Saturday, February 25, 2012

Getachew Reda P.O. Box 2219 San Jose, CA 95109
408-561-4836 getachre@aol.com  Few copies remain.

የቅዳሜ ዜና
ወደ ትችቱ ከመግባታችን በፊት መጀመርያ ዜና፡


አባ ኒቆዲሞስ ምስክርንት (ኦነግ በበደኖ የዘር ማጥፋት እልቂት መሳተፉን መሰከሩ!)
  ወያኔ በኦሮሞ አካባቢ በአማራው ዘር ማጥፋት ወንጀል መካፈሉን ከማንም የተሰወረ እንዳልሆነ የታወቀ ነው። የኢሳት ሰዎች እና በኢሳት ዙርያ ድጋፍ የሚሰጡ አካሎች ግን በአማራ ደም የተጨማለቀው “ኦነግ”ን ካሁን  በፊት ኦነግን ላለመንካት ያልሞከሩት ፕሮፓጋንዳ አልነበረም።
ቆሻሻ ፕሮፓጋንዳቸውን ለማሳመር ሲሉ የኦነጐቹን የድሮ መሪው(ወንጀሉ ሲፈጸም መሪ የነበረው (ዲማ ነገዎ) ኦነግ በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳልተካፈለ የተናገረው የውሸት መልሱን ይዘው፤እንደ እውነተኛ መረጃ “ደጋግመው” እርስ በርሳቸው የክብ ጠረፔዛ ውይይታቸው ሲያካሂዱ ያንንኑን የተግማማ መረጃ በማቅረብ ያልቦዘኑበትት ወቅት አልነበረም ።  
የተጨማለቀው ኦነግን ነፃ ለማውጣት ምን በሽታ እንደያዛቸው አላውቅም፡ ፋሲል የኔሰው የተባለው የኢሳቱ ጋዜጠኛ “አባ ቄሱን” ደጋግሞ በመጫን ሲጠይቃቸው የነበረው እና ጊዜው የፈጀው በኦነግ መሪዎች እና ወንጀል ሳይሆን “አብዛኛው” ያተረው በወያኔ ወንጀል ተሳታፊነት ነበር። ለምን?
ወያኔ የተሳተፈበት ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠያቂ መሆኑን ማንም የሚያውቀው ነው። ፋሲል/ኢሳቶች የሚያተኩሩት የዘወትር ጨዋታቸው ግን  በወያኔ ብቻ ነው። ለምን? አክራሪ እስላም አማራውን ሲገድል “አሁንም ትኩረታቸው “በወያኔ” ብቻ ነው። ሻ ዕቢያ እና ኦነግ ቦምብ ሲያፈነዱ “ዊኪ ሊኪ” “አሜሪካ’” እገሌ; እገሌ ወያኔ ነው ብለው በቃዡ ቁጥር  ወንጀለኞችን ነጻ እያወጡ ትኩረታቸው በወያኔ ብቻ ማትኮር ነው። ወያኔ በተዘዋዋሪ የወንጀሉ አስፈጻሚ ቢሆንም “በዛው የወንጀል ድርጊት በቀጥታ ድርጊቱን  የፈጸሙ “ኦነጐች፤አክራሪ እስላሞች” ጋር የተያያዘ ወንጀል ለምንድነው ዘጋቢዎች (ጠቅላላ አብዛኛዎቹ የተቃዋሚ ሚዲያዎች) ቸል የሚሉት? እስከመቸ ነው ቀጥተኛ ተሳታፊ ወንጀለኞችን  ሕዝቡ እንዳያውቃቸው በወያኔ ብቻ እያተኰሩ ወንጀለኞችን “ሽፋን የሚሰጣቸው?”
 ዱዳው ተቃዋሚ መዘገብ ከፈራ እኛ ይህ አንገብጋቢ  ጥያቄ በቸልታ አናየውም። የፋሲል አትኩሮት ለማድመጥ ከታች የተለጠፈው መስኮት በመጫን ያድምጡ።  ከዚያ እራስዎ ይፍረዱ።
“ይህ ወንጀል ሲፈጸም የኦነግ መሪዎች እንማን ነበሩ ሳይሆን  ሲጠይቅ የነበረው ወንጀሉ ሲፈጸም “የኦሕዴድ” መሪዎች እነማን ነበሩ? በማለት ነበር ደግሞ ደጋግም “አባ ቄሱን” ሲጫናቸው እና ግራ ሲያጋባቸው የነበረው። ቄሱ ስለ ኦነግ በስፋት ሊናገሩ ሲሉ አሁንም ወደ ኦሕዴድ እና ወያኔ ይጠመዝዛቸው ነበር።፡ያ ብቻ ሳይሆን “ኦነግ የአማራን/ነፍጠኛን ከኦሮሞ ማስወጣት በፕሮግራሙ ዘግቦታል (መረጃው አለኝ) መመሪያው እንደሆነ እየታወቀ፡ ጋዜጠኛው ፋሲል ግን “ኦነግ የግድያ ወንጀል ሲፈጽም አማራ ይውጣ ብሎ ነው ወይስ ከወያኔ ጋር ያበሩ ብቻ ነው?” ብሎ ቄሱን ያምታታቸዋል? የግድያው መነሻ ለምን ብሎ ቄሱን ይጠይቅ እና መልሱ እራሱ እንዲህ ይላል’- “ምክንያቱም ለወደፊቱ ኦነግ ተሳክቶለት ስልጣን ቢይዝ አማራውን የሚያባርር እና የማያባርር መሆኑን ለማወቅ ነው።” ብሎ እራሱን አጃጅሎ ቄሱንም አድማጩንም በማጃጃል የወደፊት የኦነግ ፖሊሲ ጋራንቲ/ማረጋጋጫ ሊሰጠን ሞክሯል።ይገርማል? ለምንድነው የወያኔ “ኦሕዴድ”መሪዎች ስም እየጠቀሰ አስሬ ቄሱን ሲጫናቸው ኦነግን የመሩ ለምሳሌ እነ (ዲማ ነገዎ፤ ዳውድ ኢብሳ፤ ሌንጮ ለታ፤ሌንጮ ባቲ፤ ኑሩ ደደፎ …….ወዘተ ወዘተ…..) አንድ ጌዘ እንኳ በወንጀሉ ዙርያ ሰፋ ያለ አትኩሮት ለማድረግ ያልሞከረው?  


የህፃናትን አንገት እየቀላ ህፃናትን የጨፈጨፈ ፋሺስቱ ኦነግ እንዲሁ በቀላሉ ወንጀሉን አሳንሶ “መንግሥት ስለደገፉ” “ዕልል ስላሉ” ነው የቀላቸው ብሎ ማመን የፖለቲካ ሞኝ መሆን ነው። ኦነግ የህፃናት አንገት ሲቀላ ህፃናቱ ወያኔ ስለደጉፉ ሳይሆን ፋሺስቱ ኦነግ “አማራን” ስለሚጠላ ነው

ኦነግ አማራ ይውጣ ብሎ ገድሎ አያውቅም? ጽፎ አያውቅም? ፋሲል ይህንን አያወቅም ማለት አልችልም። እንዲሁ ብቻ “አለመታደል” ጋዜጠኞቹ እና “ዱውይ ተቃዋሚው” ከኦነግ ጋር መተሻሸትን ይዘዋል። መልካም ስካር እንመኝላቸዋለን!!!! 
 Yesamentu Engeda AbaNikodimos http://youtu.be/7To9rdOpFxQ
ሌላው ሁለተኛው ዜና

 በትምህርት ቤት እያለ ኢትዮጵያ ነኝ ወይንም ኢትዮጵያ እንወዳታለን የምትሉ እጃችሁን አውጡ ተብሎ ሲጠየቅ ‘ኢትዮጵያ ምንም አልሰራችልኝም” ብሎ እጁን ሳያወጣ የቀረው እውቀቷን ለግሳ ያሳደገቺውን አገር ከድቶ ወያኔንን በፕሬስ መምሪያ እና በፕሮፓጋንዳው መስክ በማገልገል ብዙ ወንጀል የፈጸመ የድሮው የወያኔ ቅጥረኛ እና የዛሬው የሻዕቢያ ምንደኛው ተስፋዬ ገብረአብ የተባለው ጸረ አማራ ግለሰብ፤ ቅዳሜ ፌብሪዋሪ 2012 በጸረ ትግሬ ጠሊታነቷ የምናውቃት ሙያዬ ምስክር (ትክክለኛ ስሟ ብዙ ወንድማገኝ) የተባለቺው  “ECADEF FORUM/ Ethiopian Current Affairs  የመድረኩ መሪ በመራቺው ዝግጅት፡ ባንዳው ተስፋዬ ገብረአብ “የወያኔው ጀኔራል ሐየሎም አርአያን  ከአርበኛው በላይ ዘለቀ” ጋር በማወዳደር “በሐየሎም አርአያ ጀግነነት የማትቀበሉ ኢትዬጵያውያን ኢትዮጵያ ትበታተናለች”ወይንም ኢትዮጵያውያን አይደላችሁም። ሲል እቅጩን ነግሮናል:: ሲሉ ቡልቻ ደመቅሳም ኢትዮጵያዊነታቸው ስላጠበቁ ኦሮሞ አይደሉም ብሏቸዋል; የሚል ወሬም አለ። ለማንኛውም አውድዮው ቢለጠፍ ጥሩ ነበር። ብዙ ኢትዮጵያውያን እንደተናደዱ ዜናው ደርሶናል። እክፍሉ ላይ ተገኝተን ለማዳመጥ ሞክረን ክፍሉ ሞለቷል የሚል ምልክት ስለሰጠን አውድዮው ማግኘት አልቻልንም;:የብርሃኑ ነጋ ጓደኛ ተስፋዬ ገብረአብ ቀጥሎስ ምን ሊላችሁ ይሆን?
"ማራኪዋ" በመባል በውሸት ስም  የምትጠራ ኢውሮጳ የምትኖር የዛኛው የካረንት አፈይርስ ዘረኛ “ፓል ቶክ” ዋናዋ የወጣቶቹ ቅመም ሆና ፤ ካሁን በፊት ‘ትግሬ ትግሬ’ ማለቷን አቁማ “ተስፋዬ ገብአብ” የውሸት መጽሐፉን ይዞላት ብቅ ሲል “ግጥም ገጥማለት” ነበር፡ አሁን ደግሞ ምን የሚሉት ግጥም እንደምትገጥምለት እስቲ እንጠብቅ።ወይ ዘመን! ወይ አገሬ!


ወያኔ ጋር እንዳንታገል፤ ወያኔን ሲያገልግሉ ኖሮው፤ አሁን ደግሞ የወያኔ በሽታቸው አልለቅ ያላቸው ባንዳዎች ወደ ተቃዋሚ እያስመጡ አቅፈዋቸው “ግጥም እየገጠሙላቸው” አገራችን ፤ህዝባችን እያስሰደቡ ተቸግረናል። የፈራሁትም ያው ነበር፤ ትግላችን ከወያኔ ብቻ ሳይሆን፤ ባንዳዎችን በግጥም አስክረው ራሳቸው የሰከሩ ተቃዋሚዎች ጋር እንደሚሆን ተምብዬ ነበር። ይሄው፤ ታሪካችሁ አርበኞቻችሁን የሚሰድቡ ባንዳዎች የምስጋና ግጥም እየተገጠመላቸው ነው። ዋት ኢዝ ኔክስት! ይላል ፈረንጅ። መሰንበት ደጉ!

ይድረስ ስሞታዬ ለመኮንን ዘለለው።
ከጌታቸው-ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com
እለቱ እና ወሩ መቸ እንደሆነ ባላውቅም  “ቃሌ” በሚባል ፓል ቶክ ገብተህ የኔን ስም አንስተህ ሰትመጻደቅ እንደነበር አውቄአለሁ።
የተጠቀሰው ክፍል እነማን እንደሚያካሂዱት እና አቋማቸው ምን እንደሆነ ባለውቅም በተጠቀሰው ፓል ቶክ ክፍል ውስጥ የርዕሱ መነሻ ወይንም የኔ ስም እንዴት ወደ ውይይቱ አንደመጣ በውል ባላወቅም፡  የኔ ስም ተነስቶ፤ መኮንን ዘለለው ሁለት ነጥብ አንስተህ እኔን እንደኮነንከኝ መረጃው ደርሶኛል።
በኔ ላይ ለቅሬታህ መነሻ የሆነህ  ከጥቂት አመታት በፊት አንደኛው  አንተ  ያዘጋጀኸው ጥቂት የወያኔ  የጫካ አለቆችህ ማለትም እነ ስየ፤ገብሩ፤አረጋዊ፤ግደይ እና ወዘተ…. እና ጥቂት ትግሬዎች በቴሌ ኮንፈረንስ ጠርተህ ሌሎች የነ ስየን ወደ ትግሉ መቀላቀል በየግል ምክንያቶቻቸው የተቃወሙ ትግሬዎችን በማግለል በምስጢር የጠራኸው ውይይት በተነሳ ጉዳይ ነው።
ሁለተኛ ጌታቸው ረዳ አብዛኛው የትግሬ ምሁር/ባጠቃላይ ትግሬዎች ወደ ትግሉ አልተቀላቀሉም፡ የምንታገለው ጥቂት ትግሬዎች ብቻ ነን; ብሎ ትግሬዎችን በማይሆን ይወነጅላል። ትግሬዎች እንደ ማንኛውም፣ሕብረተሰብ ታግሏል እየታገለ ነው። ስትል ነጥቦችን በማንሳት ተመጻድቀሃል/ስሞታ አሰምተሃል።
እዚህ ለይ አንዳንድ  ነጥብ አሉኝ። እነሱን አንድ ባንድ እዘረዝራለሁ።
በአንደኛው ነጥብ ላይ ልጀምር። ኮንሰፒራሲ አልነበረም፤ ስትል ምን ማለትህ ነው? ኮንስፒራሲ/በትግርኛው/ዓረብኛው ሽጣራ/ተንኮል ማለት ነው። ሁለት ወይንም ከዛው በላይ የሆኑ ሰዎች፤ በምስጢር መጥፎ እቅድ ማቀድ ማለት ነው። ያንተ ዓላማ በእነ ስየ ላይ ቅሬታ ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ስሞታ ለማፈን ያደረግከው ሙከራ “መጥፎ እቅድ ነው”። ስለሆነም በዛው ስሜት የተሰማቸው ሰዎች እኔን በስልክ ደውለው ኮዱን ሰጥተው ወደ ኮንፈረንሱ እንድገባ እና አንተ ያቀድከው መጥፎ ተንኮል እንዳዳምጥ እና ዘገባ እንድዘግብ ደውለው ነገሩኝ።
ከመግባቴ በፊት ሰዎቹን አነጋግሬ መኮንን ዘለለው ለምን እናንተን ለይቶ ስብሰባ ጠራ? ስላቸው፤ “መኮንን የስየ ጠበቃ ሆኖ፤ ስየ በትግራይ ሕዝብ እና ወላጆቻችን ፤ዘመዶቻችን እንዲሁም ባገሪቱ ላይ ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ ስለሆነ አምኖ ከልቡ ይቅርታ ጠይቆ  ምን እንደተሰራ እንዲነግርን፡ ካልሆነ ደግሞ ኣንጋፈጠዋለን፤ ይቅርታ መጠየቅ አለበት፤ ያ ከማድረጉ በፊት መኮንን ዘለለው ግን ሁኔታው እያወቀ ስየን ጎትቶ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ማስገባቱ “በኛ እና በቤተሰቦቻችን ንቀት እና ደባ መፈጸም ነው” (ኮንሰፒራሲ) ነው። አሉኝ።
እኔም ቅሬታቸው ትክክለኛ እንደሆነ አምኜበት ፤ ስብሰባውን አዳመጥኩ።
እነ ስየም ሆኑ እነ ገብሩ እንዴት መታገል እንዳለባቸው ወይንም በምን ሁኔታ ትግሉ መግፋት እንዳለበት መረዳት እንደሚችሉ መጠነኛ ንግግር ካደረጉ በሗላ  በእነስየ ላይ ቅሬታ የነበራቸው ግለሰዎች ካሁን በፊት ስለፈጸሙት ወንጀል “ጥያቄ እንዲያቀርቡላቸው”  ሲጠይቁ መኮንን ዘለለው መጀመሪያ ንግግራቸው ይፈጽሙ ከዚያ ጥያቄ ታቀርባላችሁ በማለት ስላፈናቸው፤ ተቃዋሚዎቹ ደግሞ “በጣም በመቆጣት” መከንን ዘለለው “አንተ የምታደርገው ስራ ትክክል አይደለም፤ ተቃዋሚ ነን፤ ተቃዋሚ ከሆንን መጀመሪያ የኛን ቅሬታ አድምጠው መልስ ሰጥተው ነው ወደ ንግግራቸው እንዲሄዱ ማድረግ ያለብህ”፤ ብለው ተቆጡ (ወያኔዎች እዚህ አገር ሲመጡ መጀመሪያ የኛን ንግግር አድምጡ በየምትሉትን እንሰማለን፤ በማለት ለተቃዋሚ ሰልፈኞች አዳራሽ ሲገቡ የሚሰጡት መልስ አይነት ፈሊጥ ነው)።
 ጭቅጭ ተነሳ፤ በሁለት ጎራ ተከፍሎ መሰዳደብ ተከተለ። መኮንን መድረኩን መቆጣጠር ስላልቻለ፤ እንዲዘጋ አደረገው። በሌላ ወቅት ስብሰባው እንደተካሄደ ሰማን።  
እንግዲህ ሁኔታው ይሄ ነው። መኮንን በወቅቱ ያልተረዳው፤ ሆን ብሎ የናቀው ነገር አለ። አንደኛው ወገን ‘በእነ ስየ፤ዓውዓሎም፤አረጋሽ..” ቅሬታ አለው። እነሱን ክብር መስጠት ማለት በእኛ ላይ/ሕብረተሰብ ላይ ንቀት እና ደባ መፈጸም ነው፤ ሲሉት፤ መኮንን ዘለለው ችል በማለት “በምስጢር ስብሰባ ጠርቶ ወደ ሕብረተሰኑ እንዲቀላቀሉ ለመርዳት የደባው ቀንደኛ ተባባሪ ሆነ። ኮንስፒራሲ/ደባ ማለት ይሄ ነው።
አንደሚታወሰው በወቅቱ በመኮንን ዘለለው ዓይን ሳይሆን በብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን እና ልብ ያላቸው ምሁራን ትግሬዎች ዓይን ስየ ማለት በበረሃ ስልጣኑም ሆነ በመንግሥት ሥልጣን እያለ በሰብአዊ እና በብሔራዊ ወንጀል ስራ እጁ የጨመረና (እሱም አይክደውም) ብዙ ምስጢር  የሚያውቅ ሆኖ የሚታይ ከፍተኛ ባለስልጣን ነው። ያኔ ስየ ወደ ጎራው መቀላቀል ማለት በጣም ትኩስ እና በተለይ ጉዳተኞች (በወያኔ የተጎዱ ሰዎች) ጥርጣሬ ውስጥ የገቡበት ወቅት ነው። ወንጀል የፈጸመ ፤ያሰረን፤የደበደበን ሁሉ ይቅርታ ሳይጠይቁ፤ምስጢራቸው ሳያጋልጡ ወደ ተቃዋሚ ጎራ በቀላሉ እየተቀላቀሉ ተቸግረናል፤ ተንቀናል፤የሚሉ ብዙ ናቸው። (እስካሁን ድረስ ይሄ ንቀት ቀጥሏል። ከሐሰን ዓሊ ጀምሮ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጓዶቹ እስከ እነ ገበሩ ስየ አውዓሎም…ወዘተ…..ወዘተ….ቤቱ ይቁጠረው)።  ስለዚህ ለመኮንን ዘለለው “ምንም አልተሰማውም”፤ ለተቀሩት ወገኖች ግን በዛው ተቃራኒ ነው።
ስለሆነም እነ ስየ እነ አውዓሎም እነ አረጋሽ ሳይታከሙ ከነ ግማታቸው ወደ ትግሉ ገብተው ትግሉን እንዲመሩ ማድረግ ለመኮንን እንደ “ኮንስፒራሲ” ደባ አይቆጠርም፤ በወቅቱ ቅሬታቸው ለገለጡ ግን በጉዳተኞች ላይ ንቀት እና ደባ መፈጸም ነው።
ደግሞ የመኮንን ዘለለው ደባ ተሳክቶለት ይኼው እነ ስየ እነ ገብሩ “ዓረና ትግራይ” የተባለው በብሄር በሔረሰብ “እስከ መገንጠል” ብሎ የመጣው በክልል እና በቋንቋ መከለልን የሚያምን ሌላው የወያኔ “ኮፒ ካርቦን” በመመስረት እና ከዚያም አልፈው መድረክ የተባለው የጎጠኞች ሰብሰብ/ሸልፍ ተመስርቶ ተሳካላቸው።
ተድላ አስፋው በዚህ ላይ የሚለውን ላስታውስ እና ወደ ሁለተኛው ነጥቤ ልለፍ።
 - The TPLF “kilil” is an arbitrary drawn line that has no legitimacy in the Ethiopians eye and we are not going to be scared by what will happen after the demise of TPLF and its servants. The real force behind Medrek, However, is Gebru Asrat, Arena party leader …. So called “prominent” individuals like Dr. Negasso Gidada and Seye Abraha are known Kilil politics defenders who failed from Meles’ favor on personal agendas. They wanted to replace TPLF by Arena, EPRDF by Medrek. Professor Mesfin Woldemariam on VOA Amharic yesterday denounced few UDJP members and leaders like-Giizachgew Sheferaw who is the vice president of Medrek for abandoning their party principle of Unity, Democracy and Justice to the Kilil lords of Gebru, Seye, Merara, Beyene, Bulcha etc.
There is no difference between the current tribal warlords and the one who are conspiring to replace it by using poor-Ethiopians “.(Medrek, the last hope of Kilil Politics in EthiopiaOctober 14th, 2009)
ይኸ የነ መኮንን ዘለለው ጥረት ነው። “ውሃ ቅዳ፤ ውሃ መልስ ፖለቲካ” በወቅቱ በእኔው በጌታቸው ረዳ የተጻፈው ተጨማሪ ንባብ ይፈልጉ። 
ሁለተኛው ነጥብ
 እኔ ስለ መኮንን ዘለለው እስካሁን ድረስ መጥፎነት አንስቼ ጽፌ አላውቅም። መኮንን ዘለለው የማየው እንደ የትግል አጋሬ እንጂ እንደጣላት አይደለም። ከድሮ ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ እሱ ግምባር ቀደም በመገኘት ይሰለፍ እንደነበር እና ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርግ የወያኔ ወተት እና የሕዝብ ደም የጠጡ በወያኔ ዱርየ ቦዲ ጋርዶች ጭንቅላቱ ላይ መፈንከቱን በወቅቱ ተቃዉሞየን ይፋ አድሬ ደግፌዋለሁ። የኔ ድረገጽንም እንደማያውቀው፤ እሱ እኔ የምጽፈው አንብቦ እንደማያውቅ እና በዓይን እንደማንተዋወቅና እንደማያውቀኝ-አነጋግሮኝም እንደማያውቅ ዋሽቷል።
እሱ በዓይን ባያየኝም፤ እኔ ግን በዓይን አወቀዋለሁ። ገና ጫካ ከመግባቱ በፊት እኔ ወጣት ሆኜ ኩሓ/መቀሌ እያለ ነው የማውቀው። በተጨማሪም እዚህ አሜሪካ ከሁለት /ሦስት ዓመት በፊት ትግሬዎች ሕብረት ፈጥረን ወደ ትግሉ ተቀላቅለን ተቀናጅተን ለመታገል እንዴት ማድረግ እንደሚበጅ በዓለም ዙርያ የሚገኙ ትግሬዎችን  እየደወልኩ ሳነጋግር እሱንም አነጋግሬዋለሁ። መኰንን ዘለለው ግን እንኳን በዓይን ላውቀው በስልክም አነጋግሬው አላውቅም ብሎ እዛው ቃሌ ከሚባለው ፓል ቶክ ውስጥ ተናግሯል።ለምን እንዲህ ይላል? ሌሎች ትግሬዎችን ሳነጋግር መኮንንም ጭምር ስልክ ደውየ እንድንረዳዳ ብየ ሳነጋግረው ምን እንዳለኝ ትዝ ይለዋል የሚል እምነት አለኝ።
ሌላው ቀርቶ አንድ ጓደኛው ይድረስ ለጎጠኛው መምህር መጽሐፌ እንድልክለት ገንዘብ ልኮ፤ የትግርኛው “ሓይካማ” ምጽሔም በግሌ በነፃ ጨምሬ ልኬለት እሱ ግን “ቂመኛ ሰው” ስለሆነ “አመሰግናለሁ” ብሎ እንኳን መልስ አልሰጠኝም።
ስለ ቴሌኮንፈረንሱ  በኢንተርኔት ዘገባውን ስጽፍ  ያልተስማማው ነገር ጽፌ ከነበር ለምን በወቅቱ ደውሎ አይነግረኝም? ወይንም በጽሑፍ አይመልስም? እኔ “ከ እስከ” ለዚህ ሰው ደግ እና ደጋፊው ሰው እንጂ መጥፎ ሰው አልነበርኩም።
 መኮንን የወያኔ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር (ክፍሊ ሕዝቢ) ሆኖ ሲሰራ በሕዝብ ላይ ብዙ ግፍ አድርሷል ብለው ብዙ መጥፎ ነገር ያደረገው ዝርዝር ስሞች እና ምን እንደፈጸመባቸው የላኩልኝ ሰዎች መረጃው በእጄ አለ። ነግር ግን ስለ መኮንን ይህ ተብሏል ብየ እስካሁን አልጻፍኩም። ወሬም ሃቅም ሊሆንም ላይሆንም ስለሚችል፤ ቸል ብየዋለሁ። የሱን ስም ማጥፋት ፍላጎት የለኝም፤ ቢኖረኝ ኖሮ ፊት ለፊት አነጋግረን ያሉኝ ሰዎች በቃለ መጠይቅ ሰዎቹ እና እሱን አነጋግራቸው ነበር።ይህም ውሸት ነው የሚል ከሆነ ሰዎቹ እና እሱን በሚዲያ አቅርቤ እንዲነጋገሩ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ። እኔ ግን ሰውየው በወያኔዎች የደረሰበት በደል ስለማውቅ የትግል አጋሬ እንጂ በመጥፎ ሰው አልተመለከትኩትም። እሱ ግን ፓልቶክ ሩም ገብቶ ስለ እኔ ማውራቱ ገርሞኛል።
መኰንን በወያኔዎች በጣም ከፍተኛ ግፍ የተፈጸመበት መሆኑን አብረውት ሲታገሉ ከነበሩ ሰዎች ነግረውኛል።  በዛው አኳያ ደግሞ ለመታገል ቆርጦ በመነሳት በግብር አሳይቷል። በዛው ልክ ደግሞ በውጭ አገር የዓረና ዋናው ተንከባካቢ እንደሆነ ደግሞ አውቃለሁ። በዛው ልክ ደግሞ ሃይሉ ሻውልን “በትምክህት ሓይል” የሚኮንን መሆኑንም አውቃለሁ (ልክ የዓረናው ብርሃኑ ሃይሉ መኮንን ዘለለው በኢንተርኔት ራዲዩ ‘ፍትሒ“ ትግርኛ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግለት ሁሌም ሃይሉ ሻውልን “በጸረ ትግሬነት/ የትምክህት ሃይል እያለ እንደሚዘላብደው ማለት ነው)። ግን ይህ ሁሉ ሲሆን መኮንን ዘለለውን አንድ ቀን በመጥፎ አንስቼው ሳላውቅ በኔ ላይ ሲመጻደቅ መስማቴ ይገርማል።ለምን? ስለ እኔ በሰዎች ምን እንደተናገርክ ይደርሰኛል፤ እኔ ግን ጊዜ ስለሌለኝ ቸል ብየው ነበር፤ አሁን ግን የግድ መነካካት የማይገባህን ሰው ምነካት ስለጀመርክ እንድታውቀው ማድረግ አለብኝ።
ሦስተኛው ነጥብ
አቶ መኮንን በእድሜ ታላቅ ወንድማችን መሆንክን አከብራሃለሁ። ግን መዋሸትና መካድ ምን ያደርጋል? ስለ ትግሬዎች ወደ ጎራው አለመደባለቅ ሁሌም በማቀርበው ቅሬታ ላይ አንሰተህ ስላለከው ጉዳይ በሚመለከት አንድ ልበል።
አዎ ትግሬዎች በጣም ጥቂት ካልሆኑ በቀር፤ ወደ ትግሉ አልተቀላቀሉም። ይኼ ደግሞ ፓልቶክ ሩም ሆነህ መቀላቀላቸው ብትመጻደቅና ተቀላቅለው እየታገሉ፤ ጌታቸው ረዳ አልታገሉም፤ ይላል፤ ብለህ ብታወግዘኝም። ከኔ ይልቅ አንተ በራዲዩ ቃለ መጠይቅ ተጠይቀህ ምን እንዳልክ ባጭሩ ልግለጽልህ እና አውነተኛው እና ሃሰተኛው ማን እንደ ሆነ ለአንባቢ እንዲመች ቃልህ ይኼው፡
 ጥያቄ፦  አበሁኑ ሰዓት የትግራይ ተወላጆች በትግሉ ጎራ ለመቀላቀል ፍላጎት እንደሌላቸው በግልጽ የምናየው ጉዳይ ነው፡ ለምን እንዲህ ሆነ?
ከዚህ ቀጥሎ የመኮንን መልስ ግን ቃል በቃሉ ምንም ሳይታረም አቀርባለሁ። በቅንፍ ሲሆን ግን አማርኛውን ለማቃንት የተጨመረ ነው። መኮንን ዘለለው፦ የትግራይ ሕዝብ 90% ወይንም 100% (90 ከመቶ ወይንም 100 በመቶ) የመንግሥት ተቃዋሚ ነው። ሚስቱ የከዳቺው ሰው(ባል) ለመታገል ዝግጁ የሆነ አይመስለኝም።
የትግራይ ሕዝብ ባሳደጋቸው በልጆቹ የተከዳ ሕዝብ ነው። አንድ ሰው የሚያምናት ሚስቱ በሚስቱ የተከዳ ሌላ ሚስት ለማግባት የሚሮጥ አይመስለኝም። ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልገዋል። የትግራይ ሕዝብም እንደዛው ነው።
ትናንትና ልጆቼ ብሎ ወደ ትግሉ የላከ ልጆቹ ራሳቸው የከዱት ሕዝብ ነው እና አሁን በቀጥታ ወደ ትግሉ ለመግባት በማሰብ ላይ ነው። አርቆ የሚያስብ እውነተኛ የሚታመን የትግል ድርጅት እስካሁን አልተገኘም። እከሌ አለ የምትልም አይመስለኝም። አሁን
የትግራይ ሕዝብ በጠቅላላ አሁን  ኢትዮጵያዊ እምነት ያለው የትግራይ ሕዝብ እየጠፋ ነው።
አሁን ያለው የትግራይ ሕዝብ ማን አለ እስቲ ከኢሕአዴግ ሃይል የተሻለ የሚል ነው። የተቆረቆረ የትግራይ ሕዝብ የምንሰማው እና ከዚህ መንግሥት የተለየ ጠባይ የተለየ አቀራረብ እንዲኖረን ያስፈልጋል።….”
በማለት የትግራይ ሕዝብ የወያኔ ደጋፊ እንደሆነ/እንደነበረ በቃልህ ነግረኸናል።  የትግራይ ሕዝብ ከወያኔ የተሻለ ተቃዋሚ የለም እንደሚል ነግረኸናል። እንደገና ወያኔዎች ስለከዱት ትግሉ ጎራ መግባት አልፈለገም። ብለሃል። ስለዚህ ጌታቸው ረዳ ምን ባጠፋሁ ነው፤ “ትግሬዎች አይታገሉም ይላል፡ ብለህ በኔ ላይ ውርጅብኝ የወረድከው? ይኼ አቋምህም እኮ ከነ ታማኝ በየነ ጋር በአዲስ ደምጽ ራዲዮ ተከራክረሃል/ደግመኸዋል። ታማኝ ምን ብሎ እንደመለሰልህ/እንደጠየቀህ አንተ ምን ብለህ እንደተናገርክ ታስተውሰው ይሆናል። እኔ ያለ መረጃ ሰውን አልነካም ፤ ሲነኩኝ ነው እኔም ሃቁን ለማውጣት ሁሌም ራሴን ለመከላከል  የምጋፈጠው። ከማንኛችሁም ጋር የምጋፈጠው ስለ አገር እንጂ በግል ተነሳስቼ የማገኘው ነገር ወይንም ጥቅም እንደሌለ ይታወቅልኝ። ማንም ሊወደኝ ወይንም ሊጠላኝ ይችላል; ሑለቱም የየሰው መብት ነው፤ አከብረለታለሁ። አንድ መታወቅ ያለበት ግን እዚህ ትግል ስገባ “ሰውን ለማስደሰት/ለማስቀየም/ለመወደድ/ ለመጠላት/ለመሾም/ዝና ለማትረፍ/ለመዋረድ ለማዋረድ/ በሚል አይደልም። የሚሰድቡኝ ካሉ ይበልጥኑ እራሳቸው ተመልሰው ማየት ይኖርባቸዋል። አገርን መዝለፍ ያልከበዳቸው እኔን አንድ ግለሰብ መስደብ ይከብዳቸዋል የሚል ሕልም የለኝም። ስለዚህ ክቡራን ወንድሞቼ ምስኪኑ ጌታቸው ረዳን በየፓል ቶኩ ስሜን ባታነሱ እና የማቀርበውን ትችት ብትጋፈጡ ይመረጣል። አቶ መኮንን ለትግልህ እና ለዕድሜህ አክብሮት እሰጣለሁ። በተረፈ የያዝከው ቂም ካለ መድረኩ ይኼው።  እለግሳለሁ።

አመሰግናለሁ።No comments: