አዲስ መጥረጊያ (The New Broom)
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
9/22/24
ፖለቲካዊ ትችቴን ካቀረብኩ ትንሽ ቆየት ቢልም ለዛሬ የማቀርብላችሁ እኔን ባስደነቀኝ ዘመናዊና ሃገራዊ የክሕነት ትምሕርት የተማሩ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊት ወጣት ምሁራን ሃገራችን የተጠቃችበት መንገድና አጥቂዎቹ እነማን እንደሆኑ የሚገርም ምሁራዊ ምጉትና ትንተና እነሆ አንድታደምጡ አቅርቤአለሁ። ተወያዮቹ አዲስ መጥረጊያ (The New
Broom) ብያቸዋለሁ።
ኢትዮጵያ በኤርትራና በትግራይ ፋሺቶች ሴራ የደረሰባት ጥቃት ፤ ”ጠባሳው” እስከወዲያኛው የሚሽር አይደለም። ሆኖም ኢትዮጵያ ወደቀች ስትባል የመነሳት አቅምዋ በሃይማኖታችን እንደተባለው “እጆችዋን ወደ ፈጣሪዋ ትዘረጋለች” በተባለው ሃገራዊ መርሆ ምክንያት ደጋግማ ስትንሳ ታሪክ አሳይቶናል። ዛሬ የመነሳትዋ ምልክትም ከነዚህ ወጣቶች አንደበትና ሃይለኛ ምጉት ማየት ችያለሁ።
በሚቀጥለው ሳምንት የማቀርበው ትችት
ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሀገራችን ለደረሰባት ጥቃት ቀዳሚ ተጠያቂዎች ምሁራን (ሁሉም ባይሆኑም አብዛኛዎቹ) ሲሆኑ፤ ከዚያ ካለፉት የጥፋት አመንጪ ምሁራን “ሳይማሩ ቀርተው” ዛሬም ፖለቲካውን በተቃዋሚነት የሚመሩ ተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች “ሠላማዊ የሽግግር መንግሥት” ለማምጣት የውይይታቸው ተሳታፊዎችን የሚጋብዙዋቸው ተሳታፊዎቹ ብዙዎቹ “በአማራና በአማርኛ፤በኦርተዶክስ ተዋህዶና በሰንደቅዓላማችን ባጠቃላይ ኢትዮጵያን ለደረሰባት ግፍ ሁሉ ተጠያቂ ለሆኑት አካሎችን ታሳታፊዎች በማድረግ በተጎጂዎች ላይ ያሾፋሉ።
ይህ አካሄድ ተደጋግሞ ወያኔን ለመጣል ሲደረግ በነበነረው ወንጀለኞችን ሁሉ መድረክ የሰጠ አንዳንዴም እንደልባቸው እንዲዋኙና እንዲዋሹ ያደረገ የመተሻሸት ትግል የከሸፈ ድጋሚ አሰራር ስለሆነ ያንን በሚቀጥለው ሳምንት ይዤ እቀርባለሁ። እስከዛው ይህንን አስገራሚ ክርክር አድምጡ።
"ቤተ ክርስቲያን ለምን ራሷን መከላከል አልቻለችም?" - ክፍል 2 | ደብተራና ካህናት በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ (ከ1900 - 2013 ዓ.ም)
https://youtu.be/r-4Q8_wdkAQ?si=pI9rEv8ApMjZOvo5
No comments:
Post a Comment