የአሳምነው ጽጌ “አንድ ሁኑ”
አደራ በመጻረር
“ሰለ ራሱ ርዕሰ” እያተኮረ ያለው “የጎጃሙ ኢጎ”
Ethiopian Semay
ጌታቸው ረዳ 7/10/24
ወዳጄ ብስራት ደረሰ አምና በጻፈው ድንቅ ትችቱን ልጀምር፡፡ “ምንም ነገር የመጻፍ ፍላጎት የለኝም፡፡ ጊዜው ሀገራችን ልትወለድ ምጥ የበዛበት በመሆኑ
ከመጻፍ ይልቅ የነገሮችን አካሄድ በጥሞና የመከታተያ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ላለፉት አራት አሠርት ዓመታት ገደማ ብዙ ብለናል፡፡
አሁን በክፉም ሆነ በደግ የገነኑ ሰዎች ወደ መድረክ ከመዝለቃቸው ብዙ ዓመታት አስቀድመን ስለሀገራችን መፃዒ ሁኔታ ሣይቀር ጥቂት
የማንባል ወገኖች ብዙብለናል፡፡ ከጮህንበት ውስጥ አብዛኛው በተግባር ታይቶ የሀገር ትንሣኤው ብቻ ይቀራል፡፡ ይህ ነባራዊ ክስተት ደግሞ በቅርቡ እውን ይሆናል፡፡ የሀገር ጠላቶችም ግብዓተ
መሬታቸው ይፈጸማል – ዓለም እያዬ!! የላል፡፡
በመቀጠልም
እንዲህ ይላል፤
በዚህን አስቸጋሪ ወቅት ነው እንግዲህ ዝም ማለት ያላስቻለኝ ነገር የተፈጠረው፡፡ ነገሩ ትናንት ማታ ነው፡፡ አንድ ሚዲያ ስከታተለል ታጋይ አርበኛ ዘመነ ካሤ ሲናገር ሰማሁና ሙሉውን አዳመጥኩት፡፡ ጥሩ ንግግር ነው፡፡ ነገር ግን የእስክንድርን ስም ሲያነሳ “ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ” ብሎ እንደቀላል ነገር ሲናገር ስሜቴ ተረበሸ፡፡ እኔ ዘመነን ብሆን “አርበኛ ፋኖ እስክንድር ነጋ” እል ነበር – “አክቲቪስት፣ ጋዜጠኛ፣ ታላቁ እስክንድር…” የሚለው ቀርቶበት አሁን በተሠማራበት የትግል መስመሩ ቢጠራ ማንም አይጎዳም፤ መከባበር ደግሞ ከቤት ይጀምራል፡፡ “ከአነጋገር ይፈረዳል፣ ከአያያዝ ይቀደዳል” እንዲሉ መላ ሕይወቱን ለሀገሩ የገበረን ሰው በዚህ መልክ አሳንሶ መጥራት ለኔ የሸተተኝ ነገር አለ – ጋ ዜ ጠኛ መ ባሉ አይደለም ማነሱ ግን እስክንድር በረሃ የወረደው የፋኖን ውሎና ውሎና አዳር ለመዘገብ ሣይሆን ለትግል እንደመሆኑ ጋዜጠኛ ተብሎ መጠራቱ ለነገር እንጂ ለበጎ አልመስልህ አለኝ ፡፡ እርግጥ ነው እስኬው ጋዜጠኛ ነበር፡፡ አሁን ግን አይደለም፡፡ እንዳልኩት አሁን ሌላ ነው፡፡ የፋኖ አደራጅና ትልቅ ሥራ በመሥራት ላይ የሚገኝ ሁለመናውን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ የሰጠ እንደማንኛውም የፋኖ አባል ሁሉ ውድ ልጃችን ነው፡፡ ጋዜጠኛ መባል ከነበረበት በፊት ነው፡፡ አሁን ግን ይህን ዕንቁ ሰው ወደ ዱሮውና አሁን ወደማይሠራበት የጋዜጠኝነት ሙያ መመለስ ውስጠ ወይራው አልገባኝም፡፡ ለምን?
ሲል ይጠይቃል፡፡
አንግዲሀ ወዳጄ ከማንም ሰው በፊት አሰቀድሞ የዘመነ ደንቃራነት ታይቶት በድፍረት የነገረን ትክክል ነበር፡፡ ወጣቱ በክፉ ኢጎ የሚሰቃይ ጠባብ ብሔረተኛ ይመሰላል (ይገባችኋልና ለዝረዝሩ ጥልቅ አልገባም)፡፡ “ኢጎ” የበቃ የአማርኛ ትርጉም ባላገኝበትም “Ego/ኢጎ” በራሴ ትርጉም “ደንቃራ ማንነት” በሚል ተርጉሜዋለሁ፡፡ አንድ ሰው “ትልቅ ኢጎ” አለው ካልን “ራሱን ሰለ ራሱ በራሱ የሚሞላ” (ፓምፐድ/የሚቆለል/የሚኮፈስ) ማለት ነው። ፋሺስቶች ይህንን ባሕሪ የተላበሱ ናቸው፡፡ በዚሀ ባሕሪ የሚነዳ ስለ ራሱ ያለው ግምት ከፍ በማድረግ አካባቢውን በዝቅታ የሚያይ ማለት ነው (የወያኔ እና የሻዕቢያ አመራሮች ለዚህ ትክክለኛ ማሳያዎች ናቸው)፡፡እንዲሀ ያሉ ሰዎች ፖለቲካ ወሰጥ ሲገቡ ከአካባቢያቸው ጋር ለመስማማት እጅግ ደንቃሮች ሰለሚሆኑ ሁለት ነገሮችን ያስከትላሉ “አምባ ገነን የሆናሉ፤ አልያም አንድነት እንዳይኖር ‘ብጥብጥ” የፈጥራሉ (ለዚህ ማሳያ “ሃመቲ እና አል ቡርሃን” ሁለቱ የሱዳን ጀኔራሎች ማየት ይቻላል)፡፡ አሁን እየተናገረኩ ያለሁት የጎጃም ፋኖ ተብሎ ስለተሰየመው መሪ ዘመነ ካሴ ነው፡፡
ስለ ዘመነ ካሴ ስተች አሁን ሳይሆን ከጸረ-አማራዎቹ ከነ “አንዳርጋቸው ጽጌ” ፤ “ብርሃኑ ነጋ” እና “ኤፍሬም ማዴቦ" ጋር ሻዕቢያ በሰጣቸው ምሽግ የግንቦት 7 ቃል አቀባይ ሆኖ ሲያገለግል ፤ <<የተቆራኘሃቸው ሰዎችና ድርጅት ጸረ-አማራዎች ናቸው “ተው” ስንለው>> ምክር መስማት እምቢ ብሎን ሲያሰቸግረን ካናዳ የምትኖር የግንቦት 7 እልም ያለች አማኝ (ካልት) ያንዲት ናላዋ የዞረባት ዘረኛ የጥንት ዘመን ጋዜጠኛ ነበረች የሚባልላት _የመጀመሪያ ሰሟን ረሳሁት አባትዋ “ወንድማገኝ” ይባላሉ፤ የምትታወቀው ሙያየ ምስክር (ቅጽል ሰም) እየተባለች የፓል-ቶክ አዘጋጅ የነበረች ተጠያቂና መልስ ሰጪ ሆኖ የነበረ ባለ ኢጎ (ተቆላሊ) ሰው ነው: ዘመነ፡፡ ስለዚህ ስለ ልጁ በወቅቱ በርካታ ትችቶች ስተች ስለነበር ልጁን በሚገባ አውቀዋለሁ ለማለት ነው፡፡
ዛሬ ስለ ፋኖ እየተሰማ ያለው ያንድ አመት የእርስ በርሳቸው ያለመስማማት ነገር ላለማባባስ ሂስ ላለመሰጠት ተቆጥቤ እንደነበርና እንዳልጻፍኩ ታስታውሳላችሁ፡፡ በቅርቡ የሰማነው ደግሞ የፋኖ አንድነት ለመመስረት ከእየ ክፍሉ ዋና የሚባሉ ተወካዮች በስልክ ለመነጋገር ሲገኙ ዘመነ ካሴ የተባለው በጥራቃ ላለመገኘት ወስኖ እሱን የሚወክል አስረስ ዳምጤ የተባለ ታጋይ መላኩን ኤርሚያሰ ለገሰ በይቱብ መድረኩ ነግሮናል፡፡ስብሰባውን የመራው ሰው ደግሞ ታወቁታላቸሁ፡፡ ‘ወያኔን በማመስገኑ ባለፍው ሰሞን የተቸሁት የዘመነ ቃል አቀባይ የሆነው ማርሸት ጸሃየ ነው፡
ፋኖን ባንድ ዕዝ ለምመራት ከተገኙ ከ9 ተወካዮች ሁለት ሰዎች ብቻ ለምርጫ እንዲቀርቡ ሲደረግ
ሁለቱ ደግሞ ተበጥራቂው ዘመነ እና አስክንድር ነጋ ሲሆኑ ፤ ተበጥራቂው
3 ድምጽ ሲያገኝ የተቀሩት ከፍተኛ ድምጽ የወገነው ለታላቁ እስክንድር ነው፡ የላል ኤርሚያሰ ለገሰ (አገኘሁ ከሚለው መንጭ ጠቅሶ)
፡፡ በዚህ የተበሳጨው ማርሸት የተባለው ሰብሳቢ ስልኩ አልሰራልኝ አለ ተብሎ ስብሰባው ያለ እልባት ቆመ ተባለ፡፡
በማግስቱ ስብሰባ ይጠራል ሲባል የጎንደሩ ተወካይ ደግሞ ባልታወቀ ምክንያት ሎምቦጩን ጥሎ አልገኝ አለ ተባለ፡፡ ወይ ትጉዱ!! እንላለን እኛ ትግሬዎች ሲገረመን፡፡ እናንተ “ወቸው ጉዱ! የምትሉት፤
ይህ ሁሉ የሚያሳየን የተበታተነው ፋኖ የሚመሩት በዙዎቹ በደንቃራ ሕሊና የሚገዙ
(በጫካ ሕግ የጎበዝ አለቃ) የሚመሩ ሲሆኑ ባንድነት ሕግ የሚያምን ካለ ከታላቁ እስክንድርና ጠቂቶች በቀር በዙዎቹ የፖለቲካ
የሕዝብ ገነኙነት ብስልታቸው ዝቅተኛ ሰዎች የሚመሩት የጥንት ዓይነት
የጎበዝ አለቆች ክፍፍል ባሕሪ መኖሩ ያሳየናል፡፡
እኔ የገረመኝ ጎንደር ፤ ጎጃም ፤ ሸዋና ወሎ አይተዋወቁም ነበር፤ እርስበርሳቸውም አይዋደዱም ፤ይናናቃሉ ሲባሉ የነበረው ሐሜታ እውነትነት ያለው የሚመስል ክስተት እያየን ነው፡፡ ወያኔ እንደሚለው፤ አማራ የሚባል አልነበረም ፤ አራቱ አይተዋወቁም አንድ አድርገን ”አማራ” ያደረግናቸው እኛ ነን፡ የሚለው እና ፕሮፌሰር መስፍን (ነብሳቸው ይማር) እንዲሁ የጎንደር ሰው፤ ከሸዋው’ የጎጃሙ ከጎንደር አይተዋውቁም፤ ጋብቻም የላቸውም ..ጋብቻ ለማድረግም ጎንደሬው የሚቀናው ከትግራይ ነው። ያሉት ንግግር አሁን ሁኔታው ስናይና ሲፈተሽ “አላልናቸሁም ወይ?!” የሚሉ አይመስላችሁም? ነገሩ መልስ የሚሻ ይመስለኛል፡፡
የፋኖዎቹ አንድ አመት ሙሉ ጠብቀን ዝርክርክነታቸውና ያለመዋደዳቸው ሲመዘን
: የተባለው ሃሜት እንዴት መከላከል ይቻላል? ጥያቄው የአሳምነው “አንድ ሁኑ!! የአደራ ቃል ዘመነ እና መሰል ፋኖዎች
ለምን አልተገበሩትም? አደራን መብላት
የተሰዋበትን መስመር መናቅ ካልሆነ አንድ ላለመሆን ሌላ ምን ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል?
ዘመነ የተባለው “ተበጣራቂ ኢጎ” ስብሰባው ላይ በስልክ ላለመገኘት የሚያሳየን ንቀት (ወይንም ፍርሐት) ልጁ ምን ያህል ከራሱ በላይ ሊዘል የሚዳዳው ተበጥራቂ “አምባገነን መሆኑን ያሳያል፡፡ ከእስክንድር ጋር ያለው አለመጣጣም ምን እንደሆነ ባናወቅም በስነ-ልቦና ሚዛን ስንገመግም እኔ ልግነን የሚለው ‘ደንቃራ ባሕሪው’ Extreme Gojame nationalism የወጠረው ይመሰላል (በግልጽ አማርኛ ለማስቀመጥ!!)፡፡ ሰለሆነም እንደ ገነፈለ ቡና 'ሰከን' በል ማለቱ አሁን ነው፡፡ አማራ ራሱን ለመከላከል የዘመነ መሳተፍ አሰፈላጊ ቢሆንም፤ ያለ ዘመነ ራሱን መመከት ይችላል፡፡ የህንን ማሰተዋል ያሰፈልጋል፡፡ በጠባብ በሔረተኛነት መወጣጠሩ ለወያኔም አላዋጣም፡፡
ብዙ የፋኖ ወታደራዊ ጀነራሎች፤ ሻለቆች ኮሎኔሎች፤ ዶከተሮች መሃንዲሶች፤ ጠበቆች፤ወታደሮች፤ ፖለቲከኞች፤ መሪዎችና ተዋጊዎች ወዘተ…. ወደ ትግሉ በተቀላቀሉበት ሰዓት የዚህ ልጅና ሸዋ ወስጥ ያለው አንድ በትረ ቀላል ጸረ እስከንድር የሚፎክር የሸዋ ፋኖ ነኝ የሚል “ደንቆሮ” ካሁኑ ካልታረሙ ትግሉ ለጠላት አመቺ እንዳያደርጉትና በመጨረሻ እጅ እንዳይሰጡ ስጋት አለኝ
በትግል እና በአመራር የተፈተነው ማን ነው? የሚል ጥያቄ ቢቅረበላችሁ; መጀመሪያ ወደ ሕሊናችሁ የሚመጣው ሰው “ታላቁ እስክንድር ነጋ ነው”! እስራት ፤ድበደባ፤ እርዛት፤ ቱሃን እና ጫና የማይበግረው በሕሊናም በጽናትና በፖለቲካም የፋሺስት ሰብስብ ወያኔን ኦሮሙማ አብይንና ኦሮሙማ ኦነጎችን ያንቀጠቀጠው የማይታጠፍ ብረት ሰው፤ እስክንድር የመጀመሪያ ሰው በሕሊናችሁ ይመጣል
የጎጃሙ ተበጥራቂና
መሰሎቹ ያንን ታላቁ ተራራ እሰክንድርን ለመነቅነቅና ለመናቅ እየዳዳው
ያለው፡ ልጁ ወደ መስመሩ ከገባ “ቪ
ቫ!!” እንለዋለን፤ ካለሆነ ደጎም “እርጉም ከመ አርዌ” ይባላል፡፡
በወዳጄ ጸሁፍ ልደምድም፦
አራት ኪሎ የሚችለው አንድ ሰው ነው፡፡ 15 ሚሊዮን ፋኖ ቢኖር ሁሉም አራት ኪሎ
አይገባም፡፡ 100 ሽህ የፋኖ መሪ ቢኖር ሁሉም ያቺን የምታሳብድና የምታቃዥ ወንበር አይዝም፡፡ በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም የሚባለው
አለነገር አይደለም፡፡ በረሃ እያለ በአልደፈርም ባይነት የሚኩነሰነስና በብዙ አጃቢ የሚቆነን ሰው አራት ኪሎ ቢገባ ምን ሊያሳየን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት አይከብድምና ከዚህ ዓይነቱ መጥፎ ጠባይ እንድትርቁ ምክራችን የሚያስፈልጋችሁ
ወገኖቻችንን ከአሁኑ እንመክራለን፡፡ ሰው ዐይን ውስጥ አትግቡ፡፡ ትሁት ሁኑ፡፡ ትኅትናችሁ ወደላይ ያውጣችሁ፡፡ ላዩን ከፈለጋችሁ ደግሞ ታቹን ምረጡ፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከክርስቶስ
ትኅትናን ተማሩ፡፡
አሁን ደግሞ የወቅቱ ትኩረት የወንበር ጉዳይ ሳይሆን የኅልውና ጉዳይ ነው፡፡ መጀመሪያ
የመቀመጫየን ብላለች ዝንጀሮ፡፡ አማራ በመሆኑ ምክንያት ተወልዶ እንዳያድግ ጽንስ ከሆድ እየተቀደደ ወጥቶ አንገቱ በቢላ በሚቀረደድበት ሰዓት፣ አማራ ቆሞ ብቻ ሳይሆን ታሞ ተኝቶም
መኖር እንዳይችል ከያለበት በአክራሪ ኦሮሞ እየታደነ በሚታጨድበት
ወቅት፣ የአማራ ምድር የሚባለው ሳይቀር በኦህዲድ መከላከያ ተወርሮ ዜጎች ቀን ከሌት እየታጨዱ በሚገኙበት ዘመን፣ አዲስ አበባ መግባት
ለአማራ ህልም በሆነበት ሁኔታ፣ የአማራ ቤትና ሰውነት በተረኛ ዘረኞች እየፈራረሰና አማራ ሎተሪ አዙሮ ወይም ዘበኝነት ተቀጥሮ እንኳን
መኖር ባልተፈቀደለት ወቅት… እንዲህ ዓይነት ቅንጡ የሥልጣን መራኮት ከአሁኑ ሲታይ በርግጥም የአማራው መረገም ሥር የሰደደ እንደሆነ
መረዳት አይከብድም፡፡
ስለዚህ እባክህን ዘመነ ሆይ! እባካችሁን ዘመነዎች ሆይ! መጀመሪያ በየቀኑ ለምንታረደው
ዜጎች ቅድሚያ ስጡ፡፡ የሥልጣን አራራውና ሽኩቻው ይደርሳል፡፡ ሀገር ሲኖር ለሚደርስ ነገር ጠላቶች እስኪስቁባችሁ ሳይቀር አትወዛገቡ፡፡
አማራን አማራ እንዲህ እየጠለፈው የትም አይደረስም፡፡” ይላል ወዳጄ ብስራት ደረሰ አምና ባሰተላለፈው
ምክር፡፡
ሰላም ለኩሉኩሙ
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን፡
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment