Thursday, October 21, 2021

መፈንቅለ መንግስትና ሕዝባዊ አልገዛም ባይነት ሁለቱ አስፈላጊ ናቸው ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) ኢትዮ ሰማይ 10/22/2021

 

 

መፈንቅለ መንግስትና ሕዝባዊ አልገዛም ባይነት ሁለቱ አስፈላጊ ናቸው

ጌታቸው ረዳ

 (Ethio Semay)

 ኢትዮ ሰማይ

10/22/2021

መፈንቅለ መንግሥት በኢትዮጵያ

አንጀት አርስ ሞጋች በታጣበት በዚህ ፈታኝ ዘመን እምዬ ኢትዮጵያ አምጣ የወለደችልንን ወጣቱ ብርቅየው ኢትዮጵያ ወዳጄ አቻምየለህ ታምሩ ስለ መፈንቅለ መንግሥት አላስፈላጊነት ያተተበትን ጽሑፍ ትናንት አንብቤው ነበር። መልእክቱ መቶ በመቶ ከእውነተኛ ስጋት የመነጨ እና እኔም ስጋቱን የምጋራው ብሆንም በሰጠው አገላለጽ ግን የማልስማማባቸው ነጥቦች አሉ።

መጀመሪያ የወንድሜን አቻምየለህ እምነት ልጥቀስ።

እንዲህ ይላል፡

ኢትዮጵያ ጠንካራና ብሔራዊ ስሜት ያለው ማዕከላዊ መንግሥት፣ ያልተከፋፈለና ከፖለቲካ አመራሩ ጋር ስምሙ የሆነ የአገር መከላከያ ሠራዊት ሲኖራት በታሪኳ ያጋጠሟትን ችግሮች ሁሉ በድል ስትወጣ ኖራለች። በተቃራኒው ደካማና ብሔራዊ ስሜት በሌለው ማዕከላዊ መንግሥት ላይ ስትወድቅ፤ የተከፋፈለና ከፖለቲካ አመራሩ ጋር ስምምነት የሌለው የመከላከያ ሠራዊት ሲኖራት ደግሞ የታሪካዊ ጠላቶቿ ሲሳይ ስትሆን ኖራለች። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንዲከፋፈል፣ መፈንቅለ መንግሥት እንዲያደርግና ለአመራሩ አልታዘዝም ብሎ ስዒረ መንግሥት እንዲሞክር ሌት ተቀን ሲወተውቱ የሚውሉ የፋሽስት ወያኔ አጋሰሶች ኢትዮጵያ የጠላቶቿ ሲሳይ እንድትሆን ተግተው የሚሰሩ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አገር በቀል ወኪሎች ናቸው።ይላል።

በጣም የሚያወያየን ነው።መጀመሪያ ከላይ የተጠቀሰው የመጀመሪያው መስመር አልስማማም። ምክንያቱምአሁን ያለው መንግሥት ጠንካራ እና ብሔራዊ ስሜት ያለው መንግሥት የለም። ስለሆነም ድሮ በድል ስትወጣ ነበረች እንጂ አሁን በድል መውጣት አልቻለችም። ለዚህ ምክንያት የሆነው፤ጠንካራ እና ብሔራዊ ስሜት ያለው መንግሥትስላለሆነ ነው። ይህ የወያኔ ወራሽ የሆነው ኦሮሙማው መንግሥትጠንካራ ብሔራዊ ስሜትአለው ከተባለ ማየት እሻለሁ።

ወንድሜ አቻም እንዳለውበተቃራኒው ደካማና ብሔራዊ ስሜት በሌለው ማዕከላዊ መንግሥት ላይ ስትወድቅ፤ የታሪካዊ ጠላቶቿ ሲሳይ ስትሆን ኖራለች አዎን ለዚህም ነው አብይ የሚመራው ስርዓት ዘረኛ እና አገራዊ አስተዳደራዊም ይሁን የማጥቃትም ሆነ የመከላከል ጦርነት ለመምራት ብቃት የጎደለው፤ ካንገት በላይ አኖህላሊ ቃላቶችን መደርደር እንጂ በጠንካራ ብሔራዊ ስሜት ያልተቃኘ ስለሆነ፤ ገንጣዮችና ሽብርተኞች የፈለጉት ሕዝብ ሲያርዱ፤ በርካታ ከተሞች ሲያወድሙ፤ከባድ ከባድ ድፍረቶች ሲፈጽሙ፤ በሚያስደነግጥ ሁኔታመናፈሻ ፓርክ እየሄደ ብስክሌት ሲነዳ ፎቶ ሲነሳ ይውላል። ስለዚህም አገራችን የጠላቶቿ ሲሳይ ሆናለች።

የመጀመሪያው ወሳኝ መመዘኛ የሆነውጠንካራ ብሔራዊ/አገራዊ/ ስሜትየለውምና የመመዘኛው ፈተና ወድቋል (እያየነውም ነው) ሁላችንም ባመንበት በተወሰነ ደረጃ ጦርነቱ መደገፍ አስፈላጊ ነበርና፤ መጀመሪያ አካባቢ ደግፈነውም ነበር። እያደረ ግን ከላይ በቁንጮ የተቀመጡ የጦር አመራሮችተንኮል የበዛበት፤ ተጠያቂነት የሌለው፤ ማፈግፈግ ሲደረግለምን እንዳፈገፈገ ግልጽ ያልሆነ፤ ቢገለጽም እውነትን ያልተከተለ አታላይ ምክንያት በማቅረብ በብዙዎቻችንም ሆነ በየከተማውና በየገጠሩ የሚኖሩ ኗሪዎች አመኔታ አጥቷል።  በርካታ ሉኣላዊ ድምበሮች በውጭ ወራሪዎች ተደፍረዋል፤ ተነጥቀዋል። ሉኣላዊነትዋ ለጥቃት አመች ሆናለችና በማንኛውም ረገደድ መወገድ የግድ ነው።

መፈንቅለ መንግሥት መደረግ አለበት የምለው የኔ አስተሳሰብጁንታተብሎ ከሚጠራው ገንጣይ ፋሺሰት ቡድን ደጋፊዎች የኔመፈንቅለ መንግሥትአመኔታ ይለያል። አቻም እንደሚለውየኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አልተከፋፈለምየሚል እምነት ካለን ያልተከፋፈለው ሰራዊት የስርዓቱ አገልጋይ ከሆነአልፈየደም ማለት ነው ምክንያቱም ሰርዓቱ ብሔራዊ ውርደት ያመጣ አገሪቱ የጠላቶች ሲሳይ እየሆነች እያየ ይህአልተከፋፈለምአንድ ነው የተባለው ሰራዊት የአንድነቱ  ፋይዳው ምንድ ነው?”

በነገራችን ላይ መፈንቅለ መንግሥት ሲካሄድ አብይ ብቻ ሳይሆንይህ ውርደት እያከናነበን ላለው መሪለማገልግል እና ለመከላከል በሙሉ ልባችን ከጎኑ ቆመናል  የሚሉትን የነቀዙ ወታደራዊ አዛዦችን እነብርሃኑ ጁላም ሆኑ እነ ባጫ ደበሌን ለሕግ ማቅርብንየሚጨምር መፍንቅለ መንግሥት ቢደረግ ምንም የሚመጣ ነገር የለም። ወያኔን ማሸነፍ ሲያቅተን አንድ አገር ወዳድ ከትግሬም ይሁን ከሌላ በቡድን ወታደር መፈንቅለ መንግሥት ቢያካሂድ እንመኝ ነበር። ሌሎች ግን ስጋት ነበራቸው። ተፈነቀለ ግን የተፈራው አልደረሰም። የተፈራው በከፊል ሊደርስ ቢችልም አብይ እና አሽከሮቹበወቅቱ እርምጃ መወሰድ የሚገባቸው እርምጃዎች ባለመውሰዳቸው፤ ለጦርነት ተዳርገናል። ይህ የሆነውየአባትና የልጅፍቅር አልቆሲሻኮቱጊዜ ወስዶ 'Frankenstein's monster' አይነት ታሪክ (ፈጣሪው በፈጠረው ሲበላ) ያመጣው ሰበብ ነው። 

ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሲደረግሳበው-ወጥርይኖራል? አዎ። ግን ድምበሮች በሱዳን ተይዘዋል፤የጦር አዛዦችሱዳኖቹ  ወንድሞቻችን ናቸው ውግያ ውስጥ አንገባምሲሉ ተደምጠዋል። ከሚገባ በላይ ውድመት እናአፍግፍግእያለ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙርከኞች የወያኔ ሲሳይ እንዲሆኑከፈቀደ ይህ አልተከፋፈለም እየተባለ ያለው ሰራዊት መፈንቅለ መንግሥት እንዲያደርግና ለአመራሩ አልታዘዝም ብሎ  ስዒረ መንግሥት እንዲሞክር ጥሪ ካልተቀበለ ብሔራዊ ስሜቱን የሚገልጸው ለአንድ መሪ ነኝ ብሎ በሁለት ምላስ ለሚናገር መሪ ወይስ ለአገሪቱ ድህንነት?

ለአመራሩ አልታዘዝም ብሎ ስዒረ መንግሥት እንዲሞክርበት ቢደርግ ከዚህ ውርደት ማውጣት የሚችሉ ወታደራዊ ቡድኖች ስርዓቱን ቢቆጣጠሩ የተሻለ እንጂ የከፋ ውርደት አይመጣም። ብሔራዊ ስሜት አላቸው የምንል ከሆነ ፤ከነዚህ ውስጥ የወጡ ወታደሮች መስመር ማስያዝ ለምን አይቻላቸውም?

ስለ መፈንቅለ ምንግሥት ስናገር ስለ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ነው፤ ስለ ሕዝባዊ አመጽ ሳወራ ደግሞ አሜሪካ ውስጥበፕረዚዳንት ትርማፕወቅት የታየውየሃብታሞች መደብ ያቀነባበሩት ፋሺስታዊ/አናርኪሳዊሲቪላያዊ መፈንቅለ መንግሥት ሳይሆንኢትዮጵያዊ ፍቅርበታጠቁ ፍትህ ባጡ ክፍሎች የተቀነባባረሕዝባዊ አልገዛምባይነት አመጽን ነው እያልኩ ያለሁት። ወታደራዊ አመጹን ከጠላነው ሕዝባዊ አመጽም አያስፈልግም እያልን ነው። በጦርነት የምናሳብብ ከሆነ፤ ይህ ጦርነት ማለቂያው መቸ ነው? የሚለው ብንጠይቅ መልስ ካለ እንጠብቃለን። መሪዎቹ ጦርነቱን ይፈለጉታል።የኩሊዎች መንግሥት ሁሌም ጦርነትንለሥልጣናቸው ማቆያስለሚያደርጉትጦርነቱ ሊቆም አይፈልጉም ስለዚህ ችካል ውስጥ ገብተን ተቸከልን ማለት ነው።

የመፈንቅለ መንግሥት አስፈላጊነት ስሜት  ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲ ትተዳደራለች በምትባለዋ ቄሳራዊት አሜሪካ የሚኖሩ ኗሪዎችዋ በጣም ብዙ አሜሪካውያን የአኗኗራቸውን መንገድ ለመጠበቅ 'መፈንቅለ መንግስት' ወይም 'ኃይል' ሊያስፈልግ ይችላል ብለው ያምናሉ። አምና 2020 ሎስ አንጀለስ ታይምስ የተባለ ታዋቂ ጋዜጣ ባሳተመው ዘገባ 2017 የዳሰሳ ጥናት ውስጥ 4 የአሜሪካ መልስ ሰጭዎች አንድ (1) “ብዙ ወንጀል ሲኖርወይምስርኣቱ በቁርቁዝና ሲበሰብስወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥትትክክለኛስልት ነው የሚሉ ዜጎች አሉ፡ በማለት ጥናቱን ያቀረቡት የቫንደርቢልት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑትኤልሳቤት ዘክሜስተርተናግረዋል።

ዜጎች መፈንቅለ መንግሥት እንደ አማራጭ ለመውሰድ የተገደዱበት ምክንያቱም ይላል 2019 የተደረገ ሌላ የምርምር ማዕከልየሕዝብ አስተያየት እንደሚያሳየው 60% የሚሆኑት የአሜሪካ ምላሽ ሰጪዎች ዲሞክራሲያቸው በሚሠራበት መንገድአልረኩም ይላል። ስለሆነም 4 1 አንዱ የተጠቀሰው አማራጭ ያልሆነውን ያልተለመደው አማራጭ መንገድ እንዲከሰት የሚፈልጉ ሰዎች አሜሪካ ውስጥ ተከስተዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አሜሪካ ውስጥ ከተደረገው ጥናት በይበልጥ መፈንቅለ መንግሥት ቢከሰት የሚሰጉ ዜጎች እንዳልሆኑ እገምታለሁ።አገሪቱ በቀውስ እየታመሰች ባለችበት የጦርነት ወቅት መፈንቅለ መንግሥት ወታደሩን ይከፋፍላል የሚሉ ስጋቾች አሉ። ሊኖር ይችል ይሆናል። ስጋቱን ለማመን ግን የተደረገ አርግጣኛ ዳታ ግን የለም። የማከብረው ወዳጄ የምጣኔ ሃብት እና የታሪክ ተመራማሪ ሊቁ ወጣት አቻምየለህ ታምሩ በጽሁፉ ላይ ያልተብራራ ለስጋቱ ምንጭ ይኖሮው ይሆናል። ይህ ለወደፊቱ የሚታይ ይሆናል።

መፈንቅለ መንግሥቱን የሚፈልጉጁንታዎችብቻ እንደሆኑ ያቀረበው መስመር ብስማማም (ጁንታ እንኳን መፈንቅለ መንግሥት አገሪቴ ብትፈፈርስም ደንታ ስለሌላቸው ምንም ቢሉ ቢሉ የሚጠበቅ ነው) የስዒረ መንግሥት ንቅናቄ ፍላጎት ግንጁንታው ቡድን  ብቻ የተወሰ ፍላጎት አይደለም: ጁንታ ካልሆኑት አንዱ እኔው ሁለት አማራጮችን ለማየት እሻለሁ።

የፋሺሰቱ ስርዓት ለማስወገድመፈንቅለ መንግስትና ሕዝባዊ አልገዛም ባይነትከሁለቱ ሌላ አማራጭ የለም።በወያኔ ትግራዋይነትቅኝት እናበኦሆዴድ ኦነግ ኦሮሙማቅኝት ሹማሙንት አጋፋሪነትምርጫተብሎ 30 አመት የተደሰኮረለትምርጫየት እንዳደረስን ስላየነው በፋሺሰቶች አስተባባሪነት የሚደረግ ምርጫቦምብን ለህጻናት ማስታቀፍስለሆነ አማራጭ ሆኖ አልተገኘም።

በምርጫ አሸነፈ የተባለለት 2014 . የነገሰው አዲሱ ንጉሳችንንጉሥ አብይ አሕምድ  አንግሳኛለች ለሚላትኢትዮጵያየሰጣት አበርክቶየአዲስ አባባ ሕዝብ ከሸርሙጦች የተደቀሉ የሸርሙጦች ልጆች ናቸውየሚሉ የቀወሱ ዕብዶች እና ኢትዮጵያ ትፍረስ የሚሉ፤ ለሦስት ሺሕ አመት እንገዛችሗለን የሚሉ አማካሪዎቹ እና አማራን በመጨፍጨፍ 1983 . ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በጭፍጨፋ እየተካፈሉ ያሉ የጨፍጫፊ ድርጅት መሪዎች ፓርላማ ውስጥም ይሁን ከፍተኛ የመንግሥት ሹመት ተሹመውኢትዮጵያ ምን ታመጪ!” ብሏታል።

 በዛ ሳያቆም ወያኔ የከፈተው ጦርነት ተዋጊው ጦር እንዲያፈገፍግ ተደርጎ መጨረሻ ላይ ከትግሬ የተነሳው የሽብር ሃይሉጎንደርን ወሎን እና ዓፋርንደፍሮ በመግባት ከተሞችን እና ገጠሮችን በመቆጣጠር ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ዝርፍያ፤ ውድመት እና ግድያ እንዲፈጸም ያደረገ መንግሥት በምርጫ ስም ምንሊክ ቤተመንግሥት ገብቷል።

ያም ሆነ ይህ ወያኔ 27 አመት ኦሮሙማ 3 አመት፤ በመፈንቅለ መንግሥት መጥተዋል። ስለዚህ በመፍንቅለ መንግሥት የመጡት እነዚህ ሁለቱ ፋሺሰት ቡድኖች፤ እንደ ዕድል ለፈጣሪ አይሳነውም እና (እንደ ሚባለው) አገር ወዳድ የሆኑ ከጦር ሃይሉ ውስጥ በትኣምር ቢገኙና ቢፈነግሉትበምን ዕድላችን ባገኘነውያሰኛል።

 እኔም ሆንኩኝ ወንድሜ አቻምየለህ አሁን ያለው ስርዓት ፋሺሰት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን በኦሮሙማ ቅኝት በመቀየስ ኢትዮጵያ ባመዳከም ወደ ኦሮሞነት ለመቀየር የሚታይ መስመር ዘርግቶጠላትብሎ ያሰመረበትንአማራከኢትዮጵያ ምድር ለማስወገድ የራሱ ወወታደሮች እና ድርጅት በጨፍጨፋው እንዲሳተፉ እንዳደረገ ከጸረ አማራ ድርጅች መሪው አንዱ/ ከማል ገልቱበዩቱብ ቀርቦ መስጢሩን ይፋ አድርል። አቻም ይህንን ያውቃል።

ይህ ብቻ ሳይሆንየጭፍጨፋው መሪሻሸመኔ ውስጥ ትምህርት ቤቶች/ ሆቴሎች፤ሕክምና መስጫ ህንጻዎች ቤተክርስተያናት እና ምዕመናን ፈርሰው ፤እሳት ጋይተው እና ታርደው የአማራና የክርስትያን ንብረት ሲዘረፍየከተማው ከንቲባ ሺመልስን ዕርዳታ እንዲልክለት ሲጠይቀውየሰጠው ምላሽ አርፈህ ተኛብሎኛል ሲሉከንቲባውተናግረዋል። እንዲህ ያለ ግልጽ ጭፍጨፋና ጸረ አነድነት አንዲካሄድ ያደረገው ማን ነው? የኦሮሞንክልልለማስተዳዳር በንጉሡ የተሾመው ሰውጭፍጨፋ እንዲካሄድ ሲፈቅድይባስ ብሎ አገር እመራለሁ የሚለው አብይ አሕመድ ሻሸመኔ እንደነደደች በአገር የየዜና ማሰራጫዎች እና  ለም አቀፋዊ የዜና ማዕከሎች ሲዘግበው እያያና እየሰማ  ኢትዮጵያ ምን ታመጪ!” ብሎ  አንጦጦ ተራራ ሄዶየህጻናት ብስክሌት እየነዳፎቶ ሲነሳና ደስታውን ሲገልጽ ነበር ሺመልስ አዱኛ አንድ ወር ተኩልጀሮ-ዳባቆይታ ወደ ሻሸመኔ ሄዶ ሲለፍልፍ ነበር የሚል ዜና ሰማን።

እንዲህ ያለውን ጸረ ኢትዮጵያ መሪ ያወምበፋሺሰትነትየተመደበ ሥርዓት በሕዝብ አመጽም ይሁን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ቢወገድ ኢትዮጵያ የምትጎዳው ምንድ ነው?  የሚቀራትስ ምንድ ነው? አብይ አሕመድ ድሮ የኦነግ ከዚያም የወያኔ ኩሊ የነበረ ዛሬ ደግሞ የኦነግ መሪዎች ኩሊ ነው። ኩሊ ራሱን ያልቻለ ተላላኪ ማለት ነው።

ፋሺሰት ሙሶሎኒ የኩሊዎች ስብስብ ነበር። ኦሮሙማ ያቀፈው ተሿሚም ብዙዎቹ በግድያ በጭፍጨፋ፤ በሌብነት፤ በዘረኝነት፤በአጭበርባ ባሕሪ የተዘፈቁ ኩሊዎች ናቸው። ስለዚህ ይህ የኩሊ ስብስብ በመፈንቅለ መንግሥት ቢወገድ ሕዝቡ ምንም አይጎዳም። ይልቁኑ መፈንቅለ መንግሥቱ አራማጆች ከተለያዩ ነገዶች የተወጣጡ ሆነውጦሩለአገሪቱ ተገዥ እንዲሆን ማስተባበር የሚችሉአገር ወዳድ ወታደራዊ ቡድኖችመፈንቅለ መንግሥት ቢያካሂዱ ተመራጭ ነው።

 የሚያስፈልገው፤ ማለትም መሪን ማስወገድ የሚችሉት መፈንቅለ መንግሥት የሚመራው (ወይወንም የሚያካሂደው ቡድን) የጋርዮሽ ፍላጎትና ትብብር ሲኖር ነው ይላሉ በዚህ ጥናት ያደረጉ ሊቃውንት።-

ማንኛውንም መፈንቅለ መንግሥት ስኬታማ ለማድረግ ይቻላል፤ ይላልየመፈንቅለ መንግሥት ተማራማሪ የሆነው የአሜሪካ ባህር ኃይል ጦር ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር “The Strategic Logic of Military Coups” የሚል መጽሐፍ ደራሲ ሕንዳዊውናውኒሃል ሲንግ” Naunihal Singh ይህንን ስልትየማስተባበር ጨዋታው” (coordination game) ማወቅ ብቻ ነው፡ ይላል።

አብይ አሕመድ የመፈንቅለ መንግሥት ውልድ መሆኑን እናውቃለን። ወያኔ 17 አመት የፈጀበት በብረት መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ ነገሠ። ከወላጁ ወያኔ ወደ ልጁ አብይ የተሸጋገረ ውርስ ነው። እርግጥ ነው ለመፈንገል ሲሞከር ሰበብ አይታጣውም።  መሪዎች ሥልጣናቸው ሲነካመፈንቅለ መንግሥትበማካሄድ እነሱን መልሶ የሚያስቀምጥ አመጸኛ ቡድን ያዘጋጃሉ። አብይ እራሱ በዚህ ተዘጋጅቶ እንደነበር እናውቃለን (ዛሬም ተዘጋጅቶ ይሆናል)

ታስታውሱ እንደሆነ ጥቂት ኮማንዶዎች ቤተመንግሥት ድረስ መጥተውመፈንቅለ መንግሥትላማካሄድ ሞክረውብኝ ነበር ባለው አንደበቱከሥልጣኔ ብወገድ መፈንቅለ መንግሥቱን ያካሄዱትን ወታደሮች የሚገዳደርከቡራዩ ,,.. ወዘተ..” በፈረስ እየጋለበ መጥቶ የሚፋለም ወጣት (ኦሮሞ ማለቱ ነው) አለኝ ሲል መፍንቅለ ምንግሥቱን በሌላ መፈንቅለ መንግሥት ላመስቆም ዝግጁ እንደነበር እራሱ ነግሮናል። አሜሪካው ትራምፕም እንዲሁ ነበር ያደረገው።

ይህንን አስመልክቶ አንድ ጋዜጠኛ ለፕሮፌሰርናውኒሃል ሲንግእንዲህ ጠይቆት ነበር፡

 በዋሽንግተን ውስጥ የሆነው ነገር አሳሳቢ ነው፡ ግን መፈንቅለ መንግሥት አይደለም። ያንን ልዩነት ማስረዳት ይችላሉ?

  ረዳት ፕሮፌሰር  ናውኒሃል ሲንግመልስ፣-

ችግሩ ፕሬዚዳንቱ የሞራል ስልጣን ስለሰጣቸው ነው እዚህ እያየን ያለነው አመፅ በመንግሥት ላይ ኃይለኛ አመፅ ተብሎ በተሻለ ይገለጻል። አመፅ ነው ግን መፈንቅለ መንግስት አይደለም።ይላል።

አብይ አሕመድም በተመሳሳይየዘር ጨፍጫፊ ነብሰ ገዳጥ ሽብርተኞችከተማ ሲያቃጥሉ አማራውን በገፍ በተከታታይ ሲጨፈጭፉጉራጌና የጋሞ እናቶች ክርስትያን አባቶችን ሲያርዱ.. “አልሰማሁም አላያሁም.. ስለችግር አታውሩ ስለ ስንዴ መዝራት አውሩእያለ ሽብርተኞችን ስለሚያበረታታ አገሪቱ ወደ ከፋ ጭለማ ገፍትሯታል። 30 አመት የደደቡ ወጣት ምሁራንም ንጉሡን አጅበው ካቢኔው ላይ ተቀላቅለውለታል። እንዲሁየሆነ ሆኗል እንቀጥልይላሉ። ይህንን አስመልክቶ ከላይ የተጠቀሰው ህንዳዊ አሜሪካ ፖለቲከኞች እንዲህ የሚሉትን ይኮንናቸዋልፖለቲከኞች 300 ዓመታት በፊት ስለ ተከሰተው ችግር የሚያወሩ እንጂ አሁን እየሆነው ስላለው ችግር ግድ ሳይላቸውእርሱን ተውት ይልቁንም ወደፊት መጓዝ አለብንእያሉ ሲናገሩ ታደምጣለህ። ሁሉ የሚያስጨንቅ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ይላል።

ስለሆነም አብይ አሕመድ ስለተደረገው አታለቃቅሱ እያለ ሲያሾፍ፤ መፈንቅለ መንግሥት ቢደረግበት ወይንም ሕዝባዊ አመጽ ተደርጎአትገዛንም ከሥልጣን ውረድካልተባለ በምን ስልት ሊወገድ ይችላል?

አፍሪካ ውስጥ ዛሬምጊኒ እና ማሊ…” የሚደረጉ ወታደራዊ ኩዴታዎች ሕዝቡ ሲደግፍ እንጂ ሲቃወም አላየንም።፡ምክንያቱም ሕዝቡ መርሮታል፤ አማራጭ የለውም!! ምሁሩ ተፈትኖ ወድቋል። በቃ!!!

አስረዱኝ? እኔ እየተከራከርኩ ያለሁት መስመርእምባ በሚያነቡ፤ ተከብበናል ድረሱልን ብለው ደራሽ አጥተው ስለ ታረዱ የመንግሥት ያለህ ብለው ጮኾው አማራጭ ስላጡ ዜጎች ምርጫ ነው እያወራሁ ያለሁት። ጥይት ተርከፍክፎባቸው ቢላዋ አንገታቸው ያረፈባቸው የሞቱንም መናገር ባይችሉም እስኪ ጫካ ውስጥ ተከብበው ድረሱል እያሉ ያሉ በህይወት ያሉትን ሴቶች እና ወጣት ወንዶች፤ እናቶች እና ህጻናት ጠይቁዋቸው ምን አንደሚሉ! አብይ በመፈንቅለ መንግሥት ከሚወገድ እኛ እንታረድ ብለው አይሉም። የኔን ሃሳብ አይጠሉትም።የመንግሥት ያለህ!! አብይ የት አለህ?!!! ብለው ለሚጮኹት ጠይቃችሁ እኔ ስለማቀርበው መፍትሄ ምን አንደሚሉዋችሁ ጠይቋቸውና መልሱን ፈልጋችሁ ንገሩኝ!!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

 (ኢትዮ ሰማይ)

 

No comments:

Post a Comment