Monday, August 2, 2010

ሁለተኛው ዕትም

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር

ደራሲ

ጌታቸው ረዳ

የመጽሐፉ ዋጋ $25.00

ከላይ የተመለከተው “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” የመጀመርያው ዕትም አልቋል። መጠነኛ መሻሻልና የአንባቢያን ግምገማ ተጨምሮበት የመጽሐፉ ገጽ ጨምሯል።

Getachew Reda

P.O.Box 2219

San Jose, CA 95109

U.S.A

(408) 561-4836

getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com

ይህ የሁለተኛው ዕትም ቅጂ/ብዛት የተወሰነ ነው። ካሁን በፊት የመጀመርያው መጽሐፉ ካለቀ በሗላ $20.00 ልካችሁ ሁለተኛውን ቅጂ እስኪታተም የጠበቃችሁ ወገኖች ለትዕግስታችሁ እያመሰገንኩ መጽሐፉ በላካችሁት ሒሳብ መሰረት ይላክላችሗል። ካሁን ወዲህ ለምትልኩ ወገኖች ግን የመጽሐፉ ዋጋ እንደጨመረ ታውቁት ዘንድ አሳስባለሁ።

“የተማረ” ነው የሚባልለት ክፍል መጽሐፍን የማንበብ ፍቅርና ልምድ እንደሌለ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ቅጂው ባልተማረው ሕብረተሰብ ሽሚያ ካለቀ በሗላ “እባክህ እንዲህ የተባለ መጽሐፍ ታትሟል ስለተባለ ላክልኝ ብትሉኝ ማግኘቱ አስቸጋሪ እንዳይሆንባችሁ ካሁኑኑ መላክና “ኢትዮጵያና የጎሰኞቹን” ሴራ ለማወቅ ካልተማረው ሕብረተሰብ ጋር ሽሚያን በመሽቀዳደም የማንበብ ልምድና የአገር ሐላፊነታችሁን (ቢያንስ በማንበብ ረሳችሁን ከግብዝነት ለማጽዳት) ተወጡ።

ሁለቱን መጻሕፍቶቼን ሳሳትም አንድ የተማርኩት ነገር ካለ የመጽሐፍ ፍቅርና የሃገሩን ሁኔታ ተንገብግቦ በችኮላ ለማንበብ የሚጣደፈ ክፍል የተማረ ክፍል ሳይሆን የኔ ብጤ ዜጋ መሆኑን ለመረዳት አስችሎኛል። በአንድ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ (ሳንሆዘ ውስጥ) ካሁን በፊት በሌላ ጉዳይ አንስቼ እንደገለጽኩት ባለፈው ወር ተራው ዜጋ መጽሐፉን ለመግዛት ሲሻማ የዶክተርና መዓረግ ያለው አንድ ምሁር ኢትዮጵያዊ ግን ፤መጽሐፉን በጎሪጥ እንግዳ እንደመጣበት ውሻ በጎን ዓይኑ በጎሪጥ ጠረጴዛው ላይ ለገዢ የተሰጣውን መጽሐፍ ሲያየው አይቼ “ግርም ብሎኝ” መግዛት ካልቻለ መጽሐፉ ምን መልዕክት እንደያዘ አንኳ ቀረብ ብሎ ባይኑም በእጁም መዳሰሱ ማን ከለከለው? ብየ ራሴን በትዝብት ዓይን ሳያውቅብኝ ሰውየውን ሰረቅ አድርጌ እኔም ተመለከትኩት።

እነኚህ የተማሩ ናቸው፤ነገር ግን የቁም ሙታን ናቸው የኔው ብጤ ያልተማረው ክፍል የሚታዘባቸው አይመስላቸውም። ይህ ባሕሪ የአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን ቋሚና ተለዋዋጭ መግለጫዎቻቸው አንዱ ባሕሪ ነው። ከዚህ አያይዤ አንድ ነገር ላስተላልፈው የምፈለገው ተመሳሳይ ነገር ግን ለየት ያለ ሌላው ነገር ልጨምር። ይህ ቅሬታየ ዓይነ ሕሊናቸው በጠና በግብዝነት በጥላቻ ሰንሰለት እጅ ተወርች የተቀፈደዱ በኢንተር-ኔት ዜና እና ትችት ለሕዝብ የሚያሰራጩ አንዳንድ አዘጋጆች በዚህ አዲሱ መጽሐፌ ሰሞኑን የታዘብኩትን አንድ ነገር ልበላችሁና ልሰናባችሁ

የኔን መጽሐፍ አንብበው በግልም በይፋም ደስታቸውንና ግምገማቸው ከገለጹልኝ አንዱ አቶ በልጅግ አሊ የተባሉ ዜጋ ስለ መጽሐፉ ያለቸውን አስተያየት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስረዳት በኢንተርኔት እንዲተላለፍላቸዉ ጽፈው የላኩትን ግምገማ እንዲለጥፉላቸዉ ከጠየቅዋቸዉ መካከል ሁለቱ www.Ethioforum.org እና http://www.ecadforum.com/ የተባሉ ናቸው። የመጀመርያው በክንፉ አሰፋና (በዳዊት ከበደም ይባላል (?) የሚዘጋጅ ሲሆን፤ የሁለተኛው ሰሌዳ የሚዘጋጀዉ በቅርቡ ወደ ዉጭ ሃገር ወደ ስደቱ ዓለም በማቅናት የተቀላቀለን ካናዳ ውስጥ የሚኖር ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ (የአማራዉ ሕዝብ ከየት ወዴት ደራሲ) የቅርብ ወዳጅ የሆነው ተክሌ “ልጅ ተክሌ…” በማለት ራሱን የሚጠራ ወጣት ሲሆን፡ ሌሎች ድረገጾች በደስታ ተቀብለዉ ግምገማውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲነበብ ሲያደርጉ እነኚህ ሁለቱ ሰዎች ግን ከኔው ጋር በፖለቲካው ስለማንጣጣም፤ የግምገማዉ መልዕክትና መጽሐፉ ያስተላለፈውን ያገሪቱን ሁኔታ በቂም በቀል ምክንያት እኔን የበደሉ መስሏቸው የአቶ በልጅግ አሊን ግምገማ ሳያወጡት ቀሩ። እንግዲህ ልብ በሉ! የእኔነት (የአካል/የጎሳ/የፖለቲካ…) እና መጽሐፉ የሚያስተላልፈዉ መልዕክት ለይተዉ ማየት ያቃታቸው እንኚህ ግለሰቦች ምንኛ በማሃይምነት ሰንሰለት ተተብትበው “መነበብ ያለበት ታላቅ መልዕክት” ሲያፍኑት የሃገሪቱ ጠላቶች “የተለያዩ ዓይነቶች መሆናቸውን ማወቅ የግድ ይላል።

ከሚገርማችሁ እነኚህ ሁለቱ ድረገጾች እንደ እነ አማኑኤል በዕደማርያም (የሻዕቢያ ቱልቱላ እና ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት እና አረመኔ ሃገር ብሎ የሚኮንናት ኤርትራዊ) እንዲሁም የኦነግ እና የመሳሰሉ ተገንጣዮችና ብሔረተኞች የሚልኩላቸው ጽሑፎችና ዜናዎች፤መገለጫዎች (ኢትዮጵያን ሁሉ የሚሰድቡ እና ታሪኳን እና ማንነቷን የሚዘልፉ ጽሑፎች ሳይቀር) ሲለጥፉላቸው ኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚገመግሟቸው መጽሐፍቶች ግን ለሕዝብ እንዳይዳረሱ ለማፈን መሞከራቸው በምን ሒሳብና ለምን እንደሆነ ፍርዱ ለናንተው ልተወው።ወንድሞቼ ያገሪቱ መከራ ብዙ ነውና አምላክ እንደፈጠራት ሳያውቁም ሆነ አውቀው ከሚንዷት ከገዛ ግብዞቿ እራሱ በጥበቡ ያድናት። እስከዛሬ ድረስ ማን እስከየት መዝለቅ እንደሚችልና እንደቻለ “አይተናል” መጪውም የምናየው በሂደት ናውና ለሁሉም “ትዕግስት”!

ማሳሰቢያ፡\

መጽሐፉን ለመግዛት ስትልኩ አድራሻችሁን፤ስልካችሁን እና ኢመይል ካላችሁም ጨምሩበት። በተለይ እባካችሁ ስልካችሁን አትርሱ። አስካሁን ድረስ ደብዳቤ የላካችሁ ሰዎች አብዛኛዎቻችሁ ስልክ ስሌለበት ደውላችሁ እንደገና ብትሰጡኝ ሲላክላችሁ መላኬን እንድነግራችሁ ያመቻል እና አደራ።በዚህ አጋጣሚ የመጽሐፉን መታተም በኢትዮጵያ ሕዝብ ጆሮ እንዲዳረስ ለማድረግ መድረካችሁን ለፈቀዳችሁልኝ አዘጋጆች ከልብ አመሰግናለሁ።

Getachew Reda

P.O.Box 2219

San Jose, CA 95109

U.S.A

(408) 561-4836

getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com

No comments: