቸው ረዳ  

 

No comments:

Post a Comment