Monday, May 4, 2009

የአስር-አለቃ ራያ እና የሊቀመንበር መንግሰሥቱ ፍጥጫ

የአስር-አለቃ ራያ እና የሊቀመንበር መንግሰሥቱ ፍጥጫ (ከታሪክ ማሕደር) (ጌታቸዉ ረዳ) www.Ethiopiansemay.blogspot.com (ትችቴ የሚመለከተዉ በፕሮፌሰር አለማዮህ ገብረማርያም፡ላይ ነዉ።ትችቴም ፕሮፌሰሩ ቋሚ አምደኛ በሆኑበቻዉ በኢትዮሚድያ፤ ለኢ ኤም ኤፍ- የህዋ ሰሌዳ እንዲቀርብ ልኬላቸዉ እንደዘወትሩ የነሱን ሰዉ የሚተች ትችት እንደማያወጡት ሁላችሁም ይሄኔ ያወቃችሁት የነኚህ ያሳዛኞቹ ከወያኔ ወገንተኛ ፕረስ ያልተናነሱ “የሚዲያ ሰዎች” ክስተት ነዉና ትግሉ ከነዚህ ሰነፎችም ይሆናል። አዘጋጆቹ አልለጠፉትም። ባይለጥፉትም- የት እንደምታነብቡኝ ፈልጋችሁ አታጡኝምና ትችቱን እነሆ። በዚህ አጋጣሚ ለሰፊዉ አንባቢ እንዲዳረስ ለተባበሩኝ ለwww.Ethiopatriots.com እና ለwww.mahder.com አዘጋጆች በአንባቢዎች ስም አመሰግናለሁ። ከላይ የሚታዩት በርካታ ፎቶግራፎች ዶ/ር ሃይሉ አርአያ በደርጉ መንግሥት የሰራተኛ ፓርቲ በኢሰፓ ማአከላዊ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጥናት ኮሚቴ ምክትል ሓላፊ እና የኢፌድሪ ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥቶች አርቃቂ ኮሚቴ ያጠናከሩትን ጥናት ለደርጉ ኮንግረስ ሪፖርታቸዉን/ዘገባቸዉን ባቀረቡበት ጊዜ የተገኘ ፎቶግራፍ ነዉ። በሚቀጥለዉ ጽሁፌም “የወያኔ መኢሶኖችና የመፈንቅለ መንግሥቱ አስቂኝ ተዉኔት” በሚል ርዕስ ሰፋ ያለ ዘገባ ይቀርባል ተከታተሉኝ። ፕሮፌስር አለማየሁ ገብረማርያም ሰሞኑ “Patriots and Tyrants” በሚል ርዕስ የበደርግ ዘመነ መንግሥት የኢሰአፓ አባል የነበሩ ዶ’ር ሃይሉ አርአያን የደርጉን ሊቀመንበር መንግሥቱ ሃይለማርያምን “በመጨረሻዋ- ሰዓት” (የጓድ መንግሥቱ የመቀበርያ ጉድጓድ ከተቆፈረ በሗላ) “እኔ ምሁር ነኝ፤ መምህርም ነኝ፤ የማከላዊ ብሔራዊ ሸንጎ አባልም ነኝ፤ ስለሆም ሃቁን መናገር አለበኝ። ሃቅን በመናገሬ ለሰይፍ የሚዳርገኝ ከሆነም ሃቁን ተናግሬ መሞትን መርጫለሁ! ክቡር ሊቀመንበር! ይህ ቤት በፕሮፌር መስፍን ወልደማርያምን የቀረበዉ “የሰላም ረቂቅ ሃሳብ” ከመወያየታችን በፊት አርስዎ ወንበርዎን ተጠቅመዉ ወደ አታካራና ማጣጣል ብሎም ማስፈራራት ዉስጥ መግበትዎ ተገቢ አይደለም። ይህ ባሕሪ ከእንግዲህ ወዲህ ተቀባይነት አይኖረዉም።ለምንድነዉ ችግሩ የግልዎ ብቻ አስመስለዉ የሚያዩት? ችግሩ የጋራችን እንጂ የእርስዎ ብቻ ስላልሆነ እረስዎ ከመንበሩ ላይ ሆነዉ አኔ ባልኩት መንገድ ይመራ ካሉ እማ መድረኩን እያፈኑት ነዉ? እርስዎም የነቀፌታዋ ከኒና መዋጥ ካለበዎት አርስዎም እኛም ሁላችንም መዋጥ አለብን … ወዘተ…” – በማለት ቃል በቃል ባልጽፈዉም ወደ እዛዉ መሳይ ዓይነት የተጠጋ በሸንጎዉ ስብሰባ የሰነዘሩትን አስተያየት ፕሮፌሰር አለማዮህ ደ/ር አርአያን “አገር ወዳድ፤ኢትዮጵያዊዉ አርበኛ እና ቆራጥ” በማለት በእንግሊዝኛዉ Dr. Hailu Araya: Ethiopian patriot. Political prisoner. Educator. Poet ሲሉ“ አወድሰዋቸዋል። ነገር ግን ዶ/ር ሃይሉ አርአያ በደርግ ጊዜ ከነበራቸዉ የፓርቲ እና የሕገመንግሠት አዋቃሪነት ሥልጣን አኳያ በመሰል ጓዶቻቸዉ ላይ በሌሎቹ ላይ ለደርግ አስታወጽኦነታቸዉ በብዛት ሲተችባቸዉ በዶክተር ሃይሉ ግን በአርበኝነት እንጂ በገንቢም ሆነ በከረረ ትችት ሲተቹ አንብበን አናዉቅም። ለምን? የሚለዉ ጥያቄ በብዛት ከጥቂት አመታት የተፈጠሩ ሚዲያዎች “የፓርቲ ወገንተኝነት” ነዉና ለዚህ ሽፍንፍን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለቸዉ ይገመታል። ይህ በእንዲህ ሆኖ ከ1975 አስከ 1980 ዓ.ም ባለዉ ጊዜ በኢሰፓ ማአከላዊ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጥናት ኮሚቴ ምክትል ሓላፊ የኢፌድሪ ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥቶች አርቃቂ ኮሚቴ በመሆን ባገለገሉበት ወቅት ዶክቶሩ ካለፉት ንግግራቸዉ ዉስጥ በሊቀመንበር መንግሥቱ ፊት ምን ዓይነት ንግግር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላልፉ እንደነበር ከታሪክ ከማሕደራች እያነሳን መነጋገርም ከጓደኞቻቸዉ ለሚሰጣቸዉ “የአርበኝነት” ማዕረግ ግምገማ እንዲያመቸን፤ በወቅቱ ሲያደርጓሸቸዉ ከነበሩት የራዲዮና የቴሌቪዥን “አገር አቀፍ” መድረኮች እናዳምጥ - “ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ ሃይለማርያም፣ የኢሠፓ ማአከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ፣-የኢፍድሪ ፕረዚደንት፣ የአብዮታዊ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣- -ጓድ የአብዮቱ የጥናቱ ተሳታፊዎች፣- ጓዶች.-- የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ሕዝብ በመራራ ትግሉ ያገኘዉ ድል ተጠቃሚ ለመሆን መመቻቸት ከነበረባቸዉ ሁኔታዎች አንዱ እና ዋነኛዉ ጉዳይ “የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሪፓብሊካዊት መመሥረት ነዉ”። ይህ ዉለታ አብዮታችን ከተቀጣጠለበት ጊዜ ጀምሮ በጉልህ የታየ ስለነበረ የኢፌድሪንን መመሥረት አስፈላጊነት በብሔራ ዲሞክራሲአዊ አብዮት ፕሮግራም በግልጽ ከተቀመጠ በሗላ በአብዮታችን ሂደት ደረጃ በደረጃ ተገቢዉ ትኩረት እያገኘ መጥቷል። የኢፍድሪ ዓላማ ምሥረታ ባዲስ ሕዝባዊ መሠረት የሚገነባዉን ፖለቲካ ከማሟላት በተጨማሪ ሠርቶ አደሩን ሕዝብ ከወረሰዉ ሗላ ቀርነት ተላቅቆ በፖለቲካ በኢኮኖሚ በማሕበራዊ እና በባሕል መስክ የተቀጣጠለ ዕድገት ለማምጣት የሚያስችለዉን የሥልጣን መሣሪያ ለማስጨበጥ ነዉ።…” ዶ/ር ሃይሉ አርአያ በኢፌድሪ ምሥረታ ከተናገሩት የተቀነጨበ። ከንግግራቸዉም በሗላ ከሌተናንት መንግሥቱ ሃይለማርያም ሽልማት ሲሸለሙ በዕለቱ የተቀረጸዉ አዉድዮ ቪድዮ ይታያል።) እንግዲህ ለሕዝብ ተናገሩትን ቃላት በቃላት አረፍተነገሮቹን ተርጉሞ ምን ማለት እንደሆኑ የሚሰጡት ትርጉም በመመርኮዝ “አርበኛ” ያሰኘቻቸዉ “በዜሮ ሰዓት/ ማለትም በደረግ የሬሳ ሳጥን የመጨረሻዋ ምስማር እንድትከነቸር አንድ ሰዓት ሲቀራት በተናገርዋት ንግግር ብቻ በመገምገም” ብዙ ዶክተሮች ስለ አርበኝነታቸዉን ሲጽፉላቸዉ እየሰማን ስለሆነ አርበኝነታቸዉን “የመቃወምና የማመጎሱ” የናንተዉ ያንባቢያን መብት በመሆኑ ለግምገማ በኔ በኩል ከላይ ያቀረብኩትን ንግግራቸዉ ለናንተ እየተዉኩኝ፣- በስሜት የሚነዱ አዳዲስ መጥ (ለትግሉ መድረክ) ምሁራኖችና የወያኔ “x-ነበር-” ባለሞያዎችና አምባሳደሮች፤ ያላቸዉን የተዛባ የአርበኝነት ትርጉም - የኔን ሚዛን ላስቀምጥ እነሆ። ዶ/ር ሃይሉ አርአያ አገር ወዳድ አይደሉም ለማለት ሳይሆን፤በተለይ ቅሬታየ አብዛኛዉን በደርጉ ወቅት ሳይሆን “አሁን” “ዛሬ” በወያኔ ጊዜ ባበላሹት የቅንጅት የሕብረቱ ፖለቲካ እንዳመዘነ ለመግለጽ እወዳለሁ)- ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ዶ/ር ሃይሉ አርአያን በአርበኝነትና በቆራጥ ምሁር ሲያወድስዋቸዉ ሰምቼ፤ እኚህ ምሁር ለመሆኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካም ሆነ በወቅቱ የተነገሩም ሆነ የተቀረጹ ተንቀሳቃሽ ፊልሞች ወይንም የተጻፉ መጽሃፍቶች ስለ አርበኞች እና መንገሥቱን የተቃወሙ ተራ ዜጎች ታሪክ አንብበዉ ይሆን? ወደ ማለቱ ሳዘነብል- ያዉም እንደ ደ/ር ሃይሉ አርአያ ከ17 ዓመት ለደርግ ኢሠአፓነት አገልግለዉ ወደ መጨረሻ ሰዓት ቁጣቸዉን ያስተነፈሱ ምሁራን ሳይሆን ገና ከጅምሩ በእሳቱ ወቅት መንግሰሥቱ ሁሉንም በሰይፍ የመግዛት ጉልበታቸዉ አፍላ በነበረበት ወቅት “የዶክተርነት ማዕረግ” ያልነበራቸዉ ‘ተራ ዜጎችና ተራ ወታደሮች” የሕሊና-ሚዘናቸዉ” ለዲክታተሮች አልመች ያሉ ፕሮፌሰሮቻችን የማያወቁዋቸዉ- ቢያዉቁዋቸዉም “ተራ መደዴ’ ስለሆኑ “ዶክተሮች ስላልሆኑ” ታሪካቸዉ “በአርበኝነት-ማሕደር” እንዲወሱ ወይንም የሕግ ጠበቆች፤ ሓኪሞች፤ ሸሞንሟኔ ምሁራን፤ ልፍስፍስ አፈኛ ፖለቲከኞች ስላልሆኑ “ተራ ዜጎች በሊቀመንበሩ ፊት ቀርበዉ “ለአንተ አልታዘዝም!” እያሉ ለሰይፍ የተዳረጉ ማዕረግ ያልጫኑ አርበኞች” ያዉቃሉ? ፕሮፌሰሩ ስለ ደ/ር ሃይሉ አርአያ እንዲህ ሲሉ በእንግሊዝኛ ጠይቀዉናል “1Who would forget that historic showdown between the patriot and the tyrant. Thus spoke Dr. Hailu: ….“ እኔ ደግሞ ለፕሮፌር አለማየሁ ገብረማርያም የምጠይቀዉ እሳቸዉ እና አልፍ ኣእላፍ ዶክተሮቻችን የማያዉቁት “ምሁር ወይንም አስተማሪ ነኝ ብሎ ሃቅን ለመናገር እና ለማስተማር 17 ዓመት ያልፈጀበት ተራ ዜጋ “ ታሪክና አርበኝነት ቆራጥነት ሰምተዉ አንብበዉ ያቃሉ? ስለ አርበኛዉ የአስር-አለቃ ራያን ነዉ ላነሳ የፈለግኩት። ምሁራን ሆይ! ለመሆኑ ያገራችን ታሪክና ጽሁፎች ትከታተላላችሁ? ታነብባላችሁ? ይህ “በዜሮ- ሰዓት” ስለ ዶ/ር ሃይሉ አርአያ ድፍረትና አርበኛነት ካሁን በፊት በብዙ ምሁራን ተደጋግሞ ሲጻፍ በማየቴ እና ስለ ተራዉ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ድፈረትና ቆራጥነት ምሁራኑ ለምን ጀሮ ዳባ እንዳሉት ሲከነክነኝ ዛሬም ስለ ዶክተሮች አርበኝነት ብቻ እየተደጋገመ ሲጻፍ ሳነብብ- ገርሞኛል”” ማዕረግ፤ሃበት እና ታዋቂነት ያላተረፈ ለትምህርት አልባዉ “እዉነት ተነጋሪ” ዜጋዎቻችን” መቸ ነዉ መቆም የምትለምዱት? ። ታሪኩን ላማታዉቁ ወይንም እንባበችሁ ችላ ላላችሁት ምሁራኖቻችን ያርበኞቻችን ድፈረትና የአርበኞች ማሕደር የዘገበዉ ሃቅ ስለ የአስራለቃ ራያ አርበኝነት (historic showdown between the patriot and the tyrant ) እነሆ፦ “… ሌተናንት ኮሎኔል መንግሥቱ የጓጉለትን የአብዮታዊ ሰደድ ድርጅት ከላይ ተጠናከረ እንጂ አግሩን ወደ ታች በቅጡ አልዘረጋም ነበርና ፤ በተለይም በመለዮ ለባሹ ዉስጥ ገብቶና ተንሰራፍቶ በሁለት እግሩ የመቆም ሂደት ገና ጅምር በመሆኑ ለዚህ ቅድሚያ መስጠት ነበረባቸዉ። ስለዚህ የእነ ሻምበል ዓለማየሁ እንቅስቃሴ እየተጠናከረ መምጣቱን ያላጤኑ መስለዉ በደርግ ዉስጥ እንደ አንድ ታላቅ ዘርፍ የሚቆጠር የወታደራዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ጠቅላይ መምሪያን አቋቋሙ። ይህ ጠቅላይ ምመሪያ መለዮ ለባሹን በአብየታዊ ሰደድ ለማጥለቅለቅና እርሳቸዉም በመለዮ ለባሹ ዉስጥ ሁለት እግራቸዉን አንፈራጠዉ የሚቆሙበትን ሥፍራ ለማደላደል ዓይነተኛ መሳሪያ እንደሚሆን ተስፋቸዉንና እምነታቸዉን ስለጣሉበት በማደራጀት ተሰጥኦአቸዉ የሚያምኑባቸዉ የነበሩትን የ ሃምሳ አለቃ ለገሠ አስፋዉንና ፒ.ቲ.ኦፊሰር ታምራት ፈረደን የጠቅላይ መምሪያዉ ሃላፊዎች አድርገዉ ሾሟቸዉ። ከዚያም ከ አዲስ አበባ እና ከአካባቢዉ የሚገኘዉ መለዮ ለባሽ እየዞሩ የማነጋገር መርሃ ግብር ዘረጉ። ዓላማዉም እንደ ደርግ ምክትል ሊቀመንበርነት ብቻ ሳይሆን እንደ ፖለቲካ ድርጅት መሪነትም ለመተዋወቅና ፖለቲካ ድርጅታቸዉም ደርከግ የላቀ ዘላቂ ዓላማ ያለዉ መሆኑን ለማስተዋወቅ ነበር። በዘረጉት መርሃ ግብር መሠረት በቅድሚያ በአዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙትን የምድር ጦር ልዩ ልዩ ክፍሎችን በምድር ጦር አየር ክፍል (አረሚ አቪየሽን) ምድር-ግቢ ሰብስበዉ አነጋገሩ። የሚመለከታቸዉ የደርጉ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ተወካዮችም በሥፍራዉ ተገኝተዉ ነበር። የንገግራቸዉ ጭብጥ የመደብ አሰላለፍና የፖለቲካ ድርጅቶች አመሠራረት በኢትዮጵያ፤ እንዲሁም የአብዮቱ ወዳጆችና ጠላቶች እነማን ናቸዉ? የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች የያዘ ነበር። በርዕሰ ጉዳዮቹ ላይ ባደረጉት ትንታኔ፤ ሕቡዕ ድርጅቶችን በስም እየጠቀሱ የአደረጃጀት ታሪካቸዉ ዘረዘሩ። ከሕቡእ ድርጅቶች በመጨረሻዉ ተራ ቁጥር ላይ የጠቀሱት አብዮታዊ ሰደድን ሲሆን ይህ ድርጅት የሕዝቡን ፍላጎት የሃገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታና የአብዮቱን ሂደት አገናዝቦ ከሁሉም ድርጅቶች ዘግይቶ እንደተቋቋመ ነገር ግን በኢትዮጵያ አንድነትና በመከለከያ ሃይሏ አደረጃጀት ከሁሉም በተለየ ሁኔታ የጠራ አቋም ያለዉ፤ በዚህም አቋም ምክንያት ብዙ ጠላቶች እንዳፈራ፤ እኒህም ጠላቶቹ የወታደር ፖለቲካ ድርጅት እያሉ ከትግሉ ሊያገልሉት እንደሚፍጨረጨሩ በመግለፅ “የዚህ ፖለቲካ ድርጅት መሪ አንተነህ፤ ድርጅቱ የቆመዉ ለእኛ ጥበቃ ነዉ” በሚያስብል አኳሗን በዘዴ አስተዋወቁ። ከሁለት ሰዓት በላይ የፈጀ ትንታኔያቸዉን እንዳበቁ፣ ጦሩ በአዥጎደፈጎደዉ የጭብጨባ ማዕበል “በቃ፤ እኚህ ሰዉ ሊመሩኝ ይችላሉ” ብሎ እንደደመደመ መገመት አያዳግትም ነበር። ከዚህ በሗላ የዉይይት ጊዜ ሆነ። ብዙ ወታደሮች ስለሃገርና ስለ አብዮቱ ደህንነት ያላቸዉን መቆርቆር እየጠቀሱ የድጋፍ አስተያየት ሰጡ። ደርግ ወደፊት ምን ማድረግ እንደሚገባዉ የመከሩም አልታጡም። በአጠቃላይ የስብሰባዉ ሂደት እርሳቸዉ ከጠበቁት በላይ የሠመረ ሆኖ ስላገኙት ደስ ብሎአቸዉ እያለ አንድ የአስር አለቃ የመናገር ተራ እንዲሰጠዉ በእጁ ምልከት ጠየቀ። ፈገግ ብለዉ እየተመለከቱት እንዲናገር ፈቀዱለትና ከስብሰባዉ መሃል ወደ ግንባር ረድፍ ወጣ ብሎ ከፊት ለፊት ቆመ። ቀጥሎም “ለመሆኑ መንግሥት እንድትሆን አንተ ማን ወከለህ?” አለና አረፈዉ። ሳቅም፤ጉርምርምታም ተሰማ። “ዝም በሉ! መጠየቅ የለብኝም እንዴ!?” በማለት የአስር አለቃዉ ባጉረመረሙት ወታደሮች ላይ ጮኸባቸዉ።ሌተናንት ኮሎኔል መነግሥቱ በንዴት ትክ ብለዉ ገፃቸዉን ጥቁር ደመና አስመስለዉ “ የአስር አለቃ ራያ ይህ ጋጠ-ወጥነትህ ዛሬም አልለቀቀህም ማለት ነዉ?” አሉት። “ያዉ የምታዉቀኝ ራያ ነኝ፤ እኔም አቅሃለሁ፤ የምለዉን ብያለሁ፤ አሁንም እደግመዋለሁ። መንግሥት እንድትሆን ማን ወከለህ?” በማለት የአስር አለቃ ራያ ሲናገር ወታደሮቹ አጉረመረሙ። የስሜታዊ ባሕሪ ያለበት መሆኑ ሰዉነቱን እያንዘፈዘፈዉ ባለዉ አንቀጥቅጥ ያስታዉቅ ነበር። ከቀድሞዉ ዝግ ባለ አነጋገር “…ያኔም ታስረኝ ነበር፤ አሁንም የህንን በመናገሬ እሰረኝ!” አላቸዉ። እሳቸዉም “የተመኘኸዉን አልነፍግህም” በሚል አኳሗን ግራ ቀኝ ማተሩና “”ማነህ…? ፖሊስ! ዉሰደዉ!” አሉ። የአስር አለቃ ራያ “ አዎ እሰረኝ… ያኔም መታሠር… አሁንም መታሠር…” በማለት እያነበነበ መለዮዉን አዉልቆ፤የወታደር ቀበቶዉን ፈትቶ ወረወረዉ። ሁለት ወታደር ፖሊሶች ክንዱን ጠምዝዘዉ እያዳፉ ወሰዱት። ሌተናነት ኮሎኔል መንግሥቱም መጠነኛ ዉጥረት የሰፈነበትን ከባቢ አየር ለመለወጥ ያህል ቀደም ብለዉ የተነሱ ጥያቄዎችን ተመርኩዘዉ አጭር ማበራሪያ ከሰጡ በሗላ መፈክር አሰምተዉ ስበሰባዉ አበቃ። ጦሩ በደስታና በሆሆታ ወደ መጣበት ተመለሰ። የአስር አለቃ ራያ፡ ሌትናት ኮሎኔል መንግሥቱን መዳፈሩ እርሳቸዉም በስሙ ለይተዉ መጥራታቸዉና በመጨረሻም ‘የእሳት እራት” የመሆኑ ነገር እያደር ስለከነከነኝ ከዚህ ቀደም ይተዋወቁ የነበሩ እንደሆነ መቶ አለቃ መንግሥቱ ገመቹን ጠየቅሁት። አርሳቸዉ በከባድ ወታደራዊ ሥነሥርዓት ጉድለት ምክንያት ለአንድ ዓመት የመቶ እልቅና ማዕረጋቸዉን አዉርደዉ በተራ ወታደርነት እንዲሰሩ ተቀጥተዉ ወደ ኦጋዴን በተላኩበት ወቅት ከ አስር አለቃዉ ጋር አብረዉ እንደነበሩና ከዚያም በሗላ እርሳቸዉ ይመሩት በነበረዉ የሦስተኛ ክፍለጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት መምሪያ ዉስጥ ሲያገለግል እንደነበር መስማቱ ነገረኝ። ጉዳዩ “እያወቅሁህ ናቅሁህ” ጣጣ መሆኑን ገባኝ።”” (ነበር- ገጽ 195- 196 ደራሲ ዘነበ ፈለቀ-1996)።/-/ ለእንዲህ ዓይነቶቹ አርበኞችስ ምሁራኖቻችን “የነብስ ይማር” ብዕራችሁ ብትለግሱላቸዉ ምንአለበት? ጌታቸዉ ረዳ ሳንሆዘ ካሊፎርኒያ www.Ethiopiansemay.blogspot.com Getachre@aol.com

3 comments:

Anonymous said...

Getachew,

If people are repent and start doing the right thing then you have to respect them. I don't know what you are so picky. Engineer Hailu served Derg and yet you support him. Why are we spending time on things that divide us instead of uniting us?

Getachew Reda said...

From the Editor- Getachew Reda-

Brother/sister- I read your comment. I could have answered your question by simply referring you to go back and read it. You will get the answer for your question. But, I guest, you didn’t read it seriously. I already said it right there on the lower top of the article saying I am not focusing mainly on his positions and contributions to the brutal Derg’s regime, - I sad “ I am simply disgusted by his fatal contribution to the disunity of the Kinijit mainly”.

Second- I brought his past record, not to humiliated him as many of you the Ginbot 7 and Bertukan;s supporters and the like think;- but, to dismissed the meaning of Arbenga given to him by Professor Al Mariam. If you have a problem with that, let us debate. You see a football game will not be a game and will be possible except for the rule of the game which we bring to the situation and which enable us to share with others the significance of various happenings.

If a person is unfamiliar with rules of the game, the behavior he sees lacks repeatability and consistent significant and hence “doesn’t make sense”. In politics, there also is a rule; - leaders, politicians will be exposing to their past ugly record- even private life when necessary when they confront the public’s stage. Hence, therefore, you don’t have to be shock when I come out with such critique. I was not even harder with him. I could, but, as I said, my aim was not as you think to be “picky” AL RIGHT!? Finally, Engeer Hailu Shaul didn’t serve the Derg. To be professional Engineer, and Minister in his filed is not similar as to be the Derg’s Worker’s party Congress and vise chairman of the Nation and nationality organizer under the Derg’s policy and Framer of the brutal Derg’s constitution the constitution recognized the Brutal Mengistu as the “center and leader” of every thing. Okay! You are talking two different stories. Hailu Shaul never walk kebele to kebele to arrest oppositions, but------- Let me cut it here before I go on. You are repeating what TPLF was airing for its political consumption to degrade Hailu Shaul’s record and present strength ;= as the pathetic hard Talk BBC reporter was trying to be smart leveling Hailu Shaul as Derg after Bereket and Meles oriented him falsely. You are welcome to debate with me, if you disagree with my response to you. Thanks!

Anonymous said...

Aya Getachew,
How is being Minister of State Farms serving in his field for an Engineer?
I admire both Hailu Shawel and Hailu Araya for standing up in front of Mengistu to tell him the bitter truth. For some reason we have a habit of going back to discredit past deeds just before we disagree with current politics of the person. That does not help to move the cause of Ethiopia an inch!
Whether you like it or not Dr Hailu Araya is an arbegna! You disagree wirth his current politics, fine make your point.

zeYeka