Wednesday, October 30, 2024

ክፍል 3 የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ምሬትና እውነታዎች ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 10/30/24

 

ክፍል 3 የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ምሬትና እውነታዎች

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 10/30/24

ወደ ዋናው ርዕስ ከመግብቴ በፊት ሚዲያ ተብየዎቹ ሚዛናዊ ያልሆኑ ባሕሪያቸው በፕሮፌሰሩ ብቻ ላይ ለይተው እንዴት አንደተንጫጩ ያሳዩት አድላዊ የትችት ሽፋን አንድ ነገር ልበል።

በበኩሌ ፕሮፌሱን በሚተችበት ጎን ተችቻለሁ። በሚመሰገንበትም እንዲሁ። አሁን በሚዲያው ላይ ሰሞኑን ያየሁት ግን እጅግ የሚገርም ዘረኛ አድላዊ እና ወገንተኛ የሚዲያ ሽፋን ነው። ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ ሲናገረው የምንጮህ (እንዲያውም ታች ካሉት የትሬ ናዚዎች እኩል ንግግር አይደለም) አሉላ ሰለሞንና ቄስ ሰረቀብርሃን፤ ወዘተ የመሳሰሉ የትግሬ “ሐሰን ንጌዜዎች” ከአምሐራ ጋር የተዋለደ ትግሬ እንዲፋታ፤ ማንኛውም ትግሬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፤ ከኢትዮጵያ ካቶሎክ፤ ከኢትዮጵያ ፕሮተስታንት ቤተጸሎቶች እንዳይጽልዩ ፡የአማራዎች ዋሻ ነው። ያ ዋሻ መፍረስ አለበት!! ብሎ  ሲያውጁ፡-

 ኢትዮጵያዊያን ምግብ ቤት አንዳትመገቡ መርዝ አድርገው እንዳይፈጅዋችሁ ፤ በመርዝ ተመርዛችሁ ከመሞት ለመዳን ከፈለጋችሁ መፍትሄው ትግሬዎች፤ ኤርትራኖች እና በአካባቢያችሁ ባሉት የኦሮሞ ንግድ ቤቶች/ቢዝነስ/ ካሉ ከነሱ ጋር ተገበያዩ። የሚለው የአሉላ ሰለሞን አዋጅ ፤ በተለይ ደግሞ ያቺ ልሙጥ ባንዴራ የሰቀሉ ወይንም በንግድ ቤቶቻቸው ውስጥ ካያችሁ እንዳትገበያዩ ሌላ ቀርቶ ቅመምም ጭምር እንዳትገዙ። ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎችን አይወዱህም እና ባጭሩ ከነሱ እራስክን ነጥል። ወዘተ…ወዘተ……..>>  የሚል

 አደገኛ ንግግር ሲያሰራጭ እና የፋሺሰቱ የወያኔው ሚሊሺያው ቄስ “ሰረቀብርሃን” (ቄስ ካቡጋ) አብረው በአምሐራ ሕዝብ ላይ የጥላቻ ንግግር ሲያውጁ እንደ ርዕዮት ሚዲያ የመሳሰሉት ግን በፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘን ላይ ለመኮነን ልዩ ዝግጅት አዘጋጅተው ያሞጠሞጡበት ምላሳቸው የትግሬ “ካቡጋዎችና  ሐሰን ንጌዜዎችን”   ከማውገዝ ይልቅ እንደውም የፖለቲካና የሃይማኖት ተንታኞቻቸው አድርገው በተደጋጋሚ እየጋበዙ እስከዛሬ ድረስ እየቀረቡ ሲየወያይዋቸው አይተናል። ለምን በፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ላይ መረባረብ ተፈለገ?

የሚለው ላንባቢዎች ትዝብት እተውና በነገራችን ላይ “ካቡጋና ሐሰን ነገዜ” ማን እንደሆኑ ለማታውቁ ካቡጋ የሚባለው ሰውየ በሩዋንዳ ዋና ከተማ “ኪጋሊ ከተማ”  አር ቲ ኤል ኤም ተብሎ የሚታወቀው በቱትሲ ጭፍጨፋ ከፍተኛ ሚና የተጫወተ የራዲዮው ዋና ሃላፊ ሲሆን “ሐሰን ነገዜ” ደግሞ በቀረጸው ዘረኛ ሰነድ 35 አመት የተፈረደበት “ካንጉራ” የተባለ መጽሔት ዋና አዘጋጅ የነበረ በመጽሔቱ ላይ “የሁቱ አስርቱ ትዕዛዛት” ተብሎ የሚታወቀው የቀረጸ ፤ ከቱትሲ ጋር የተጋቡ ሁቱዎች እንዲፋቱ ፤ግብይት እንዳያደርጉ ….የጥላቻ  ሰነድ  ያሳተመ ሁቱ ነው።

ፍርዱን ለናንተ ልተውና ወደ ርዕሴ ልግባ።

ባለፈው ሁለት ተከታታይ ትችቶች ስለ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ  “ዓለም አቀፍ የፋኖ አስተባባሪ ኮሚቴ” ተብሎ በሚጠራ የሚዲያ ውይይት ቀርቦ ስለ ልደቱ አያሌውና ስለ መሳሰሉ ፖለቲከኞች ከገንጣይ እና አስገንጣይ ቡድኖች ጋር ሁሌም እያደረገ ያለው የጋራ ውይይት ማድረጉን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን የሰጠው አስተያየት ተገቢ ሲሆን። በዛው ውይይቱም ተጓዳኝ የማይገቡ ብየ የፕሮፌሰሩ የማይጥም ንግግሮቹም አብሬ በክፍል 1 ስተች በሁለተኛው ክፍል ትችቴ  ደግሞ ሊናቁ የማንችላቸው እጅግ ጠቃሚ ክርክቹ ሕዝብ እንዲያውቃቸው አቅርቤአለሁ። ከፕሮፌሰሩ ንግግር የተደመጡ የቁጣ ንግግሮቹ  ምክንያት ተሳብቦ እውነታ ያለቸው ያቀረባቸው የታሪክ ፤ የፖለቲካዊና አሁናዊ አምሐራ ላይ እየደረሰ ያለው አድላዊ እና የዘር ጭፍጨፋ መታፈን እንደሌለባቸው ነው የዚህ ተከታታይ ትችቶቼ።

ስለዚህም በዚህ እንቀጥል፡

አንዳንዶቻችሁ አንደምታውቁት ይህ አብይ አሕመድ የሚመራው “መንግሥት” የኦነግ ኦረሙማ ሥርዓት ነው። ባጭር አገላለጽ <<ኦነጎች የሚመሩት ኦሮሞአዊ ሰርዓት ነው>> በሌላ መንገድ ኦሮማዊ ነው ስንል ብዙ ኦሮሞዎች (3/4ኛው- 95%) የሚደግፉት ርዕዮት የሚያራምድ ነው ማለት ነው። አብይ አሕመድ ኦነግ ነው። በሥሩ ያሉ የሾማቸው ቀጀላ መርዳሳ፤ እነ ደ/ር ዲማ ነገዎ፤ እና በጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አምሐራ ታወቀው ሌንጮ ባቲ (እኛ ኦሮሞዎች  ኢትዮጵያን ኦሮሞ አምሳያ እንደገና ቀርጸን ለ3000 አመት አንገዛችሗለን ብሎ የተናገረ፡ አሁን ዋሺግተን ከተማ የሚገኘው በአሜሪካ የአብይ አሕመድ ኤምባሲ የኦነግ አምባሳደር ተወካይ) እና ከንቲባ (የነበረች) ጫልቱ የምትባለዋ አደገኛ ኦነግ አባል (ከብዙ አመታት “ኦርቶዶክስ ታቦትን ሽንት ቤት ተጥሎ እንዲሰነብት” ያዘዘች) ፤ “የኦሮሞው ካቡጋ” የኦሮሚያ ክልል ፕረዚዳንት ሽመልስ አብዲሳአበበች አደኔታከለ ኡማብርሃኑ ጁላ ፤ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ይልማ መርዳሳ፤ ዲና ሙፍቲ - (የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ቃል አቀባይ የነበረና "ገዱ አንዳርጋቸው" ፓርላማ ውስጥ አማራን ትጥቅ ማስፈታትም ሆነ "በደል ስለ መፈጸሙ በመቃወም ለታሪክ የሚቀረጽ አስገራሚ ንግግር ሲያደረግ “ዲና ሙፍቲ” ለመሰል ኦነግ ፓርላማዎች በዓይኑ ጥቅሻ እያመላከተ "ገዱ አንዳርጋቸው" በክፉ እንዲታይ በካሜራ ተቀርጾ ለሕዝብ ተላልፎ ያነው ሌላው ኦነግ ነው) እንዲሁም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ከፍተኛ እና ዝቅተኛ በፍትሕ መ/ቤቶችና በፖሊስ ሰራዊት የተሰገሰጉ … ወዘተ… ወዘተ…. የመሳሰሉ  የኦነግ አባሎችና የሰልቃጩ የኦሮሙማ ፕሮጀክት አስፈጻሚ ለኦነግ ፖለቲካ ያደሩ ናቸው ስርዓቱን የሚመሩት።

 ከተጠቀሱት አንዱ ዛሬ በሚኒሰትር/በፓርላማ አባልነት ደረጃ ተሹሞ የሚገኝ “የኦነግ መሪ አንዱ” እና የመሳሰሉትን  ሰዎች በሚመለከት ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ አንዲህ ብሎ ነበር፡

“<< የዶ/ር ዲማ ነገዎ ንግግርና የእሱ ትንቢትና ምኞት ዛሬ ላይ እየተፈጸመ ስለ መሆኑ>> እንዲህ ሲል ያስታውሰናል፦

አቢይ አህመድ ሥልጣን ላይ እንደወጣ በሕገወጥ መንገድ አቶ ታከለ ኡማ የተባለ አንድ በዘረኝነት አስተሳሰብ የሰከረ የኦሮሙማን ፓለቲካ በቅጡ ሊያስፈጽም የሚችል የኦሮሞ ካድሬ በከንቲባነት ሾመ። ታከለ ኡማ ከተነሳ በኋላ ደግሞ የኦሮሙማው መንግሥት ወ/ሮ አዳነች አበቤ የተባለችውን የኦህዴድ ካድሬ ከንቲባ በማድረግ የአዲስ አበባን ከተማ የህዝብ ስብጥር ሥር ነቀል በሆነ መንገድ የመቀየር እቅዱን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ። እነዚህ ሁለት ከንቲባዎችና በስራቸው ያሰለፏቸው የኦሮሙማ ፋሽስታዊ ፓለቲካ አራማጆች ባለፉት አምስት ዓመታት የፈጸሟቸው ድርጊቶች፤ የተገበሯቸው ዘረኛ ፓሊሲዎች በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባሉ ከተሞችና ክፍለ ከተማዎች ዛሬም የቀጠለው የዘር የማጽዳት ድርጊት (በሱሉልታ፤ ሰበታ፤ አቃቂ፤ ቦሌ ቡልቡላ፤ ለገጣፎ፤ አሁን ደግሞ ሸገር ብለው በሰየሙት የአዲስ አበባ ክፍል ወዘተ) ከዚሁ የፋሽስታዊ አገዛዝ መሰረት ከሆነው የሶሻል ዳርዊኒስት አስተሳሰብ የሚነሳ ነው።

እነ ሀጂ ጀዋር መሃመድ ዓቢይ አህመድ ሥልጣን ላይ በወጣ ማግስት ሃሮምሳ ኦሮሚያ  (Resurgence of a Dominant Oromo Nationalism and Consciousness) በሚል ሥም በአዲስ አበባ ያሉትን የኦሮሞ ተወላጆች በዜግነት ሳይሆን በአዲስ የኦሮሞን የበላይነት፤ የኦሮሞን ልዕለ-ሰብዕና የሚሰብክ ፋሽስታዊ አስተሳሰብና አመለካከት በመቅረጽ (super-man status of Oromos) ያከናወኑት ሰፊ የሆነ የፓለቲካ ሥራ፤ ተስፋፊነትን፤ ድንበር-ገፊነትን፤ እብሪተኛናትን ጦረኛነትን የሚያበረታታ፤ የኦሮሞን ልዩ ጥቅምና የኦሮሞን የበላይነት የሚሰብክ ፋሽስታዊ የሆነ በሶሻል ዳርዊንዝም አስተሳሰብ የተቃኘ አደገኛና ጽንፈኛ እንቅስቃሴ ነበር። የአዲስ አበባ አካል የነበረን ሰፊ አካባቢ “ሸገር” በሚል ሥም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በማካተት አሁን ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጽዳት ድርጊት (እስካሁን 112000 ቤቶች ፈርሰዋል፤ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች (አማራዎች፤ ደቡቦች፤ ጉራጌዎች ወዘተ) መንገድ ላይ እንዲበተኑና ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። ናዝሬትና ደብረዘይትን በመሳሰሉ ከተሞችም ተመሳሳይ ማንነትን መሰረት ያደረገ የማፈናቀል ድርጊት በስፋት እየተፈጸመ ነው። የአዲስ አበባን ኦሮሞነት ለማረጋገጥ በፍጥነት እየተገነቡ ያሉት የኦሮሚያ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች ግንባታ፤ በከተማዋ ውስጥ ያሉትን የአስተዳደር፤ ቢሮክራሲና የፓሊስ ተቋሞች በኦሮሞ ተወላጆች የሙሙላት ግልጽና ሰፊ እንቅስቃሴ ወዘተ ከዚህ ፋሽስታዊ የኦሮሙማ የአፓርታይድ ሥርዓት መስፋፋት ጋር የተገናኙ ናቸው።

የኦሮሞ ቋንቋን ትምህርት በግዴታ ኦሮምኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ባልሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች ላይ የመጫኑ ድርጊት፤ ነባር የሆኑና ህብረ-ብሄራዊ ቀለም ያላቸው ሀገራዊ ምልክቶችን፤ ህንጻዎችን፤ ተቋሞችን፤ ታሪካዊ ስፍራዎችን በታላቅ ፍጥነት የማፍረስና የማጥፋቱ ዘመቻ  የፋሽስታዊው የኦሮሙማ እቅድ አካል ነው። ይህ የኦሮሙማ የፓለቲካ ንድፍ ወይም ፕሮጄክት ታሪካዊ ስፍራዎችና ምልክቶችን የማፍረስና የማውደም ዘመቻን የሚያካትት ሲሆን በተጨማሪም ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣን የአንድ ሀገር ህዝብ የወል ትውስታ ሥር-ነቀል በሆነ መንገድ (destroying the collective memory of a people in a radical manner) በማጥፋትና በመደምሰስ ኦሮሙማ የተባለውን የኦሮሞን ነገድ የበላይነት የሚሰብክ ፋሽስታዊና ጽንፈኛ የሆነ የአፓርታይድና የአድሎ ሥርዓት ለመተካት የሚደረግ አደገኛና ሀገር-አፍራሽ የሆነ ድርጊት ነው። እዚህ ላይ አንባቢ እንዲረዳ የምፈልገው ፋሽስቶች እነሱ የራሳቸውን ጥቅም በተመለከተ እናስከብራለን የሚሉትን ዓላማ ሁሉ በጭፍንነት ለማሳካት ከፍተኛ ቁርጠኛነትና የዓላማ ጽናት ያላቸው መሆኑን ነው፡፡

ይህንን በምሳሌ ለማስረዳት ዲማ ነገዎ የተባለው (ዛሬ የዓቢይ አህመድ አንዱ ዋነኛ አማካሪና የፓርላማም ተወካይ የሆነ የኦነግ ዋና ሊቀመንበር በነበረበት ወቅት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር መስከረም 1990 ዓመተ ምህረት (ማለትም ከዛሬ 33 ዓመት በፊት) ሙላሃየም (Mulheim) በምትባል ትንሽ የጀርመን ከተማ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ የተናገረውን ነገር ላስታውሳችሁ። ከ33 ዓመት በፊት በዚች የጀርመን ከተማ የኢትዮያ ተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅቶች (ኢህአዴግ፤ ኢህአፓ፤ መኢሶንና ኦነግ) በጀርመን የኢትዮጵያ መንግስት አምባሳደር (አቶ ጥበቡ በቀለ) ጭምር በተገኙበት ስብሰባ ላይ የኦነግ መሪ የነበረው ዲማ የሚመራውን ኦነግ የተባለውን ድርጅት የፓለቲካ መዳረሻና ግብ በተመለከተ “የኦነግ የፓለቲካ ዓላማ ምንድነው” ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው ምላሽ የሚከተለው ነበር። “የኦነግ ዓላማ ኦሮሚያን ነጻ አውጥቶ ፊንፊኔ ላይ የኦሮሚያን ነጻነት ማወጅ ነው”። በዚህ ስብሰባ ላይ እንደኔው ተገኝቶ አዳማጭ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ

<< “አቶ ዲማ አንተ ፊንፊኔ የምትላት የዛሬው አዲስ አበባ ናት። በዛሬዋ አዲስ አበባ ውስጥ ደግሞ አብዛኛው ነዋሪ ኦሮምኛ ተናጋሪ አይደለም። ታዲያ እናንተ ኦነጎች ፊንፊኔ የምትሏት አዲስ አበባ ላይ ነጻነታችሁን ስታውጁ፤ የኦሮሞ ነገድ ተወላጆች ያልሆኑት የዚች ከተማ ነዋሪዎች ምን ይሆናሉ? እጣ ፈንታቸውስ ምንድነው” >> ብሎ ጠየቀው።

 ዲማ ነገዎም

<< “ኦሮሞ ያልሆኑትን ኮሪዶር ከፍተን እናስወጣቸዋለን” >> ብሎ መልስ ሰጠ>>

  ይላል ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ።

በመቀጠል

በወቅቱ እዚያ ስብሰባ ላይ የነበርነው ብዙዎቻችን ይህንን የዲማን ምላሽ እንደ አስቂኝ ነገር ወይም የእብድ ንግግር አንድርገን ቆጥረን ያለፍነው ይመስለኛል። በወቅቱ በዚህ የዲማ ንግግር ሲስቁ የነበሩ ሰዎች እንደነበሩ አስታውሳለሁኝ። ግን ዲማ የሚናገረው ነገር አስቂኝ አልነበረም፤ አስቂኝ እንዳልነበረም ባለፉት አምስት ዓመታት ዲማ ይናፍቀው የነበረው የኦሮሞ መንግሥት ሥልጣን ላይ ወጥቶ ያደረጋቸውን ነገሮች ማየቱ በቂ ነው። ፋሽስቶች የራሳቸውን ጥቅም በተመለከተ እናደርገዋለን፤ እንፈጽመዋለን ለሚሉት ቃል ታማኝ ስለሆኑ ዲማ ከ33 ዓመት በፊት የተናገረውን ነገር ዛሬ እሱ የሚሳተፍበት የኦሮሙማው መንግሥት በተግባር እየፈጸመው ነው

 

ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን የኦሮሙማው መንግስት ዛሬ በሸገር፤ በሱሉልታ፤ በለገጣፎ፤ በሰበታ፤ በናዝሬት፤ በደብረዘይት፤ በአዲስ አበባ ወዘተ ሥልታዊ በሆነ መንገድ እያካሄደ ያለው የዘር ጽዳት ነው። ይህንን ከእዚህ በላይ ዲማ ነገዎ የተናገረውን ሁሉ እሱ መናገሩን የሚመሰክሩ በርካታ ሰዎች ዛሬም በጀርመን ሀገር ይኖራሉ ብዬ አስባለሁኝ። እኔ በምኖርበት በሆላንድ ሀገር የሚኖርና እንደ እኔው እዚያ ስብሰባ ላይ የነበረ ሀገሬ ሃዲስ የተባለ ግለሰብ በህይወት ስላለ ምስክርነቱን ሊሰጥ ይችላል።

እንደምታሳውሱት የወያኔ ትግሬዎች መንግሥት ከትግራይ ክልል በታች በሚኖረውና በዚህ የፋሽስታዊ ሥርዓት በተመረረው ህዝብ ትግል በሚንገዳገድበት ወቅት እነ ዲማ ነገዎ ግንቦት ሰባትን ሽፋን በማድረግ ጥቂት ለዝናና ለታይታ በየቦታው ጥልቅ ብለው የሚገቡ የአማራ ተወላጆችን በአጃቢነትና በአጫፋሪነት ይዘው ግንባር Formation of Alliance of Arbegnotch Ginbot 7 & Oromo Democratic Front

ፈጠርን ብለው ኢሳት በሚባለው የግንቦት ሰባት ልሣን በነበረው የፕሮፓጋንዳ ቴሌቪዥን ሰፊ ሽፋንና ህዝብን የማደናገር ሥራ ይሰሩ ነበር። በተለይም ብርሃኑ ነጋን በመሳሰሉ እጅግ ጸረ-አማራ የሆኑ ግለሰቦች ሲዘወር የነበረው ግንቦት ሰባት ኦነግ ከተባለው በአማራ ጥላቻ ጥርሳቸውን ነቅለው ባደጉ የኦሮሞ ፋሽስቶች ጋር በማበር አማራ የተባለውን ሰፊ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ አካል ከማናችውም የኢትዮጵያ ፓለቲካ ለማግለል በብርቱ ሰርተው ጥረታቸውም ሰመረላቸው። ወያኔን አሽቀንጥሮ የአማራዎች አስተዋጽዖም ተረስቶ አማራን ጭራሹኑ የማያቋርጥ የጥቃት ዒላማ ያደረገ የኦሮሙማ መንግሥት ወደ ሥልጣን ላይ መጣ። የዚህን የኦነግና የግንቦት ሰባት ጥምረት በማምጣት ዋና አስተባባሪ በመሆን ኦነግ ውስጥ ለውጥ መጥቷል እያለ ድንቁርናና የእውቀት-እጥረት በሚፈጥረው ግትርነት በየመድረኩ ሲሰብክ የነበረውና በተለይም በእነ ኢሳት ላይ ሰፊ ሽፋን ይሰጠው የነበረው ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ነበር።

እነሆ ጌታቸው በጋሻው በ2011 እ.አ.አ. በመድረክ ላይ ወጥቶ ካደረገው ንግግር ኦነግን የመሳሰሉ የነገድ ድርጅቶችን አስመልክቶ የተናገረው የሚከተለው ነው።

<< “ሁለተኛ፡ የዘር ድርጅቶች የትግሉ አካል እንዲሆኑ መጣር ያስፈልጋል:: ይህ አዲስ ሀሳብ አይደለም፣ ያልተጀመረ ሙከራም አይደለም። በዚህ ረገድ ድርጀት ለድርጅት ውይይት ለጀመሩትና አንዳንድ ትብብሮችን እያሳዩ ላሉት የፖለቲካ ኃይሎች፣ ማለትም ለግንቦት 7፣ ለኦነግ፣ ለኦብነግ፣ ለአፋር ድርጅትና ተባባሪ ለሆኑት ሌሎችም ያለኝን ምስጋናና አድናቆት ለመግለጥ ይፈቀድልኝ።...................ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የዘር ድርጅቶችን፣ በተለይም ኦነግን፣ እንደ ፀረ-አንድነትና እንደ ጠላት በመፈረጅ፣ ምናልባት ወንዝ ለማታሻግር ትንሽ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ለመሸመት ባዶ የመግለጫ ጋጋታና ፍሬ-ቢስ ጫጫታ የሚረጩ እንዳሉ መገንዘብ ይበጃል። በኢትዮጵያ ሰላማዊ ሕዝብ መሀል ጥላቻን የሚዘሩና በድርጅቶች መሀል ሊኖር የሚችለውን መግባባትና መተባበር ለማደፍረስ የሚያከሄዱት ኃላፊነት የጎደለው ተግባራቸውም ሊጋለጥ ይገባል።..........

......ለመሆኑ፣ በመጀመሪያ ደረጃ፣ እነኝህ “በኢትዮጵያ አንድነት” ስም ይህንን ያህል የዘር ጥላቻ የሚነዙ ከፋፋይ ኃይሎች ዛሬ ማን ሆነው ነው፣ ዬት ቆመው ነው፣ ማንን ይዘው ነው የዘር ድርጅቶችን እንዋጋቸዋለን የሚሉት? ለአገር አስባለሁ የሚለው ወገን እውነት ለአገር አሳቢ ከሆነ በመጀመሪያ የራሱን ድርጅታዊ ድርሻና አቅም ከነዚህ ሁሉ የዘር ድርጅቶች ጋር አነጻጽሮና አወዳድሮ ይመለከታል፤በዚያም የሚናገረውን ይመጥናል፤ የሚጽፋቸውና የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች በሕዝበ የወደፊትና የዛሬ ህይወት ላይ ምን የፖለቲካ ውጤት እንደሚኖራቸው ይመረመራል፣ በዚህም ኃላፊነትን ይወስዳል። እስቲ ስለ እውነት እንጠይቅና ከእነኝህ ድርጅት ኮናኞች ውስጥ ዬትኛው “የአንድነት ኃይል” ነው፣ ዛሬና ወደፊት፣ ይህን የሚቀፈቅፈውን የጠላትነት አቋሙን ይዞ ኦሮሚያና ኦጋዴን ተብለው በተከለሉ ግዛቶች ውስጥ ሄዶ ለማደራጀት፣ ለመመልመል ለማስታጠቅና የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ የሚችለው? ምነው ሁኔታዎችን ቢለዩና የሚናገሩትን ቢያውቁ፤ ምነው አቅማቸውን ቢመዝኑና አደብ ቢገዙ!>>  (ጌታቸው በጋሻው ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ የምንለውን ለኦበ2011 እ.አ.አ. በመድረክ ላይ ወጥቶ ካደረገው ኦነግን የመሳሰሉ የነገድ ድርጅቶችን አስመልክቶ የተናገረው)  ምንጭ -(ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ (Ethiopian Semay) 4/6/23 ከኦሮሙማው የፋሽስት መንግሥት ጋር ድርድር አይሞከር ለፋሽስቶች ድርድር ጠላቶቻቸውን አዘናግቶ የማጥፊያ መሳሪያ ነውና!!!!!! ክፍል ሁለት፡) ከሚል የተገኘ።

ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው በአሜሪካ ባሉት ዩኒቨርሲቲዎች ተቀጥሮ  የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ነው። የጸረ ኢትዮጵያውና ጸረ አማራው የ60ዎች የተማሪዎች እንቅስቃሴ  አመራር አባል እና ቆይቶም የኢሕአፓ አመራር አባል የነበረ ነው። አርባ ምንጭ ያደገ የአምሐራ ነገድ ተወላጅ ነው። እኛንኑን “ኢትዮጵያ፤ኢትዮጵያ” እያልን ኦነጎችን በመቃወማችን << እነዚህ የጥላቻ ቀፍቃፊዎች ምነው ሁኔታዎችን ቢለዩና የሚናገሩትን ቢያውቁ፤ ምነው አቅማቸውን ቢመዝኑና አደብ ቢገዙ!>> እያለ ለኦነጎች ወግኖ ሲዘልፍን ሲንቀን ከላይ አይታችኋል። ጭራሽኑ እንደውም “ኦነጎች የመገንጠል ጥያቄ ጠይቀው አያውቁም” የሚለው ንግግሩ ቪዲዮው ከብዙ አመታት በፊት አቅርቤላችሁ እንደነበር አስታውሳለሁ።ዶ/ር ጌታቸው በጋሻውም ለኦነጎች እንደ ልደቱ አያሌው ለወያኔዎች ስስ ልብ የነበረው ፖለቲከኛ ነው።

ይህንን በሰነድ ሳስጨብጣችሁ የፕሮፌሰር ብታሙ ተገኘ ንግግር ይህንን አንዳንዶቻችን የምንቀበለው <<ኦሮሙማ የውስጥ ቅኝ ግዛት ስርዓት>> የሚከተሉት ባሕሪ ለአምሐራ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ ህልውና አደገኛ እየሆነ መምጣቱና <<የኦሮሞና የትግሬ ናዚዎች በአምሐራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየፈጸሙ የሕዝቡን ኑሮ ከሚያመሰቃቅሉ የኦሮሞ ናዚዎችም ሆኑ የትግሬ ናዚ ፖለቲከኞች ጋር አምሐራ ነኝ የሚል ፖለቲከኛ አብሮ የሚወያይበት መንገድ ለናዚዎቹ መንገድ መጥረግ ካልሆነ ለተጨፍጫፊው ሕዝብ ምንም የሚያመጣው ጠቀሜታ የለውም ፤ ባይ ነው ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ።

ፕሮፌሰር ሃብታሙ ልክ ነው። እኔም ሆንኩ አንዳንድ ወዳጆቼ  አምሐራዎች ራሳቸውን ችለው በመሳሪያ የመከላከል አቅማቸው  እኩል እስኪገነቡና “ሪኮግኒሽን/ርስፔክት” እስክያገኙ ድረስ ከጠላት ጋር መሞዳሞድ እርባና ቢስ ነው ብየ በዚህ ጉዳይ ተደጋጋሚ ጽሑፍ ለብዙ አመታት አቅርቤ ሰሚ አላገኘሁም ነበር። ውጤቱ ደግሞ ከላይ በማስረጃ እንዳሳየሁዋችሁ ነው። ስለዚህ የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ጠቃሚ ክርክሩ መታፈን የለበትም ፤ በአመክንዮና በእውነተኛ ታሪክና ፖለቲካ የተደገፈ ምሬቱንም መቀበል አለብን የሚለው የመጨረሻ ጽሑፌ እዚህ ላይ እያቆምኩ ፤ ከናዚ ኦነጎችም ሆኑ ፋሺሰት ትግሬዎች ጋር የሚደረግ የጋራ ውይይት ሳይሆን ካስፈለገም የሚዲያ “ዲቤት” እንጂ እንደ ዕርግብ እየተላላሱና “ጋሼ…” እየታባሉ እየተጋገሱ አፍ ላፍ ገጥሞ መፍትሄ አምጠለሁ ማለት መቆም አለበት።

ናዚዎችና ፋሺሰቶች ውይይት ሳይሆን ሃይል ያስፈታቸዋል ፤ ለውይይት በተጠጋሃቸው ቁጥር ሕዝብን ወደ መጨፍጨፍና ማባረር ነው የገቡት ፤ በፍቅር፤ በወንድምትና በዕልልታ ተሞክረው ተፈትነው ወድቀው አይተናል። እነ ጃዋርን ጃኖ እና ካባ ያለበሰ ፡ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ስለፍቅር ስለ ሰላም ብላ ለአክራሪ “ኦርሞፕሮዎቹ” ፕሮተስታንቶቹ ለአብይ አሕመድ ከነ ባለቤቱ የጣት ቀለበት አበርክታ ፤ በአምሐራ ሕዝብና በኦርቶዶክስ አማኞች የተነጠፈላቸው ዘምባባና አበባ ረግጠው የአምሐራ ሙስሊምና አምሐራ ኦርቶዶክስኖችን ደም ካፈሰሱ አካላት ጋር መሞዳሞድ ይብቃ። የዳንኪራው ምት ሲቀየር እስክስታውም እንዲሁ መቀየር አለበት።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) ድረገጽ አዘጋጅ

 

 

 

No comments:

Post a Comment